cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

Publicaciones publicitarias
5 379
Suscriptores
-424 horas
-347 días
-24030 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

አዲሱን የኤርፖርት ሲቲ ግንባታ ዲዛይን የሚያከናውን የአማካሪ ድርጅት መረጣ እስከ መጪው መስከረም ይጠናቀቃል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱን የኤርፖርት ሲቲ ግንባታ ለማስጀመር ዝርዝር ዲዛይኑን የሚያከናውን አማካሪ ድርጅት መረጣ እስከ መጪው መስከረም እንደሚጠናቀቅ አስታወቀ። አየር መንገዱ በፍጥነት እያደገ የመጣውን የደንበኞቹን ቁጥር ታሳቢ በማድረግ ዘመናዊና ግዙፍ የኤርፖርት ከተማ ግንባታ እንደሚያከናውን ከ4 ዓመት በፊት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ከቢሾፍቱ ከተማ ወጣ ባለ ሥፍራ ላይ የሚገነባው ይህ ፕሮጀክት፥ የካርጎ ሎጂስቲክ ማዕከል፣ ዘመናዊ ሆቴሎችና ከቀረጥ ነጻ የተለያዩ የግብይት ስፍራዎች እንደሚኖረውም ተገልጿል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ፕሮጀክቱ በተለያዩ ምክንያቶች በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ሳይጀመር ቆይቷል። የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በዓመት እስከ 25 ሚሊዮን ያህል ብቻ መንገደኞችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑን ያነሱት ዋና ስራ አስፈጻሚው፣ ሆኖም የደንበኞች ቁጥር በመጪዎቹ ጥቂት ዓመታት በእጥፍ እንደሚያድግ ይጠበቃል ብለዋል። በመሆኑም የአየር መንገዱን እድገት እና የመንገደኞችን ቁጥር መጨመር ታሳቢ ያደረገ ግዙፍ አውሮፕላን ማረፊያ (ኤርፖርት ሲቲ) መገንባት የግድ መሆኑን በማመን ወደ ስራ መገባቱን ጠቅሰዋል። ከቢሾፍቱ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ ስፍራ የሚገነባውን አዲሱን ፕሮጀክት ግንባታ ለመጀመርም የተለያዩ የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል። ለአብነትም የኤርፖርት ሲቲ ግንባታውን ዲዛይን የሚሰሩ ሁለት አማካሪ ድርጅቶችን ለመቅጠር ይፋዊ ጨረታ መውጣቱን ጠቅሰው፥ የአማካሪዎች መረጣ እስከ መጪው መስከረም እንደሚጠናቀቅ አመላክተዋል። ፕሮጀክቱ ከዘገየባቸው ምክንያቶች አንዱ ኤርፖርት ሲቲው በሚገነባበት ቦታ የሚኖሩ አርሶ አደሮችን ሁኔታ ለማስተካከል ረጀም ጊዜ በመውሰዱ ነው ብለዋል። በአሁኑ ወቅት አርሶ አደሮቹ ኑሯቸውን የሚመሩበትን ስራ ለመፍጠር የሚያስችል ጥናት መከናወኑን ገልጸዋል። የአርሶ አደሮቹን ፕሮጀክት ወደ ተግባር ለማስገባትም የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን የታወቀ ሲሆን፥ የፕሮጀክት ዲዛይን የሚሰራ አማካሪ እየመረጥን ነው ብለዋል። አዲስ የሚገነባው ኤርፖርት ሲቲ ለአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክና ለሞጆ ደረቅ ወደብ ቅርብ በመሆኑ ትልቅ የኢንዱስትሪያል ሎጂስቲክ ማዕከል እንደሚሆንም ተገልጿል። የኤርፖርት ሲቲ ግንባታ ሲጠናቀቅ በዓመት 100 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም እንዳለውም ነው የገለጹት፡፡(ENA)
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በአቃቂ ግዙፉን ዋና መስሪያ ቤት ግንባታ በ 1.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ሊገነባ ነዉ መንግስታዊዉ ነዳጅ አቅራቢ የሆነዉ ድርጅቱ 1.6 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚያደርግበትን ግዙፉን ህንፃ ለመገንባት የኮንትራት ዉል ስምምነት ማድረጉ ታዉቋል። በአቃቂ የሚገነባው 2B+G+14 ስማርት የችርቻሮ ጣቢያ ዋና መስሪያቤት በ 24 ወራት ዉስጥ ለማጠናቀቅ ዕቅድ መያዙን ካፒታል ሰምቷል። ኢኢአይጂ ከተባለው ተቋራጭ ጋር የዉል ስምምነት ያደረገው የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ አማካሪ ነዉ። (capital)
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
አዋሽ ባንክ ለ3ኛ ጊዜ ከኢትዮጵያ ምርጥ ባንክ በመባል መመረጡ ተገለፀ። ግሎባል ፋይናንስ ማጋዚን ለ31ኛ ጊዜ የምርጥ ባንኮችን ዝርዝር ይፋ ባደረገው መሠረት ከ36 የአፍሪካ አገራት ውስጥ ከተመረጡ ባንኮች መካከል አዋሽ ባንክ አንዱ ሆኗል። የምርጥ ባንኮች ልየታ የተደረገው በተለያዩ መስፈርቶች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ የባንኮቹ ትርፋማነት፣ የሀብት ዕድገት፣ተደራሽነት እና የመሳሰሉት ከመስፈርቶቹ መካከል የተካተቱ ናቸው። በዚህ መሠረት አዋሽ ባንክ ከ36 አገራት ከተመረጡ የአፍሪካ ባንኮች መካከል አንዱ ሆኖ መመረጡን እና ከኢትዮጵያ ደግሞ ብቸኛው ባንክ መሆኑን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው ገልጸዋል። በዚህኛው አመት በተካሄደው ምርጫ ከ1መቶ50 በላይ አገራት የሚሰሩ ባንኮች የተካተቱበት መሆኑም ነው የተገለጸው። አዋሽ ባንክ በአሁኑ ጊዜ ከ9መቶ38 በላይ ቅርንጫፎች በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች እንዳለው የተገለፀ ሲሆን ከ12.1 ሚሊየን በላይ ደንበኞችንም ማፍራቱ ተነግሯል። የባንኩ ጠቅላላ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ2መቶ15 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱም ተገልጿል። ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የተሰጠው የብድር መጠንም ከብር 1መቶ78 ቢሊየን ብር በላይ መሆኑንም ነው ያስታወቁት። የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ እንደገለፁት ለባንኩ የሚሰጠው ዕውቅናና የሽልማት ስነ-ስርዓት የአለም ገንዘብ ድርጅት እና የአለም ባንክ በዋሽንግተን ዲሲ በኦክቶበር 2024 በሚያደርጉት ጉባኤ ወቅት እንደሚከናወን አስታውቀዋል።(ethiofm)
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የፌደራል መንግሥት በኤሌክትሪክ እና በውሃ አገልግሎት ላይ ቫት የሚጥል ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ አቀረበ የኤሌክትሪክ እና የውሃ አገልግሎት በገደብ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እንዲከፈልባቸው የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ። ከታክሱ ነጻ የሚሆኑት የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ ከሚወሰን በታች የኤሌክትሪክ እና ውሃ ፍጆታ ያላቸው እንደሆኑ ተገልጿል። አዋጁ ሲጸድቅ ለሁለት አስርት ዓመታት በስራ ላይ ቆየውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ እና ከዛ በኋላ እሱን ለማሻሻል ሁለት ጊዜ የወጡትን የማሻሻያ አዋጆች ሙሉ በሙሉ የሚሽር ነው ተብሏል። “አነስተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል ያለበትን ወጪ ለማርገብ ሲባል” የኤሌክትሪክ እና የውሃ አገልግሎት ከታክሱ ነጻ ተደርገው እንደነበር ሲገለፅ ረቂቁ “የተጨማሪ እሴት ታክስ ከሚታይበት ጉድለት አንዱ እና ዋነኛው በርካታ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ከታክሱ ነጻ መደረጋቸው ነው” ይላል። በረቂቅ አዋጁ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ በማድረግ የተሰጠውን “ልዩ መብት” እንደገና በመፈተሽ ማስተካከያዎች መደረጋቸውን ማብራሪያው ይገልጻል። ከታክስ ነጻ ተደርገው አሁን ታክስ እንዲከፈልባቸው ከተደረጉ አግልግሎቶች መካከል የውሃ እና ኤሌክትሪክ እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎቶች ይገኙበታልም ተብሏል። በስራ ላይ ያለው አዋጅ የኤሌክትሪክ፣ የኬሮሲን [ናፍጣ] እና የውሃ እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎትን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ እንዲሆኑ እድርጎ ነበር። ይህን አዋጅ የሚሽረው አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ግን የውሃ የኤሌክትሪክ፣ የውሃ እና የትራንስፖርት አገልግሎቶች በገደብ ታክስ እንዲከፈልባቸው አድርጓልም ነው የተባለው። ምንጭ፦ BBC Amharic
Mostrar todo...
👍 1
Ethiopia Vies to Host Prestigious Logistics Congress Read More 👉🏾 https://onestop.et/ethiopia-vies-to-host-prestigious-logistics-congress/
Mostrar todo...

👍 1
Ethio-Djibouti Railway Marks New Era with Handover Ceremony Read More 👉🏾https://onestop.et/ethio-djibouti-railway-marks-new-era-with-handover-ceremony/
Mostrar todo...
Ethio-Djibouti Railway Marks New Era with Handover Ceremony

In Addis Ababa, the Ethio-Djibouti Railway transitioned to joint management by Ethiopia and Djibouti. For six years, the Chinese Railway Construction

👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
#LocalNews | EIH, Toppan Gravity to transform security printing industry Ethiopian Investment Holdings (EIH), a recently established sovereign wealth fund (SWF) that has teamed up with a dominant global security printing firm, is making its first greenfield investment. By 2026, the initiative aims to transform the security printing industry. The facility called Toppan Gravity Ethiopia (TGE), established by Toppan Gravity, EIH, Berhanena Selam Printing Enterprise, and Education Materials Production and Distribution Enterprise, both of which are under EIH, will be equipped with cutting-edge technology and stringent security measures to produce high-quality passports, ID cards, and banking cards, setting new standards for security and integrity. Read More Source: Capitalethiopia @Ethiopianbusinessdaily
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የሚያዚያ ወር ሀገር አቀፍ የዋጋ ግሽበቱ 23.3 በመቶ ሆኖ መመዝገብን አስታውቋል የዋጋ ግሽበቱ በመጋቢት ወር ከነበረበት 26.2 በመቶ ወደ 23.3 በመቶ በመሆን ቅናሽ አሳይቷል ብሏል። በወሩ ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ምግብ ነክ ዕቃዎች 27 በመቶ እንዲሁም ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች ደግሞ 18 በመቶ ድርሻ መያዛቸዉ ታዉቋል ። Source: Capitalethiopia @@Ethiopianbusinessdaily
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኩዌት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን በሀገሯ ለማሰራት የሰራተኛ ምልመላ ልትጀምር ነው ተባለ ኢትዮጵያ እና ኩዌት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በኩዌት ሀገር የስራ አድል አንዲያገኙ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነቱን ለማጠናቀቅ የመጨረሻው ሂደት ላይ መሆኑን የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡ የመግባቢያ ስምምነቱ በዚህ ወር መጨረሻ ይፈረማል የተባለ ሲሆን ስምምነቱ የሰራተኞችን መብት፤ አሰሪዎች የስራ ውል በሚያቋርጡበት ጊዜ ሰራተኞች ስለሚያገኙት ክፍያ፤ የሰራተኞች የሳምንት፣ የአመት እረፍት እና ተያያዥ ስምምነቶችን የያዘ መሆኑ ተነግሯል፡፡ የሰራተኛ ምልመላው ስምምነቱ እንደተፈረመ ይጀመራል የተባለ ሲሆን ስምምነቱ ኩዌት ያጋጠማትን የሰራተኞች እጥረት ይቀርፋልም ነው የተባለው፡፡ @TikvahethMagazine
Mostrar todo...
👍 1 1👏 1