cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

መዝሙር ከነ ግጥሙ

የብዙ ክርስቲያኖች ችግር መዝሙር ማግኘት ሳይሆን የመዝሙሩን ግጥም ጠንቅቆ ማወቁ ነው። ይህ ቻናል አዳዲስ እና ቆየት ያሉ መዝሙሮችን ከነ ሙሉ ግጥማቸው ያደርሳቹሃል። ከእኛ ጋር ይሁኑ ለ ወዳጆም ዝማሬዎቹን ይጋብዙ ተባረኩ https://t.me/mezemur_lyrics

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
13 196
Suscriptores
+1424 horas
+1657 días
+69130 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

✴️ውድ የቻላናችን ቤተሰቦች በዚህ ድንቅ 💽አልበም ውስጥ የሚገኙ  💿መዝሙሮች እነዚ ናቸው። እንደምትባረኩባቸው እርግጠኛ ነኝ:: የግጥም ስህተት ካለ በዚህ ንገሩን እንዲሁም ሀሳብ አስተያየት ካላቹ አድርሱን🙏 👇 @Eyosii @DN1Asaf2 💛የወደዳቹትን መዝሙር ለምትወዷቸው ሰዎች #share አድርጉላቸው። ተባረኩልኝ እወዳቹሃለው💛 🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣👇 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼 @mezemur_lyrics @mezemur_lyrics ❖ ───  ✦ ─── ❖
Mostrar todo...
❤‍🔥 13👍 10😍 4🥰 3
"እሄዳለሁ" 🎙ዘማሪት ሰላም ደስታ🎙 °•°•°•°•°•°•°•°•°•°•°•° እኔማ ፡ አለኝ ፡ ክብር /*2 እኔማ አለኝ አክሊል /*2 ለጽዮን ስብሰባ ተጠርቻለሁ ስራው በእኔ ተቆጥሮ ትገቢያለሽ ተብያለሁ ኩነኔ የለብኝም ከሳሼስ ማነው እርሱ በደሙ አጽድቆ ልጁ ተብያለሁ ከግብጽ ምድር ቢወጡ ወደ ተስፋይቱ ምድር ወደ ውቧ ከነዓን ቢጠሩ ብዙዎቹ ቀሩ ምድረ-በዳ ሳይደርሱ ሳይገቡ ከእርስታቸው/ከግባቸው ጋር ያ ተስፋ ከፊቴ ካለው ጋራ ፍጹም አይወዳደር የኔማ አዲሲቱ ነው እየሩሳሌም በበጉ ቅኔ በሙሴ ዜማ እዘምራለሁ ከመላዕክት ጋራ ክበር ክበር እያልኩ ፊቱ እቆማለሁ እርሱ ስለረዳኝ እኔ እዘምራለሁ እሄዳለሁ ልዘምር ወደላይ ወደላይ እጠራለሁ ልዘምር ወደላይ ወደላይ ከእነአብርሀም ጋራ ከእነይስሀቅ ከእነእስራኤል ጋራ ከእነቅዱሳን እሄዳለሁ ልዘምር ወደላይ ወደላይ እጠራለሁ ልዘምር ወደላይ ወደላይ share♻️share♻️share♻️ 🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ    🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics     ❖ ───  ✦ ─── ❖
Mostrar todo...
Ehedalew(256k).mp34.95 MB
👍 5 1
"ጌታ ይወድሀል" 🎙ዘማሪት ሰላም ደስታ🎙 °•°•°•°•°•°•°•°•°•°•°•° እርቆ ለጠፋ ድርሻውን ይዞ ከአባቱ ቤት ኮብልሎ ወደ ምኞት ጉዞ እጅግ ክፉን ቢያደርግ ቢሆን ተላላ ነፍሱን አልጠቀመም ከፍቶታል በጣም አንድ ቀን ሲመለስ ወደ ልቡ ሀሳቡን ሰብስቦ ሲቃኝ አባቱን ይኖር ነበረ በደስታ አሁን ግን ገብቶታል መሆኑ ጎስቋላ እንደ ልጁ ባያየኝ እንኳን ልሁን እንደ ባሪያ ብሎ ለወሰነ ለቆረጠ ጀግና ገና ሳይገባ ወደ መንደሩ አባቱ አቀፈው በፍቅር እጁ/ልክ እንደበፊቱ ና ና ና ጌታ ይወድሀል ና ና ና ደጁ ላይ ቆሞ ይጠራሀል ና ና ና ውዴ ይወድሀል ና ና ና ደጁ ላይ ቆሞ ይጠራሀል ሁሉ እንዲመለስ በንስሀ ወዶ ይታገሳል ጌታ ዝምታው በኃጥያት አይደለም ማለት በርታ ቀን እጅግ ሳይከፋ ሳይመጣ የጥፋት ውሀ እንዳን በልጁ ግባ ወደ መርከቡ መርከብ ኢየሱስ ነው ማምለጫ መርከብ ወጀቡ ቢያልም ፍፁም አትሰጋበት ና ና ና ጌታ ይወድሀል ና ና ና ደጁ ላይ ቆሞ ይጠራሀል ና ና ና ውዴ ይወድሀል ና ና ና ደጁ ላይ ቆሞ ይጠራሀል ቢጠላ እንጂ ሀጥያትን ኃጥያተኛን ከልቡ ይወዳል ይሉት የለ ወይ ቀድሞም እርሱ ከአመጸኞች ጋር ይወዳጃል መሪ አጥተው ለተበተኑ እውነተኛ እረኛ ነው ይሰበስባል በፍቅር እጁ አቅፎ ያሞቃል በእቅፉ share♻️share♻️share♻️ 🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ    🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics     ❖ ───  ✦ ─── ❖
Mostrar todo...
Na_Geta_Yiwedehal(256k).mp35.09 MB
5👍 1
"ተመርጫለው" ዘማሪት ሰላም ደስታ ተመርጫለው ፡ እኔ ተወድጃለው ፡ እኔ ፀድቄአለው ፡ በእርሱ እንድኖርለት ፡ ለእርሱ (፪x) ፀጋው ፡ በእምነት ፡ አድኖኝ ኢየሱስ ፡ ጽድቁን ፡ አልብሶኝ ስለኔ ፡ በአብ ፡ ፊት ፡ ታይቶ ፈጽሞታል ፡ ሥራዬን ፡ ጨርሶ (፪x) ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ፀጋው ፡ አቁሞኛል ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ምህረቱ ፡ አኑሮኛል ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ቸርነቱ ፡ በዝቶልኛል ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ስግደት ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ልዕልና ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ አምልኮ ፡ ይገባዋል ገና ፡ ከፍጥረት ፡ በቁጣ ፡ ነበርኩኝ በበደሌ ፡ ምክንያት ፡ ሙት ፡ የሆንኩኝ በኃጢአቴ ፡ መብዛት ፡ ሙት ፡ የሆንኩኝ (፪x) ግን ፡ በምህረቱ ፡ ባለጠጋ ፡ ስለሆነ ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ሕይወትን ፡ ለእኔ ፡ አደለ ግን ፡ በምህረቱ ፡ ባለጠጋ ፡ ስለሆነ ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ሕይወትን ፡ ለእኔ ፡ እንኪ ፡ አለ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ፀጋው ፡ አቁሞኛል ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ምህረቱ ፡ አኑሮኛል ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ቸርነቱ ፡ በዝቶልኛል ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ስግደት ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ ልዕልና ፡ ይገባዋል ለዚህ ፡ ጌታ ፡ አምልኮ ፡ ይገባዋል share♻️share♻️share♻️ 🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ    🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics     ❖ ───  ✦ ─── ❖
Mostrar todo...
Temerechalew(256k).mp33.47 MB
5👍 1
" ክብርህ የሌለበት " 🎙ዘማሪት ሰላም ደስታ🎙 °•°•°•°•°•°•°•°•°•°•°•° ሴም ካም ያፌት ትውልዳቸው/*2 በዝቶ ቢታይም ዘር ሀረጋቸው /*2 ሳንበታተን እንዲ ባለንበት ስማችን ይጠራ ብለው ቢነሱ በድፍረት ልባቸው ሳይፈራ መች ተፈፀመ ሀሳባቸው ከመንገድ ቀረ ህልማቸው ክብርህን ሳይሉ ክብሬን ስላሉ በመንገድ ትጥቃቸውን አላሉ አስበኝ እኔን ለክብርህ እንድኖር /*2 አስበኝ እኔን ለሀሳብህ እንድቆም /*2 ክብርህ የሌለበት አይሁን ክብሬ ማትጠራበት አይሁን መጠሪያዬ ማትገኝበት አይሁን መገኛዬ ከእቅፍህ ስር ይሁን መዋያዬ/ማደሪያዬ/*2 ከእቅፍህ ስር ይሁን መዋያዬ ከእቅፍህ ስር ይሁን ማደሪያዬ ከእቅፍህ ስር ይሁን መሞቻዬ መኦዝያን ዝናው ገነነ ከዳር እስከ ዳር ታወቀ /*2 ዝናው በወጣ ልክ ስራውም ደመቀ ሞገሱን እያየ በአምላክ ላይ ታበየ ክብሩን እያየ በአምላክ ላይ ታበየ ..... አለ በፊቱ ሞገስን አነሳ ከሕይወቱ አለም/ሕዝብ የሚያውቀውን መኦዝያ እፍረት አለበሰ በቤቱ አስበኝ እኔን ለክብርህ እንድኖር /*2 አስበኝ እኔን ለሀሳብህ እንድቆም /*2 ለራስ ትኩረት መሮጥ ለማን በጀ ልታይ ባይነት ያልደበቀውስ ማን አለ እየሱስን የሸፈነ ዘመን/ህይወት ከኔ ይራቅ በጥቂቷ ዘመኔ እየሱስ ደምቆ ይታይ /*2 እየሱስ ደምቆ ይታይ እየሱስ ከፍ ብሎ ይታይ እየሱስ ከብሮ ይታይ እየሱስ ደምቆ ይታይ ባከበርከኝ ልኩ ልዋረድ ከፍ ባልኩኝ ቁጥር ዝቅ ልበል ግብዝነት የሌለው ሕይወት በኔ ይገለጥ በፊትህ ዘመኔ/ሕይወቴ ይመረጥ /*2 ለስሜ አልሮጥም ለክብሬ ለታይታ አልኖርም ደፍሬ ያንን ይህንን ለኔ አልልም ካልከበርክበት ጋር አልባክንም ክብርህ የሌለበት.... 🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉን @mezemur_lyrics ❖ ───  ✦ ─── ❖
Mostrar todo...
Kibrehe_Yelelebet(256k).mp36.44 MB
4👍 1
"ያልኖርክበት" ዘማሪት ሰላም ደስታ °•°•°•°•°•°•°•°•°•° ያልኖርክበት ዘመን የለም ካንተ በፊት ዘመን አልነበረም /*2 ዘለዓለምን ፈጥረህ ለዘላለም ትኖራለህ /*2 ከምልህ በላይ ካልኩህም በላይ ትልቅ ነህ ጌታ ዘመን ዘምኖ ያልቀየረህ አንተ ነሃ/*2 ዘመን ዘምኖ ያልለወጠህ አንተ ነሃ ዘመን ዘምኖ ያልቀየረህ አንተ ነሃ ዘመንህ አይቆጠርም አመታቶችህ አያልቁም ለመንግስትህ ፍፃሜ የለውም /*2 ሁሉ ያረጃል ሁሉ ያልፋል እንደ መጎናፀፊያ ይጠቀለላል አንተነትህን በምንም አይለወጥም ጥንትም አሁንም ያለህ ዘለዓለማዊ ነህ ከምልህ በላይ ካልኩህም በላይ ትልቅ ነህ ጌታ ዘመን ዘምኖ ያልለወጠህ አንተ ነሃ ዘመን ዘምኖ ያልቀየረህ አንተ ነሃ ዘመን ዘምኖ ያልለወጠህ አንተ ነሃ ከአማልክት መሀል አንዱ አይደለህም ከጌቶች መሀል አንዱ አይደለህም ከአባቶች መሀል አንዱ አይደለህ ከአዋቂዎች መሀል አንዱ አይደለህ ከሁሉ የበላይ ትልቅ የሆንህ ከብረህ ያለህ ማንም ሳይተካከልህ ከሁሉ የበላይ ሀያል የሆንህ ነግሰህ ያለህ ማንም ሳይተካከልህ የለም የለም እንዳንተ ያለ የለም የለም የለም እንዳንተ ያለ የለም እንዳንተ ያለ የለም እንዳንተ ያለ የለም /*2 share♻️share♻️share♻️ 🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ    🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics     ❖ ───  ✦ ─── ❖
Mostrar todo...
Yalnorkebet(256k).mp36.75 MB
👍 3
"አቤቱ" 🎙ዘማሪት ሰላም ደስታ🎙 °•°•°•°•°•°•°•°•°•°•°•° ምን አቃተህና ማህተሙን ፈትተሀል ሰባቱን ጥቅልል መጽሐፍ ልትከፍት ችለሀል እንቆቅልሽ ፈቺ በማደሪያህ አለህ በዙፋን ላይ ሆነህ ሁሉን ታድሳለህ አቤቱ ውበትህን ማን ይመዝነዋል የዳዊት ስር እና ዘር ስግደት ይገባሃል በማደሪያህ ላይ አለህ/3 ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ በችሎትህ ላይ አለህ/3 ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ አልፋና ኦሜጋ ፊተኛ ኋለኛ ጅማሬህ አይታወቅ ያንተ መጨረሻ ገደብ ልክ የሌለህ ሀያል የእኛ ጌታ በግርማ ሞገስህ ሁሉን የምትረታ አቤቱ ውበትህን ማን ይመዝነዋል የዳዊት ስር እና ዘር ስግደት ይገባሃል የሞትና የሲኦል መክፈቻ በእጅህ ነው በላይ ቢሆንም በታች ስልጣን ያንተ ነው አዶናዩ ጌታ ምንስ ይሳንሀል ቋጠሮውን ልትፈታ ብቻህን ችለሀል አቤቱ ውበትህን ማን ይመዝነዋል የዳዊት ስር እና ዘር ስግደት ይገባሃል በማደሪያህ ላይ አለህ/3 ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ በችሎትህ ላይ አለህ/3 ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ በረከት እና ክብር ጥበብም ምስጋና ለታረደው በግ ይሁን ለዚያ ለገናና ሰቃይን እና ችግር መከራን ያስረሳ ኢየሱስ ብቻ ነው የይኁዳ አንበሳ አቤቱ ውበትህን ማን ይመዝነዋል የዳዊት ስር እና ዘር ስግደት ይገባሃል በማደሪያህ ላይ አለህ /3 ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ በችሎትህ ላይ አለህ /3 ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ share♻️share♻️share♻️ 🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ    🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics     ❖ ───  ✦ ─── ❖
Mostrar todo...
Abetu(256k).mp34.49 MB
👍 6😍 2🥰 1
"ፀጋህ ይርዳኝ" 🎙ዘማሪት ሰላም ደስታ🎙 °•°•°•°•°•°•°•°•°•°•°•° አብልጬ/አብዝቼ እንድወድህ አብዝቼ/አብልጬ እንዳፈቅርህ አንተን ከመካድ ይልቅ እራሴን እንድክድ ፀጋህ ይርዳኝ ፀጋህ ይርዳኝ እኔ እንኳን በአቅሜ እጅግ ደካማ ነኝ ሞት ቢሆን እስራት አንተን ለሚያገኝህ እኔ እራሴን እሰዋለሁ ከአንተ አይበልጥብኝም ብሎ ፊትህ እንዳላልማለ በገረድ ፊት ካደ ፀጋህ/ኃይልህ ዳግም አቆመና ስለአንተ መስካሪ/ሰባኪ አረገ ፀጋህ ይርዳኝ ፀጋህ ይርዳኝ እኔ እንኳን በአቅሜ እጅግ ደካማ ነኝ ብዙ ፍቅርን መግለጥ በአፌ መቻሌ ለተግባር ፈጥኜ/ቸኩዬ ግን አንተን መካዴ ከአንተ ያነሰን ነገር ማድነቄ ቀርቶ እንድወድህ/እንድመስልህ ፀጋህ ይርዳኝ አብዝቶ /*2 ፀጋህ ይርዳኝ ፀጋህ ይርዳኝ እኔ እንኳን በአቅሜ እጅግ ደካማ ነኝ ውድህ ያረከኝን አንተን ውዴ እንዳደርግህ ከነፍስህ/ከክብርህ በላይ የወደድከኝን እንድወድህ ጸጋህ/ሀይልህ በረዳኝ መጠን እንድቀርብህ እኔም እሻለሁ የእውነቴን ልወድህ/ልመስልህ ፀጋህ ይርዳኝ ፀጋህ ይርዳኝ እኔ እንኳን አቅሜ እጅግ ደካማ ነኝ share♻️share♻️share♻️ 🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ    🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics     ❖ ───  ✦ ─── ❖
Mostrar todo...
Tsegaw_Yirdagne(256k).mp35.79 MB
👍 2 2
"ፍቅር ነህ" 🎙ዘማሪት ሰላም ደስታ🎙 °•°•°•°•°•°•°•°•°•°•°•° እንዳንተ የወደደኝ ማነው እንዳንተ ያፈቀረኝ ማነው እንዳንተ ያቀረበኝ ማነው የምክንያተ ውጤት ያልሆነ ፍቅር ያለው ማነው እንዳንተ የወደደኝ ማነው እንዳንተ ያፈቀረኝ ማነው እንዳንተ ያቀረበኝ ማነው የሰበብ ውጤት ያልሆነ መውደድ ያለው ማነው ኢየሱስ*12 ፍቅር ነህ እውነተኛ ወዳጅ ነህ እውነተኛ አባት ነህ እውነተኛ ከነፍስህ በላይ ወደኸኛል ከክብርህ በላይ ወደኸኛጨ ከስምህ በላይ ወደኸኛል ከነፍስህ በላይ ወደኸኛል ከራስህ በላይ ወደኸኛል የተናቀ እጅግም የተጠላ የህማም ሰው ደዌንም እነደሚያውቅ ብዙ ፊቱን እነደሚሰውር ገዢ ለሻጭ እንደሚገምት እንደ በግ ዝም ያለ ለእርድ እንደሚነዳ ጠቦት አፉን ያልከፈተ(*2) ፍቅር ነህ እውነተኛ ወዳጅ ነህ እውነተኛ አባት ነህ እውነተኛ ከነፍስህ በላይ ወደኸኛል(*2) ከክብርህ በላይ ወደኸኛል ከስምህ በላይ ወደኸኛል ከነፍስህ በላይ ወደኸኛል ከራስህ በላይ ወደኸኛል ከጥም ሊረኩ ከራባቸው ሊጠግቡ ብዙዎች ይቀርባሉ ሲያጡ ይሸሻሉ ያለ ሰበብ/ምክንያት ወዶ የቀረበኝ ማን አለ የተጠማ መስለህ ጥሜን ያረካህ አንድ አንተ ብቻ ነህ(*2) ፍቅር ነህ እውነተኛ ወዳጅ ነህ እውነተኛ አባት ነህ እውነተኛ ከነፍስህ በላይ ወደኸኛል(*2) ከክብርህ በላይ ወደኸኛል ከስምህ በላይ ወደኸኛል ከነፍስህ በላይ ወደኸኛል ከራስህ በላይ ወደኸኛል share♻️share♻️share♻️ 🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ    🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics     ❖ ───  ✦ ─── ❖
Mostrar todo...
Selam_Desta_እዉነተኛ_Ewnetegna_New_Ethiopian_Gospel_Song_2020256k.mp35.91 MB
🥰 3 1
"አልደራደርም" 🎙ዘማሪት ሰላም ደስታ🎙 °•°•°•°•°•°•°•°•°•°•°•° ሃይማኖቴን እምነቴን/ማኅተሜን አንተን ጌታ ከላይ ያኔ ያገኘሁህ የእኔን ቤዛ ያምላኬን ፀጋ በመሴሰን አለውጥም ንጉሤን አንተን ኢየሱሴን አልክድም አልደራደርም በአንተ ጉዳይ እንደ ቀልድ አላይም የሆንከውን መስቀል ላይ ከአብ ዘንድ ያገኘሁህ ውዱ ስጦታ አንተ ነህና የእኔ ጌታ /*2 በመረቀልን በአዲሱና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስቲቱ በኢየሱስ ቀርበን የእውነትን እውቀት ካገኘን ወይ ወደን ከሃጥያት እንዴት እንፀናለን ወደን ሃጥያትን እንዴት እናደርጋለን አንደራደርም በአንተ ጉዳይ እንደ ቀልድ አናይም የሆንከውን መስቀል ላይ ከአብ ዘንድ ያገኘንህ ውዱ ስጦታ አንተ ነህና የእኛ ቤዛ /*2 share♻️share♻️share♻️ 🟡የመዝሙር ግጥሞችን ከፈለጉ ይህን link👇ተጭነው ይቀላቀሉ    🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣⬇️ 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚  🎼      @mezemur_lyrics      @mezemur_lyrics     ❖ ───  ✦ ─── ❖
Mostrar todo...
Alederaderem(256k).mp33.30 MB
👍 3