cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Gozam times

የተጣራ መረጃ በማቅረብ.......

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
203
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ‼️ በረዥሙ የሀገረ መንግሥትነት ታሪካችን ውስጥ ኢትዮጵያ  ያለፈችባቸው ወሳኝ የታሪክ  አንጓዎችና ውጣውረዶች ብዙ ናቸው። ቢሆንም ግን በታሪካችን ሂደት በገጠሙን ፈተናዎች ወድቀን ሳንቀር  ፈተናዎችን በአኩሪ ገድል እየተሻገርን አኩሪ አገራዊ የጋራ እሴቶችን አፍርተን ከዚህ ደርሰናል። ስለሆነም ይኸኛው ትውልድ የተረከባቸው በከፍተኛ ውጣውረዶች መካከል ተፈንትነው ያለፉ፣ የነጠሩና በጋርዮሽ መስተጋብሮቻችን የተሳለጡ እጅግ የምንኮራባቸው የባሕል፣ የትውፊትና የታሪክ ሀብቶቻችን ዘርፈ ብዙ ናቸው። በውልና በገሃድ እንደሚታወቀው በዘመናችን ሁሉ ላካበትናቸው አገራዊ እሴቶች እንደ ሌሎች ቀደምት ሃይማኖቶች ሁሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተጫወተችው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ በታሪክ ሂደታችን ውስጥ እያጋጠሙን ከምናልፋቸው  እንደ አንዱ የሚቆጠር ችግር ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ውስጥ ተፈጥሯል፡፡ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰውን ይህንን ፈተና  በትኩረት ሲከታተለው  ቆይቷል፡፡ በመሆኑም መንግሥት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በውስጧ የተፈጠረውን ችግር  በቤተ ክርሰቲያኗ  ሕግ እና ሥርዓት መሰረት መፈታት አለበት የሚል እምነት በመያዝ ጉዳዩን ሕገ ቤተ ክርስቲያን እና ቀኖናው በሚፈቅደው የአሠራር ስርዓት እንዲፈታ የበኩሉን አስተዋጽኦ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጅ የተፈጠረው ችግር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ሕግጋት መሰረት መፈታት ሲገባው ባለመፈታቱ ምክንያት ችግሮች በመባባሳቸው  በሃገራችን አንዳንድ አካባቢዎች ለሰው ልጆች ሕይወት መጥፋት፤ አካል ጉዳት እና የምዕመናን እንግልት መድረስ የክልሉ መንግሥት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን እረፍተ ነፍስ እንዲሰጥልን ቤተሰቦቻቸውን እና ወዳጅ ዘመዶቻቸውንም ፈጣሪ  መጽናናትን እንዲያድልልን እንመኛለን፡፡ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መግሥት የጉዳዩን አሳሳቢነት እና አደጋውን በመገንዘብ እጅግ በበሰለ መንገድ በመጓዝ ታላቋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነቷ ጸንቶ እና ተጠብቆ እንዲቀጥል እና የተፈጠረው ችግር በውይይት እንዲፈታ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። በሌላ በኩል ደግሞ ከውይይቱ የሚያፈነግጥ አካል ካለ በሀገሪቱ ሕግ እና ስርዓት መሰረት እንዲፈታ ቤተ ክርስቲያኗ አቅጣጫ አስቀምጣ ሲሠራ የነበረበትን መንገድ እና የተሄደበት ርቀት የሰከነ እና ጥበብ የተሞላበት ትክከለኛ አካሄድ መሆኑን ይገነዘባል፡፡ ስለሆነም  የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማስጠበቅ የተሄደበትን ርቀት እያደነቀ በዛሬው እለት  በፌደራል መንግሥት እና  በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል በተካሄደው ውይይት  መግባባት ላይ በመደረሱ የተሰማውን ደስታ ይገልጻል፡፡  በቀጣይም ለረጅም ዘመናት ጸንታ የቆየችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድ መንበር፣ አንድ ሲኖዶስ እና አንድ ፓትርያርክ የሚለውን የቤተ ክርስቲያኗን ሕግና ቀኖና ተፈጻሚነት እንዲኖረው ሁልጊዜም ድጋፉን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያስገነዝባል፡፡ የሃይማኖት አባቶችም ችግሩ ካጋጠመበት ጊዜ ጀምሮ  የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ ለማድረግ ጉዳዩ በሕግ እና ስርዓት እንዲፈታ ያሳዩት ትእግስት እና  አስተውሎት የተሞላበት ተግባር ትምህርት የሚወሰድበት እና በቀጣይ ለሚያጋጥሙ ችግሮች  አርዓያ የሚሆን ነው፡፡ መላው የክልላችን  ሕዝብ እና የቤተ ክርስቲያኗ ምዕመናንም ችግሩን ከሰማንበት ጊዜ ጀምሮ ሃይማኖታዊ ስርዓቱ በሚፈቅደው እና ቅዱስ ሲኖዶስ  በወሰነው መሰረት ችግሩ  በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ በጾም፣ በጸሎት እና ምህላ  ላበረከታችሁት ፍጹም ሰላማዊ፣ የሰከነ እና በአስተምህሮት የጸና አካሄድ መንግሥት ላቅ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል። የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ባሕር ዳር
Mostrar todo...
ነጠብ..ጣብ °°°°°°°°°°° እርስዎ፡ ገና ሲመጡ ያለ ጎሳ፣ ያለ ሃይማኖት ልዩነት 'ሆ!' ብሎ የተቀበልዎ ህዝብ አንዳች ተአምራት እንዲፈጥሩለት ፈልጎም አልነበረም። የፈለገው ከመባከን ማረፍን ነበር። የተናገሩትን እየጠቀሰ፣ ቅጥ በሌለው ስሜታዊ ውዴታ ለወንበርዎ አበቃዎ። አሻግርሃለሁ ሲሉት አመንዎ!...የሚሻገረውን መከራ ከግዚሃር ተልከዋል ስላለ እርስዎን አከበረ። በግል ህይወትዎ ዙሪያ የተጋነኑ ማንነቶች በመንግስት ሚዲያ ሲንዠቀዠቁ ህዝቡ ሳያላምጥ ውጦ ሲያበቃ ደም ያድርቁ ሰላምን ያረጋግጡለት ዘንድ ከልብ ታገስዎ ጠበቅዎ! በወንድሙ ላይ ሲዘምት ወንድም ለወንድም ሲጋደል፣ ካህናትና አድባራት ሲዋረዱ፡ ገበናዎን ደብቆና አስታምሞ..." ጊዜ እንስጣቸው " እያለ ያለውን ሰጠ የሌለውንም ከገባበት ገብቶ ለገስዎ! በእንደራሴዎች ፊት ደጋፊዎችዎን ሳይቀር በሚያሳቅቁ ያልተቀደሱ ቃላትዎና ዘለፋዎችዎ እንደፈለጉ ሲፏልሉ፡ ግድየለም ይህም ከልምድ ማነስ ነው ብሎ አቀፍዎ። ዛሬ የሚናቆሩት 'ጳጳሳት' ከመንገድ ወጥተው በየጉድባውና ሸንተረሩ የርስዎን ፖለቲካ እስኪያስተጋቡና ትዝብት ውስጥ እስኪገቡ ተሳጡልዎ! ▪▪ እና ለዚህ ህዝብ የሚከፈለው ይህ ነው? ቤተክርስቲያን የምትጠይቀውንስ የሚመልሱላት በዚህ የዕብሪት ምት ነው? ሌላው ይቅር ህዝብ ላይ የዕምነት መቃቃር ለመፍጠር የሚሞክሩት፡ ህዝቡ እንዲቀበልዎ በማሰብ ነው? የእምነት ግጭቶችን አቀጣጥለው በሰላም ይ'ተኛል? ዳሩ እርስዎ ብቻ መች ሆኑ?! ለነገሩማ፡ ሰድበን ለሰዳቢ የምንሰጥስ እኛ አይደለንም? እርስዎ ባልታየ ሽንቁር ይህን ያህል ሊደፍሩ ባልቻሉ ነበር። ከዚህ በኋላስ?...ምን ቀርዎ? የእምነት እሳት መጫር እንደብልህነት ወስደው በታላቋና ገናናዋ ቤተክርስቲያን ልጆች ደም ሊሳለቁ ነው? አሁን ይሄ የጤና ነው?... በሚወስኗቸው አደገኛ ውሳኔዎች ሃገሪቷን ወደለየለት ስርአት አልበኝነት እንዳይከቱ ሳንፈልግ ለጤናው ልንጸልይ ምን ቀረን?.... የእምነትን እሳት እባክዎ አይጫወቱበት! ▪▪ የሌሎች ቤተ እምነት አባቶች፣ የመንግስት ሚዲያዎችና ሲቪክ ማህበራትስ?..የት ናችሁ? መጥኔ!!!!
Mostrar todo...
በአካል ተገናኙ😳 "የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኙ የፌዴራል መንግሥት እና የህወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜ በሐላላ ኬላ ተገናኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለመጀመያ ጊዜ ከሰላም ስምምነት ትግበራ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ምክክር አደረገዋል። በውይይታቸው እስካሁን በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት የተገመገሙ ሲሆን በቀጣይ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ  ተቀምጧል። የሰላም ድርድሩ ኮሚቴ አስተባባሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመጀመሪያውን የገፅ ለገፅ ግንኙነት ያደረጉት የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል በሆነው ሐላላ ኬላ ነው። "መረጃው የዋልታ ነው።
Mostrar todo...
ያሳዝናል‼ ሀገር እንዲህ እየታመሰች ባላችበት ወቅትና የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ላይ በተፈጸመው ሕገወጥ ድርጊት ኹሉም ትኩረቱን ወደዚያ ባደረገበት አሳቻ ጊዜ ተጠብቆ ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጎቡ ሰዮ ወረዳ አኖ ከተማ ላይ እንዲሁም መቂና ባፈኖ በሚባሉ አካባቢዎች “የኦነግ ሸኔ ቡድን” በቡድን መሣሪያና ስለት በመጠቀም ቤት ለቤት ሕዝብን እየጨፈጨፈ እንደሆነ ለፓርቲያችን የድረሱልን ጥሪ ያሰሙ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ሐሙስ ጥር 25 ቀን ንጋት 11:00 የጀመረው ጭፍጨፋ እስከ ምሽት መቀጠሉን፣ ከጭፍጨፋው የተረፉት ነዋሪዎችም የሞቱ ቤተሰቦቻቸውን አስከሬን እንኳን መሰብሰብ እንዳልቻሉ ገልጸዋል፤ የድረሱልን ጥሪም እያሰሙ ይገኛሉ። "የአማራ ማንነት ያላቸውን ነዋሪዎች እየመረጡ ለእናንተ ጥይት አናባክንም እያሉ በአሰቃቂ ኹኔታ ነው እየጨፈጨፉን ያሉት የሚሉት እማኞች ቤትና ሱቅ ሌላም ንብረት እየተመረጠ በጋሪ ጭምር ነው የተጫነው፣ ከተማዋን በአንድ ቀን ጠፍ ምድር አድርገዋታል" ብለዋል። በተጨማሪም "የተሻለ ይከላከልልናል የምንለው መከላከያ ነቀምት ላይ አለ ተባልን እስከ አኹን ግን አልደረሰለንም" ያሉት እማኞች "እንዲህ ከሰውነት በወጣ አኳኋን ስንጨፈጨፍ ደራሽ እንዴት ጠፋ? እኛ ሰው አይደለንም ወይ? ለምንስ እንድንጠፋ ተፈረደብን?" ሲሉ ጠይቀዋል። ፓርቲያችን ጉዳዩን እንደኹልጊዜው በቅርበት እየተከታተለው ሲሆን መከላከያ የእነዚህን ከጭፍጨፋው የተረፉና በማንነታቸው ምክንያት ያለማቋረጥ እንደዱር አውሬ እየተሳደዱ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቹን እንዲታደግ ተማጽኗችንን ለማቅረብ እንወዳለን። እናት ፓርቲ ጥር 26,2015 ዓ.ም አዲስአበባ
Mostrar todo...
ልዩ መረጃ! በሻሸመኔ ከተማ የሚገኘው የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች በመንግሥት የጸጥታ አካላት ወደ ጽሕፈት ቤቱ እንዳይገቡ መከልከላቸው ተገለጸ። በትናንትናው ዕለት የሀገረ ስብከቱ ዋና ፀሐፊና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው በድጋሚ መታሰራቸውን መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን ሌሎች የሀገረ ስብከት ሰራተኞችም እየተሳደዱ እንደሆነ ተገልጿል። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ሕገ ወጡን ቡድን ተቀበሉ የሚል እንደሆነ ተ.ሚ.ማ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። @gech habesha
Mostrar todo...
ደብረብርሃን‼ የደብረብርሃን  ከተማ አስተዳደር  አገልግሎት ጽ/ቤት ምክትል ስራ አስኪጅ አቶ ነብዩ ባዩ እና ሁለት የከተማው መሀንዲሶች ጉቦ ሲቀበሉ ዛሬ እጅ ከፍንጅ ተይዘው ወደ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውን የመረጃ ምንጮቼ ከስፍራው ያደረሱኝ የውስጥ ጥቆማ ያመለክታል።ከሰሞኑን በደብረብርሃን  ከተማ በተካሄደ መድረክ ላይ አልሚዎች ሙስና እንዳስቸገራቸው በምሬት ተናግረው ነበር። @wasu mohamed
Mostrar todo...
#የቅጥር ማስታወቂያ
Mostrar todo...
ለትሬኒ ባንከር (Trainee Banker) የሥራ መደብ አመልካቾች በሙሉ! ፀሐይ ባንክ አ.ማ በትሬኒ ባንከር (Trainee Banker) የሥራ መደብ ላወጣው የሥራ ማስታወቂያ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ፈተና በኦንላይን መስጠቱ ይታወቃል፡፡ አመልካቾች ስለፈተናው የተለያዩ አስተያየቶችን ስላደረሳችሁን እያመሰገንን፤ በቀጣይ በአካል ተገኝታችሁ የምትወስዱት የጽሑፍ ፈተና ለመስጠት በሂደት ላይ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡ የጽሑፍ ፈተና የሚሰጥበትን ቀንና ቦታ በቀጣይ በማኅበራዊ የትስስር ገጾቻችን እና በአጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS) የምናሳውቅ መሆኑን በታላቅ አክብሮት እንገልጻለን፡፡ ፀሐይ ባንክ    ለሁሉ! ፀሐይ ባንክ ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች፡- Facebook: https://www.facebook.com/tsehaybanksc Instagram: https://www.instagram.com/tsehay_bank/ Twitter: https://twitter.com/tsehaybank LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/tsehaybank/ YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCqj_qre7CVg_8vBtn2zTNQA Telegram: https://t.me/tsehaybanksc #TsehayBank #forall #bank #Newbranch #finance #services #products #saving #loan #Ethiopia
Mostrar todo...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

⬆️ የተዳፈኑ #ሶስት ሰሞንኛ ኹነቶች! 1. ከአጣዬ እስከ ሸዋ ሮቢት፣ ከማጀቴ እስከ ጀውሀ፣ ከሰንበቴ እስከ ባልቲ... ወዘተ ባሉ በርካታ አካባቢዎች የተፈጠረው እጅግ ከባድ የፀጥታ ችግር እልባት ሳያገኝ፣ አንድም የመንግስት ሚድያም ሳይዘግበው ዛሬ ላይ ደርሷል። በሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች እና የጤና ባለሙያዎች ያደረሱኝ መረጃ እንደሚያስረዳው ባለፈው ቅዳሜ በጀመረው የፀጥታ መደፍረስ በርካታ ሰው ሞቷል፣ ቁስለኛ ሆኗል፣ ቢያንስ 200,000 የሚሆን ሰው ደግሞ ቀዬውን ለቆ እየተሰደደ ይገኛል። ህይወታቸውን ካጡት ውስጥ ንፁሀን ዜጎች፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የአማራ ልዩ ሀይል እና የኦሮሞ ነፃ አውጪ ጦር (በመንግስት አጠራር ኦነግ ሸኔ) አባላት እንደሚገኙበት መረጃዎቹ ይጠቁማሉ። የሚገርመው እነ ኢቢሲ ይባስ ትናንትና "በአጎራባች ክልሎች መካከል ለዓመታት የቆዩ ግጭቶች ተፈተዋል" የሚል ማደንዘዣ ዜናዎች ላይ ተጠምደዋል። ሰምቼ ባልፅፈው፣ አውቄ ባልናገረው እንዳይቆረቁረኝ ብዬ እንዲህ በአጭሩ አቅርቤዋለሁ። 2. የዛሬ ወር ገደማ (ታህሳስ 13 ቀን) ከዛሬ ጀምሮ ሲሚንቶ በነፃ ገበያ ይሸጣል ተብሎ ተነግሮ ነበር። ሁለት ወር እንኳን ሳይሞላው ትናንት ደግሞ "የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ ይፋ ተደረገ" ተብሏል። በዚህ ግብይት ዙርያ ከሚደርሱኝ መረጃዎች እንደምረዳው ገበያው በሰንሰለት የሚሰራና በሙስና የተጨማለቀ ነው። በጥቅም የተሳሰረ የቢሮ ሀላፊ፣ ባለሀብት፣ ነጋዴ እና ተጠቃሚ ይፈነጭበታል፣ ብር ያፍስበታል። እንደ ብረት ያሉ ሌሎች የግንባታ ግብአቶችም በጥቂቶች በሞኖፖል የተያዙ ናቸው። 3. በትናንትናው እለት ቅዱስ ሲኖዶስ አንድ ውሳኔ አሳልፎ ነበር። ሲኖዶሱ ጥር 14/2015 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሶዶ ዳጩ ወረዳ ሐሮ ባለወልድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሶስት የሀይማኖት አባቶች 26 ኤጴስ ቆጰሳትን ሾመናል፤ ሲኖዶስ አቋቁመናል በማለት በማኅህበራዊ እና በብሮድካስት ሚዲያዎች ካስተላለፉ በኋላ "በዚህ ድርጊታቸው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያንን በማታለል የክህደት እና የኑፋቄ ተግባር ፈፅመዋል" ብሏል። ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ተግባር እንደሚያወግዝ ገልጾ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር አውግዞ እንደለያቸው አሳውቋል። ይህ ትልቅ ክስተት በማህበራዊ/በዲጂታል እና በግል ሚድያው እንጂ በትልልቆቹ ሚድያዎች በዝምታ ታልፏል። ለምን? መልሱ ግልፅ ይመስላል። መልካም ቀን! @EliasMeseret
Mostrar todo...
አቶ በረከት ስምኦን ከእስር ተፈቱ ላለፉት አራት ዓመታት በእስር ላይ የቆዩት አቶ በረከት ስምኦን “የአመክሮ ጊዜያቸውን ጨርሰው” ዛሬ ረቡዕ ጥር 17፤ 2015 ጠዋት ከባህር ዳር ማረሚያ ቤት መፈታታቸውን ጠበቃቸው ህይወት ሊላይ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።  አቶ በረከት ከጥረት ኮርፖሬሽን የገንዝብ ብክነት ጋር በተያያዘ በቀረበባቸው ክስ፤ የስድስት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸው እንደነበር ይታወሳል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
Mostrar todo...