ሰዋስው ☘☘☘☘
Ir al canal en Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
Mostrar más1 161
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
1 161
ቅዱስ መጽሐፍ ይህች አለም በጊዜዋ አክብራ በጊዜዋ ያዋረደቻቸውን ሰዎች አስቀምጦልን እናገኛለን
★ እዚህ ላይ በዓለም መሳብ ማለት የእግዚአብሔርን ህግ ትቶ ራስን ለዓለማዊ ነገር ሰውቶ ወይም ራስን አሳልፎ መስጠት እንደሆነ ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡
ይህ ማለት ግን በዓለም ውስጥ መኖር ኃጢያት ነው ማለት ሳይሆን ተዘክሮ እለተ ሞትን ማለትም የሞትን ቀን እያሰቡ ለሥጋ ሳይሆን ለነፍስ ለሐሰት ሳይሆን ለጽድቅ እያደሉ መኖር ነው፡፡
ይህች በመዘንጋት ገመድ የምትስበንን ዓለም የቀድሞው ዘመን ባለሥልጣን እና ባለቅኔ ራስ ወልደ ገብርኤል በሥላሴ ቅኔያቸው የዓለምን ከንቱነት ገልጸዋል ይህንን ቅኔያቸውን ልብ ብሎ ላየው በግልጽ የዓለምን ሀላፊነት እና ከንቱነት ያሳያል ሊቁ ሲያመሰጥሩ እንዲህ አሉ :-
ሥላሴ ዘራስ ወልደ ገብርኤል
ዓለም እስከጊዜሃ በሀብለ ዝንጋኤ ትስህበነ
ወታወርደነ ካዕበ ኀበዘቀዳሚ መርገም
ለዘተወለድነ በሥጋ ወደም
ዘአዕመራሰ ማእምር ለባዊ ለህልፈተ ዛቲ ዓለም
ፍዳወይን ይስተይ ማየዝናም
ወህየንተልብስ ይትከደን ቆጽለ አዕዋም
እስመዛቲ ጽላሎት ወህልም
ትርጉም :-
ዓለም እስከጊዜዋ በመዘንጋት ገመድ ትስበናለች ዳግመኛም በሥጋና ደም የተወለድን እኛ ሰዎችን ወደ ቀደመ መርገም ታወርደናለች ፡፡ የዚህችን ዓለም ማለፍ ያወቀ አዋቂ ልበኛ ግን ስለወይን ፈንታ የዝናም ውሃ ይጠጣ በልብስ ፈንታ የጫካ ቅጠልን ይልበስ ይህች ዓለም እንደ ጥላ ኃላፊ እንደ የቅዠት ህልምም ናትና፡፡
በነገራችን ላይ እኚህ ሊቅ በቤተክህነቱም ሆነ በቤተመንግስቱ ምንም ያልጎደለባቸው ታፍረው እና ተከብረው የሚኖሩ በዓለሙ አጠራራ የደላቸው ናቸው ፡፡ ነገር ግን ቅኔያቸው የዓለምን ኃላፊነት እና ከንቱነት እረ እንዲያውም ከወይን የዝናም ውሃን አስበልጦ ይናገራል ፡፡ እኚህ ሊቅ የዓለምን ጣፋጭነት ቢናገሩ አያስገርምም ነበር ነገር ግን ካልጎደለበት የማይጠበቅ ነገር ግን እውነታውን በቅኔያቸው ይናገራሉ ይህም እኚህ ሊቅ ከቅዱሳት መጻሕፍት የዓለምን ከንቱነት እንደተረዱ ያጠይቃል ፡፡
ዓለም በመዘናጋት ገመዷ በፍላጎት ወጥመዷ ስባ ከጣለቻቸው መካከል አባታችን አዳም ከውድ ባለቤቱ ከሔዋን ጋር አንዱ ነው፡፡ ይህንን ታላቁ ሊቅ ክፍለዮሐንስ
አዳምሰ ወሄዋን በገነተ ትፍስሕት ወተድላ
እንዘፍሬበለስ የሀስሱ ቀሰሙ አሜከላ....ብሎ በቅኔው ተራቆበታል፡፡
በዚህችን ዓለም ላይ እኛ የአዳም ልጆች ስንኖር ብዙ ፈተናዎች እና ተግዳሮት በጠላታችን በዲያብሎስ አማካኝነት ይመጡብናል እነዚህን የጠላታችን ፈተናዎች እና ተግዳሮቶች ድል መንሻ ኃይላችን ማርከሻ መድኃኒታችን ዐቂበ ህጉ ከ ተዘኪሮተ ዕለተ ሞትነ ጋር ነው ፡፡
የኔታ ከብዙኅ የሕይወት ልምዳቸው እና እንደ ባሕር ከጠለቀ ሊቅነታቸው እንዲሁም ከአባታዊ ፍቅራቸው የተነሳ አባታዊ ምክራቸውን ሲያካፍሉኝ እንዲህ አሉኝ ...ልጄ ብልጥ ሁን አንድን ነገር ሞክረክ ሳይሆን አስቀድሞ ከሞከረ ሰው ተማር......ይሉኛል ፡፡ ይህ ምክር የዘለዓለም የሚሆን ስንቅ ነው፡፡
ይህን ምክር ወደ እዚህች ዓለም ስናመጣው በመዘንጋት ገመዷ ጠልፋ የጣለቻቸው ከዓለም ጋር ውል የፈፀሙ እነ ናቡከደነፆር እንደ አውሬ ሳር ሲግጡ እነ ፈርዖን የውሃ እራት ሲሆኑ ከቅዱሳን መጻሕፍት እየሰማን ከእሷ ጋር ሕብረትን ከፈጠርን ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ ያለበዚያ.......
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፮ (6) ቀን።
❤ እንኳን ከዐበይት ነቢያት አንዱ ለሆነው ለታላቁ ነቢይ ለአሞጽ ልጅ ለቅዱስ ኢሳይያስ ለዕረፍት በዓልና በከሀዲ ንጉሥ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበለች ቅድስት ሰብልትንያ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን ። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከመነኰስ ያዕቆብ፣ ከኤጲስቆጶስ ከአናቲሞስ፣ ከባስሊስና ከአሮጦስ፣ ከውርዋና፣ ከሳውልስ፣ ከሰማዕቱ ከሰውላስም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ "ሰላም ለኢሳይያስ ነቢይ ወልደ አሞጽ ዘፈጸመ ገድሎ በሞሠርተ ዕፅ ደራሲ ትንቢተ እምነቢያት ልዑላተ"። ትርጉም፦ በዕንጨት መጋዝ ተተርትሮ ገድሉን የፈጸመ ለኾነ፤ ከታላላቆች (ከዐበይት) ነቢያት ይልቅ ትንቢትን ለጻፈ ለነቢዩ ለኢሳይያስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ የአሞጽ ልጅ ታላቁ ነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ፦ ይህም ነቢይ ለይሁዳ በነገሡ በአምስቱ ነገሥታት ዘመን አስተማረ ትንቢትም ተናገረ እሊህም አዝያን ኢዮአታም አካዝ ሕዝቅያስና ምናሴ ናቸው።
❤ በአካዝ ዘመንም እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ። "እነሆ ስለዚህ እግዚአብሔር ምልክትን ይሰጣችኋል። እነሆ ድንግል ፀንሳ ወንድ ልጅን ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች። ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ አንድ ሆነ ማለት ነው"። እርሱም በኃጢአታቸው ከሚመጣባቸው ፍዳ ወገኖቹን የሚያድናቸው ወደ ሃይማኖቱም የሚአስገባቸው እንደሆነ የእስራኤልንም ልጆች መሥዋዕታቸውንና ክህነታቸውን እንደሚሽር ከሐዲስ ወገኖችም የሚያመሰግኑት ካህናትን እንደሚሾም ተናገረ።
❤ የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬምም ኢየሩሳሌምን ከቦ የስድብ ቃልን በክብር ባለቤት በእግዚአብሔር ላይ በተናገረ ጊዜ የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬምን ያጠፋው ዘንድ እግዚአብሔር እንዳለው ለሕዝቅያስ ትንቢትን ተናገረ።
በዚያች ሌሊትም እግዚአብሔር የላከው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደ ሠናክሬም ሰፈር መጥቶ ከፋርስ ሠራዊት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ አርበኞችን ገደለ። የለኪሶ ሰዎች ሲነጋ በተነሡ ጊዜ የሞቱትን ሰዎች ሬሳ ሁሉ አዩ ።
❤ ሕዝቅያስም ታሞ ለሞት በተቃረበ ጊዜ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደርሱ መጥቶ "እግዚአብሔር ትሞታለህ እንጂ አትድንም ብሏልና ቤትህን አዘጋጅ" አለው። ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳው መልሶ ወደ እግዚአብሔር ለመነ ፈጽሞ ጽኑ ልቅሶንም አለቀሰ።
ይህን ከነገረው በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ነቢዩ ወደ ኢሳይያስ መጣ "ሒደህ ለሕዝቅያስ "የአባትህ የዳዊት ፈጣሪ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰማሁ ዕንባህንም አየሁ። እነሆ በዘመንህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት ጨመርኩልህ" አለ በለው"።
❤ ዳግመኛም ስለ እስራኤል መማረክና ከምርኮ ስለ መመለሳቸው ትንቢት ተናገረ የፈሳሽ ውኃን ምንጭ በማፍሰስ በእጆቹ ላይ እግዚአብሔር ምልክትን ገለጠ።
ክብር ይግባውና ስለ መድኃኒታችን ክርስቶስ መከራ ትንቢት ተናገረ እንዲህም አለ። "እርሱም በመከራው ጊዜ ነገርን አልተናገረም እንደ በግ ይታረድ ዘንድ መጣ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንደ ማይናገር እንዲሁ በመከራው ጊዜ አልተናገረም"።
❤ ከዚህም በኋላ ደግሞ በሕዝቅያስ ልጅ በንጉሥ ምናሴ ላይ ትንቢት ተናገር ጣዖትን ስለማቆሙና ስለማምለኩ ገሠጸው። ስለዚህም ንጉሥ ምናሴ ተቆጥቶ በዕንጨት መሰንጠቂያ መጋዝ በራሱና በእግሮቹ መካከል ሠነጠቀው ምስክርነቱንም በዚህ መስከረም 6 ቀን ፈጸመ ።
❤ ትንቢት እየተናገረ የኖረበትም ዘመን ሰብዓ ዓመት ከዚያም በላይ ይሆናል ። እርሱም ያስተማረው ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት በዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሦስት ዓመት ነው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ሰማዕቷ ቅድስት ሰብልትንያ፦ ይችንም ቅድስት ዕድሜዋ ዘጠኝ ዓመት ሲሆን ከሀድያን ያዙዋት እጆቿንና እግሮቿንም አሥረው ከሚነድ እሳት ውስጥ ጣሏት የክብር ንጉሥ በሆነ በእግዚአብሔርም ኃይል ከእሳት ዳነች።
❤ ውኃን በተጠማች ጊዜ እግዚአብሔርን ለምናው ውኃን አፈለቀላትና ጠጣች ክብር ምስጉን የሆነ ጌታችንንም አመሰገነችው። ከዚህም በኋላ ነፍሷን በእግዚአብሔር እጅ አደራ ሰጥታ ራሷን ከእሳት ውስጥ ወረወረች ምስክርነቷንም ፈጸመች። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ሰብልትንያ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 6 ስንክሳር።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ቃለ እግዚአብሔር ያድለቀልቆ ለገዳም። ወያድለቀልቆ እግዚአብሔር ለሐቅለ ቃዴስ። ቃለ እግዚአብሔር ያጸንዖሙ ለኃየላት። መዝ 28፥8-9። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 3፥1-7።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወገሠጸ ነገሥተ በእንቲአሆሙ። ወኢትግሥሡ መሲሐንየ። ወኢታሕስሙ ዲበ ነቢያትየ"። መዝ104፥14-15። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 9፥25_ፍ.ም፣ 2ኛ 1፥19-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 28፥25-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 12፥36-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም የነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፮ (6) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ለታላቁ አባት ለአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ዐፅማቸው ከዋልድባ አብረንታንት ወደ ደብረ ዓባይ ለፈለሰበት ቀን መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ የአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ የሥጋ ፍልሰት፦ ከዋልድባ አብረንታንት ወደ ደብረ ዓባይ፤ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ትውልዳቸው ከካህናቱ ወገን አክሱም ነው አባታቸው እስጢፋኖስ እናታቸው አመተ ማርያም ይባላሉ። ለመምህር ሰጥተዋቸው ሲማሩ አድገው በኋላም ወላጆቻቸው በሞት ሲለዩአቸው ደብረ በንኰል ገዳም ገብተው ሥርዓተ ምንኩስናን ከአበው እያጠኑ ለትልቁም ለትንሹም በትሕትና እየታዘዙ ውሃ እየቀዱ እንጨት እየሰበሩ በትኅርምት በጽሞና በጸሎት ይኖሩ ነበር።
❤ ሰይጣን በውዳሴ ከንቱ ጾር ቢመጣባቸው ከማሕበረ መነኰሳቱ ተለይተው በተባሕትዎ ለመኖር ሽተው ወጥተው ሲሔዱ ተከዜ ደረሱ። ወንዙ ሞልቶ የማያሻግራቸው ቢሆን ውሃውን በትምህርተ መስቀል ባርከው በአንድ እጃቸው መጽሐፍ በአንድ እጃቸው መብራት እንደያዙ ገብተው መብራቱ ሳይጠፋ መጽሐፉ ሳይበላሽ ተሻግረዋል። ዋልድባ ሲደርሱ ጌታ እዚህ ተቀመጥ ስላላቸው ገዳም መሥርተው ሥርዓተ ምንኩስናን እያስተማሩ ተቀመጡ። ዛሬ በዋልድባ የሚያመሰግኑበት ውዳሴ ማርያም ቅዳሴ ማርያምን ከተከዜ ወዲህ ያመጡ እሳቸው ናቸው። ይህንን እየጸለዩ ሲሔዱ ክንድ ከስንዝር መሬት ለቀው ይታዩ ነበር።
❤ አንድ ቀንም ይህንን ጸሎት ደግመው ውኃውን ቢባርኩት ኅብስተ ሕይወት ሆነላቸው ከነደቀ መዛሙርቶቻቸው ተመግበውታል። እመቤታችንም የፍቅር መግለጫ ዕጣን፣ ወርቅ፣ እንቁ ሰጥታቸዋለች። "ውዳሴዬን ከቅዳሴዬ አንድ አድርጎ የደገመውን አንተ ከገባህበት መካነ ሕይወት አስገባዋለሁ" ብላ ቃልኪዳን ሰጥታቸዋለች። ጊዜ ዕረፍታቸው ሲደርስ ጌታን በስብሐተ መላእክት ተገልጦ "በስምህ የተማጸነውን በጎ የሰራውን፣ ዜና ገድልህን የጻፈውን፣ ያስጻፈውን፣ ያነበበ፣ የተማረ፣ ያስተማረ፣ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ ምሬልሃለሁ። በዚህ ቦታ በዋልድባ የሚሰበሰቡ ልጆችህን ከእዳ ከፍዳ እሰውርልሃለሁ" አላቸው። እንኪያስ ቦታዋን ባርክልኝ ብለው እንደ መሶብ አንስተው አስባርከዋታል ጌታችንም "እህል አይብቀልብሽ ኃጢአት አይሻገርብሽ" ብሎ ቃል ኪዳን ገባላት ለገዳመ ዋሊ። አባታችን አቡነ ሳሙኤል በበዓታቸው ውስጥ ጸንተው ሲኖሩ ታህሣሥ 12 ቀን ያረፉ ሲሆን ዛሬ መስከረም 6 ግን ፍልሰተ አጽማቸው የተከናወነበት ዕለት ነው። ከአባታቸው ከአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ማቴ. 13:31-44 "ከልእተ ምሳሌ አምጽአ ሎሙ" - "ሌላ፡ምሳሌ፡አቀረበላቸው፡እንዲህም፡አለ፦መንግሥተ፡ሰማያት፡ሰው፡ወስዶ፡በዕርሻው፡የዘራትን፡የሰናፍጭ፡ቅንጣት፡ትመስላለች፤
እርሷም፡ከዘር፡ሁሉ፡ታንሳለች፥ባደገች፡ጊዜ፡ግን፥ከአታክልቶች፡ትበልጣለች፡የሰማይም፡ወፎች፡
መጥተው፡በቅርንጫፎቿ፡እስኪሰፍሩ፡ድረስ፡ዛፍ፡ትኾናለች። ሌላ፡ምሳሌ፡ነገራቸው፡እንዲህም፡አለ፦መንግሥተ፡ሰማያት፡ሁሉ፡እስኪቦካ፡ድረስ፡ሴት፡ወስዳ፡በሦስት፡መስፈሪያ፡ዱቄት፡የሸሸገችውን፡እርሾ፡ትመስላለች። ኢየሱስም፡ለሕዝቡ፡ይህን፡ዅሉ፡በምሳሌ፡ተናገረ፤በነቢዩም፦በምሳሌ፡አፌን፡እከፍታለሁ፥ዓለም፡ከተፈጠረ፡ጀምሮ፡የተሰወረውንም፡እናገራለሁ፡የተባለው፡ይፈጸም፡ዘንድ፡ያለምሳሌ፡አልተናገራቸውም። በዚያን፡ጊዜ፡ሕዝቡን፡ትቶ፡ወደ፡ቤት፡ገባ።ደቀ፡መዛሙርቱም፡ወደ፡እርሱ፡ቀርበው፦የዕርሻውን፡እንክርዳድ፡ምሳሌ፡ተርጕምልን፡አሉት። እርሱም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦መልካምን፡ዘር፡የዘራው፡የሰው፡ልጅ፡ነው፤ ዕርሻውም፡ዓለም፡ነው፤ መልካሙም፡ዘር፡የመንግሥት፡ልጆች፡ናቸው፤ እንክርዳዱም፡የክፉው፡ልጆች፡ናቸው፥የዘራውም፡ጠላት፡ዲያብሎስ ነው፤መከሩም፡የዓለም፡መጨረሻ፡ነው፥ዐጫጆችም፡መላእክት፡ናቸው። እንግዲህ፡እንክርዳድ፡ተለቅሞ፡በእሳት፡እንደሚቃጠል፥በዓለም፡መጨረሻ፡እንዲሁ፡ይሆናል። የሰው፡ልጅ፡መላእክቱን፡ይልካል፥ከመንግሥቱም፡እንቅፋትን፡ሁሉ፡ዐመፃንም፡የሚያደርጉትን፡ይለቅማሉ፥ ወደ፡እቶነ፡እሳትም፡ይጥሏቸዋል፤በዚያ፡ልቅሶና፡ጥርስ፡ማፋጨት፡ይሆናል። በዚያን፡ጊዜ፡ጻድቃን፡በአባታቸው፡መንግሥት፡እንደ፡ፀሓይ፡ይበራሉ።የሚሰማ፡ጆሮ፡ያለው፡ይስማ። ደግሞ፡መንግሥተ፡ሰማያት፡በዕርሻ፡ውስጥ፡የተሰወረውን፡መዝገብ፡ትመስላለች፤ሰውም፡አግኝቶ፡ሰወረው፥ከደስታውም፡የተነሣ፡ሄዶ፡ያለውን፡ሁሉ፡ሸጠና፡ያን፡ዕርሻ፡ገዛ።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "አዋልደ ንግሥት ለክብርከ። ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት"። መዝ 44፥9።
https://t.me/Eotcw
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ዮሐ. 1:15-25 "ዮሐንስ ሰማዕቱ በእንቲአ" - "ዮሐንስ፡ስለ፡ርሱ፡መሰከረ፡እንዲህም፡ብሎ፡ጮኸ፦ከእኔ፡በዃላ፡የሚመጣው፡እርሱ፡ከእኔ፡በፊት፡ነበረና፡ከእኔ፡ይልቅ፡የከበረ፡ሆኗል፤ስለ፡እርሱ፡ያልሁት፡ይህ፡ነበረ። እኛ፡ሁላችን፡ከሙላቱ፡ተቀብለን፡በጸጋ፡ላይ፡ጸጋ፡ተሰጥቶናልና፥ሕግ፡በሙሴ፡ተሰጥቶ፡ነበርና፤ ጸጋና፡እውነት፡ግን፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ሆነ። መቼም፡ቢሆን፡እግዚአብሔርን፡ያየው፡አንድ፡ስንኳ፡የለም፤በአባቱ፡ዕቅፍ፡ያለ፡አንድ፡ልጁ፡እርሱ፡
ተረከው። አይሁድም፦አንተ፡ማን፡ነህ፧ብለው፡ይጠይቁት፡ዘንድ፡ከኢየሩሳሌም፡ካህናትንና፡ሌዋውያንን፡በላኩበት፡ጊዜ፥የዮሐንስ፡ምስክርነት፡ይህ፡ነው። መሰከረም፡አልካደምም፤እኔ፡ክርስቶስ፡አይደለሁም፡ብሎ፡መሰከረ። እንኪያስ፡ማን፡ነህ? ኤልያስ፡ነህን? ብለው፡ጠየቁት፦አይደለሁም፡አለ፦ነቢዩ፡ነህን? አይደለሁም፡ ብሎ፡መለሰ። እንኪያስ፦ማን፡ነህ? ለላኩን፡መልስ፡እንድንሰጥ፤ስለ፡ራስህ፡ምን፡ትላለህ? አሉት። እርሱም፦ነቢዩ፡ኢሳይያስ፡እንዳለ፦የጌታን፡መንገድ፡አቅኑ፡ብሎ፡በምድረ፡በዳ፡የሚጮህ፡ሰው፡
ድምፅ፡እኔ፡ነኝ፡አለ። የተላኩትም፡ከፈሪሳውያን፡ነበሩና፦እንኪያስ፡አንተ፡ክርስቶስ፡ወይም፡ኤልያስ፡ወይም፡ነቢዩ፡ካይደለህ፥ስለ፡ምን፡ታጠምቃለህ? ብለው፡ጠየቁት።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
5/1/2015 ዓ.ም (፭/፩/፳፻፲፭ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
ብዙኀ ገበርከ እግዚኦ አምላኪየ መንክረ
ወአልቦ ዘይመስሎ ለሕሊናከ ።
አይዳዕኩ ወነገርኩ ወበዝኀ እምኁልቁ፡፡ መዝ. 39፥5
🕯 ትርጉም
አቤቱ አምላኬ ያደረግኸው ተኣምራት ብዙ ነው። ዐሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም። ባወራም ብናገርም ከቍጥር ሁሉ በዛ።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
1 161
ነበር፡፡ አቡነ መልክአ ክርስቶስም በጸሎቱ ክፉ ጠላትን ድል አደረገለት፡፡ "ልጄ አይዞህ አትፍራ ጽና" ይለው ያበረታው ነበር፡፡
❤ ከዚኽም በኋላ በጎንደር ዙሪያ ብዙ መነኰሳት ሰማዕት በሚሆኑበት ዘመን ማኅደረ ክርስቶስ ለአባታችን በራእይ ያየውን ነገረው፤ "አንተ
ሰማዕት ለመሆን ሒድ፣ አቡነ መልክአ ክርስቶስ ግን አይሔድም፣ ብዙ ሥራ ከፊቱ አለ፣ ብዙዎችን ወደ መንግስተ ሰማያት ይጠራልና" ተብያለው በማለት የተነገረውን መልእክት አስረዳው፡፡ አባታችንም "የነብያትን መንገድ ያቀና ሰማዕታትን በፈተና ሁሉ ያጸና አምላክ መንገድህን ያቅናልህ ያስፈጸምህ" ብሎ ልጁን መረቀውና ሰማዕትነት ወደሚቀበልበት ቦታ ሰደደው፡፡ ማኅደረ ክርስቶስም ወደ ንጉሥ ወታደሮች ዘንድ ቀርቦ ስለ ሃይማኖቱ መስክሮ አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ የክብር አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ አንገቱንም በሰይፍ ከቆረጡት በኋላ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ራስ የሰማዕቱ ማኅደረ ክርስቶስ ራስ መዝሙረ ዳዊት መኃልየ ሰሎሞን ውዳሴ ማርያም ዘመረች፡፡
❤ የአቡነ መልክአ ክርስቶስ የዕረፍቱ ቀን በደረሰ ጊዜ በጽኑ ደዌ ታመመ፡፡ ከመረጣቸው ጋር ቃልኪዳን ያደረገ መድኀኔዓለም ለአቡነ መልክአ ክርስቶስም እንዲሁ አደረገ፡፡ "…ድካምህን ተቀብያለሁ፣ በእጅህ የመነኰሱ፣ በመስቀልህ የተባረኩ፣ ከሩቅ አንተን ብለው ደጅህ የመጡ፣ በስምህ መታሰቢያህን የሚያደርጉትን ሁሉ የልባቸውን በጎ መሻት እፈጽምላቸዋለሁ፤ በደላቸውን ሳልመለከት ጸጋ በረከትን እሰጣቸዋለሁ፤ የወዳጆችህን ትውልድ እስከ 15 ትውልድ እምርልሃለሁ" ብሎ ቃልኪዳን
ከገባላቸው በኋላ መስከረም 5 ቀን በዕለተ ቀዳሚት በ86 ዓመታቸው ነፍሳቸው ከሥጋው ተለየች።
❤ ከመቃብራቸውም ላይ ሕሙማን የሚፈወሱበት ድንቅ ድንቅ ተኣምራትን የሚያድርግ ጠበል ፈለቀ፡፡ አቡነ መልክአ ክርስቶስ ለአገልግሎት ሲጓዙ በመንገድ ላይ ከሞተ 900 ዓመት የሞላውን ሰው ዐፅም አግኝነተው ወደ እግዚአብሔር ጸልየው በመስቀላቸው ባርከው ከሞት አስነሥተውታል፣ ከሞት የተነሣውም ሰው ኢአማኒ ስለነበር ጻድቁ አጥምቀው
ለክርስቶስ መንግሥት አብቅተውታል፡፡
❤ ጻድቁ አቡነ መልክአ ክርስቶስ ያደረጉት ታላቅ ተአምር ይኽ ነው፡- ለጻድቁ እንደ ሰው እየተላላከ ከበሸሎ ወንዝ ውኃ እየቀዳ ወደ ገዳማቸው የሚያመጣላቸው አንድ አህያ ነበራቸው፡፡ አህያውም ሰው ሳይጭነው ባዶ እንስራ ወደ ወንዙ ወስዶ በተአምር ውኃው በእንስራ ሲሞላለት ሳያጋድል ይዞ ሩቅ መንገድ ተጉዞ ከአባታችን ገዳም ይደርሳል፡፡ ነገር ግን በአንደኛም ቀን ይህንን አገልጋይ አህያቸውን ጅብ በላባቸው፡፡
❤ አቡነ መልክአ ክርስቶስም በአህያቸው ፈንታ ጅቡን 7 ዓመት ውኃ አስቀድተውታል፡፡ ቅዱሳኑ አቡነ መልክአ ክርስቶስ እና አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ በአንድ ዘመን አብረው የኖሩ ሲሆን ኹለቱ ቅዱሳን የቅርብ ወዳጆችም ነበሩ፡፡ ገድላቸው እንደሚናገረው አቡነ መልክአ ክርስቶስ ከግራኝ አህመድ የ15 ዓመት ጥፋት በኋላ የቅዱስ ያሬድን የቅዳሴ ዜማ ትምህርት ጠብቆ ለትውልድ በማበርከት እጅግ የጎላ ድርሻ አላቸው።
❤ አቡነ መልክአ ክርስቶስ ዐቢይ ጾም ሲገባ ብዙ ጊዜ ብቻውን ሱባኤ ይይዛል፡፡ በዐቢይ ጾም ወቅት ከዕለታት በአንደኛው ቀን በግሸቅ ማርያም ሳለ ክፉ ጠላት በከባድ ረኀብ ፈተነው፡፡ አባታችንም በዚህ አዝኖ ሲጨነቅ ክብርት እመቤታችን ተገጻለት "ሰላም ለአንተ ይሁን ወዳጄ መልክአ ክርስቶስ" አለችው፤ ዳግመኛም "ስለምን ትተክዛለህ? አይዞህ ጽና…" ብላ በልጇ ቸርነት ሰማያዊ ኅብስት መገበችው፡፡ አባታችንም ይህን ምሥጢር ለልጁ ለአባ ሚካኤል ከነገረው በኋላ "እስከምሞት ድረስ ይህን ለማንም አትንገር፣ በኋላ ግን እንደፈቃድህ" አለው፡፡ ቅዱሳን ከውዳሴ ከንቱ ለመሸሽ ሲሉ በሕይወት እያሉ በጎ ሥራቸውን መደበቅ ልማዳቸው ነው፡፡ ከአቡነ መልክአ ክርስቶስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከት ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ የድባ አቡነ ሙሴ ገዳም ገጽ የተወሰደ።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ መስከረም ፭ (5) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያው ጻድቅ የሚያገለግላቸውን አህያ ጅብ ቢበላባቸው በአህያቸው ፋንታ ጅቡን ለ7 ዓመት ውሃ እየቀዳ እንዲያገለግላቸው ላደረጉት ለታላቁ አባት ለአቡነ መልክአ ክርስቶስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ አቡነ መልክአ ክርስቶስ፦ የእህ ጻድቅ አባታቸ ጣዕመ ክርስቶስ እናታቸው አውጋንያ ይባላሉ፡፡ እነርሱም ልጅ አልነበራቸውምና የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ዘወትር ወደ እግዚአብሔር ይማጸኑ ነበር ነገር ግን "የተባረከ ፍሬ የማትሰጠን ከሆነ ልጅ አትስጠን" እያሉም ይጸልዩ ነበር፡፡ ጣዕመ ክርስቶስና አውጋንያ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ሕጉን ዘወትር የሚጠብቁ፣ ለተቸገሩ የሚራሩ ናቸው፡፡ የተራቡትን በመመገብ የታረዙትን በማልበስ የበረቱ በመሆናቸው ዘወትር ከቤታቸው ድኆች አይጠፉም ነበር፡፡
❤ የቅዱሳኑን ልመና የተቀበለ አምላክ የእነርሱንም ልመናቸውን ሰምቶ የተባረከ ልጅ አቡነ መልክአ ክርስቶስን ሰጣቸው፡፡ አባታችን በምድረ ኢትዮጵያ ሳርካ በሚባል ቦታ ሰኔ 26 ተፀንሶ መጋቢት 27 ቀን ተወለደ፡፡ዕድሜውም ለትምህርት ደርሶ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲማር ከዕለታት በአንድ ቀን ከሕፃናት ጋር ሲጫወት እመቤታችን ተገልጻለት "ልጄ ከእንግዲህ አንተ የምትጫወተው ከቅዱሳን መላእክት፣ ከጻድቃንና ከሰማዕታት ጋር ይሁን" አለችው፡፡ እርሱም
ዘወትር ጸሎትን መጸለይ ጀመረ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ስለገለጠለት የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ወድያው አጠናቀቀ፡፡
❤ ከዚኽም በኋላ አቡነ መልክአ ክርስቶስ ገና በለጋ ዕድሜው ስለ ጌታችን መስክሮ ሰማዕት ይሆን ዘንድ በመመኘት በዘመኑ ሰማዕታት ሰማዕትነትን ከሚቀበሉባቸው ቦታዎች ቢሔድም ሰማዕትነት ለእርሱ አልተፈቀደለትም ነበር፡፡ ወደ ወግዳ እና ምድረ ሰርማት የሚባሉ ቦታዎች ቢሔድም የተመኘውን ሳያገኝ ቀረ፣ በዚኽም ጊዜ ቃል ከሰማይ ወደ እርሱ መጣና "ወዳጄ መልክአ ክርስቶስ ሆይ! ሰማዕትነት ክፍልህ አይደለም ይልቁንም እንደ አብርሃም የብዙሃን አባት የሕፃናትና የደካሞች መጠጊያ ትሆናለህ" አለው፡፡
❤ ከዚኽም በኋላ ጻድቁ በመንዝ፣ በጎንደር፣ በመቄት፣ በዳውንት፣ በላስታ፣ በዋድላና በሌሎቹም ቦታዎች ተዘዋውሮ የከበረች ወንጌልን በመስበክ ድዉያንን በመፈወስ ብዙ አገልግሏል፡፡ መንዝ ሪቅ በሚባል ቦታ አቅም የሌላቸውን በዕድሜም የገፉትን እናቶችንና አባቶችን ውኃ በመቅዳት ምግብ በማብሰል ዕንጨት በመሸከም አገለገላቸው፡፡ እንግዶች ሲመጡ እግራቸውን አጥቦ ያሳርፋቸዋል፡፡ ሥራዎችን በሚሠራ ጊዜም ከአንደበቱ ጸሎት አይቋረጥም ነበር፡፡
በእንዲህ ያለ ምግባር ዐሥር ዓመት ካገለገለ በኋላ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ከሆነው ከአቡነ አኖሬዎስ ቤተ ክርስትያን ደብረ ጽጋጃ አባ ጴጥሮስ በተባለ መምህር እጅ መነኰሰ፡፡
❤ አባ ጴጥሮስም አቡነ መልክአ ክርስቶስን ካመነኰሰው በኋላ ወደ ቀደመ ቦታው ሔዶ በዚያ ያሉትን በክህነቱ እንዲያገለግላቸው እንዲያመነኵሳቸው መስቀል ሰጥቶ ሸኘው፡፡ እርሱም ተጨማሪ 12 ዓመት አገልግሏቸው በአጠቃላይ 22 ዓመት ሲሞላው የእግዚአብሔር ጸጋ የበዛላት ወለተ ጽዮን ስታርፍ ፍትሐት አድርሶ ከቀበራት በኋላ ወደ ሌላ ቦታ በመሔድ የእግዚአብሔር መልአክ እየመራው ዳውንት ደረሰ፡፡ በዳውንት አጽፍት ሚካኤል ዘጠኝ ዓመት አገልግሎ ብዙዎችን አመነኰሰ፡፡ ከዚያም ወደ ሌላ ቦታ እንዲሔድ እግዚአብሔር ነግሮት ለሔድ ጉዞ ሲጀምር ድንጋዮች ዕፅዋቶች ከነበሩበት ተነሥተው ይከተሉት ጀመር፣ እርሱ ግን በሥልጣኑ በቦታቸው እንዲወሰኑ አዘዛቸው፡፡ ወደ ዋድላ በመሔድ በሰለልኩላ በየጭራ በሐዲስ አምባ እና በደብረ ዳሪት አቡነ አሮን ተመላልሶ ወንጌልን ሰበከ ድዉያንን
ፈወሰ ብዙዎችንም አመነኰሰ፡፡
❤ ከዚኽም በኋላ ዐብይ ጾምን ወደ ጎንደር ሔዶ ሱባኤውን በዚያ ከቆየ በኋላ ወደ ሰለልኩላ ተመለሰ፡፡ የቅድስት ድንግል ማርያምና የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል ታቦታት አብሮ ይዞ ስለነበር ሀገሩ እንዲባረክ በሰላልኩላ የቅዱስ ሚካኤልን ቤተ ክርስትያን
ሠርቶ ታቦተ ሚካኤልን አስገብቶ አከበረ፡፡ ዛሬም ድረስ በዋድላ ሰለልኩላ ሚካኤል በሰለልኩላ ቅዳሴ መገኛነቱ በብዙዎች ዘንድ ይታወቃል፡፡ አባታችንም ጥቂት ጊዜ በሰለልኩላ ሚካኤል እንደቆየ እመቤታችን "…ይህ ስፍራህ አይደለምና ወደ ደብረ አብ ደብረ ወልድ ደብረ መንፈስ ቅዱስ ሒድ" አለችው፡፡ በተነገረው ቦታም ተወስነው የሚጸልዩ ሦስት ደገኛ መነኰሳት አባቶች "በቶሎ ወደዚህ ና ፣በዚህ አንተ የብዙዎች አባት ትሆናለህ" ብለው ወደ አቡነ መልክአ ክርስቶስ መልእክት ላኩበት፡፡
❤ አባታችንም ከዳውንት ወደ ግሸቅ መሔጃ መንገዱ ላይ መንኳክ ማርያም ደርሶ አደረ፤ ጸሎት አድርሶ ቦታዋን ቢባርካት ጠበል ፈለቀ፤ የገዳም ሥርዓትንም ሠራላት፡፡ ዛሬም ድረስ አባታችን ያፈለቀው ጠበል ብዙ ተኣምራት እያደረገ ምስክር ሆኖ በቦታው ላይ አለ፡፡አቡነ መልክአ ክርስቶስ የእመቤታችንን ታቦት ይዞ በሽሎ የሚባል ወንዝ ሲደርስ እንደ ሱራፌል ቀንና ሌሊት ሳያስታጉሉ የሚያመሰግኑ ሥዉራን ቅዱሳን በደብሩ እንዳሉ አስተዋለ፡፡ እመቤታችን እየመራችው በደብሩ አናት አድርሳው "ይህ ቦታህ ይሁን፣ ስሙም ግሸቅ ይባል፣ ታቦቴንም በቀኝህ አኑር" አለችው፡፡ዳግመኛም "ልጄ ገዳመ አስቄጥስን፣ ገዳመ ሲሐትን እንደባረከ ይህን ገዳምህንም ይባርክልህ፤ ማህበረ መቃርስ ወማኅበረ ጳኩሚስ፣ ማኅበረ ሖር ወአባ አብሎ፣ ደብረ ኮኖብዮስ እና ሌሎችንም እንድባረከ ይባርክልህ፤ ከአንተ የሚወለዱ አንዱስ እንኳን አይጠፋም፤ በገዳምህ የተቀበረ አይጠፋም" አለችው።
❤ አባታችንም ገዳሙን ግሸቅ ካደረገ በኋላ ገዳማዊ አንድነቱ እየጠነከረ በመምጣቱ በደብሩ ዙሪያ የነበሩ ክፉዎች "ቦታችንን ሊቀሙን ነው" ብለው በማሰብ ክፋትን ማድረግ ጀመሩ፡፡ በድንግልና ራሳቸውን ጠብቀው ከዓለም የተለዩ ደናግል መነኰሳት ሴቶቹን በማየት እንዲፈተኑ ተንኮል አስበው መነኰሳት
አባቶች ውኃ ከሚቀዱበት ማይ ዘአጋም ከተባለ ምንጭ ሴቶች ልጆቻቸውን መላክ ጀመሩ፡፡ መነኰሳቱም በዚህ አዝነው ውኃ ሳይቀዱ በመመለስ ለአቡነ መልክአ ክርስቶስ የሆነውን ሲነሩት "ልጆቼ ይህን ቦታ እመቤታችን ነች የሰጠችኝ፣ "አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የፈቀዱልህ ቦታህ ነው፣ ለአንተና ለልጆችህ ለዘለዓለም ማደርያ ርስትህ
ይሁን፣ ወገን የሌላቸው ታማሚዎች ስምህን በመዘከር ከመከራ ይዳኑ" ብላ ተናግራ ሰጥታኛለች፤ እግዚአብሔር ለኛ ካለው ያድርገው ለእነርሱ ካለው ይሁን" ብሎ ሱባኤ ይዞ እናትና ልጅን ለመነ፡፡ የአካባቢው ሰዎችም እግዚአብሔርን አሳዝነዋልና ከእነርሱ ውስጥ ብዙዎች በሕማም በደዌ
ተመቱ፤ ብዙ ሰው መሞት ሲጀምር ቀሪዎቹ ከገዳሙ ክልል ሸሽተው ወጡ፡፡
❤ በዚህም ጊዜ የአቡነ መልክአ ክርስቶስ ዝና በመላው ኢትዮጵያ ደረሰ፡፡ ዳግመኛም አባታችን "…የኤርትራን ባሕር ከፍለህ ሕዝብህን ያሻገርኽ፣ እንዳይርባቸው በበረሓ መና ያወረድኽ፣ እንዳይጠሙ ከዓለት ውኃ ያፈለቅኽ አምላክ ሆይ! ዛሬም አንተ ነኽና ውኃ አፍልቅልኝ" ብሎ ቢማጸን በግሸቅ ተራራ ላይ ውኃ ፈለቀለት፡፡ በገዳሙ የነበሩ ሁሉ ከእርሷ ተጠምቀው ጠጥተው ተፈወሱ፡፡ የጎንደሩ ንጉሥ አድያም ሰገድ ኢያሱ ሙያተኞችን ልኮ በግንብ አሰራት፡፡ የአጼ ኢያሱ ልጅ ልዑል ሰገድ ተክለ ሃይማኖትም ውኃ የሚቀዱበት በቅሎ ሰጥቷቸዋል፡፡ ማኅደረ ክርስቶስ የሚባል ክፉ ጠላት በብዙ ፈተና የሚያሠቃየው የአቡነ መልክአ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር በደብሩ
