cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

kehulum bota ከሁሉም ሰብሰብ

እዚህ ቻናልላይ ምንም የምናጣው መረጃ የለም. ፖለቲካ, ስፖርት, ድንቃድንቅ, እንዲሁም አገረኛ ወሬዎችን እናናፍስበታለን! ብቻ ከናንተ የሚጠበቀው በመቀላቀል ቤተሰብ መሆን ነው!

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
194
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
አንድ ፈረስ ብቻ የነበረው አንድ ገበሬ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን፥ ፈረሱ ለግሞ ከቤቱ ያመልጣል። ጎረቤቶቹም እቤቱ መጥተው “ፈረስህ መጥፋቱንና ማዘንህን ሰማን። ልናፅናናህ መጥተን ነው።” አሉት። ገበሬውም “ አላዘንኩም! ለበጎ ነው” አላቸው። ከጥቂት ቀናት በኋላ ፈረሱ ከጠፋበት ቦታ ብዙ ወርቅና ማዕድናት፥ አስለምዶ ከጫነው ሰው አምልጦ ገበሬው ጋ ይመለሳል። ጎረቤቶቹ ወደ ቤቱ መጥተው "እንኳን ደስ አለህ። ፈረስህ ብዙ ወርቅና ብር ይዛልህ በመምጣቱ እንደተደሰትክ ሰምተን መጣን። " አሉት። እሱም "ብዙም አልተደሰትኩም። ለበጎ ነው!" አላቸው። ከጥቂት ጊዜም በኋላም ፈረሱ የብቸኛ ወጣት ልጁ እግር በርግጫው ይሰብረዋል። ጎረቤቶቹም አሁንም መጥተው " የልጅህ እግር መሰበር አይተህ እንዳዘንክ ሰምተን ልናፅናናህ መጣን። " አሉት። እሱም በመቀጠል እንዲህ አላቸው "ብዙም አላዘንኩም። ለበጎ ነው!" ከጥቂት ቀናት በኋላ በሀገሪቱ ከፍተኛ ጦርነት ተከፍቶ፤ ሁሉም ጤነኛ ወጣት በግዴታ እንዲዘምት አዋጅ ተላለፈ። የጎረቤቶቹም ልጆች ሲዘምቱ፤ የእርሱ ልጅ እግሩ ስለተሰበረ ከዘመቻው ይቀራል። ከጥቂት ቀናት በኋላ ጦርነቱ አለቀ። ከጦርነቱ የተረፈ አንድም ወጣት አልነበረም። ጎረቤቶቹም ልጆቻቸው መሞታቸው ተነገራቸው። ገበሬውም ወደ ሰማይ አንጋጦ "የልጄ እግር መሠበር ለበጎ ሆነለት። ተመስገን!" አለ። ወዳጄ፦ በነገር ሁሉ 'ሁሉም ለበጎ ነው!' በል። መልካም ቀን
Mostrar todo...
በሰው ተስፋ አትቁረጥ “You must not lose faith in humanity. Humanity is an ocean; if a few drops of the ocean are dirty, the ocean does not become dirty”—Mahtama Gandih   #ምናልባት ሰዎች በድለውህ ፤ አልያም አስከፍተውህ ሊሆን ይችላል ። ማን ያውቃል ያመንከው ከድቶህ ፤ የጠበቅከው እረስቶህ ፤ ተስፋ የጣልክበት ጥሎህ ሊሆንም ይችላል ። ወይም ደግሞ የእለቱን ዜና ስትሰማ ፤ ሰው በሰው ሲጨክን ስታይ እውነት መልካም ሰዎች ይኖሩ ይሆን ብለኽ አስበህ ሊሆንም ይችላል ። .... ማን ያውቃል ከልብህ ወደህ ልብህን የሰጠኸው ሰው ፤ ልብህን የጣለበት ጠፍቶት ሌላ መውደጃ ልብ አጥተኽ ይሆናል ። ..... ደግመህ ለመውደድ አትፍራ ፤ ደግመህ ይቅር ለማለት አትስጋ ፤ የዋህ መሆንህን አትጥላው ። አለምን በርቀስ አርገን ብናያት ፤ ማመን ከሚከብደን በላይ መልካም ሰዎች አሏትና ። “አለም ልክ እንደ ውቂያኖስ ናት ፤ ጥቂት የክፉ ሰዎች ጠብታ ስላለባት ብቻ ውቂያኖሱ ተበክሏል ብለህ ፤ ተስፋ አትቆረጥ ።” መልካም ምሽት t.me/kehulum_bota!!
Mostrar todo...
kehulum bota ከሁሉም ሰብሰብ

እዚህ ቻናልላይ ምንም የምናጣው መረጃ የለም. ፖለቲካ, ስፖርት, ድንቃድንቅ, እንዲሁም አገረኛ ወሬዎችን እናናፍስበታለን! ብቻ ከናንተ የሚጠበቀው በመቀላቀል ቤተሰብ መሆን ነው!

ሰላም የተከበራችሁ የዚህ ቻናል ተከታታዮች. we come back! t.me/kehulum_bota
Mostrar todo...
kehulum bota ከሁሉም ሰብሰብ

እዚህ ቻናልላይ ምንም የምናጣው መረጃ የለም. ፖለቲካ, ስፖርት, ድንቃድንቅ, እንዲሁም አገረኛ ወሬዎችን እናናፍስበታለን! ብቻ ከናንተ የሚጠበቀው በመቀላቀል ቤተሰብ መሆን ነው!

#ስለ_ወደድኩት ተጋሩልኝ: 😋😋😋፨   አራቱ ሻማዎች ፨ “በአንድ ቤት ውስጥ አራት ሻማዎች በርተው ይታዩ ነበር ፡፡ “ እነዚህ አራት ሻማዎች በሹክሹክታ ይጨዋወታሉ ፡፡ አንደኛው እንዲህ አለ” እኔ ሰላም(PEACE) ነኝ ማንም ግን እንዳበራ የሚፈልግ የለም፡፡ስለዚህ መሄድ አለብኝ “ ወዲያው ነበልባሉ ቀንሶ ሙሉ ለሙሉ ጠፋ ፡፡ ሁለተኛው ሻማ “ እኔ እምነት(FAITH) ነኝ ፡፡ አብዛኛው ጊዜ እታመማለሁ ፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ አላስፈልግም ፡፡ በመሆኑም እየበራሁ መቆየቴ ዋጋ የለውም ፡፡ ” ይህን እንደተናገረ ወዲያው ንፋስ ነፍሶ አጠፋው ፡፡ በተራው ሶስተኛው ሻማ በሀዘን ይናገራል ። “እኔ ፍቅር(LOVE) ነኝ ፡፡ በርቼ ለመቆየት ብርታቱ የለኝም ፡፡ ሰዎች እኔን ጠቀሜታ ወደ ጎን ብለውታል ። አጠገባቸው ያሉትን መውደድ ዘንግተውታል፡፡” ብሎ ይጠፋል፡፡ ወዲያው አንድ ልጅ ወደ ቤት ሲገባ ሶስቱ ሻማዎች ጠፍተው ተመለከተ፡፡” ለምን አልበራችሁም …እስከመጨረሻው መብራት ይጠበቅባችኃል!” አለ፡፡ ይህን ብሎ ልጁ ማልቀስ ጀመረ ፡፡ ይህን ጊዜ አራተኛው ሻማ “ አይዞህ እኔ እየበራሁ። እስካለሁ ድረስ ሌሎቹን ሻማዎች ደግመን ማቀጣጠል እንችላለን ፡፡ እኔ ተስፋ(HOPE) ነኝ አለ ፡፡ ልጁ አይኖቹ ብሩህ ሆነው በደስታ ፊቱ ተሞላ ፡፡ የተስፋ ሻማውን አንስቶ የጠፉትን ሶስቱን ሻማዎች (አበራቸው) ፡፡ የተስፋ ነበልባል በጭራሽ ከህይወታችን ውስጥ መጥፋት የለበትም ፡፡ እንዲህ ሲሆን እያንዳንዳችን ተስፋን (HOPE) ፣ እምነትን (FAITH) ሰላምን (PEACE) እና ፍቅርን (LOVE) ማቆየት እንችላለን ። ተስፍ ካጣን ግን ሁሉን ነገር እናጣለን ። ፨ ዙሪያችንን ስንመለከት አብዛኛው ነገር በጭለማ የተዋጠ መስሎ ሊታየን ይችላል ፤ የምንሰማቸው ነገሮች የመንፈስ ስብራት አድርሶብን ይሆናል ፤ ሳቃችንን ከተነጠቅን ቆይተን ሊሆን ይችላል ፤ ነገር ግን ሊነጋ ሲል የበለጠ መጨለሙ አይቀርምና ጭለማው ተገፎ ፣ የወፎቹን የብስራት ዜማ ሰምተን ንጋቱን ለማየት በተስፋ መጠበቁ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነውና ። ፨ በማንኛውም ሁኔታ ብንሆን ተስፋ አንቁረጥ
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
🎯ፑሽ አፕ በ1900ዎቹ መጀመሪያ ላይ ተፈጠረ። ጄሪክ ሬቪላ የተባለ ታጋይ በ1905 ፑሽ አፕ ብለን የምናውቀውን መልመጃ አዳበረ።“ታላቁ ጋማ” በመባልም የሚታወቀው በ5,000 የትግል ግጥሚያዎች አልተሸነፈም። ለስኮትላንድ ንግስት በተከታታይ 5,000 የሂንዱ ፑሽ ​​አፕዎችን በማድረግ የፑሽ አፕ ብቃቱን አሳይቷል። በእንግሊዝ በተካሄደው ኤግዚቢሽንም 10,000 ፑሽአፕ አሳይቷል።💪 እንዴት አደራችሁ ቤተሰቦች 🙏🙏🙏
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ይህንን ያውቃሉ😁 👉 ኮልጌት ስፓኒሽ ቋንቋ ተናጋሪ ሃገራት ውስጥ ተቀባይነት ለማግኘት ተቸግሮ ነበር ። ምክንያቱም ኮልጌት በ ስፓኒሽ "ሂድ ራስህን አጥፋ" ማለት ነው ።😅
Mostrar todo...
መቶ በመቶ እርግጠኛ! አንድ እጅግ በጣም የተራበ ተኩላ አንድን ከጓደኞቿና ከእረኛዋ የተለየች በግ ከሩቅ ተመለከተ፡፡ መልካም ራት እንዳገኘ ቢያስብም ከሩቁ አይታው የመደንበር ምልክት ስላሳየች ቢሮጥ ሊደርስባት እንደማይችል ስላሰበ እያግባባ ርቀቱን ለማሳጠርና በቀላሉ ለመያዝ በሚመቸውና ማምለጥ በማትችልበት ክልል ውስጥ ለመቅረብ አሰበ፡፡ ትንሽ እርምጃ ጠጋ አለና ድምጹን ከፍ አድርጎ፣ “የዛሬ ሁለት አመት በጣም ተዳፍረሽኝ ነበር” አላት፡፡ በጊቱ ለማምለጥ ሲቃጣት “የዛሬ ሁለት ዓመት” በማለት ስለዋሸ አበሳጭቷት፣ “ምንድን ነው የምታወራው፣ የዛሬ ሁለት አመት እኮ እኔ አልተወለድኩም ነበር” አለችው፡፡ ተኩላው እንደገና ትንሽ እርምጃዎችን ከጨመረ በኋላ፣ “ባለፈው አመት የመጫወቻ ሜዳየን ሳር በልተሽ የጨረስሽው አንቺ መሆኑን ሰምቻለሁ” አላት”፡፡ በጊቱ ጊዜ ሳታባክን ማምለጥ እንዳለባት ቢገባትም አሁንም ለዚህ ቅድ ውሸቱ ተገቢውን ምላሽ መስጠት እንዳለባት ስላሰበች፣ “የዛሬ አመት ሳር የሚባል ነገር አልቀመስኩም፣ እሺ!!!” አለችው፡፡ ተኩላው ዓላማው የተሳካለት መሆኑ ስለገባው፣ አሁንም ትንሽ ጠጋ ብሎ፣ “ከስድስት ወር በፊት እኛ ተኩላዎች ብቻ ከምንጠጣበት ምንጭ ተደብቀሽ ስትጠጪ ቆሻሻሽን አራግፈሽ አደፍርሰሽብናል” አላት፡፡ በጊቱም፣ “አሁንስ አበዛው፣ አንድ ጊዜ ጠጋ ብዬ በጩኸት ልክ ልኩን እነግረውና እሮጣለሁ” ብላ በማሰብና የተወሰኑ እርምጃዎችን ጠጋ በማለት፣ “አሁንስ አበዛኸው! የዛሬ ስድስት ወር ገና የእናቴን ጡት በመጥባት ላይ ስለነበርኩ ውኃ መጠጣት አልጀመርኩም” ብላ ጮኸች፡፡ በዚህ ጊዜ በጊቱ ማምለጥ የማትችልበት ቅርበት ውስጥ ራሷን ስላቀረበች ተኩላው ያቀደውን እቅድ ፈጸመ፡፡ አብዛኛው የሕይወት ክስተቶች በመደራደር፣ በመከራረከርና እስከመጨረሻው ሃሳብን በመለዋወጥ ሊያዙ የሚገባቸው የመሆኑ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አንዳንድ ጊዜ ግን ጊዜ ሳናባክን ካልተለየን ራሳችንን ለወጥመድ አሳልፈን የምንሰጠጥባቸው ሁታዎች እንዳሉ ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ •  መቶ በመቶ ማድረግ እንዳለብህና ጊዜውም ትክክለኛ እንደሆነ ያመንክበት ነገር ካለ አታዘግየው፡፡ •  መቶ በመቶ መወሰን እንዳለብህና ጊዜውም ትክክለኛ እንደሆነ ያመንክበት ነገር ካለ አንድ ቀን አታሳድረው፡፡ •  መቶ በመቶ መለየት የሚገባህ ሰው ወይም ሁኔታ እንዳለ ካመንክና ጊዜውም ትክክልኛ እንደሆነ ካመንክ አንድ ቀን አታሳድረው፡፡ •  መቶ በመቶ እንደማያዛልቅህ እርግጠኛ በሆንክበት ስፍራና ሁኔታ ውስጥ ምን ታደርጋለህ? •  እንደማያስቀጥልህና እንደማያዛልቅህ በሚገባ እርግጠኛ ከሆንክበት ሰው ጋር ለምን ትደራደራለህ? መወሰን፣ መውጣት፣ ማቆም ፣ መለየት . . . እንደሚገባህ መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆነህ በመደራደር ያከረምከው ጉዳይ፣ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ሳታስበው መውጣት የማትችልበትን ሁኔታ ፈጥሮ እንደሚቆይህ አትዘንጋ፡፡ ቻናላችንን በመቀላቀል ብርታት ይሁኑን! t.me/kehulum_bota
Mostrar todo...
kehulum bota ከሁሉም ሰብሰብ

እዚህ ቻናልላይ ምንም የምናጣው መረጃ የለም. ፖለቲካ, ስፖርት, ድንቃድንቅ, እንዲሁም አገረኛ ወሬዎችን እናናፍስበታለን! ብቻ ከናንተ የሚጠበቀው በመቀላቀል ቤተሰብ መሆን ነው!

#"የኔልሰን ማንዴላ .. ☞ኔልሰን ማንዴላ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የህግ ትምህርት በሚማሩበት ጊዜ ነጭ ፕሮፌሰር አስተማሪ ነበራቸው ። ስሙም ፒተር ይባላል ።       አንድ ቀን ፕሮፌሰር ፒተር በአንድ ምግብ ቤት ምግባቸውን እየበሉ ሳለ ማንዴላ በአጋጣሚ ምግብ ይዘው ከአጠገባቸው ይቀመጣሉ ። ዘረኛው ፒተርም "አቶ ማንዴላ! አሳማና ወፍ ለመብል አብረው አይቀመጡም!" አላቸው ፣ ብልሁ ማንዴላም " አይጨነቁ ፕሮፌሰር በርሬ እሄዳለሁ" ብሏቸው ሌላ ወንበር ላይ ይቀመጣሉ ። በዚህ የተናደደው ፒተር በሌላ ቀን ቂሙን ሊወጣበት ያስባል።        አንድ ቀንም ፕሮፌሰሩ ክላስ ውስጥ እያስተማሩ .... ►"ማንዴላ በመንገድ ላይ እየሄድክ ሁለት ቦርሳዎችን ብታገኝና በአንደኛው ቦርሳ ብር በሌላኛው ቦርሳ ደግሞ ጥበብ ቢኖር በቅድሚያ የትኛውን ትወስዳለህ?" ብሎ ማንዴላን ጠየቀው ፣ ►ማንዴላም "ገንዘቡን አወስደዋለሁ" ብሎ መለሰለት ። ►ፕሮፌሰሩም በግልምጫ " አንተ ሞኝ ነህ እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ጥበብ ያለበትን ቦርሳ አወስድ ነበር" አለው፣ ►ማንዴላ ፈገግ እያለ" ልክ ነህ ማንም የሌለውን ነው የሚወስደው" አለው ።           በዚህ ሁሉ ነገር የተበሳጨው ፕሮፌሰር ፒተር የማንዴላ የፈተና ወረቀት ላይ 'ደደብ' ብሎ ይፅፋል ። ሌሎች ተማሪዎች የታረመላቸውን የፈተና ወረቀት ሲያዩ ማንዴላ ደደብ የሚለውን ፅሁፍ ከወረቀቱ ላይ አየና ተገረመ ፣ ከዛም ወደ ፕሮፌሰሩ ሄዶ " ይቅርታ ቲቸር ፊርማህን ብቻ ነው ያስቀመጥክልኝ ውጤቴን ፃፍልኝ" @kehulum_bota
Mostrar todo...
"ብርሃንን ወደ ውስጣችሁ አስገቡ ... ህይወት በጣም አጭር ነች : በጣም ጊዚያዊ ነች። እናንተም በመጣላት ታባክኗታላችሁ? ትሞታላችሁ። ይህን እያወቃችሁ ሳለ እንዴት ትጣላላችሁ...?" 👍👍👍 t.me/kehulum_bota
Mostrar todo...
kehulum bota ከሁሉም ሰብሰብ

እዚህ ቻናልላይ ምንም የምናጣው መረጃ የለም. ፖለቲካ, ስፖርት, ድንቃድንቅ, እንዲሁም አገረኛ ወሬዎችን እናናፍስበታለን! ብቻ ከናንተ የሚጠበቀው በመቀላቀል ቤተሰብ መሆን ነው!

.............................. . ...................... አንዴ አንድ ሰው ሰዎች በተሰበሰቡት መድረክ ላይ ይወጣና አንድ ቀልድ ይነግራቸዋል፡፡ሁሉም ይስቃሉ፡፡ሳቁ እንዳባራ እንደገና ለሁለተኛ ግዜ ያንኑ ቀልድ ይደግምላቸዋል፡፡አሁን የተወሰኑት ብቻ ይስቃሉ፡፡መሳቅ እንዳቆሙ ደግሞ ለሶስተኛ ግዜ ያንኑ ቀልድ ደገመው፡፡አሁን ማንም አልሳቀም፡፡ከዛ ይህን ጥያቴ ጠየቀ......... <<<ለተመሳሳይ ቀልድ ለብዙ ግዜ አትስቁም ታዲያ ለተመሳሳይ ችግር ሁሌ ለምን ታለቅሳላችሁ፡፡>>> << !!!መልስ የለም! እኔም ደግሜ ልጠይቃችሁ እስኪ? ለምን ለተመሳሳይ ችግር ታለቅሳላችሁ! comment እጠብቃለሁ. !!!>> t.me/kehulum_bota
Mostrar todo...
kehulum bota ከሁሉም ሰብሰብ

እዚህ ቻናልላይ ምንም የምናጣው መረጃ የለም. ፖለቲካ, ስፖርት, ድንቃድንቅ, እንዲሁም አገረኛ ወሬዎችን እናናፍስበታለን! ብቻ ከናንተ የሚጠበቀው በመቀላቀል ቤተሰብ መሆን ነው!