cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Ethiopia first(ቅድምያ ለሀገር)

ሀገር ከግል ፍላጎት በላይ ናት

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
205
Suscriptores
-224 horas
-27 días
-530 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ጓደኛቸውን በመግደል ሲያሽከረክረው የነበረውን መኪና ወስደው ተሰውረዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በ24 ሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️ የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሰሜን ማዘጋጃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ከአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል እና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ  የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ገ/ሚካኤል ሰይፉ የተባለው ሟች የወንጀል ፈፃሚዎቹ የቅርብ ጓደኛ በመሆኑ በየዕለቱ እየተገናኙ አብረው የሚውሉ፣ የሚዝናኑ እና በእጅጉ የጠነከረ የጓደኝነት ግንኙነት ያላቸው የሱሉልታ ከተማ ነዋሪዎች እንደሆኑ  ተጠርጣሪዎቹ ለፖሊስ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል። በዕለቱ ሟች በወንጀሉ ከተጠረጠሩት ከሁለቱ ጓደኞቹ ጋር አብሮ ሲዝናና እንዳመሸ ታውቋል።ተጠርጣሪዎቹ  ቴዎድሮስ ታከለ እና  ሲሳይ ጥላሁን ከምሽቱ 5 ስዓት ገደማ የጓደኛቸውን  አንገት በማነቅ ህይወቱ እንዲያልፍ ካደረጉ በኋላ አስክሬኑን መንገድ ላይ በመጣል  ሞባይል ስልኩንና መታወቂያውን ጨምሮ በወቅቱ ሲያሽከረክረው የነበረውን የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 4-15624 ኢት መኪና ወስደው ተሰውረዋል ተብሏል፡፡ ፖሊስ የወንጀሉ ሪፖርት ከደረሰው በኋላ ባደረገው ያልተቋረጠ ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩትን ግለሰቦች ለይቶ በማወቅ በ24 ሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡ አንደኛው ተጠርጣሪ ከአየር ጤና አካባቢ የተያዘ ሲሆን ሁለተኛው ተጠርጣሪ  ደግሞ ሱሉልታ ከተማ ውስጥ ሊገኝ ችሏል፡፡ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተከናወነ ምርመራ የማስፋት ስራ የሰረቁትን ተሽከርካሪ በሸገር ከተማ ወለቴ ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ በመውሰድ እንዲሸጥላቸው ለአንድ ግለሰብ እንደሰጡት በማረጋገጥ መኪናው ከቆመበት በምሪት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ተሽከርካሪውን ለመሸጥ ተስማምቶ ከተጠርጣሪዎቹ የተቀበለውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ የክትትል እና የምርመራ ስራው  የቀጠለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
Mostrar todo...
በሕግ የማስከበር ሥራው የልማት ተግባራት እንዲከናወኑ ተደርጓል‼️ 🗣የሰሜን ሸዋ ኮማንድ ፖስት በዞኑ የተሠሩ የጸጥታና የልማት ሥራዎችን የሚገመግም መድረክ እየተካሄደ ነው። በመድረኩም የኮማንዶና አየር ወለድ ዋና አዛዥና የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሌተናል ጀኔራል ሹማ አብዴታ እና የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ምክትል አዛዥና የሰሜን ሸዋ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ብርጋዴል ጄኔራል አበባው ሰይድን ጨምሮ የሠራዊቱ፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል። ብርጋዴል ጄኔራል አበባው በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በዞኑ የጸጥታ ኃይሉን እንደገና ማደራጀት በመቻሉ አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን የተጀመሩ ሥራዎች ውጤት እንዲያመጡ አስችሏል ብለዋል፡፡ ግብርናው በአግባቡ እንዲከናወን፣ ማዳበሪያn ለአርሶ አደሩ እንዲደርስ እና ከተሞች ሰላም እንዲሆኑ መደረጉንም አብራርተዋል፡፡ ሕዝቡ ለሠራዊቱና ለመንግሥት የጸጥታ ኃይል ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው በአጭር ጊዜ አስተማማኝ ሰላም ማስፈን እንደሚቻልም አመላክተዋል፡፡
Mostrar todo...
መሃመድ ሞክበር የኢራን ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ‼️ የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ሃሚኒ መሃመድ ሞክበርን የኢራን ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት አድርገው ሾመዋል፡፡ መሃመድ ሞክበር በሄሊኮፕተር አደጋ ሕይወታቸው ያለፉት ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ምክትል እንደነበሩ ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ አደጋ ሕይወታቸው ያለፉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚር አብዱላሂን በመተካት ደግሞ አሊ ባጌሪ ካኒ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል፡፡ አሊ ባጌሪ ካኒ ቀደም ሲል የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ሲያገለግሉ እንደነበር ተመላክቷል፡፡ በኢራን ከ50 ቀናት በኋላ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚካሄድ መገለጹንም አልጀዚራ በዘገባው አስፍሯል፡፡ በተያያዘ ዜና በሄሊኮፕተር አደጋው ለደረሰው ሀዘን የተለያዩ ሀገራት ለኢራን ህዝብና መንግስት መጽናናትን ተመኝተዋል።            በዚህም የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ፣ የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼሃባዝ ሻሪፍ ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪም የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ቢን ዛይድ አል ናህያን እና የቬንዝዌላው ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማድሮ እና በርካታ የሀገራት መሪዎች ሀዘናቸውን ገልጸዋል።
Mostrar todo...
#BREAKING የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን ሆሴን አሚራብዶልሂያንን ጭኖ ሄሊኮፕተሩ በተከሰከሰበት ቦታ "የተረፈ ሰው የለም" ሲል የኢራን መንግስት ሚዲያ ዘግቧል‼️ በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ውስጥ ለሰዓታት ያህል ተራራማ ቦታዎችን ሲዘዋወር ከቆየ በኋላ የነፍስ አድን ቡድኖች የተከሰከሰውን ሄሊኮፕተር ሙሉ በሙሉ ወድሟል ብለዋል።
Mostrar todo...
ሀገሪቷ ከወጪ ንግድ ከ2.5 ቢሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሏ ተገለፀ‼️ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር እንደገለፀዉ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ ከ 2.5 ቢሊየን በላይ የአሜሪከን ዶላር ገቢ መገኘት ችሏል ብሏል። ሚንስትሩ እንደገለፀዉ በዘጠኝ ወሩ 3.56 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ  2.511 ቢሊዮን ዶላር ወይም 70.49 በመቶ ገቢ ማግኘት ተችሏል፡፡ ከተገኘው ገቢ የግብርና ምርቶች 73.6%፣ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ 51.54%፣ ማዕድን ዘርፍ 66.53% እዲሁም  ኤሌክትሪክና ሌሎች ምርቶች 71.25% ዕቅድ አፈፃፀም ማሳየት ችለዋል በማለት በሪፖርቱ ገልጿል ። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ክትትል የሚደረግባቸው የቅባት እህሎች፣ የጥራጥሬ ምርቶች፣ የብርዕና አገዳ ሰብሎች፣ የጫት ምርት፣ የቁም እንስሳት እና የደንና ደን ውጤቶች እንዲሁም የቁም እንሰሳት መኖ  811.13 ሚሊዮን ገቢ ለማግኝት ታቅዶ 699.11 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘት ችሏል ማለቱን ካፒታል ዘግቧል።
Mostrar todo...
1 ሺህ 147 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ‼️ በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ከተመለሱት 1 ሺህ 147 ዜጎች ውስጥ 1ሺህ 46ቱ ወንዶች፣ 80 ሴቶች እና 21 ጨቅላ ህፃናት መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከሚያዝያ 4 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ25 ሺህ 800 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን ከሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Mostrar todo...