cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

እስልምና ወይንስ ክርስትና

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
243
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የሚያጅበት በኢሳይያስ 9፥6 ላይ ከማሶሬት በተቃራኒው ከ 330–360 ድኅረ ልደት በክርስቲያኖች እጅ በተዘጋጀው በኮዴክስ ሲናቲከስ ኮድ በፊደል S በቁጥር 01ውስጥ የግሪክ ሰፕቱአጀንት ቅጂ፦ "የታላቁ ጉባኤ መልአክ" ይለዋል፦ ኢሳይያስ 9፥6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፦ "የታላቁ ጉባኤ መልአክ" ይባላል፥ በአለቆች ላይ ሰላምን እና በእርሱ ላይ ጤናን አመጣለው። ὅτι παιδίον ἐγεννήθη ἡμῖν, υἱὸς ἐδόθη ἡμῖν, οὗ ἡ ἀρχὴ ἐγενήθη ἐπὶ τοῦ ὤμου αὐτοῦ, καὶ καλεῖται τὸ ὄνομα αὐτοῦ Μεγάλης βουλῆς ἄγγελος· ἄξω γὰρ εἰρήνην ἐπὶ τοὺς ἄρχοντας καὶ ὑγείαν αὐτῷ. For a child is born to us, and a son is given to us, whose government is upon his shoulder, and his name is called the angel of great counsel, for I will bring peace upon the princes, and health to him. "ሜጋሌስ ቡሌስ አንጌሎስ" Μεγάλης βουλῆς ἄγγελος ማለት "የታላቁ ጉባኤ መልአክ"the angel of great counsel" ማለት ነው፥ በማሶሬት ላይ፦ "ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ" የሚለውን አሽቀንጥረው ጥለው "የታላቁ ጉባኤ መልአክ" ብለውታል። ይህም ጉባኤ የቅዱሳን መላእክት ጉባኤ ነው፦ መዝሙር 88(89)፥6 ጌታ ሆይ! ሰማያት ተኣምራትህን እውነትህንም ደግሞ በቅዱሳን ጉባኤ ያመሰግናሉ፥ ἐξομολογήσονται οἱ οὐρανοὶ τὰ θαυμάσιά σου, Κύριε, καὶ τὴν ἀλήθειάν σου ἐν ἐκκλησίᾳ ἁγίων. መዝሙር 88(89)፥7 ጌታን በሰማይ የሚተካከለው ማን ነው? ከአምላክ ልጆች ጌታን ማን ይመስለዋል? ὅτι τίς ἐν νεφέλαις ἰσωθήσεται τῷ Κυρίῳ; καὶ τίς ὁμοιωθήσεται τῷ Κυρίῳ ἐν υἱοῖς Θεοῦ; መዝሙር 88(89)፥8 በቅዱሳን ጉባኤ አምላክ ክቡር ነው፥ በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው። ὁ Θεὸς ἐνδοξαζόμενος ἐν βουλῇ ἁγίων, μέγας καὶ φοβερὸς ἐπὶ πάντας τοὺς περικύκλῳ αὐτοῦ. ኢየሱስን የዚህ ጉባኤ መልእክተኛ ማድረግ የመላእክት አለቃ ከሚለው ማዕረግ ዝቅ ማድረግ ነው። በእርግጥ "መልአከ ምክር(የጉባኤ መልአክ) ሚካኤል ነው፦ ድርሳነ ሚካኤል ዘወርኃ መጋቢት 7፥184 "ተአምሪሁ ለመልአክ ክቡር ሚካኤል ሊቀ መላእክት "መልአክ ምክሩ" ለአብ" ቅዳሴ ዮሐንስ አፈ ወርቅ 15፥17 "ፈነወ ለነ ወልዶ መድኅነ ወመቤዝወ "መልአከ ምክሩ" የማኑ እደ መዝራዕቱ ኃይሉ ወጥበቡ ለአቡሁ" ለአብ የጉባኤ መልአክ ማን ነው ሚካኤል ወይስ ኢየሱስ? በእርግጥ ዐበይት ክርስትና ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ አንግሊካን እና ፕሮቴስታንት በሥነ-መለኮት ትምህርታቸው "ኢየሱስ ሚካኤል ነው" ባይሉም "ኢየሱስ ብሉይ ኪዳን ላይ ሲላክ የነበረ መልአክ ነው" ብለው ያምናሉ፦ ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 83 ቁጥር 12 "-"የእግዚአብሔር ልጅ፣ መልአክ፣ ክንድ፣ ነቢይ" ተባለ።" ሰይፈ ሥላሴ ምዕራፍ 4 ቁጥር 48 "መልአክ የተባለውም የእግዚአብሔር ልጅ ነው" እውን መልአክ ይመለካልን? "መልአክ" የሚለው የግዕዝ ቃል "ለአከ" ማለትም "ላከ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ተላላኪ" "መልእክተኛ" ማለት ነው፥ እንግዲህ ኢየሱስ መልእክተኛ ከሆነ እርሱ ጋር የሌለ ግን ሌላ ማንነት ጋር ያለው ዕውቀት ለማስተላለፍ የተላከ ተላላኪ ነው ማለት ነው። አንድ ሁሉን ዐዋቂ አምላክ ሙሉ ዕውቀት ካለው ለሌላ ምንነት እና ማንነት እንዴት መልእክተኛ ይሆናል? ከሌላ ምንነት እና ማንነት ምን እንደሚናገር መልእክት እየተቀበለ እንዴት ይናገራል? መልእክተኛ የሌላ መልእክት እንጁ የራሱን አይናገርም፥ ከራሱ ምንም መናገር ካልቻለ እራሱ ጋር በቂ ትምህርት፣ ዕውቀት እና መልእክት የለውም ማለት ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Mostrar todo...
ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ-አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

ሚካኤል በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 2፥98 ለአላህ እና ለመላእክቱ፣ ለመልእክተኞቹ፣ ለጂብሪል፣ ለሚካኤል ጠላት የኾነ ሰው አላህ ለከሓዲዎች ጠላት ነው፡፡ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّلَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَرُسُلِهِ وَجِبْرِيلَ وَمِيكَالَ فَإِنَّ اللَّهَ عَدُوٌّ لِّلْكَافِرِينَ "ሚካኢል" مِيكَائِيل የሚለው የዐረቢኛው ቃል ከሦስት ቃላት የተዋቀረ ነው፥ "ሚ" مِي ወይም "መን" مَن ማለት "ማን" ማለት ሲሆን መጠይቅ ተውላጠ ስም ነው፣ "ካ" كَا ወይም "ከ" كَ ማለት "እንደ" ማለት ሲሆን መስተዋድድ ነው፣ "ኢል"  ئِيل ወይም "ኢላህ" إِلَـٰه  ማለት "አምላክ" ማለት ሲሆን ስም ነው። በጥቅሉ "ሚካኢል" مِيكَائِيل ማለት "ማን እንደ አምላክ" "መኑ ከመ አምላክ" ማለት ነው፦ 2፥98 ለአላህ እና ለመላእክቱ፣ ለመልእክተኞቹ፣ ለጂብሪል፣ ለሚካኤል ጠላት የኾነ ሰው አላህ ለከሓዲዎች ጠላት ነው፡፡ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّلَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَرُسُلِهِ وَجِبْرِيلَ وَمِيكَالَ فَإِنَّ اللَّهَ عَدُوٌّ لِّلْكَافِرِينَ ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59 , ሐዲስ 47 ሠሙራህ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “በሌሊት ላይ ሁለት ሰዎች ወደ እኔ ሲመጡ አየሁኝ፥ ከእነርሱ አንዱ እንዲህ አለ፦ “ያ እሳት የሚያይዝ “ማሊክ” ሲሆን የእሳት ዘበኛ ነው፥ “እኔ ጂብሪል ነኝ”። ይህ ሚካኢል ነው”። عَنْ سَمُرَةَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ رَأَيْتُ اللَّيْلَةَ رَجُلَيْنِ أَتَيَانِي قَالاَ الَّذِي يُوقِدُ النَّارَ مَالِكٌ خَازِنُ النَّارِ، وَأَنَا جِبْرِيلُ، وَهَذَا مِيكَائِيلُ ‏”‌‏.‏ በኢሥላም አስተምህሮት ሚካኢል ከመላእክት ሊቃውንት(አለቆች) አንዱ ሊቀ መላእክት እና እራሱ በምንነቱ መልአክ ነው። በባይብል "ሚካኤል" מִיכָאֵל የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ከሦስት ቃላት የተዋቀረ ነው፥ "ሚ" מִי ማለት "ማን" ማለት ሲሆን መጠይቅ ተውላጠ ስም ነው፣ "ካ" כָ ማለት "እንደ" ማለት ሲሆን መስተዋድድ ነው፣ "ኤል" אֵל ማለት "አምላክ" ማለት ሲሆን ስም ነው። በጥቅሉ "ሚካኤል" מִיכָאֵל ማለት "ማን እንደ አምላክ" ማለት ነው፦ ዘዳግም 33፥26 እንደ አምላክ ማንም የለም። אֵ֥ין כָּאֵ֖ל እዚህ አንቀጽ ላይ "እንደ አምላክ" ለሚለው ቃላት የገባው ቃላት "ካኤል" כָּאֵ֖ל እንደሆነ ልብ አድርግ! "ሚካኤል" מִיכָאֵל የሚለው ስም ለሰዎች የተጸውዖ ስም ሆኖ መጥቷል፦ ዘኍልቍ 13፥13 ከአሴር ነገድ የ-"ሚካኤል" ልጅ ሰቱር። ዕዝራ 8፥8 የሰፋጥያስ ልጆች የ-"ሚካኤል" ልጅ ዝባድያ፥ ከእርሱም ጋር ሰማንያ ወንዶች። ነገር ግን ይህ ስም ለመላእክት አለቃ ለመልአኩ የተጸውዖ ስም ነው፥ ሚካኤል ከመላእክት አለቆች አንዱ ነው፦ ይሁዳ 1፥9 የመላእክት አለቃ ሚካኤል..። ዳንኤል 10፥13 ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤ ዳንኤል 12፥1 በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል። ኢያሱ 5፥14 እኔ የያህዌህ ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ። በኢያሱ ፊት የተመዘዘ ሰይፉን የያዘው የያዘው የመላእክት አለቃ ሚካኤል እንደሆነ ድርሳነ ሚካኤል ይናገራል፦ ድርሳነ ሚካኤል ዘወርኃ ኅዳር 3፥148 "የነዌ ልጅ ኢያሱ በንጉሡ የጦር ቢትወደድ አምሳል ክቡር ገናና ሀኖ ያየው ይህ ሚካኤል ነው" ይህ ከመሆኑ ጋር ከ 1695 እስከ 1758 ይኖር የነበረው የአይሪሽ ፕሮቴስታንት መሪ ሮበርት ክላይቶን"Robert Clayton፣ የአድቬንቲስት ቤተክርስቲያን እና የይሆዋ ምስክሮች፦ "ኢየሱስ ብሉይ ኪዳን ላይ ሲላክ የነበረ መልአክ ወይም የመላእክት አለቃ ሚካኤል ነው" ብለው ያምናሉ፥ ምክንያታቸው ደግሞ የጥንት የቤተክርስቲያን አባቶች፦ "ኢየሱስ ብሉይ ኪዳን ላይ ሲላላክ የነበረ የመላእክት አለቃ እና መልአክ ነው" ብለው ስለተናገሩ ነው። ሰማዕቱ ዮስጦስ፦ "ክርስቶስ ንጉሥ፣ ካህን፣ አምላክ፣ ጌታ፣ መልአክ፣ ሰው እና አለቃ ነው፥ ኢያሱ 5፥13-15" Justin Martyr’s Dialogue w/ Trypho Ch. 34 የልዮኑ ኢራኒዮስ፦ ፨"እርሱ(ክርስቶስ) ሁሉ በሁሉ ነው፥ ከአባቶች መካከል አባት ነው፣ በሕግጋት መካከል ሕግ ነው፣ በካህናት መካከል ሊቀ ካህናት ነው፣ በነገሥታት መካከል ገዥ ነው፣ በነቢያት መካከል ነቢይ ነው፣ በመላእክት መካከል መልአክ ነው፣ በሰዎች መካከል ሰው ነው" Fragments of Irenaeus Ch. 53 ፨"እርሱ በካህናት መካከል ካህን ነው፣ በነገሥታት መካከል ጠቅላይ ገዥ ነው፣ በነቢያት መካከል ነቢይ ነው፣ በመላእክት መካከል መልአክ ነው፣ በሰዎች መካከል ሰው ነው፣ በአብ ደግሞ ልጅ ነው" Fragments of Irenaeus Ch. 54 የሰርዴሱ ሚልጦን፦ "እርሱ በሕግ ሕግ ነው፣ በካህናት መካከል ሊቀ ካህናት ነው፣ በነገሥታት መካከል ገዥ ነው፣ በነቢያት መካከል ነቢይ ነው፣ በመላእክት መካከል የመላእክት አለቃ ነው" Melito of Sardis’ Fragments Ch. 4 የቂሳርያው አውሳቢዮስ፦ ፨"እርሱ አምላክ እና የቅዱሳን ጌታ ተብሎ ቢጠራም ነገር ግን የልዑል አባቱ መልአክ ነው" Eusebius’ The Proof of the Gospel Book 1 Ch. 5 ፨"እርሱ(ክርስቶስ) የሰማይ ሰራዊት አለቃ ነው፥ የጌታ ሠራዊት አለቃ ኢያሱ 5፥13-15።" Eusebius’ The Proof of the Gospel Book 4 Ch. 10
Mostrar todo...
ዲነል ኢስላም 1 https://t.me/Mahdi_Quran_Recitation
Mostrar todo...
1.31 MB
"ኢስላም" በብሉይ ኪዳን -በወንድም ሀቢብ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ مِّلَّةَ أَبِيكُمْ إِبْرَاهِيمَ ۚ هُوَ سَمَّاكُمُ الْمُسْلِمِينَ مِن قَبْلُ وَفِي هَٰذَا لِيَكُونَ الرَّسُولُ شَهِيدًا عَلَيْكُمْ وَتَكُونُوا شُهَدَاءَ عَلَى النَّاسِ ۚ 22፥78 የአባታችሁን የኢብራሂምን ሃይማኖት ተከተሉ፤ እርሱ አላህ ከዚህ በፊት “ሙስሊሞች” الْمُسْلِمِينَ ብሎ ሰይሟችኋል፡፡በዚህም (ቁርኣን)፤ መልክተኛው በእናንተ ላይ መስካሪ እንዲሆን እናንተም በሰዎቹ ላይ መስካሪዎች እንድትኾኑ (ሙስሊሞች ብሎ ሰይሟችኋል)፡፡ የኢስላም ትርጉም :- الإسلام معناه الاستسلام لله تعالى بالتوحيد والانقياد له بالطاعة والخلوص من الشرك وترك نواهيه ኢስላም ማለት የራስ ፈቃድን ለሀያሉ ፈጣሪ አላህ በብቸኝነት ወደ እርሱ ትዕዛዝ መዘንበል በርሱም ሌላን አምላክ ከማጋራት ፍፁም መራቅ እንዲሁም ክልከላው መተው ነው " "ኢሥላም" ኢሥላም ወደ ነብያት የተወረደው ጭብጥ ነው፤ “ኢሥላም” إِسْلَٰم የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ “ታዘዘ”፣ “ተገዛ”፣ ” አመለከ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን ትርጉሙ “መታዘዝ”፣ “መገዛት”፣ "ማምለክ" ማለት ነው፤ አንዱን አምላክ ብቻ ማምለክ ኢሥላም ይባላል፤ የኢስላም አስኳሉ፦ "ላ ኢላሀ ኢላ አና" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَ ማለትም "ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም" የሚል ነው " -ወሒድ ዑመር በጥቅሉ የራስን ፈቃድ ለብቸኛው ለፈጣሪ አላህ ትዕዛዝ ማስገዛትን ይመለከታል ኢየሱስም “የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።” — ዮሐንስ 5፥30 ኢስላም إِسْلَٰم ማለት “መታዘዝ” ማለት ሲሆን የአላህ ሃይማኖት ነው፦ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ ۗ አላህ ዘንድ (የተወደደ) ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው፡፡ የተከታዩም (ምዕመኑ) መጠሪያ በጉባዔ ስብስብ ስያሜ የተሰጠው ሳይሆን በሀያሉ አላህ የተሰየመ መሆኑ ቀድሞውኑ መግቢያዬ ላይ ባወሳሁት የአላህ ቃል ቁርዐን አንቀጽ እንዲሁም በሌሎች የቁርዐን ክፍል ይህን ሀቅ እናገኛለን هُوَ سَمَّاكُمُ الْمُسْلِمِينَ እርሱ አላህ ከዚህ በፊት “ሙስሊሞች" ብሎ ሰይሟችኋል፡፡ ኢሥላም” إِسْلَٰم የሙስሊም ሃይማኖቱ ሲሆን "መታዘዝ" መገዛት" "ማምለክ" ማለት ነው፤ አላህ፦ "ሁላችሁም በመታዘዝ ውስጥ ግቡ" የሚለን፤ “መታዘዝ” ለሚለው ቃል የገባው “ሲልም” سِّلْم መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፦ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ادْخُلُوا فِي السِّلْمِ كَافَّةً وَلَا تَتَّبِعُوا خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ ۚ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሁላችሁም በመታዘዝ *السِّلْمِ* ውስጥ ግቡ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ፤ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና፡፡ የኢስላም ሀይማኖት የሁሉም ቀደምት ነቢያት ሀይማኖት ነው ከላይ የኡስታዝ ወሒድ ዑመር ፁሁፍ አጣቅሻለው በዝርዝር ሊንኩን ተጭነው ያንብቡ። ማስረጃ ይኖር ይሆን ሙስሊም የሚለው ቃል ለምዕመናን መዋል በመፅሀፍ ? መፅሐፍን (BIBLE) በጥልቀት ስንመረምር ይህ እውነታ የበለጠ ፍንትው ብሎ እናገኘዋለን የሚከተለውን የመፅሐፍ ክፍል እንዳስ ትንቢተ ኢሳያስ “ከባሪያዬ በቀር ዕውር ማን ነው? እንደምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ደንቆሮ የሆነ ማን ነው? *እንደ* *ፍጹሙ* [{ כִּמְשֻׁלָּ֔ם }] ወይስ እንደ እግዚአብሔር ባሪያ ዕውር የሆነ ማን ነው?” — ኢሳይያስ 42፥19 እዚህ ክፍል ላይ በይብራይስጥ የገባው ቃል כִּמְשֻׁלָּ֔ם ከሙሽለም ይላል ከፊት የገባችው የሂብሩ ፊደል ካፍ (כִּ) በዚህ ቃል ላይ በመስተዋዳድነት ገብታለች *ልክ* *እንደ* (as,like) የሚለውን ታመለክታለች *እንደ* ፍፁሙ ሲል ካፍ(כִּ) *እንደ* የሚለውን ትወክላለች በተመሳሳይ በአረበኛም እንዲሁ ካፍ (ك) ለዚሁ ጥቅም ትውላለች። ዋናው ቃል מְשֻׁלָּ֔ם ሙሽሊም የሚል ይሆናል ባለ አራት ፊደል የያዘ የሂብሩ ቃል ሜም(מְ) ሺን(שֻׁ) ላሜድ(לָּ֔) ሜም(מְ) የአረበኛውን ቃል እንይ مسلم *ሙስሊም* በተመሳሳይ ባለ አራት ፊደል የአረበኛ ቃል ሚም(م) ሲን(س) ላም(ل) ሚም(م) ሁለቱ ቃል *ሙሽሊም* እና *ሙስሊም* የሁለቱ ቃላት ልዩነት በ ሺን(שֻׁ) ፊደል እና በ ሲን(س) ነው። ነገር ግን ሁለቱ ልዩነትን አያመጡም ! ምክንያት ? በሂብሩ ያሉ ቃላት በ ሺን(שֻׁ) ሲመጡ በአረበኛ በ ሲን(س) ይነበባሉ ሁለት ምሳሌ ልውሰድ ሻሎም שָׁלוֹם ሺን(שֻׁ) ከፊት መጥታለች ሰላም سلام ሲን(س) ከፊት ትመጣላች ይሽማኤል יִשְׁמָעֵאל ኢስማኢል إسماعيل አሁን ደግመን ትንቢተ ኢሳያስን እንየው “ከባሪያዬ በቀር ዕውር ማን ነው? እንደምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ደንቆሮ የሆነ ማን ነው? እንደ ሙስሊሙ (כִּמְשֻׁלָּ֔ם) ወይስ እንደ እግዚአብሔር ባሪያ ዕውር የሆነ ማን ነው?” — ኢሳይያስ 42፥19 ይህ ቃል מְשֻׁלָּ֔ם ሙሽሊም በብሉይ ኪዳን 25 ጊዜ በተወጽዖ ስምነት ሲጠቀስ ክርስቲያን የሚለው ቃል ለነቢያት (ዐ.ሰ) በብሉይ ሳይጠሩበት እየሱስ(ዐ.ሰ) እንኳን ራሱን ሳይጠራበት ተከተያቹን ሳያስጠራ ከእርሱ እርገት በሆላ በስድብ መልክ ተሰይሟል በአዲስ ኪዳን 3 ጊዜ ተጠቅሶ እናገኛዋለን። ኢሳይያስ 42፥19 ይህ ትንቢት በህዘበ ክርስቲያኑ ለኢየሱስ ነው የዋለ የሚል እምነት አለ ሌላ ጊዜ አላህ ካለ በዝርዝር የምናየው ይሆናል። እስካሁን ያወሳከው የራስህን የግል አስታየየት በመፅሐፍ (bible) እየተፈላሰፍክ ነው ልባል ይቻላል። በቀጣይ ክፍል የክርስትና የሀይማኖት ሊህቃን የመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት የመፅሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ የኔን ሀሳብ ይደግፉ ይሆን? አብረን ምንመለከት ይሆናል ! قُولُوا آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْنَا وَمَا أُنزِلَ إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَمَا أُوتِيَ النَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ «በአላህና ወደኛ በተወረደው (ቁርኣን) ወደ ኢብራሂምም ወደ ኢስማዒልና ወደ ኢስሐቅም ወደ ያዕቁብና ወደ ነገዶቹም በተወረደው በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን አመንን፤ እኛም ለርሱ *ሙስሊሞች* ነን» በሉ፡፡ ይቀጥላል .... ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱህ ✍️ወንድም ሀቢብ https://t.me/ewnet_lehulum
Mostrar todo...
እዉነት ለሁሉ [truth for all]

ይህ ቻናል ዓላማው በማስረጃና በመረጃ በመታገዝ እውነትን ከውሸት በመለየት፣ በአላህ ፈቃድ በጨለማ የሚኖሩ ወገኖችን ብርሃን ወደሆነው ኢስላም መጣራት ነው። قُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَمَا يُبْدِئُ الْبَاطِلُ وَمَا يُعِيدُ [ ሱረቱ ሰበእ - 49 ] «እውነቱ መጣ፡፡ ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውም (ተወገደ)» በላቸው፡፡

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿احْرِصْ على ما يَنْفَعُكَ، واسْتَعِنْ باللَّهِ وَلا تَعْجِزْ، وإنْ أَصابَكَ شَيءٌ، فلا تَقُلْ: لو أَنِّي فَعَلْتُ كانَ كَذا وَكَذا، وَلَكِنْ قُلْ: قَدَرُ اللهِ وَما شاءَ فَعَلَ؛ فإنَّ (لو) تَفْتَحُ عَمَلَ الشَّيْطانِ.﴾ “በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ። በአላህ ታገዝ። አትስነፍ። አንዳች ነገር ባጋጠመህ ጊዜ ይህን ይህን ነገር ባደርግ ኖሮ ይሄ ነገር አይከሰትም አትበል። ነገር ግን ‘አላህ የወሰነው ሆነ። እሱም የፈለገውን ነገር ያደርጋል’ በል። ለው ‘እንዲህ ባደርግ ኖሮ’ የሸይጧንን ስራ ትከፍታለች።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 2664 ጆይንhttps://t.me/nstest
Mostrar todo...
እኚህ ሰው ማን ናቸው? በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 15፥95 *"ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንልሃል"*፡፡ إِنَّا كَفَيْنَاكَ الْمُسْتَهْزِئِينَ ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ከሕፃን እስከ አዋቂ፣ ወጣትም ሆነ አዛውንት ስለ እሳቸው ሲወራ "ጆሮ ዳባ ልበስ" የሚል የለም። ሁሉ ስለ እሳቸው ሲወራ አዳሜ ሆነ ሔዋኔ ጆሮውን አስግጎ ይሰማል፥ ከሁሉም ከሁሉም የሚገርመው ደግሞ የሚጠሏቸው ሳይቀር እንኳን ቢሆን ስለ እሳቸው ለመስማት እና ስለ እሳቸው ለማወቅ ይፈልጋሉ። ዝም ብለህ ሰው የተሰበሰበበት መሀል ገብተህ እና ድምጽክን ከፍ አድርገህ፦ "እከሌ" ብለህ ወይም "እከሊት" ብለህ ብትጣራ ፊቱን እና ትኩረቱን ወደ አንተ የሚያዞረው የጠራከውን ስም ባለቤት ብቻ ነው፥ ከሌለም ደግሞ ማንም ፊት እና ትኩረት የሚሰጥክ አይኖርም። ነገር ግን ሰው የተሰበሰበበት ስፍራ ሄደህ የእሳቸውን ስም ጠርተህ ንግግር ብትጀምር ሁሉም ፊቱን እና ትኩረቱን ወደ አንተ ያደርጋል፥ ትኩረት የማይሰጥህ የለም ቢባል ማጋነን እና ማበል አይሆንም። ስለ እሳቸው ለማወቅ የማይሰለፍ አይኖርም፥ እኚህ ሰው፦ 1ኛ. የእልፍ አእላፋት መጻሕፍት ርእስ በመሆን ብዙ ጸሐፊያን የከተቡላቸው ናቸው፣ 2ኛ. በሁሉም ልብ ውስጥ በአሉታዊ ሆነ በአንታዊ በሁለት ወገን እንደተሳለ ሰይፍ ሰርስረው የገቡ ናቸው፣ 3ኛ. አስተምህሮታቸው የተሟላ መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ የሕይወት ዘይቤ በመሆኑ የዓለማችን ተግዳሮት ነው የተባለላቸው ናቸው፣ 4ኛ. "የዓለማችን ቁጥር አንድ አውንታዊ እና አሉታዊ ተጽዕኖ አሳዳሪ" ተብለዋል፥ ለሕሩያን አውንታ ተጽዕኖ እንዲሁ ለእኵያን አሉታዊ ተጽዕኖ አሳዳሪ ናቸው፣ 5ኛ. ስለ እርሳቸው ማንነት የገባው ሰው፦ "ሕይወትህን መስዋዕት አርግ" ቢባል ያለ አንዳች ማቅማማት ሕይወቱን እስከ ሞት የሚያደርግላቸው ናቸው። 6ኛ. በታሪክ ውስጥ እሳቸውን ለማነወር፣ ለማበሻቀጥ፣ ለማብጠልጠል ብዙ ጦማሪያን ጦምረዋል፣ ብዙ ኃያሲያን ኃይሰዋል፤ ብዙ ተቺዎች ተችተዋል፣ ብዙ ተሳላቂዎች ተሳልቀዋል። ቅሉ ግን የጦማሪያን ጦማር፣ የኃያሲያን ኂስ፣ የተቺዎች ትችት፣ የተሳላቂዎች ስላቅ ከሟቾች ጋር ሲያልፍ የእሳቸው ስም እና የሰዎችን ሕይወት የቀየሩበት መጽሐፍ እስካሁን አለ የተባለላቸው ናቸው። እኚህ ሰው ማን ናቸው? አዎ! የዓለማቱ ጌታ የአሏህ መልእክተኛ እና የነቢያት መደምደሚያ ነቢዩ ሙሐመድ"ﷺ" ናቸው። በእርሳቸው ላይ የወረደው ሐቅ ለሰዎች የሚጠቅም ስለሆነ በምድር 1400 ዓመት ቆይቷል፥ ባጢል ቢሆን ኖሮ በእንጭጩ ኮረፋት ሆኖ ተግበስብሶ ይጠፋ ነበር፦ 13፥17 *"እንደዚሁ አላህ ለእውነት እና ለውሸት ምሳሌን ያደርጋል። ኮረፋቱማ ግብስብስ ኾኖ ይጠፋል፥ ለሰዎች የሚጠቅመውማ በምድር ላይ ይቆያል፡፡ እንደዚሁ አላህ ምሳሌዎችን ይገልፃል"*፡፡ كَذَٰلِكَ يَضْرِبُ اللَّهُ الْحَقَّ وَالْبَاطِلَ ۚ فَأَمَّا الزَّبَدُ فَيَذْهَبُ جُفَاءً ۖ وَأَمَّا مَا يَنفَعُ النَّاسَ فَيَمْكُثُ فِي الْأَرْضِ ۚ كَذَٰلِكَ يَضْرِبُ اللَّهُ الْأَمْثَالَ ሐዋ. ሥራ 5፥38-39 አሁንም እላችኋለሁ፦ ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም! *ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፥ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም። በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ"*። ገማሊያ እንደተናገረው ይህ የነቢያችን"ﷺ" እሳቦት ከሰው ከሆነ ይጠፋ ነበር፥ ግን የነቢያችን"ﷺ" ግልጠተ-መለኮት ከፈጣሪ ስለሆነ ገና በእንጭጭነቱ የመካህ ቁሬይሾች፣ የመዲና በኑ ቁሬይዛህ፣ የሮሙ ባዛንታይን በዕውቀት መሞገት ሲያቅታቸው በጉልበት ሊጠፉት ሞክረው አልተሳካላቸው። ከርሞም ሆነ ዘንድሮም እሳቸው ላይ ለሚሳለቁን ተሳላቂዎች አሏህ በቅቶላቸዋል፥ በእርሳቸው ላይ የወረደውን የአሏህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ቢፈልጉ እና ቢጠሉም አሏህ ብርሃኑን ገላጭ ነው፦ 15፥95 *"ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንልሃል"*፡፡ إِنَّا كَفَيْنَاكَ الْمُسْتَهْزِئِينَ 61፥8 *"የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፥ ከሓዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ አላህ ብርሃኑን ገላጭ ነው"*፡፡ يُرِيدُونَ لِيُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَاللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ ይህንን ብርሃን ለማጥፋት እፍ ባሉ ቁጥር እያነደዱት መሆኑን ይዘነጋሉ፥ ኢሥላም በፍጥነት መጠነ-ሰፊ የእድገት መርሓ-ግብር እየታየበት ያለው በምዕራባውያን መሆኑ እፍ ባሉ ቁጥር የሚያነዱበት ውጤት ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን! አሚን። “ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ ረሡሉሏህ” فِدَاكَ أَبِي وَأُمِّي يَا رَسُول اللَّه ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Mostrar todo...
ቁርኣን ፍጡር ነውን?” በሚለው ርዕስ በወንድሞች መካከል የተደረገ አጭር የጥያቄ እና መልስ ውይይት። ® T.me/EAAAresponse
Mostrar todo...
record.ogg32.69 MB
የሃይማኖት ንጽጽር ኮርስ 4ኛ ዙር የሙቃረናህ ደርሥ! "ሙቃረናህ" مُقَارَنَة የሚለው ቃል "ቃረነ" قَارَنَ ማለትም "አነጻጸረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንጽጽር" ማለት ነው፥ ሙቃረናህ የሃይማኖት ንጽጽር"Comparative Religion" ሲሆን በእሥልምና እና በክርስትና መካከል ያለው የሥነ-መለኮት አንድነት እና ልዩነት እየተነጻጸረ የሚቀርብበት ጥናት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 6 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሁለት ተርም አለው። ፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ-አሳብ በፈጣሪ እሳቦት ላይ የሚያውጠነጥኑ ሲሆኑ የሚከተሉት ናቸው፦ ምዕራፍ አንድ ሥላሴ"trinity" ምዕራፍ ሁለት ነገረ-ክርስቶስ"Christology" ምዕራፍ ሦስት ነገረ-ማርያም"Mariology" ምዕራፍ አራት ነገረ-መላእክት"angelology" ምዕራፍ አምስት ነገረ-ምስል"Iconlogy" ፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በቅዱሳን መጽሐፍት ላይ የሚያውጠነጥኑ ሲሆኑ የሚከተሉት ናቸው፦ ምዕራፍ አንድ አህሉል ኪታብ"People of the Book" ምዕራፍ ሁለት መጽሐፍት"scriptures" ምዕራፍ ሦስት የመጽሐፍ አጠባበቅ"preservation" ምዕራፍ አራት የመጽሐፍት ልኬት"Standardization" ምዕራፍ አምስት የባይብል ግጭት"Contradiction" ምዕራፍ ስድስት ኦሪት"Torah" ምዕራፍ ሰባት ወንጌል"Gospel" ደርሡ በሳምንት አንዴ የሚለቀቅ ሲሆን በሁለት ሳምንት አንዴ የሁለቱ ሳምንት ጥያቄ ፈተና ይኖራል። ፈተናው ከ 10 የሚወሰድ ሲሆን ከ 6-10 ማምጣት ይጠበቅባችኃል። ከ 6 በታች ሦስት ጊዜ ካመጣችሁ በሰርተፍኬት አናስመርቅም። የሙቃረናህ ደርሥ ቦርድ አባላት አሥር ሲሆኑ ዋና ዋናዎቹ አራት ናቸው፥ እነርሱ፦ 1. ወንድም ወሒድ የደርሡ አስተማሪ፣ 2. እኅት ሐደል የደርሡ አቅራቢ፣ 3. እኅት ሐናን የደርሡ ፈተና አርቃቂ 4. ወንድም መህዲይ የደርሡ ፈታኝ እና ውጤት ክፍል ናቸው። ለመመዝገብ ከታች የተዘረዘሩት የቦርዱ አካላት በውስጥ ያናግሩ! እኅት ሐድልን፦ https://t.me/Ohanw9 እኅት ረምላን፦https://t.me/REMLANEG እኅት ሰላምን፦ http://t.me/SeuweSe አኅት ዘሃራን፦ https://t.me/Zhara_mustefa እኅት ሐቢባን፦ https://t.me/Mahbubo እኅት አበባ፦http://t.me/temariwa_lji ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ! ወጀዛኩሙሏህ ኸይራ!
Mostrar todo...
የመሢሑ አወጣጥ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 3፥36 «እኔም እርስዋን እና ዝርያዋን ከተረገመው ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ» وَإِنِّي أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ አምላካችን አሏህ በአደም፣ በኑሕ፣ በኢብራሂም፣ በዒምራን ቤተሰብ ውስጥ መሢሑ እንዲመጣ አድርጓል፥ መርየም የዒምራን ልጅ ስትሆን መሢሑ ደግሞ ዘሯ ነው፦ 3፥33 አላህ አደምን፣ ኑሕንም፣ የኢብራሂምንም ቤተሰብ፣ የዒምራንንም ቤተሰብ በዓለማት ላይ መረጠ፡፡ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَىٰ آدَمَ وَنُوحًا وَآلَ إِبْرَاهِيمَ وَآلَ عِمْرَانَ عَلَى الْعَالَمِينَ 3፥36 «እኔም እርስዋን እና ዝርያዋን ከተረገመው ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ» وَإِنِّي أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ "ዙሪያህ" ذُرِّيَّة ማለት "ዘር"offspring" ማለት ሲሆን "ዙሪያህ" ذُرِّيَّة በሚለው መድረሻ ቅጥያ ላይ "ሃ" هَا የሚለው አንስታይ አገናዛቢ ተውላጠ ስም መርየምን አመላካች ስለሆነ ዒሣ የመርየም ዘር መሆኑን ቁልጭ እና ፍንትው አርጎ ያሳያል። በተመሳሳይ ባይብል ላይ መሢሑ ከአብርሃም፣ ከይስሐቅ፣ ከያዕቆብ፣ ከይሁዳ፣ ከእሴይ ወዘተ ... እንደሚወጣ ተተንብይዋል፦ ሚክያስ 5፥2 አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል። וְאַתָּ֞ה בֵּֽית־לֶ֣חֶם אֶפְרָ֗תָה צָעִיר֙ לִֽהְיֹות֙ בְּאַלְפֵ֣י יְהוּדָ֔ה מִמְּךָ֙ לִ֣י יֵצֵ֔א לִֽהְיֹ֥ות מֹושֵׁ֖ל בְּיִשְׂרָאֵ֑ל וּמֹוצָאֹתָ֥יו מִקֶּ֖דֶם מִימֵ֥י עֹולָֽם እዚህ አንቀጽ ላይ "ቀድሞ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ቄዴም" קֶדֶם ሲሆን ይህ "ቀድሞ" የተባለው ጊዜ አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ የነበሩበትን ጊዜ ነው፦ ሚክያስ 7፥20 ከ-"ቀድሞ" ዘመን ጀምረህ ለአባቶቻችን የማልህላቸውን እውነት ለያዕቆብ፥ ምሕረትንም ለአብርሃም ታደርጋለህ። תִּתֵּ֤ן אֱמֶת֙ לְיַֽעֲקֹ֔ב חֶ֖סֶד לְאַבְרָהָ֑ם אֲשֶׁר־נִשְׁבַּ֥עְתָּ לַאֲבֹתֵ֖ינוּ מִ֥ימֵי קֶֽדֶם "ለአባቶቻችን የማልህላቸውን" የሚለው ይሰመርበት! ይህም መሃላ ከእነርሱ ዘር በሚወጣው መሢሕ እንደሚባረኩ ነው፥ ዘፍጥረት 22፥18 ዘፍጥረት 26፥4 ዘፍጥረት 28፥14 ተመልከት! "ቄዴም" קֶדֶם ሌላ ትርጉሙ "ምሥራቅ" ማለት ነው፦ ዘፍጥረት 10፥30 ስፍራቸውም ከማሴ አንሥቶ ወደ ስፋር ሲል እስከ "ምሥራቅ" ተራራ ድረስ ነው። וַֽיְהִ֥י מֹושָׁבָ֖ם מִמֵּשָׁ֑א בֹּאֲכָ֥ה סְפָ֖רָה הַ֥ר הַקֶּֽדֶם እዚህ አንቀጽ ላይ "ምሥራቅ" ለሚለው የገባው ቃል "ቄዴም" קֶדֶם እንደሆነ ልብ አድርግ! ከ 306 እስከ 373 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረ ሶሪያዊ ኤፍሬም ድንግል ማርያምን "ምሥራቅ" ኢየሱስን "ኮከብ" በማለት "አወጣጡ ከምሥራቅ ነው" የሚለውን ፈሥሯታል፦ ውዳሴ ማርያም ዘዐርብ ቁጥር 6 "አንቲ ውእቱ ምሥራቅ ዘወጽአ እምኔኪ ኮከብ" ትርጉም፦ "ኮከብ ከአንቺ የወጣብሽ ምሥራቅ አንቺ ነሽ" "ከዘላለም የሆነ" የሚለውን ደግሞ በቀጣይ የመጣ ነው፥ “ዘላለም” የሚለው የዕብራይስጡ ቃል “ዖላም” עוֹלָ֗ם ሲሆን አላፊ ወይም መጻኢ ውስን ጊዜን ለማመልከት ይውላል፥ ለምሳሌ፦ ዘዳግም 33፥15 በቀደሙትም ተራሮች ከፍተኛነት፥ በዘላለሙም ኮረብቶች ገናንነት። וּמֵרֹ֖אשׁ הַרְרֵי־קֶ֑דֶם וּמִמֶּ֖גֶד גִּבְעֹ֥ות עֹולָֽם׃ እዚህ አንቀጽ ላይ ለተራራ ቀዳማይነት የገባው ቃል "ቄዴም" קֶדֶם ሲሆን ለኮረብታ የገባው ቃል ደግሞ “ዖላም” עוֹלָ֗ם ነው፥ ለጌታው ባሪያ ለዘላለምም ባሪያው ይሁን ሲባል የተጠቀመበት ቃል “ዖላም” עוֹלָ֗ם ነው፦ ዘጸአት 21፥6 ወደ ደጁም ወደ መቃኑ አቅርቦ ጆሮውን በወስፌ ይብሳው፤ “ለዘላለምም” ባሪያው ይሁን። וְהִגִּישֹׁ֤ו אֲדֹנָיו֙ אֶל־הָ֣אֱלֹהִ֔ים וְהִגִּישֹׁו֙ אֶל־הַדֶּ֔לֶת אֹ֖ו אֶל־הַמְּזוּזָ֑ה וְרָצַ֨ע אֲדֹנָ֤יו אֶת־אָזְנֹו֙ בַּמַּרְצֵ֔עַ וַעֲבָדֹ֖ו לְעֹלָֽם׃ ס መሢሑ ከ-"ቀድሞ" ዘመን ጀምሮ አወጣጡ ከአብርሃም፣ ከይስሐቅ፣ ከያዕቆብ፣ ከይሁዳ፣ ከእሴይ ወዘተ ... ነው፦ ዘኍልቍ 24፥17 ከያዕቆብ ኮከብ “ይወጣል”። ዘኍልቍ 24፥19 ከያዕቆብም “የሚወጣ” ገዥ ይሆናል። ዕብራውያን 7፥14 ጌታችን ከይሁዳ ነገድ “እንደወጣ” የተገለጠ ነውና። ኢሳይያስ 11፥1 ከእሴይ ግንድ በትር “ይወጣል”። መሢሑ ከ-"ቀድሞ" ዘመን ጀምሮ አወጣጡ ከአብርሃም፣ ከይስሐቅ፣ ከያዕቆብ፣ ከይሁዳ፣ ከእሴይ ወዘተ ... ነው፦ ዘኍልቍ 24፥17 ከያዕቆብ ኮከብ “ይወጣል”። ዘኍልቍ 24፥19 ከያዕቆብም “የሚወጣ” ገዥ ይሆናል። ዕብራውያን 7፥14 ጌታችን ከይሁዳ ነገድ “እንደወጣ” የተገለጠ ነውና። ኢሳይያስ 11፥1 ከእሴይ ግንድ በትር “ይወጣል”። ስለዚህ ሚክያስ 5፥2 ኢየሱስ ዓለም ሳይፈጠር እና ዘመን ሳይቆጠ አብን አህሎ እና መስሎ እንዲሁ ከባሕርይው ባሕርይው እና ከአካሉ አካሉ ወስዶ ወጣ፣ ተገኘ፣ ተወለደ ለሚለው የዘላለማዊ ውልደት”eternal generation” ደርዛዊ ሥነ-መለኮት ማስረጃ መሆን አይችልም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Mostrar todo...
Repost from Sαlαh Responds
Photo unavailableShow in Telegram
أنَّ لُقمانَ كان يَقولُ: يا بُنَيَّ، لا تَعَلَّمِ العِلمَ لِتُباهيَ به العُلَماءَ، أو تُماريَ به السُّفَهاءَ، وتُرائيَ به في المَجالِسِ ሉቅማን ለልጁ እንዲህ ይለው ነበር ❝ልጄ ሆይ ! እውቀትን ከሊቃውንት ጋር ለመፎካከር፣ ከአላዋቂዎች ጋርም ለመከራከር፣ በአደባባይም ለማሳየት ብለህ አትማር። (📚ተኽሪጅ አል-ሙሰነድ ሐዲስ 1651) የዚህን ከያኒ (ጥበበኛ) ሰው ተጨማሪ ምክሮች ከፈለጋችሁ የቁርኣንን ሠላሳ አንደኛ ምዕራፍ ያንብቡ። እኔምለው ሉቅማን ኢትዮጵያዊ መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን ? ነገ እመለስበታለሁ ኢንሻአላህ። ------------------------------------------- ® Sαlαh Responds
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.