es
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Ir al canal en Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Mostrar más
1 161
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ጎየ ዮሴፍ ብሐረ ግብፅ ተንሢኦ እምንዋሙ። መልአከ እግዚአብሔር ሌሊተ በከመ ነገሮ በሕልሙ። ነሢኦ ሕፃን ዘምስለ ማርያም እሙ። ይእቲ ትበኪ ወትቤ ቀቲሎትየ ይቅድሙ እምእርአይ ለወልድየ ዘይትከዐው ደሙ"። ትርጉም፦ የእግዚአብሔር መልእተኛ የሆነ ቅዱስ ገብርኤል ሌሊት በሕልሙ እንደነገረው ዮሴፍ ከእንቅልፋ ነቅቶ ሕፃኑን ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ይዞ ወደ ግብፅ አገር ሸሸ ድንግል ማርያምም የልጄ ደም ሲፈስ ከማይ ይልቅ የኄሮድስ ሰራዊት እኔን አስቀድመው ይግደሉኝ እያለች አለቀሰች"። ሰቆቃወ ድንግል። https://t.me/Eotcw

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለዕንባቆም ነቢይ ዘርእየ ርደቶ ለሊቅ፤ ዘጸዳለ ወልታሁ ከመ መብረቅ፤ ዘብርሃኑ ማዕበል ወቅድመ ገጹ ዘየሐውር ቃል፤ እምቴማን ምጽአቱ ዘእምዓለም ፍኖቱ፤ ርእየ ፈርሀ ወአንከረ"። ትርጉም፦ ከዓለም በፊት የነበረ ጎዳናውን አይቶ የፈራና ያደነቀ፤ አመጣጡ ከቴማን የኾነ አካላዊ ቃል በፊቱ የኼደ፤ የጋሻው ብርሃን እንደ መብረቅና ብርሃኑም ቀስትነት ያለው የመምህር ክርስቶስን አወራረድ ያየ ለኾነ ለነቢዩ ዕንባቆም ሰላምታ ይገባል። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

መጨረሻው ተናገረ ከነቢያት መጻሕፍትም ጋራ ደመርዋት። ❤ ከዚህ በኋላ ከእስራኤል ልጆች አንዲት ሴት ወደርሱ መጣች እያለቀሰችም እንዲህ አለችው "ሁለት ልጆች ነበሩኝ ጣዖት እንዲአመልኩ ፈለጉአቸው እምቢ በአሉ ጊዜም ገድለው በጐዳና ላይ ጣሉአቸው"። ተገድለው ወደአሉበትም አብሮዋት ሔደ ነፍሳቸውንም ይመልስላቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ለመነው ልመናውንም ተቀብሎ በሕይወት አነሣቸው"። ❤ ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ ዘመዶቹን ጠራቸው። እንደሚሞትም ነገራቸውና አንዲት ሰዓት ያህል ወደላይ እየተመለከተ ተቀመጠ። እንሆ እንደ ሰው ክንድ ያለች ታላቅ ክንድ የቤቱን ጣሪያ ሠንጥቆ ወረደች ወደ አፉም ተዘርግታ ነፍሱን ወሰደች ያን ጊዜም ዐረፈ። በክርስቲያን ንጉሥ በአንስጣስዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ ገድሉን በአነበበ ጊዜ አድንቆ በግብጽ ደቡብ ቀርጣስ በሚባል ቦታ በስሙ ቤተ ክርስቲያን ሠራለት እርሷም በዚች ቀን ከበረች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የነቢዩ ቅዱስ ዕንባቆም በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ቀሲስ ቅዱስ አብቊልታ፦ ይህ የእንጽና አገር የሆነ ባለ መድኃኒት ነው በሽተኞችን በጎ ሥራ በመሥራት ያለ ዋጋ ያክማቸዋል ደግሞም የሚበሉትን፣ የሚጠጡትን፣ የሚለብሱትን የሚሹትን ሁሉ ይሰጣቸዋል። ❤ በዚያም ወራት ወደ ሰዒዲ አውራጃ ወደ መኰንኑ አርያኖስ ዲዮቅልጥያኖስ ላከ የዚያችን አገር ሰዎች ለጣዖታት እንዲሰግዱ ያስገድዳቸው ዘንድ። በዚያንም ጊዜ ይህን ቅዱስ ያዙት ወደ እስሙናይንም ወስደው በመኰንኑ ፊቱ አቆሙት መኰንኑም ወደርሱ ይመልሰው ዘንድ በጎ ቃልን ተናገረው ሊመለስም ባልቻለ ጊዜ ቆዳው እስቲሠነጣጠቅ እንዲገርፉት አዘዘ ከዚያም በኋላ በሕይወት እያለ በእሳት አቃጠሉት ገድሉንም በዚህ ፈጸመ ምዕመናን ወጥተው በድኑን ወሰዱ ከከተማው ደብባዊ በሆነ ተራራ ላይ ገንዘው በክብር ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የቅዱስ አብቊልታ በረከቱም ከእኛ ለዘላለሙ ይኑር አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት24 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለአልዓዛር ወፊንሐስ ካህናት ዐበይት እለ ቅቡዓን በቅብዐ ዕረፍት"። ትርጉም፦ በጣፈጠ ቅብዐ ክህነት ለተቀቡ ለታላላቆች ካህናት አልዓዛር ና ፊንሐስ ሰላምታጨይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወየአም እግዚአብሔር ፍኖተ ንጹሐን። ወለዓለም ውእቱ ርስቶሙ። ወኢይተሐፈሩ በመዋዕለ እኩያት"። መዝ 36፥18-19። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥40-ፍ.ም። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦"ዘገብረ ተአምረ በግብጽ። ወመንክረ በሐቅለ ጣኔዎስ። ወረሰየ ደመ ለአፍላጊሆሙ"። መዝ 77፥43-44። የሚነበቡት መልዕክታት ገላ 4፥4-13፣ ራእ.ዮሐ 12፥13-ፍ.ም ወይም 1ኛ ጴጥ 1፥8-13 እና የሐዋ ሥራ 12፥20-ፍ.ም የሚነበበው ወንጌል ማቴ 2፥13-16። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ግንቦት ፳፬ (24) ቀን። ❤ እንኳን ለክብር ባለቤት ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከአረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ከቅድስት ሰሎሜ ጋራ ወደ ግብጽ ምድር በስደት ለወረዱበት ዓመታዊ በዓል፣ ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቅ ነቢያት አንዱ ለሆነው ለነቢዩ ዕንባቆም ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል፣ ለአሮን ልጅ ለካህኑ ለቅዱስ አልዓዛር ለዕረፍት በዓልና ከእንጽና አገር ለሆነ ለከበረ ለቀሲስ ቅዱስ አብቊልታ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡት፦ ከቅዱሳን አርከሌድ፣ ከቴፍላስና ከማርዩ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን፡ያሳትፈን። + + + ❤ በዚች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከአረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ከቅድስት ሰሎሜ ጋራ ወደ ግብጽ ምድር ወረደ። ❤ ያን ጊዜም እርሱ ጌታ የሁለት ዓመት ሕፃን ነበር። ወንጌላዊ እንዳለ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ "ተነሥተህ ሕፃኑና እናቱ ን ይዘህ ወደ ግብጽ ምድር ሽሽ ተመለስ ብዬ እስምነግርህም በዚያው ኑር"። ❤ ጌታችንም ወደ ግብጽ መምጣት ስለ ሁለት ሥራዎች ነው። አንዱ ኄሮድስ ቢያገኘው ሊገድለው እንደአይችል። ስለዚህ ሌሎች ትስብእቱ ምትሐት ነው ብለው አንዳያስቡ። ሁለተኛው የግብጽ ሰዎች በመካከላቸው በመመላለሱ ጸጋውን እንዲያገኙ ጣዖታትንም ቀጥቅጦ ለማጥፋት "እንሆ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብጽ ይወርዳል ጣዖታትም በፊቱ ይወድቃሉ" ያለው የነቢይ ኢሳይያስ ትንቢት ይፈጸም ዘንድ። ❤ የክብር ባለቤት ጌታችንም በረቀቀ ጥበቡ ሸሸ በመጀመሪያም የደረሰበት አገር ስሙ በስጣ ይባላል አልተቀበሏቸውም በዚያም የውኃ ጒድጓድ ቆፈሩ ያቺም ውኃ ለሩቆች ፈዋሽ ስትሆን ለዚያች አገር ሰዎች ግን መራራ ሆነች። ከዚያም በጉምኑዲ መንገድ ተጒዘው ወንዝ ተሻግረው ወደ ምዕራብ ደረሱ። የክብር ባለቤት ጌታችንም ተረከዙን በአለት ላይ አደረገ በተረከዙም አምሳል በአለቱ ላይ ተቀረጸች እስከ ዛሬ ያም ቦታ የጌታችን የተረገዝ ቅርጽ ተባለ። ጌታችንም እመቤታችን ድንግል ማርያምን "እናቴ ሆይ በዚህ ቦታ ቤተ ክርስቲያን በስምሽ ይሠራ ዘንድ እንዳለው ዕወቂ። በውስጡም ድንቅ ተአምራትን አደርጋለሁ ስሙም ደብረ ምጥማቅ ይባላል" አላት። ❤ ከዚያም ወደ ፀሐይ መግቢያ ወዳለ ባሕር ሔዱ የአስቄጥስንም በረሀ ዱር ከሩቅ አዩ። ጌታም በላዩ ባረከ እናቱንም "እናቴ ማርያም ሆይ በዚህ ዱር ውስጥ ብዙዎች ሰዎች መነኰሳትን ሁነው በገድልም ተጸምደው በመላእክት አምሳል ያገለግሉኛል"። ❤ ከዚያም በፀሐይ መውጫ በኵል ወደአለ ተራራ ሒዱ ዮሴፍም የሚመረኰዘው በትር በእጁ ነበር ጌታችንም "ይህ ቦታ የሚቃጥል በረሀ ነውና እንቀመጥ" አለ። ጌታችንም የዮሴፍን በትር አንሥቶ ሰበራት ጥቃቅን ስብርባሪዎች አድርጎ በዚያ ቦታ ተከላቸው። በከበሩ እጆቹ ጒድጓድ ማሰ መዓዛው የሚጣፍጥ ውኃ ፈልቆ ፈሰሰ ከእዚያ ውኃም በመሐል እጁ እየዘገነ የተከላቸውን ስብርባሪዎች አጠጣቸው። ወዲያውኑ በቀሉ አድገውም ታላላቅ ዛፎች ሆኑ ከእርሳቸውም ጣፍጭ ሽታ ሸተተ። እርሱም ከሽቱዎች ሁሉ እጅግ የሚጣፍጥ ነው በለሳንም ብሎ ጠራቸው። እናቱን ድንግል እመቤታችንንም "እናቴ ሆይ ይህ የተከልኩት በለሳን እስከ ዓለም ፍጻሜ ከዚህ ይኖራል የክርስትና ጥምቀትንም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ለሚጠመቁ ከእርሱ ቅባት ይገኛል" አላት የዚያም ቦታ ስም መጠሪያ ነው። ❤ ከዚያም ብንህሳ ወደሚባል አገር ሔዱ ትርጓሜው ቤተ ኢየሱስ የሆነ በይሱስ ወደሚባልም ቦታ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በሽታውን ደዌውን ሁሉ የሚፈውስ የጒድጓድ ውሃ አደረገ። ሁለተኛም በአንዲት የጒድጓድ ውኃ ምልክትን በየዓመቱ አደረገ ይኸውም ከቀኑ እኵሌታ በማዕጠንትና በጸሎት ጊዜ ለእግዚአብሔር በዚያች ውኃ ጒድጓድ ዕጣንን ሲያሳርጉ የከበረ የወንጌል ንባብም ሲፈጸም በዚያች ጒድጓድ ውስጥ ያለ ውኃ ወደ ላይ ወጥቶ እስከ ጒድጓዱ አፍ ይደርሳል። ከእርሱም ይባረካሉ ከዚያም በኋላ እንደ ቀድሞው ወደ ቦታው ይመለሳል። ውኃው ከነበረበት እስከ ደረሰበት ይሰፍሩታል። ሃያ ክንድ የሆነ እንደሆነ የጥጋብ ዘመን ይሆናል ዐሥራ ሰባት ክንድ ከሆነ ግን በግብጽ አገር ታላቅ ረኃብ ይሆናል። ❤ ከዚያም ወደ እስሙናይን አገር ሔዱ በዚያ ያሉ ጣዖታትም ወድቀው ተሰባበሩ። እነርሱም ስሙ አፍሎን ከሚባል ሰው ዘንድ ተቀመጡ። በዚያም የእሸ እንጨት ዛፎች አሉ ለጌታችንም ሰገዱ እስከ ዛሬም እንደ ሰገዱ ናቸው። ከዚያም ወደ ደብረ ቊስቋም ሒደው በውስጧ ስድስት ወር ተቀመጡ በዚያም በሽታን ሁሉ የሚያድን የጉድጓድ ውኃ አደረገ። ❤ ጌታችንም የፈቀውን በግብጽ የሚኖርበት ወራት በፈጸመ ጊዜ ይኸውም ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ነው። ኄሮድስም ከሞተ በኋላ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ "የሕፃኑን ነፍስ የሚሹት ሙተዋልና ተነሣ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ተመለስ" አለው። ያንጊዜም ተመልሰው ወደ ምስር ደረሱ ወደ መዓልቃም በዚያ በዋሻ ውስጥ አደሩ እርሷም እስከ ዛሬ የቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን ናት። ከዚያም ወጥተው ወደ መጣርያ ደርሰው በውስጧ ታጠቡ። ይቺም የውኃ ምንጭ አስቀድመን እንደተናገርን ጌታችን ያፈለቃት ከዚያች ሰዓት ጀምሮ የተባረከችና የከበረች ሆነች። ከዚያም ጌታችን የተከለው የክርስትና ጥምቀት የሚፈጸምበት በለሳን ቅባት የሚመጣው ነው። በእርሱም ደግሞ አብያተ ክርስቲያናት ንዋየ ቅዱሳትና ታቦተ ሕጉም የሚከበርበት ድኅነትም የሚደረግበት ለክርስቲያኖች ሁሉ መመኪያቸው ነው። ❤ በጌታችን መመለስም "ልጄን ከግብጽ ጠራሁት" ያለው የኦዝያን ትንቢት ተፈጸመ። ስለዚህም ተአምራትን በግብጽ ድንቅ ሥራንም በጣኔዎስ በረሀ ያደረገ በማለት እየዘመርን በዚች ዕለት መንፈሳዊ በዓልን ልናደርግ ይገባናል። ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ስለ እኛ ለተሰደደ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በእኛ ላይም ይቅርታውና ምሕረቱ ይሁን። አምላክን የወለደች የተባረከች የድንግል እመቤታችን ማርያም በረከቷ የቅዱስ ዮሴፍና የቅድስት ሰሎሜም በረከታቸው ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ነቢዩ ቅዱስ ዕንባቆም፦ ይህም ቅዱስ በአንዲት ዕለት እህሉን ለሚያጭዱለት ምሳቸውን አዘጋጅቶ ተሸክሞ ሲሔድ መልአክ ተገልጾለት "ይህን መብል በባቢሎን አገር በአንበሶች ጒድጓድ ውስጥ ላይ ለነቢዩ ቅዱስ ዳንኤል ውሰድ" አለው። ዕንባቆምም "ጌታዬ ሆይ ባቢሎንን አላየኋት ጒድጓዱንም አላውቀው" አለው። የእግዚአብሔር መልአክም በራሱ ጠጉር ያዘው ምግቡን በእጁ እንደያዘ ወሰደውና ጒድጓዱ እንደተዘጋ አስገባው ምግቡንም ሰጥቶ መገበው ወዲያውኑ ዕንባቆምን ወደ ይሁዳ አገር መለሰው። ❤ በአረጀና በሸመገለም ጊዜ የእስራኤል ልጆች ከተማረኩበት ተመልሰው ቤተ መቅደስን ሠሩ። ቅዱስ ዕንባቆምም ኢየሩሳሌም ደርሶ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ በታላቅ ደስታም ተቀበሉት ትንቢቱንም ሊሰሙ ወደርሱ ተሰበሰቡ አፉንም ከፍቶ በመንፈስ ቅዱስ እንዲህ አለ "አቤቱ ድምፅህን ሰማሁ ሰምቼም ፈራሁ ሥራህንም አይቼ አደነቅሁ" አለ። ስለ መድኃኒታችንም መውረድና በይሁዳ ክፍል በሆነች በቤተ ልሔም ስለመወለዱ ሲናገር "የተመሰገነ እግዚአብሔር ግን ከፋራን ተራራ ከቴማን ከይሁዳ አውራጃ ይመጣል" ብሎ እስከ

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ❤ ❤ ግንቦት ፳፫ 23 ቀን ❤ እንኳን ለኢትዮጵያኑ ጻድቃን እንደ ሐዋርያው ቅዱስ ታዴዎስ ግመልን በመርፌ ቀዳዳ ላሾለኩ ለታላቁ አባት ለአቡነ ታዴዎስ ዘጽላልሽ ለልደታቸው በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ ታዴዎስ ዘጽላልሽ፡-አባታቸው ካህኑ ሮማንዮስ የደብረ ሊባኖሱ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት አጎት ሲሆኑ እናታቸው ማርታ ይባላሉ፡፡ የትውልድ ቦታቸው ጽላልሽ ዞረሬ ነው፡፡ ሲወለዱ ዓምደ ብርሃን ተተክሎ የታየ ሲሆን እርሳቸውም በብርሃን ልብስ ተጠቅልለው ታይተዋል፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ለሊቀ ካህናቱ ለሕይወት ብነ በጽዮን ተሰጥተው ሃይማኖትን በሚገባ ተምረዋል፡፡ ❤ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዳሞት ተሻግረው ሞተሎሚን አስተምረው ካሳመኑት በኋላ አቡነ ታዴዎስን ወደ እርሳቸው እንዲመጡ ልከውባቸው ሄደው አቡነ ተክለ ሃይማኖትን እያገለገሉ ዘጠኝ ዓመት ተቀመጡ፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ግን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ አባ በጸሎተ ሚካኤል ሲሄዱ አቡነ ታዴዎስም ወደ ጽላልሽ ተመልሰዋል፡፡ ሁለቱም ከ32ዓመት በኋላ ተመልሰው በጽላልሽ ተገናኘተው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለአቡነ ታዴዎስ ማዕረገ ምንኩስናን ሰጥተዋቸዋል፡፡ ❤ አቡነ ታዴዎስም በሥጋ ዕድሜ ታላቅ ቢሆኑም እንደታናሽ ብላቴና አቡነ ተክለ ሃይማኖትን እያገለገሉ በደብረ ሊባኖስ ተቀምጠዋል፡፡ ከዚህ በኋላ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አቡነ ታዴዎስን ወደ ጽጋጋ እንዲሄዱ ነገሯቸው ምክንያቱም አቡነ አኖሬዎስ በዚያ ሲያስተምሩ ከሃዲያን ደብድበው አስረዋቸው ነበር፡፡ እሳቸውም ታስረው ሳለ ወደ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘንድ የሚላካቸው ሲያስቡ ቁራ መጥቶ "እኔ እላክሃለሁ" ቢላቸው "ክፋትህ እንደ መልክህ ነው"ብለው እምቢ አሉት፡፡ ፀአዳ ኦፍ መጥቶ እኔ ከሀገራችሁ ኮዞረሬ የመጣሁ ነኝ "እኔ እላክሃለሁ" ብትላቸው "መጥተህ አድነኝ" ብለው በክንፏ ላይ ጽፈው ልከዋት እርሷም መልእክቱን ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት አድሳ ነበር፡፡ ስለዚህም ነው አቡነ ታዴዎስን ሕዝቡን ከኃጢአት ግዞት አኖሬዎስን ከእስራት እንንዲያስፈቱ የላኳቸው፡፡ ❤ አቡነ ታዴዎስም ከደብረ ሊባኖስ ወደ ደብረ ማርያም በሠረገላ ነፋስ ተጭነው በአንድ ሰዓት ደርሰው መዩጥ ከተባለውና አኖርዮስን ካሰራቸው ንጉሥ ፊት ቢደርሱ ንጉሡ በግንጋጤ መልአክ የመጣበት መስሎት ሲፈራ ከሰው ወገን መሆናቸውን ነግረው ክርስትናን አስተማሩት፡፡ ጋኔን ከእሳት ጥሎት ሲሠቃይ የሚኖርና ሊሞት የደረሰ ልጁን ቢፈውሱለት በትምህርታቸውና በተአምራታቸው አምኖ ሕዝቡ ክርስትናን እንዲቀበል በአዋጅ አስነገረ፡፡ አፍጃል የሚባለው ባለጸጋ ወደ አቡነ ታዴዎስ ቀርቦ ሲማር "ባለጸጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀላል" ማቴ 19፥24፣ ማር10፥25፣ ሉቃ18፥25) የሚለውን የወንጌል ቃል ሲሰማ ለአእምሮው ረቆበት "እስቲ አድርገህ አሳየኝ?" አላቸው፡፡ አቡነ ታዴዎስም እናቲቱን ግመል ከነጇ ቀጥሎም 28ግመሎችን በየተራ በመርፌ ቀዳዳ እያሾለኩ አሳይተውታል፡፡ ሕዝቡ ሁሉ በእጅጉ ሲገረምና "በአምላከ ታዴዎስ ስም አምናለሁ" ሲል የባለጸጋው ልጅ ሙሳ ግን "በምትሀት አሳይቶን ነው እንጂ የእውነት አይደለም" በማለት አባቱንም እንዳያምን ይናገር ጀመር፡፡ ይህንንም ሲናገር በመጀመሪያ ያለፈችው እናቲቱ ግመል እረግጣ ገደለችው፡፡ ❤ አቡነ ታዴዎስም ንጉሡን፣ አባቱን አፍጃልንና ሕዝቡን የሞተ እንደሚነሣ ሲያስምሯቸው "የሞተ ይነሣልን? እስኪ ይህ የሞተው ልጅ ይነሳና ሁሉም አይቶ ይመን" አሏቸው፡፡ እሳቸውም "ዛሬ ተቀብሮ ይዋልና ነገ በሦስተኛው ቀን ይነሣል" ብለዋቸው ተቀብሮ ዋለ፡፡ በማግሥቱም አፍጃልን ጠርተው "አልዓዛርን ከሞት ባስነሣው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ልጄ ሆይ ና ውጣ" ብለህ ከልጅህ መቃብር ላይ አኑረው" ብለው ዘንጋቸውን ሰጡት፡፡ ሄዶም እንዳሉት ቢያደርግ ልጁ አፈፍ ብሎ ተነሥቷል፡፡ ይህንን ያዩ የአገሩ ሰዎች ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል፡፡ እሳቸውም 12አብያተ ክርስቲያናትን አሳንጸው ሞቶ የተነሳውን ሙሳን ሙሴ ብለው ሰይመው አስተምረው ሊቀ ካህናት አድርገው ሾመውት አቡነ አኖሬዮስን ይዘው ወደ ጽላልሽ ዞረሬ ተመልሰዋል፡፡ ❤ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ካረፉ በኋላ አባ ያዕቆብ የተባሉ ጳጳስ ከግብፅ መጡ፡፡ የአቡነ ታዴዎስን ዜና ሲሰሙ ተደስተው ከአቡነ ፊሊጶስ ጋር ሆነው አስጠርተዋቸው "የአባታችሁን ዜና ገድል ንገሩኝ" አላቸው፡፡ አቡነ ታዴዎስም ጨዋታ በአስተርጓሚ አይሰምርም" ብለው ወደ ጌታችን ቢጸልዩ የጳጳሱ ቋንቋ ለአቡነ ታዴዎስ፣ የአቡነ ታዴዎስም ቋንቋ ለጳጳሱ ተገልጦላቸው የመሸ የነጋ ሳይመስላቸው40 ጾምን ሲጨዋወቱ ቆይተዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ጳጳሱ ከንጉሡ ተማክረው "ሊቀ ካህናት ዘጽላልሽ" ብለው ሾመዋቸዋል፡፡ ❤ በነግህና በሰርክ ቤተ ክርስቲያንን እያገለገሉ፣ ቀን ወንጌልን እየሰበኩ፣ ሌሊት ከባሕር ገብተው ሲጸልዩ እያደሩ በታላቅ ተጋድሎ እየኖሩ ሳለ ከ10ዓመት በኋላ ሰይጣን በንጉሡ በዓምደ ጽዮን ፍቅረ ዝሙት አሳድሮበት በክፉዎችም ምክር አታሎት የአባቱን ቅምጥ አገባ አቡነ ታዴዎስም ይህን ሲሰሙ እንደ ነቢዩ ኤልያስና እንደ መጥምቁ ዮሐንስ በቀጥታ ሄደው ንጉሡን ገሥጸው አወገዙት፡፡ ገሥጸውና አውግዘው አቡነ ማትያስን አስከትለው ሲመለሱ ቅምጧ የንጉሡ ሚስት በፈረስ ተከትላ ደርሳ የኋሊት አሳስራ ዛሬ "ማርያም ገዳም" ከሚባለው ቦታ ፊት ለፊት ካለው ትልቅ ገደል ውስጥ ሁለቱንም ጣለቻቸውና ጥር29 ቀን በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡ ❤ በሰማዕትነት ዐርፈው ደማቸው ከፈሰሰበት ከገደሉ ስር በፈለቀው ጸበላቸው "ታዴዎስ ወማትያስ" እያለ ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እያለ የተጠመቀ ሰ እንደ 40 ቀን ሕፃን እንደሚሆን ጌታችን ቃል ኪዳን ገብቶላቷቸዋል፡፡ ይህ ሰማዕትነት በተቀበሉበት አካባቢ የተሠራው ቤተ ክርስቲያናቸው በጠላት ወረራ ጊዜ ፈርሶ ቦታው ጠፍ ሆኖ የኖረ ቢሆንም የአካባቢው ሕዝብ ቦታውን ከልሎ በክብር ሲጠብቀው ስለኖረ ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ የአቡነ ታዴዎስ ታቦታቸው በ2005ዓ.ም ከኢቲሣ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ወጥቶ ጻድቁ ሰማዕትነት በተቀበሉበት አካባቢ በተሠራው መቃኞ ቤተ ክርስቲያናቸው በታላቅ ክብር ገብቷል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑም ከኢቲሣ በእግር የአንድ ሰዓት ተኩል ርቀት ላይ ይገኛል። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳንና የጣና ሐይቅ ደብረ ማርያም ገዳም አጭር ታሪክ ከምትላው መጸሐፍ። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ግንቦት ፳፫ (23) ቀን። ❤ እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት ለሆኑ ለሐዋርያው ቅዱስ ዮልዮስ ለዕረፍት በዓል፣ ለሐዋርያው ቅዱስ አፍሮዲጡ ለመታሰቢያ በዓሉና በደብረ ምጥማቅ ለእመቤታችን መገለጥ ለሦስተኛ ቀን መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ ሰማዕታት ከሆኑ ከአንስያ፣ ከዮልያና ከቀሲስ ታኦድራጦስ፣ ከጳጳስ ታድሮስ፣ከዮልያኖስና ከእናቱ ከእስክንድርያ፣ ከኤስድሮስ፣ ከሚስቱና ከሁለት ወር ልጅዋ እኔ ከእናቴ ጋራ ክርስቲያን ነኝ ብሎ ከተናገረና ዲዮቅልጥያኖስ ከገደላቸው ለእነርሱም ማኅበር ከመታሰቢያቸው ከሆነ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ቅዱስ ዮልዮስ፦ የዚህም ቅዱስ ትውልዱ ከይሁዳ ነገድ ከእስራኤል ልጆች ከቤተ ገብርኤል ነው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መረጠው። ከሰባ ሁለቱ አርድእትም የተቆጠረ ሆነ የመንፈስ ቅዱስንም ሀብት ከሐዋርያት ጋራ ተቀበለ ከእርሳቸውም ጋራ ታላቅ መከራ ደርሶበታል። ❤ ከዚህ በኋላ ሐዋርያት በአንብሮተ እድ ኤጲስቆጶስነት ሹመው ከቅዱስ እንድራኒቆስ ጋራ በአገሮች ውስጥ እንዲሰብክ ላኩት። ቅዱስ እንድራኒቆስም በአለፈው ዕለት በዐረፈ ጊዜ ይህ ቅዱስ ዮልዮስ ገንዞ ቀበረው። ከዚህ በኋላ ከርሱ እንዳይለይ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ በማግሥቱ ዛሬ ግንቦት 23 ቀን ዐረፈ። ❤ እንሆ የከበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስም እሊህን ሐዋርያ በሮሜ ክታቡ ቅዱስ እንድራኒቆስንና ቅዱስ ዮልዮስን ሰላም በሏቸው ሲል አስታውሷቸዋል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባቶቻችን ሐዋርያት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 23 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለዮልዮስ እምቤተ ገብርኤል ልደቱ። ዘተወክፈ ጸጋ ለመንፈስ ቅዱስ ጊዜ ርደቱ። ለእንድራኒቆስ ረድእ ሳኒታ ዕረፍቱ። እግዚአብሔር አግዐዞ እምቅኔ ዓለም ዝንቱ። በከመ ሰአለ ኢይፍልጦ ሎቱ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ(አርኬ) የግንቦት 23። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር። ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን። በዘአዝፋረ ወርቅ ዑፅፍት ወኊብርት"። መዝ 44፥12-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥16፥19። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ44፥9-10። የሚነበበው መልዕክታት ሮሜ 16፥7-10፣ ይሁ 1፥20-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 21፥15-21። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ10፥17-25። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ ዮልዮስና የእመቤታች የደብረ ምጥማቅ በዓል ሰሞን። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "አመ ትበርቂ በደብረ ምጥማቅ ኀምሰ ዕለታተ። ትእምርተ ገጽኪ ይርአይ እስከ ይትነሣእ ዘሞተ። ሚ መጠነ ማርያም ታሥተፌሥሒ ትፍሥሕተ። ኅድጊሰ ጽጌ ፍቅርኪ በጊዜ ንቃሑ መዓልተ። ብፁዕ ዘርእየኪ በሕልሙ ሌሊተ"። ትርጉም፦ የፊትሽን መልክ ያይ ዘንድ የሞተ ሰው እስኪነሣ ድረስ በደብረ ምጥማቅ ለአምስት ቀናት ያኽል በተገለጽሽ ጊዜ ማርያም ምን ያኽል ደስ ታሰኚ ኖሯል! በቀን የታየው የፍቅርሽ አበባ ይቅርና ሌሊት በሕልሙ ያየሽ ምስጉን ነው። ሊቆቹ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም በማኅሌተ ጽጌ። https://t.me/Eotcw

photo content
+1

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ግንቦት ፳፪ (22) ቀን። ❤ እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት ለአንዱ ለከበረና ለተመሰገነ ለሐዋርያው ቅዱስ እንድራኒቆስ ለዕረፍቱ በዓል፣ በደብረ ምጥማቅ ለእመቤታችን መገለጥ ለሁለተኛ ቀን መታሰቢያ በዓልና ለትንሣኤ አምስተኛ ሳምንት በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከምሥራቃዊ ከቅዱስ ያዕቆብ ከመታሰቢያው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ቅዱስ እንድራኒቆስ፦ ይህንንም ሐዋርያ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መረጠው። እርሱም የእግዚአብሔር መንግሥት እንዲሰብኩ ጌታ ከመከራው በፊት ከላካቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የተቆጠረ ነው። ❤ በጽርሐ ጽዮንም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከሐዋርያት ጋራ መንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀብሎ በብዙ አገሮች ውስጥ ሰበከ። በኒውብያ አገር ላይም ሐዋርያት በአንብሮተ እድ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት በውስጧም ሰበከ በጨለማ በድንቁርና የሚኖሩ ብዙዎች አረማውያንንም የክብር ባለቤት ወደሆነ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት አስገባቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ሐዋርያ ቅዱስ ዮልዮስን ወሰደው በአንድነትም በብዙ አገሮች ዙረው አስተማሩ። ብዙ ሰዎችንም አጠመቁ ተአምራትንም በማድረግ ከሰዎች ላይ አጋንንትን አባረሩ። ብዙዎች በሽተኞችንም ፈወሱአቸው የጣዖታትንም ቤቶች አፍርሰው የክብር ባለቤት የሆነ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናትን አነፁ። አገልገሎታቸውንም በፈጸሙ ጊዜ ጌታችን ከድካም ወደ ዕረፍት ከኀዘንም ወደ ደስታ ሊወስዳቸው ወደደ። ❤ ከዚህም በኋላ ሐዋርያ ቅዱስ እንድራኒቆስ ታመመና በዚች ቀን ግንቦት 22 ቀን ዐረፈ ቅዱስ ዮልዮስም ገንዞ በመቃብር አኖረው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባቶቻችን ሐዋርያት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት22 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ሰላም ለእንድራኒቆስ ዕብሎ። ውኂዝ መንፈስ ዘሰትየ ምስለ ሐዋርያት በአመ ድብሎ። ኀበ ሖረ ይስብክ አህጉራተ አድያም ኵሎ። አብያተ ክርስቲያን ሐኒፆ ወአብያተ ጣዖት አንሒሎ። ዕሴተ ተስፋሁ አድምዐ በሰማይ ዘሀሎ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የግንቦት 22። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "በትርከ ወቀስታምከ አማንቱ ገሠፀኒ። ወሠራዕከ ማእደ በቅሜየ። በአንፃሪሆሙ ለእለ ይሣቅዩኒ"። መዝ 22፥4-5 የሚነበበው ወንጌል 27፥27-31። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ 18፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 16፥6-10፣ 1ኛ ዮሐ 2፥27-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 21-15-21። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 10፥1-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ እንድራኒቆስ የዕረፍት በዓልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw