cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ብዙ ልጆች አሉት....

በዚህ ቻናል የተለያዩ + መንፈሳዊ ዝማሬዎችን ተ የመዝሙር ግጥሞችን +መንፈሳዊ ምስሎችን +አስተማሪ ስነ ፅሁፎችን ያገኛሉ።ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ዝም አንልም በፍፁም ዝም አንልም ✓ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር🙏🙏🙏

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
198
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
ሰበር ዜና ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዶ/ር አረፉ ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ ዕድ የሾሙት ጳጳሳት 14 ኤጲስ ቆጶሳት መካከል አንዱ ነበሩ። በቀድሞ ስማቸው አባ ኃይለማርያም መለሰ ዶ/ር በጵጵስና ስማቸው ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዶ/ር የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። ብፁዕነታቸው ለረጅም ጊዜ ከሀገር ውጪና በሀገር ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ሳይችል ቀርቶ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለይተዋል። ምንጭ :- ኢኦተቤ ቴቪ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE 💚  •✥• @abenet_tmhert •✥•💚 💛  •✥• @z_tewodros •✥•💛 💖✥ @abenet_tmhert •✥• 💖              ✧━━━━━━━━━━━✧‌‌
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
የሞዛምቢክ ፓስተር እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ 40 ቀናት ለመጾም ሲሞክር ህይወቱ አለፈ አንድ የሞዛምቢክ ፓስተር በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተገለጸዉ ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ለ40 ቀናት የጾመዉን ጾም ክብረወስን ለመጋራት ሲሞክር ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።በሞዛምቢክ ማዕከላዊ ማኒካ ግዛት ውስጥ በሚገኘው የሳንታ ትሪንዳድ ቤተ ክርስቲያን ፓስተር እና መስራች የሆኑት ፍራንሲስኮ ባራጃህ ረቡዕ እለት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል። በከባድ ሁኔታ የጤና ችግር ዉስጥ ከወደቀ በኃላ ወደ ቤይራ ሆስፒታል ተወስዶ ሲታከም ቢቆይም ህይወቱ አልፏል።ከ25 ቀናት ጾም በኋላ መቆም፣ መታጠብና መራመድ እስከማይችልበት ደረጃ ድረስ ክብደት ከድቶት እንደነበር መገለፁን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል። ከቀናት በኋላ፣ በዘመድ አዝማድና በአማኞች ግፊት፣ ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም ወደ ጤናው ለመመለስ የተደረገው ሙከራ ግን አልተሳካም።በቤተክርስቲያኑ አማኞች ዘንድ እና በጎረቤቶቹ ያሉ አማኞች በሁኔታዎች ለውጥ አልተገረሙም ፣ምክንያቱም ከቅርብ ቀናት ወዲህ የታየበት የሰውነት አካል ለዉጥ በህይወት ለመትረፍ አስፈሪ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ የቻናላችን ቤተሰብ በመሆን ይከታተሉ:: ለወዳጆ ያጋሩ🙏🙏🙏 https://t.me/ImpactTrainingConsultancey
Mostrar todo...
ዐቢይ_ጾም ዐቢይ ለምን ተባለ ቢሉ ‹‹ዐበየ›› ማለት ከፍ አለ ማለት ሲሆን ከዚህም ግስ ዐቢይ የሚለው ቅጽል ይገኛል፡፡ዐቢይ ማለት ከፍ ያለ ትልቅ ማለት ነው፡፡ ዐቢይ ጾም የተባለበት ምክንያት፡- ሀ. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም ስለሆነ ለ. በቀኑ ቁጥር ከሌሎች አጽዋማት የሚበልጥ ስለሆነ ሐ. ሦስቱ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች ማለትም ➛ ትዕቢት ➛ ስስት ➛ ፍቅረ ነዋይ ድል የተመቱበት ስለሆነ ነው፡፡ በቤተክርስቲያን ስያሜ መሰረት በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚውሉ ሰንበታት እያንዳንዳቸው መጠሪያ ስም ሲኖራቸው እነርሱም፡- ዘወረደ የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሰንበት ሲሆን ይህም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን ፈጥሮ የሚኖር አልፋና ኦሜጋ ከሰማየ ሰማያት መውረዱንና ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመለክት ሥያሜ ነው፡፡ ቅድስት ይህ የሁለተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን የተባለበትም ምክንያት ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ነው፡፡ እንዲሁም ይህ ዕለት ዕለተ እግዚአብሔር የተባለች የሰንበት ክርስቲያን ቅድስናን ያመለክታል ምክንያቱም የዚች ዕለት ጌታ እርሱ ቅዱስ እግዚአብሔር ነውና ስለዚህም ዕለተ ሰንበት ቅድስት ተብላለች፡፡ ምኩራብ ይህ የሦስተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን በዚህ ሰንበት ጌታ በመዋዕለ ትምህርቱ በምኩራብ ገብቶ ማስተማሩ ይነገራል፡፡ እንዲሁም ይህች ዕለት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ ገብቶ እንዳስተማረ የሚታሰብበት ዕለት ነው፡፡ ምኩራብ ማለት የቤተ አይሁዳውያን የጸሎት ቤት ነው፡፡ መጻጉዕ ይህ የአራተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱ እውራንን ማብራቱ ለምጻምን ማንጻቱ ሽባዎችን መተርተሩ የሚያነሳ መዝሙር የሚዘመርበት እንዲሁም እነዚህ ሁሉ ድንቅ ገቢራተ ታምራቶች የሚዘከሩበት ዕለት ነው፡፡ ደብረ_ዘይት ይህ የአምስተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆኖ ነገረ ምጽአቱን እንዳስተማረ የሚወሳበት ሰንበት ነው፡፡ ደብረ ዘይት ማለት ወይራ የበዛበት ተራራ ማለት ነው፡፡ ገብርኄር ይህ የስድስተኛው ሳምንት ሰንበት ስያሜ ሲሆን ይህም ዕለት ለጌታው ታማኝና በጎ የሆነው ባርያ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ተብሎ እንደተመሰገነ የሚነገርበት ዕለት ነው፡፡ ኒቆዲሞስ ይህ የሰባተኛው ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ይህም ዕለት ኒቆዲሞስ የተባለው የአይሁድ መምህር በሌሊት ወደ ጌታው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እየመጣ ይማር እንደነበረ ይታሰብበታል በዚም ዕለት የኒቆዲሞስን ታሪክ የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡ ሆሳዕና ይህ የስምንተኛው ሳምንት ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት በነቢዩ በዘካርያስ ላይ የተጻፈው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያይቷ እና በውርንጭላይቷ ላይ ተቀምጦ ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ተብ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ መግባቱ የሚተሰብበት ዕለት ነው፡፡ ሆሳዕና ማለት ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው:: ጾሙን የበረከት ጾም ያድርግልን፡፡ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE 💚  •✥• @abenet_tmhert •✥•💚 💛  •✥• @z_tewodros •✥•💛 💖✥ @abenet_tmhert •✥• 💖              ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌
Mostrar todo...
#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ጉዳይ የሚከታተለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች ምድብ ችሎት #የዕግድ ትዕዛዝ መስጠቱ ተገለፀ። ፍርድ ቤቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የእግድ አቤቱታ መሠረት ቤተ ክርስቲያኗ አውግዛ በለየቻቸው ተጠሪዎች ላይ የእግድ ትእዛዝ መስጠቱን የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በዚህ ጉዳይ የቤተክርስቲያኗ የህግ ክፍል ዝርዝር መግለጫ ይሰጣል ተብሏል። @tikvahethiopia
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
#ሰበር_መረጃ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የእግድ አቤቱታ መሠረት ቤተ ክርስቲያኗ ባወገዘቻቸው ተጠሪዎች ላይ ፍርድ ቤቱ የእግድ ትእዛዝ መስጠቱ ተገልጿል። ዝርዝሩን እንደደረሰን እናቀርባለን፡፡
Mostrar todo...
Repost from N/a
።ውዶች እንደምን አላችሁ ዛሬ በደረሰን መረጃ መሰረት በአቶ ደመላሽ(አካለወልድ) የሚመራው ቡድን ሻሸመኔ ሚካኤል ላይ እንዳደረገው ሁሉ በዓለምገና ቅ.ሚካኤል ሊሿሿሙ ሀሙስ እንደሚገቡ የተረጋገጠ ሲሆን አሁን አመሻሽ ላይ መንገድ ጠራጊው ሀይላቸው አለም ሆቴል አርፏል ። ይህን አስመልክቶ የሀሙሱን ህገወጥ ተግባር ተመቃወም ከአ.አ ወጣቶች ዝግጅታቸውን አጠናቀው እየተጠባበቁ ነው እነሱ ከዛ ሲመጡ እኛ እጃችን አጣምረን መቀመጥ አይገባንም መረጃውን ለቤተሰብ ለቅድስት ሀዋርያዊት ቤ/ክ ለሚገደው ሁሉ በማሳወቅ በተጠንቀቅ ተዘጋጁ በክርስትና የሚገኝ በረከት በራችን ላይ ቆሟል A.h
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ሰልፉን ለማኮላሸት የተሠራ ሴራ የካቲት 5 የተጠራውን ሰልፍ ለማኮላሸት ሔገ ወጡ ቡድን ከመንግሥት ጋር ተነጋግሮ በተመሳሳይ ቀን ሰልፍ ጠርቷል። በሴራቸው መሠረት ሁለት ሰልፍ ስለተጠራ የጸጥታ ችግር አለ በሚል ምክንያት ክልከላ ይጣላል። ይህ ሕገወጡና መንግሥት የሠሩት ሒሳብ ነው። ይህንን ሰልፍ ከቅዱስ ሲኖዶስ በቀር የማስቀረት መብት ያለው አካል እንደሌለ ወዳጅም ጠላትም ማወቅ አለበት። https://t.me/onesinod
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ምን  አልባት Internet ሊዘጋ ይችላል እየተባለ ነው እና ይቺን ነገር ብናውቃት ጥሩ ነው 🙏 ደውል በተለያየ ሰዓት በቤተክርስቲያን ውስጥ ለአገልግሎት ይደወላል። ነገር ግን ለሁሉም አገልግሎት አንድ ዓይነት ደውል አይደውልም! "በአደጋ ጊዜ ሲደወል ከሌሎቹ የሚለየው ደውሉን ቶሎ ቶሎ በፍጥነት ሲደወል ቤተ ክርስቲያን ላይ ችግር አለ ድረሱልን ማለት ነው።" ቤተክርስቲያን ችግር ከገጠማት "ያለማቋረጥና በደውሎቹ መካከል ያለምንም እረፍት በተከታታይ ትደውላለች።" ይህ ጥሪ ቤተክርስቲያን የተለያየ ድንገተኛ አደጋ ሲገጥማት ነው። ቤተ ክርስቲያን የተለያዩ የደውል አደዋወል አላት ነገር ግን በአደጋ ጊዜ ሲደወል ከሌሎቹ የሚለየው ደውሉን ቶሎ ቶሎ በፍጥነት ሲደወል ቤተ ክርስቲያን ላይ ችግር አለ ድረሱልን ማለት ነው ሼር አድርጉ ለጎደኞቻችሁ በቁምነገር መሃል አውሩት።🙏
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.