cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

✝ቅዱስ ሚካኤል✝

ለመንፈሳዊ ህይወታችን የሚጠቅሙ ስብከቶች ፣የቅዱሳን ገድሎችና መዝሙሮችን እንማማራለን

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
479
Suscriptores
-424 horas
+37 días
+1330 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ስለ ምስጢረ ስላሴ በደንብ ለመረዳት ይጠቅማል በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw: #ነገረ #ክርስቶስ #ምዕራፍ ፫ #ክፍል ፩ የምሥጢረ ሥጋዌ ትምህርት መሠረት ምሥጢረ ሥላሴ ነው። ሥላሴ ማለት "ሦስትነት" ማለት ነው። ቅድስት ሥላሴ ስንል ደግሞ ልዩ ሦስትነት ተብሎ ይተረጎማል። ይኽውም ከፍጡራን ሦስትነት የተለየ ሦስትነት ለማለት ነው። በባሕርይ አንድ የሆነ እግዚአብሔር በአካል ሦስት መሆኑን የምንማማርበት ትምህርት ምሥጢረ ሥላሴ ይባላል። ልዩ ሦስት ያሰኛቸው ነገር ምንድን ነው? #አንደኛ አንዱ አካል በአንዱ አካል ህልው መሆኑ ነው። ይኽውም እኛ ሰዎች ሦስት ብንባል አንዳችን በአንዳችን ላይ አንኖርም። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ግን አንዱ አካል በአንዱ አካል ህልው ሆነው ይኖራሉ። ይህንንም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "እኔ በአብ እንዳለኹ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ ባይኾንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ" ብሎ ገልጾታል (ዮሐ. ፲፬፣፲፩)። ሊቅም "ነአምን ከመ አብ በወልድ ወበመንፈስ ቅዱስ ወወልድ በአብ ወበመንፈስ ቅዱስ ወመንፈስ ቅዱስ በአብ ወወልድ" ብሎ ገልጾታል (ሃይ.አበ.፲፩)። #ሁለተኛ መገነዛዘባቸው ነው። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን ልዩ ሦስት ያሰኛቸው መገነዛዘባቸው ነው። በፍጡራን ዘንድ አንዱ በአንዱ ህልው ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አንዱ አንዱን ገንዘብ አያደርገውም። ለምሳሌ ሦስት አንፖሎችን በአንድ ቤት ውስጥ ብናበራቸው የአንዱ ብርሃን ከአንዱ ብርሃን ህልው ይሆናል። ነገር ግን ብርሃናቱ መገነዛዘብ የላቸውም። የፀሐይ ብርሃን በሕዋ ካለው አየር ጋር በህልውና አንድ ይሆናሉ። ነገር ግን ገንዘብ አይደራረጉም። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ግን በህልውና አንድ መሆን ብቻ ሳይሆን በከዊን መገነዛዘብ አላቸው። የአብ የሆነው ሁሉ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ነው፣ የወልድ የሆነው ሁሉ የአብ የመንፈስ ቅዱስ ነው፣ የመንፈስ ቅዱስ የሆነው ሁሉ የአብ የወልድ ነው። ይኽውም ከግብረ ልደት ውጭ ነው። "ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው" እንዲል (ዮሐ. ፲፮፣፲፭)። ሦስቱ አካላት የሚገነዛዘቡት ደግሞ በከዊናቸው አማካኝነት ነው። የአብ ከዊን ልብነት፣ የወልድ ከዊን ቃልነት፣ የመንፈስ ቅዱስ ከዊን እስትንፋስነት ነው። አብ ልብ ሆኖ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስም ልባቸው ነው። ወልድ ቃል ሆኖ ለአብ ለመንፈስ ቅዱስም ቃላቸው ነው። መንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ ሆኖ ለአብና ለወልድም እስትንፋሳቸው ነው። ስለዚህ ሦስትነታቸው መገነዛዘብ ስላለው ልዩ ሦስትነት ተብሏል። #ሦስተኛ በቅድምና አንድ መሆናቸው:- ወልድና መንፈስ ቅዱስን ከአብ የተገኙ ብንላቸውም መገኘታቸው (ተረክቧቸው) መቀዳደም ሳይኖርበት ነው። ይኽውም አብ ቀድሞ ኖሮ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በኋላ የተገኙ አይደሉም። የፀሐይ ብርሃንና ሙቀት ከፀሐይ ክበብ ሲገኙ ምንም እንኳ ተገኙ ብለን ብንናገርም ቀድሞውንም ከክበቡ እንዳልተለዩና ክበቡ ያለ ብርሃንና ሙቀት ቀድሞ የነበረበት ዘመን እንዳልነበረው ያለ ነው። "ኢሀሎ አብ ግሙራ ዘመነ እምነ አዝማን እንበለ ወልድ ወኢወልድ ዘእንበለ መንፈስ ቅዱስ" እንዲል (ሃይ.አበ. ፷፱)። እንዲሁም "አሐቲ ይእቲ ቅድምናሆሙ ለሥላሴ" ይላል (ሃይ.አበ. ፺፩)። አብርሃም ይስሐቅንና ያዕቆብን ሦስት ብንላቸው በዘመን መቀዳደምም አለባቸው። ያዕቆብ ከይስሐቅ ይስሐቅ ከአብርሃም ተወልደዋል። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን ሦስት ስንል ግን በዘመን መቀዳደም የሌለባቸው ሦስት ስለሆኑ ልዩ ሦስት እንላቸዋለን። #የአብ #የወልድ #የመንፈስ #ቅዱስ #ሦስትነታቸው #በምን #በምን #ነው? ፩ኛ በአካል:- የአብ የራሱ ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው፣ የወልድም የራሱ ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው፣ የመንፈስ ቅዱስም የራሱ ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው። "ነአምን በሠለስቱ አካላት ፍጹማን ወበሠለስቱ ገጻት ፍጹማን ዕሩያነ መልክዕ" እንዲል (ሃይ.አበ. ፻፲)። ሦስቱ አካላት በመልክም በምልዐትም በርቀትም የተካከሉ ናቸው። ሦስቱ አካላትም ስማቸው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ነው (ማቴ. ፳፰፣፲፱)። እነዚህ አካላት እጅ፣ እግር፣ ዓይንና በጠቅላላው በቅዱሳት መጻሕፍት የተጠቀሱ አካላት አሏቸው። ነገር ግን እጃቸው፣ እግራቸው፣ ዓይናቸው እና ሌሎችም አካሎቻቸው ወሰን የሌለባቸውና ከሰው ኅሊና መታሰብ በላይ ናቸው። ሁሉ በሁሉ አሉ። "ወዘይቤሉ መጻሕፍት ከመቦ ለእግዚአብሔር አዕይንት ወአዕዛን ወኵሉ ዘተብህለ እለተርፉ በእንተ እግዚአብሔር ነአምን ከመእሙን ወጽድቅ ውእቱ ወባሕቱ ኢይትረከብ ወኢይትኄለይ" እንዲል (ሃይ.አበ.፲፱)። ፪ኛ በአካላዊ ግብር:- የአብ አካላዊ ግብር መውለድ ማሥረጽ ነው፣ የወልድ አካላዊ ግብር መወለድ ነው፣ የመንፈስ ቅዱስ አካላዊ ግብር መሥረጽ ነው (ሃይ.አበ.፲)። ወልድ ከአብ ስለተወለደ የአብ የባሕርይ ልጅ (ወልደ አብ) ይባላል (ዮሐ. ፲፣፴፮)። መንፈስ ቅዱስም ከአብ ስለሠረጸ ከአብ የሚወጣ ይባላል (ዮሐ.፲፭፣፳፮)። በአካላዊ ግብር ስማቸውም አብ ወላዲ አሥራፂ፣ ወልድ ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስ ሠራፂ ይባላሉ። ፫ኛ በከዊን:- አብ አካላዊ ልብ ነው፣ ወልድ አካላዊ ቃል ነው፣ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ እስትንፋስ ነው። ሦስቱ አካላት በአካል ሲለያዩ የሚገነዛዘቡት ደግሞ በከዊን ነው። ስለዚህ ኵነታት ተገናዝቦ እንጂ እንደ አካላት ተሌልዮ አይነገርላቸውም። የሦስቱ ኵነታት ተገናዝቦ መለኮት ወይም ባሕርይ እየተባለ ይጠራል። "ይትዋሐዱ በመለኮት ወይትሌለዩ በአካላት" እንዲል (ሃይ.አበ.፺፯)። #የአብ #የወልድ #የመንፈስቅዱስ #አንድነታቸውስ #በምንድን #ነው? #አንደኛ በባሕርይ:- ባሕርይ ማለት አካል ያልሆነ ነገር ግን አካላዊ የሆነ አካል የሚገልጠው የአካል መሠረት ማለት ነው። ሦስቱ አካላት በባሕርይ አንድ ናቸው። ባሕርይ ሦስቱን አካላት የሚያገናዝብ ነው። አንድም የሦስቱ አካላት መገናዘብ ባሕርይ ነው። በደንብ መረዳትና ማስተዋል ያለብን ባሕርይ ከሦስቱ አካላት ውጭ የሆነ አራተኛ ማንነት አይደለም። የሦስቱ አካላት በከዊን መገናዘብ ነው እንጂ። ኪራኮስ የተባለ ሊቅ እንደተናገረው አካል ያለ ባሕርይ ባሕርይ ያለ አካል አይገኝም። ይህም ማለት ባሕርይ የሌለው አካል፣ አካል የሌለው ባሕርይ የለም ማለት ነው። "ኢይደሉ ይኩን ህላዌ ዘእንበለ አካል። ወኢይደሉ ይትረከብ አካል ዘእንበለ አምሳሉ ለአካል። ባሕርይ ያለ አካል አካል ያለ ባሕርይ ይገኝ ዘንድ አይገባም" እንዲል (ሃይ.አበ.፺፩፣፳፰)። የሦስቱ አካላት ባሕርይ ደግሞ አንድ ነው። ከባሕርይ የወጣ አካል ደግሞ የለም። #ሁለተኛ በግብረ ባሕርይ አንድ ናቸው። ግብረ ባሕርይ የሚባለው መፍጠርን፣ መግዛትን፣ ንጉሥ መሆንን፣ ዘለዓለማዊነትን፣ ሁሉን ቻይነትን በጠቅላላው አምላካዊ ሥራዎችን ያመለክታል። ማንኛውንም አምላካዊ ሥራ ሦስቱ አካላት ተገናዝበው የሚሠሩት ስለሆነ በአምላካዊ ሥራ ሦስቱ አንድ ናቸው። በግብረ ባሕርይ አብ የሚሠራውን ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይሠሩታል፣ ወልድ የሚሠራውን አብ መንፈስ ቅዱስ ይሠሩታል፣ መንፈስ ቅዱስ የሚሠራውን አብ ወልድ ይሠሩታል። "ወአኮ አብ በርእሱ ባሕቲቱ ዘይገብር ወወልድኒ አኮ በርእሱ ባሕቲቱ ዘይገብር ወመንፈስ ቅዱስኒ አኮ በርእሱ ባሕቲቱ ዘይገብር። ወምግባሮሙኒ አሐዱ እስመ አሐዱ መለኮቶሙ" እንዲል (ሃይ.አበ.፺፩)። በግብረ ባሕርይ ሦስቱ አካላት አንድ ናቸው። በምሥጢረ ሥጋዌ ሥጋን አምላክ በማድረግ፣ በማዋሐድ፣ በማክበር ሦስቱ አንድ ናቸው። ለሥጋ በተለየ አካሉ ክብር መሆን ግን የወልድ ነው። ይኽውም ሰው የሆነው በተለየ አካሉ ወልድ
Mostrar todo...
ስለሆነ ነው። ሥጋም ወልድን ሆነ እንጂ አብን መንፈስ ቅዱስን አልሆነምና ነው። ይህን ትቶ መንፈስ ቅዱስ ለሥጋ ክብር ሆነው ማለት ግን መንፈስ ቅዱስን ሰው ሆነ የሚያሰኝ ትልቅ ክሕደት ነው። ሃይ.አበ. ፻፳፩፣፴፫ "እመቦ ዘይብል በእንተ አሐዱ እግዚአብሔር እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ለሊሁ ከብረ በመንፈስ ቅዱስ ወተሰብሐ ውጉዘ ለይኩን" እንዲል። ይቆየን ምዕራፍ ፫ ክፍል ፪ ይቀጥላል መ/ር በትረማርያም አበባው
Mostrar todo...
👍 1
የማሕሌት ተወዛዋዦች ማሕሌት ማለት ዝማሬ ማለት ነው ፣ ፈልፈለ ማሕሌት ቅዱስ ያሬድ በዚሁ የምስጋና ክፍል ታላቁን ድርሻ ይይዛል ፤ በአንድ ወቅት በንጉሡ አፄ ገብረ መስቀል በትር እግሮቹ ተወግተው ቢደሙም ቅዱሱ ማሕሌቱን በተመስጦ እያለ የእግሮቹ መወጋት አልተሰማውም ነበር ። ዛሬ ለወጉ ማሕሌት አንቀርም ፣ ቸብቸቦ ይጀመራል ፣ ወጣቶች ከበሮውን ለማንሳት ሪከርድ በሚያሻሽል ፍጥነት የከበሮውን ገመድ ከጀርባቸው ያዋሕዱታል (እንዲያው ወጣቶች ስንል በእድሜ ማለታችን አይደለም ቆብ የደፉ መስቀል የጨበጡ ቀጣይ በምናየው መልኩ የሚሳተፉትንም የሚገልጽ ቃል ነው እንጅ ) : አፍታም ሳይቆይ እንደ አሎሎ ወርዋሪ መሽከርከር ይጀመራል : አንድ እጅ ተዘርግቶ እስክስታው ይቀልጣል: ሁለት እግር ከፍ እያለ መዝለል ይጀመራል : አሁን በአንደበት የሚነገረው ስብሐተ እግዚአብሔር ነው መሬት ላይ ደግሞ ኅብረ ብሔራዊ ጭፈራ ሁኗል : ነፍስ ምን እየተካሄደ እንዳለ ዘንግታለች : ስጋ ግን እየተንቀጠቀጠ ነው : የስሜት እሳት ተቀጣጥሏል : እሽሽሽሽሽሽ የሚል ማጀቢያ መሆኑ ነው ከአንደበት አትጠፋም : የሙቀቱ መጠን ከቁጥጥር እየወጣ ነው : ወደ ሴቶች ጉዞ ይጀመራል : አሁን ሴቶች በቅርበት እየተመለከቱ ነው ከበሮው ላይ ብትሩ ይበረታል : የዝላዩ ከፍታ ይጨምራል : ጿጿጿጿጿ የሚል የጽናጽል ድምጽ የሚያሰማ ቢኖርም ፈገግ ተብሎ ታልፎ ጭፈራው ይደራል : ሊቃውንቱ ቢናገሩም የተጠሉ ይሆናሉ : ነፍስ ከተኛች ቆይታለች ከዱካካዋ ልትነቃ አልቻለችም : ከጎን ከበሮ የሚመታው ጓደኛ በመቺው ትዕዛዝ አመታቱን እየቀረጸ ነው : Tik Tok ቀጣዩ የቪዲኦው መሰራጫ መድረክ ነው : የታይታ ክርስትና ! እንደ ፈሪሳውያን ሰው እንዲያይ ብሎ መዘመር ! ተቃራኒ ጾታ እያዩ መስፈንጠር ! በከበሮ ትዳር አይፈለግም ! መዝለል ፣ መሽከርከር ፣ መስፈንጠር፣ መንቀጥቀጥ ፣ እሽሽሽሽሽ ማለት ፣ ወደ ተቃራኒ ጾታ አንጋጦ መዞር ይቁሙ ! ሁለት እጅ ስላለህ እና መምታት ስለቻልክ ብቻ ከበሮ አትሸከም ምስጢሩን ተረዳ ያኔ ሲገባህ ዕንባህ ከዐይንህ ያለማቋረጥ ጉንጮችህን መወረጃ አድርጎ ሲጎርፍ ይታወቅሀል : ያኔ ልብህ እንጅ እግርህ አይዘልም : ያኔ የምትንቀጠቀጠው እግዚአብሔርን በመፍራት ይሆናል: ያኔ ስትዘል አፍአዊ ላብ ሳይሆን ሕሊናህ ይሆናል በተመስጦ የሚያልበው : ያኔ እንደ መላእክት የሰማይ የመቅደሱ በር እስኪከፈት እንዲዘምሩ አንተም የልቦናህ በር ተከፍቶ ለምስጋና ትታትራለህ ። አየኋት : አወቅኳት : ወደድኳት ብሎ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ የመላዕክትን ዝማሬ ሰምቶ መጦ ባቀናት ቤተክርስቲያን ምድራዊ ተወዛዋዦች ገብተናልና ወደ ልቦናችን እንመለስ ። በወንዶች ብቻ የሚቆም ግብር አይደለም በአንስቶችም ተመሳሳይ ፍሬ አፍርቶ ተንዠርቅቆ እናገኘዋለን : በሰንበት ትምህርት ቤት እንዲሁ በአደባባይ በዓላት ቁጥራቸው ትቂት ያልሆኑ በከበሮ ላይ መከራ አጽንተው በመከራ ድር ተተብትበው ይኖራሉ : አንቲ ተቃራኒ ጾታሽ እንዲያይሽ ካልሆነ ምን ያሽከረክርሻል ? ምን ያዘልልሻል ? ወደ እነማን ፊትሽን ዙረሽስ ትመቻለሽ ? ወደፊት ወደ ኋላ ስትይ የክርስቶስን መገፋት ታስቢያለሽ ወይስ ወደፊት ሄደሽ ልብሽ የወደደውን ትፈቅጃለሽ ? ከንቱ ውዳሴን ሽተሽ በሰፈሩ የከበሮ አመታትሽ እንዲወራ ከሆነ እኅቴ ሆይ የገሀነም ደጃፍ ላይ ነሽና ሳትገቢ ተመለሽ! በአደባባይ ምድርን የሚያበራ እሳት ከማቀጣጠል በሕሊና መቅረዝ ትቂት መንፈሳዊ ማኅቶት ማብራት ይሻላል ! በእውነት እናስተውል ! እነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እኮ በዝማሬያቸው ሕሙም ይፈውሱ ነበር በእኛስ? ዘመርን ብለን እራሳችን ሕሙም ሆነን እንመለሳለን ! ወደ እነእንተና ለይቶልን በኅብረ ብሔራዊ ጭፈራ እግዚአብሔር ቢመለክ ምን ችግር አለው ብለን የኅብረት ዘፋኞች ከመሆናችን በፊት ለብው ! አምላከ ያሬድ ወዳዊት ወእዝራ የቀናውን መንፈስ ያድለን ! የቅዱሳኑ ዝማሬ ወላዲተ ቃል ድንግል ማርያም በረድኤት አትለየን። ✍በትረሙሴ ዘደብረ ኀንታ ከሌላ ቻናል የተላከ https://t.me/kidus_mikael_12
Mostrar todo...
👍 3
*ምክረ አጋንንት* በቅዱስ አቡነ ዮሴፍ ዘላስታ 📌ልጹም ትላለህ ፤ ተው አትጹም ይልሃል!አንተም ትተወዋለህ። 📌ልመጽውት ትላለህ ፤ ተው አትመጽውት ይልሃል። አንተም ትተወዋለህ። 📌ንስሐ ልግባ ትላለህ ፤ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ያለንስሐ ትሞታለህ። 📌ልቁረብ ትላለህ ፤ ገና ነህ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ሳትቆርብ ትሞታለህ 📌ላስቀድስ ትላለህ ፤ ትንሽ ተኛ ይልሃል። አንተም ሳትሄድ ታረፍዳለህ። 📌ጸበል ልግባ ትላለህ ፤ ጤነኛ ነህ ይልሃል። 📌ገዳም ልባረክ ልሂድ ትላለህ ፤ ተው ስራን ስራ ይልሃል፡፡ አንተም ሳትሄድ ስትቆጭ ትኖራለህ። 📌አስራት በኩራት ልስጥ ትላለህ ፤ ተው አትስጥ የለህም ይልሃል። አንተም ትተወዋለህ። 📌በአንድ ልወሰን ትላለህ ፤ ተው ቆንጆዎቹ ያልፉሃል ይልሃል። አንተም በዝሙት ትወድቃለህ። በመጨረሻም የተወሰነልህ ግዜ ያልቃል  ነፍስህን አጋንንት እንደ ኳስ እየተቀባበሉ ይወስዷታል።😢 📌ልጠጣ ስትል ፤ ጠጣ ይልሃል። ያሰክርሃል። 📌 ልዝፈን ስትል ፤ዝፈን ይልሃል። ያስጨፍርሃል 📌ልስረቅ ስትል ስረቅ ይልሃል። ያሰርቅሃል! 📌 ልጣለው ስትል ተጣላ ይልሃል። ያጣላሃል። 📌ልዋሽ ስትል ዋሽ ይልሃል። ያስዋሽሃል! ስጋዊ ተድላን ይሰጥሃል። ይመችሃል፡ስጋህ ወፍሮ፣ ቀልቶ ፣ ወዝቶ በጓደኞችህ ‹ ተመቸህ እኮ ! › ያስብልሃል። አንተም ደስ ይልሃል! በዛው ትገፋበታለህ። ሃሳብህ ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ቀርቶ ወደ ጅምናዝየም ቤት መሔድ ይሆናል። 📌ሃሳብህ ሁሉ የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ ይሆናል። ሃሳብህ ሁሉ ሳውና ባዝ ፣ስቲም ቤት ፣ማሳጅ ቤት ሂደህ መታሸት እና መዝናናት ይሆናል። እግርህ ሁሉ ወደ ሲኒማ ቤት ፣ ወደ ናይት ክለብ ቤት ፣ ወደ ሆቴል ቤት ፣ ወደ ግሮሰሪ ቤት ፣ ወደ ሱፐር ማርኬት ፣ ወደ ምናምን ቦታ ይሆናል።😭😭😭 በእነዚህ ሁሉ ስጋህ ሲመቸው ቁሞ መጸለይ ይደክምሃል። መስገድ ያቅትሃል። መጾም ይከብድሃል። ቤተክርስቲያን ለመሄድ ይጨልምሃል። ስጋህ በአጋንንት መረብ ይጠመዳል። ደም ብዝት አስይዞ ሴት ያዝልሃል። ደም ብዛት አሲይዞሽ ወንድ ያዝልሻል። የነርቭ በሽታ አስይዞ መቆምና መሄድ ያስቅትሃል። ስኳር በሽታ አሲይዞ ከጾም ይከለክልሃል። ጨጓራ በሽታ አስይዞ ጾምን ይከለክልሃል። ❗️ምላስህ እግዚአብሔርን ማመስገንን ሳይሆን ዘወትር ስለ በሽታህ እንድትዘምር ያደርጋታል። ❗️በጣም ብዙዎች ሃብት ሞልቷቸው በሽተኛ ያደርጋቸዋል። ገና ከጥዋቱ እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትለው ቢሄዶ ኖሮ ፤ እንደ አብርሃም ፣እንደ ይስሐቅ እና እንደ ያዕቆብ በምድር ሃብታም እንደ ሆኑ ሁሉ በሰማይም እንደ ቅዱሳኑ የገነት ባለቤት በሆኑ ነበር። 📌 ሰይጣን ክፉ ነው! ሃብታሙን በሽተኛ ፣ ድሃውን ደግሞ ጤነኛ አድርጎ አምላክን ወቃሽ ያደርገዋል። እንዲህ እንዲህ እያለ የመሰናበቻ ጊዜ ይደርሳል። በኃጢአት የዳበረው ስጋችን አፈር ነውና በቅጽበት እሬሳ ተብሎ ወደ አፈር ይገባል። ነፍስ ግን እያዘነችና እየተፀፀተች ወደ ሲዖል ትወረወራለች። 📌የምናያቸው ቆንጆ ሴቶች ፣ የምናያቸው ቆንጆ ወንዶች ፣ የምናየው የልኳንዳ ስጋ ፣የምናየው መጠጥና ምግብ ሁሉ ያምረናል። ስጋችን ያሸንፈናል፥ ነፍሳችን ትሸነፋለች። ለገነት ተፈጥረን ለሲዖል እንሆናለን።ሁላችንም ወደ እግዚያብሔር ተመልሰን ንሰሀ እንግባ። "...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው" --2ኛ ቆሮ 6፥2
Mostrar todo...
✝ቅዱስ ሚካኤል✝

ለመንፈሳዊ ህይወታችን የሚጠቅሙ ስብከቶች ፣የቅዱሳን ገድሎችና መዝሙሮችን እንማማራለን

👍 3🙏 1
አንተ ሰውን አትጥላ እንጂ ሰው ይጠላኛል ብለኽ አትጨነቅ።  አንተ ብቻ ሰውን ውደድ እንጂ ሰው አይወደኝም ብለኽ አታስብ። ሰዎች ስለ እኛ በጎ እንዲያስቡ በመጣር መድከም አያስፈልግም። "ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፥ እርሱም፦ ጋኔን አለበት አሉት። የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፥ እርሱም፦ እነሆ፥ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ ይሉታል" ማቴ.11:18
Mostrar todo...
🙏 4
እስኪ ንገሩኝ! ከእናንተ መካከል ከመዝሙረ ዳዊት ውስጥ አንዲትዋን ምዕራፍ ወይም ከሌላው የቅዱሳት መጻህፍት ክፍል ውስጥ ጥቂት በቃልህ ድገም ቢባል ይህን ማድረግ የሚችል ማን ነው? አንድ ሰውስ እንኳ አይገኝም። የሚያሳዝነው ነገር ግን ይኼ ብቻ አይደለም። ከመንፈሳዊ ነገሮች አንፃር እንደዚህ አእምሮ የጎደላችሁ ኾናችሁ ሳለ ዲያቢሎሳዊ በኾኑ ነገሮች ላይ ግን ከእሳት በላይ ኀያላን ናችሁ። እንዲህም በመኾናችሁ አንድ ሰው መጥቶ ዲያቢሎሳዊ ዘፈኖችንና የዝሙት ዜማዎችን ንገሩኝ ቢላችሁ ከእናንተ መካከል እነዚህን የሚያውቁና ደስ ተሰኝተው የሚደግሟቸው ብዙ ሰዎችን ያገኛል። ነገር ግን"ለምንድን ነው እንደዚህ የምትኾኑት?" ተብላችሁ ስትጠየቁ የምትመልሱትስ መልስ ምን የሚል ነው? "እኔ ከመነኮሳት አንዱ አይደለሁም። ሚስት አለቺኝ፣ልጆችም አሉኝ፣የቤተሰብ መሪ ነኝ" የሚል ምክንያት ታቀርባላችሁ። ለምን እንደዚህ ትላላችሁ? ከመነኮሳቱ ይልቅ ይበልጥ ማንበብ ያለባችሁ እናንተ ኾናችሁ ሳለ ብዙዎች እንዲጠፉ ያደረገው "ቅዱሳት መፃህፍትን ማንበብ ለመነኮሳት ብቻ ነው" የሚለው አመለካከታችሁ ነው። ይበልጥ ብዙ መድኃኒት የሚያስፈልጋቸው በማእከለ ዓለም የሚኖሩትና ዕለት ዕለትም መንፈሳዊ ቁስል የሚያገኛቸው ሰዎች ናቸውና። ስለዚህም ከለማንበባችሁም በላይ" የእኛ ማንበብ ትረፍ ነገር ነው" ብላችሁ ማሰባችሁ በራሱ የዲያብሎስ አሳብ ነው። ወይስ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ "ዝንቱ ኵሉ ተጽሕፈ ለተግሣጸ ዚአነ - ይህም ኹሉ እኛን ሊገስጸን ተፃፈ"(1ኛ ቆሮ 10:11) ያለውን አላዳመጣችሁምን? ቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ
Mostrar todo...
"ማንኛውም የመዳን ምክንያት ምንጩ የጌታ አዳኝነት ነው።ሰው በእምነቱና በሥራው መዳንን ቢያገኝ እምነቱና መልካም ሥራው አዳኝ ሊሆኑለት የቻሉት በቅድሚያ ጌታ ስላዳነው እንጂ ሰው በገዛ ራሱ ችሎታ መዳን የሚችል ሆኖ አይደለም።የቅዱሳን ማዳንም ሆነ የምሥጢራተ ቤተክርስቲያን አዳኝነት ከአንድ ከእግዚአብሔር አዳኝነት የተገኘ የእርሱ የማዳን ውጤት እንጂ የእርሱን አዳኝነት የሚተኩ ወይም የሚተካከሉ አይደሉም።" ዳዊት አብርሃም (ዕቅበተ እምነት በእንተ ነገረ ድኅነት ገጽ 58 ) "ለመዳናችን ማመናችን የሚኖረውን ዋጋ መልካም ሥራ አይተካውም እንዲሁም መልካም ሥራ ለመዳናችን አስፈላጊ መሆኑ የእምነትን አስፈላጊነት አይሽረውም።" (ዳዊት አብርሃም ፣ ዕቅበተ እምነት በእንተ ነገረ ድኅነት) ይሄው ነው እንግዲህ የቤተክርስቲያን ትምህርት!!!
Mostrar todo...
ምን ያሆሎቻችን ነን ሕይወተ ወራዙት ወይም የወጣቶች ሕይወት ከሚለው መፅሐፍ ላይ ተወስዶ በክፍል የሚቀርበውን ፅሁፍ የምናነበውAnonymous voting
  • ሀ, እኔ ሙሉ ሙሉ ክፍሉን እየተከታተልኩ አነባለሁ
  • ለ, ለማንበብ ፅሁፉ በጣም ይረዝምብኛል
  • ሐ, ለማንበብ ከጊዜ አንፃር አይመቸኝም
  • መ, መፅሐፉን አንብቤዋለሁ
0 votes
ምን ያሆሎቻችን ነን ሕይወተ ወራዙት ወይም የወጣቶች ሕይወት ከሚለው መፅሐፍ ላይ ተወስዶ በክፍል የሚቀርበውን ፅሁፍ የምናነበውAnonymous voting
  • ሀ, እኔ ሙሉ ሙሉ ክፍሉን እየተከታተልኩ አነባለሁ
  • ለ, ለማንበብ ፅሁፉ በጣም ይረዝምብኛል
  • ሐ, ለማንበብ ከጊዜ አንፃር አይመቸኝም
  • መ, መፅሐፉን አንብቤዋለሁ
0 votes
   ከዚህ በኋላ ውስጥ ለውስጥ ያረካት የነበረው ውኃ ዝናብ ሆኖ እየመጣ ምድርን ከውጭ ያጨቀያት ጀመር፡፡ ምድር ለሔዋን ምሳሌ ናት ሰው ምድር ይባላልና፡፡ «እስመ አንተ ምድር፣ ዘምድረ ሰብሰ» የሚሉት መጽሐፍ ቅዱሳዊና መንፈሳዊ ጥቅሶች ሰው ምድር ለመባል ምስክሮች ናቸው፡፡ ዝናብ ደግሞ የወር አበባ ምሳሌ ነው:: ከውስጥ ለውስጥ ይሄድ የነበረው ውኃ ከጊዜ በኋላ በውጭ ተገልጦ ምድርን ማጨቅየቱ በሔዋን ባሕርይ የነበረ ደም ከጊዜ በኋላ በአፍአ መታየት መጀመሩን ያስረዳል::     በዚህ ምስጢር መሠረት ሔዋን የወር አበባ ማየት የጀመረችው ከገነት ውጭ ነው፡፡ ጊዜውም አዳምና ሔዋን የፈጣሪን ትዕዛዝ ተላልፈው ከገነት ከተባረሩ በኋላ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በወር አበባ ወቅት የሚያጋጥም የሕመም ስሜት     ለዐቅመ ሔዋን የደረሰች ሴት ደመ ፅጌ በምታይባቸው ዕለታት የጡንቻና የአጥንት መልፈስፈስ (ድካም) ያጋጥማታል:: በተጨማሪም የጀርባ ወይም የወገብ ሕመም ሆድ ቁርጠት፣ የምግብ መንሸራሸር ችግርና የምግብ ፍላጐት ማጣት ለመሳሰሉት የሕመም ስሜቶች ስለምትጋለጥ በአመጋገብና በቂ ዕረፍት በማግኘት ረገድ ምቾት ያስፈልጋታል፡፡     በቂ ዕረፍት ማለት ተኝቶ መዋል ማለት አይደለም፡፡ በወር አበባ ወቅት የሚኖረውን የሕመም ስሜት ለመቀነስ በቂ ዕረፍት ማግኘት እንደተጠበቀ ሆኖ ቀልጣፋ የተግባርና የእንቅስቃሴ ሰው ሆኖ መገኘት እንደሚያስፈልግ ባለሙያዎች ይስማሙበታል፡፡     ከሚኖረው የሕመም ስሜት በተጨማሪ ትዝብት ላይ እስከ መውደቅ የሚያደርስ መቅበጥበጥና አንዳንድ ጊዜም የመደበር (መደበትና) በሆነው ባልሆነው በቀላሉ የመከፋት ሁኔታ ሊንጸባረቅ ይችላል፡፡      ከላይ የተጠቀሱትን የሕመም ስሜቶችንና በጠባይ ላይ የሚከሰቱትን ለውጦች መረዳት በወር አበባ ላይ የሚገኙትን ሴቶች በሚገባ ለመንከባከብ ይረዳል:: በዚህ ወቅት የሚገኙ ሴቶችን መንከባከብ እንደሚገባ ከቀደሙት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪኮች መረዳት ይቻላል::     ላባ የተባለ ሰው የጠፋበትን ዕቃ በሚፈልግበት ጊዜ በወር አበባ ላይ ትገኝ የነበረችውን ልጁን ራሔልን ከተቀመጠችበት ቦታ ላለማስነሣት የተቀመጠችበትን ስፍራ ከመበርበር ተቆጥቧል፡፡ በምን አውቆ ቢባል እርሷም አባትዋን «በፊትህ ለመቆም ስላልቻልኩ አትቆጣብኝ በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ ደርሶብኛል» አለችው ስለሚል ከዚህ የይቅር በለኝ ቃሏ ያለችበትን ሁኔታ ለመገንዘብ ችሎ ነበር፡፡ ዘፍ 31፥35 ይህ የላባ ታሪክ በወር አበባ ላይ ለሚገኙ ሴቶች ሌሎች ሰዎች ሁሉ ማድረግ ያለባቸውን እንክብካቤ በግልጽ ያስረዳል፡፡ በቀጣይ ምዕራፍ ሰባት ክፍል ሁለት <<የወር አበባ «ርኩሰት» ነውን?>> በሚል ይቀጥላል... https://t.me/kidus_mikael_12 https://t.me/kidus_mikael_12
Mostrar todo...
✝ቅዱስ ሚካኤል✝

ለመንፈሳዊ ህይወታችን የሚጠቅሙ ስብከቶች ፣የቅዱሳን ገድሎችና መዝሙሮችን እንማማራለን

👍 1