ሰዋስው ☘☘☘☘
Ir al canal en Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
Mostrar más1 161
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
1 161
በእነስድስታይ አገር ላሉ ሰዎችም ሁሉ አባት ሆናቸውና የመንፈስ ቅዱስ ልጁንም ታዲዮስን መምህርና አባት አድርጎ ሾመላቸውና ጽላልሽ ሄዶ እናቱን ይዞ ጽጋጋ ምድረ ወገግ ወስዶ አመነኰሳት፡፡
❤ አቡነ ሳሙኤል ወደ ምድረ ርስቱ ደብረ ወገግ እየሄደ በዚያ ያሉ ልጆቹን እያጽናና ወደ እንደግብጦን አውራጃም እየተመለሰ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ፣ ወንጌልን እያስተማረ፣ ጣዖት አምላኪዎችን ወደ ክርስትና እየቀየረ፣ አጋንንትንና መመለኪያ ቦታዎቻቸውን እያጠፋ፣ አብያተ ክርስቲያናትን እያነጸ በብዙ ተጋድሎ ኖረ፡፡ በቅዱስ ገድሉ ውስጥ በጣም አስገራሚ በሆነ መልኩ እጅግ ብዙ ታሪኮች ተጠቅሰዋል፡፡ እነዚህም ታሪኮች ውስጥ አቡነ ሳሙኤል በሀገራችን በጣም ብዙ ጣዖታትንና መመለኪያ ቤቶቻቸውን እያጠፉ፣ በሰዎች (በጠንቋዮች) ላይ፣ በዛፍና በባሕር ውስጥ አድሮ ይመለኩ የነበሩ ሰይጣናት አጋንንትን በሚያመልኳቸው ሰዎች ፊት እያጋለጡና እያዋረዱ ሰዎቹን አስተምረው አጥምቀው ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር እየመለሷቸው ቤተክርስቲያንም በመሥራት ሐዋርያትን መሰሉ፡፡
❤ ሰይጣን አድሮባቸው የነበሩ ጠንቋዮች ይጠቀሙባቸው የነበሩ ዕቃዎችን ጻድቁ እየባረኩና እየቀደሱ ለቤተክርስቲያን መሥሪያና መጠቀሚያነት ያውሉት ነበር፡፡ ይህም ገና ሳይወለዱ በአቡነ ተክለሃይማኖት ትንቢት ተነግሮላቸው ነበር፡፡ አቡነ ተክለሃይማኖት "ጣዖታትን የሚሰብር፣ አጋንንትን በጸሎቱ የሚያርቅ፣ ሕዝብን ከኃጢአት በሽታ የሚያድን፣ ፈጣሪውን የሚያስደስት ደግ ልጅ ይሆናል" ብሎው ትንቢት እንደተናገሩላቸው አቡነ ሳሙኤል በሰዎች፣ በባሕርና በዛፍ ላይ እያደሩ ይመለኩ የነበሩ በጣም ብዙ አጋንንትን አጠፏቸው፡፡ ጠንቋዮችንም በውስጣቸው ካደረባቸው ሰይጣን እያላቀቁ የእግዚአብሔር አገልጋይ ያደርጓቸውና ያመነኩሷቸው ነበር፡፡
❤ ጻድቁ አባታችን አባ ሳሙኤል ወንጌልን ዞረው በማስተማር ሐዋርያትን መሰሉ፣ ከዓላውያን ጋር ለመዋጋት ሰውነታቸውን ለሞት በመስጠት ሰማዕታትን መሰሉ፣ በጾም በጸሎት በስግደት በተጋድሎ ቅዱሳን ጻድቃንን መሰሉ፣ ይህን ኃላፊና ጠፊ ዓለም ንቀው በመተው ባሕታውያንን መሰሉ፣ በደልንና ኃጢአትን በማስተሠረይ ካህናትን መሰሉ፣ በጽሕናና በቅድስና መላእክትን መሰሉ እንደዚሁም ሌሎች ብዙ አስደናቂ ተአምራትንም በማድረግ ይታወቃሉ፡፡ በትእምርተ መስቀል አድርገው እንደሙሴ ባሕርን ለሁለት ከፍለዋል፣ እንደ ኢያሱ በጸሎታቸው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ ሳሙኤል ተጋድሎአቸውን ፈጽመው ከጌታችን ታላቅ ቃኪዳን ተቀብለው በዚህች ዕለት በሰላም ዐርፈዋል፡፡
❤ በአሰቦት ደብረ ወገግ ገዳም ውስጥ የተሰወሩ እጅግ በርካታ ቅዱሳን ስለመኖራቸው በገድለ አቡነ ሳሙኤል መቅድም ውስጥ በሰፊው ተጠቅሷል፡፡ አሁንም ሆነ ወደፊት በቦታው ላይ የተሰወሩት ቅዱሳን ለገዳማውያንኑም ሆነ በዓለም ለሚኖሩ ምግባርን ከሃይማኖት አስተባብረው ለያዙ ሰዎች እየተገለጡላቸው ይታዩዋቸዋል፣ መልእክትም ይነግሯቸዋል፡፡ እንዲሁም ስውራኑ ባሉበት ቦታ የከበሮ ድምጽ ይሰማል፣ ዕጣን ይሸታል፣ ቀንና ሌሊት አራዊት ሲሰግዱበትና ሲጠብቁት ይታያል፡፡ ከአባታችን አቡነ ሳሙኤል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን።
+ + +
❤ የደብረ ዘኸኝ መምህር አባ ጸቃውዐ ድንግል፦ የዚህም ቅዱስ አባቱ ካህን ነው በጥበብና በበጎ ተግሣጽም አሳድገው መለኮታዊ ትምህርትን ሁሉ አስተማረው አድጎ አርባ ዓመትም በሆነው ጊዜ አባቱ ከአንድ ገዳም ውስጥ መነኰሰ ለመምህርነትም ተመርጦ በአባ ገብረ ማርያም ወንበር ላይ ተሾመ። በዚያንም ጊዜ አባቱ ለልጁ የምንኵስና ልብስ አለበሰው ስሙንም ጸቃውዐ ድንግል ብሎ ሰየመው ከዚያችም ጊዜ ጀምሮ ያለማቋረጥ በጾም በጸሎት ብዙ በመስገድም ታላቅ ተጋድሎንም ተጋደለ።
❤ ከዚህም በኋላ አባቱ በዐረፈ ጊዜ በአባቱ ፋንታ ተሾመ መንጋዎቹንም እንደ ሐዋርያት ሥርዓት በመልካም አጠባበቅ ጠበቃቸው። በሌሊቱም ሁሉ ከባሕር ውስጥ ቁሞ ያድራል ከባሕሩ ሲወጣ ወዙ በምድር ላይ እስከሚንጠፈጠፍ ሥግደትን ያዘወትራል ምግቡም ደረቅ እንጀራ ነው ጠጅ ወይም ጠላ አይጠጣም እግዚአብሔርም በእጁቹ ላይ ተዓምራትን አደረገ በጎዳናም ሲጓዝ ከታናሽነቱ ጀምሮ ሔዶ የማያውቅ መፃጒዕን አገኘ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ" ብሎ የተጸለየበትን ውሃ በላዩ ረጨ በመስቀልም ምልክት አማተበ በዚያን ጊዜ ዳነ።
❤ ከዚህም ዓለም የሚለይበት ሰዓት በደረሰ ጊዜ ጥቂት ታሞ ጥምቀት 29 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጸቃውዐ ድንግል ጸሎት ይማረ በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር። ምንጭ፦ የጥቅምት 29 ስንክሳር።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ጥቅምት ፳፱ (29) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያኑ ጻድቃን ለታላቁ አባት ለአቡነ ታዴዎስ ዘጽላልሽ ግመልን በመርፌ ቀዳዳ አሳልፈው ሙት አስነስተው ብዙ ሕዝብ ላሳመኑበት ለተአምራት በዓላቸው፣ በምዕራብ ሐርጌ በሜኤሶ ወረዳ የሚገኘውን ታላቁ ገዳም አሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ለመሰረቱት ለታላቁ አባት ለአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ለዕረፍታቸው በዓልና ለተመሰገነና ለከበረ ለዘኸኝ መምህር ለጸቃውዐ ድንግል ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ አቡነ ታዴዎስ ያደረጉት ተአምር ይህ ነው፦ በአቡነ ታዴዎስ አላምንም የሚል ኢሳ የሚባል አንድ የእስላም ንጉሥ ተነሳ እና እንዲህ አላቸው "ስም ታዴዎስ ነው ሐዋርያው ታዴዎስ ግመል በመርፌ ቀዳዳ አስወጥቷል ይባላል አስወጣና ልመንብህ" አላቸው። ይህን ቃል ሲናገራቸው አቡነ ታዴዎስ ሳቁበት "በል ግመልና መርፌ አምጣ እኔ አሳይሃለው" ሲሉት ሠላሳ ግመል አመጣ አቡነ ታዴዎስም "በል መርፌውን በእጅህ ያዘው ቀዳዳውን ወደ ግመሊቱ አዙረህ" አሉት ወደ ግመሊቱ ቀርበው "በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አዝዝሻለሁ" ሲሏት አንገቷን በመርፌው አስገብታ ከልጇ ጋር ወጣችና ሃያ ስምንቱን መጀመሪያ የወጣችቱ ግመል እንደ ሰው እየጠራቻቸው ወጡ ይህንን ድንቅ ስራ ያየ መርዩጥም ሆነ ሰራዊቱ የደብረ ማርያም ህዝብ ሲያደንቁ።
❤ በዚያን ጊዜ የኢሳ ልጅ ሙሳ ሳቀ "በምትሃት እንጂ በብቃት አላወጣም" ብሎ ሲጠራጠር አንዲቱ ግመል ሆዱን በእርግጫ ስትመታው ሞተ አንጀቱ ተጎለጎለ በዚያን ጊዜ ሰው ሁሉ ደነገጠ ንጉሡም ደነገጠ ወዲያ ወዲህ እየሮጠ "አባቴ ሆይ እማፀንሃለው ማረኝ እንደሙሳ አልሳቅሁም" አቡነ ታዴዎስም "መዩጥ ሆይ ከልብህ እመን ከዚህ በላይ ታያለህ ከእግዚአብሔር የሚሆንን ነገር ምንም የሚያገኝህ ነገር የለም አትፍራ ከልብህ ካመንክ የሞተው ይነሳል ስላንተ አምላኬ ያነሳዋል" በዚህ ጊዜ መዩጥ አቡነ ታዴዎስን "እንዴት ሆኖ የሞተ ሰው ይነሳል በል አንተ አስነሳው የደራ ህዝብ ያምን ዘንድ በአምላክህ" አቡነ ታዴዎስ መዩጥን "ይቅበሩት እዘዝ ነገ ያነሳዋል ከተቀበረ በኋላ ነገ ሁሉ ሰው ከዳር እስከ ዳር ወንድ ሴት ትልቅ ትንሽ ሳይባል ይሰብሰብ ይህ ሬሳ የተነሳ እንደሆነ በአምላኬ እንድታምኑ ካልተነሳ እኔን ግደለኝ ከዚህ በኋላ ቅበሩት በዚች ቀን ጠዋት ከደብረ ማርያም ያልተገኘ ክፉ ሞት ይሞታል" አለ በዚች ሌሊት አቡነ ታዴዎስ ከደብረ ማርያም ቤተ ክክርስቲያን ውስጥ ከቅድስት ሆነው በየሰዓቱ መቶ መቶ ስግደት እየሰገዱ "ከመቃብር አላዓዛርን እንዳስነሳህ ይህንንም ሙት አንሳው" መዩጥ እንዲምን ብሎ እየጸለዩ ሳሉ ከሌሊቱ 11ሰዓት ጥቅምት 29 ቀን መልአከ እግዚአብሔር ወርዶ "የሞተው ይነሳል ስለ አንተ ጸሎት ብሎ ይችን ደብረ ማርያምን አሥራት አድርጌ ሰጥቸሃለሁ በእኔም ስም ስላገኘህ ችግር በጾም በጸሎት ሃይማኖትን በማስተማር ከአጋንንት ጋር በመጋደልህ ከክፉ ሰዎች ጋር በመጋደልህ ደብረ ማርያምን የልጆችህ ርስት አድርጌ ሰጥችሀለሁ እስከ መጨረሻው ድረስ" ብሎት መልአከ እግዚአብሔር ወደ ሰማይ አረገ።
❤ አቡነ ታዴዎስም እስከ ከቀኑ ሦስት ሰዓት ሲጸልዩ አደሩ ህዝቡ ተሰብስበው ሳለ መዩጥ መጣና ከሰራዊቱ መካከል ተቀመጠ አቡነ ታዴዎስም ጠራቸው "አባቴ ሆይ ትናት እዳልከኝ አድርግ በህዝቤ መካከል የሰበሰብኋቸው ስላንተ ነውና" ሲላቸው "በል የሙቱን አባት አምጣው ወደ እኔ" ሲሉ አቀረቡላቸው አቡነ ታዴዎስም ለአባቱ መስቀላቸውን ሰጡትና እንደ "አላዓዛር ተነስ በለው ይነሳልሃል" አሉትና የአቡነ ታዴዎስን መስቀል ይዞ ተነሳ ሲለው ሙቱ ተነስቷል ከዚህም በኋላ የደራ ህዝብ በመላው አምኖ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቀው ሃይማኖትን አስተምረው 12 ቤተ ክክርስቲያን አሳነጹ። ከአባታችን አቡነ ታዴዎስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን። ምንጭ፦ የጣና ሐይቅ ደብረ ማርያም ገዳም አጭር ታሪክ ከምትላው መጸሐፍ።
+ + +
❤ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ፡- ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል እንድርያስና አርሶንያ ከሚባሉ የበቁ ደጋግ አባትና እናታቸው የተወለዱት በሸዋ ሀገረ ስብከት ቀድሞ ጽላልሽ ዛሬ ቡልጋ በሚባለው አውራጃ ነው፡፡ የወላጆቻቸው በጎ ምግባርና ሃይማኖት ቅዱስ ተክለሃይማኖትን ከደብረ ሊባኖስ አነሣስቶ በቤታቸው ሄደው እንዲስተናገዱ አድርጓል፡፡ ልጅ ስላልነበራቸው ያዝኑ ነበርና አቡነ ተክለሃይማኖትም በጸጋ እግዚአብሔር ተገልጾላቸው "እግዚአብሔር ጣዖታትን የሚሰብር፣ አጋንንትን በጸሎቱ የሚያርቅ፣ ሕዝብን ከኃጢአት በሽታ የሚያድን፣ ፈጣሪውን የሚያስደስት ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ" ብለው ትንቢት ነግረዋቸዋል፡፡ በትንቢቱም መሠረት አቡነ ሳሙኤል ሐምሌ 10 ቀን 1248 ዓ.ም ሲወለዱ መልካቸው በአራት ልዩ ልዩ ሕብረ መልክ እየተለዋወጠ አንድ ጊዜ እንደ በረዶ፣ አንድ ጊዜ እንደ እሳት፣ አንድ ጊዜ እንደ ልምላሜና ቢጫ ሆነው ታይተዋል፡፡
❤ አቡነ ተክለሃይማኖትም በአባቱ እንድሪያስ በኩል የሥጋ ዘመዱ ሲሆኑ የመንፈስ ቅዱስም አባት ሆኑትና በ40 ቀን ክርስትና አንስተው ስመ ክርስትናውን "ሳሙኤል" አሉት፡፡ ትርጓሜውም "እግዚአብሔር ጸለቴን ሰማኝ" ማለት ነው፡፡ ከሕፃንነትም ጀምረው በምግባር በሃይማኖት ኮትኩተው አሳድገው ለዲቁና አብቅተው በኋላም አመንኵሰውታል፡፡ የመሠረቱት ገዳም "ደብረ ወገግ" የሚለው ስያሜ የተገኘው ከመላእክት ነው፡፡ ድርሳነ ዑራኤል በሰፊው እንደሚያትተው ቅዱስ ዑራኤል የጌታችንን ደም በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ ዓለምን እየረጨ ሲቀድሳት የያዘውን ጽዋ በደብረ ወገግ ቆሞ ሳለ ነው ጨልጦ ያንጠፈጠፈው፡፡ ያንጊዜም ደብረ አስቦን የብርሃን ውጋጋን ሲያጥለቀልቀው መላእክትም "ቦታውን ደብረ ወገግ" (የብርሃን ተራራ) ብለው ሰይመውታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም "ወደፊት ፈጣሪውን የሚያገለግል ታላቅ ጻድቅ ይወጣባታልና ይህችን ቦታ ባርካት" ብሎ ቅዱስ ዑራኤልን በነገረው መሠረት ባርኳት" እንዳረገ ድርሳነ ዑራኤል ላይ በሰፊው ተጽፏል፡፡
❤ በቦታው ላይ ብዙ ጊዜ የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ መታየቱን የበቁ ገዳማውያን ብቻ ሳይሆኑ በከተማ ያሉና ለመሳለም ወደ ቦታው የሄዱ ደገኛ ሰዎችም በዐይናቸው ያዩትን ይናገራሉ፡፡ በገዳሙ ዙሪያ እጅግ በጣም ብዙ ስውራን ቅዱሳን እንዳሉ በግልጽ ይታወቃል፡፡
❤ ንጉሥ ዓምደ ጽዮን በክፉዎች ምክር የአባቱን ሚስት እንጀራ እናቱን በማግባቱ ምክንያት አቡነ ፊሊጶስ ጋር ሆነው ያወገዙትን የቅዱስ ተክለሃይማኖትን ወገኖች በየአውራጃው በተናቸው፡፡ አቡነ ፊሊጶስንም ደሙ በምድር ላይ እስከሚንጣለል ድረስ ገርፈው ወደነበረበት ቤቱ ወሰዱት፤ ፊሊጶስም በሚሄድበት ቦታ ላይ ሳይደርስ በመንገድ ሞተ፡፡ እንድርያስ፣ አኖሬዎስና ተክለ ጽዮን ሁላቸው ከተከታዮቻቸው ጋር በሰማዕትነት አርፈው እነስድስተይ በምትባል ምድር ተቀበሩ፡፡ ጳጳሱን አቡነ ያዕቆብንም ደሙ በምድር ላይ እንደውኃ እስኪወርድ ድረስ ገርፈው ወደ ሀገሩ እንዲሰደደ አደረጉት፡፡ ከዚያም በኋላ ሃይማኖቱ የቀና ደግ ጻድቅ ንጉሥ ዳዊት በነገሠ ጊዜ አባታችን ሳሙኤል ዘወገግን አገኘውና "መማጸኛ እንዲሆነኝ በእንድርያስ መቃብር ላይ ቤተክርስቲያን ሥራልኝ" ብሎ ለመነውና የሩፋኤልን ቤተ ክርስቲያን ሠራለት፡፡ የእንድርያስንም አጽም ከመቅደሱ ስር አኖረው፡፡ ንጉሡም በዚያ በእንደግብጦን አውራጃ ሁሉ ላይ ፓትርያርክ አድርጎ ሾመው፡፡
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ሉቃ. 20:37-41 "ወከምሰ የሐይው ምውታን" - "ሙታን፡እንዲነሡ፡ግን፡ሙሴ፡ደግሞ፡በቍጥቋጦው፡ዘንድ፡ጌታን፡የአብርሃም፡አምላክ፡የይሥሐቅም፡አምላክ፡የያዕቆብም፡አምላክ፡በማለቱ፡አስታወቀ፤ ሁሉ፡ለርሱ፡ሕያዋን፡ስለ፡ሆኑ፥የሕያዋን፡አምላክ፡ነው፡እንጂ፡የሙታን፡አይደለም። ከጻፊዎችም፡አንዳንዶቹ፡መልሰው፦መምህር፡ሆይ፥መልካም፡ተናገርህ፡አሉት። ወደ፡ፊትም፡አንድ፡ነገር፡ስንኳ፡ሊጠይቁት፡አልደፈሩም። እንዲህም፡አላቸው፦ ክርስቶስ፡የዳዊት፡ልጅ፡ነው፡እንዴት፡ይላሉ?"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
28/2/2015 ዓ.ም (፳፰/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
ትውልደ ጻድቃን ይትባረኩ።
ክብር ወብዕል ውስተ ቤቱ።
ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም። መዝ 111፥2
🕯 ትርጉም
የቅኖች ትውልድ ትባረካለች።
ክብርና ባለጠግነት በቤቱ ነው።
ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ማቴ. 12:44-ፍ፡ም፡"ወእምከመ ወጽአ መንፈስ" - "በዚያን፡ጊዜም፦ወደወጣሁበት፡ቤቴ፡እመለሳለሁ፡ይላል፤ቢመጣም፡ባዶ፡ሆኖ፡ተጠርጎና፡አጊጦ፡
ያገኘዋል። ከዚያ፡ወዲያ፡ይሄድና፡ከእርሱ፡የከፉትን፡ሰባት፡ሌላዎችን፡አጋንንት፡ከእርሱ፡ጋራ፡ይወስዳል፥ገብተውም፡በዚያ፡ይኖራሉ፤ለዚያም፡ሰው፡ከፊተኛው፡ይልቅ፡የኋለኛው፡ይብስበታል።ለዚህ፡ክፉ፡ትውልድ፡ደግሞ፡
እንዲሁ፡ይሆንበታል። ገናም፡ለሕዝቡ፡ሲናገር፥እንሆ፥እናቱና፡ወንድሞቹ፡ሊነጋገሩት፡ፈልገው፡በውጭ፡ቆመው፡ነበር። አንዱም፦እንሆ፥እናትህና፡ወንድሞችህ፡ሊነጋገሩህ፡ፈልገው፡በውጭ፡ቆመዋል፡አለው። እርሱ፡ግን፡ለነገረው፡መልሶ፦እናቴ፡ማን፡ናት? ወንድሞቼስ፡እነማን፡ናቸው?አለው። እጁንም፡ወደ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ዘርግቶ፦እንሆ፥እናቴና፡ወንድሞቼ፤ በሰማያት፡ያለውን፡የአባቴን፡ፈቃድ፡የሚያደርግ፡ሁሉ፥ርሱ፡ወንድሜ፡እኅቴም፡እናቴም፡ነውና፥አለ።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
28/2/2015 ዓ.ም (፳፰/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
ይጸንሑኒ ወይትኀብኡኒ።
እሙንቱሰ ሰኰናየ ያስተሐይጹኒ።
ወዘልፈ ይጸንሕዋ ለነፍስየ፡፡ መዝ. 55:6
🕯 ትርጉም
ይሸምቁብኛል ይሸሽጉኝማል።
እነርሱም ተረከዜን ይመለካከታሉ።
ሁልጊዜም ነፍሴን ይሸምቁባታል።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ "ሰላም ለአባ ይምአታ ዘከለሎ እግዚአብሔር ወልታ"። ትርጉም፦ ጋሻ እግዚአብሔር የጋረደው ለኾነ ለአባ ይምታ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ "ሰላም ሰላም ለአባ ይምዓታ ዘተሳተፈ አዕሩገ። እለ ኃሠሡ ሥርዓተ ወእለ ዐቀቡ ሕገ። በሥምረተ አምላክ ከሃሊ እንተ ሠጠቀ አፍላገ። በድነ ሥጋሁሰ አመ መልዕልተ ደብር ዐርገ። ዐሠረ ግንዘቱ በኰኵሕ ለትእምርት ተኀድገ"። ትርጉም፦ በከሃሊ አምላክ ፈቃድ ወንዝን ለኹለት የከፈለ፤ ሥርዐትን ከሹና ሕግንም ከጠበቁ ሽማግሎዎች ጋር የተባበረ ለኾነ ለአባ ይምአታ ሰላምታ ይገባል፣ የሥጋው በድን ግን ወደ ተራራ ላይ በወጣ ጊዜ የግንዘቱ ምልክት በዐለት ላይ ለምልክት ቀረ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት 28።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ጥቅምት ፳፰ (28) ቀን።
❤ እንኳን ለቅዱስ አማኑኤል ዓመታዊ በዓል፣ አባቱ ኖኅ እግዚአብሔር የያፌትን አገር ያስፋለት ብሎ ለመረቀው ለቅዱስ ያፌት ለመታሰቢያ በዓሉ፣ ለቅዱሳን ሰማዕታት ለመርትያኖስና ለመርቆሬዎስ ዕረፍታቸው በዓል፣ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአባ መቅብዩ፣ ከአባቶቻችንም ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፭ "ጸገየ ወይን ወፈርየ ሮማን ወፈርዩ ኵሉ ዕፀወ ገዳም ቀንሞስ ዕቁረማየ ልብን ሠርዐ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ ጸገዩ ጽጌያት ጸገዩ ደንጐላት፤ አዝ፣ ኃለፈ ክረምት ቆመ በረከት ተሠርገወት ምድር በስነ ጽጌያት፤ አዝ፣ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት ሠርዐ ለነ ሰንበተ ለእረፍተ ዚአነ ሠርዐ ለነ ሰንበተ ለዕረፍት ወለመድኃኒት። ትርጉም፦ አበቦች አበቡ የሱፍ አበቦችም አበቡ፣ ክረምት አለፈ በረከት ተተከለ፣ ምድር በአበቦች ውበት ተጌጠች አቤቱ የሰንበት ጌታ የምረት አባቷ ለዕረፍትና ለመድኃኒት ሰንበት ሠራ። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ ቅዱሳን ሰማዕታት መርትያኖስና መርቆሬዎስ፦ እሊህም ለቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ለአባ ጳውሎስ ደመ መዛሙርቱ ናቸው ይህም እንዲህ ነው አርዮሳዊ የሆነው ሁለተኛው ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ አባ ጳውሎስን በተጣላው ጊዜ ወደ አርማንያ አጋዘውና በዚያም በሥውር አሥር ቤት ውስጥ አንቀው እንዲገድሉት አደረገ እሊህ ቅዱሳን መርትያኖስና መርቆሬዎስ ግን የዕረፍቱን ቀን ገድሉንም ጻፉ አርዮሳዊውያን ንጉሥ ረገሙት።
❤ አንድ ክፉ ሰውም ወደ ንጉሡ ሒዶ እነርሱ እንደረገሙት ወነጀላቸው ንጉሡም ያን ጊዜ ከአታክልት ቦታዎች በአንዲቱ ቦታ ተቀምጦ ሳለ ወታደሮች ልኮ ወደርሱ አስቀረባቸው በሰይፍም እንዲገድሏቸው አዝዞ ገደሏቸው በዚያም በገደሏቸው ቦታ ቀበሩአቸው እስከ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ዘመንም በዚያ ቦታ ኖሩ እርሱም ዜናቸውን በሰማ ጊዜ መልእክተኞችን ልኮ ሥጋቸውን ወደ ቊስጥንጥንያ በክብር አስመጣ ያመረች ቤተ ክርስቲያንንም ሠርቶላቸው ሥጋቸውን በውስጧ አኖረ በዚችም ቀን ጥቅምት 28 በዓልን አደረገላቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ቅዱሳን ሰማዕታት መርትያኖስና መርቆሬዎስ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት28 ስንክሳር።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ትውልደ ጻድቃን ይትባረኩ። ክቡር ወብዕል ውስተ ቤቱ። ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም"። መዝ 111፥12-13። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 6፥9-15፣ 1ኛ ጴጥ 4፥12-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 3፥12-17። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 20፥36-41። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ አማኡኤል በዓል፣ የአቡነ ይምአታ የዕረፍት በዓልና የጽጌ ጾም ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ጥቅምት ፳፰ (28) ቀን።
❤ እንኳን ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ ለሆኑት በሞት በዐረፉ ጊዜ የሥጋቸው ሥርዓተ ግንዘት በቅዱሳን መላእክት እጅ ለተከናወነው ለታላቁ አባት ለአቡነ ይምዓታ ዘጎሕ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ አቡነ ይምዓታ ዘጎሕ፦ አቡነ ይምዓታ ከዘጠኙ ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ እጅግ አስገራሚው ቤተ መቅደሳቸው ትግራይ ገርዓልታ ልዩ ስሙ "ጎሕ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ይገኛል፡፡ ቤተ መቅደሱ ሰማይን እንደ ምሰሶ ደግፈው የያዙ የሚመስሉ በጣም ረጃጅም ተራሮች መካከል በአንደኛው ጫፍ ላይ ይገኛል፡፡ ቤተ መቅደሱ ከባሕር ወለል በላይ በ2300 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ቤተ መቅደሱ ያለበት የተራራው ርዝመት ብቻውን 300 ሜትር ነው፡፡ ቤተ መቅደሱ በር ላይ ለመድረስ በጭንቅና በፍርሃት ሆኖ ተራራውን እንደዝንጀሮ በእጅ እየቧጠጡ መውጣት ይጠይቃል፡፡
❤ ቤተ መቅደሱ እጅግ የሚደንቀው በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ ብቻ አይደለም ውስጡ ያሉት የግድግዳ ላይ ሥዕሎችም በ15 ኛው መ/ክ ዘመን የተሣሉ እጅግ ድንቅና ጥንታዊ ናቸው፡፡ ስለዚሁ የአቡነ ይምዓታ እጅግ አስደናቂ ቤተ መቅደስ ገድለ አቡነ አረጋዊ" በሞት በዐረፉ ጊዜ የሥጋቸው ሥርዓተ ግንዘት በመላእክት እጅ ነው የተከናወነው፡፡ ይልቁንም ቁመቱና ርዝመቱ ከታላላቅ ገደል እጅግ በጣም የሚበልጥ የድንጋይ ዓምድ ከወንዝ ማዶ ዘንበል ብሎ መጥቶ ሥጋቸውን በክብር ተቀብሎ በተራራው ጫፍ ላይ እስከዛሬም ድረስ ፈጽሞ ሳይነቃነቅና ሳይናወፅ ቀጥ ብሎ ቆሞ ይገኛል" በማለት ይገልጻል፡፡ ከአቡነ ይምአታ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
#መልካም ሚስት ለመሆን ሁሉም ሴት ሊያነበዉ የሚገባ 30 መንፈሳዊ የህይወት መርህ ህግ! አብቡ ይጠቅማችዃል።
ሴት ሆይ
1ኛ በምንም ምክንያት ባልሽ ላይ ጮክ ብለሽ አትናገሪ።
ምክንያቱም ባል ላይ መጮህ የመናቅ ምልክት ነዉና። ምሳ 15÷1
2ኛ የባልሽ ድክመት የቤተሰቦችሽ ሆነ ለጓደኞችሽ ከቶ አትግለጪ። ምክንያቱም መልሶ ወዳንቺ ነገሩ ይመጣልና።አንቺ የእያንዳንዳችሁ ጠባቂ ነሽና።ኤፌ 5÷12
3ኛ ከባልሽ ጋር ስትነጋገሪ የተለየ የአካል እንቅስቃሴዎችሽን እንደ ሚተርጉም አታዉቂም።ኃይለኛ እና ቁጡ ሴት ደስተኛ ቤት አይኖራትም።ምሳ 15÷13
4ኛ ባልሽ በፍጹም ከሌላ ወንድ አታመሳስይዉ የሌሎች ወንዶች ህይወት ምን እንደሆነ ከባልሽ በቀር አታዉቂም ባልሽ ከሌሎች ጋር በማነጻጸር በራሱ መተማመኑ ከነጠቅሽ ላንቺ ያለዉን ፍቅር ከልቡ ያጠፋዋል።
5ኛ የባልሽን ጓደኞች ህመም አታስታሚ ምክንያቱም ትጠያቸዋለሽና የነሱ ህመም ሊያስታም የሚገባዉ ራሱ ባልሽ ሊሆን ይገባል።ምሳ 11÷22
6ኛ ባልሽ ወዶሽ እንዳገባሽ እንዳትረሺ።አንቺ ሰራተኛ ወይም ሌላ አይደለሽምና የሚስትነት ኃላፊነት ተወጪ።ዘፍ 2÷24
7ኛ ማንም ባልሽ ላይ ትኩረት እንዲያደርኩ አትፍቀጂ።ሌሎች ያሻቸዉ ሊያደርጉ ይችላሉ ባልሽ ግን ያንቺ ኃላፊነት ነዉ።ኤፌ 5÷33
8ኛ ባልሽ ባዶ እጁ ወደቤት ቢመጣ አትዉቀሹ ይልቁንም አረታችዉ።
9ኛ ከቶም አባካኝ አትሁኚ።የባልሽ ላብ የማያባክኑ እጅግ ዉድ ነዉና።
10ኛ ለግብረ ሥጋ ግኑኝነት በፍጹም እያመመሽ በማስመሰል ባልሽ አትከልኪይዉ።ባልሽ እስከ ፈለገዉ ሁኚለት።ለባል የግብረ ሥጋ ግኑኝነት መሰረታዊ ነዉ።አንቺ ግን በተደጋጋሚ ከከለከልሽዉ ከሌላ ሴት ጋር እንዲወሰልት በር ትከፍቺለታለሽ ወንድ በፍጹም በግብረ ሥጋ ግኑኙነት ለረዥም ጊዜ መቋቋም መዝለቅ አይችልምና።መኃልይ 7÷12
11ኛ ባልሽን ከዚህ ቀደም ከሌላ ወንድ ጋር (ከቀድሞ ፍቅረኛሽ ጋር)ግንኙነት ካረግሽዉ ጋር የእሱ የሥጋ ግኑኙነት በፍጹም አታነጻጽሪ።ይሄ የትዳርሽ ቀድሞ ግኑኙነትሽ ከቶ አይካካስምና።መኃልይ 5÷9
12ኛ ለባልሽ በአደባባይ መልስ አትስጪ።እሱ በአደባባይ ተናግሮሽ ቢሆንም እንኳን ነገሩን በልብሽ ያዢዉ።ምሳ 31÷23
13ኛ ባልሽ ላይ በልጆችሽ ፊት አትቆጪዉ ወይም አትቋቋሚዉ ።ብልህ ሴት ይህ አታደርግምና።ኤፌ 4÷31
14ኛ ባልሽ በሚሰናዳዳበት ጊዜ ተሰማሪዉ እና የሚያስፈልገዉን ታሟይለት ዘንድ አትዘንጊ ።ምሳ 12÷4
15ኛ ጓደኞችሽ ለባልሽ እንዲቀርቡት አታድርጊ።
16ኛ በመዋበያ እና በመታጠቢያ ክፍልሽ ከቶ አትቻኮይ።ዉበትሽን ጠብቂ።ባልሽ በሌላ ቆነጃጂት ተከቦ ሊዉል ስለሚችል እንዳይሰናከል ሁሌም ዉብ ሁኚ።1ኛ ሳሙ 25÷3
17ኛ ወላጆችሽ ወይም ቤተሰቦችሽ ወይም ጓደኞችሽ የህይወትሽ ወሳኝ እንዲሆኑ አትፍቀጂላቸዉ።እነሱ ስላንቺ ትዳር ዉሳኔ እንዲሰጡ አትጠብቂያቸዉ።ማድረግ ካለብሽ ካለማንም ጣልቃ ገብነት በራስሽ አድርጊዉ።ሉቃ 21÷16
18ኛ ገዘብ የፍቅርሽ መሰረት አታድርጊዉ።
19ኛ ባሎች ትኩረት የምትሰጥና በትኩረት የምታዳምጥን ሚስት እንደሚፈልጉ በፍጹም አትዘንጊ።ለሱ የሚሆን ጊዜ በፍጹም እንዳታጪ።መልካም ንግግር የደስተኛ በቶች መሰረት ነዉ ።(ገላ 6÷9)
20ኛ ያንቺ ስራ ከባልሽ በብዙ ነገር የተሻለ ቢሆንም እንኳን ከቶ ከባልሽ ጋር አታነጻጽሪ።ገላ 6÷10
21ኛ ባልሽ ላይ ጨቅጫቃ አትሁኚበት።ባሎች ጨቅጫቃ ሚስት አይፈልጉምና።ኤፌ 4÷29
22ኛ ሰነፍ ሚስት ለምንም ነገር ግድ የላትም።ሌላዉ ቢቀር ለሰዉነቷ መታጠብያ እንደሚያስፈልጋት አታዉቅም።ሰነፍ ሚስት አትሁኚ።ምሳ 20÷13
23ኛ ባልሽ በጥሩ ሞያ የተሰራ ምግብ የሚወድ ስለሆነ በጥሩ ሞያ ግብ ስሪለት።ባል በምግብ ቀልድ አያዉቅም።ምሳ 31÷14
24ኛ ባልሽ በጣም አትቆጣጠሪዉ።ይልቁንም እያንዳንዷን ቅጽበት ተዝናኑበት ።ገቢያችሁ ተጠቀሙበት።ሉቃ 11÷3
25ኛ ባልሽ ከድካም ሲመጣ ሁሌም ቀዝቃዛ ዉኃ ስጪዉ።መልካም ባህሪሽና ትህትናሽ ዉበትሽ ነዉና።ምሳ 31÷11
26ኛ ስለትዳር መልካም አመለካከት ከሌላት ሴት ጋር በፍጹም ህብረት አትፍጠሪ። ምሳ 22÷14
27ኛ አንቺ ዋጋ የሰጠሹዉን ያክል ትዳርሽ ላንቺ ዋጋ አለዉና ግዴለሽነትን አስወግጂ።እብ 13÷14
28ኛ የማህጸንሽ ፍሬዎች የፈጣሪሽ ስጦታዎችሽ ናቸዉና ዉደጂያቸዉ።ተከባከብያቸዉ አስተምሪያቸዉም።ምሳ 22÷6
29ኛ ቤትሽ ለማስተዳደር ሁሌም አታረጂምና መቼም ቢሆን ለቤተሰቦችሽ ያለሽ እንክብካቤ አይቀንስ።ምሳ 31÷28
30ኛ የምትጾምና የምትጸልይ ሚስት ሁሌም ጠንካራ ናትና ሁሌም ስለባልሽና ስለ ቤተሰቦችሽ ጸልይ።1ኛ ተሰ 5÷17
ምንጭ፦unofficial Lifestyle ኢንግሊዘኛ ወደ አማርኛ የተረጎምኩት እኔዉ ነኝ።
ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን
እነሆ በቶሎ እመጣለሁ ለእያንዳንዱም እንደስራዉ መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ
አልፋ እና ዖሜጋ ፊተኛዉ እና ኋለኛዉ መጀመርያዉ እና መጨረሻዉ እኔ ነኝ። ራዕ 22÷12÷14)
መልካም ሚስት እንድሆን እግዚአብሔር ይርዳን አሜን ፫
