es
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Ir al canal en Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Mostrar más
1 161
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
photo content
+3

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፲፮ (16) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያኑ ጻድቃን ለአርባ ስምንት ዓመታት ከሰው ጋር ሳይነጋገሩ በዝምታ ብቻቸው ለኖሩ ነብር ሰባት ዓመት ውሃ ሲቀዳላቸው ሲያገለግላቸው ለነበሩ ለታላቁ አባት ለአቡነ አሮን ዘአርምሞ ለዕረፍት በዓልና በሰሜን ሸዋ መራቤቴ እንሳሮ በቆላማው ክፍል የሚገኘው፤ የስውራን ግኁሳን ባሕታውያን መኖርያ የሆነውን፤ ዓመቱን ሙሉ ከበሮ የማይመታበት ታላቁ ገዳም ጀር ቅድስት ሥላሴን ለመሰረቱት ለኮከበ ገዳም ለታላቁ አባት ለአቡነ ኢያሱ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላምና በጤና እግዚአብሔር አምላክ አደረሰን። + + + ❤ አቡነ አሮን ዘአርምም፦ መጽሐፍ አሮን ዘከትሞ ወዘአርምሞ ይላችዋል። የትውልድ ሀገራቸው ትግራይ ተንቤን ነው። ለ48 ዓመታት ከሰው ጋር ምንም ሳይነጋገሩ በዝምታ ብቻ የኖሩ ታላቅ አባት ሲሆኑ ቀዳማዊ ዘኢትዮጵያ ከተባሉት የመጀመርያዎቹ ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው። ቤተ መቅደስ ገብተው ሲያጥኑ ርግብ ዕጣን ታመጣላቸው ነበር። ምግባር ቱሩፋታቸው እጅግ ያማረው እኚህ አባት በዘመናቸው ድርቅ በሆነ ጊዜ የእህል እጦት ሆኖ ሕዝቡን ሰብስበው እግዚኦታ ካደረሱ በኋላ የሀገሩን ሁሉ ጎተራ በተአምራት በእህል ሞልተው አትረፍርፈውታል። በዚህም አስገራሚ ተአምራቸው ሕዝቡንም ከችግርና ከርሃብ አድነውታል። ❤ አቡነ መድኃኒነ እግዚአ ዘደብረ በንኰል አህያቸውን የበላባቸውን አንበሳ በአህያው ምትክ ሰባት ዓመት ውኃ እንዳስቀዱት ሁሉ አቡነ አሮንም ነብርን ሰባት ዓመት ውኃ እያስቀዱ እንዲያገለግላቸው አድርገውታል። ሌሎች የዱር አራዊትም ያገለግሏቸው ነበር። በአንድ ወቅት በሀገሩ ድርቅ ሆኖ ሰው ግማሹ ተሰዶ ግማሹ ደክሞ ስለነበር ጻድቁ ግን የዱር አራዊትን ጠርተው ሠራተኛ አድርገው በማዘዝ ጥንቸልን ውኃ በማስቀዳት፣ ጅብን ጭቃ በማስረገጥ፣ አንበሳን በአናጺነት እንዲሠራ፣ ነብርን ደግሞ አቀባይ በማድረግ እያዘዙ በማሠራት በእመቤታችን ስም እጅግ አስደናቂ ቤተ ክርስቲያን መስከረም 10 ቀን ሠርተዋል። የአቡነ አሮን ዘአርምሞ የአንድነት ገዳማቸው ትግራይ ሽሬ ውስጥ ይገኛል። ምንጭ፦ መዝነበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍና ቅዱሳን በዓላት። + + + ❤ አቡነ ኢያሱ፦ አስደናቂው ገዳማቸው ዛሬም በስውራን ግኁሳን ባሕታውያን የተመላ ቃል ኪዳን ያልተሻረበት ግዝት ያልተነሳበት የቅዱሳን በዓት የሆነው በሰሜን ሸዋ መራቤቴ እንሳሮ በቆላማው ክፍል የሚገኘው በመሰላል የሚወረደው ደብረ ቅዱሳን መካነ ሱባኤ ወተመስጦ ጀር ቅድስት ሥላሴ ገዳም።ገዳሙ በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት የተመሠረተ ታላቅ የምናኔ ቦታ ነው። ❤ ለሐገር ሰላም ለሕዝበ ክርስቲያን ደሕንነት የሚጸልዮ ባሕታውያን የመሉበት ነው ዛሬም የጠመመ የሚያቀኑ ያዘነ የሚያጽናኑ ስውራን እግዚአብሔር ለፈቀደለት የሚገለጡለት ቅዱስ መካን። ❤ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ብዙ ገጸ በረከት የሰጡበት ፈጻሜ መንግሥት አፄ ኃይለ ሥላሴ በክቡር አባቴ ሐና ጅማ መሪነት ገዳሙ ድረስ በመሰላል ወርደው ቡራኬ የተቀበሉት በየዓመቱ የአትርሱኝ መባ የሚልኩበት በአዲስ አበባ ለገዳሙ በኪራይ የሚተዳደርበት ሱቆች አሰርተው ጃንሆይ የሰጡበት ልዕልናው ከሸዋ ገዳማት የላቀ ታላቅ ገዳም ነው። ❤ ይህ ገዳም ዛሬ አስታዋሽ አጥቶ ቀርቷል የእግዚአብሔር ስራ ግን አልቆመበትም ብዙዎች ቦታውን በመርገጥ ከስጋ ደዌ ድነውበታል። ውድ አያቴ ልጅ በክብካብ ገብረ ማርያም ሲነግረኝ የቅርብ ቤተሰባችን የሆኑት የመራቤቴ ገዥ ክቡር ደጃዝማች ታዬ ጉልላቴ ለሞት በሚያደርስ ክፉ ሕመም ተይዘው ከለሚ በቃሬዛ ይዘናቸው ጀር ሥላሴ ገና ከግዝቱ መሬት ስንረግጥ ከአልጋው አፈፍ ብለው ተነስተዋል ነጭ የለበሰ መነኮስ "በስመ ሥላሴ ተነስ።" ሲለኝ ነቃሁ ብለው መስከረዋል። ❤ በዘመናችን ለሳይንስ ግራ ያጋባ ተስፋ የተቆረጠበት ሕመም የታመመ ከውጭ ሐገር ሄጄ ልሙት ያለ ወንድም ሰውና ሳይንስ ሲጨርስ እግዚአብሔር ስራ ይጀምራልና ከሕመሙ ድኖ ዛሬም በሕይወት አለ። ጻድቁ ሙት ያስነሱት መስቀላቸው በእቃ ቤቱ ይገኛል። እግዚአብሔር ለፈቀደለት ብዙ የሕይወት መንገድ በሱባኤ የሚያገኝበት ስውራን ግኁሳን ተገልጠው የሚባርኩበት ነው። "መካነ ሱባኤ ወተመስጦ ጀር ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ኢያሱ ገዳም"። ❤ አቡነ ኢያሱ በደብረ ሊባኖስ ገዳም የመነኰሱ ገዳማዊ ናቸው ትውልዳቸው አማራ ሳይንት ነው። ጀር ሥላሴን በቅዱስ ሚካኤል መሪነት ያቀኑ ባሕታዊ ናቸው። 365 ቀን ዓመቱን ሙሉ ማሕሌት የማይቆምበት ከበሮ የማይመታበት ዓመታዊ በዓላቸው እንኳን በጽሞና በአርምሞ በቅዳሴ እና በሰዓታት የሚከብርበት እንደ ዓለመ መላእክት ኢዮር ራማ ኤረር መላእክት የሚገናኙበት ግኁሳን ባሕታውያን እንደ መብራት በርተው የሚታዮበት 24 ሰአት በምስጋና የሚታወድበት የስውራኑ ማእጠንት የሚሸትበት ቅዱስ መካን ነው።ዜና ገድላቸውን እግዚአብሔር ከተራፊ ከራሚዎቹ ይደምረንና ከእጃችሁ ይገባል የገድላቸው ገበታ ሳይገባን ያሰማን እግዚአ አለማት ሥላሴ ክብር ይግባው። የጻድቁ በረከት ይደርብን በጸሎታቸው ኢትዮጵያን ይጠብቋት ከዘረኝነት ደዌ ከፍቅር ረሐብ ከዝሙት እሳት ከምንፍቅና አሽክላ ምልጃ ጸሎታቸው ይሰውረን!። ምንጭ፦ ነገረ ቅዱሳን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

1.55 KB

15/2/2015 ዓ.ም (፲፭/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 እነግሮሙ ስመከ ለአኀውየ። ወበማዕከለ ማኅበር እሴብሐከ። እለትፈርኅዎ ለእግዚአብሔር ሰብሕዎ፡፡ መዝ. 21፥22 🕯 ትርጉም ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ። በጉባኤም መካከል አመሰግንሃለሁ። እግዚአብሔርን የምትፈሩ አመስግኑት። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

photo content
+1

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለ፲ወ፪ቱ ሐዋርያተ መድኅን። እለ ስሞሙ ጴጥሮስ፣ ወእንድርያስ፣ ያዕቆብ፣ ወዮሐንስ፣ ፊልጶስ ወበርተሎሜዎስ፣ ቶማስ፣ ወማቴዎስ፣ ታዴዎስ ወናትናኤል ወያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ ወማትያን"። ትርጉም፦ ስማቸው ጴጥሮስና እንድርያስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ፣ ፊልጶስና በርተሎሜዎስ፣ ቶማስና ማቴዎስ፣ ታዴዎስና ናትናኤልና የእልፍዮስ ልጅ ለያዕቆብና ማትያን በመባል ለሚጠሩ ለ፲፪ቱ የመድኅን ሐዋርያት ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content
+1

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፲፭ (15) ቀን። ❤ እንኳን ለዐሥራ ሁለቱ ቅዱሳን ሐዋርያት ዓለም በእጣ ለተካፈሉበት ለመታሰቢያ ቀን፣ ለቅዱስ ጳውሎስ ረድ ለቅዱስ ሲላስና ለኒቆድምያ አገር ለሆነ ለሰማዕቱ ለቅዱስ ቢላሞን ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቢላሞን ማኅበር ከሆኑ ከመቶ ሃምሣ ስምንት ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው፣ ከሰላትዮን፣ ከአጥራኪስ ከአርሞቅስ፣ ከአድማንያ፣ ከአርሚስ፣ ከቅድስት ጾመታ፣ ከአባት ኢሳይያስና ከሐዋርያትም ከዕፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ከኒቆምድያ አገር የሆኑ ቅዱስ ቢላሞን፦ የዚህም ቅዱስ አባቱ ጣዖት አምላኪ ነው እናቱ ግን ክርስቲያን ናት ጥበብንም አስተማሩት ከዚህም በኋላ ስሙ አርማላስ ከሚባል ቄስ ጋር ተገናኘ። እርሱም ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የቀናች ሃይማኖት አስተማረው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቀው ታላቅ የሆኑ ድንቆች ታምራትን የማድረግ ሀብትን እግዚአብሔር እስከ ሰጠው ድረስ በጾም በጸሎት ታላቅ ገድልን ተጋደለ። ❤ በአንዲት ቀንም ለዓይኖቹ መድኃኒትን እንዲአደርግለት አንድ ዕውር ሰው ወደርሱ መጣ ቅዱስ ቢላሞንም "በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም" እያለ በዕውሩ ዐይኖች ላይ የመስቀልን ምልክት አደረገ ያን ጊዜ ዐይኖቹ ድነው አየባቸው ጤነኛም ሆነ። ንጉሥም ዐይኖቹ የተገለጡለትን የዚያን ዕውር ዜና በሰማ ጊዜ ወደርሱ አስቀረበውና "ዐይኖችህን ማን አዳነህ?" ብሎ ጠየቀው እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት "ቅዱስ ቢላሞን ፈወሰኝ እርሱ እጁን በዐይኖቼ ላይ አድርጎ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እያለ በመስቀል ምልክት አማተበብኝ ያን ጊዜ አየሁ" ይህንንም ብሎ"እኔ ክርስቲያን ነኝ" እያለ በንጉሡ ፊት በግልጽ ጮኸ። ንጉሡም ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡት የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ❤ ከዚህም በኋላ ወታደር ልኮ ቅዱስ ቢላሞንን አስቀረበው ስለ ሃይማኖቱም በጠየቀው ጊዜ እርሱም "ክርስቲያን ነኝ" ብሎ በፊቱ ታመነ ንጉሡም ብዙ ሽንገላን በመሸንገል አባበለው። ብዙ ቃል ኪዳንም ገባለት ባልሰማውም ጊዜ በእርሱ ላይ ተቆጥቶ ድምፁን ከፍ አድርጎ "ካልሰማኸኝ እኔ ጽኑ ሥቃይን አሠቃይሃለሁ" አለው። ቅዱስ ቢላሞንም "እኔ ከሥቃይህ የተነሣ ፈርቼ ሃይማኖቴን ለውጬ ፈጣሪዬን አልክድም" አለው። ❤ ከዚያችም ቀን ጀምሮ በብዙ አይነት ሥቃይ በብዙ ቀኖች ውስጥ ማሠቃየትን ጀመረ። በግርፋት በስቃላትም በባሕር ስጥመትም ወደ እሳት በመወርወርም የሚያሠቃይበት ጊዜ አለ። በዚህም ሥቃይ ውስጥ ሳለ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአጠመቀው ቄስ በአርሜላዎስ አምሳል ተገልጾለት እንዲህ የሚል የደስታ ቃል አሰማው። "የመረጥኩህ ቢላሞን ሆይ ደስ ይበልህ እኔ ሰማያዊ መንግሥትን አዘጋጅቼልሃለሁና"። ❤ የንጉሡ ጭፍሮችም ይህን የደስታ ቃል ሰሙ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አምነው እነርሱ በሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የአመኑ መሆናቸውን በንጉሡ ፊት ገለጡ በዚያንም ጊዜ ራሳቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ ንጉሡ አዘዘ። ቅዱስ ቢላሞንንም እንዲቆርጡት አዘዘ ከእሊህ ጭፍሮች ጋርም እንዲህ ገድሉን ፈጸመ ቁጥራቸውም መቶ ኀምሣ ስምንት ነው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ቢላሞን ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት 15 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም እብል ለርክበተ ዐፅምክሙ ወርቅ። አዝቂር ወኪርያቅ። ወሰላም ለሲላስ ረድአ ማዕነቅ። ዘጸለለ በጌጋይ እምነጽሮታ ለጽድቅ። ዐይነ ሐሊናየ ፈውሱ በምራቅ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት15። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እነግሮሙ ስመከ ለአኀውየ። ወበማዕከለ ማኅበር እሴብሐከ። እለ ትፈርህዎ ለእግዚአብሔር ሰብሕዎ"። መዝ 21፥22-23። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 8፥31-35፣ ይሁ 1፥17-22 እና የሐዋ ሥራ 15፥22-30። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 18፥12-21። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው። መልካም በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችን ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለገብረ ክርስቶስ ብእሴ እግዚአብሔር ለነፍሱ ዘኮነ ኬንያ ዘአብዕዎ መላእክት ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ እንዘ ይብሉ ሃሌ ሉያ"። ሃሌ ሉያ እያሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት መላእክት ያስገቡት ለነፍሱም ጠቢብ የእግዚአብሔር ሰው ለኾነ ለገብረ ክርስቶስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለአባ አረጋዊ ምንኵስናሁ ዘፈጸመ፤ በፍኖተ ጽድቅ ዘቆመ"። ትርጉም፦ በእውነት ጐዳና የቆሞ ኾኖ ምንኩስናውን ፍጹም ላደረገ ለአባ አረጋዊ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፲፬ (14) ቀን። ❤ እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ለሆነው፤ ሐዋርያት ኮሾሟቸው ከሰባቱ ዲያቆናት ውስጥ የተቆጠረ ለሆነ፤ ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ ባኮስን (አቤላክን) ላጠመቀው ለቅዱስ ፊሊጶስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ "ይቤሎ መንፈስ ቅዱስ ለፊልጶስ ሑር ወትልዎ ለዝንቱ ሠረገላ ዘአፍራስ። ፊልጶስ መሀሮ ለባኮስ በእንተ ክርስቶስ ወአጥመቆ በማየ ጥምቀት ሐዲስ"። ትርጉም፦ አለው መንፈስ ቅዱስ ፊልጶስን ሂድና ተከተለው ይህን የአፍራስ ሠረገ፡፡ ፊልጶስ አስተማረው ለባኮስ ስለ ክርስቶስ አጠመቀው በማየ ጥምቀት ሐዲስ፡፡ የቅዱስ ፊሊጶስ መዝሙር። + + + ❤ ቅዱስ ፊሊጶስ፦ ጌታችንም በቂሣርያ አገር ውስጥ በአለፈ ጊዜ በውስጧ አስተምረ ትምህርቱም ሰምቶ ክብር ይግባውና ጌታችንን አምኖ ተከተለው ከሰባ ሁለቱ አርድዕትም ጋር ተቆጠረ። ❤ ጌታችንም ይሰብኩ ዘንድ ሁለት ሁለት አድርጐ በላካቸው ጊዜ ከእርሳቸው አንዱ ይህ ደቀ መዝሙር ነው። ከመድኃኒታችንም ዕርገት በኋላ ሐዋርያት ኮሾሟቸው ከሰባቱ ዲያቆናት ውስጥ የተቆጠረ ነው። እርሱም ወደ ሰማርርያ ወርዶ አስተማረ ብዙዎችንም አሳምኖ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው። ❤ ከዚህም በኋላ የተጎዳውን ሥራየኛ ሲሞንንም አጥምቆት ነበር እርሱ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በገንዘብ ሊገዛ አስቧልና። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ጋዛ በሚወስደው መንገድ ይሔድ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ፊሊጶስን አዘዘው በሔደም ጊዜ ለኢትዮጵያ ንግሥት ለህንደኬ በጅሮንዷ የሆነ ጃንደረባውን አገኘው እርሱም እንደ በግ ሊታረድ መጣ የሚለውን የነቢይ ኢሳይያስ መጽሐፍ ያነብ ነበር። ፊልጶስም ጃንደረባውን "የምታነበውን ታስተውለዋለህን?" አለው። ጃንደረባውም "ያስተማረኝ ሳይኖር እንዴት አውቃለሁ" አለ። ፊሊጶስም ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አመነ ያን ጊዜም በፊሊጶስ እጅ ከወንዝ ውኃ ውስጥ ተጠመቀ ከውኃውም በወጡ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ፊሊጶስን ነጥቆ ወሰደው ጃንደረባውም ሁለተኛ አላየውም። ❤ ፊሊጶስ ወደ አዛጦን ከተማ ደረሰ እያስተማረም እስከ ቂሣርያ ሔደ በከተማዎች ሁሉ በመዞር ወንጌልን ሰበከ ከአይሁድና ከሳምራውያንም ብዙዎችን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን መልሶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው። ❤ ለሐዋርያው ፊሊጶስም ከእርሱ ጋር ወንጌልን የሚሰብኩ አራት ሴቶች ልጆች ነበሩት። አገልግሎቱንም ፈጽሞ ጥቅምት 14 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ቅዱስ ፊሊጶስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት 14 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለከ ፊሊጶስ ሐዋርያ። እምሰብአ ፍልስጥኤም ወቂሣርያ። ምስለ አዋልዲከ አርባዕ እለ ይትኔበያ። አርውየኒ እምትምህርትከ በከመ ትካት ረወያ። ሀገረ ሳምር ወዓዲ እስያ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት 14። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ይባርኩ ጻድቃኒከ። ስብሓት ይብሉ ለመንግሥትከ። ወይነግሩ ኃይለከ"። መዝ 140፥10። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 14፥8-15። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አፅናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ 18፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 7፥36-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 2፥18-21 እና የሐዋ ሥራ 8፥26-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 19፥26-30። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ፊሊጶስ የዕረፍት በዓል፣ የአቡነ አረጋዊ የስዋሬ በዓል፣ የቅዱስ ገብረ ክርስቶስ፣ የቅዱስ ሙሴ ብእሴ እግዚአብሔር የዕረፍት በዓላቸውና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content