cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Zemedkun Bekele(ዘመዴ)ነጭ ነጯን

ትክክለኛ መረጃን በማቀበል ፍቅርን እንስበክ👇 @share @join በማድረግ የመረጃ ቻናላችንን እድገት እናፍጥን 👇👇👇👇 @zemda_offical @zemda_offical

Mostrar más
Etiopía4 576Amárico4 060La categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
1 731
Suscriptores
Sin datos24 horas
+167 días
+26930 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ሰበር ዜና በአዋበል ወረዳ ሉማሜ ከተማ በቅርብ ጌዜ ''የአዋበል መብረቅ ፍኖ ''ተብሎ የተሰየመው አማራ ህዝባዊ ሀይል ከሁለት ቀን በፊት 11ሰአት ገደማ  ሬሽን ጭኖ ከደብረ ማርቆስ አካባቢ የተነሳውን  አጃቢ አንድ ሴኖ ትራክ ወታደር ወደ አመድነት ቀይረውታል።የቀረው ደግሞ እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጧል። ድል ለአማራ ፍኖ
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ  በተከሰተው የትራፊክ አደጋ የ 9 ሰዉ ህይወት አለፈ! በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ በቆንጋ ቀበሌ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ12 ሰዎች ደግሞ ከባድ አደጋ  ደርሷል፡፡ ከዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ እንደተገኘው መረጃ ከሆነ፤ አደጋው የደረሰው  መነሻውን ያቤሎ አድርጎ ወደ ሻሸመኔ ሲጓዝ የነበረው መኪና በመገልበጡ እንደሆነ  የይርጋጨፌ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ታምራት ምትኩ የገለፁት። በተከሰተው የመኪና አደጋ የ9 ሰዎች  ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን የገለፁት ኢንስፔክተር ታምራት ከሞት በተጨማሪ 12 ከባድና 19 ቀላል አደጋ ማስከተሉን ነዉ የገለፁት። የአደጋ መንስኤ በማጣራት ሂደት ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ኢንስፔክተር ታምራት ምትኩ በአደጋ ምክንያት ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በዲላ ሪፈራል አጠቃላይ  ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
Mostrar todo...
የቤተክርስቲያኒቱ የይቅርታ ጥያቄ የዘገየ ነው ሲሉ በትግራይ አባቶች ወቀሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትግራይ ውስጥ ከተካሄደው ጦርነት ጋር በተያያዘ የሚጠበቅብኝን ባለመወጣቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ” ያለችው የይቅርታ ጥያቄ የዘገየ ነው ሲሉ የትግራይ አባቶች ተናግረዋል፡፡ የሽረ እንደ ሥላሴ አገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ እና በቅርቡ “በመንበረ ሰላማ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን” በማለት ራሳቸውን የሰየሙ የሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት ንቡረእድ ተስፋይ ተወልደ “ይቅርታ ጥሩ ቢሆንም የዘገየ ነው” በማለት ለቢቢሲ ትግርኛ ተናግረዋል። ለኹለት ዓመታት በትግራይ ውስጥ በተካሄደው ጦርነት ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጦርነቱን በመደገፍና በትግራይ በደረሱ ጥፋቶች ዝምታን መርጣለች ሲሉም አክለዋል፡፡ “ይቅርታው የፈሰሰውን ደም አይተካውም፣ የደረሰውን ጉዳት እና የመብት ጥሰት አይመልሰውም፣ የፈሰሰውን እንባም አያብሰውም በማለትም ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ "በትግራይ የተደረገውን ጦርነት ቤተክርስቲያኗ በገንዘብ በሞራል እንዲሁም አባቶች አሰስከ ድንበር ጭምር በመሄድ በጦርነት ቅስቀሳ ውስጥ ተሳታፊ ነበሩ።" ሲሉም ተናግረዋል፡፡ አክለውም በትግራይ የምትገኘው ቤተክርስቲያን ያለ መሪ፣ ያለ በጀት ለሦስት ዓመት ተዘንግታ እንደቆየች በማንሳት፤ “አሁን ሕዝባችንን ማገልገል የእኛ ፋንታ ነው ብለን ተነስተናል፣ ይቅርታው የመጣው ይህን ጊዜ ነው” ብለዋል። በግለሰብ አባቶች የተደረገ ነገር ቤተክርስቲያኒቱን እንዴት ሊወክል ይችላል ተብለው የተጠየቁት ንቡረእድ ተስፋይ፤ “ጳጳሳቱ የሲኖዶስ አባላት ናቸው በማለት ከተናገሩ በኋላ፣ አስተያየታቸው እኛን አይወክልም ብላ ቤተክርስቲያኗ መግለጫ አልሰጠችም” ሲሉ አስረድተዋል፡፡ መንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ወደፊት የራሱን ፓትሪያርክ ይመርጥ የሆን ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ፤ “ይህን መቼም አናደርገውም ሐሳቡም የለም፣ ፓትሪያርካችን ቅዱስነታቸው አቡነ ማቲያስ ናቸው” ሲሉ መልሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትግራይ ውስጥ ከተካሄደው ጦርነት ጋር በተያያዘ የሚጠበቅብኝን ባለመወጣቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ በማለት መግለጫ ማውጣቷ የሚታወስ ሲሆን፤ በትግራይ በቅርቡ “በመንበረ ሰላማ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን” በማለት “የራሳችንን መንበር አቋቁመናል” ማለታቸው ይታወቃል፡፡ በሰሜኑ ጦርነት  ምክንያት ቅራኔ ውስጥ የገቡት ኹለቱ የቤተክርስቲያን አካላት፣ የተፈጠረውን ክፍተት በንግግርና በይቅርታ እንዲፈቱ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡  ይህንኑ ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የሚመራ የልዑካን ቡድን ሐምሌ 3/2015 በወደ ክልል ትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ ይጓዛል። ልዑካን ቡድኑ ወደ መቐለ የሚጓዘው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ መሰረት ለትግራይ ክልል እንዲሰጥ የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስና በትግራይ ከሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በሰላም ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር መሆኑ ተገልጿል። @zemda_offical @zemda_offical
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
በክልሎች ከዛሬ ጀምሮ ነዳጅ በኤሌክትሮኒክ ግብይት እንደሚፈፀም የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ገለፀ!! በክልሎች ከዛሬ ግንቦት አንድ ጀምሮ ነዳጅ በኤሌክትሮኒክ ግብይት እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል። በአዲስ አበባ ከተማ ከሚያዝያ 16 ቀን 2015 ጀምሮ ነዳጅ በኤሌክትሮኒክ ግብይት እንዲፈፀም በማድረግ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች  በሌሎች ክልሎች እንዳይከሰቱ  የሚመለከታቸው አካላት ዝግጅት እንዲያደርጉ መደረጉን በባለስልጣኑ የነዳጅ ስርጭት ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር   አቶ ዴሬሳ ኮቱ በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር ገልጸዋል። በአዲስ አበባ ነዳጅን በኤሌክትሮኒክ መገበያየት ሲጀመር የነበረው ሰልፍ አሁን መስተካከሉንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። የነዳጅ እጥረት ማጋጠም፣ የመተግበሪያ አጠቃቀም እውቀት ማነስ ፣ ነዳጅን በኤሌክትሮኒክ የግብይት ስርዓት የመግዛት ፍላጎት ማጣት   አሁንም ያልተቀረፉ ችግሮች እንደሆኑም አቶ ዴሬሳ ጠቁመዋል። ነዳጅ በሁሉም ማደያዎች እንዲኖር የነዳጅ አቅራቢ ድርጅትም ከክልሎች ጋር ተቀናጅቶ ያለውን ችግር ለመፍታት እንደተዘጋጁም ተጠቁሟል። በአዲስ አበባ ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት መነሻ በማድረግ የነዳጅ ግብይቱ በኤሌክትሮኒክ ግብይት የተለያዩ አማራጮች እና በኩፖን ጭምር እንደሚከናወን  አቶ ዴሬሳ ገልጸዋል። በክልሎች ግን በኩፖን እና በካርድ የነዳጅ ግብይት እንደማይከናወን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። ከኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይቱ ጋር በተያያዘ በክልሎች ከኔትወርክ ጋር ለሚስተዋሉ ችግሮች ከወዲሁ ጊዜያዊ መፍትሄ እንዲሰጥ ለኢትዮ-ቴሌኮም ጥያቄ  ማቅረቡን የነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን አስታውቋል ።  
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ኦነግ ሸኔ በምዕራብ እና በምስራቅ ሸዋ ዞን የመንግሥት ጦር ሰራዊት ጥቃት ከፍቶብኛል አለ እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራውና በመንግሥት "ኦነግ ሸኔ" ተብሎ በሚጠራው ቡድን ከትላንት ሚያዚያ 30/2015 ማለዳ ጀምሮ በመንግሥት ጦር አዲስ ጥቃት ተከፍቶብኛል ሲል በቡድኑ ቃል አቀባይ በኩል አስታውቋል። የቡድኑ ቃል አቀባይ አዳ ታርቢ በቲውተር ገፃቸው እንዳሰፈሩት፤ የመንግሥት ጦር በምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ እና በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ በኩል ጥቃት ተከፍቶብናል ብለዋል። በመንግሥት እና በኦነግ ሸኔ መካከል ለዘጠኝ ቀናት ያህል በታንዛኒያ የተካሄደው የሰላም ውይይት ባለመግባባት መጠናቀቁን አዲስ ማለዳ ከዚህ ቀደም መዘገቧ ይታወሳል። ትላንት ተከፈተ ስለተባለው ጥቃት ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከመንግሥት በኩል ምንም የተባለ ነገር የለም።(አዲስማለዳ)  
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
አቶ ልደቱ አያሌው ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ እጃቸውን እንደሚሰጡ አስታወቁ !! መንግስት ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለማናጋት ሙከራ አድርገዋል በሚል በሽብርተኛነት ከወነጀላቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆኑት አንጋፋው ፖለቲከኛ የተከሰሱበትን ክስ በአደባባይ ለመሞገት መወሰናቸው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡ በፅሁፋቸውም ‹‹ከአገዛዙ አፈና ፣ እስርና ግድያ ሸሽቶ በማምለጥ የሚመጣ መፍትሄ የለም። ትግላችን ሰላማዊና ህጋዊ እስከሆነ ድረስ በገፍ እየታሰርንና እየሞትን አገዛዙ በሀይልና በአፈና ሊያሸንፈን እንደማይችል ተስፋ ልናስቆርጠው ይገባል። በዚህ መጠን ዋጋ ለመክፈል ካልቆረጥን በስተቀር የአገርና የህዝብ ህልውና ከጥፋት ሊድን አይችልምና። ›› ያሉ ሲሆን ‹‹ይህንን በለጋ የልጅነት ዘመኔ ለራሴ የገባሁትን የትግል ቃል-ኪዳንና የምታመንለትን የሰላማዊነትና ህጋዊነት መርህ መሰረት በማድረግ ወደ አገሬ ለመመለስና የዶ/ር ዐቢይን የፈጠራ የአሸባሪነት ክስ እንደተለመደው በፍትህ አደባባይ ለመጋፈጥ ወስኛለሁ። ›› ማለታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አስታውቀዋል፡፡ ‹‹ስለሆነም በታሰርኩ ቁጥር ከእኔ በላይ ስቃዬን የምትሰቃዩ ቤተ-ዘመዶቸ፣ ጓደኞቸ፣ የሃሳብ ደጋፊዎቸና የትግል አጋሮቸ ይህንን ውሳኔዬን የሞኝነት፣ የአጉል ጀብደኝነት ወይም የመንግስትን የጭካኔ ደረጃ በአግባቡ ያለመረዳት ድክመት አድርጋችሁ እንዳታዩብኝና ያልተገባ ጫና እንዳትፈጥሩብኝ በዚህ አጋጣሚ በአክብሮት እማፀናለሁ። ይህንን ውሳኔ በሚገባ አስቤበትና ከልቤ አምኘበት የወሰንኩት ስለሆነ በሞራል ልታግዙኝ ይገባል እንጂ ልታዝኑልኝም ሆነ ልታዝኑብኝ አይገባም እላለሁ። " ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡    ---ETHIO-MEREJA---    T.me/ethio_mereja
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ላገኙ አራት የኮሌጁ ፕሮፌሰሮች ዕውቅና ሰጠ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት በቅርቡ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሰጣቸው የኮሌጁ ፕሮፌሰሮች በሕይወት ዘመናቸው በአካዳሚክ፣ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በዛሬው ዕለት ዕውቅና ሰጥቷል፡፡ በኮሌጁ ዕውቅና የተሰጣቸው ፕሮፌሰር አበራ ቁሜ፣ ፕሮፌሰር ምትኬ ሞላ፣ ፕሮፌሰር ግርማ ስዩም እና ፕሮፌሰር የወርቅአበባ አበበ ሲሆኑ፣ የአካዳሚክ፣ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ተሞክሯቸው ለኮሌጁ ማሕበረሰብ አካፍለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አንዱአለም ደነቀ ለፕሮፌሰሮቹ የተዘጋጀላቸውን የዕውቅና ሰርተፍኬት ከሰጡ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ‹‹የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በአገራችን በርካታ ፕሮፌሰሮችን በማፍራት ረገድ ቀዳሚ ነው፡፡›› ብለዋ ዛሬ ዕውቅና የተሰጣቸው ፕሮፌሰሮችም ለኮሌጁ እና ለአገር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ጠቁመው፣ በቀጣይም ይህንኑ አበርክቷቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አደራ ማለታቸውን ከኮሌጁ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
Mostrar todo...
በአፋር ክልል የብልፅግና ፓርቲ የወረዳ አመራር ተገደሉ ከአዳማ ወደ አዋሽ በሚወስደው መንገድ ላይ ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ሚያዚያ 28/2015 በተከፈተ ተኩስ በአፋር ክልል በገቢ ረሱ የሓንሩካ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ጽ/ቤት ኃላፊ ኡመር ለማ መገደላቸውን የአፋር ክልል የብፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት አሳውቋል። ኡመር "አሸባሪዎች በከፈቱት ተኩስ" ሕይወታቸውን ማጣታቸውን የገለጸው ጽሕፈት ቤቱ፤ በኃላፊው ድንገተኛ ሞት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል። ጽሕፈት ቤቱ ስለጥቃት አድራሾቹ ማንነት፣ ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት በሌሎች ላይ ጉዳት ስለመድረሱና ስለተወሰደው እርምጃ በዝርዝር የገለጸው ነገር የለም።   
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ሩሲያና አሜሪካ ወደ ቀጥታ ጦርነት ለመግት ከጫፍ ደርሰዋል ተባለ! ሩሲያና አሜሪካ ወደ ቀጥታ ጦርነት ለመግባት ከጫፍ መድረሳቸውን በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ሰርጌይ ራይባኮቭ አስታወቁ።› ፑቲንን ለመግደል አልሟል ከተባለው ጥቃት ጀርባ አሜሪካ አለች ሲል የሩሲያው ክሬምሊን ቤት መንግስት ከሷል። ይህንን ተከትሎም አሜሪካ እና ሩሲያ ቃታ ስበው እርስ በእርሳቸው ለመታኮስ ከጫፍ መድረሳቸውን ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ሰርጌይ ራይባኮቭ የተናገሩት። “አሁን ላይ ከአሜሪካ ጋር ወደ ቀጥታ ጦርነት ለመግበጣ ጫፍ ላይ ነን” ያሉት ሚኒስትር ደኤታው፤ “ከአሜሪካ ጋር ያለን ግንኙነት ወደ ወታደራዊ ግጭት እንዳይገባ የሚቻለንን ሁሉ እየሰራ ነው” ሲሉም ተናግረዋል። ሰርጌይ ራይባኮቭ አክለውም በሁለቱ ሀገራት መካከል አሁን ላይ ትክክለኛ ዲፕሎማሲ የለም ያሉ ሲሆን፤ ምክንያቱ ደግሞ አሜሪካ ጦርነቱን የማባባስ ስራ ላይ ስለተጠመደች ነው ሲሉም አስታውቀዋል። አሜሪካ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገች ባለው ጦርነት ላይ በቀጥታ እየተሳተፈች ነው ያሉ ሲሆን፤ በሀገራን ላይ ሁሉን አቀፍ ጦርነት ለመቀስቀስ እየሰራች ነው ሲሉም ከሰዋል።በክሬምሊን ቤተ መንግስት ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ሩሲያ፥ ዩክሬ በቀጥታ ጥቃቱን እንደፈጸመች እንዲሁም አሜሪካ ደግሞ ከጥቃቱ ጀርባ አለች ስትል መክሰሷ ይታወሳል። ዩክሬንም ይሁን አሜሪካ በክሬምሊን ቤተ መንግስት ጥቃት ላይ እጃቸው አለበት መባሉን ባወጡት ግለጫ ውድቅ አድርገዋል።ይህንን ተከትሎ ክሬምሊን ቤት መንግስት ባወጣው መግለጫ፤ አሜሪካና ዩክሬን በክሬምሊን ላይ የተፈጸመውን የድሮን ጥቃት ውድቅ ማድረጋቸው "አስቂኝ ነው" ብሏል።  
Mostrar todo...
መረጃ‼️ ኢጋድ የኢትዮጵያ መንግሥትና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ተወካዮች ታንዛኒያ ዛንዚባር ውስጥ ንግግር መጀመራቸውን መግለጡን ሮይተርስ ዘግቧል። ኢጋድ የኹለቱ ወገኖች ንግግር ወደ ፖለቲካዊ ስምምነት ያመራል ብሎ እንደሚጠብቅ ቃል አቀባዩ ኑር መሐመድ ሼክ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ሮይተርስ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትን ወክሎ የሚደራደረውን ቡድን የሚመሩት የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የብሄራዊ ደኅንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን መኾናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች ሰምቻለሁ ብሏል።
Mostrar todo...