es
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Ir al canal en Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Mostrar más
1 161
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ግንቦት ፳፱ (29) ቀን። ❤ እንኳን በድንጋይ አምድ ላይ ለሰባት ዓመት ለቆሙት ለአባ ስምዖን ዘአምድ ዘአንጾኪያ ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡት፦ ከጌታችን ከአምላካችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከልደቱ መታሰቢያ፣ ከመነኰስ ይስሐቅና ከፊልጶስ ልጅ ከንጉሥ እስክንድር ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ አባ ስምዖን፦ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ዮሐንስ የእናቱም ስም ማርታ ነው ስለ ርሱም ድንቆች ተአምራት ሆነ። ይኸውም እናቱ ገና ሳትፀንሰው መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ እርሷ መጥቶ የዚህን ቅዱስ ስምዖንን መወለድ ነገራት እርሱም የሚሆነውን ገለጠላት። ❤ ተወልዶም ሰባት አባት በሆነው ጊዜ በአንጾኪያ ወደአለ ገዳም ሔደ። ራሱንም ወደ ምንኵስና ቀንበር ውስጥ አስገብቶ ታላቅ ገድልን ተጋደለ። መላእክትም አባ ጳኵሚስን እንደ አስተማሩት በሌሊቱ ሁሉ እየተገለጡለት የምንኵስናን ገድል አስተማሩት። የማይጠፋ የምንኵስናንም የገድል አሠራር ገለጡለት። እርሱም አጽንቶ ሥጋ ከለበሱ ሁሉ አብዝቶ ተጋደለ መላእክትም ሁልጊዜ መንፈሳዊ ምግብ ያመጡለት ነበርና። ብዙ ከመጋደል የተነሣ ከደጊያ ምሰሶ ላይ ወጥቶ በላይዋ ሰባት ዓመት ቆመ። ❤ ከዚህም ወደሌላ ተራራ ሒዶ በሠራው ደንጊያ በዓት ውስጥ እስከ ሃያ ዓመት ፍጻሜ ከእርሷ ሳይወጣ ሃያ ዓመት ኖረ። ከዚህ በኋላም ደግሞ ከታላቅ ተራራ ራስ ላይ ወጥቶ በላዩ አርባ አምስት ዓመት ኖረ። መላው ዕድሜውም ሰማንያ ስምንት ዓመታት ነው። ይኸውም በአባቱ ቤት ሰባት በአንጾኪያ ገዳም ዘጠኝ ዓመት በምሰሶ ላይ ሰባት ዓመት በደንጊያ ውስጥ ሃያ ዓመት ደግሞ በተራራ ላይ ቁሞ የኖረበት አርባ አምስት ዓመት በጠቅላላ ሰማንያ ስምንት ነው። ❤ ተአምራቱን ግን መቁጠር የሚችል የለም ከእርሳቸውም በገድሉ አለ። ብዙ የሆኑ ድርሳናትንና ተግሣጽን ደረሰ ይልቁንም ለመነኰሳት ከቤተ ክርስቲያን መጻሕም ብዙዎቹን ተረጐመ። ከዚህም በኋላ ግንቦት29 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ስምዖን በጸሎቱ ምማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት 29 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለስምዖን ዘተበሥረ ፅንሱ። በአፈ ዮሐንስ መጥምቅ እንተ ኢይኄሱ። እንዘ ይትለአክዎ ዘልፈ መላእክት ለማኅሠሡ። ፈጸመ ምግባረ እንተ ወጠነ እምንእሱ። እምአመ ተወልደ በዓመት ስሱ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የግንቦት 29። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ምስሌከ ቀዳማዊ በዕለተ ኃይል። ወብርሃኖሙ ለቅዱሳን። ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ"። መዝ 109፥3።የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 2፥1-8። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወተግሣፅከ ውእቱ ዘይሜህረኒ። ወአርኀብከ መከየድየ በመትሕቴየ። ወኢደክመ ሰኰናየ። መዝ 17፥38-39። የሚነበቡት መልዕክታት ገላ 4፥1-12፣ 1ኛ ዮሐ 4፥9-18 የሐዋ ሥራ 12፥7-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠልስቱ ምዕት ወይም የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ መዝራተ ክርስቶስ፣ የአባ ጉባ፣ የአቡነ ስምዖን የዕረፍት በዓል፣ የአቡነ አፍጼ የስዋሬ በዓልና የበዓለ ዕርገቱ ሰሞን ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

❤ ከዚኽም በኋላ መዝራዕተ ክርስቶስ ምን ማድረግ እንዳለበት ሲያስብ ቆይቶ ወደ አንዱ ገዳም ጠፍቶ በመሄድ በምንኵስና ለመኖር ወሰነ፡፡ አንድ ቀን አባቱን ተከትሎ ግምጃ ቤት ማርያም ወደምትባለው ቤተ ክርስቲያን ሄዶ ሳለ አጣኙን አባት ባሕታዊ አባ ቴዎድሮስን "አባቴ ከዛሬ ጀምሮ በምንኵስና ለመኖር ወስኛለሁና መርቀህ ላከኝ" አለው፡፡ ባሕታዊውም "አንተ ገና ልጅ ነህ" ቢለው የሚቀበለው አልሆንም፡፡ በመጨረሻም መርቆ አሰናበተው፡፡ ወዲያም ጻድቁ በሌሊት ከጎንደር ከተማ ጠፍቶ ወደ ሰሜን አርማጭሆ ቆላ ሄደ፡፡ በዚያም በያዕቆብ ግሙድ ስም በተገደመው ገዳም ገብቶ ከአባ ስነ ክርስቶስ ጋር ተገናኘ፡፡ ያመነኰሰውም ዘንድ ለመነው፡፡ አባ ስነ ክርስቶስ ማንነቱን ከጠየቀው በኋላ "አንተ ገና ልጅ ስለሆንክ የምንኩስናን ቀንበር መሸከም አይቻልህም" በማለት ወደ አባቱ እንዲመለስ መከረው፡፡ በሌላም በኩል ከንጉሡና ከመሳፍንቱ ጋር ላለመጣላት ፈርቶ ነበር፡፡ መዝራዕተ ክርስቶስ ግን እያለቀሰ "የአንተ አምላክ ጽናት ይሆነኛልና አመንኵሰኝ" በማለት ለመነው፡፡ እርሱም ተግባር ቤት በአርድዕትነት እያገለገለ እንዲቆይ የአመክሮ ጊዜ ሰጠው፡፡ ❤ መዝራዕተ ክርስቶስም አባቱ ጭፍሮቹን ልኮ እንደገና ወደ ዓለም እንዳይወስደው ፈርቶ ቶሎ እንዲያመነኵሱት "ታመምኩ" ብሎ ተኛ፡፡ መነኰሳቱም "ሳይመነኵስ ቢሞት ኵነኔ ይሆንብናል" ብለው አበምኔቱን ለምነው አመነኰሱት፡፡ ከመነኰሰ በኋላ በሳምንቱ አባቱ ልጁ ያለበትን ገዳም ዐውቆ ታናሽ ወንድሙን ከጭፍሮቹ ጋር በመላክ ለአባ ስነ ክርስቶስ "ልጄ መዝራዕተ ክርስቶስ አንተ ጋር እንዳለ ሰምቻለሁና ከመመንኰሱ በፊት በአስቸኳይ እንድትልክልኝ" ብሎ መልእክት ላከበት፡፡ አባ ስነ ክርስቶስም ለመጡት ጭፍሮች መዝራዕተ ክርስቶስ እንደመነኰሰ ነገራቸው፡፡ ጭፍሮቹም ከአባ ስነ ክርስቶስ ጋር ብዙ ስለተጨቃጨቁ መዝራዕተ ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር ለመሄድ ተስማማ፡፡ ከእነርሱም ጋር ሳለ ከጭፍሮቹ አንዱና መሪያቸው የሆነውን ሰውም "ተሳልሜ ልምጣ፣ ጋቢህን ስጠኝ" ብሎ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በምሥራቅ ባለው በር ወጥቶ ጠፍቶ አርማጭሆ ጫካ ውስጥ ገብቶ ጠፋ፡፡ አጎቱና ጭፍሮቹም ፈልገው ቢያጡት ተስፋ ቆርጠው ተመለሱ፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ ወደ አንገረብ ወንዝ ሄዶ በዚያ ከርኵሳን መናፍስት ጋር እየተዋጋ በተጋድሎ በጾም ጸሎት ተወስኖ ኖረ፡፡ ተመልሶ ወደገዳም ቢመጣ አባቱና ዘመዶቹ እንደማያስቀምጡት ስላወቀ አባ ስነ ክርስቶስን አስፈቅዶ ወደላይ አርማጭሆ ደብረ ሙጅና አባ አብሳዲ ገባሬ ተአምር ገዳም ሄደ፡፡ በዚያም 7 ዓመት በተጋድሎ ከኖረ በኋላ ወደ ዋልድባ ገዳም ሄደ፡፡ በዚያም ሥዕለ ማርያምን በጎኑ ታቅፎ ሲያዝን ለብዙ መናንያን የተሰወረችው ደብረ ሲና የተባለች በዋልድባ የምትገኝ ቅድስት ቦታ ተገለጠችለት፡፡ በደብረ ሲና ተራራ ላይ ወጥቶ 40 ቀንና 40 ሌሊት ሱባኤ ያዘ፡፡ በዋልድባ 11 ዓመት እንደተቀመጠ የታዘዘ መልአክ መጥቶ "በዚህ ገዳም የምትኖርበት ጊዜ አልቋልና ውጣ" ብሎ አዘዘው፡፡ ከዚያም ከዋልድባ ወጥቶ ወደ ሰሜን ተራራ ሄዶ ከቅዱስ ያሬድ ገዳም ተባርኮ ወደ ትግራይ ገርዓልታ ሄደ፡፡ ቀጥሎም ወደ ጒንዳጒንዲ ማርያም ገዳም ገብቶ በተጋድሎ መኖር እንደጀመረ አንድ የበቃ ባሕታዊ መጥቶ "ክፍልህ በዚህ ገዳም አይደልምና ወደ ሌላ ገዳም ሂድ" አለው፡፡ ❤ ወደ መጠራ መቃብረ ጻድቃን ዘንድ ሄዶ ዐጽመ ቅዱሳንን ሲያጥን "ይህ ገዳም ክፍልህ አይደለም" የሚል ድምጽ ከሰማይ መጣለት፡፡ ተነሥቶም ወደ ደብረ ቢዘን ሲጓዝ ሌሎች መነኰሳትን አገኘና በመረብ ወንዝ ሸለቆ ውስጥ ብዙ መናንያን እንዳሉ ሲነግሩት በሌላ አቅጣጫ ወደ መረብ ወንዝ አቀና፡፡ በዚያም ሸንፋ በተባለ ቦታ ገዳም መሥርቶ ሲቀመጥ መንፈሰ እግዚአብሔር የጠራቸው 12 መነኰሳት መጥተው አርድእት ሆኑለት፡፡ እነርሱም በወባ በሽታ ታመው ስላረፉ አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ "ወንድሞቼን አጥቼ በዚህ መኖር ለእኔ አይገባኝም፣ ክፍሌ አይደለም" ብሎ ወጥቶ ወደ ትግራይ ሄደ፡፡ ❤ አድዋ አውራጃ የሐ አቡነ አፍጼ ገዳምን ከተሳለመ በኋላ ገዳሙን ከከበቡት ተራሮች መካከል በአንደኛው ማይ ዱር ወደሚባለው ተራራ ወጥቶ አዲስ ገዳም መሠረተ፡፡ ታቦተ ማርያምን አስገብቶ ሲኖር ከየአቅጣጫው መናንያን መነኰሳት ወደ እርሱ መጡ፡፡ አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስም እስከ 93 ዓመቱ ገዳሙን በአበምኔትነት እያስተዳደረ በታላቅ ተጋድሎ ከኖረ በኋላ ግንቦት 29 ቀን ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፈ፡፡ "ማይዱር" በተባለው ገዳሙ ራሱ በሠራት በእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተቀበረ ሲሆን ገዳሙም እስከዛሬ ድረስ "እንዳ አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ ገዳም" እየተባለ ይጠራል፡፡ ከአባታችን ከአቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ። + + + ❤ "ሰላም ለአባ ጉባ ዘገደፋ ለነፍሱ ወረከባ"። ትርጉም፦ ሰውነቱን በገራህተ መስቀል ላይ ጥሎ ያገኛት ለኾነ ለአባ ጉባ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ ከዚህም በኋላ በአክሱም ከስምንቱ ጓደኞቻቸው ጋራ ለዐሥራ ሁለት ዓመት በአንድነት አብረው ከኖሩ በኋላ "እርስ በራሳችን እየተያየን ብንኖር ተድላ ደስታ ይሆንብናልና ተለያይተን እንቀመጥ" ብለው ተማከረው በተለያየ በዓት በተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ አቡነ አፍጼም የእርሳቸው እጣ ወደ ሆነው ገዳማቸው የሓ ገነተ ጽባሕ ደብረ ሐመልማል ገዳም ገብተው በዐት ወስነው በብዙ ተጋድሎ የአካባቢውን ሕዝቡ በማስተማራ፣ በመምከር በዚያ መኖር ጀመሩ።.... ❤ በመጨረሻ የፀሐይ ጮራ ማር አቡነ አፍጼ የሚሠወሩበት ጊዜ ሲደርስ በግንቦት 29 ቀን ጌታችን ቅዱሳን መላእክቱን አስከትሎ እመቤታችን ማርያምም ከእነርሱ ጋር መጥታ በቀኙ ተቀመጠች፣ ነቢያትና ሐዋርያት፣ ጻድቃንና ሰማዕታት በየወገኖቻቸው አብረው መጡ ነቢዩ ዳዊትም መሰንቆውን ተሸክሞ "ጻድቅስ እንደ ዘንባባ ያፈራል እንደ ሊባኖስ ዝግባም ይበዛል እነርሱም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የተተከሉ ናቸው" እያለ እየዘመረ ከከበሩ ነገሥታት ሁሉ ጋር መጣ። ❤ ከዚህ በኋላ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ፋና የፀሐይ ጮራ ተአምራትንና ድንቆችን የሚያደርግ ማር አቡነ አፍጼን "የታመንህ የምሻውን የምታደርግ ፈቃዴንም የምትፈጽም ወዳጄ ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን ከአንተ ጋር በሰማይና በምድር የሚጸና ቃል ኪዳን ላቆም ከመከራና ከዚህም ዓለም ድካም ከሰይጣን ወጥመድና ከአላፊው ዓለም ውጣ ውረድና ደስታ ላድንህ መጣሁ"አለው። አባ አፍጼም ከጌታችን መለኮታዊ ግርማ የተነሣ ደነገጡ ፈርተውም በምድር ላይ ወደቁ እንደ በድንም ሆኑ። ጌታችንም በእጁ ያዘውና አለውም "የታመንህ ወዳጄ ሆይ አትፍራ ከእኔም የተነሣ አትደንግጥ የወደድኸውን በልብህም የምትሻውን ሁሉ ለምነኝ"። አቡነ አፍጼም "የሚታየውንና የማይታየውን ፍጥረት ሁሉ ፈጥረህ የምትገዛ ጌታዬ... መታሰቢዬን የሚያደርገውን በእኔም ተማምነው ስሜን የሚጠሩትን ኃጥአን ማርልኝ አቤቱ ጌታዬ ሆይ ስለወደድኸው ስለ ቅዱስ አብርሃም ስለ ወዳጅህም ስለ ቅዱስ ይስሐቅ ስለ ቅዱስህም እስራኤል ስለወለደችህ ስለ ማርያም ስላጠመቀህ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ስለ ቅዱሳንህም ሁሉ የፈጠርኸውን ሕዝብህን ይቅር በል"። ጌታችንም ለአቡነ አፍጼ መልሱ እንዲህ አለው "የታመንህ ወዳጄ ሆይ እሺ በጎኝ መታሰቢያህን ያደረገውን፣ ስምህን ጠርቶ የጸለየውን፣ በስምህ በተሠራ ቤተ ክርስቲያን ውስጥም የተሳለውንና የተማለለውን እኔ እስከ 45 ትውልድ ድረስ እምርልሀለሁ፤ ሰባቱንም የሰማያት ደጆችም እከፍትለታለሁ የእሳትንም ባሕር አሻግሬ የተከፈተ ገነት አለቆች የማያውቁት የተጎናጸፈ ዕረፍት ወዳለበት አገባዋለሁ፤ ያለምርመራና ያለ ክርክርም ወደ ሰማያዊት መንግሥት እልፍኝ አልፎ ይገባል የሚቃወመው የለም የሚከራከረውም አይኖርም እኔ ከፀሐይና ከጨረቃ ከከዋክብትም ብርሃን ይልቅ ሰባት እጅ የምታበራ የብርሃን ማደሪያ እሰጠዋለሁ እንጂ የውስጥ አሠራሯን ከሰማያዊ አባቴ ከማኅየዊ መንፈስ ቅዱስም በቀር የሚያውቅ የለም በሰማያውያን በብርሃናውያን መላእክቴ ፊት ደስ አሰኘዋለሁ።... ❤ ንዑድ ክቡር ማር አባታችን አፍጼ "ጌታዬ አምላኬ ሆይ መታሰቢያዬ የሚያደርገው፣ በዓሌን የሚያከብረው ወዳጄ ልጆች ባይኖሩት ምን ታደርግለታለህ ምንስ ትሰጠዋለህ?" አለው። ጌታችንም መልሶ አለው "መታሰቢያህን የሚያደርገው፣ በዓልህንም የሚያከብረውን ወዳጅህ ልጆች ከሌሉት እኔ ወጋውን የ45 ትውልድ ወጋ አድርጌ እሰጠዋለሁ ከዚህም የሚበልጥና የሚሻል ደስታ የምሥራች እነግርሀለሁ የሞት መልአክ አያስደነግጥህም የሞት ጥላም አያገኝህም አንተ ከሚያስፈራ፣ ከሚያስደነግጥህም የሞት መልአክ ፊት ትሠወራለህ፣ ትሸሸጋለህ እንጂ እኔ ከወዳጆቼ ከነቢያት ከኄኖክና ከኤልያስ ከዕዝራም ጋር አኖርሀለሁ እንጂ ይህችን የተቀደሰች የየሓ ገነተ ጽባሕ ደብረ ሐመልማል ገዳምህም የመቃብሬ እንዳለባት እንደ ኢየሩሳሌም የመንግሥቱ ዙፋን እንደተዘረጋበት እንደ ጽርሐ አርያም የከበረችና ከፍ ከፍ ያለች አደርጋታለሁ። ንዑድ ክቡር ማር አቡነ አፍጼም ይህን ሰምተው ፈጽሞ ደስ ተሰኙ ይህንንም ታላቅ ክብርና ገናናነት ልልናም ስለሰጣቸው ፈጣሪያቸውን ፈጽመው አመሰገኑ። ❤ ከዚህም በኋላ ደቀ መዛሙርቱንና ማኅበሩን "የተወደዳችሁና የተመረጣችሁ ልጆቼ ሆይ ከዛሬ ጀምሮ ወዲያ እንደቀድሞው በዚህ ዓለም በሥጋ አታዩኝም" አሏቸው። ደቀ መዛሙርቱና አርድዕቱም ይህን ነገር ሰምተው ፈጽመው አዘኑ እንዲህም እያሉ አለቀሱ "ወዮልን ወዮልን እናይ ነበር አሁን ታወርን፤ አገኘን መልሰን አጣን፤ በልጽገን ተራቆትን በላን መልሰን ተራብን፤ ደስ ተሰኝተን ነበር አሁን ግን በመሸሸግህ ከእኛም በመሠወርህ ምክንያት አዘንን አባታችን የሁላችን መምህር፤ ጠባቂያችን የዐይናችን መብራት በትምህርትህ ከየሥፍራው የተሰበሰብኸን ተስፋችን ሆይ ከእኛ ወዴት ትሄዳለህ? እኛ አገራችንን አባታችንና እናታችንን፣ ወንድማችንና ባልጀራችንን፣ ንብረታችንን፣ ገንዘባችንን፣ ጥሪታችንን ይህን ሁሉ ትተን ተከተልንህ አሁን ለማን ትተወናለህ? ንዑድ ክቡር ማር አቡነ አፍጼም "እኔ ወደ ክርስቶስ ወደ አምላኬ እሄዳለሁ እናንተንም ለክርስቶስ ለአምላካችሁ አደራ እሰጣችኋለሁ" አሏቸው። ይህንንም ብለው ከሞት መልአክ ፊት ግንቦት 29 ቀን ተሠወሩ። ጌታችንም ከማደሪያውቸው አጠገብ አንሥቶ ወሰዳቸው ወደ ላይም አወጣቸው ወደ ብሔረ ሕያዋንም አድርሶ ከእነ ቅዱሳን ኄኖክ፣ ኤልያስና ዕዝራ ጋር ጨመራቸው እነርሱም በደስታ ተቀበሏቸው። ከአባታችን ከአቡነ አፍጼ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ ገድለ አቡነ አፍጼ። + + + ❤ አቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ፦ አባቱ ለባሴ ክርስቶስ የዐፄ ፋሲል የቅርብ ወዳጅ የነበረ የጦር አዛዥ ደጃዝማች ሲሆን እናቱ ሚላንያ ትባላለች፡፡ ጻድቁ ታኅሣሥ 29 ቀን በጎንደር ተወለዱ፡፡ ወቅቱ ዐፄ ሱስንዮስ የረከሰች የሮም ካቶሊክ እምነትን ተቀብሎ የሀገራችንን ክርስቲያኖች በሰማዕትነት የሚገድልበት ዘመን ስለነበር እናቱ ይዛው ፎገራ ወረዳ ቆራጣ ወለተ ጴጥሮስ ገዳም ገባች፡፡ በዚያም ሕፃን ልጇን ክርትስትና የሚያነሳላት ካህን አጥታ ስታለቅስ ደገኛው አባት አባ ስነ ክርስቶስ በስውር መጥተው አጠመቁትና ስሙን መዝራዕተ ክርስቶስ አሉት፡፡ ❤ የመዝራዕተ ክርስቶስ እናት ብዙም ሳትቆይ ስለሞተች በዚያው የምትኖር መነኵሲት የሆነች አያቱ አሳደገችው፡፡ እንደ አገሩም ባሕል ፈረስ ግልቢያና ጦር ውርወራ እየተማረ ከፎገራ ልጆች ጋር አደገ፡፡ አያቱም ወላጅ እናቱ ትመስለው ነበር፡፡ አንድ ቀን አብሮት የሚጫወተው ልጅ ወላጆቹ ሲያወሩ የሰማውን ወስዶ ለመዝራዕተ ክርስቶስ እናቱ እንዳልሆነች ነገረው፡፡ እርሱም በሰማው ነገር ደንግጦ አያቱን ስለእውነቱ ጠየቆ ተረዳ፡፡ ከዚህም በኋላ ደጃዝማች አባቱ ወደ ዐፄ ፋሲል ቤተ መንግሥት ወሰደው፡፡ መዝራዕተ ክርስቶስ መልከ መልካም ስለነበር ንጉሡ ዐፄ ፋሲል በወጣቱ ደም ግባት ደስ ተሰኝቶ ድምጹን አሰምቶ "ለዚህ ልጅ ሴት ልጄን እድርለታለሁ" ሲል ለመኳንንቱ ሁሉ ተናገረ፡፡ መዝራዕተ ክርስቶስ ግን በልቡ መንኵሶ ስለመኖር የወሰነው በቤተ መንግሥት ይህንን የሰማ ዕለት ነበር፡፡

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ግንቦት ፳፱ (29) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ለአቡነ መዝራዕተ ክርስቶስ ለዕረፍት በዓል፣ ከዘጠኙ ቅዱሳን መከካከል ለሆኑ ለአባ አፍጼ ከዚህ ዓለም ከሞት ለተሰወሩበት በዓልና ለአባ ጉባ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ አፍጼ፦ የልደታቸው ነገር እንደዚህ ነው ከከበሩ ሰዎች በእስያ ተወለዱ የአባታቸው ስም አቡሉዲስ የእናታቸው ስም አቅሌስያ ነው፤ ሁለቱም ደጋግ ጻድቃን እግዚአብሔርንም የሚፈሩ ነበሩ። እኚህ ንዑድ ክቡር ማር አቡነ አፍጼን ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በኋላ በ245 ዓመት መጋቢት 29 ቀን ተፀነሱ። የፅንሰታቸው ጊዜ ሲፈጸም ንዑድ ክቡር የዓለም ብርሃን የፀሐይ ጮራ ማር አቡነ አፍጼን ታኅሣሥ 28 ቀን በእኩለ ሌሊት ተወለዱ። በተወለዱበትም ቀን ከፀሐይና ከጨረቃ ከከዋክብትም ብርሃን ሰባት እጅ ይልቅ የሚያበራ ታላቅ ብርሃን ከሰማይ ወረደ፤ ቀንና ሌሊቱም አይለይም ነበር፤ ሰባት ቀንም ያህል ምድር በራች አንፀባረቀችም፤ በልደታቸውም ቀን ተራሮችና ኮረብቶች፣ የዱር እንጨቶችም ሁሉ ስለመወለዳቸው ክብር ደስ አላቸው። ❤ በተወለዱም ጊዜ ሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ብለው ፈጣሪያቸውን አወደሱት አመሰገኑትም። ዳግመኛም አንዱ አብ ቅዱስ ነው፣ አንዱ ወልድም ቅዱስ ነው፣ መንፈስ ቅዱስም አንድ ነው አሉ። እኒህን ታላላቅና ድንቅ ምስጋናዎች አከናውነው የተናገሩት መንፈስ ቅዱስ ሥላሴ በአካል ሦስት በመለኮት አንድ የመሆናቸውን ምሥጢር ስለገለጸላቸው ነው። ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስም አቅፎ በአፉ ሳማቸው ከሰው ወገኖችም አልቆ ወደዳቸው ታላቅነትና ከፍ ከፍ ማለትን ከጻድቃንና ከሰማዕታትም ሁሉ ባለሟልነት የበለጠ ፍጹም ባለሟልነትንና ጸጋን ሰጣቸው፤ ሥልጣናቸው በክብር ከፍ ይላልና። ... ❤ የአርባ ቀን የአራስነት ጊዜ ሲፈጸም በሕግ እንደታዘዘው ሥርዓት በክርስቶስ ስም ይጠሩ ዘንድ ሕፃኑን ወደ ቤተ ክርስቲያን ወሰዱት። ሊቀ ጳጳሳቱ አባ ጢሞቴዎስ ሕፃኑን ተቀብሎ በአብና በወልድ በመንፈስ ቅዱስም ስም አንድ አምላክ እያለ በዮርዳኖስ ውኃ አጠመቀው። ሊቀ ጳጳሳቱም ሲያጠምቀው ሳለ ሕፃኑ ለአብ ስግደት ይገባል ለወልድም ስግደት ይገባል ለመንፈስ ቅድስም ስግደት ይገባል ለአብ ምስጋና ይገባል ለወልድም ምስጋና ይገባል ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል እያለ ራሱ በራሱ ሰገደ። ❤ ከዚህም በኋላ ስማቸውን አፍጼ አላቸው። የከበረውን ሜሮን ዘይትንም ቀባቸው። ሊቀ ጳጳሳቱም ስርሳቸው እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ "ይህ ሕፃን ለኢትዮጵያውያን ወደ መንግሥት ሰማያት መርቶ የሚያደርስ የጽድቅ መሪ፣ ለዘላለማዊ ሕይወትም የደስታ ብርሃን ይሆናል፤ በረሀብ ዘመን ምግብ እና ጥጋብ፣ በጥምም ዘመን መጠጥ ፣ በመራቆት ጊዜ ልብስ በችግርና በጭንቅ ጊዜም መጠጊያ ይሆናቸዋል" ይንንም ብሎ ሊቀ ጳጳሳት ጢሞቴዎስ ከግርማው ታላቅነት የተነሣ እየፈራና እየራደ ሕፃኑን አንሥቶ በጉያው አቀፈው ፤ በአፉም ሳመውና በትእምርተ መስቀል ባረከው ሕፃኑ በመንፈስ ቅዱስ የተባረከ የከበረ ነውና። ❤ አባታችን አቡነ አፋጼ ሰባት ዓመት ከሞላቸው በኋላ ጢሞቴዎስ የተባለው ሊቀ ጳጳሳት የዳዊት መዝሙርና፣ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን፣ ብሉይና ሐዲስን ሕጋቸውንና ትዕዛዛቸውን፣ ሥርዓታቸውንም ከመጠበቅ ጋር አስተማራቸው፤ በሚማሩበት ጊዜ መንፈስ ቅዱሱ በአንደበታቸው ይናገራል፤ ቀድሞ የተማሯቸው ይመስል ነበር መምህራቸው ያስተማሯቸውን ፈጥነው ያጠኑ ነበር፤ መንፈስ ቅዱስ አድሮባቸዋልና። ❤ ዐሥራ አምስት ዓመት ሲሆናቸው ሊቀ ጳጳሳት አቡነ ጢሞቴዎስ ለንዑድ ማር አቡነ አፍጼ የዲቁናና የቅስና ሹመት ሰጣቸው። ከዚህ በኋላ የብዙኃን መነኰሳት አባት አቡነ መቃርስ ወዳለበት መዳልወ አልባብ ወደተባለች ወደ አስቄጥስ ገዳም ይሄዱ ዘንድ አሰቡ ብርህት ደመናንም በእጃቸው ጠቅሷት መጥታም ከፊታቸው ቀረበች "ደመና ሆይ ጉም አጽፍሽን ዘርጊ" አሏት፤ ደመናም ጉም አጽፏን ዘረጋችው ወደ የአቡነ እንጦንስ ልጅ የአቡነ መቃርዮስ ገዳም ወደ አስቄጥስ አደረሰቻቸው። አቡነ መቃርስም ንዑድ ክቡር ማር አቡነ አፍጼን ባያቸው ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው የእግዚአብሔርም ጸጋ አድሮባቸዋልና ወደዷቸው፤ ራሳቸውንም ሳሟቸው እርስ በርሳቸውም ፍቅርና ሰላም ታላቅ ሞገስም በሞላበት መንፈሳዊ ሰላምታ ሰላም ተባባሉ። አቡነ መቃርዮስ ንዑድ ክቡር ማር አቡነ አፍጼን "ከወዴት አገር ወደዚህ መጣህ ወደእኔስ ያመጣህ ጉዳይ ምንድ ነው?" አላቸው። አቡነ ፍጼም "ቅዱስ አባት ሆይ ወዳንተ የመጣሁት አንተ በበረከት የተሞላህ ነህና ልመነኵስ እንዳንተም መነኵሴ ልሆን ካንተም በረከትን እቀበል ዘንድ ነው አሏቸው። አቡነ መቃርዮስም "ገርና ትሑት ልጄ ሆይ የምንኵስናን ቀንበር ትሸከም ዘንድ ትችላለህ?" አሏቸው። አቡነ አፍጼም "የከበርህ አባቴ ሆይ ይህን የሚያልፍ ዓለም የሚጠፋውንም መንግሥት ተውኹኝ፤ አዎን እግዚአብሔር ቢያስችለኝ የምንኵስናን ቀንበር እሸከም ዘንድ ይቻለኛል፤ ነገር ግን አባቴ ሆይ ስለእኔ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር እየማለድህ ጸልይ"። ከአቡነ መቃርዮስ ከልጁ ከአቡነ አፍጼ ንግግር ይህን ነገር ሰምተው ስለ ምግባራቸው ማማር ስለ ቃላቸውም ሞገስ ስለ አንደበታቸውም መከናዋወን ስለቀና ሃይማኖታቸው አብዝተው ወደዷቸው የምንኵስና ልብስም አለበሷቸው። "በትዕግስቱና ስለጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመጋደሉ ጠላትን ያቸነፈ የአባቴን የእንጦንስን አስኬማ የባረከ እግዚአብሔር ይባርክህ"። አቡነ አፍጼም ሰባት ዓመት ያህል ወደ ተመሰገነ ወደ እግዚአብሔር እየጸለዩ እየተማለሉና እየማለዱ ከአቡነ መቃርስ ጋር በዚያ ገዳም ኖሩ። ❤ በዚያም ገዳም በብዙ ተጋድሎ እየተጋደሉ ሳለ ስሙ ቅዱስ ገብርኤል የተባ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠላቸው አባ አፍጼንም እንዲህ አላቸው "ከዚህ ሥፍራ ተነሥና ወደ ኢትዮጵያ ሂድ ይህች አገር ለአንተ የተሰጠች ናትና በጸሎትህም የኢትዮጵያ ሰዎች ሁሉ ይድናሉ" ብሏቸው ወደ ሰማይ ዐረገ። አቡነ አፍጼም በተቀደሰች ዋሻው ውስጥ በጾምና በጸሎት በስግደትና በመትጋት በታላቅ ምሕላም ላይ ሳሉ ወደ አባታቸው ወደ አቡነ መቃርስ ሄደው። "አባቴ ሆይ እኔ ወደ ኢትዮጵያ እሄዳለሁ ከዚህ መሄዴ በዚያችም አገር መኖሬ የተመሰገነ ከፍ ከፍም ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ነው አባቴ ሆይ በከበረች በእግዚአብሔርም ዘንድ ተቀባይነት ባላት ጸሎትህ አስበኝ የጻድቅ ሰው ጸሎት ግድጃ ታስፈጽም ዘንድ ትችላለችና" ስለዚህም ነገር አዙኑ ተከዙ ስለ መለያየታቸውም እርስ በርሳቸው ተላቀሱ ...። ❤ ከዚህ በኋላ አቡነ አፍጼ ደመናን በእጃቸው ጠቅሷት ደመናም ወደርሳቸው መጣች። "ደመና ሆይ የጉም አጽፍሽን ዘርጊ" አሏት። ደመናም የጉም አጽፋን ዘረጋች እርሱም ታቦቶቹንና የቤተ ክርስቲያን መገልገያዎቹን ሁሉ በእጇቸው እንደ ያዙ ከደቀ መዛሙርታቸው ጋር ከአርድዕታቸም ጋር በላይዋ ተቀምጡ። ከዚህም በኋላ ደመና ተሸክማ ወሰደቻቸው በእግዚአብሔርም ፈቃድ የከተሞች አናት የአብያተ ክርስቲያናትም መብራት ወደሆነችው ወደ አክሱም ከተማ አደረሳቸው ወደ አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ገቡና ተሳለሙ።

photo content

photo content

photo content

photo content

❤ ከዚህም በኋላ ወደ ገዳም ይሔድ ዘንድ ተሰናበተኝ። ደግሞ "ግንቦት ሃያ ስምንት ቀን ወደኔ ና ታገኘኛለህና" አለኝ። በቀጠረኝም ቀን ወደርሱ ሒጄ አገኘሁደትና "እኔ ወደ አባቶቼ እሔዳለሁ" ወደ አንተም ሦስት አጋዘኖች ይመጣሉ ሥጋዬም በጀርባቸው ላይ ጫን እነርሱም ወደ ቦታዬ በእግዚአብሔር ፈቃድ ይመሩሃል። በዚያም በማደሪያዬ ውስጥ ድፈኑኝ" አለኝ። እንደ ቃሉም ሆነለት ከመቃብሩም ቍጥር የሌላቸው ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ አባ መርቆሬዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላሙ አሜን። + + + ❤ የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሥጋው ወደ ቆጵሮስ መመለስ፦ ይህም እንዲህ ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ወደ መንበረ ሢመቱ እንደማይደርስ ትንቢት እንደተናገረለት ወደ ቆጵሮስ ሳይደርስ በመርከብ ውስጥ ሳለ ግንቦት ዐሥራ ሰባት ቀን ዐረፈ። በዐረፈም ጊዜም በመርከብ ጭነው ወደ ቆጽሮስ ከተማ አደረሱት። ካህናቱና ሕዝቡ ሁሉ መጡ ከሳቸውም ጋር ወንጌሎች መስቀሎች መብራቶችና ማዕጠንቶችም የሐዋርያት ጉባኤ ከታላቂቱ ቤተ ክርስቲያን እስኪያደርሱት በዝማሬ በማኅሌት በሚገቡት ጸሎቶች ሁሉ እያመሰገኑ ሥጋውን ተሸክመው ካህናቱም መቃብሩን በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ሊያዘጋጁ ወደዱ። ቀድሞ ስለ ክፉ ሥራቸው ቅዱስ ኤጲፋንዮስ አውግዞአቸው የነበሩ ሁለት ዲያቆናት ተቃወሟቸው። ስለዚህም አርባ ቀን ተቀመጠ ነገር ግን ሽታው እንደ ሙታኖች ሽታ አልተለወጠም እንደ አንቀላፋ ሰው እንጂ። ❤ ከዚህም በኋላ አንድ ደግ ዲያቆን ወደ ቅዱስ ሥጋ ቀርቦ "አባቴ ሆይ በእግዚአብሔር ዘንድ አንተ ባለሟልነት እንዳለህ እኔ አውቃለሁ። ብትፈቅድስ ክፉዎች ተቃዋሚዎችን ልታሸንፋቸው ትችላለህ" አለ። የቅዱስ ኤጲፋንዮስንም እጅ ይዞ ምድርን መታባት በዚያንም ጊዜ ሁለቱ ዲያቆናት በግምባራቸው ተደፉ። ለመሞትም ደረሱ ወደ ቤታቸውም ወስደዋቸው ሞቱ። ❤ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም ካህናቱ በሚጣፍጡ ሽቱዎች ገንዙት። በከበሩ ልብሶችም ጠቅልለው ከከበረ ደንጊያ በተሠራ ሣጥን ውስጥ ጨምረው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቀበሩት። ቀድሞ በሕይወቱ ሳለ እንደሚሠራው ከሥጋው ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ኤጲፋንዮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት28 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለአመተ ክርስቶስ መንበርተ ዓለም መኒና። እንተ ረሰየት ይእቲ ንቅዓተ ኰኵሕ መካና። ሠላሳ ወስምነ ዓመታት እስከ ኮና። ይቤሉ ነጋድያን ሶበ ምውተ ረከብና። ውሳጤ በዓት በህየ ቀበርና"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የግንቦት 28። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቅ ዓረብ። ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ። ወኵሎ አሚረ ይድኅርዎ"። መዝ71፥15 ወይም መዝ 4፥4። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 2፥1-21 ወይም ሉቃ 9፥18-23። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ግንቦት ፳፰ (28) ቀን። ❤ እንኳን ለቅዱስ አማኑኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓል ለአርስተ አበው ቅዱሳን ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ ለያዕቆብ ለመታሰቢያቸው በዓል፣ ተጋዳይ ለሆነች ዓለምን ንቃ ለተወች፤ አባ ዳንኤል ስርሷ እንደተናገረ የዓለምን ፍላጎት ሁሉ ድል ለነሣች፤ ለሠላሳ ስምንት ዓመታት አንዴ ወደ ገዳም ይዛ በሔደች ሽንብራና የጽዋ ውኃ ሳያልቅባት በተሰነጠቀ ዐለት ውስጥ ስትጋደል ለነበለች ለቅድስት አመተ ክርስቶስ ለዕረፍት በዓል፣ ለአባ ጳኵሚስ ገዳም ለሆነ በዕረፍቱ ጊዜ ሥጋው አጋዘን ተሸክመው ወደ ሚቀበርበት ቦታ ላመጡቱ ለአባ መርቆሬዎስ ለዕረፍት በዓልና ለታላቁ ለቆጵሮስ አገር ሊቀ ጳጳስ ለቅዱስ ኤጲፋንዮስ ሥጋው ወደ ቆጰሮስ ለደረሰበት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ከሚታሰቡ፦ በሰማዕትነት ከዐረፉ ከአባ ጌርሎስና ከአርባ አምስት ልጆቹ፣ ከአባ ስንጣና ከሰማዕት አጋቦስ ከመታሰብያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ "ሰአሉ ለነ አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ አበወ ሕዝብ ወአሕዛብ ወዘመሐይምናን መክብብ ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ"። ትርጉም፦ የምዕመናን ሹሞች የአሕዛብና የሕዝብ አባቶች ቅዱሳን አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ፈጽማችሁ ለምኑልን አማልዱ፡፡ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታት ላይ፡፡ + + + ❤ ቅድስት አመተ ክርስቶስ፦ አባ ዳንኤል እንዲህም አለ "በረሀም ሳለሁ በሌሊት ተነሥቼ በጨረቃ ብርሃን ተጓዝኹ በተራራ ላይ የተቀመጠ ሰውንም አየሁ ጠጉሩም ሁለመናውን ሸፍኖታል በልቤም ወደርሱ ሔድሁ። በአየችኝም ጊዜ ወደ ተሠነጠቀው አለት ውስጥ ገባች "ሰው ሆይ ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ በረከትህን እንድቀበል እማልድሃለሁ" አልሁ እጅግም አብዝቼ ለመንሁ። ከዚህም በኋላ "አባት ሆይ አልወጣምና ይቅርታ አድርግልኝ" አለችኝ። እኔም "ስለምን አልኋት" እርሳም "እኔ ሴት ነኝ ራቁቴን ስለሆንኩ" አለችኝ። ይህንንም ሰምቼ የለበስኩትን ዐጽፍ ጣልሁላት ለብሳም ወጣች በአንድነትም ጸለይን። ❤ ከዚህ በኋላ "እናቴ ሆይ ከዓለም ወደዚህ ስለመውጣትሽ ይኸንን የተሠነጠቀ ዐለት እንዴት እንዳገኘሽ ንገሪኝ አልኋት"። እርሷም እንዲህ ብላ መለሰችልኝ በወላጆቼ ቤት ድንግል ሁኜ በኢየሩሳሌም የምኖር ነኝ ሁል ጊዜ የሚጎበኘኝ ከእኔ ጋራ የሚነጋገር አንድ መነኰስ ነበር። ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ወደርሱ ሔድኹ በእግዚአብሔር ፊትም ኃጢአቴን እየታመነ ሲአለቅስ አገኘሁት። ደጅንም በአንኳኳሁ ጊዜ አልከፈተልኝም እየተጸጸተ ልቅሶን አበዛ እንጂ። በዚያን ጊዜ በልቤ እንዲህ አልኩ እኔስ ስለ ጒስቍልናዬና ስለ ኃፍረቴ የማላለቅስና የማልጸጸት ለምድነው ወደ ማደሪያዬም ፈጥኜ ሔድኹ ማቅ ለበስኩ በዘንቢልም ሽምብራ በጽዋ ውኃን ያዝሁ። በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ዘንድ እንዲህ ብዬ ጸለይኩ "አቤቱ ጽኑዕ ኃያል ለዘላለሙ ድንቅ የሆንክ የጠፋትን የምታድን የወደቁትንም የምታነሣቸው ወደ አንተ የሚጮኹትንም የምትሰማቸው የታመነችብህ ባሪያህን ታድናት ዘንድ ይቅርታህንና ምሕረትህን ላክ። ከምግባር ድኃ የሆንኩ ባሪያህን ጐብኘኝ ንስሐዬንም ተቀበል። ለረጅም ዘመን ስንቅ ይሆነኝ ዘንድ ይህን ሽምብራና ይህን የጽዋ ውኃ ባርከው ስለ ነፍሴ ድኅነት የአሰብኩትን እንዳላቃልል ለሆዴ ምግብ ስለሚአሻኝ"። ❤ ከዚህ በኋላ ነፍሴን በእግዚአብሔር ላይ በመጣል ወጥቼ ወደ በረሀ ሔድኹ እስከ ኤርትራ ባሕርም ደረስኩ። ከዚያም ወደዚህ በረሀ መጥቼ ይህን የተሠነጠቀ ዐለት አገኘሁ ይህ እግዚአብሔር ያዘጋጀልኝ መኖሪያዬ ነው አልሁ። "እንሆ በዚህ በረሀ ውስጥ ሠላሳ ስምንት ዓመት ሆነኝ ያለ አንተ ሰው አላየሁም። ይህም የዘንቢል ሽምብራና የጽዋ ውኃ ሠላሳ ስምንት ዓመት ከእርሳቸው ስመገብ አልጎደሉም ልብሴ ግን አለቀ ነገር ግን ይህ ቦታ ስለ ልብስ መከለያ ሆነኝ። የበጋ ፀሐይ ትኵሳትም አላስቸገረኝም ቊር ቢሆንም በዕድሜዬ ዘመን ሁሉ አላስጨነቀኝም"። ከዚህ በኋላም ከዘንቢል ካለው ሽምብራ እንድመገብ ማለደችኝ ከሽምብራውም በላሁ ከውኃውም ጠጣሁ። ግን አልጐደለም እግዚአብሔርንም አመሰገንሁት ልብሴንም ልተውላት ወደዱሁ እርሷም "ከዚህ የተሻለ አምጣልኝ" ብላ ይህን እምቢ አለችኝ። ❤ ከዚህ በኋላም ከእርሷ ዘንድ ሔድኩ ወደ ገዳም ደርሼ ስርሷ ለአበ ምኔቱ ነገርኩት። "እርሱም ሁለት ልብስ ያለው ለሌለው አንዱን ይስጥ ብሎ ጮኸ ፈቃደኞች የሆኑም አመጡለት ያን ጊዜም ይዤ ሔድኩ ለአመተ ክርስቶስ ልሰጣት ብዙ ደከምኩ እርሷን በመፈለግ ዞርኩ አላገኘኋትም። ከጥቂት ቀኖች በኋላም አረጋውያን ወደ እኔ መጡ እንህም አሉኝ "ወደ ኤርትራ ባሕር የሚያደርሰውን መንገድ ይዘን በጣኔዎስ በረሀ ስንጓዝ ከዋሻ ዘንድ ሴት ተቀምጣ አይተን ከእርሷ በረከት ለመቀበል ሮጥን ሽሽታ ከዋሻው ገባች ወደ ዋሻውም አፍ ቀረብን ግን አላየናትም። ሽምብራ በዘንቢል ውኃም በጽዋ አግኝተን በላን ጠጣን ያን ጊዜም አለቀ እስከ ንጋትም አደርን። ❤ በነጋም ጊዜ በረከቷን ለመቀበል ቅድስቲቱን ፈለግናት ሙታም አገኘናት ጠጒሯም ሥጋዋን ሁሉ ሸፍኖአል። በዚያም ሰገድን በበዓቷም ውስጥ ቀበርናት የዋሻውንም አፍ በደንጊያ ዘጋን የቅድስቲቱን በረከት እንድንቀበል አድሎናልና እግዚአብሔርን እያመሰገን ወደ በዓታችን ገባን"። በሰማሁም ጊዜ አስቀድሜ ያገኘኋት እንደሆነች አወቅሁ የነገራችኝንም ሁሉ ነገርኳቸው። ጠላት ዲያብሎስን ድል ያደረገው ዘንድ ክፉዎች አጋንንትንም ደካማውን ድኃ የሚረዳ የተመሰገነ እግዚአብሔርን ፈጽመን አመሰገን ነው። ለእግዚአብሔር ይስጋና ይሁን እኛንም በዘመች ቅድስት አመተ ክርስቶስ ጸሎት ይማረን በረከተበም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ አባ መርቆሬዎስ፦ አባ እንጦንዮስ እንዲህ አለ "ለእኔ ገዳም አለኝ ይኸውም የወንድማችን የመርቆሬዎስ ዕረፍቱ ቀረበ" እያሉ ወደእኔ መነኰሳት የመጡበት ነው እኔም በረከቱን ለመቀበል ወደርሱ በሒድኩ ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ሳትለይ በተመሥጦ ላይ አገኘሁት። ከመነኰሳቱ ጋራ በእርሱ ዘንድ ሦስት ሌሊቶች ኖርን በሦስተኛዪቱም ዕለት ነፍሱ ተመልሳ ዐይኖቹን ገለጠ በአየንም ጊዜ "ከእኔ ዘንድ ምን ሰበሰባችሁ" አለን እኛም የሆነውን ሁሉ ነገር ነውና ከዚህም በኋላ ያየውን እንዲነግረን ለመነው እርሱም የሚያስፈራ ሰው ወደርሱ መጥቶ ነፍሱን እንደወሰደ የኃጥአንን ሥቃይ እንዳሳየው የጻድቃንንም ዋጋቸውንና ተድላቸውን እንዳየው ነገራቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ወዮ ብሎ በማልቀስ በግምባሩ ከምድር ላይ ተደፋ እንዲህም አለን "ወንድሞቼ ሆይ ወደ ሐራጺት ገዳም ወደ አባ ጊዮርጊስ ማደሪያ ሒዱ። ከእኔ ጋራ የነበረውን መለአክ መርቆሬዎስን መልሳችሁ በትንሽ በዓት ውስጥ ሲጋደል የኖረ ጊዮርጊስን አምጡት ሲል ሰምቼዋለሁና ይቺም ሥጋው አስቲቋጠር የተጋደለባት የጨው በረሀ ናት"። ወንድሞች መነኰሳትም በሔዱ ጊዜ ሙቶ አገኙት ወደዚህ ገዳምም አምጥተው ቀበሩት። ይህም ወንድም መርቆሬዎስ እንደ ደረቀ እንጨት እስቲሆን ሥጋውን እጅግ አሠቃየ።

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ገዛዛ አቡዬ (አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል፣ በአባ ጽጌ ድንግልና ወደ ሌሎች አድባራት ገዳማት። ❤ የጉዞ አላማ፦ የቅዱስ ላሊበላ ጽላት ለመጀመርያ ጊዜ ለማስገባት እና ለገዳሙ የተሠራ የልማት ሥራ ለመመረቅ የተዘጋጀ ጉዞ። ❤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በደበብ ወሎ በወግዲ ወረዳ የሚገኘው፤ ቅዱስ ላሊበላ ከባለቤቱ ከቅድስት መስቀል ክብራ ጋር ለመጀመርያ ጊዜ የፈለፈለው ዋሻ ቤተ መቅደስ፤ ከ950 ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረው፤ ከአዲስ አበባ በ625 ኪ.ሜ እርቀት ላይ የሚገኘው ወደ ምስካየ ቅዱሳን ዋሻ ገዛዛ አቡዬ (አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም) እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ለመጀመርያ ጊዜ የቅዱስ ላሊበላ ጽላት ለማስገባት እና በገዳሙ ላይ ሊሰሩ ከታሰቡት የልማት ሥራዎች መካከል ጥቂቶቹን ለማስመረቅ አርብ ሰኔ 3 ጀምሮ እስከ ሰኞ ሰኔ 6 ቀን 2014 ዓ.ም ወደ ገዳሙ መንፈሳዊ የበረከት ጉዞ የተዘጋጀ ሲሆን እርሶም ትኬቱን በመቁረጥ በገዳሙ ላይ ይገኙልን ዘንድ በጻድቁ ስም አደራ እንላለን። በጉዞአችን ወቅት የሚነሳለመን ገዳም 1. የታላቁ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን ገዳም። 2 የአቡነ በጸሎተ ሚካኤልን ገዳም 3 የአባ ጽጌ ድንግል ገዳም 4 መርጦረ ማርያም 5 ድማ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንሰለማለን። ❤ የጉዞ መነሻ አርብ ሰኔ 3 ቀን 2014 ዓ.ም አራዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን። ❤ የጉዞ መመለሻ ቀን ሰኞ ሰኔ 6 ቀን 2014 ዓ.ም። ❤ የጉዞ ወጋ ከነሙሉ መስተንግዶ ጋር 1650 ብር። ❤ የጉዞው አዘጋጅ፦ ቤተ ጳውሊ የጉዞ ወኪል። ❤ የጉዞ ትኬት ለማግኘት፦ 09 11 41 48 52 ቀጨኔ፣ አዲሱ ገቢያ፣ ሜክሲኮና ሰንጋ ተራ አካባቢ ይደውሉ። ❤ ለበለጠ መረጃና ትኬቱ ለማግኘት አራዳ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በማኅበሩ ቢሮ ገነተ ጽጌ ሕንጻ ላይ፦ 09 64 02 02 02፤ 09 12 69 98 25 ይደውሉ። https://t.me/Eotcw