cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Abu hatim Abduselam Aselefiy

ትክክለኛው እስላማዊ አስተምህሮ ከቁርአንና ከሐዲስ ከደጋግ ቀደምቶች አረዳድ ከታማኝ ዑለሞች ንግግር የሚሰራጭበት ቻናል ነው።

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 340
Suscriptores
Sin datos24 horas
+57 días
+5330 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

በአንድ ቀን ፆም የአመት ወንጀል… ——— የዓሹራ ቀን ፆም ትሩፋት! ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- قال النبي صلى الله عليه وسلم: "صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ وَصِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ " رواه مسلم “የዐረፋ ቀን ፆም ከፊቱ ያለውን (አንድ) አመት እና ከኋላው ያለውን (አንድ) አመት ወንጀል ያስምራል (ያሰርዛል) ብዬ በአላህ ላይ እገምታለሁ። #የዓሹራ_ፆም_ከፊቱ_የነበረችውን_አመት_ወንጀል_ያስምራል (ያሰርዛል) ብዬ በአላህ ላይ እገምታለሁ።” ሙስሊም 1162 ዘግበውታል። عن أبي قتادة رضي الله عنه – في صفة صوم النبي صلى الله عليه وسلم وهو حديث طويل – قال : وسئل عن صوم يوم عاشوراء فقال : " يكفر السنة الماضية " أخرجه مسلم , والترمذي , وابن ماجه አቢ ቀታዳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ስለ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፆም ሁኔታ በረጅም ሀዲስ የሚከተለውን ብሏል:- ነቢዩ ﷺ ስለ ዓሹራ ፆም ተጠይቀው ሲመልሱ “ያለፈውን አንድ አመት ወንጀል ያስምራል (ያሰርዛል)።” ብለዋል። [ሙስሊም፣ ትርሚዚይ፣ እና ኢብን ማጃ ዘግበውታል።] ይህ አላህ ለኛ የዋለው ትልቅ ውለታ ነው!። በአንድ ቀን ፆም ምክንያት የአመት ትናንሽ ወንጀሎች ይሰረዛሉ። በመሆኑ በአላህ ፈቃድ ይህን ፆም የወፈቀው ሰው 9ኛውን ቀን ሰኞ ሙሀረም 9/1446 ዓ.ሂ: እንዲሁም በኢትዮ ሐምሌ 8/2016: በፈረንጆች ደግሞ ጁለይ 15/2024 ስለሆነ ሰኞን ፆሞ ማክሰኞን 10ኛውን ቀን ለመፆም እንዲዘጋጅ ሁላችንም በተቻለን መጠን እናነቃቃ፣ (እናስተውስ)። በመልካም ነገር ላይ በማስታወስ ተጨማሪ አጅር ከአላህ ዘንድ ለማግኘት መሽቀዳደም ነው። ✍🏻ኢብን ሽፋ: ሙሀረም 8/1446 ዓ. ሂ #Join ⤵️ የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
Mostrar todo...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

👍 1
አዲስ ወቅታዊ የንባብ መፅሃፍ ግብዣ ለአንባቢያን በሙሉ ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ «فضل يوم عاشورء» ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ «የዓሹራ ቀን ቱሩፋት » ➴➴➴➴➴ ==================== إعداد: الشيخ عبد الرزاق بن عبد المحسين البدر - حفظة الله- ዝግጅት:-በሸይኽ ዓብዱረዛቅ ቢን ዓብዱልሙህሲን ሃፊዘሁሏህ ተዘጋጅቶ ➴➴➴➴➴ ==================== ትርጉም:‐ አቡ ዓብዲልዓዚዝ/ዩሱፍ አህመድ ሃፊዞሁሏህ በቻልነው ሁሉ ለሌሎች እንዲደርስ የበኩላችንን እናበርክት ባረከሏሁ ፊኩም ➴➴➴➴➴ ==================== የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ كن على بصيرة Use one of the best PDF Reader. Download free now! http://bit.ly/PDFReader_alldocumentreader
Mostrar todo...
የዓሹራ ቀን ትሩፋት.pdf9.20 KB
የዓሹራ ቀን አጿጿም እና በዕለቱ የሚከሰቱ ቢድዓዎች ————— እንደሚታወቀው የዓሹራ ቀን ፆም ማለትም ሙሀረም 10ኛውን ቀን መፆም ከታላላቅ ሶናዎች ነው። ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- (أَفْضَلُ الصِّيَامِ بَعْدَ رَمَضَانَ شَهْرُ اللَّهِ الْمُحَرَّمُ) رواه مسلم “ከረመዷን በኋላ በላጩ ፆም የሙሀረም ወር ፆም ነው።” [ሙስሊም 1163 ዘግበውታል።] ይህ ፆም የረመዷን ወር ከመደንገጉ በፊት ግዴታ ነበርም ተብሏል። የሚፆምበትን ምክንያት:- በመሰረቱ እንደ ሙስሊም ማንኛውም በቁርኣን እና በሶሂህ ሀዲስ የመጣን መልካም ስራ፣ ትእዛዝም ይሁን ክልከላ ምክንያቱን አወቅነውም አላወቅነውም መተግበርና መቀበል ግዴታችን ነው። በግልፅ ማስረጃ የመጣ ነገር እስከሆነ ድረስ መተግበር ነው። የዓሹራ ፆም ምክንያት አለው። በሚከተለው ሀዲስም ተብራርቷል:- عن ابن عباس ((قَدِمَ النَّبِيُّ -صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ- المَدِينَةَ فَرَأَى الْيَهُودَ تَصُومُ يَوْمَ عَاشُورَاءَ فَقَالَ مَا هَذَا؟ قَالُوا: هَذَا يَوْمٌ صَالِحٌ، هَذَا يَوْمٌ نَجَّى اللَّهُ بَنِي إِسْرَائِيلَ مِنْ عَدُوِّهِمْ فَصَامَهُ مُوسَى، قَالَ فَأَنَا أَحَقُّ بِمُوسَى مِنْكُمْ فَصَامَهُ وَأَمَرَ بِصِيَامِهِ)).  في صحيح البخاري ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ:- “ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና በገቡ ጊዜ አይሁዶች የዓሹራን ቀን (ሙሀረም 10ኛውን ቀን) ሲፆሙ አዩዋቸው፣ ነቢዩም ለአይሁዶች ይህ ምትፆሙት ምንድነው? አሉዋቸው፣ ይህ ምርጥ ቀን ነው፣ ይህ ቀን አላህ በኒ ኢስራኢሎችን ከጠላታቸው የገላገለበት ቀን ነው፣ ሙሳ ፆሞታል። አሉ፣ ነቢዩም እኔ ለሙሳ ከናንተ የበለጠ የቀረብኩኝ ነኝ ብለው ፆሙት፣ እንዲፆምም አዘዙ።” [ቡኻሪ ዘግበውታል።] አጿጿሙን በተመለከተ:- ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል:- (( لَئِنْ بَقِيتُ إِلَى قَابِلٍ لَأَصُومَنَّ التَّاسِعَ )) ، أخرجه مسلم “ወደፊት ከቆየሁ ዘጠነኛውንም (ቀን) እፆማለሁ።” [ሙስሊም ዘግበውታል።] በዚህ መሰረት ዘጠነኛውንና አስረኛውን ቀን እንፆማለን ማለት ነው። ይህም ከምንም አይነት ጭቅጭቅ ነፃ የሆነው አጿጿም ነው። 10ኛው እና 11ኛው??? ዘጠነኛው ቀን ያመለጠው 10ኛውን እና 11ኛውን መፆሙን በተመለከተ ግን የተወሰኑ ጭቅጭቆች አሉበት። እንደ ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) ያሉ ሊቃውንቶች 10 እና 11 መፆም ይቻላል ሲሉ የሚከተለውን ሀዲስ ማስረጃ ያደርጋሉ:- (صُومُوا يَوْمَ عَاشُورَاءَ ، وَخَالِفُوا فِيهِ الْيَهُودَ ، صُومُوا قَبْلَهُ يَوْمًا أَوْ بَعْدَهُ يَوْمًا). رواه أحمد في مسنده “የዓሹራን ቀን ፁሙ፣ አይሁዶችን በመቃራንም ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድ ቀን ፁሙ።” ኢማሙ አሕመድ በሙስነዳቸው የዘገቡት ሲሆን አልባኒን ጨምሮ ሌሎችም በርካታ ዓሊሞች ዷዒፍ ነው ብለውታል። የዚህን ሀዲስ ዷዒፍነት ያመኑ ዑለማዎች ሆነው ዘጠነኛው ቀን ያመለጠው ሰው 11ኛውን ለመፆሙ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) "በሚቀጥለው ካደረሰኝ 9ኛውን እፆማለሁ።” ማለታቸው፣ ምክንያቱ ለ11ኛው ቀንም ይሆናል። ይላሉ፣ 9ኛውን ቀን እፆም ነበር ያሉበት ምክንያቱ አይሁዶችን ለመቃረን ነውና። 9ኛውን እና 10ኛውን ቀን ብቻ መፆም ነው፣ 9ኛው ካመለጠ ደግሞ 10ኛውን ብቻ መፆም ነው እንጂ 11ኛው የለም የሚሉት ደግሞ፣ "9ኛውን ቀን እፆም ነበር" ያሉበት ምክንያት አይሁዶችን ለመቃረን ቢሆንም  11ኛውን ለመፆም ማስረጃ አይሆንም ብለዋል። 1ኛ, ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በወቅቱ 10ኛውን ፆመው ነው ያቆሙት እንጂ 11ኛውን አልፆሙም። 2ኛ, በሚቀጥለው ካደረሰኝ 9ኛውን ወይም 11ኛውን እፆማለሁ ሳይሆን ያሉት 9ኛውን ብቻ ነው ከ10ኛው ጨምረው እንደሚፆሙት የተናገሩት። በነዚህ ምክንያቶች አንድ ሰው 9ኛው ካመለጠው 10ኛውን ብቻ ነው የሚፆመው ይላሉ። እንደ ማስረጃው አመዛኝነት ግን ከጭቅጭቁ ለመውጣትም በተቻለ መጠን 9ኛው እንዳያመልጥ ጥረት አድርጎ 9 እና 10 መፆም፣ 9ኛው ካመለጠ ግን ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ንም 9ኛው አምልጧቸው 10ኛውን ብቻ ስለ ፆሙ 10ኛውን ብቻ መፆም ነው። ወላሁ አዕለም!! የዓሹራ ቀን ቢድዓዎች። ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:- “መኳኳልን እና መጋጌጥን፣ በቀኑ ለየት ያለ ሶላትን መስገድም ሆነ ሌሎች ለየት ያሉ ተግባሮችን በላጭነት አስመልክተው የመጡ ሀዲሶች በጠቅላላ ዷዒፍ ናቸው። የዚያን ቀን ከመፆም ውጭ ሌሎችን ነገሮች የሚጠቁም አንድም ትክክለኛ ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የተረጋገጠ ሀዲስ የለም። "የዓሹራ ቀን ባለው አቅም ሰፋ አድርጎ ያመቻቸ ሰው፣ የሌሎችንም አመታት አላህ ሰፋ ያድርግለት።” የሚለው ሀዲስ ኢማሙ አሕመድ ሶሂህ አይደለም ብለውታል። የዚያን ቀን እለቱን አስመልክቶ መኳኳል፣ መቀባባት፣ ሽቶ መጠቀም፣ ውሸታሞች ያስቀመጡትና ሌላውም ተቀብሏቸው ከሀዘን ወደ ደስታ የሽግግር ቀን ብለው መጋጌጫ አድርገው የያዙት ነው። ይህን ያደረጉት ሙብተዲዕና ከአህሉ ሱንና ያፈነገጡ ጭፍሮች ናቸው። አህሉ ሱንናዎች ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ያዘዙበትን የሚፈፅሙና ሸይጧን ያዘዘበትን ቢድዐ የሚጠነቀቁ (የሚርቁ) ናቸው።” [አልመናር አልሙነይፍ ፊ ሶሂሂ ወዷዒፍ 89] የሳዑዲ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴም "ይህን ቀን በመጋጌጥም ሆነ በምግብ ለየት ማድረግ አይፈቀድም። እንዲሁም ሺዓዎች እንደሚያደርጉትም የሀዘን ቀን አድርጎ ራስን በስለት መሰል ነገር መጉዳት አይፈቀድም። በዚያን ቀንም ሆነ በሌሎች ቀኖች ፋጢማን መለመን አይፈቀድም፣ በተውበት እንጂ አላህ ከማይምረው ከትልቁ ሺርክም ነው። ” ብሏል። [ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ ቁ. 22177] ሸይኽ ረቢዕ ቢን ሃዲ ዑመይር አልመድኸሊ (ሀፊዘሁላህ) በዚያ ቀን ለዕለቱ ብሎ ለየት ያለ ምግብ አዘጋጅቶ መብላት ይፈቀዳል ወይ? ተብለው ተጠይቀው፣ ሲመልሱ:- "በዓሹራ ለየት ያለ ነገር መዘጋጀት አለበት፣ ወደ አላህ ያቃርባል የሚል እምነት ኖሯቸው ከሆነ የሰሩት ይህ ቢድዓ ነው። ባረከላሁ ፊኩም።” ብለዋል። በሀገራችን በዚህ ቀን የተለያዩ ቢድዐዎች በተለይ ሱፊዮች ዘንድ ይፈፀማልና በዚህ ቀን ከፆም ውጪ ምንም አይነት ለየት ያለ ተግባር እንደሌለ አውቀን ከተለያዩ ቢድዐዎች ተጠንቅቀን ልናስጠነቅቅ ይገባል!!። ✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) #Join ⤵️  የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
Mostrar todo...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

👉 ዓሹራእና ምንዳውዓሹራእ ማለት የሙሐረም ወር 10ኛ ቀን ሲሆን ከነብዩላሂ ሙሳ አስገራሚ ታሪኮች አንዱን የሚያስታውሰን ቀን ነው። ➧ ነብዩላሂ ሙሳ ፊርዓውን ህፃናቶችን በሚያርድበት ዘመን ተወልደው በራሱ ቤት እንዲያድጉ አላህ ያሻውን ሰሪ የሆነው ጌታ አደረገ። ይህም ፊርዓውን በይተል መቅዲስ አካባቢ የተነሳ እሳት የግብፅን ምድር ሲያጠፋ በህልሙ ያይና ለጠንቋዮቹና ድግምተኞቹ ሲነግራቸው ከእስራኤላዊያን የሚወለድ ህፃን የንግስናው  መጥፊያ ሰበብ እንደሚሆን ነግሩት። ፊርዓውንም ከሚወለዱት ህፃናት ሴቶቹ ቀርተው ወንዶቹ እንዲታረዱ አዘዘ።ይህ ነገር አገልጋይ እንዳያሳጣቸው የፈሩት ግብፃዊያን ፊርዓው ዘንድ ሄደው አቤቱታ ሲያቀርቡ አንድ አመት የሚወለደው ተትቶ በሌላኛው አመት የሚወለደው እንዲታረድ አዘዘ። የአላህ ፍላጎት ሆነና ነብዩላሂ ሙሳ ወንድ ህፃናቶች በሚታረዱበት አመት ተወለዱ። የእስራኢላዊያን ህፃናት መወለድ የሚጠባበቁ ሰራዊቶች በመኖራቸው የነብዩላሂ ሙሳ እናት ጊዜዋ በመድረሱና አመቱ ወንድ ህፃናት የሚታረዱበት በመሆኑ ጭንቅ ውስጥ ገባች። የተፈራው አልቀረም ህፃኑ ተወለደ። እናት ምን ይዋጣት!!!? ↪️ አላህ ሁሉን ቻይ መሆኑን ሊያሳያት በሳጥን አድርገሽ ወደ ቀይ ባህር ወርውሪው የሚል መልእክት እንዲመጣላት አደረገ። ወረወረችውም። ወደ አላህም ፍፁም ተማፀነች። አላህም ልጇን እንደሚመልስላት ቃል ገባላት። ባህሩ ሳጥኑን ወደ ፊርዓውን ቤተመንግስት እየነዳ አደረሰው። የፊርዓው አገልጋይ ሴቶች ሳጥኑን አገኙት ሲከፍቱት የሚያምር ህፃን ነው!!!። ወደ ቤተመንግስት ተወሰደ። ኣሲያ የፊርዓው ባለቤት የአይናችን ማረፊያ ይሆናል ልጅ አድርገን እንያዘው አትግደለው አለችው ተቀበላት።     ➲ ረሃብ ይዞት ሲያለቅስ የሚቀርብለት ጡት በሙሉ እንቢ አለ። ምናልባት የሚስማማው ጡት ከተገኘ ብለው ሴቶችን ሲፈለጉ እህታቸው ማንነቷን ደብቃ አንድ ህፃናት በሙሉ ጡቷን የሚጠቡላት ሴት ላመላክታችሁ ወይ ብላ ጠየቀች አው አሉ። እናታቸው ወደ ቤተመንግስት መጣች!!!። ሱብሃናላህ በፊርዓውን ቤተመንግስት በእሱ ተንከባካቢነት በእናታቸው ጡት እንዲያድጉ አላህ አደረገ። በወቅቱ እስራኤላዊያን በቂብጦች የመከራ ገፈት ይጎነጩ ነበር። አላህ በሙሐረም 10ኛ ቀን ፊርዓውንን ከነሰራዊቱ አጥፍቶ እሳቸውንና ህዝቦቻቸውን ነጃ አወጣ። የአላህ መልእክተኛ ነብዩ ሙሐመድ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – ወደ መዲና ሲሄዱ አይሁዶች ይህን ቀን ሲፆሙ አገኙዋቸው። ለምንድነው የምትፆሙት ብለው ሲጠይቁዋቸው ይህ ቀንማ አላህ ፊርዓውን አጥፍቶ ሙሳን ያዳነበት ቀን ነው። ለዚህ ነው የምንፆመው አሉዋቸው። እሳቸውም ለሙሳማ እኔ ከናንተ የቀረብኩኝ ነኝ ብለው መፆም ጀመሩ ተከታዮቻቸውንም እንዲፆሙ አዘዙ። ያለውንም ምንዳ ሲናገሩ እንዲህ አሉ:– "صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ وَصِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ"     رواه مسلم   ( 1162). "የዓረፋ ቀንን መፆም ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። የዓሹራእ ቀንን መፆም ደግሞ ያለፈውን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።" ♻️ አዩዶችን ለመኻለፍ አላህ ካቆየኝ የሚመጣውን አመት ዘጠነኛውን የሙሐረም ቀን እፆማለሁ ብለው ነበር። ከዚህ በመነሳት የሙሐረምን ዘጠነኛና አስረኛ ቀን መፆም ይወደዳል። አብዛኛዎች ፉቀሃዎች ዘጠነኛ አስረኛና አስራ አንደኛውን ቀን መፆም ሱና ነው ይላሉ። ነገር ግን ከመረጃ አንፃር ዘጠነኛና አስረኛው ነው። ይህ ካልተቻለ አስረኛና አስራ አንደኛውን በመፆም አይሁዶችን መኻለፍ ይቻላል።         አላህ ይወፍቀን። ከተወሰነ ማስተካከያ ጋር በድጋሚ የተለቀቀ። http://t.me/bahruteka
Mostrar todo...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

የሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) አጭር የሕይወት ታሪክ:(pdf)
ሷሊሃ የሆነችዋ የፊርዐውን ሚስት ኣሲያህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) አሳማሚ ቅጣትና አማሟቷ: ነቢ ሙሳ ❨ዐለይሂ ሰላም❩ ይዘው የመጡትን ጥሪ ሳታንገዳግድ ሙሉ በሙሉ ተቀበለች፣ወደ እስልምናም ሙሉ በሙሉ ገባች፣ እንደታዘዘችው አላህንም ተገዛች፣ባለቤቷ ግን ጨካኝ፣ አረመኔ፣ አምባገነን፣እብሪተኛ... እና በመሬት ላይ እየኮራ የሚሄድ ሰው ነበር። አምባገነኑ ፊርዐውን እሷ (ኣሲያ) እስልምናን መቀበሏን ካወቀ በኃላ አሳማሚ የሆነ ቅጣት ሲቀጣት የነበረ አረመኔ ሰው ነበር። የሱ ቅጣት እሷን ለሞት አበቃት። የገደላት አገዳደል አጅግ በጣም አስከፊና አስቀያሚ በሆነ ሁኔታ ነበር የገደላት፤ነገር ግን እሷ ከትክክለኛው አቋሟ «ፍንክች» አላለችም ነበር። አስከ መጨረሻ እስትንፋሷ ደረስ በእስልምናዋ ለይ ጸናች። ፊርዐዉን ኣሲያን ሲያሰቃያት እንዲህ ነበር ያደረጋት፡ በጠራራ ፀሃይ ሜዳ ላይ አውጥቷት ትከሻዋን፣እግሯን፣እጇን...በብረት ሚስማር ወጥሯት ትቷት ሄደ። በጠራራ ፀሃይ ወጥሯት ከሄደ በኃላ በዛችኑ ቅፅበት ኣሲያህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ ነበር ያለችው፦«ጌታዬ ሆይ! አንተ ዘንድ በጀነት ውስጥ ለእኔ ቤትን ገንባልኝ፡፡ ከፊርዐውንና ከሥራውም አድነኝ፡፡ ከበደለኞቹ ሕዝቦችም አድነኝ» ይህንን ዱዓ ካደረገች በኃላ መላኢካዎች መጡ። በክንፋቸውም አጠለሏት (ክንፋቸውን ጥላ አደረጉላት) አላህ ጀነትን ከፈተላት!!!፣በጀነት የተገነባላትን ቤቷንም አሳያት። ረሡል (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦ "ከሴቶች በኩል እነኝህ አራቶቹ ብቁ ናቸው፡ መርየም ቢንትዒምራን፣ኸዲጃህ ቢንት ኹወይሊድ፣ ፋጢማህ ቢንት ሙሐመድ እና ኣሲየህ የፊርዐውን ሚስት። (ከፒዲኤፉ) 📝 አዘጋጅ: ሸይኽ አቡ ኸዲጃ (ሀፊዘሁሏህ) 📝 ትርጉም: አቡ ሀፍሳህ https://t.me/semirEnglish
Mostrar todo...
_ሙሳ_ዐለይሂ_ሰላም[1].pdf1.80 MB
👉 አዲስ pdf 👉 40 ሐዲሶች عنوان: الأربعون المكية في التوحيد والسنة .pdf ርእስ:- አርባዎቹ መኪይ (መካ ላይ የተዘጋጁ) በተውሒድና በሱንና ላይ የሚያተኩሩ ሀዲሶች بقلم الشيخ الدكتور حسين بن محمد بن عبد الله السلطي حفظه الله ✍🏻አዘጋጅ:- ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ኢብኑ ሙሀመድ ኢብኑ ዐብደላህ አስ-ስልጢ (ሀፊዘሁላህ) ከሳዑዲ ዐረቢያ መከህ ቴሌግራም ቻናል ⤵️ https://t.me/HussinAssilty 🔹እነዚህ በተውሒድና በሱና ላይ የሚያጠነጥኑ ከሶሂህ ሀዲስ የተውጣጡ ለጀማሪ ተማሪዎች ለሽምደዳ የሚቀሉ ወሳኝና አንገብጋቢ ሀዲሶች ናቸው፣ በተለይ በክረምቱ በየ ቦታው የሚያስተምሩ ኡስታዞች ለልጆች እነዚህን ሶሂህ ሀዲሶች ብታሸመድዱ የተመረጣና መልካም ነው። የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
Mostrar todo...
الأربعون_المكية_في_التوحيد_والسنة_للحفظ.pdf7.17 KB
Photo unavailableShow in Telegram
🏝 ❝አስደሳች ዜና❞ 📚 አዲስ ኪታብ በተለይ ለኡስታዞችና ለዲን ተማሪዎች 📖 ⚙️ የታላላቅ መሻይኾች ተማሪ የሆነው ዓሊም ሸይኽ ሑሰይን ቢን ሙሀመድ ቢን ዐብደላህ አል-ኢትዮጲ አስ-ስልጢይ (ሀፊዘሁላህ) ከተዘጋጁ ኪታቦች አንዱ የሆነው « እስልምና ዒሳን {ዓለይሂ ሰላም} ማላቁ እና ከእስልምና ሀይማኖት የመካድ ምክንያቶች» በሚል በዐረቢኛ የተዘጋጀ አዲስ ኪታብ በቅርቡ ገበያ ላይ ይውላል ኢንሻ አላህ!!! 📮 📔 تعظيم الإسلام لعيسى عليه السلام وأسباب الارتداد عن دين الإسلام 📝 إعداد وجمع:-             🔑 الشيخ حسين بن محمد بن عبد الله الإتيوبي السلطي 📝  አዘጋጅ:- ሸይኽ ሑሰይን ቢን ሙሀመድ ቢን ዐብደላህ አል-ኢትዮጲ አስ-ሲልጢይ (ሀፊዘሁላህ) የኪታቡን PDF ለማግኘት https://t.me/shakirsultan/1860 📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ 👇👇👇 🌐 https://t.me/shakirsultan
Mostrar todo...
ሰምንተዊ የቁሪአን ተፊስር ልጀምር ነዉ ገባ        ገባ                 በሉ https://t.me/abuhatimaselefiy
Mostrar todo...
Abu hatim Abduselam Aselefiy

ትክክለኛው እስላማዊ አስተምህሮ ከቁርአንና ከሐዲስ ከደጋግ ቀደምቶች አረዳድ ከታማኝ ዑለሞች ንግግር የሚሰራጭበት ቻናል ነው።

1
ሸይኹ ለኡማው ካበረከቱት ኪታቦች መካከል በጥቂቱ እነሆ፡ [1]: ኪታብ አት-ተውሒድ [2]: ኪታብ አል-ከባኢር [3]: ከሽፍ አሽ-ሹብሃት [4]: ሙኽተሰር ሲረት አር-ረሱል [5]:መሳኢል አል-ጃሂሊየህ [6]: ኡሱል አል-ኢማን [7]: ፈዳኢል አል-ቁርኣን [8]: ፈዳኢል አል-ኢስላም [9]: መጅሙዕ አል-አ'ሃዲስ [10]: ሙኽተሰር አል-ኢንሳፍ ወ-አሽ-ሸርህ አል-ከቢር [11]: አል-ኡሱል አስ-ሰላሰህ [12]: ኣዳብ አል-መሻኢል አስ-ሶላት....የመሳሰሉ ኪታቦችን አበርክተው ከዚህ ዓለም ተለይተዋል። ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) እስከመጨረሻው አስትንፋሳቸው ደረስ ከደርዒያው አስተዳደር እንዲሁም ከሙሐመድ ብን ሰዑድና ልጁ...ከሸይኹ ጎን በመቆም ለተውሒድ ትልቅ የሆነን ዋጋ ከፍለዋል። በመጨረሻም፣ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) ከዚች ዓለም በመሞት የተለዩት በሒጅራው ቀመር አቆጣጠር፣በዙል ቀዕዳ በመጨረሻው ዕለት፣1206 ዓመተ ሒጅራ ላይ ነበር። ባጭሩ የሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) አጭር የሕይወት ታሪክ ይህን ይመስል ነበር። አላህ ተጠቃሚዎች ያድርገነ!!!!!!! @semirEnglish @semirEnglish
Mostrar todo...
👍 2
የሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) አጭር የሕይወት ታሪክ:
ክፍል-2 (የመጨረሻው ክፍል) ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) የዑወናው አስተዳደር አቀባበል ካደረገላቸው በኃላ፣ሸይኹ በከፍተኛው ሞራልና ትግል ዳዕዋቸውን በቁርጠኝነት ቀጠሉ። ዑወይነህ ላይ ሲፈፀሙ የነበሩ አስቀያሚ ሽርኪያቶች ሸይኹ ሰበብ በማድረሳቸው በአላህ ፍቃድ ሊጠሩ ችለዋል። እዛው ዑወይነህ ከተማ ውስጥ ሸይኹ ከመሄዳቸው በፊት፣ መቃብሮች፣ዋሻዎች፣ዛፎች...በሙስሊም ተብዬዎች ይመለኩ ነበር፤ሆኖምግን በዑወይነህ አስተዳደር አሚር ዑስማን ቢን መ'ዕመር...ከሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) ጎን በመሰለፍ የተለያዩ የባዕድ አምልኮ ተግባራትን በአላህ ፍቃድ ሊያስወግዱ ችለዋል። ይህ ደግሞ የሆነው፣ዑወይነህ ከተማ ብቻ ሳይሆን ዙሪያውን ጭምር ነው። ይህ በንዲህ እንዳለ፣በዑወይነህ ከተማ ውስጥ የእስልምና ህግጋት ተግባራዊ መሆን ጀመሩ። ለአብነት ያክልም...አንዲት ባለትዳር ሆና ዝሙት የፈፀመች ሴት ኢስላማዊ ህግጋት በሷ ላይ ተግባራዊ አንዲሆን ሸይኹን መጥታ ጠይቃለች። ዝሙት የፈፀምችው ሴትዮዋ ኢስላማዊ ህግጋት በሷ ላይ ተግባራዊ ኢንዲሆን መጠየቋን ተያይዞ፣ ስለ ሁኔታዋ፣ማለትም ጤነኛ ነች ወይ? ተገዳ ነው ወይ? የሚሉ ምርመራዎች ከተካሄዱ በኃላ፣እንዲሁም ወንጀሉ ከተረጋገጠ በኃላ፣ ሸይኹ ተወግራ እንድትገደል አዘዙ። የሸይኹ ዝናና ጀብድ በተለያዩ ከተሞች እየተስፋፋና እየተሰራጨ መሄድ ጀመረ። ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) "የዑወይነህ" ቆይታቸውን ካጠናቀቁ በኃላ፣ "ደርዒየህ" ወደ ተሰኘች ከተማ አቀኑ። ሸይኹ ወደ "ደርዒየህ" ማቅናታቸውን ከታወቀ በኃላ፣የአል-አህሳ አስተዳደርና እንዲሁም ብን ሱለይማን የሸይኹን ገናናነት እና ተፅኖ-ፈጣሪ መሆናቸውን ለመለየት በህዝብ መካከል ሆኖ ይከታተል ነበር። ሁኔታው አጅግ በጣም አስፈራው፤ምክንያቱም ስልጣኔ ይነጠቃል የሚል ስጋትም ጭምር አደረበት። ይህ ሱለይማን የተባለው ግለሰብ፣ለአሚር ዑስማን ስጋቱን በመግለፅ ሸይኹን እንዲገላቸው ጥያቄ አቀረበ፤ይሁንእንጂ አሚር ዑስማን የሱለይማንን ጥያቄ ለመቀበል ፍቃደኛ አንነበሩም። ሱለይማን የአሚር ዑስማንን አቋም ከተረዳ በኃላ ተሸበረ፣ተጨነቀ፣ምድር ሰፊ ከመሆኗም ጋር ጠበበችው....አሚር ዑስማን ሸይኹን ተቀበሏቸው፤ በግዛቱ የፈለጉበት ቦታ መንቀሳቀስ እንደሚችሉ አስረግጦ አሳውቋቸው። የደርዒየህ ነዋሪዎችና ህዝቦች የሸይኹን የተውሂድ ተልእኮ ተረዱ። የደርዒያው አስተዳዳሪ አሚር ሙሐመድ ብን ሰዑድ፣ ሸይኹ ወደ ግዛቱ ስለገቡ በእጅጉን ተደሰተ። አስተዳዳሪው ቀጥታ ሸይኹ የሚገኝበት ድረስ በመሄድ ጉብኝት አድርጓል። በሸይኹ የተውሒድ ጥሪም ተደስቷል። ከሸይኹም ጋር የሃሳብ ልውውጥ አድርጓል። አሚር ሙሐመድ ብን ሰዑድ ለሸይኹ ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ቃል ገባላቸው። ሸይኹም ለአሚሩ ዱዓ አደረጉለት። ሸይኹ ይህንን ወርቃማ የሆነውን አጋጣሚ በመጠቀም፣አያሌ የሆኑ ህዝቦችን ማስተማር ጀመሩ። የደርዒየህ እና አካባቢዋ በተውሂድ ተናወጠች፤የተውሂድ ሰንደቅዓላማ መውለብለብ ጀመረ... ምን ይሄ ብቻ የደርዒያው ዋና አስተዳዳሪ አሚር ሙሐመድ እራሱን እና ቤተሰቦቹን ይዞ እንደተማሪ ሆኖ በመቅረብ፣ ከህዝቡ ጋር በመታደም የሸይኹን ትምህርቶችን መከታተል ጀመረ። ይህ ዜና በተለያዩ አከባቢዎች ተሰራጨ። ዜናውን የሰሙ ሰዎችም ከበረከቱ ለመቋደስ፣እውቀት ለመቅሰም ወደ ደርዒየህ መሰደድ ጀመሩ። ደርዒየህ የተውሂድ ማዕከል ሆነች። ይህ በንዲህ እንዳለ፣የሸይኹ ጠላቶች በሸይኹ ላይ የተለያዩ ቅጥፈቶችን መንዛት ጀመሩ። ምን ይሄ ብቻ?! ጠንቋይ፣ ድግምተኛ፣ ሙናፊቅ (ዚንዲቅ)...በመሳሰሉ ቃላቶች በሸይኹ ላይ መንዛት ጀመሩ። በተለያዩ የውሸት ቅጥፈቶች ሸይኹን ለማሸማቀቅና ከዳዕዋው ለማሰናከል በሚክሩም፣ሙከራቸው ሳይሳካ ቀርቷል። ሸይኹ የተቺ ተቺዎች ሴራ ሳይበግራቸው ተልዕኮውን ቀጠሉ። በል እንዳውም ተቃራኒ ከሆኑ አካላቶች ጋር ጨዋነት በተሞላበት ስልት ተከራክረዋል። ከዚህም በተጨማሪ፣ከተለያዩ ከአረብ ደሴት (Arabian peninsula) የመጡ የተለያዩ ልዑካን ቡድኖችን ትክክለኛው የተውሒድ ጥሪ ካደረጉላቸው በኃላ፣ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ህዝባቸውን ወደ ተውሒድ እንዲጠሩ አጥበቀው መክረዋል። ሸይኹ በዚህም ብቻ አላቆሙም ለአረብ ደሴት መሪዎችና ሊቃውንቶች ደብዳቤዎችነ ፃፉ። የደብዳቤው ዋና መልእክት ሽርክን እንዲሁም ኢስላም የማያውቀው ባዕድ የሆኑ አምልኮዎችን ህዝባቸውን እንዲታደጉ ነበር። ሸይኹ ደብዳቤዎችን የፃፉት ለነጅድ፣ ሪያድ፣ኸርጅ፣ ቀሲም፣ሀዬል፣ወሽም፣ ሱደይር፣አህሳ፣ መካ፣ መዲና፣ የመን...ለመሳሰሉት ሀገራቶች ፅፈው ነበር። ልብ ይበሉ! ደብዳቤው የተፃፈው በሀገሩ ለሚገኙ አስተዳደር እና ዑለማች ነው። ሸይኹ አሁንም በዚህ አላበቁም፤ከአረብ ደሴት ውጭ ለሆኑ ሀገራትም ደብዳቤዎችን ፅፈዋል፤ለምሳሌ፡ ለነ ሶሪያ፣ ኢራቅ፣ሕንድ...ለመሳሰሉት ሃገራት በደብዳቤ የዳዕዋ ጥሪ አቅርበዋል። ሸይኹ ቁርኣንና ሱንናን አብራርተዋል። ምስጋና ለአላህ የተገባ ይሁንና ዳዕዋቸው ግብ መቷል። የሸይኹን ዳዕዋ ከተቀበሉ ሀገራቶች መካከል፡ ሕንድ፣ኢንዶኔዥያ፣አፍጋኒስታን፣አፍሪካ፣ሞሮኮ፣ግብፅ፣ሶሪያ...የመሳሰሉ ሀገራቶች የሸይኹን ዳዕዋ በመቀበል ትልቅ ተፅዕኖ አድሮባቸዋል። ይህም ብቻ ሳይሆ ከሸይኹ ጎንም ጭምር ተሰልፈዋል። ሸይኹ በሒጅራው ቀመር አቆጣጢ ከ"1158" እስከ "1206" ባሉት ጊዜያት ውስጥ ትልቅ የሆነ ተግል በማድረጋቸው አመክንዮ፣ በነጅድ ሙሉበሙሉ በሚባል ደረጃ አላህ ሸይኹን ድል አጎናፀፋቸው። ሰዎች ዶሪህን፣ ቀብርን፣ እንጨትን፣ዛፍን...ማምለክ ተው። ጭፍን ተከታይነት ሚባል ነገር ጠፋ። ይህ ባህል ነው፣የአባቴ መንገድ ነው፣የአያቴ መንገድ ነው...ከማለት ሰዎች ተወገዱ። ጥርት ወዳለው እስልምና ገቡ። አላሁ አክበር ዲን እንደገና ሕያው ሆነ። ቁርኣንና ሱንና በሰዎች ላየ ተንፀባረቀ። በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል ተግባራዊ ስራ ሆኖ ቀጠለ፤ መስጂዶች ውስ ሰዎች ሞልተው መስገድ ጀመሩ። በሀገሪቷ ሰላምና መረጋጋት ሰፈነ። ገጠሬዎችም ከተሜዎች...በሰላም መኖር ጀመሩ። የተውሒድ ሰንደቅዓላማ ተውለበለበ። ከሸይኹ እወቀትን የቀሰሙ አካላቶች በመላው ዓረቢያ ደሴት የተውሒድ ተልዕኮን ይዘው ተሰሬጩ። ሸይኹ በሕይወት ካለፉ በኃላም ልጆቻቸው እና ተማሪዎቻቸው ዳዕዋውን በአላህ ፍቃድ ማስቀጠል ችለዋል። ከልጆቻቸው መካካል ዳዕዋውን ካስቀጠሉ እንደነ፡ ሸይኽ ኢማም ዐብዱሏህ ብን ሙሐመድ፣ ሸይኽ ሑሰይን ብን ሙሐመድ፣ ሸይኽ ዐሊይ ብን ሙሐመድ፣ሸይኽ ኢብራሂም ብን ሙሐመድ....ይገኙበታል። ከሸይኹ ከልጅ ልጆቻቸው መካከል ደግሞ፣ሸይኽ ዐብዱር-ረሕማን ብን ሐሰን፣ሸይኽ ዐሊይ ብን ሑሰይን፣ሸይኽ ሱለይማን ብን ዐብዱሏህ... ይገኙበታል። ከተማሪዎቻቸው መካከል ደግሞ፡ እንደነ ሸይኽ ሐምድ ብን ናሲር...የመሳሰሉ ይገኙበታል። ሸይኹል ኢስላም ሙሐመድ ብን ዐብዱል-ወ'ሓብ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) ለዚህ ኡማ ትልቅ የሆነን አሻራ ጥለው አልፈዋል። ለዚህም ነው ሰዎች በሺርክና በተለያዩ ባዕድ በሆኑ አምልኮ ተጨማልቀው ሳለ፣ በአላህ ፍቃድ ሸይኹ ትግል አድርገው፣የአንበሳውን ድርሻ ተጫውተው ነው ከዚች ዓለም ያለፉት።
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.