es
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Ir al canal en Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Mostrar más
1 161
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
3.66 KB

🔸🔸🔸🔸🔸🔸 የመስከረም ፲፪ ምስባክ ❣❣❣❣❣❣ ዘነግህ ሐለዩ ወነበቡ ከንቶ፣ ወነበቡ ዓመፃ ውስተ አርያም፣ ወአንበሩ ውስተ ሰማይ አፉሆሙ። መዝ ፸፪፤፰ ወንጌል፦ማቴ ፲፫፥፳፬-፵፬ ምስባክ ዘቅዳሴ ፩ቆሮ ፭፥፫-፲፩ ይሁ ፩፥፱-፳ ግብ.ሐዋ ፳፥፳፰-፴፩ ወንጌል፦ ማቴ ፲፱፥፲፭-፲፱ ቅዳሴ፦ ዘቄርሎስ ይትዐየን መላከ እግዚአብሔር ዐውዶሙ፣ ለእለ ይፈርህዎ ወያድኀኖሙ፣ ጣዕሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር ። መዝ ፴፫፤፯ https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መስከረም ፲፪ (12) ቀን። ❤ እንኳን በኤፌሶን አገር በ 431 ዓ.ም (ሦስተኛው ጉባኤ) ሁለት መቶ ኤጲስ ቆጶሳት ሁለት ባሕሪ ሁለት አካል ብሎ የተነሣው መናፍቁንና ከሀዲውን ንስጥሮስን በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት በቅዱስ (አባ) ቄርሎስ ሊቀ መንበርነት ለማውገዝ ለተሰበሰቡበት ቀን ለመታሰቢያ በዓል ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤል እግዚአብሔር ወደ አሞፅ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ለንጉሡ ሕዝቅያስ ከደዌው እንዳዳነው በዕድሜው ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እንደተጨመረለት ንገረው ብሎ ለተላከበት ለወራዊ መታሰብያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሰማዕት ቅዱስ አፍላሆስ ከመታሰቢያውና ከሥጋው ፍልሰት፣ ከእስክድርያ አገር ከሆኑ ከባልንጀሮቹ ሰማዕታትም ከመታሰቢያቸው፣ ከሰማዕታት ከቅዱሳን ከሉዩራስና ባሌኒኮስ፣ ከቅዱስ ኢያቄምና ከቅድስት ሐናም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ "ሰላም ለ ፪፻ ኤጲስ ቆጶሳት እለ ተጋብኡ በኤፌሶን ሀገር፤ ወአጽንኡ ሃይማኖተ በእግዚአብሔር"። ትርጉም፦ በኤፌሶን ሀገር ተሰብስበው ሃይማኖትን በእግዚአብሔር የጸኑ ለኾኑ ለኹለት መቶው ኤጲስ ቆጶሳት ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ በዚችም ቀን ደግሞ በኤፌሶን ከተማ የቅዱሳን የሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ስብሰባ ሆነ ይህም ለታላላቆች ጉባኤያት ሦስተኛ ነው። ❤ ስብሰባቸውም የተደረገው የታላቁ ቴዎዶስዮስ ልጅ አርቃድዮስ የወለደው ታናሹ ቴዎዶስዮስ በነገሠ በሃያ ዓመት ነው። የስብሰባቸውም ምክንያት የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት በሆነ በንስጡር ነው። እርሱ ስቶ እንዲህ ብሏልና "እመቤታችን ድንግል ማርያም አምላክን በሥጋ አልወለደችውም እርሷ ዕሩቅ ሰውን ወልዳ ከዚህ በኋላ በውስጡ የእግዚአብሔር ልጅ አደረበት ከሥጋ ጋር በመዋሐድ አንድ አልሆነም በፈቃድ አደረበት እንጂ። ስለዚህም ክርስቶስ ሁለት ጠባይ ሁለት ባህርይ አሉት" የተረገመ የከሐዲ ንስጡር የከፋች ሃይማኖቱ ይቺ ናት። ❤ ስለ እርሱም የተሰበሰቡ እሊህ አባቶች ከእርሱ ጋር ተከራከሩ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው አምላክ እንደሆነ ገብርኤል መልአክ በአበሠራት ጊዜ ከተናገረው ቃል ምስክር አመጡ። እንዲህ የሚል "እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው ከአንቺ የሚወለደውም ጽኑዕ ከሀሊ ነው የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል"። ዳግመኛም "እነሆ ድንግል በድንግልና ፀንሳ ወንድ ልጅን ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች" ብሎ በትንቢቱ ከተናገረው ከኢሳይያስ ቃል ሁለተኛም "ከእሴይ ዘር ይተካል ከእርሱም ለአሕዛብ ተስፋቸው ይሆናል"። ❤ ዳግመኛም የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ቄርሎስ ገሠጸው መከረው ስለዚህም እንዲህ ሲል አስረዳው "ክብር ይግባውና የክርስቶስ የመለኮቱና የትስብእቱ ባሕርያት በመዋሐድ አንድ ከሆኑ በኋላ አይለያዩም አንድ ባሕርይ በመሆን ጸንተው ይኖራሉ እንዲህም አምነን ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃል አንዲት ባሕርይ ነው እንላለን"። ❤ ከሀዲ ንስጥሮስ ግን ከክፉ ሐሳቡ አልተመለሰም ከሹመቱም ሽረው እንደሚአሳድዱትም ነገሩት። እርሱ ግን የጉባኤውን አንድነት አልሰማም ስለዚህም ከሹመቱ ሽረው ረግመው ከቤተ ክርስቲያን ለይተው አሳደዱት ወደ ላይኛውም ግብጽ ሒዶ በዚያ ምላሱ ተጎልጒሎ እንደ ውሻ እያለከለከ በክፉ አሟሟት ሞተ። ❤ እሊህም ሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት አባቶች ሃይማኖትን አጸኑዋት በዚህም ጉባኤ ውስጥ እንዲህ ብለው ጻፉ "እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእርሷ ሰው የሆነውን የእግዚአብሔርን አካላዊ ቃል በሥጋ ወለደችው"። ❤ ከዚህም በኋላ ሥርዓትን ሠርተው ሕግንም አግገው በእጆቻቸው ጽፈው ለምእመናን ሰጡ። እኛም የሕይወትንና የድኅነትን መንገድ ይመራን ዘንድ እግዚአብሔርን እንለምነው። ለእርሱም ክብር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ በዚች ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው። ❤ በዚችም ቀን ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢይ ኢሳይያስ ላከው ይቅርም ብሎት ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሕዝቅያስ ሒዶ እግዚአብሔር ይቅር እንዳለውና ከደዌው እንዳዳነው በዕድሜውም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እንደ ጨመረለት ይነግረው ዘንድ አዘዘው። ንጉሱም ሚስት አግብቶ ምናሴን እስከወለደው ድረስ እንዲሁ ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ይማረን። + + + ❤ "ሰላም ለክሙ ሐራ ክርስቶስ መድኅን። ጥዑማነ ዜና ወዝክር እምአስካለ ወይን። ርእሰ ንስጥሮስ ትምትሩ በሰይፈ ሃይማኖት ርሱን። ዘተጋባእክሙ ሀገረ ኤፌሶን። ክልኤቱ ምዕት ጳጳሳት ኄራን"። ትርጉም፦ በጋለ የሃይማኖት ሰይፍ የንስጥሮስን ራስ ትቆርጡ ዘንድ በኤፌሶን አገር የተሰበሰባችኊ የኾናችኊ ደጋጎች (የተመረጣችሁ) ኹለት መቶ ሊቃውንት ዜናችኹና መታሰቢያችኊ ከወይን ፍሬ ይልቅ የጣፈጠ የመድኅን ክርስቶስ ጭፍራ ሰላምታ ለእናንተ ይገባል። + + + ❤ "ሰላም ለምቅወምከ ዘልዑል ማዕረጋ። እምቅዋመ አእላፍ እንግልጋ። ሚካኤል መንፈስ ዘንበለ ሥጋ። ታድኅን ዘተመንደበ ለማዕበለ ባሕር እምጹጋ ወለእለ በበድው ትባልሕ በጸጋ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 12። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦"ሐለዩ ወነበቡ ከንቶ። ወነበቡ ዓመፃ ውስተ አርያም። ወአንበሩ ውስተ ሰማይ አፉሆሙ"። መዝ 72፥8-9። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 13፥424-44። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዐውዶሙ። ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙ። ጠዐሙ ወታእሙሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር"። መዝ 33፥7-8። የሚነበቡት መልዕክታት 1ቆሮ 5፥3-11፣ ይሁ 1፥9-20 እና የሐዋ ሥራ 20፥28-31። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 18፥15-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ የቅዱስ ቄርሎስ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ሚካኤል ወራዊ በዓልና የኤፌሶን ጉባኤ የተሰበሰቡ የ200 ኤጲስቆጶሳት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

5.26 KB

✝✝✝✝✝✝✝✝ ዘመስከረም ፲፩ ምስባክ 🌹🌸🌹🌸🌹🌸🌹🌸 ዘነግህ ተንሥኡ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ፣ ወዘኢየአምር ነበቡ ላዕሌ፣ ፈደዩኒ እኪተ ህየንተ ሠናይት። መዝ ፴፬፤፫ ወንጌል፦ማቴ ፲፮፥፳፬-ፍ ምስባክ ዘቅዳሴ ዕብራ ፲፪፥፩-፲፪ ያዕ ፫፥፩-፲፫ ግብ.ሐዋ ፲፥፩-፱ ወንጌል፦ሉቃ ፳፩፥፲፪-፳፩ ቅዳሴ፦ዘባስልዮስ ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ፣ በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ፣ ይባዕ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን። ✝ ✝🇪🇹✝ መልካም አገልግሎት ✝

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

አደርጋለሁ"። ጌታችንም ይህን ካለው በኋላ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ ቅዱስ ፋሲለደስም በፍጹም ደስታ ደስ ተሰኘ። ❤ ከዚህም በኋላ መጽሩስ መኰንን ከአማካሪዎቹ ጋር ተማከረ እንዲህም አላቸው "ስሙ ፋሲለደስ ስለሚባል ስለዚህ ሰው ምን ላድርግ እርሱን ያላሠቃየሁበት የሥቃይ መሣሪያ ምንም የቀረ የለም ከሐሳቡም አልተመለሰም" እነርሱም እንዲህ ብለው መከሩት "ራሱን በሰይፍ ቆርጠህ ከእርሱ ተገላገል እነሆ የዚች አገር ሰዎች በእርሱ ምክንያት አልቀዋልና"። ❤ በዚያንም ጊዜ የቅዱስ ፋሲለደስን ራስ በሰይፍ እንዲቆርጡ መኰንኑ አዘዘና ቆረጡት የድል አክሊልን ተቀበለ ንቆ ሰለ ተዋት ምድራዊት መንግሥት ፈንታም ሰማያዊት መንግሥት አገኘ። ከሥጋውም ድንቆች የሆኑ ታላላቅ ተአምራት ተገለጡ ከእርሱም ጋር ሰማዕት ሁነው የሞቱ ሁሉም ቊጥራቸው ሃያ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ዘጠና ሦስት ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ ፋሲለደስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ቅዱስ ቆርኔሌዎስ፦ ይህም ቅዱስ የጭፍራ አለቃ የሆነ ትሩፋቱና ገድሉም ያማረ ጻድቅ፤ በቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት ዘመን እግዚብሔርን ያገለገለ ነው። ❤ የእግዚአብሔር መልአክም ተገልጦለት ሐዋርያ ጴጥሮስን ይጠሩት ዘንድ ሰዎችን እንዲልክ ጴጥሮስም ወደርሱ እንዲመጣ ሊሠራው የሚገባውን ከእርሱ ከጴጥሮስ እንዲሰማ አዘዘው። ❤ ጴጥሮስም ወደርሱ በደረሰ ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል አስተማረው ለርሱና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ ከሁሉ ቤተሰቡ ጋር አምኖ ተጠመቀ። ከዚህ በኋላ ጴጥሮስ ለእስክንድርያ አገር ቅስና ሾመው ወደርሷ በደረሰ ጊዜ የጣዖታትን አምልኮ ተመልታ አገኛትና አስተማራቸው ብዙዎችንም ወደቀናች ሃይማኖት መልሶ አጠመቃቸው መኰንኑ ድሜጥሮስም አምኖ ከወገኖቹ ጋር በእርሱ እጅ ተጠመቀ። ❤ የኑሮውን ዘመንና ሐዋርያዊ ተጋድሎውን አድርሶ በሰላም አረፈ እርሱም ከአሕዛብ አስቀድሞ ያመነ የመጀመሪያ አማኒ ነው። + + + ❤ ቅድስት ታዖድራ፦ ይችንም ቅድስት ሌላ ሰው አስገድዶ ከባሏ ወስዶ ከባሏ ጋር ያላትን አንድነት አበላሸ ያን ጊዜም ታላቅ ኀዘን በማዘን ተጸጸተች መሪር ልቅሶንም አለቀሰች የወንዶችንም ልብስ ለብሳ ወንድ መሰላ ከእስክንድርያ በሥውር ወጣች ስሟንም ቴዎድሮስ ብላ ሰየመችና ወደ ወንዶች ገዳም ገባች የምንኲስና ልብስንና የመላእክትን አስኬማ ለበሰች። የሚያዩዋት ሁሉ እርሷ እንደ ጃንደረባ የሆነች ወንድ ትመስላቸው ነበር እርሷ ግን በረኃብ፣ በጽምዕ ሌሊት በመትጋት ቀን በመቆም ጸንታ በመጋደል ላይ ታገሠች እንዲህም በመጋደል ተጠምዳ ብዙ ዘመን ኖረች። ❤ በዚያም ወራት እንዲህ ሆነ አንድ ሰው ከአንዲት ብላቴና ጋር አመነዘረ እርሷም ፀንሳ ወንድ ልጅን ወለደች ወላጆቿም "ድንግልናሽን ያጠፋው ማነው" ብለው ጠየቋት እርሷም "በገዳም ውስጥ የሚኖር አባ ቴዎድሮስ እርሱ ደፍሮኝ ከእርሱ ፀነስኩ" ብላ በዚች ቅድስት ታኦድራ ላይ በሐሰት ተናገረች። ❤ ወላጆቿም በሰሙ ጊዜ እጅግ አዘኑ ሕፃኑንም ወደዚያ ገዳም አበ ምኔት ወሰዱት እንዲህም አሉት "ይህ ሕፃን የልጅህ የመነኵሴው የቴዎድሮስ ልጅ ነው"። ያን ጊዜም አበ ምኔቱ ይቺን ቅድስት ታኦድራን ጠራትና እንዲህ አላት "ይህን ክፉ ሥራ ለምን ሠራህ በመነኰሳቱም ሁሉ ላይ ኀፍረትንና ጒስቁልናን አመጣህ" እርሷ ሴት መሆኗን አላወቀምና እርሷም አባቴ ሆይ "በድያለሁና ይቅር በለኝ" አለችው። ❤ አበ ምኔቱም ተቆጥቶ ከገዳሙ አስወጥቶ አባረራት በበረሀ ውስጥ ሰባት ዓመት ኖረች ያም ሕፃን ከእርሷ ጋር ሁኖ ከሰይጣናት በሚመጡባት በብዙ መከራዎች ብዙ መከራዎች ላይ ታገሠች ብዙ ሥቃያትንም ፈጽሞ አሠቃዩዋት። ❤ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ ተቀብለው ወደ ገዳም አስገቡአት ጥቂት ቀንም ኖረች መልካም ተጋድሎዋንም ፈጽማ በሰላም አረፈች ነፍሷንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጥታ የዘላለም ሕይወትን አገኘች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ታኦድራ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ሰማዕቷ ቅድስት በነፍዝዝ፦ የስሟ ትርጓሜ ጣፋጭ የሆነ ማለት ነው። ይቺም ቅድስት በእድሜዋ ፈጽማ የሸመገለች ነበረች በፋርስ ንጉሥ በሳቦር ዘመንም መከራ ተቀበለች ከዘጠኝ መቶ ክርስቲያን ጋር ማርከው ወስደው አሠሩዋት የሠራዊቱም አለቃ ታላቅ ሥቃይን አሠቃይቶ ከዚያ በኋላ ራሷን በሰይፍ ቆረጠ። ❤ ራሷንም ከአስቆረጣት በኋላ ከአንገቷ የፈሰሰው ደም እስከ ራቀ ድረስ ወደ ላይ ወጣ ከዚያ የተቀመጡ ጠላቶችም ኃይላቸው ደከመ። የፀሐይ ብርሃንም ጨለመ በዚያም ቦታ ደግሞ ጣፋጭ የሆነ መዐዛ ተመላ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት በነፍዝዝ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የእስና አገር ሰዎች ሦስቱ ቅዱሳን ሰማዕታት ገበሬዎች ሱርስ፣ አጤኬዎስ፣ መስተሐድራ፦ አርያኖስም ከሀገሪቱ በስተደቡብ ምንም ሳያስቀር ወታደሮቹ እስከ ደከሙ ድረስ ሰይፋቸውንም ወደ አፎቱ መልሰው ነበር የአገር ሰዎችን ጨርሶ ገድሎ ሲመለስ እሊህ ሦስቱ ገበሬዎች ከዱር ሲመለሱ በከተማ መካከል በተገናኙት ጊዜ "እኛ ክርስቲያኖች ነን" ብለው በግልጥ ጮኹ አርያኖስም ሰምቶ ወታደሮቹን "እሊህን ገበሬዎች ትገድሏቸው ዘንድ ይገባል" አላቸው። ❤ ወታደሮቹም "እኛ ደክመናል ሰይፎቻችንንም ወደ አፎታቸው አስገብተናል" አሉት እሊህ ቅዱሳንም ሰምተው "እነሆ መቆፈሪያዎች ከእኛ ጋራ አሉ" በእነርሱ ግደሉን አሉ ከዚያም አንገታቸውን በደንጊያ ላይ አድርገውላቸው ቆረጡአቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 11 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለፋሲለደስ እምነ ክሣዱ ዘአንጠብጠበ። ደመ ቀይሐ ወጸዓድዒደ ሐሊበ። ምስለ አዝማዲሁ ወሰብኡ እስመ ለሞት ተውህበ። በከመ ኮኖሙ ዲበ ምድር አበ። ዘበሰማያት ተሠይመ አቡሆሙ ካዕበ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 11። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ተንሥኡ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ። ወዘኢየአመር ነበቡ ላዕሌየ። ፈደዩኒ እኪት ህየንተ ሠናይት"። መዝ 34፥3-4። የሚነበበው ወንጌል 16፥24-ፍ.ም። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ። በቀለ ደሞሙ፡ለአግብርቲከ፡ዘተክዕወ። ይባዕ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ 78፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 12፥1-12፣ ያዕ 3፥1-13፣ የሐዋ ሥራ 10፥1-9። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 21፥12-21። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ፋሲለደስ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መስከረም ፲፩ (11) ቀን። ❤ እንኳን ለአንጾኪያ ነገሥታት አባታቸው፤ መካሪያቸው ለሆነ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ለነበረው፤ ጌታችን ከሞት እያስነሣው በጽኑ ሥቃይና ተጋድሎ ሲጋደል ለኖረው ለታላቁ ሰማዕት ለቅዱስ ፋሲለደስ፣ በቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት ዘመን እግዚአብሔርን ያገለገለ የጭፍራ አለቃ (፻አለቃ) ለሆነ ትሩፋቱና ገድሉም ላማረ ለጻድቁ ሰው ለቅዱስ ቆርኔሌዎስ፣ ለእስክድርያ አገር በንጉሥ ዘይኑን ዘመን ለነበረች ለቅድስት ታዖድራ ለዕረፍት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን፡፡ በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ የስሟ ትርጓሜ ጣፋጭ ከሆነ ከከበረች ከሰማዕቷ ከቅድስት በነፍዝዝ ከዕረፍት በዓል፣ ስማቸው ሱርስ፣ አጤኬዎስና መስተሐድራ ከሚባሉ ሦስት ገበሬዎች ከእስና አገር ሰዎች በሰማዕትነት ከዐረፉ፣ ከቅዱሳን ከባስልዮስ ሰማዕትና ከኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ከቴዎድሮስ ከሰማዕት አለቃ ከቀውስጦስም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "በዛቲ ዕለት ይሴብሑከ መላእክት እለ ተጋብኡ ውስተ ዝንቱ ቤት ፋሲለደስ ሰማዕት ዘነገሥከ በሰማያት አማን ምዑዝ ከመ እፍረት። ትርጉም፦ ሰማዕቱ ፋሲለደስ ሆይ በሰማያት የነገሥክ በእውነት እንደ መልካም ሽቶ የምትጣፍጥ በዚች ቀን በዚህ ቤት ውስጥ የተሰበሰቡ መላእክት ያመሰግኑሃል። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ ለአንጾኪያ ነገሥታት አባታቸውና መካሪያቸው የሆነው ሰማዕቱ ቅዱስ ፋሲለደስ፦ እርሱም ለሮም ንጉሥ የሠራዊት አለቃ ነው መንግሥቱም ሁለመናዋ በእርሱ ምክር የጸናች ናት። ብዙዎችም ወንዶችና ሴቶች የቤት ውልዶች አገልጋዮች አሉት። ❤ ዝምድናውም እንዲህ ነው ስሙ ኑማርያኖስ የተባለ የሮም ንጉሥ ለቴዎድሮስ በናድሌዎስ እናቱ የሆነች የቅዱስ ፋሲለደስን እኅት አግብቶ ዮስጦስን፣ ገላውዴዎስን፣ አባዲርን ወለደችለት እሊህም ለቅዱስ ፋሲለደስ የእኅቱ ልጆች ናቸው። የቅዱስ ፋሲለደስም ሚስት ለቅዱስ ፊቅጦር እናት እኅት ናት ከእርሷም ስማቸው አውሳብዮስና መቃርስ የተባሉ ሁለት ልጆችን ወለደ። ❤ በዚያም ወራት የቊዝና የፋርስ ሰዎች የሮምን ሰዎች ሊወጓቸው በላያቸው ተነሡ ያን ጊዜ የንጉሥ ልጅ ዮስጦስን የፋሲለደስ ልጅ አውሳብዮስን ከጦር ሠራዊቶቻቸው ጋር ለውጊያ ላኳቸው። ንጉሡ ኑማርዮስም ሌሎች ጠላቶች በተነሡበት በኩል ለጦርነት ሒዶ በውጊያው ውስጥ ሞተ የሮም መንግሥትም የሚጠብቃትና የሚመራት የሌላት ሆነች። ❤ እንዲህም ሆነ በዚያ ወራት ስለ ጦርነት ለመደራጀት የሮም ሰዎች ከሀገሩ ሁሉ አርበኞች የሆኑ ሰዎችን ሰበሰቡ ከውስጣቸውም ከላይኛው ግብጽ ስሙ አግሪጳዳ የሚባል የፍየሎች እረኛ የሆነ አንድ ሰው አለ። እርሱንም መኳንንቱ ወስደው በመንግሥት ፈረሶች ላይ ባልደራስ አድርገው ሾሙት እርሱም በጠባዩና በሥራው ሁሉ ኃይለኛና ብርቱ ነበር። ❤ ከንጉሥ ኑማርያኖስ ሴቶች ልጆች አንዲቱ ወደርሱ በመስኮት ተመለከተች ወደደችውም መልምላም ወስዳ አገባችው ስሙንም ዲዮቅልጥያኖስ ብላ ሰይማ አነገሠችው። ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ሰማይና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔርን ትቶ ጣዖታትን አመለከ ቅዱስ ፋሲለደስም ሰምቶ እጅግ አዘነ የመንግሥትንም አገልግሎት ተወ። ❤ ከዚህም በኋላ የንጉሥ ኑማርያኖስ ልጅ ዮስጦስና የፋሲለደስ ልጅ አውሳብዮስ ጠላቶቻቸውን ድል አድርገው የጠላቶቻቸውንም አገሮች አጥፍተው ደስ ብሏቸው ተመለሱ። ነገር ግን የነገሠው ዲዮቅልጥያኖስ የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክዶ አምልኮ ጣዖትን አቁሞ አገኙት እጅግም አዘኑ ተቆጥተውም ተነሡ ሰይፎቻቸውን መዝዘው ዲዮቅልጥያኖስን ገድለው የንጉሥ ኑማርያኖስን ልጅ ዮስጦስን ሊያነግሡ ወደዱ ፋሲለደስም ከዚህ ሥራ ከለከላቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ፋሲለደስ ዘመዶቹን፣ ሠራዊቱን፣ አገልጋዮቹንም ሁሉ ሰበሰባቸውና በክብር ባለቤት በክርስቶስ ስም ደሙን ሊያፈስ እንደፈለገ አስረዳቸው ሁሉም እንዲህ ብለው መለሱለት "አንተ በምትሞትበት ሞት እኛ ከአንተ ጋር እንሞታለን" በዚህም ምክር በአንድነት ተሰማሙ። ❤ ከዚህም በኋላ በንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ፊት ቁመው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ከእርሳቸውም ግርማ የተነሣ ታላቅ ፍርሃትን ፈራ እነርሱ የመንግሥት ልጆች ናቸውና። ❤ የቅዱስ ፊቅጦር አባት ኅርማኖስም ወደ ግብጽ አገር ይልካቸው ዘንድ በዚያም እንዲያሠቃዩዋቸው መከረው ሁሉንም እየአንዳንዳቸውን ለብቻቸው አድርጎ ላካቸው አባዲርንና እኀቱ ኢራኒን ወደ አንዲት አገር፣ አውሳብዮስንና ወንድሙ መቃርስን ወደሌላ ቦታ፣ ገላውዴዎስንም እንዲሁ አደረጉ። በናድሌዎስ ቴዎድሮስም እሼ በሚባል ዕንጨት ላይ በመቶ ሃምሳ ሦስት ችንካር ተቸንክሮ ገድሉን ፈጸመ። ❤ ቅዱስ ፋሲለደስን ግን አምስት ከተማዎች ወዳሉበት ወደ አፍሪካ ምድር ወደ መኰንኑ ወደ መጽሩስ ላከው መጽሩስም በአየው ጊዜ መንግሥቱን ክብሩን ስለ ተወ እጅግ አደነቀ። ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስም መልአኩን ልኮ በመንፈስ ወደ ሰማይ አውጥቶ በብርሃን ያጌጠ መንፈሳዊ ማደሪያን አሳየው ነፍሱም እጅግ ደስ አላት ከዚህም በኋላ ወደነበረበት መለሰው። ባሮቹን ግን ነፃ ያወጣቸው አሉ የቀሩትም ከእርሱ ጋር የሰማዕትነት አክሊልን የተቀበሉ ሰባት ሺህ ሠላሳ ሦስት የሚሆኑ አሉ። ❤ ቅዱስ ፋሲለደስንም ታላቅ ስቃይን አሰቃዩት በመንኰራኲርና በተሣሉ የብረት ዘንጎች ሥጋውን ሰነጣጥቀውት ሞተ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያለ ጥፋት ከሞት አድኖ አስነሣው አሕዛብም ሁሉ ይህን ድንቅ ተአምር በአዩ ጊዜ አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አመኑ መኰንኑንም ረገሙት ጣዖቶቹንም ሰደቡ በእነርሱ ላይም ተቆጥቶ ራሶቻቸውን በሰይፍ ይቆርጧቸው ዘንድ ወታደሮቹን አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ ቊጥራቸውም ዐሥራ አራት ሺህ ሰባት መቶ ወንዶች ሠላሳ ሰባት ሴቶች ናቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ፋሲለደስን ሥጋው ሁሉ ቀልጦ እንደ ውኃ እስከሚሆን በብረት ምጣድ ውስጥ አበሰሉት መኰንኑም በተራራ ላይ ጥልቅ ጒድጓድ ቆፍረው በዚያ እንዲቀብሩት አዘዘ እንዲሁም አደረጉ። ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ፋሲለደስን ከሞት ደግሞ አስነሣው ወደ መኰንኑም መጥቶ እንዲህ ብሎ ጮኸ "መኰንን መጽሩስ ሆይ እፈር ከሀዲ ንጉሥህም የረከሱ ጣዖቶችህም ይፈሩ እነሆ ክብር ይግባውና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ጉዳት ከሞት ጤነኛ አድርጎ አስነሥቶኛልና"። ሕዝቡም ይህን ተአምር በአዩ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ሞቱ ቁጥራቸውም ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ሆነ። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ፋሲለደስን በውስጧ መጋዝ ካላት መንኰራኲር ላይ አውጥቶ ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው ዳግመኛም በብረት ዐልጋ ላይ በሆዱ አስተኝተው ከበታቹ እሳትን አነደዱ ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለት ከዚያ ስቃይም ውስጥ አንስቶ ያለ ጉዳት ጤነኛ አደረገው እንዲህም ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው "ፋሲለደስ ሆይ ዕውቅ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ ወይም ለድኆች በስምህ ምጽዋትን ለሚሰጥ ወይም ለተራቈተ ልብስን ወይም በመታሰቢያህ ቀን ለቤተ ክርስቲያን መባ ለሚሰጥ በብዙም ቢሆን በጥቂት መታሰቢያህን ለሚያደርጉ ሁሉ እኔ በደላቸውን ሁሉ እተውላቸዋለሁ መኖሪያቸውንም በመንግሥተ ሰማያት ከአንተ ጋራ

​​መስከረም ፲ ✞ጼዴንያ ማርያም✞ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን እመቤታችን ድንግል ማርያምን የምትወድና በሚቻላትም ሁሉ የምታገለግላት፣ ቤቷንም ለእንግዳ ማደሪያ ያደረገች አንዲት ማርታ የምትባል ሴት ነበረች፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን አባ ቴዎድሮስ የሚባሉ ኢትዮጵያዊ መነኮስ ከእርሷ ዘንድ በእንግድነት አድረው በማግሥቱ ከቤቷ ሲወጡ ማርታ የሚሔዱበትን አገር በጠየቀቻቸው ጊዜ እርሳቸውም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደው ቅዱሳት መካናትን እንደሚሳለሙ ነገሯት፡፡ ማርታም ከእርሷ ገንዘብ ወስደው የእመቤታችንን ሥዕል ገዝተው ይዘውላት እንዲመጡ ለመነቻቸው፡፡ መነኵሴውም በራሳቸው ገንዘብ ሥዕሉን ገዝተው እንደሚያመጡላት ቃል ገቡላት፡፡ አባ ቴዎድሮስ ኢየሩሳሌም ደርሰው ቅዱሳት መካናትን ከተሳለሙ በኋላ ሥዕሏን ሳይገዙ ወደ አገራቸው ለመመለስ ጉዞ ጀመሩ፡፡ ያን ጊዜም "ሥዕል መግዛትን ለምን ረሳህ?" የሚል የሚያስደነግጥ ቃልን ሰምተው ተመልሰው መልኳ ያማረና የተወደደ የእመቤታችን ማርያምን ሥዕል ገዝተው በሐርና በንጹሕ ልብስ ጠቅልለው ይዘው እየተጓዙ ሳሉ ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ሲደርሱ ወንበዴዎች ተነሱባቸው፡፡ ሊሸሹ ሲሉም "መንገድህን ሒድ" የሚል ቃል ከሥዕሏ ወጣ መነኵሴውም መንገዳቸውን በሰላም ተጓዙ፡፡ ሁለተኛም አንበሳ ሊበላቸው በተነሣባቸው ጊዜ ከዚያች ሥዕል የሚያሥፈራ ድምፅ ወጥቶ አንበሳውን አባረረላቸው፡፡ አባ ቴዎድሮስ ይህን ኹሉ ድንቅ ተአምር ባዩ ጊዜም ያቺን ሥዕል ለማርታ ከመስጠት ይልቅ ወደ አገራቸው ሊወስዷት ወደዱ፡፡ በመርከብ ተሳፍረው በሌላ አቅጣጫ ሲሔዱም ታላቅ ነፋስ ተነሥቶ ወደ ማርታ አገር ወደ ጼዴንያ ወሰዳቸው፡፡ ከመርከብም ወርደው ከብዙ እንግዶች ጋር ወደዚያች መበለት ቤት ደረሱ፡፡ነገር ግን ማንነታቸውን ለማርታ አልገለጡላትም እርሷም አላወቀቻቸውም ነበር፡፡ በማግሥቱም ተሠውረው ወደ አገራቸው ሊሔዱ ሲሉ የቅፅሩ ደጃፍ ጠፍቶባቸው ሲፈልጉ ዋሉ በመሸባቸው ጊዜም ወደ ማደሪያቸው ተመለሱ፡፡ ማታ ማታ በሩን ያዩታል፤ ነግቶ መሔድን ሲሹ ግን የበሩ መንገድ ይሠወርባቸዋል፡፡ እንዲህም ኾነው እስከ ሦስት ቀን ድረስ ቆዩ፡፡ ማርታም "አባቴ ሆይ አእምሮህ ተነክቷልን? ስትቅበዘበዝ አይሃለሁና ምን ኾነህ ነው?" ሰትል ጠየቀቻችው፡፡ እርሳቸውም ከእመቤታችን ሥዕል የተደረገውን ተአምር ሁሉ ነገሯት፤ ራሳቸውንም ገለጡላትና ሥዕሏን ሰጧት፡፡ እርሷም የእመቤታችንን ሥዕል ተቀብላ የተጠቀለለችበትን ልብስ በፈታችው ጊዜ ወዝ ከሥዕሊቱ ሲንጠፈጠፍ አገኘች፡፡ ከደስታዋ ብዛት የተነሣም የአባ ቴዎድሮስን እጃቸውንና እግራቸውን ሳመች፡፡ ሥዕሏም ቅዱስ ሉቃስ የሳላት ነበረች፡፡ ከዚህም በኋላ ያቺን ሥዕል ወደ ጸሎት ቤቷ ወስዳ በታላቅ ክብር አኖረቻት፡፡ ማንም እንዳይዳስሳትም የነሐስ መስኮትን ሠራችላት፡፡ በቀንና በሌሊትም የሚያበሩ መቅረዞችን በፊቷ ሰቀለች፤ ከመቅረዞች ውጭም የሐር መጋረጃን ጋረደች፡፡ ከሥዕሊቱ በታችም እየተንጠፈጠፈ የሚወርደው የወዝ ቅባት የሚጠራቀምበት ከዕብነ በረድ የተሠራ ወጭት አኖረች፡፡ እኒያ መነኰስም እስከሚሞቱበት ቀን ድረስ የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ሥዕል እያገለገሉ ኖሩ፡፡ የአገሩ ሊቀ ጳጳስም የእመቤታችን ሥዕል ሥጋ የለበሰች ሆና ባገኙና ተአምሯንም በተመለከቱ ጊዜ ከዚህ አምላካዊ ግብር የተነሣ አደነቁ፡፡ ከሥዕሏ ከሚንጠባጠበው ቅባት ቀድተው ለበረከት ሲካፈሉም ወዲያውኑ በወጭቱ ውስጥ መላ፡፡ ሥዕሊቱን ወደ ሌላ ቦታም ሊወስዷት በፈለጉ ጊዜም ንውጽውጽታ ሆኖ ብዙዎች በድንጋጤ ወደቁ፡፡ ሥዕሊቱም እስከ ዛሬ ድረስ በዚያች አገር በጼዴንያ ትገኛለች፡፡ "እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው"ተብሎ እንደ ተጻፈ መዝ ፷፯፥፴፭ እግዚአብሔር አምላካችን በልዩ ልዩ መንገድ ለሰው ልጅ ተአምራቱን ይገልጣል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግቦ እንደምናገኘው እግዚአብሔር ከዓለት ላይ ውኃ እያፈለቀ ሕዝቡን ያጠጣል፡፡ ከግዑዝ ዓለት ውስጥ ውኃ የሚያፈልቅ አምላክ ከሥጋዋ ሥጋ፤ ከነፍሷ ነፍስ ተዋሕዶ ካከበራት ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ወዝ እንዲፈስ ቢያደርግ ምን ይሳነዋል? እንደዚሁም ቅዱሳን ሐዋርያት በቃላቸውም፣ በልብሳቸውም፣ በጥላቸውም ሙታንን በማስነሣት፤ ሕሙማንን በመፈወስ ተአምራትን ያደርጉ ነበር፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላው፤ ቅዱስ ጳውሎስም በልብሱ ቅዳጅ ያደርጓቸው የነበሩ ተአምራትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ሐዋርያት ከእግዚአብሔር ዘንድ በተሰጣቸው ጸጋ በልብሳቸውና በሰውነታቸው ጥላ ተአምራትን ማድረግ እንደ ተቻላቸው ኹሉ አምላክን በማኅፀኗ የተሸከመችው ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምም በሥዕሏ ወዝ ብዙ ሕሙማንን መፈወስ ይቻላታል፡፡ ከቅዱሳን ልብስና ጥላ የእርሷ ሥዕል ይከብራልና፡፡ በየዓመቱም መስከረም ፲ ቀን ቤተ ክርስቲያናችን ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት ውስጥ አንዱ አድርጋ በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፤ የልጇ፣ የወዳጇ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነት አይለየን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፦የመስከረም ፲ ስንክሳር፣ ተዓምረ ማርያም፣ ማህበረ ቅዱሳን ብሎግ ዲ/ን የአብስራ ጌታሁን https://t.me/Eotcw

#ቡርክት_አንቲ ቡርክት አንቲ ጼዴንያ ዘመልዕልተ አድባር ትነብሪ ቡርክት አንቲ(፪) እስመ ኩሉ ዘሥጋ(፪) ያንቅአዱ ሀቤኪ ያንቅአዱ ጼዴንያ ማርያም #ትርጉም፦ ከ አድባራት ሁሉ ከፍ ብለሽ የምትታይው ጼዴንያ ቡርክት ነሽ። ሥጋውያን ፍጥረታት ሁሉ ወዳንቺ ያንጋጥጣሉ። በፍኖተ ብርሃን ጼዴንያ ስመኝ ማርያም ሰ/ት/ቤት https://t.me/Eotcw

✞ጼዴንያ ማርያም✞ ጼዴንያ ማርያም(፪) ታላቅ ነሽ ዘለዓለም(፪) ክብርሽም ገነነ በዓለም ገስግሼ መጣሁኝ - - - ንዒ ድንግል ማለዳ ቤትሽ - - - ንዒ ድንግል ዝክርሽን አስቤ - - - ንዒ ድንግል ቀስቅሶኝ ፍቅርሽ - - - ንዒ ድንግል አዝ= = = = = እንደ አባ ቴዎድሮስ - - - ቅዱስ ስዕልሽ እንደ ደጓ ማርታ - - - ቅዱስ ስዕልሽ ነፍሴ ተደሰተች - - - ቅዱስ ስዕልሽ ስዕልሽን አይታ - - - ቅዱስ ስዕልሽ አዝ= = = = = ሽፍታው ክንዱ ዛለ - - - በአንቺ ብርሃን አንበሳው ተረታ - - - በአንቺ ብርሃን በአስፈሪው በረሃ - - - ንዒ ድንግል አዛኝቷ መጥታ - - - ንዒ ድንግል አዝ= = = = = ሉቃስ የሳላት - - - ቅዱስ ስዕልሽ ስመኛት ነበረ - - - ቅዱስ ስዕልሽ ዛሬ ተሳለምኳት - - - ቅዱስ ስዕልሽ ሀሳቤ ሰመረ - - - ቅዱስ ስዕልሽ በፍኖተ ብርሃን ጼዴንያ ስመኝ ማርያም ሰ/ት/ቤት https://t.me/Eotcw