cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

ይህ ቻናል በላፍቶ ቢላል መስጂድ የሚሰጡ ደርሶችን እና የተለያዩ ሙስሊሙን የሚጠቅም ሙሀደራዎችና አጫጭር መልዕክቶች የሚለቀቅበት ሲሆን ሊንኩን በመጠቀም ለራሳችንም ሌሎችም እንዲጠቀሙ እናድርግ https://t.me/lafto_qirat

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 378
Suscriptores
+124 horas
+27 días
+3130 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ሀዘንና ደስታ إنا للہ وإنا إليہ راجعون 🔅በትላንትናው ዕለት (ረቡዕ ዙል-ቀዕዳህ 7/1445 ዓ.ሂ) የአንድ ወንድማችን የሰባት ዓመት ህፃን ልጅ ወደ ኣኺረህ እንደሄደና ሰላተል-ጀናዛ እንድሰግድ አባቱ እንደሚፈልግ ተደውሎ ተነግሮኝ እንደምንም ብዬ ሄጄ የጀናዛ ሽኝቱ ላይ ታድሜ የጀናዛ ሰላት የተሰገደበት መስጂድ መደበኛ ኢማምም (ጀዛሁላሁ ኸይረን) በወላጅ አባቱ ጥያቄ መሰረት ፈቅዶ ሰላተል-ጀናዛ አሰግጄ የአባቱ ምኞትና ፍላጎት ተሳክቶ ጀናዛውን አጅበን ቀብረን ተመለስን። 💥 አላህ ቀብሩን የጀነት ጨፌ ያድርግለት፤ ከቀብር  ፈተናም ይጠብቀው፤ ለወላጆቹም ሸፊዕ ያድርገው፤ ያማረ ሰብርም ይስጣቸው። 🔅ልጁ (ህፃን አሕመድ ነስሬ) በዕድሜ ትንሽ ቢሆንም ያማረ ስነምግባር የነበረውና ዲኑ ላይ ጎበዝ እንደነበረ እንዲሁም ደዕዋና የዳዕዋ ሰዎችን አብዝቶ ይወድ እንደነበረ ስሰማ በጣም ደስ ብሎኛል። 🔅እንደዚህ ዓይነት ልጆች መኖራቸውን ማየትና መስማቱ ብዙ የተበላሹ የዘመናችን ልጆችን ሁኔታ በማየት የታመሙና በስጋት የተወጠሩ ልቦችንም በከፊል ያረጋጋል። 🔅በዘመናችን ብዙ ልጆች በዚህ ዕድሜ ከኳስ ጨወታና ከኳስ ሰዎች፤ ባስ ሲልም ከፊልምና ከድራማ ሰዎች ውጪ ሲወዱና ሲያደንቁ እምብዛም አይታይም! ይህም የሚሆነው አብዛኛውን ጊዜ በወላጆች የቤት ውስጥ አያያዝ፣ በዘመን ወለዱ ስልክና ሶሸል ሚዲያ፣ በትምህርት ቤትና በመኖሪያ አካባቢዎች በሚያገኟቸው ሰዎች (ልጆች) ምክንያት ነው። 🔅በመሰረቱ ህፃናት ቤት ውስጥ ወላጆቻቸው ሁሌ የሚያደንቁትን ነገር ያድንቃሉ፤ ለሚጨነቁለት ነገር ይጨነቃሉ፤ ጊዜና ትኩረት ለሚሰጧቸው ነገሮችም ጊዜና ትኩረት ይሰጣሉ። 🔅የልጅ አዋቂ የነበረው ወዳጃችን ሟች (አሕመድ ነስሬ تغمدہ اللہ برحمتہ) ከአላህ እንክብካቤ ቀጥሎ በዚህ እድሜው ምን ዓይነት ሰዎችን መውደድና መምሰል እንዳለበት ያወቀውና የልጅ አዋቂ መሆን የቻለውም ቤት ውስጥ ዘውትር ከቤተሰቦቹ ያየውና ይሰማው በነበረው ሁኔታና ተግባር ምክንያት ነው። 🔅ስለዚህ ወላጆች ሆይ ለልጆቻችሁ መልካም አርዓያ ሁኑ! ቤት ውስጥ የሚያቱትና የሚሰሙት ማንኛውም ነገር የነገ ማንነታቸው ላይ ትልቅ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ጠንቅቃችሁ እወቁ። 🔅ልጅ በዱኒያም ይሁን በኣኺረህ ለወላጆቹ የሚጠቅመውና የሚያኮራቸውም በዲን ተኮትኩቶ ሲያድግ ነውና ምግብና ልብስ በሟሟላት ብቻ ሳይሆን በዲን ተርቢያ በማድረግም ጭምር እውነተኛ ወላጆች እንሁን። 🔅ወዳጃችን ህጻን አሕመድ ነስሬን አላህ በነቢዩ ኢብራሂም (عليہ السلام) እንክብካቤ ስር አቆይቶ የቂያም ቀን በሰላም ከወላጅና ቤተሰቦቹ ጋር አገናኝቶ ከነቢያትና ከደጋጎች ጋር በጀነተል-ፊርደውስ ያኑረው! اللهم آمين ✍ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም ሃሙስ ዙል-ቀዕዳህ 8/ 1445 ዓ.ሂ ዛዱል-መዓድ
Mostrar todo...
👍 1
ነቢያች ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “ከየአድማስም ያሉ (የኩፍር ሃይላት) ሕዝቦች፣ ልክ ወደ ማእድ ተመጋቢዎች እንደሚጠራሩ ሁሉ ይጠራሩና ሊቀራመቷችሁ ይቃረባሉ።” የአላህ መልእክተኛ ሆይ! “በዚያ ጊዜ ሙስሊሞች ጥቂቶች ይሆናሉን? ተብለው ተጠየቁ። እርሳቸውም፡- “አይሆኑም፤  እንዲያውም ብዙ ናቸው  ግን ጎርፍ ይዞት እንደሚሄደው ግሳንግስ ናቸው። የቅርቢቱን አለምን በማፍቀራችሁ እና ሞትን በመጥላታቹ የተነሳ ከጠላታችሁ ልብ ላይ እናንተን መፍራት ይወገዳል።” አሉ።
Mostrar todo...
👍 1
ወህብ ኢብኑ ሙነቢህ እንዲህ ይላሉ፦ “የኒዕማ ቁንጮዎች ሦስት ናቸው፣ የመጀመርያው፡  ያለሱ ኒዕማዎች የማይሟሉበት የሆነው የእስልምና በረከት። ሁለተኛው ደግሞ፡ ያለ እሱ ሕይወት የማይጥምበት የሆነው የጤንነት በረከት። ሦስተኛው፣ ያለሱ ሕይወት ሙሉ የማትሆነበት የሆነው የመብቃቃት በረከት።” 📚ዒደቱ አስሷቢሪን ሊብኒል ቀዪም ገፅ (117)
Mostrar todo...
👍 1
ጀነት በሚፈለግባቸው ስራዎች ከንቱ ዝናን እና መሪነትን መፈለግ ይብቃ! ሰሞኑን ከየመን የተላኩ ጥቂት ኪታቦች ደረሱኝ ። አላህ የዒልም እና የጀነትን መንገድ ያግራለትና አንድ የሱና ወንድሜ ነበር ኪታቦቹን የላከልኝ ። ከነዚህ ኪታቦች ውስጥ አይኔ አጠር ያለች አንዲት አጭር ሪሳላ ላይ አረፈ ። ርእሱ ልቤን ሳበው ! ሪሳላዋን ላነብ አለቅጥ ጓጓሁ ... ርእሱ በዘመናችን የተንሰራፉ ሁለት የልብ ነቀርሳዎችን መሰረት ያደረገ ነው - ዝናን ማንፍነፍ ! መሪነትን ማሰስ! ! حب الرئاسة والظهور يورث الشقاق والشرور ይላል ... ፀሃፊው ከየመን መሻይኽ ዉስጥ አንዱ የሆኑት الشيخ أنيس بن صالح المهندس اليافعي ናቸው ... ሪሳላዋ ውስጥ በርእሱ ዙሪያ ጠቃሚ እና ልብን የሚያክሙ ገሳጭ ምክሮችን በሰፊው  እናገኛለን ወላሂ! ነገሩ ያሳስባል ! ርእሱ እጅጉን ያስጨንቃል ! ለመሆኑ ... ስንቶቻችን እንሆን እንዲህ አይነቱን በሽታ በልባችን አምቀን ከመልካሞች የምንታሰብ !? ስንቶቻችን እንሆን ... በመልካም ስራዎቻችን እና ንግግሮቻችን  ዝናን እያነፈነፍን ውለን የምናድር? ስንቶቻችን እንሆን  እነዚህን ሁለት የኢኽላስ ጠላቶች ተሸክመን ስለ ኢኽላስ የምንሰብከው ? ! ስንቶቻችን እንሆን  ዝናን በማሰስና ፣   መሪነትን በማሰብ ሌሎች ወንድሞች በእኛ ቦታ  የአላህ ቤቶች ውስጥ እንዳያስተምሩ እንቅፋት የምንሆነው ?!! ስንቶቻችን እንሆን ዝናን እና የበላይነትን  ፍለጋ ሊትተቹ የማይገባቸው አማኞችን አለአግባብ የተቸን ?! ስንቶቻችን ... አላህ ይመልሰን ጀነት በሚፈለግባቸው ስራዎች ከንቱ ዝናን እና መሪነትን መፈለግ ይብቃ! © ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ
Mostrar todo...
👍 2
ኢትዮጵያ ኒቃብ መልበስን ልትከለክል ነው‼ ============================= (የአዲሱ ረቂቅ አዋጅ 15+ ስጋቶች!) || ✍ የኢትዮጵያ መንግስት ኒቃበ ለብሶ መማርንና መሥራትን የሚከለክል ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቶ ለማፅደቅ በሂደት ላይ ነው። እስካሁን ድረስ በሃገሪቱ ኒቃብን በግልፅ የሚከለክል ህግ ባይኖርም፤ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ሙስሊም ጠል ኃይሎች ባልተጻፈ ህግ ኒቃብ መልበስን ሲከለክሉ ነበር። ለናሙና ያክል በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ በኒቃብ ሳቢያ 2000 ገደማ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው የታገዱበት ሁኔታ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ለነዚህና መሰል ኒቃብን በግል ጥላቻቸው ተነሳስተው ለሚከለክሉ አካላት ሽፋን የሚሰጥ አዲስ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለመፅደቅ በሂደት ላይ ነው። ከኒቃብ ጉዳይ ባሻገር በመሰል ተቋማትና አንዳንድ የህዝብ መገልገያ አካባቢዎች በጀማዓህ ሶላት መስገድን የሚከለክል ክፍልም አለው። ረቂቅ አዋጁ ከመዘጋጀቱ በፊት ለግብዓትነት የሚሆን ጥናት ቀድሞ የተዘጋጀ ሲሆን፤ በጥናቱ ውስጥ ከተሳተፉ 10 አባላት መካከል ሙስሊሙን የወከለው አንድ ግለሰብ ብቻ ነበር። ግና ከጥናት ዝግጅቱ ጀምሮ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ሙስሊም ማኅበረሰብ በአግባቡ ያልወከለው ሂደት፤ ጭራሽ ረቂቅ አዋጁ ላይ ግልፅ የሙስሊሙ መብት ጥሰቶች ተካተዋል። በዚህ በባለ 15 ገፅ በንድፍ ላይ ያለ ረቂቅ አዋጅ ውስጥ በቀጥታ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጋር ከሚጋጩ ነጥቦች መካከል፤ የሚከተሉት አንቀፆችና ንዑስ አንቀፆች ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጋር የሚያጋጩና ጥያቄ የሚያስነሱ ናቸው። 1) 13.8 "የተከለከሉ ቦታዎች ቅስቀሳ ማድረግ" ማለት የትኞቹ በታዎች ናቸው? 2) 13.9 other (ሌሎች) ማለት ምን ማለት ነው? 3) 15.1 መስጂድ ሲጠበን ከመስጅድ ውጪ መስገድ አንችልም ማለት ነው? መስጅድ በሌለበት መስገድ አይቻልም? ይህን መሠረት አድርገው ሰበብ ፈላጊዎች ከመስጅድ ውጭ መስገድን እንዲከለክሉ መንገድ ስለሚከፍት ይህን እንደማይመለከት በግልፅ ሌላ ንዑስ አንቀፅ ላይ መስፈር አለበት። 4) 15.4 ሁሉም ቦታ በሚባል ደረጃ ሶላትን ይከለክላል፡፡ 5) 17.4 "በቡድን አምልኮ" በሚል ሽፋን የጀመዓህ ሶላትን ለመከልከል ይውላል። 6) 17.7 ቅጣቶች ለመንግስት መ/ቤቶች ክፍት ሆነዋልና ሌላ ችግር እንዲፈጠር በር ይከፍታል፡፡ ምክንየተቱም የትኛውም መሥሪያ ቤት ተነስቶ የራሱን ቅጣት በጥላቻ ቢያስተላልፍ መብት አለው ማለትን ያሲዛል። 7) 19.1 "ከኃይማኖት ተፅዕኖ ነፃ መሆን" ማለት ምን ማለት ነው? እስከምን ደረጃ? 8) 19.2: የአንዳንድ ኢስላማዊ ትምህርት ቤቶችን አሠራር ለማፈን በር የሚከፍት ነገር አለው። 9) 19.5 በትምህርት ቤቶች የጀመዓህ ሶላት ተከልክሏል፡፡ 10) 19.6: "ማንነትን ለመለየት" በሚል ሽፋን  ኒቃብን ይከለክላል። በዚህ ቴክኖሎጂው ባደገበት ዘመን እንደ አሻራ ያሉ ቀላል ወጪ የሚጠይቁ ዘዴዎች እያሉ፣ በተለመደው አሠራርም በሴት የጥበቃ ሠራተኛ ማንነታቸውን መለየት እየተቻለ፣ በቢዝነስ ተቋማት ዘንድ ይህ ጥያቄ ሳይነሳ መኗኗር ሲቻል እያዬን… በዚህ ሽፋን ኒቃብን መከልከል ነውር ነው። 11) 22.2 በተለይም በሸሪዓው ውርስንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ ለአንዳንድ ሙጅሪሞች በር ይከፍታል። 12) 24.1 የመጅሊሱንና የአንዳንድ የበጎ አድራጎት ኢስላማዊ ተቋማትን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡ በተለይም በሙስሊሙ ዘንድ ሶደቃ የተለመደ ነውና! 13) 25.1: ይህም የመጅሊሱንና የአንዳንድ የበጎ አድራጎት ኢስላማዊ ተቋማትን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡ 14) 25.3 ይህም የመጅሊሱን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡ መጅሊስ በአዋጅ የተቋቋመ ራሱን የቻለ ተቋም ከሆነ በዚህ ደረጃ በሌላ የበላይ አካል control መደረግ የለበትም። 15) 25.4: ይህም የመጅሊሱን ነፃነት የሚያሳጣ ነው፡፡ "በአዋጅ መቋቋም" የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ ትርጉም አሳጥቶ እንደተለመደው ወደ ተራ NGO ከማውረድ አይተናነስም። 16) 26: "ከኃይማኖት ተፅዕኖ የተላቀቀ" ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሚወስኑት የየትምርት ቤቱ ኃላፊዎች ቢሆኑ የተሻለ ይሆናል፡፡ አለበለዚያ የኢስላማዊ ት/ቤቶችን ነፃነት ያፍናል። …  ባለ 15 ገፁ ይህ ረቂቅ አዋጅ በሶፍቲ ኮፒ በዚህ ሊንክ ስለሚገኝ፤ አንብቡትና እናንተም የታዘባችኋቸውን ስጋቶችና ህፀፆች አስፍሯቸው። https://t.me/MuradTadesse/35726 ♠ ይህ አፈና ሳይጻፍ የተበደልነው አንሶን ጭራሽ ተልፎ ሊተገበርብን ጫፍ ሲደርስ በዝምታ ማሳለፍ የለብንምና ሁሉም ሰላም ወዳድና ለእምነቱ ተቆርቋሪ ከወዲሁ ጉዳዩ ሳይጸድቅ ይስተካከል ዘንድ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ ግደታችን ነው። መልዕክቱን ለሌሎችም በማሰራጨት ህዝበ ሙስሊሙ እየመጣ ስላለው አዲስ አዋጅ ከወዲሁ በቂ መረጃና ግንዛቤ ኖሮት የሚጠበቅበትን እንዲያደርግ እናድርግ። || t.me/MuradTadesse x.com/MuradTadesse fb.com/MuradTadesse
Mostrar todo...
👍 4💔 2
ዱንያ የተፈጠረችው ለመከራ ነው፣ስለዚህ ጤናማ አእምሮ ያለው ሰው በትዕግስት ላይ ራሱን መፋለም አለበት። (ኢብኑል ጀውዚይ)
Mostrar todo...
00:31
Video unavailableShow in Telegram
. ምንም ነገር ከማሰራጨታችን ወይም ከማየታችን በፊት ይህን አያ እናስታውስ ــــــــــــــــــــــــــــــــــــ🍃🌸🍃
Mostrar todo...
"~ቸሩ ጌታችን አላህ ሌላ አዲስ ቀን ጨመረልን፤ አልሐምዱሊላህ፡፡ ስንነሳ ዝም ብለን አይደለም መነሳት ያለብን፡፡ ዛሬም ለመሻሻል ሌላ እቅድ ይኑረን፡፡ የትናንቱን ስህተት ላለመድገም እንጥራለን፣ ዛሬን ለመሻሻል እንቆርጣለን፡፡ ካለፈው እንማራለን፣ ከቀደመው ልምድ እንቀስማለን፣ በተቻለን መጠን ሥርዓት ለመያዝ እንሞክራለን፡፡ የሰው ልጅ በሕይወት እስካለ ድረስ ዕድሜዉን በሙሉ ይለፋል፣ ይወጣል፣ ይወርዳል፡፡ አንሠራለን እንኖራለነ፤ እንኖራለን፡፡ እንኖራለን እንሠራለን፡፡ ዱንያ ላይ መልካም ነገር ከመሥራት የሚያቆመን ሞት ብቻ ነው፡፡ ሙእሚን ከኸይር ነገር አይጠግብምና፡፡"
Mostrar todo...
👍 2
"~ቸሩ ጌታችን አላህ ሌላ አዲስ ቀን ጨመረልን፤ አልሐምዱሊላህ፡፡ ስንነሳ ዝም ብለን አይደለም መነሳት ያለብን፡፡ ዛሬም ለመሻሻል ሌላ እቅድ ይኑረን፡፡ የትናንቱን ስህተት ላለመድገም እንጥራለን፣ ዛሬን ለመሻሻል እንቆርጣለን፡፡ ካለፈው እንማራለን፣ ከቀደመው ልምድ እንቀስማለን፣ በተቻለን መጠን ሥርዓት ለመያዝ እንሞክራለን፡፡ የሰው ልጅ በሕይወት እስካለ ድረስ ዕድሜዉን በሙሉ ይለፋል፣ ይወጣል፣ ይወርዳል፡፡ አንሠራለን እንኖራለነ፤ እንኖራለን፡፡ እንኖራለን እንሠራለን፡፡ ዱንያ ላይ መልካም ነገር ከመሥራት የሚያቆመን ሞት ብቻ ነው፡፡ ሙእሚን ከኸይር ነገር አይጠግብምና፡፡"
Mostrar todo...
𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥

➜ ከዚህ ቻናል አንብባችሁ በተጠቀማችሁ ቁጥር፤ይህን ደካማ እና ስህተቱ ብዙ የሆነውን ወንድማችሁን በመልካም ዱዓችሁ አስታውሱት! || ✍ወንድማችሁ አቡ ሱፍያን―