cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ተዋህዶ ⛪️ሚድያ ማእከል

ኦርቶዶክሳዊያን ለቤተክርስትያናችን ጠበቃ የምንሆንበት እና ኦርቶዶክሳዊና ኦርቶዶክሳዊያን ላይ በማህበራዊ ሚድያ ላይ ኦርቶዶክስን የሚያንቋሽሹ የትኛውም ቻናሎችን በህብረት የምናዘጋበት ቻናል ነው እኔ ለቤተክርስትያኔ ጠበቃ ነኝ እኛን ማግኘት ከፈለጉ @Moatewahdo_bot ላይ ያገኙናል

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
585
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 días
+1030 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰኞ እለት ተቋቁሟል የተባለውን " መንበረ ጴጥሮስ " አወገዘች‼️ አሁን በሕገወጥ ድርጊታቸው የቀጠሉትን ቡድኖች በፍርድ እንደምትጠይቅ አሳውቃለች፡፡ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት ቤተክርስቲያን " ሕገወጥ " ባለችው መንገድ በጵጵስና ተሹመናል ካሉት እና በኃላም በእርቅ ወደቤተክርስቲያን ሳይመለሱ ከቀሩት መካከል አባ ገብረማርያም ነጋሳን ጨምሮ 4 አባቶች ትላንት በሰጡት መግለጫ " የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተክህነት መንበረ ጴጥሮስ " አቋቁመናል ብለዋል። ይህ በ2015 ዓ/ም ተቋቁሟል ላሉት የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መንበር መሰየም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው ሲሉ ተናግረዋል።ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቋሚና ጊዜያዊ ፕሮጀክት መምሪያ ኃላፊ መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ወ/ኢየሱስ ሰይፉ መግለጫ ሰጥተው ነበር።በዚህ መግለጫ ፤ " ግለሰቦቹ በሌላቸው ክህነት ነው መግለጫ እየሰጡ ያሉት " ብለዋል። እነዚህን አካላት ያደረጉት ከቀኖና ውጭ ስለሆነ ዛሬም ቤተክርስቲያን አጥብቃ ታወግዛለች ሲሉ ተናግረዋል።"ቤተክርስቲያን በሕግ በፍርድ ቤት ትጠይቃችለች ፤ በፍትህ መንፈሳዊ ከዚህ ቀደም እንዳወገዘችው አሁንም ህጌ፣ ስርዓቴ፣ ልብሴ ፣ ዶግማዬ ይከበር ትላለች " ሲሉ አክለዋል።"ከዚህ ቀደም በፍ/ቤት ከቤተክርስቲያን እውቅና ውጭ የትም እንዳይንቀሳቀሱ ፣ አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደው ነበር ያንን ተላልፈዋል ከዚህ በኃላ በፍርድ እንጠይቃቸዋለን፤ የለበሱት ልብስም የቤተክርስቲያን ስለሆነ እናስወልቃቸዋለን፤ ህገወጥ ናቸው " ብለዋል። "ከዚህ ባለፈ ይህ የሕገወጥ የሹመት እንቅስቃሴ ጉዳይ ከኦሮሚያ ወገን የተነሱትን ብቻ ሳይሆን ከትግራይ ወገን የተነሱትንም የሚመለከት ነው " ያሉ ሲሆን ሲመቱ ትክክለኛ አይደለም ቅዱስ ሲኖዶስም አይቀበለውም ብለዋል።
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
መታሰራቸው ተሰምቷል‼ " የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ጵጥሮስ " አቋቁመናል ካሉት ውስጥ ሶስቱ መታሰራቸውን የእንቅስቃሴው አስተባባሪ ነኝ ያሉ ዲያቆን አክሊሉ ዓለሙ የተባሉ ግስለሰብ ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል ተናግረዋል። ሶስቱ አባቶች የታሰሩት " መንበረ ጴጥሮስ " አቋቁመናል የሚል መግለጫ ከሰጡ በኃላ ሸገር ከተማ አስተዳደር በሚገኘው ቢሯቸው እንደሆነ እኚሁ አስተባባሪ ተናግረዋል። የታሰሩት ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ማዕረጋቸውን ገፍፌዋለሁ ያለቻቸው አባ ገብረማርያም ነጋሳ፣ አባ ወልደ ኢያሱስ ኢፋ እንዲሁም አባ ወልደኢየሱስ ተስፋዬ እንደሆኑ ለመረዳት ተችሏል። ሌሎችም አብረው የነበሩ ግለሰቦች መያዛቸውም ተነግሯል። የሸገር ከተማ አስታዳደር ፖሊስ ስለጉዳዩ ምንም ያለው ነገር የለውም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትላንት ተቋቁሟል የተባለውን " መንበረ ጴጥሮስ " አውግዛ ፤ አሁን በሕገወጥ ድርጊታቸው የቀጠሉትን ቡድኖች በፍርድ እንደምትጠይቅ አሳውቃ ነበር።
Mostrar todo...
ከባድ የጭነት መኪና የቃና ዘገሊላ በዓል እያከበሩ በነበሩ ምዕመናን ላይ በፍጥነት በመውጣት ባደረሰው ጉዳት 7 ሰዎች ወዲያውኑ ሕይወታቸው ሲያልፍ በርካቶች ከባድና ቀላል ጉዳት ደረሰባቸው ! ጥር 12 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) ++++ በዛሬው ዕለት ከቀትር በኋላ በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በደበሶ ደብረ ልዕልና ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን መነሻውን ከድሬደዋ ያደረገና ወደ ጭሮ ጭነት ይዞ ሲጓዝ የነበረ ከባድ የጭነት መኪና የቃና ዘገሊላ በዓል እያከበሩና ታቦት ከባሕረ ጥምቀት ወደ መንበረ ክብሩ በዝማሬ እና በእልልታ እያጀቡ በነበሩ ምዕመናን ላይ በፍጥነት በመውጣት ባደረሰው ገዳት 7 ሰዎች ወዲያውኑ ሕይወታቸው ማለፉን የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ለቲክቫህ አስታውቋል። ሀገረ ስብከቱ ፤ ከ7 በላይ ሰዎች ከባድ ጉዳት ፣ ወደ 10 የሚደርሱ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑንና አሁን ላይ በጭሮ ሆስፒታል በድንገተኛ ጽኑ ሕሙማን ክፍል እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ጨምሮ ገልጿል። ከሟቾች መካከል ህፃናት እና የፀጥታ አካላት ይገኙበታልም ብሏል። ጉዳቱን ያደረሰው መኪና መንሥኤው ምን እንደሆነ በባለሙያዎች ይጣራል ሲልም አሳውቋል። በተያያዘ መረጃ ትላንት በጥምቀተ ባሕሩ ሥፍራ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት አሳውቋል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ላረፉት ምዕመናን ዕረፍተ ነፍስን ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ፤ ለተጎዱ ወገኖቻችን ፈውስን ይመኛል። ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ
Mostrar todo...
የጥምቀት በዓል በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተከብሮ መጠናቀቁን የጋራ ግብረ ኃይሉ አስታወቀ የጋራ ግብረ ኃይሉ  ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ ካስመዘገበቻቸው ከማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ሀገራችን ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሮ ተጠናቅቋል። የሃይማኖት አባቶች፣ የየአድባራቱ አስተዳዳሪዎች፣ የበዓሉ አስተባባሪዎች እና የበዓሉ ታዳሚዎች በየደረጃው ከሚገኙት የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በመሥራታቸው በዓሉ በድምቀት መከበሩም በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ከተራ ምንድን ነው? ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡ በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡ በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ። በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ በዋዜማው የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡ መልካም የከተራ በዓል
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
የዓመቱ ምርጥ የምስራች *** ከአቃቂ ቃሊቲ መነሻቸውን አድርገው ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል በዓልን በቁልቢ አክብረው በመመለስ ላይ ሳሉ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ 11 ኦርቶዶክሳውያን ዛሬ ታህሳስ 29 ማለዳ ላይ ከአጋች ታጣቂዎች በመለቀቅ ወደ ቤታቸው እና ቤተሰባቸው በሠላም መቀላቀላቸው ተሰምቷል።
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ምዕመናን በነገው ዕለት በሚካሄደው የ"አእላፋት ዝማሬ" ላይ እንዲሳተፉ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ ጥሪ አቀረቡ ! ታኅሣሥ 26 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) +++ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነገው ዕለት በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል በሚካሄደው የ"አእላፋት ዝማሬ" ላይ በከተማው የሚገኙ ምዕመናን እንዲሳተፉ እና በረከት እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርበዋል። ብፁዕነታቸው የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን መልእክት በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊ ቅኔም እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ (ኤፌ 5፥19) እንዳለ ይህንኑ ቃል መነሻ በማድረግ እጅግ በተወደደ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በመሰባሰብ በዝማሬ አምላካችንን እንድናመሠግነው በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ይኸው የምስጋና መርሐግብር ተዘጋጅቷል ብለዋል። በዚህ ታሪካዊ መርሐግብር ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንደሚገኙ የገለጹት ብፁዕነታቸው አቡነ ሄኖክ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ በዚህ ታሪካዊ የዝማሬ መርሐግብር ላይ በመገኘት በረከት ትቀበሉ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪ ቀርቦላችኋል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። #Ethiopia #Tewahedo_Media_Center #TMC_Addia_Ababa ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ
Mostrar todo...
"የአእላፋት ዝማሬ" የታዳሚዎች መመሪያ | ጃንደረባው ሚዲያ | ታኅሣሥ 2016 ዓ.ም.| አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በቅድሚያ የአእላፋት ዝማሬን በጉጉትና በጸሎት የምትጠባበቁ ምእመናን የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደመሆናችን ይህንን መግለጫ አንብባችሁ ስትፈጽሙ በያላችሁበት "አቡነ ዘበሰማያት" በማድረስ የምስጋና ባለቤት ልዑል አምላካችን በምሕረቱ ብዛት የአእላፋት ዝማሬን ዕውን እንዲያደርግልን እና ስብሐተ እግዚአብሔርን በማስታጎሉ ከክብሩ የወደቀው ጸላዔ ሠናያት ክፉ ምክሩ ይፈርስበት ዘንድ ጸሎት አድርሱ ስንል እንጠይቃለን:: በዕለቱ የሚካሔደውን የአእላፋት ዝማሬም በተመለከተም የሚከተሉትን ማሳሰቢያዎች አንብባችሁ እንድትፈጽሙ በአክብሮት እንጠይቃለን:: 1ኛ. "የአእላፋት ዝማሬ" ከቀኑ 9:30 ተጀምሮ 12:30 ላይ ይጠናቀቃል:: ዝማሬው በጃንደረባው ሚድያ ቻናልና በልዩ ልዩ አጋር ሚድያዎች ስለሚተላለፍ በሥፍራው ለመገኘት የማትችሉ ምዕመናን በያላችሁበት በመንፈስ እንድትሳተፉ ጥሪያችንን እናቀርባለን:: በሆስፒታል ፣ በጠበል ሥፍራ ፣ በወኅኒ ቤት በአጠቃላይ ምቹ ባልሆነ ሁኔታ እንዲሁም በሥራ ገበታ ላይ የጌታችንን በዓለ ልደት የምታከብሩ ሁሉ በያላችሁበት በጸሎተ ምሕላውና በአእላፋት ዝማሬው ላይ እንድትካፈሉ ተጋብዛችኋል:: (ለሕሙማን አስታማሚዎችና ሐኪሞች ፣ ለታራሚዎች የሕግ ሰዎች ዝማሬውን በማሳየት እንድትተባበሩን እንጠይቃለን) 2ኛ. የአእላፋት ዝማሬው በሚካሔድበት በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም በቤተ ክርስቲያኑም ቅጽር ጊቢም ሆነ በአስፋልት ዳር ከቅዳሜ 3፡00 ጀምሮ መኪና ማቆም ስለማይቻል ምእመናን ከሕንጻዎቹ ጀርባ ብቻ መኪና እንዲያቆሙ ይጠበቃል:: ስለዚህ መኪና ያላችሁ ምእመናን መርሐ ግብሩ ሲጠናቀቅ ወደናንተ አቅጣጫ የሚሄዱ ክርስቲያን እኅት ወንድሞችን በመጫን የትራንስፖርት ሰርቪስ እንድትሠጡ አደራ እንላለን:: ለትራንስፖርት ተጠቃሚ ምእመናን የአካባቢው የታክሲና የሀይገር ባስ ትራንስፖርት ማኅበር በተቻለው አቅም ትራንስፖርት የሚያቀርብ ስለሆነ ይህንን አማራጭ መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ እንዲሁም ዋን ራይድ ትራንስፖርት ድርጅት የአላፋት ዝማሬን በማስመልከት 17% ቅናሽ ስላለው በ9744 ጠርተው “በዋን ራይድ አስጀምርልኝ” በማለት በቅናሽ ሂሳብና በቡድን ሆነው በመሄድ የ”shared trip” አገልግሎት መጠቀም ትችላላችሁ:: 3ኛ. በዕለቱ ምእመናን ቀድመው በመምጣት ቦታ እንዲይዙ የሚጠበቅ ሲሆን ከቤተ ክርስቲያኑ በሮች በጊብሰን በር በኩል ያለው በር ለቅዱስ ፓትሪያርኩና ለሊቃነ ጳጳሳት መግቢያ እንዲሁም ለልዩ ተጋባዥ እንግዶች ብቻ የተተወ በመሆኑ ምእመናን ሌሎቹን በሮች በመጠቀም ወደ ግቢው እንዲገቡ ይጠበቃል:: ቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ ውጪ ለሚቆሙ ምእመናንም ስክሪኑና የሳውንድ ሲስተሙ እነርሱን ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ ከዝማሬው ማዕድ መካፈል ይችላሉ:: በጃን ያሬድ ኅብረ ዝማሬ መዘምራን እና በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም የፈለገ ዮርዳኖስ ሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን የሚቀርቡትን ዝማሬዎች በትልቅ ስክሪን በግቢው የተለያዩ ቦታዎች ላይ የተዘጋጀና የዝማሬ ግጥሞቹና ኹነቱ በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል፡፡ ዝማሬውን ግጥም በቃላችሁ ያልያዛችሁና ለዋናው መድረክ ጥሩ እይታ አይኖረን ይሆን የሚል ሥጋት ሳይገባችሁ ዝማሬውን እንድትሳተፉ እንጠብቃለን:: 4ኛ. መርሐግብሩ ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናትን አያስተናግድም:: (የእነርሱ የአእላፋት ዝማሬ ባለፈው ሰንበት መካሔዱ ይታወሳል) ነጭ የአእላፋት ዝማሬ የልብስ ቀለም ነው፡፡ ነጭ ልብስ ከሌለዎት ያለዎትን ማንኛውም ልብስ አንጽተው ክርስቲያናዊ አለባበስ ለብሰው ይምጡ:: ለጌታ ልደት ያለ እጅ መንሻ እንደማይኬድ የታወቀ ነውና የቻሉ ምእመናን 10 ጧፍ ይዘው በመምጣት አንዱን ለራሳቸው በማስቀረት ዘጠኙን የተዘጉ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን ለመደገፍ በተዘጋጀው የጧፍ መሰብሰቢያ ቦታዎች ለአስተባባሪዎች ያስረክቡ ዘንድ እንጠይቃለን:: 5ኛ. የቦሌና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ለአካባቢው ፖሊስና ትራፊክ ጽሕፈት ቤት ባቀረበው የትብብር ጥያቄ መሠረት ዝግጅቱን በሰላም ለማካሔድ የሚመደቡ የጸጥታ አስከባሪዎች ይኖራሉ:: በመሆኑ ምእመናን ለጥበቃ አካላት ለፍተሻ መተባበር፤ ለአስተባባሪዎች በፍቅር በመታዘዝ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር እና ኦርቶዶክሳዊ ጨዋነት የማሳየት የተለመደ መገለጫቸው ለአእላፋት ዝማሬም ላይ ይጠበቃል:: የአእላፋት ዝማሬ ፍጹም መንፈሳዊ መድረክ እንደመሆኑ ምእመናን በፍጹም ተመሥጦ ስለ ሀገራቸው ሰላም እና ስለቤተ ክርስቲያን መጠበቅ የሚጸልዩበት የልደቱን ሰላም ለሀገራችን ሰላም እንዲወለድና ለመከራችን ፍጻሜ እንዲሆንልን ስእለት የምንሣልበት የጸሎት ጉባኤ መሆኑን አስቦ ሕሊናን ማዘጋጀት ከታዳሚዎች ይጠበቃል:: 6ኛ. የአእላፋት ዝማሬን እንዲቀርጹ ከተፈቀደላቸውና የሚዲያ ባለሙያ የሚል መለያ ካደረጉ የተመረጡ የሚዲያ ሰዎች ውጪ ቀረጻ ማድረግ ዝማሬውን መረበሽ በመሆኑ ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ ሙሉ መርሐግብሩ በጃንደረባው ሚዲያ ዩቲዩብ ገጽ በቀጥታ ሥርጭት፣ በሀገሬ ቴሌቭዥን በቀጥታ ስርጭት፣ በኢቲ አርት ሚዲያና በተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ፣ በፋና ቴሌቭዥን 90 ደቂቃ ላይ በቀጥታ ሥርጭት የሚተላለፍ በመሆኑ አእላፋት ዝማሬ ላይ በተለያየ እክል ምክንያት መገኘት ያልቻላችሁና ከአዲስ አበባ ውጪ የምትገኙ ኦርቶዶክሳዊያን በእነዚህ የሚዲያ አማራጮች መርሐ ግብሩን በቀጥታ በመታደም የበረከቱ ተካፋይ ትሆናላችሁ፡፡ 7ኛ. በአእላፋት ዝማሬ ወቅት ቀድመው የሚገኙና እስከ ሰርክ የሚቆዩ ታዳሚዎችን በማሰብ በቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ 18 ተንቀሳቃሽ መጸዳጃ ቤቶችን ያዘጋጀን መሆኑን እያሳወቅን አያድርገውና አንዳች የጤና መታወክ ለሚያጋጥማቸው ምእመናን ደግሞ በኢጃት - ጃን ሉቃስ ከመቅረዝ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ጊዜያዊ ክሊኒክ ማዘጋጀታችንን እናሳውቃለን:: ከዚህ በተጨማሪ ለአካል ጉዳተኛች የተዘጋጀ ሥፍራ ስላለ ምእመናን ሳይጨነቁ መካፈል ይችላሉ:: 8ኛ. የአእላፋት ዝማሬ በጊዜ ሲጠናቀቅ የቻሉ ምእመናን በዚያው በደብረ ሳሌም መድኃኔ ዓለም እንዲቆዩ ደብሩ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ያንን ማድረግ ያልቻሉ ምእመናን በጊዜ ወደየአጥቢያቸው በመሔድ በማሕሌትና ቅዳሴ ብርሃነ ልደቱን እንዲያዩ ይጠበቃል:: መኑ ይከልአኒ ዘምሮ እንዳልዘምር የሚከለክለኝ ምንድን ነው? የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
Mostrar todo...
👍 2