es
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Ir al canal en Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Mostrar más
1 161
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
photo content

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መስከረም ፳፱ (29) ቀን። ❤ እንኳን ለታላቋ ሰማዕት ለቅድስት አርሴማ ለእመቤቷ አጋታና ለደናግል ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል፣ ለሐዋርያው ለነባቤ መለኮት ለቅዱስ ዮሐንስ ለሥጋው ፍልሰት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከጌታችንና መድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ ከተወለደበት ከልደቱ (ከበዓለ ወልደ) ከወራዊ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ "ሰላም ለአርሴማ ቅድስት ከመ በቀልት ዘይመስል ቆማ፤ ወዘከለላ ዘመንፈስ ግርማ ዘፈጽመት ገድላ በጻማ ወበመንግሥተ ሰማይ ዐቢይ ስማ"። ትርጉም፦ ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች፤ የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቁመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትኾን ለቅድስት አርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታቱ ላ­ይ። + + + ❤ ታላቋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ እና እመምኔቷ አጋታና ደናግል፦ ይህም እንዲህ ነው በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን እርሱ መልኳ ውብ የሆነ ብላቴና ድንግል ሊአገባ ሽቶ በየሀገሩ ሁሉ ሒደው መርጠው ያመጡለት ዘንድ አሽከሮቹን አዘዘ። ይችንም የሚመስላት የሌለ ቅድስት አርሴማን በሮሜ አገር በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ አገኙዋት። ሥዕሏንም ሥለው ለንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ላኩለት ንጉሡም ሥዕሏን በአየ ጊዜ እጅግ ደስ አለውና ለሠርግ እንዲመጡ ወደ መኳንንቱ ላከ። ❤ እሊያ ደናግልም ይህን ነገር በአወቁ ጊዜ ይረዳቸው ዘንድ ድንግልናቸውንም ይጠብቅ ዘንድ አልቅሰው ወደ እግዚአብሔር ለመኑ። ከዚህም በኋላ ተነሥተው በሥውር ሸሹ የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደ ሆነ ወደ አርማንያ ሀገርም ደርሰው በአንድ ቦታ ተቀመጡ ከእርሳቸውም ጋር የተሰደዱ ቁጥራቸው ሰባ አምስት የሆነ ወንዶች፣ ሴቶችም ሠላሳ ዘጠኝ የሆኑ ከእርሳቸው ጋራ አሉ። ምግባቸውን አያገኙም ነበርና በታላቅ ችግር ውስጥ ኖሩ ከእነርሱም መብራት የምትሠራ አንዲት ሴት ነበረች ከእርሷም የእጅ ሥራ ከሚገኘው በየጥቂቱ ይመገባሉ። ❤ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም የከበረች አርሴማን በፈለጋት ጊዜ አላገኛትም ግን በአርማንያ አገር እንዳለች ስለርሷ ሰማ። ደግሞ ለአርማንያ ንጉሥ ለድርጣድስ ስለርሷ ከዲዮቅልጥያኖስ ሸሽታ እንደ መጣች የአርሴማን ሥራ ነገሩት እርሱም አንዱን የአርማንያ መኰንን ለእኔ ጠብቃት ወደ እኔም ላካት ብሎ አዘዘው። ❤ ደናግሉም ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ተሠወሩ ወደ ንጉሥም ወነጀሉአቸው ንጉሡም ቅዱስት አርሴማን በክብር አድርገው ያመጧት ዘንድ አዘዘ እርሷም ወደ እርሱ መምጣትን እምቢ በአለች ጊዜ እየጎተቱ ወስደው ወደርሱ አደረሷት። የቅድስት አርሴማንም ላህይና ደም ግባቷን በአየ ጊዜ ድንግልናዋን ሊያረክስ ሽቶ እናቷ አጋታን አባብላ እሺ ታሰኝለት ዘንድ አዘዛት አጋታም ወደርሷ ሒዳ ልቧን አስጨከነች እንዲህም አለቻት። "ዕወቂ ይህ ርኲስ አረሚ እንዳያረክስሽና ሰማያዊ ሙሽራሽን እንዳትተዪ እርሱም ክብር ይግባውና የእግዚአብሔር ልጅ ሕያው ክርስቶስ ነው"። ❤ ንጉሡም ይዞ ወደ እልፍኙ ሊአስገባት ከአደባባይ መካከል ተነሥቶ ድንግል አርሴማን ያዛት። በዚያንም ጊዜ በቅድስት አርሴማ ላይ የእግዚአብሔር ኃይል አደረባትና በምድር ላይ ጣለችው እርሱ ግን በጦርነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለ ነበር በታናሽ ሴት ብላቴና ስለተሸነፈ ያን ጊዜ አፈረ። ራሷንም በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጧት ከዚህም በኋላ ደናግሉን ሁሉ ከእናታቸው አጋታ ጋር ይገድሏቸው ዘንድ አዘዘ። ❤ አንዲት የታመመች ድንግል ነበረች በዐልጋዋ ላይም እንደተኛች ወደ ወታደሮች ጮኸች መጥተውም እንደ እኅቶቿ ራሷን ቆረጡ ሁሉም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ እነዚያንም ከሮሜ አገር አብረው የመጡ ወንዶችን ገደሏቸው ቁጥራቸውም ሰባ አምስት ናቸው ሥጋቸውም በተራራ ላይ የተጣለ ሁኖ ቀረ። ❤ ሰማዕታትም ከተገደሉ በኋላ በንጉሡ ላይ ጋኔን ተጫነበት መልኩም ተለውጦ እንደ እርያ ሆነ። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ወደርሱ መጥቶ በላዩ ጸልዮ እስከ አዳነው ድረስ ስለዚህም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ። የቅዱሳን ሰማዕታትንም ሥጋቸውን ከተጣለበት ሰብስበው በአማረ ቦታ አኖሩአቸው ያማረች ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ተሠራችላቸው። ከእነርሱም ታላላቅ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት አርሴማና በቅዱሳን ሰማዕታት ሁሉ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 29 ስንክሳር። + + + ❤ "በፆታ ኅሩያን ዕደው እንዘ ተኀብሪ ፆታ። እንበለ ትፍርሂ ምንተ ብልሀተ ኵያንው ወሰይፍ ልሳን መንታ። ዘፈጸምኪ ስምዐ በእንተ ኢየሱስ ንጉሠ ኤፍራታ። ሰላም ለኪ አርሴማ ምስለ እምኪ አጋታ። ወለደናግል ሰላም ምስሌኪ ዘሞታ"። ትርጉም፦ በተመረጡ ወንዶች ወገንነት ተባብረሽ ኹለት አፍ ያለው ሰይፍንና የጦሮችን ስለትን ምንም ሳትፈሪ የኤፍራታ ንጉሥ ስለሚኾን ስለ ኢየሱስ ምስክርነት የፈጸምሽ ቅድስት አርሴማ ከእናትሽ ከአጋታ ጋር ሰላምታ ላንቺ ይገባል፤ ካንቺ ጋር የሞቱ ለኾኑ ደናግል ሰላምታ ይገባል። + + + ❤ "ሰላም እብል ዘሥጋከ ፍልሰተ። ኀበ ኢይጥዕም ሞተ። ዮሐንስ ንጹሕ ዘኢተአምር ጥልቀተ። አርፈቀከ ውስተ ሕፅኑ ወሰዓመከ ስዕመተ። መለኮት ወልድ ዘለብሰ ትስብእተ፡፡ ትርጉም፦ ሞት ወደማያገኘው ( ብሄረ ኅያዋን) ሥጋህ ለመፍለሱ ሰላም እላለሁ፣ ማደፍን የማታውቅ ንጹሕ ዮሐንስ ወልድ የተባለ መለኮት ሰውነትን የለበሰ ከእቅፉ አስቀመጠህ መሳምን ሳመህ። ሊቀ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 29። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ይትፌሥሐ አድባረ ጽዮን። ወትሐሠያ አዋልደ ይሁዳ። በእንተ ፍትሕከ እግዚኦ"። መዝ 47፥11-12። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 25፥1-14። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "እግዚአብሔር ይቤለኒ ወልድየ አንተ። ወአነ ዮም ወለድኩከ። ሰአል እምኔየ እሁበከ አሕዛበ ለርስትከ"። መዝ2፥7-8። የሚነበቡት መልዕክታት ገላ 4፥1-12፣ 1ኛ ዮሐ 1፥1-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 3፥1-12። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 21፥21-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የቅድስት አርሴማ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

Amen lehulachn

+ነጽር ፡ ከመ ፡ ጕየተ ፡ ሕፃን ፡ አጕየዮ ፡ ለዲያብሎስ ፤ እስመ ፡ ኢጐየ ፡ ፈሪሆ ፡ አላ ያስተአምን ፡ ትስብእቶ ፡ ከመ ፡ ኮነ ፡ ሰብአ ፡ በእንቲአከ!!+ ቴዎዶጦስ ዘዕንቆራ 🌹እናቱ እስከ
+ነጽር ፡ ከመ ፡ ጕየተ ፡ ሕፃን ፡ አጕየዮ ፡ ለዲያብሎስ ፤ እስመ ፡ ኢጐየ ፡ ፈሪሆ ፡ አላ ያስተአምን ፡ ትስብእቶ ፡ ከመ ፡ ኮነ ፡ ሰብአ ፡ በእንቲአከ!!+ ቴዎዶጦስ ዘዕንቆራ 🌹እናቱ እስከነ ልጇ በልባችን ማረፊያ/መሸሸጊያ የምታገኝበት መልካም ወርኀ-ጽጌ ይሁንልን🌹

እመቤቴ ሆይ ለእኔም መልካሙን ስደት አስለምጂኝ። ስለ ልጅስ ስለወዳጅሽ ብለሽ የተሰደድሽ የክርስቶስ እናቱ እኔ ልጅሽን ተመልከቺኝ አንቺ ስለ ልጅሽ ተሰደድሽ እኔ ግን ከልጅሽ ተሰደድኩ። መልካሙን ስደ
እመቤቴ ሆይ ለእኔም መልካሙን ስደት አስለምጂኝ። ስለ ልጅስ ስለወዳጅሽ ብለሽ የተሰደድሽ የክርስቶስ እናቱ እኔ ልጅሽን ተመልከቺኝ አንቺ ስለ ልጅሽ ተሰደድሽ እኔ ግን ከልጅሽ ተሰደድኩ። መልካሙን ስደት ዘነጋሁት ክፉውን ስደት ግን ተያያዝኩት። ስለ ልጅሽ ሳይሆን ከልጅስ ተሰደድኩ ማዳኑንም ሁሉ ዘነጋሁት። እመቤቴ ሆይ ለእኔም መልካሙን ስደት አስለምጂኝ ከሃጢአት ሀገር ወደ እውነተኛ ሀገር ወዳቺ ቅዱስ ስደት እሰደድ ዘንድ ስጪኝ። ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ክፉን ስደት ከአንተ እርቄ እሰደድ ዘንድ ኀጢአቴ ግድ አለቺኝ ባዶ እግሬንም አስቀረቺኝ ለልቦናዬ(እግሮች) ንሰሃ የተባለ ቅዱስ መንገድን ሰራህለኝ ልመላለስበት ግን አልወደድሁም ። ስለ እኔ በምድር እንደተሰደድህ እኔም ወደ አንተ እንድሰደድ ቅዱስ መሰደድን ስጠኝ። ጌታዬ ሆይ ይህንንም ጊዜ ከሰጠኸንም ዘንድ መልካም የተመስጦ የፅሞና የንሰሐ ጊዜ አድርግልኝ። ከአንተ የምርቅበት ክፉ ስደት ሳይሆን ወደ አንተ የምቀርብበት ቅዱስ ስደትን እሰደድም ዘንድ ስጠኝ። “ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።”   — ማቴዎስ 5፥10 🌹🌹🌹

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ዮሐ. 8:1-12፡ "ወአምጽኡ ኀቤሁ ጸሐፍት" - "ጻፊዎችና፡ፈሪሳውያንም፡በምንዝር፡የተያዘችን፡ሴት፡ወደ፡እርሱ፡አመጡ፡በመካከልም፡እርሱዋን፡አቁመው። መምህር፡ሆይ፥ይህች፡ሴት፡ስታመነዝር፡ተገኝታ፡ተያዘች። ሙሴም፡እንደነዚህ፡ያሉት፡እንዲወገሩ፡በሕግ፡አዘዘን፤አንተስ፡ስለ፡እርሷ፡ምን፡ትላለህ? አሉት። የሚከሱበትንም፡እንዲያገኙ፡ሊፈትኑት፡ይህን፡አሉ። ኢየሱስ፡ግን፡ጎንበስ፡ብሎ፡በጣቱ፡ በምድር፡ላይ፡ጻፈ፤ መላልሰው፡በጠየቁት፡ጊዜ፡ግን፡ቀና፡ብሎ፦ከእናንተ፡ኃጢአት፡የሌለበት፡አስቀድሞ፡በድንጋይ፡ይውገራት፡አላቸው። ደግሞም፡ጎንበስ፡ብሎ፡በጣቱ፡በምድር፡ላይ፡ጻፈ። እነርሱም፡ይህን፡ሲሰሙ፡ኅሊናቸው፡ወቀሳቸውና፡ከሽማግሌዎች፡ጀምረው፡እስከ፡ኋለኛዎች፡አንድ፡አንድ፡እያሉ፡ወጡ፤ኢየሱስም፡ብቻውን፡ቀረ፥ሴቲቱም፡በመካከል፡ቆማ፡ነበር። ኢየሱስም፡ቀና፡ብሎ፡ከሴቲቱ፡በቀር፡ማንንም፡ባላየ፡ጊዜ፦አንቺ፡ሴት፥እነዚያ፡ከሳሾችሽ፡ወዴት፡አሉ፧የፈረደብሽ፡የለምን? አላት። እርሷም፦ጌታ፡ሆይ፥አንድ፡እንኳ፡አለች።ኢየሱስም፦እኔም አልፈርድብሽም፤ሂጂ፥ካሁንም፡ጀምሮ፡ደግመሽ፡ኃጢአት፡አትሥሪ፡አላት። ደግሞም፡ኢየሱስ፦እኔ፡የዓለም፡ብርሃን፡ነኝ፤የሚከተለኝ፡የሕይወት፡ብርሃን፡ይሆንለታል፡እንጂ፡በጨለማ፡አይመላለስም፡ብሎ፡ተናገራቸው።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.24 KB

28/1/2015 ዓ.ም (፳፰/፩/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 እስመ አድኀንካ ለነፍስየ እሞት። ወለአእይንትየኒ እምአንብዕ። ወለአገርየኒ እምዳህፅ። መዝ 55፥13 🕯 ትርጉም ነፍሴን ከሞት እግሮቼን ከመውደቅ አድነኻልና። በሕያዋን ብርሃን እግዚአብሔርን ደስ አሠኘው ዘንድ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ሉቃ. 12:22-32፡ "ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ በእንተ" - "ለደቀ፡መዛሙርቱም፡እንዲህ፡አለ፦ስለዚህ፡እላችኋለሁ፥ለነፍሳችሁ፡በምትበሉት፡ወይም፡ለሰውነታችሁ፡በምትለብሱት፡አትጨነቁ። ነፍስ፡ከመብል፡ሰውነትም፡ከልብስ፡ይበልጣልና። ቍራዎችን፡ተመልከቱ፤አይዘሩም፡አያጭዱምም፥ዕቃ፡ቤትም፡ወይም፡ጐተራ፡የላቸውም፥እግዚአብሔርም፡ይመግባቸዋል፤እናንተስ፡ከወፎች፡እንዴት፡ትበልጣላችሁ? ከእናንተ፡ተጨንቆ፡በቁመቱ፡ላይ፡አንድ፡ክንድ፡መጨመር፡የሚችል፡ማን፡ነው? እንግዲህ፡ትንሹን፡ነገር፡እንኳ፡የማትችሉ፡ከሆናችሁ፥ስለ፡ምን፡በሌላ፡ትጨነቃላችሁ?አበባዎችን፡እንዴት፡እንዲያድጉ፡ተመልከቱ፤አይደክሙም፡አይፈትሉምም፤ነገር፡ግን፥እላችኋለሁ፥ሰሎሞንስ፡እንኳ፡በክብሩ፡ሁሉ፡ከነዚህ፡እንደ፡አንዲቱ፡አለበሰም። እግዚአብሔር፡ግን፡ዛሬ፡ያለውን፡ነገም፡ወደ፡እቶን፡የሚጣለውን፡በሜዳ፡የሆነውን፡ሣር፡እንዲህ፡የሚያለብሰው፡ከሆነ፥እናንተ፡እምነት፡የጐደላችሁ፥እናንተንማ፡ይልቁን፡እንዴት?እናንተም፡የምትበሉትን፡የምትጠጡትንም፡አትፈልጉ፥አታወላውሉም፤ይህንስ፡ሁሉ፡በዓለም፡ያሉ፡አሕዛብ፡ይፈልጉታልና፤የእናንተም፡አባት፡ይህ፡እንዲያስፈልጋችሁ፡ ያውቃል። ዳሩ፡ግን፡መንግሥቱን፡ፈልጉ፡ይህም፡ሁሉ፡ይጨመርላችኋል። አንተ፡ታናሽ፡መንጋ፥መንግሥትን፡ሊሰጣችሁ፡የአባታችሁ፡በጎ፡ፈቃድ፡ነውና፥አትፍሩ።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.30 KB

28/1/2015 ዓ.ም (፳፰/፩/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ዘይሁቦሙ ሲሳዮሙ ለእንስሳ። ወለእጕለ ቋዓት እለ ይጼውዕዎ። ኢይፈቅድ ኃይለ ፈረስ። መዝ. 146÷9 🕯 ትርጉም ለሚጠሩት ለቍራዎች ጫጩቶች ለእንስሳዎችም ምግባቸውን ይሰጣል። የፈረስን ኃይል አይወድም። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

photo content

ከቷም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ቅዱስ አባዲርና ቅድስት እኅቱ ኢራኢ፦ ይህም ቅዱስ ለአንጾኪያ መንግሥት የሠራዊት አለቃ ለሆነ ለፋሲለደስ የእኅቱ ልጅ ነው እርሱም በአባቱ መንግሥት የሠራዊት አለቃ ነበር በውስጡም የሚጸልይበት እልፍኝ አለው። ከሌሊቱም እኩሌታ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለትና እንዲህ አለው "የሰማዕትነት አክሊልን ትቀበል ዘንድ እኅትህ ኢራኢን ይዘህ ወደ ግብጽ አገር ሒድ። ስለ ሥጋችሁም እንዲአስብ ሳሙኤል የሚባለውን አንድ ሰው እኔ አዛለሁ" ከዚህም በኋላ ሰላምታ ሰጥቶት በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ። ❤ እንዲሁ ለእኅቱ ኢራኢ ተገልጦላት እንዲህ አላት "የወንድምሽን ቃሉን ስሚው ትእዛዙንም አትተላለፊ" ከእንቅልፏም ነቅታ እጅግ ተንቀጠቀጠች ወደ ወንድሟም ሒዳ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተገለጠላትና እንደ ተናገራት አስረዳችው። እጅግም ደስ አላቸው ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስም ስለ ስሙ ወደ ግብጽ አገር ሒደው ደማቸውን ያፈሱ ዘንድ በዚህ ምክር ተስማሙ። ❤ የቅዱስ አባዲር እናትም ይህን ነገር በአወቀች ጊዜ ልብሷን ቀዳ አለቀሰች ከባሮቿም ጋር ወደ ቅዱስ አባዲር መጥታ በሰማዕትነት እንዳይሞት ታምለው ጀመር እርሱም ስለ ሰማዕትነት ነገር ዲዮቅልጥያኖስን እንዳይናገረው ማለላት በዚያንም ጊዜ ከልቅሶዋ ታግሣ ጸጥ አለች። ወደ ሌላ ቦታ ሒዶ በሰማዕትነት እንደሚሞት ግን አላሰበችም። ቅዱስ አባዲርም በየሌሊቱ ሁሉ እንዲህ የሚያደርግ ሆነ ልብሱንም ለውጦ ከቤቱ ይወጣል በወህኒ ቤት ላሉ እሥረኞችም ውኃ በመቅዳት ያጥባቸዋል እስከሚነጋም እንዲህ ያደርጋል በር የሚጠብቀውንም እንዲህ ብሎ አዘዘው "ይህን ለማንም አትናገር ይህንንም ሥራ ብትገልጥ እኔ ራስህን በሰይፍ እቆርጣለሁ"። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ አባዲር ተነሣ እኅቱን ኢራኢንም ይዞ ወደ ግብጽ አገር ሒዶ እስክንድርያ ደረሰ። ከወታደሮችም ያወቁት አሉ "አንተ የሠራዊት አለቃ ጌታችን አባዲር አይደለህም እንዴ" አሉት። እርሱም ፈገግ ብሎ "ብዙዎች እንዲሁ ይሉኛል እኔ ግን እመስለው ይሆናል እንጂ እርሱን አይደለሁም" አላቸው ከዚያም ወደ ሌላ ቦታ ሔደ። በዚያም እንደቀድሞው እርሱ አባዲር እንደ ሆነ ተናገሩት እርሱም አይደለሁም ይላቸው ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ከእስክንድርያ ከተማ ወጥቶ ወደ ታላቋ የምስር ከተማ ሔደ በዚያም ከአባ አበከረዙን ጋር ተገናኝተው ከእርሱ ቡራኬ ተቀበሉ። ከዚያም ወደ እስሙናይን ደርሰው ከዲያቆን ሳሙኤል ጋር ተገናኙ በማግሥቱም ወደ እንጽና ከተማ ሔዱ በመኰንን አርያኖስም ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመኑ። መኰንኑም ጽኑዕ ሥቃይን ሊአሠቃያቸው ጀመረ ቅዱስ አባዲርም በሥቃይ ውስጥ ያጸናቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ለመነ ያን ጊዜ ጌታችን የእርሱን ነፍስና የእኅቱን ነፍስ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ወስዶ ሰማዕታት የሚኖሩበትን የብርሃን ቤቶችን አሳያቸውና ከዚህም በኋላ ወደ ሥጋቸው መለሳቸው። ❤ መኰንኑም ማሠቃየት በሰለቸ ጊዜ ራሳቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። ራሳቸውንም ከሚቆርጧቸው በፊት መኰንኑ አርያኖስ ቅዱስ አባዲርን እንዲህ አለው "አንተ ማን እንደሆንክ ስምህም ማን እንደሆነ አንተም ከወዴት እንደሆንክ ትነግረኝ ዘንድ በፈጣሪህ አምልሃለሁ" አለው። ቅዱስ አባዲርም "በነገርኩህ ጊዜ ራሳችንን እንዲቆርጡ ያዘዝከውን ትእዛዝ እንዳትለውጥ አንተም ማልልኝ" አለው መኰንኑም ማለለት ያን ጊዜም "የሠራዊት አለቃ እኔ አባዲር ነኝ" አለው መኰንኑ አርያኖስም እንዲህ ብሎ ጮኸ "ወዮልኝ ጌታዬ ሆይ በአንተ ፈንታ እኔ ልሞት ይገባኛል ይህን ሁሉ ጽኑ ሥቃይ እስከ አሠቃየሁህ ድረስ አንተ ጌታዬ እንደሆንክ እንዴት አላስረዳኸኝም ቅዱስ አባዲርም አንተም እንደኔ በሰማዕትነት ትሞት ዘንድ አለህና አትዘን አሁንም ምስክርነታችንን በፍጥነት ፈጽም" ብሎ መለሰለት። ❤ በዚያንም ጊዜ ራሳቸውን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አርያኖስ አዘዘና እርሱንና እኅቱ ኢራኢን ቆረጧቸው። ያማሩ ልብሶችንም ዘርግተው ገነዙአቸው ዲያቆን ሳሙኤልም የመከራው ወራት እስከሚያልፍ ወደ ቤቱ ወስዶ አኖራቸው ከዚያም በኋላ ያማረች ቤተ ክርስቲያን ታነፀችላቸውና ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከእርሳቸውም ታላላቅ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት በአባዲርና በእኅቱ ኢራኢ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 28 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለሶስና ዘተዓገሠት ምንዳቤ። አመ አዕተቱ እምገጸ ወእምላዕለ ርእሳ ግልባቤ። ሶበ ፈተዉ ምስሌሃ ረበናተ አይሁድ ሩካቤ። ወዲቅ ይኄሰኒ ወኢ ገቢር ሶቤ። ለአምላኪየ እምአብስ ትቤ"። ትርጉም፦ ከፊቷና ከራሷ ላይ መሸፈኛዋን ባራቁ ጊዜ መከራን የታገሠች ለኾነች ለሶስና ሰላምታ ይገባል፤ የአይሁድ ረበናት ከርሷ ጋር ጾታዊ ግንኙነትን በፈለጉ ጊዜ አምላኬን ከምበድል በእጃችኊ መውደቅና ኀጢአትን አለማድረግ ይሻለኛል አለች። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 28። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ዘይሁቦሙ ሲሳዮሙ ለእንስሳ። ወለእጒለ ቋዓት እለ ይጼውዕዎ። ኢይፈቅድ ኃይለ ፈረሰ"። መዝ 146፥9-10 የሚነበበው ወንጌል 12፥22-32። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "እስመ አድኀንካ ለነፍስየ እሞት። ወለአዕይንትየኒ እምአንብዕ። ወለእገርየኒ እምዳኅዕ"። መዝ 55፥13-14። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥8-22፣ 2ኛ ያዕ 4፥11-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 12፥12-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 8፥3-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መስከረም ፳፰ (28) ቀን። ❤ እንኳን ከብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ውስጥ አንዱ በስማ ለተሰየመ ለታማኟ ለኬልቅዩስ ልጅ ለቅድስት ሶስና ለዕረፍት በዓል፣ ለቅዱስ አባዲርና ለእኅቱ ቅድስት ኢራኢ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሰማዕታት ኢራኢ ከጳውፍርና ከሐና ከመነኰስ ሉቃስም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ "ሰላም ለሶስና እምእደ ረበናት እግዚአብሔር ዘአድኃና፤ ረዳኤ ዘኮና"። ትርጉም፦ ረዳትን የኾናት ከረበናት እጅ እግዚአብሔር ያዳናት ለሶስናም ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ የኬልቅዩስ ልጅ ቅድስት ሶስና፦ ዜናዋም እንዲህ ነው ይችን ቅድስት ሶስናን በባቢሎን የሚኖር ስሙ ኢዮአቄም የሚባል አንድ ሰው አገባት እርሷ እጅግ መልከ መልካም የሆነች ፈጣሪ እግዚአብሔርንም የምትፈራው ነበረች። ❤ እናትና አባቷም ደጋግ ነበሩ ለልጃቸውም ሙሴ የጻፋትን ኦሪት አስተምረዋት ነበር። ባሏ ኢዮአቄም ግን እጅግ ባለጸጋ ነበር በቤቱም አጠገብ የተክል ቦታ ነበረው ከሁሉ እርሱ ይከብር ነበርና አይሁድ ወደርሱ ይመጡ ነበር። ኃጢአት ከባቢሎን አገር ሕዝቡን እንጠብቃቸዋለን ከሚሉ ከግብዞች ወገኖች እንደ ወጣች እግዚአብሔር ስለነርሱ የተናገረባቸው ግብዞች የሆኑ ሁለት መምህራን በዚያ ወራት ታዩ። ❤ እነርሱም በኢዮአቄም ቤት የለመዱ የሚአገለግሉም ናቸው። የሚፈራረዱም ሁሉ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር። ሕዝቡ ሁሉ ወደ ቤታቸው ከገቡ በኋላ ቀትር በሆነ ጊዜ ሶስና ወደ ባሏተክል ቦታ ገብታ በዚያ ትመላለስ ነበር። ገብታ በተመላለሰች ጊዜ እነዚያ መምህራን ሁልጊዜ ያዩዋት ነበርና ተመኙዋት። ልቡናቸውንም ለወጡ ሰማይንም እንዳያዩ ዐይኖቻቸውን ግልብጥብጥ አደረጉ ሰማያዊ እግዚአብሔርን እንዳያስቡ እውነትኛ ሕግን አላሰቡም። ❤ ሁለቱም ሁሉ ወደዷት ፈቃዳቸውን መናገር አፍረዋልና እርስበርሳቸው በልቡናቸው ያለውን ነገር አልተነጋገሩም ይደርሱባትም ዘንድ ይወዱ ነበር ያገኟትም ዘንድ ሁልጊዜ ይጠብቋታል። አንዱም አንዱን "የምሳ ጊዜ ነውና ወደ ቤታችን እንግባ" አለው እየራሳቸውም ተለያይተው ሔዱ። ተመልሰውም በጎዳና አንድነት ተገናኙ ሁለቱም ተያዩ ያን ጊዜም ፍላጎታቸውን ተነጋገሩ ብቻ ለብቻ እሷን የሚያገኙበትን ጊዜ ተቃጠሩ። ❤ ከዚህም በኋላ በቀን ሲጠብቋት ሶስና ሁል ጊዜም ትገባ እንደነበር ከሁለቱ ደንገጡሮቿ ጋር ገባች አልቧታልና በተክል ውስጥ ትታጠብ ዘንድ ወደደች። ተሠውረው ከሚጠብቋት ከሁለቱ ረበናት በቀር በዚያ ማንም ማን አልነበረም። ዘይትና ሽቱ አምጥተው ያጥቧት ዘንድ ልትታጠብ የተክሉንም ደጅ ይዘጉ ዘንድ ደንገጡሮቿን አዘዘቻቸው። እነርሱም እንዳዘዘቻቸው አደረጉ የተክሉን ደጃፍ ዘግተው ያዘዘቻቸውን ያመጡ ዘንድ በስርጥ ጐዳና ወጡ የተሠወሩ እነዚያን ረበናት ግን አላዩአቸውም። ❤ እነዚያ ደንገጡሮች ከወጡ በኋላ ሁለቱ ረበናት ተነሥተው ወደርሷ ሮጡ "እነሆ የተክሉ ደጃፍ ተዘግቷል የሚያየን የለምና እንደርስብሽ ዘንድ እንወዳለንና እሺ በይን" አሏት። "ይህ ካልሆነ ካንቺ ጋር ሰውን እንዳገኘን ተናግረን እናጣላሻለን ስለዚህም ደንገጡሮችሽን ከአንቺ አሰወጥተሽ ሰደድሽ"። ሶስናም አለቀሰች "በሁሉም ፈጽሞ ተጨነቅሁ ባደርገው እሞታለሁ ባላደርገውም አልድንም ከእጃቸው ማምለጥንም አልችልም በእግዚአብሔር ፊት ከምበድል ኃጢአት ሳልሠራ በእጃችሁ መውደቅ ይሻለኛል" አለች። ❤ ሶስና ቃሏን አሰምታ ጮኸች። እነዚያም ረበናት ከእርሷ ጋር ጮኹ አንዱ ሩጦ ሒዶ የተክሉን ደጃፍ ከፈተ በቤቷም ያሉ በተክል መካከል ጩኸትን ሰምተው ወጡ ምን እንደሆነ ያዩ ዘንድ በሥርጥ ጐዳናም ሮጡ። እነዚህ ሁለቱ ረበናት ይህንን ነገር በተናገሩ ጊዜ በሶስና ላይ እንዲህ ያለ ነገር ፈጽሞ ተሰምቶ አያውቅም ነበርና ዘመዶቿና አሽከሮቿ እጅግ አፈሩ። ❤ በማግሥቱም ሕዝቡ በባሏ በኢዮአቄም ዘንድ ተሰበሰቡ እነዚያም ሁለቱ ረበናት ሶስናን ያስገድሏት ዘንድ ከዓመፀኛ ልባቸው ጋራ መጡ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ያመጡአት ዘንድ "ወደ ኢዮአቄም ሚስት ወደ ሶስና ላኩ" ብለው አዘዙ ወደርሷም ላኩባት። እርሷም ከእናት ከአባቷ ከወገኖቿ ከዘመዶቿ ከሚያውቋትም ሁሉ ጋር መጣች። ❤ ሶስና ግን እጅግ ደመ ግቡ ነበረች መልኳም ያማረ ነው። ዓመፀኞች የሆኑ እነዚያ ሁለቱ ረበናት መልኳን ለመጥገብ ይገልጧት ዘንድ አዘዙና ገለጧት። አባቷ፣ እናቷ፣ ቤተሰቦቿ፣ የሚያውቋትም ሁሉ አለቀሱላት። እነዚያም ሁለቱ መምህራን በሕዝቡ መካከል ተነሥተው እጆቻቸውን በራሷ ላይ አኖሩ። እርሷ ግን ልቡናዋ በእግዚአብሔር ታምኗልና እያለቀሰች ወደ ሰማይ ተመለከተች። ❤ እነዚያም ረበናት "ብቻችንን በተክል ውስጥ ስንመላለስ እርሷ ከሁለቱ ደንገጡሮቿ ጋር ገባች ደንገጡሮቿንም ልካቸዋለችና የተክሉን ደጃፍ ዘግተው ሔዱ ከዚያም በኋላ አንድ ጐልማሳ ከተሠወረበት መጥቶ አብሮዋት ተኛ። እኛ ግን በዚያ ተክል ዳርቻ ሁነን ኃጢአታቸውን አየን ወደነርሱም ሮጥን አንድነት ተኝተውም አገኘናቸው። እኛም እርሱን መያዝ ተሳነን እርሱ በርትቶብናልና አመለጠን የተክሉንም ደጃፍ ከፍቶ ወጣ። እርሷን ግን ይዘን ሰውዬው ማን እንደ ሆነ ጠየቅናት ግን አልነገረችንም ለዚህም ነገር ምስክሩ እኛ ነን" አሉ። ❤ የሕዝቡ መምህራንና መኳንንትም ነበሩና በአደባባይ የተሰበሰቡ ሰዎች ነገራቸውን አመኑላቸው ትሙት በቃ ብለውም ፈረዱባት። ሶስናም ቃሏን አሰምታ ጮኸች "ዘለዓለም ጸንተህ የምትኖር የተሠወረውን የምታውቅ የሚደረገውን ሁሉ ሳይደረግ የምታውቅ ፈጣሪ ሆይ በሐሰት እንዳጣሉኝ አንተ ታውቃለህ እነዚህ መምህራን ክፉ ነገርን ባደረጉብኝ ገንዘብ የሠራሁት ኃጢአት ሳይኖር እነሆ እሞታለሁ" አለች። እግዚአብሔርም ቃሏን ሰማ። ❤ ይገድሏት ዘንድ ሲወስዷት እግዚአብሔር ስሙ ዳንኤል በሚባል ልጅ ላይ ልቡናን አነሣሣ "እኔ ከዚች ሴት ደም ንጹሕ ነኝ" ብሎ ቃሉን አሰምቶ ተናገረ። ሕዝቡም ሁሉ ወደርሱ ተመልሰው "አንተ የምትናገረው ይህ ነገር ምንድን ነው" አሉ። ዳንኤልም "በመካከላቸው ቁሞ አላዋቆች የምትሆኑ እናንተ የእስራኤል ልጆች ሳትመረምሩና ነገሩን ሳትረዱ በእስራኤል ልጅ ላይ እንዲህ አድርጋችሁ እንደዚህ ያለ ፍርድን ትፈርዳላችሁን" አለ "እነዚህ መምህራን በሐሰት አጣልተዋታልና ወደ አደባባይ ተመለሱ" አላቸው። ❤ ሕዝቡም ሁሉ እየሮጡ ወደ አደባባይ ተመለሱ አለቆችም ዳንኤልን "እግዚአብሔር አንተን አልቆሃልና በመካከላችን ተቀምጠህ ተናገር" አሉት። ዳንኤልም "እየራሳቸው አራርቃችሁ አቁሙአቸው እኔም ልመርምራቸው" አላቸውና አንዱንም አንዱን አራርቀው አቆሟቸው። ዳንኤልም ከእርሳቸው አንዱን ጠርቶ "ከዚያ ሰው ጋር በምን ዕንጨት ሥር ሲነጋገሩ አየሃት" አለው "በኮክ ዕንጨት ሥር ሲነጋገሩ አየኋቸው" አለ እርሱንም አርቆ ሁለተኛውን "ሲነጋገሩ ያየህበት ዕንጨት ምንድን ነው?" አለው "ሮማን ከሚባል ዕንጨት ሥር ነው" አለ። ሕዝቡም ሁሉ ቃላቸውን አሰምተው በመጮህ ያመነችበት ሶስናን ያዳናት እግዚአብሔርን አመሰገኑት። ❤ ለእግዚአብሔርከቃላቸው የተነሣ ዳንኤል አስነቅፏቸዋልና ምስክርነታቸውንም ሐሰት አድርጎባቸዋልና በነዚያ በሁለቱ መምህራን ላይ በጠላትነት ተነሥተው ገደሏቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ሶስና ጸሎት ይማረን በረ

+1
5ኛ ዓመት አንደኛ እሁድ @EOTCW

ዓዲ/ምርጫ መዝሙር ፻፴፩÷፮ ወረከብናሁ ውስተ ዖመ ገዳም ንበውዕ እንከሰ ውስተ አብያቲሁ ለእግዚአብሔር ወንሰግድ ውስተ መካን ኅበ ቆመ እግረ እግዚእነ #ትርጉም፦ በዱር ውስጥም አገኘነው። ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን፤ እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content