es
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Ir al canal en Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Mostrar más
1 161
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ ነው። "ጾመ ነቢያት" የተባለበት ምክንያት ነቢያት ስለጾሙት ነው፡፡ ነቢያት የጾሙት ለአዳም የተሰጠውን "አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚለውን የተስፋ ቃል በማሰብ ከሰማየ ሰማያት ይወርዳል፣ ከድንግል ማርያም ይወለዳል፣ በሞቱም ሞት የተፈረደበትን የሰው ልጅ ነፃ ያወጣዋል ብለው ነው፡፡ እኛ የነቢያትን ጾም የምንጾመው እንደቀደሙት ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል እያልን ሳይሆን የቀደሙት ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል እያሉ የጾሙትን በማሰብ በመጾማችን ድኅነተ ሥጋ፣ ድኅነተ ነፍስ፣ በረከተ ሥጋና በረከተ ነፍስ እንድናገኝበት ነው። ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)  ከኅዳር ፲፭ ጀምሮ እስከ ታኅሳስ ፳፰ ቀን (በዘመነ ዮሐንስ እስከ ታኅሳስ ፳፯ ቀን)  ድረስ ለ፵፬ ቀናት (በዘመነ ዮሐንስ ለ፵፫ ቀናት)  ይጾማል፡፡ ከእነዚህም መካከል ፵ ቀናት ጾመ ነቢያት፣ ፫ ቀናት ጾመ አብርሃም ሶርያዊ ሲሆኑ የቀረው ፩ ቀን ደግሞ የገሃድ ጾም ነው። የነቢያት ጾም ስያሜዎች ፨ ጾመ ነቢያት   የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ፨ ጾመ አዳም ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ፨ ጾመ ስብከት ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑ ፨ ጾመ ልደት የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ፨ ጾመ ሐዋርያት ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡ ፨ ጾመ ፊልጶስ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ ወንጌልን ሲያስተምር ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋልና ፨ ጾመ ማርያም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ክርስቶስን እንደምትወልድ ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ጸንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና በዚህም መሠረት  አምላካችን ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ሁላችንም በዚህ ጾም ወቅት በጾምና በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡         ወስብሐት ለእግዚአብሔር

photo content

photo content

❤ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ኅዳር ፲፭ 15 ቀን። ❤ እንኳን ለነቢያት (ለስብከተ ጌና) ጾም በሰላም አደረሰን። + + + ❤ "ጾም ትፌውስ ቁስለ ነፍስ ወታጸምም ኲሎ ፍትወታተ ዘሥጋ ትሜህሮሙ ለወራዙት ጽሙና እስመ ሙሴኒ ጾመ በደብረ ሲና"። ትርጉም፦ ጾም የነፍስን ቁስል ታድናለች የሥጋ ፍትወትንም ታስወግዳለች ለጎልማሶችም ደህንነትን (መታገስን) ታስተምራለች ሙሴም በሲና ተራራ ጾሟልና፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው ላይ። + + + ❤ በዚችም ቀን የስብከት ጌና (የነቢያት) ጾም መጀመሪያ ነው ይህም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለተወለደበት በግብጽ የሚኖሩ ያቆባውያን ክርስቲያኖች የሠሩት ነው። ይቅርታው ቸርነቱ ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ❤ እግዚአብሔር አምላክ ጾሙን በአገራችን ኢትዮጵያ የተጀመረውን ስምምነት የሚያጸና ያድርግል። አምላከ ቅዱሳን ጾሙን በሰላም ጀምረን በሰላም እንድጨርስ ረድቶን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም ያድርሰን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለቂርቆስ ወሬዛ በመንፈስ በልደት ንዑስ፤ ንጹሕ ከመ ዕጣን ወፍሡሕ ከመ ወይን"። ትርጉም፦ በልደተ ሥጋ ታናሽ በመንፈስ ጐልማሳ፤ እንደ ዕጣን ንጹሕ እንደ ወይንም አስደሳች ለኾነ ለቅዱስ ቂርቆስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። https://t.me/Eotcw

photo content

❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለሚናስ ኅሩይ ዘክርስቶስ ሐራይ ጽድቅ ዘአብደረ እምነ ንዋይ፤ አምሳለ ወርኅ ወከመ ፀሓይ ብሩህ"። ትርጉም፦ የክርስቶስ ምርጥ ጭፍራ ከገንዘብ ይልቅ ጽድቅን የመረጠ እንደ ምሳሌው እንጨረቃ ለደመቀና እንደ ፀሓይም ብሩህ ለኾነ ለሚናስ ሰላምታ ይገባል። + + + ❤ "ሰላም ለከ ሐራዊ መስፍን። ሰማዕተ መድኅን። ዘሰመየተከ ሚናስ ዘፆረተከ ማሕፀን። አመ ጸለየት ጸሎተ እንዘ ይእቲ መካን። እምሥዕለ ማርያም ሰሚዓ ዘይቤ አሜን"። ትርጉም፦ መካን ሳለች ጸሎትን እየጸለየች ሳለች ከእመቤታችን ማርያም ሥዕል አሜን የሚልን ቃልን ሰምታ የተሸከመችኽ ማሕፀን ሚናስ ብላ የሰየመችኽ የመድኅን ክርስቶስ ምስክር፤ የጦር መኰንን ለኾንኽ ላንተ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 15። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

አሜን። ምንጭ፦ የጥር 15 ስንክሳር። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ። በ­ቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ። ይባዕ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ 78፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 12፥14-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 2፥21-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 13፥1-13። የሚነበበው ወንጌል፡ዮሐ5፥1-5። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው። የቅዱስ ሚናስ የዕረፍት በዓልና የቅዱስ ቂርቆስ የልደት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

"ስምሽን ስጪ ተናገሪ" አላት እርሷም "የኔ ስም ክርስቲያን መባል ነው" አለችው። መኰንኑም "ይህስ ስንፍና ነው የሚጠቅምሽ አይደለም እንዳትሞቺ ስምሽን ስጪ ተናገሪ" አላት። የከበረች ኢየሉጣም "የኔ ስም ክርስቲያን መባል እንደሆነ ነገርኩህ ሞት የሚሽረው በሰዎች ዘንድ የምጠራበትን ከፈለግህ ስሜ ኢየሉጣ ነው" ብላ መለሰችለት። መኰንኑም "ጽኑ የሆኑ ሥቃዮችን በላይሽ ሳያመጡ ተነሥተሽ መሥዋዕትን ለአማልክት አቅርቢ" አላት። የከበረች ኢየሉጣም "ዕውነት ነገርን ለመሥራት የምትሻ ከሆነ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነ ሕፃን ልጅ ይፈልጉ ዘንድ ወደ አገሩ መንደር ላክ ወዳንተም ያምጡትና የምንገዛለትንና የምናመልከውን እርሱ ይነገረን" አለችው። ❤ ያን ጊዜም የሦስት ዓመት ልጅ ይፈልጉ ዘንድ መኰንኑ ወታደሮችን ላከ የአገር ሰዎችም ልጆቻቸውን ሠውረዋልና አላገኙም ከዚያም ከከተማው ቅጽር ውጭ በፀሐይ መውጫ ወዳለው በረሀ በኩል ወጡ የቅድስት ኢየሉጣንም ልጅ አገኙት ይህ ሕፃን "የስንት ዓመት ልጅ ነው" ብለው ስለርሱ ጠየቁ ሰዎችም "ይህ ሕፃን የሦስት ዓመት ሲሆን የክርስቲያናዊት መበለት ልጅ ነው" አሏቸው። ያንንም ሕፃን ይዘው ወደ መኰንኑ ወሰዱት መኰንኑም መልኩ የሚያምርና ደም ግባት ያለው እንደሆነ በአየ ጊዜ "ደስ የምትል ደስተኛ ሕፃን ሰላምታ ይገባሃል" አለው። ሕፃኑም "እኔን ደስተኛ ማለትህ መልካም ተናገርክ ላንተ ግን ደስታ የለህም እግዚአብሔር ለዝንጉዎች ደስታ የላቸውም ብሏልና ብሎ መለሰለት መኰንኑም ሕፃኑን "ሳልጠይቅህ ይህን ያህል ትመልስልኛለህን" አለው። ሕፃኑም "ገና ከዚህ የሚበዛ ነገርን እመልስልሃለሁ" አለው። ❤ መኰንኑም "ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ "ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውኃ የተገኘ ሕፃን ስሜ ክርስቲያን መባል ነው" ብሎ መለሰለት። መኰንኑም "ዳግመኛ እንዳትሞት ስምህን ንገረኝ" አለው የከበረ ሕፃንም "ስሜ ክርስቲያን መባል እንደሆነ ነገርኩህ ሞክሼ ስም የምትሻ ከሆነ እናቴ የሰየመችኝ ቂርቆስ ነው" በማለት መለሰለት፡፡ መኰንኑም ሕፃን ቂርቆስን "እሺ በለኝና እሾምሃለሁ በብዙ ወርቅና ብርም አከብርሃለሁ" አለው። ሕፃኑም "የሰይጣ መልእክተኛ ለዕውነትም ጠላቷ የሆንክ ከእኔ ራቅ" አለው። መኰንኑም ሰምቶ ተቆጣ ደሙ እንደ ውኃ እስከሚፈስ ቆዳውን እንዲጨምቁትና እንዲግፉት አዘዘ። የከበረች ኢየሉጣሜ የልጅዋን ትዕግሥት በአየች ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነችው። ❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑ "ጨውና ሰናፍጭ አምጡ አለ። የሁለቱንም አፍንጮቻቸውን ከፍተው ያንን ጨውና ሰናፍጭ እንዲጨምሩባቸው አዘዘ ያን ጊዜ ሕፃኑ "ትእዛዝህ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ሆነ ከማርና ከስኳርም ለአፌ ጣመኝ" ብሎ ጮኸ። ሁለተኛም መኰንኑ እንዲህ ብሎ አዘዘ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች አምጡ ሰባቱን በእናቱ አካላት ውስጥ ጨምሩ በሕፃኑም ሁለት ጆሮዎቹ ሁለት በዐይኖቹ ሁለት በአፉና በአፍንጫው አንድ በልቡ ጨምሩ እንዲህ ሲጨመርበት ጆሮዎቹ እንዲአሩ ዐይኖቹም ይጠፋ ዘንድ አንደበቱም ይቃጠል ዘንድ ወደ ልቡም ጽኑ ሕማም ገብቶ እርሱ ከዚህ ዓለም በሞት እንዲለይ ለእናቱም እንዲሁ አድርጉ ችንካሮችም በቅዱሳኑ በሥጋቸው ሁሉ ተጨመሩ። የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ትእዛዝ የብረቶቹ ግለት ጠፍቶ እንደ በረዶ ቀዘቀዘ ጤነኞችም ሆኑ መኰንኑም "ወደ ወህኒ ወስዳችሁ በዚያ አሥራችሁ ዝጉባቸው" አለ። ❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑ "የሥቃይ መሣሪያን ይሠራ ዘንድ እንዳዝዘው ብረትን የሚያቀልጥ ሰው አምጡልኝ" አለ። በአመጡለትም ጊዜ ሰይጣን ወደ መኰንኑ ልብ ገብቶ አንደበቱን ዘጋውና መናገር ተሳነው ሕፃኑ ፈጥኖ አክሊልን ለመቀበል እንደሚተጋ ሰይጣን ስለ አወቀ ስለዚህ ዘጋው። ❤ ከዚህም በኋላ ሕፃኑ ሠራተኛውን ጠርቶ "እኔንና እናቴን የሚያሠቃዩ በትን የሥቃይ መሣሪያ መሥራት ትችላለህ ይህ መኰንን ግን ምንም የሚያውቀው ነገር የለም" አለው። ሠራተኛውም እንደምትሻው በል ንገረኝ እምታዝዘኝ እኔ መሥራት እችላለሁ" አለው። ሕፃኑም ቅዱስ ቂርቆስ እያዘዘው...። ብረት ሠሪውም ሰምቶ እጅግ አደነቀ የሚረዱትንም ከአገር ውስጥ መቶ ሠራተኞችን ሰብስቦ መሥራት ጀምረ በአርባ ቀንም ጨረሰ። ❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑ እለእሰሰክድሮስ ቂርቆስንና እናቱን ወደ አደባባይ ያመጡአቸው ዘንድ አዘዘ ያን ጊዜ አንደበቱ ተፈትቶ ነበርና እንዲህ አለ "ሕፃኑንና እናቱን ከቆዳቸው ጋር ራሳቸውን ላጩአቸውና በላያቸው የእሳት ፍሞችን ጨምሩ እርር ብለው እንዲቃጠሉ ዳግመኛም አራት ችንካሮችን ከትከሻዎቹ እስከ ተረከዙ ድረስ እንዲተክሉበት አዘዘ የእግዚአብሔርም መልአክ መጥቶ ሥቃዩን ከርሱ አራቀ። ዳግመኛም ከጥዋት እስከ ማታ ከሥቃይ መሣሪያዎች ውስጥ ጨምረው አዋሏቸው ግን ማሠቃየት ተሳናቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ከማምጠቂያው ውስጥ ጨምረው መገዙአቸውና አመድ እስከሆኑ ከቅባትና ከጨው ጋር በብረት ምጣድ ውስጥ ቆሉአቸው ጌታችንም አስነሥቶ አዳናቸው። ወደ መኰንኑም በገቡ ጊዜ እንዲህ አላቸው "በእውነት ከሙታን ተለይታችሁ የተነሣችሁ ከሆነ ይህ ጫማዬ በእግሬ ወጥቶ እንደ ቀድሞው ሕያው እንዲሆን አድርጉ ሕፃን ቂርቆስም በጸለየ ጊዜ ያ ጫማ ታላቅ በሬ ሆነ ከአንገቱም ፍየል ወጣ። በዚያንም ሰዓት ለዐሥራ አንድ ሽህ አራት ሰዎች በሬውንና ፍየሉን አርደው ምሳ እንዲአደርጉላቸው መኰንኑ አዘዘ እንዲህም አለ ይህ "በቅቷቸው ከጠገቡ ከዚህም ሌላ ምግብ ካልፈለጉ የተሠራው ሁሉ ዕውነተኛ ነዋሪ ነው"። ❤ ከዚህም በኋላ አርደው ምሳ አደረጉላቸውና ከፍየሉ ሥጋ ስድስት እንቅብ ከበሬው ሥጋ አራት እንቅብ አተረፉ መኰንኑም የተረፈውን ሥጋ አይቶ ወደ ባሕር እንዲጥሉት አዘዘ። መኰንኑም ቢያፍር የሕፃኑን ምላስ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ጌታችንም ምላሱን መለሰለት ዳግመኛም በታላቅ ጋን ውኃ አፍልተው ሕፃን ቂርቆስንና እናቱን ኢየሉጣን ይጨምሩአቸው ዘንድ አዘዘ እናቱም አይታ ፈራች። ልጅዋም ወደ እግዚአብሔር በጸለየላት ጊዜ አምላካዊ ኃይልን አሳደረባትና ከልጅዋ ጋር ወደ ጋኑ ገባች። እንደ ውርጭም ቀዝቃዛ ሆነ ደግሞም በውስጡ መንኲራኵር ወዳለበት የብረት ምጣድ እንዲጨምሩአቸውና ሥጋቸው እስከሚቦጫጨቅ እንዲስቡአቸው አዘዘ የእግዚአብሔርም መልአክ ቅዱስ ገብርኤልም በሕይወት አወጣቸው። ❤ መኰንኑም እነርሱን ማሸነፍ በተሳነው ጊዜ ቸብቸቧቸውን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ በዚያን ጊዜ ለስም አጠራሩ ስግደት የሚገባው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወረደ ሕፃን ቅዱስ ቂርቆስንም "የምትሻውን ለምነኝ" አለው። ሕፃኑም "ሥጋዬ በምድር አይቀበር ስሜን ለሚጠራ መታሰቢያዬን ለሚያደርግ ቤተ ክርስቲያኔን ለሚሠራ የተጋድሎዬን መጽሐፍ ለሚጽፍና ለሚያጽፍ ወይም ለሚያነበው ለቤተ ክርስቲያኔ መባ ለሚያገባ በውስጧም ለሚጸልይ ለሁሉም ፍላጎታቸውን ስጣቸው ኃጢአታቸውንም ይቅር በል ስሜም በሚጠራበት በዚያች ቦታ የከብት ዕልቂት አይምጣ በሰውም ላይ አባር ቸነፈር በእህልም ላይ ድርቅ የውኃም ማነስ አይሁን"። ❤ መድኃኒታችንም "የለመንከኝ ሁሉ አስጥሃለሁ አንተም በቀኜ ትኖራለህ ሥጋህንም ኤልያስ በዐረገበት ሠረገላ ውስጥ አኖራለሁ" አለው ሕፃን ቂርቆስ በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ብሎት ጌታችንን አመሰገነው። ከዚህም በኋላ በሌሊቱ እኩሌታም ከእናቱ ጋር አንገቱን ተቆረጠ መድኃኒታችንም በማይጠፋ አክሊል ጋረደው ነፍሶቻቸውንም በታላቅ ክብር ከእርሱ ጋር አሳረገ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ቂርቂቆስና በእናቱ ቅድስት ኢየሉጣ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ

❤ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ኅዳር ፲፭ 15 ቀን። ❤ እንኳን ለታላቁ ሰማዕት የስሙ ትርጓሜ ቡሩክና የታመነ ለሆነ ለቅዱስ ሚናስ ለዕረፍት በዓል፣ ለታላቁ ሰማዕት ለሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ለልደት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰ። በተጨማሪ በዚችን ቀን ከሚታሰበው፦ ከአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ አንደኛ ከእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ከቅዱስ አባት ከሁለተኛው አባ ሚናስ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳፈን። + + + ❤ ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ሚናስ፦ የዚህም ቅዱስ አባቱ አናቅዮስ ከሚባል አገር ነው ስሙም አውዶክስዮስ ነው እርሱም አገረ ገዥነት ተሹሞ ሳለ ወንድሙ ቀንቶበት በንጉሥ ዘንድ ነገር ሠራበት ንጉሡም ወደ አፍራቅያ አገር ሰደደውና በዚያም አገረ ገዢ አድርጎ ሾመው የአገር ሰዎችም ሁሉ ደስ አላቸው እርሱ ለሰው የሚራራ እግዚአብሔርም የሚፈራ ደግ ሰው ነውና። ❤ እናቱም ልጅ አልነበራትም በአንዲት ዕለት ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በበዓልዋ ቀን ገብታ የክርስቲያንን ወገኖች ያማሩ ልብሶችን ለብሰው ከልጆቻቸው ጋር ደስ እያላቸው ሲገቡ አየቻቸው። በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት አለቀሰች ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ ልጅዋ ወደ እግዚአብሔር እንድትለምንላትም ለመነቻት በዚያን ጊዜ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል አሜን የሚል ቃል ወጣ። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ቤቷ ገብታ ይህን ቃል ለባሏ ነገረችው እርሱም "የእግዚአብሔር ፈቃዱ ይሁን" አለ። ከጥቂት ቀኖችም በኋላ እግዚአብሔር ይህን የተባረከና የከበረ ልጅን ሰጣት የእመቤታችንም ሥዕል "ሚናስ" ብላ እንደሰየመችው ስሙን ሚናስ ብለው ሰየሙት። ጥቂት በአደገ ጊዜም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተማሩት። ዐሥራ ሁለት ዓመትም ሲሆነው በመልካም ሽምግልና አባቱ ዐረፈ ከእርሱም በኋላ በሦስተኛ ዓመት እናቱ ዐረፈች ቅዱስ ሚናስም ብቻውን ቀረ። መኳንንቱም አባቱን አብዝተው ከመውደዳቸው የተነሣ ሚናስን በአባቱ ፈንታ ምስፍናን ሾሙት እርሱም የክርስቶስን አምልኮት አልተወም። ❤ ዲዮቅልጥያኖስም በካደ ጊዜ ሁሉንም ሰዎች ጣዖታትን እንዲአመልኩ አዘዛቸው ብዙዎችም ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ሞቱ። በዚያንም ጊዜ ቅዱስ ሚናስ ሹመቱን ትቶ ወደ ገዳም ገባ ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ ብዙ ዘመናት ኖረ። በአንዲትም ዕለት ሰማይ ተከፍቶ ሰማዕታትን የብርሃን እክሊሎችን ሲአቀዳጁአቸው አየ "ስለ ክርስቶስ ስም በመከራ የደከመ ይህን አክሊል ይቀበላል" የሚል ቃልን ሰማ። በዚያንም ጊዜ ወደ ከተማ ተመለሰና ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ ሰዎችም አብዝተው አባበሉት በወገን የከበረ እንደሆነ እነርሱ ያውቁ ነበርና። መኰንኑም ብዙ ቃል ኪዳን ገባለት ባልሰማውም ጊዜ ጽኑዕ በሆነ ሥቃይ እንዲአሠቃዩት አዘዘ። ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ኅዳር 15 ቀን ተቀበለ ብዙዎችም በእርሱ ምክንያት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ሞቱ። ❤ የቅዱስ ሚናስንም ሥጋ ወደ እሳት እንዲጥሉት መኰንኑ አዘዘ እሳትም አልነካውም ምእመናን ሰዎችም የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ወስደው በአማሩ ልብሶች ገነዙት የስደቱ ወራትም እስከሚፈጸም በአማረ ቦታ ውስጥ አኖሩት። ❤ በዚያንም ወራት የመርዩጥ አገር ሰዎች ከአምስቱ አገሮች ሠራዊትን ሊአከማቹ ወደዱ የቅዱስ ሚናስንም ሥጋ ረዳት ይሆናቸው ዘዘንድ በመንገድም እንዲጠብቃቸው ከእርሳቸው ጋር ወሰዱት። እነርሱም በባሕር ላይ መርከብ ውስጥ ሳሉ ፈታቸው እንደ ከይሲ አንገታቸው እንደ ግመል አንገት ያለ አውሬዎች ከባሕር ወጡ ይልሱትም ዘንድ ወደ ቅዱስ ሚናስ ሥጋ አንገታቸውን ዘረጉ ከቅዱ ሚናስም ሥጋ እሳት ወጥታ እነዚያነሰ አራዊት አቃጠላቻቸው ሰዎችም አይተው አደነቁ ደስታም አደረጉ ፈርተው ነበርና። ❤ ወደ እስክንድርያ አገርም ደርሰው ሥራቸውን ፈጽመው ወደ አገራቸው በሚመለሱ ጊዜ የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ከእርሳቸው ጋር ሊወስዱ ወደው በገመል ላይ በጫኑት ጊዜ ገመሉ ከቦታው የማይነሣ ሆነ። ሁለተኛም በሌላ ገመል ጫኑት እርሱም መነሣትን እመቢ አለ አብዝተውም ደበደቡት ገመሉም ከቶ አልተንቀሳቀሰም እነርሱም ያቦታ እግዚአብሔር የፈቀደለት መሆኑን አወቁ ቦታውንም አዘጋጅተው ቀበሩት። ❤ ጌታችንም በበግ እስከገለጠው ድረስ ብዙ ዘመናትን በዚያ ቦታ ኖረ ይህም ቤተ ክርስቲያኑ በከበረችበት በሰኔ ዐሥራ አምስት ቀን ተጽፎአል። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚናስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የእስክንድርያ ስልሳ አንደኛ ሊቀ ጳጳሳት ሁለተኛ አባ ሚናስ፦ ይህም ቅዱስ ሚናስንም ከታናሽነቱጨያለ ፍላጎቱ ወላጆቹ ሚስት አጋቡት ትእዛዛቸውን መተላለፍ ስለአልፈለገ የጋብቻውን ሥርዓት ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ፈጸመ። ለርሱ ይህ ሁሉ ሕልም ይመስለው ነበር ወደ ሙሽሪትም ወደ አዳራሽ በአስገቡት ጊዜ ተቀምጦ እንዲህ ብሎ ተናገራት "እኅቴ ሆይ ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ካጠፋ ምን ይጠቅመዋል እንደ ተጻፈ ሁሉ ያልፋልና ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ለዘላለሙ ይኖራል አሁንም ድንግልናችንን እንድንጠብቅ ነይ ቃል ኪዳን እናድርግ" እርሷም ቃሉን ተቀብላ ከእርሱ ጋር ተስማማች። ❤ ከዚህም በኋላ ትቷት ወደ አስቄጥስ ገዳም ሒዶ በአባ መቃርስ ገዳም ውስጥ መነኰሰ ብዙ ዘመናትም በገድል ተጠምዶ ኖረ። ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳትም በዐረፈ ጊዜ ይህን ቅዱስ አባት ሚናስን ያለውዴታው ወስደው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስም ወንበር ላይ መንጋዎቹን በቅን ፍርድ እየጠበቃቸው እያስተማራቸው ዐሥራ ስምንተሰ ዓመት ኑሮ ኅዳር 15 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የአባ ሚናስ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 15 ስንክሳር። + + + ❤ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ፦ በዚያንም ወራት የክብር ባለቤት የሆነ ክርስቶስን በሚያምኑ የክርስቲያን ወገኖች ላይ ታላቅ መከራና ስደት ሆነ። ስሟ ኢየሉጣ የሚባል አንዲት ሴት ነበረች እርሷም ከታናሽነቷ ጀምራ ደግ ናት ስደትም እንደሆነ በሰማች ጊዜ መኰንኑን ከመፍራት የተነሣ ሕፃኗን ይዛ ከሮሜ ከተማ ተሰዳ የኪልቅያ አውራጃ ከሆነ ከጠርሴስ ደርሳ ከዚያም በአገሮች ውስጥ እየተዘዋወረች ተቀመጠች። ወደዚያች አገርም ያ ከእርሱ የሸሸችው መኰንን እለእስክድሮስ መጣ ጭፍሮቹም ክርስቲያኖችን ፈለጓቸው። ይቺንም ቅድስት ኢየሉጣን አግኝተው ያዝዋትና ወደ መኰንኑ አደረሷት የክርስቲያን ወገንም እንደሆነች ነገሩት። ❤ መኰንኑም "ሴትዮ ተናገሪ ከወዴት ሕዝብ ወገን ነሽ ነገድሽ ምንድን ነው አገርሽስ ወዴት ነው" አላት። የከበረች ኢየሉጣም እንዲህ ብላ መለሰችለት "የአንጌቤን ሰው ለሆንኩ ለእኔ ወገኖቼ ኤሳውሮሳውያን ናቸው እኔም በአንተ ምክንያት ሸሽቼ ነበር እነሆ ዛሬ ግን በእጅህ ውስጥ ነኝ" አለችው። መኰንኑም "በእጄ ውስጥ እንደተገኘሽ ታውቂያለሽን" አላት "አሁንም የሚሻልሽን ምረጪ ስምሽንም ተናገሪ እኔንም እሺ በይኝና ለአማልክት ሠዊ" የከበረች ኢየሉጣም አለችው "ለረከሱ አማልክት እኔ አልሠዋም" አለችው መኰንኑም

photo content
+2

ሰባቱ የፆም ጥቅሞች ፆም በመንፈሳዊ ህይወታችን ውስጥ ትልቅ ስፍራ አለው፡፡ ፆም ለህይወታችን የሚጠቅመውን ነገሮች ከእግዚአብሄ ቃል እንመልከት 1. ስጋ ያለልክ እንዳይጠግብ ይጠቅማል ፆም እግዚአብሄርን የማይፈልገው የወደቀው የሃጢያት ማንነት እንዳያይል ስጋን ለመጎሸም እና ለእግዚአብሄር ፈቃድ ብቻ ለማሰገዛት ይጠቅማል፡፡ ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡27 2. ፆም ስጋችን እንዳይከብደው ያደርጋል ምግብን የማድቀቅ ስርአት በጣም ጉልበትን የሚጠይቅ ስርአት ነው፡፡ ሰውነታችን የምግብን ውህደት ሂደት የሚያካሂደው እንደትልቅ ፋብሪካ ነው፡፡ ከባድ ምግብ ልክ እንደበላን ድካም ድካም የሚለን ስለዚህ ነው፡፡ ፆም የሰውነታችንን ትልቅ የምግብ ማድቀቅ ስርአት ነፃ በመሆን ሰውነታችን ቀለል እንዲለውና እንድንነቃ በመንፈሳዊ ሁኔታ ላይ እንድናተኩር ይረዳናል፡፡ 3. ፆም በመንፈሳዊ ነገር ላይ እንድናተኩር ይረዳል ፆም በማይታየው በእግዚአብሄር በአምልኮ ላይ እንድናተኩር ያደርገናል፡፡ ፆም ስጋችነነ ስለሚያደክመው የምድሩን ሳይሆን ቅድሚያ መስጠት ያለብንን ሰማያዊውን እንዳናስብ ይረዳናል፡፡ በአንጾኪያም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም በርናባስ፥ ኔጌር የተባለው ስምዖንም፥ የቀሬናው ሉክዮስም፥ የአራተኛው ክፍል ገዥ የሄሮድስም ባለምዋል ምናሔ፥ ሳውልም ነበሩ። የሐዋርያት ሥራ 13፡1 4. ፆም መንፈስ እንዲያሸንፍ ይረዳል ፆም መንፈስን እንዲያሸንፍ መንፈስን ለመደገፍ ይጠቅማል፡፡ ፆም ስጋ እንዳያሸንፍ ለመጫን ይጠቅማል፡፡ ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ወደ ገላትያ ሰዎች 5፡17 የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። ወደ ገላትያ ሰዎች 5፡24 5. ፆም ለመንቃት ይጠቅማል ብዙ ስንበላ እንቅልፍ እንቅልፍ ይለናል መንቃትም ይከብደናል፡፡ ብዙ ካልባለን ግን ነቅተን ስራችንን ማቀላጠፍ እንችላን፡፡ በጣም ብዙ በልቶ ከተኛ ሰው እና ጥቂት በልቶ ከተኛ ሰው መካከል ማነትው ንቁ እና ቶሎ የሚነቃው ብንል ትንሽ በልቶ የተኛው ሰው ነው፡፡ ብዙ ከጠጣውና ጥቂት ከጠጣው ሰው መካከል ማነው በቶሎ ሊነቃ የሚችለው ብለን ብንመለከት ጥቂት የጠጣው በቶሎ ነገሮችን ማስተዋል ወደ አእምሮው መመለስ እንደሚችል እናስተውላለን፡፡ በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፡8 6. ስጋ ፍላጎቱ እንዲገደብ ያደርጋል ስጋ በሰጠነው መጠን ሌላ ይጠይቃል፡፡ ስጋ ባሟላልነት መጠን የሚቀጥለውን ይጠይቃል፡፡ ነገር ግን ፆም ስንይዝ ስጋ በምግብ ጥያቄ ብቻ ላይ እንዲቆም እንገድበዋለን፡፡ ይህ እንደ ገዛ ፈቃድህ በማምለክና በትሕትና ሥጋንም በመጨቆን ጥበብ ያለው ይመስላል፥ ነገር ግን ሥጋ ያለ ልክ እንዳይጠግብ ለመከልከል ምንም አይጠቅምም። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡23 7. ፆም የስጋችንን ድምፅ በመቀነስ የመንፈስን ድምፅ እንድንሰማ ይረዳናል ፆም የስጋን ድምፅ በመቀነስ የመንፈስ ድምፅ እንዲያይል ለማድረግ ይጠቅማል፡፡ እግዚአብሄር በመንፈሳችን አማካኝነት ሁልጊዜ ፈቃዱን ይናገራል፡፡ የመንፈስን ድምፅ ለመስማይት የሚያስፈልገውን ነገር ማድረግ ያለብን እኛ ነን፡፡ ስጋውን እንደፈለገ የሚመግበው ሰው የመንፈስን ድምፅ ለመስማት ይቸግረዋል፡፡ በፆም የስጋውን ድምፅ የሚያዳክም ሰው ግን የመንፈስን ድምፅ በጥራት መስማት ይችላል፡፡ እንግዲያስ እንንቃ በመጠንም እንኑር እንጂ እንደ ሌሎች አናንቀላፋ። 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5፡6 በፀሎት እግዚአብሄርን ይበልጥ መስማት የምንችለው ስንፆም ነው፡፡ ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ፤ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4፡8 ምንጭ አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa @lij28

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።         ጾመ ነቢያት/ጾመ ስብከት ""ጾም የስጋ የነፍስ ቁስልን ትፈውሳለች""" ↪️ ፆመ_ነብያት_መቼ_ይገባል?                 ለምንስ_እንፆማለን? ፆመ ነብያት ወይም የገና ፆም  ህዳር 15 ይጀምራል ታህሳስ 29 በዕለተ ይፈታል። ይህ ማለት የዘንድሮ የገና ፆም ቅበላ እስከ ማክሰኞነው ከረቡዕ ጀምሮ የፍስክ ምግቦች አይበሉም። ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው  ነብያት የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነፅር እየተመለከቱ የፆሙት ታላቅ ፆም ነው። ዛሬም እኛ ክርስቲያኖች የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በፆምና በፀሎት ወቅቱን በማሳለፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ አለም መምጣቱንና የዓለም ቤዛ መሆኑን የምናስብበት ነው።     🔂ይህ ፆም፣  ፆመ ድህነት፣ ፆመ ማርያም ፣ ፆመ አዳም ፆመ ፊሊጶስ ፆመ ስብከት በመባል ይጠራል።           ↪️  ፆመ_ድህነት ፦ የተባለበት ምክንያት መርገመ ስጋ መርገመ ነብስ የአዳም እዳ በደል ጠፍቶ ድህነት ስለተገኘበት ነው።            ⤴️  ፆመ_ማርያም፦ የተባለበት ምክንያት ንፅይተ ንፁሃን ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስ ድንግል ማርያም ጌታን በማህፀኔ ተሸክሞ ልፆም ልፀልይ ይገባል ብላ ለ40 ቀን እስከ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ድረስ የፆመችው ፆም ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል።         ✅  ፆመ_አዳም፦ የተባለበት ምክንያት ለአዳም የተነገረው ትንቢት፣ የሚጠበቀው ሱባኤ እንደደረሰ የሚያበስር በመሆኑ ጾመ አዳም ይባላል፡፡ አዳም ቢበድልም ንስሐ ገብቶ በማልቀሱ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለሁ ብሎ የተነገረው ተስፋ መድረሱን፣ ምሥጢረ ሥጋዌ እውን ሊሆን መቃረቡን የሚያስረዳ ጾም ነው፡፡          ↪️  ፆመ_ፊሊጶስ፦ የተባለበትም ምክንያት ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ ሲያስተምር በሰማዕትነት ሲሞት አስከሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስከሬን እንዲገልጽላቸው ከኅዳር አስራ ስድስት ጀምረው ሲጾሙ በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስከሬን ቢመልስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል ለዚህም ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡           ↩️  ፆመ_ስብከት ፦ የተባለበትም ምክንያት የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት የሰውልጆች ተስፋ የተመሰከረበት የምሥራቹ የተነገረበት ስለሆነም ጾመ ስብከት ይባላል፡፡ ፆሙን የሀጥያታችን መደምሰሻ መንግስተ ሰማያተን መውረሻ ያድርግልን። የቅዱሳን ነብያት አባቶቻችንንም በረከት በሁላችንም ላይ ያሳድርብን።            ስብሐት_ለእግዚአብሔር                  ወለወላዲቱ_ድንግል                         ወለመስቀሉ_ክቡር                                   ይቆየን።

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ዮሐ. 4:46-ፍ፡ም፡ "ወሀሎ ፩ ገብረ ንጉሥ" - "በቅፍርናሖምም፡ልጁ፡የታመመበት፡ከንጉሥ፡ቤት፡አንድ፡ሹም፡ነበረ። እርሱም፡ኢየሱስ፡ከይሁዳ፡ወደ፡ገሊላ፡እንደ፡መጣ፡ሰምቶ፡ልጁ፡ሊሞት፡ስለ፡አለው፡ወደ፡ርሱ፡ሄደ፡ወርዶም፡እንዲፈውስለት፡ለመነው። ስለዚህም፡ኢየሱስ፦ምልክትና፡ድንቅ፡ነገር፡ካላያችሁ፡ከቶ፡አታምኑም፡አለው። ሹሙም፦ጌታ፡ሆይ፥ብላቴናዬ፡ሳይሞት፡ውረድ፡አለው። ኢየሱስም፦ሂድ፤ልጅህ፡በሕይወት፡አለ፡አለው። ሰውዬውም፡ኢየሱስ፡የነገረውን፡ቃል፡አምኖ፡ሄደ። እርሱም፡ሲወርድ፡ሳለ፡ባሮቹ፡ተገናኙትና፦ብላቴናህ፡በሕይወት፡አለ፡ብለው፡ነገሩት። እርሱም፡በጎ፡የሆነበትን፡ሰዓት፡ጠየቃቸው፤እነርሱም፦ትናንት፡በሰባት፡ሰዓት፡ንዳዱ፡ለቀቀው፡አሉት። አባቱም፥ኢየሱስ፦ልጅኽ፡በሕይወት፡አለ፡ባለው፡በዚያ፡ሰዓት፡እንደ፡ሆነ፡ዐወቀ፤እርሱም፡ከቤተ፡ ሰዎቹ፡ሁሉ፡ጋራ፡አመነ። ይህም፡ደግሞ፡ኢየሱስ፡ከይሁዳ፡ወደ፡ገሊላ፡መጥቶ፡ያደረገው፡ሁለተኛ፡ምልክት፡ነው።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.46 KB

14/3/2015 ዓ.ም (፲፬/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 እስመ አቡየ ወእምየ ገደፉኒ። ወእግዚአብሔር ተወክፈኒ። ምርሀኒ እግዚኦ ፍኖተከ፡፡ መዝ. 26፥10 🕯 ትርጉም አባቴና እናቴ ትተውኛልና። እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ። አቤቱ መንገድህን አስተምረኝ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በዕለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 5፥21-27፡ "ሰማዕክሙ ዘትብህለ" -"ለቀደሙት፦አትግደል፡እንደ፡ተባለ፡ሰምታችኋል፤ የገደለም፡ሁሉ፡ፍርድ፡ይገባዋል። እኔ፡ግን፡እላችኋለሁ፥በወንድሙ፡ላይ፡የሚቈጣ፡ሁሉ፡ፍርድ፡ይገባዋል፤ወንድሙንም፡ጨርቃም፡የሚለው፡ዅሉ፡የሸንጎ፡ፍርድ፡ይገባዋል፤ደንቈሮ፡የሚለውም፡ዅሉ፡የገሃነመ፡እሳት፡ፍርድ፡ይገባዋል። እንግዲህ፡መባህን፡በመሠዊያው፡ላይ፡ብታቀርብ፥በዚያም፡ወንድምህ፡አንዳች፡ባንተ፡ላይ፡እንዳለው፡ ብታስብ፥ በዚያ፡በመሠዊያው፡ፊት፡መባኽን፡ትተኽ፡ሂድ፥አስቀድመህም፡ከወንድምህ፡ጋራ፡ታረቅ፥በኋላም፡መጥተህ፡መባህን፡አቅርብ። አብረኸው፡በመንገድ፡ሳለህ፡ከባላጋራህ፡ጋራ፡ፈጥነህ፡ተስማማ፤ባላጋራ፡ለዳኛ፡እንዳይሰጥህ፡ዳኛም፡ለሎሌው፥ወደ፡ወህኒም፡ትጣላለህ፤እውነት፡እልሃለሁ፥የመጨረሻዋን፡ሳንቲም፡እስክትከፍል፡ድረስ፡ከቶ፡ከዚያ፡አትወጣም። አታመንዝር፡እንደ፡ተባለ፡ሰምታችኋል።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨