cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

አማርኛ እና አረበኛ ደዓዋ

ይህ ቻናል ዋነኛው አለማው የፈዘዙ ልቦችን ማንቃት ፣ የተዘነጉ ልቦችን ማስታወስ ፣ የደረቁ ልቦችን ማርጠብ ነው ። " ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ፣........" ቁርኣን (3:104) 👉 ሀሳብ አስተያየት ካሎት Babubi👈

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
449
Suscriptores
Sin datos24 horas
-37 días
-2830 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ሀብት ማግኘት የለማኝ ምኞት ነው ፍቅርን መሻት ግን የንጉስ ምኞት ነው ይላሉ ፈላስፋዎች... #እኔ_ግን_ሁለቱም_ቢኖሩኝ_አልጠላም 😉 እናንተስ ምን ትላላቹ
Mostrar todo...
የዛሬው ሀዲስ (part60) وعن أبي هريرة رضي الله عنه: أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: ((اتقوا اللاعنين)) قالوا: وما اللاعنان؟ قال: ((الذي يتخلى في طريق الناس أو في ظلهم)). رواه مسلم. አቡ ሁረይራ رضي الله عنه እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم:- "እርግማንን የሚያመጡ ሁለት ነገሮችን ተጠንቀቁ" በማለት ተናገሩ። "እነርሱ የትኞቹ ናቸው?" ተብለው ተጠይቀውም:- "ከሰዎች መተላለፊያ መንገድ ወይም ከጥላዎቻቸው ላይ መጸዳዳት ናቸው" ሲሉ መለሱ። (ሙስሊም) Join and share @yezarewhadis @yezarewhadis @yezarewhadis
Mostrar todo...
እስልምና ግን ምን አይነት ውብ እምነት ነው‼ አንተ ና በዚህ ውጣ ወይም ግባ ብሎ የሚያስገድድህ አንድም አካል የለም። ፍርድህ በፍትሐዊው አምላክ በአንድ አላህ ብቻ ነው። ሰው'ማ ቢሆን አልቆልን ነበር። አል-ሐምዱ ሊላህ!
Mostrar todo...
ከህይወት ፀጋዎች አንዱ ያለምንም ምክንያት የሚወድህ በሩቁ ዱዓ የሚያደርግልህ ለራሱ የሚወደውን የሚወድልህ ሰው መኖሩ ነው፡፡
Mostrar todo...
ቀጣይነት ያለው መልካም ተግባር ለቀጣዩ አለም ቤታችን… ከአቡ ሁረይራ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ۔إِذا ماتَ الإنْسانُ انْقَطَعَ عنْه عَمَلُهُ إِلّا مِن ثَلاثَةٍ: إِلّا مِن صَدَقَةٍ جارِيَةٍ، أَوْ عِلْمٍ يُنْتَفَعُ بِهِ، أَوْ وَلَدٍ صالِحٍ يَدْعُو له.﴾ “የሰው ልጆች ስራ በሚሞቱ ግዜ ይቋረጣል ሶስት አይነት ነገሮች ሲቀሩ። ቀጣይነት ያለው ሰደቃ ‘ምፅዋት’ ወይ ደግሞ ሰዎችን የሚጠቅም እውቀት ወይ ደግሞ ለሱ ዱዓ የሚያደርግለት መልካም ልጅ ናቸው።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1631
Mostrar todo...
የምር አግቡ ብልህ ባል ሚስቱን አስማተኛ ያረጋል። ውዴ አንቺ እኮ ባለሞያ ነሽ የነካሽው ሁሉ ይጣፍጣል ዘይት ባታደርጊስ ሲለኝ በደስታ ተፍነክንኬ ስተው ደሞ በርበሬ ምን ጥቅም የኔ ፍቅር ተይው ዝም ብለሽ ስሪው ሲል ስተው ቲማቲም ሲል ስተው ድንች ሲል ስተው........ ሁሉንም ትቼ አሁን ቁርስ ምሳ እራት ተሞጋግሰን ጠግበን ነው የምናድረው😊 ብላ ነገረችኝ መሰላችሁ ታድላ 😂😍
Mostrar todo...
#አላፊዋ_ዱንያ ! ~~~~ አይ የዱንያ ነገር በጣም ይገርምሀል ትልቅ ትንሽ ክስተት ሥንቱ ታይቶ ያልፋል ሁሉም እንደ ቧልታ ያለፈ ይሆናል ደስታና ጭንቀቱ ለቅፅበት ይረሳል የትናንት አይመስልም ጌዜያት ያስቆጥራል                        / ደግሞ ሌላ ታሪክ ይመጣና እንደ አድሥ ከፊቱ የሚሻል ወይንም የሚብሥ በደሥታ የሚያሥቅ ወይም የሚያሥለቅሥ ወይ ራስ የሚመልጥ ወይ  አንጀት የሚያርሥ ባጭር የሚያቋርጥ ወይ ምኞት የሚያደርሥ                  / #ያም_አለ #ያም_ሆነ ተከናውኖ ያልፋል #መልካም_ሥራ #መጥፎ ሁለቱ ይቀራል አሏህ በጥበቡ ፅፎ ያስቀምጣል እኩልኛው ሚዛን ያዛኔ ይቀርባል ሁሉም በየ ሥራው ዋጋውን ያገኛል                   / ታድያ ለዚህ ሂዎት ለሆነ ትርምስምሥ ይዞን ለሚጋልብ እንደ ሜዳ ፈረሥ ኋላን ሥናበጃጅ ፊት ለሚገሰግሥ በሩጫ ላይ ያለን ጥሎ ለሚያሥነክሥ       ሥለዚህ መንቃት ነው ቀንጣጤ በመንከስ       መፋዘዝ አይሻም መሞቻ ቀን ድረሥ       ቶሎ መፍጠን ይሻል ወደ አሏህ መመለሥ @AmharicAndArbicDawa
Mostrar todo...
ሰው ሲሄድ የምትሄዱ፤ ሰው ሲቆም የምትቆሙ ደካማ ፍጡር አትሁኑ። ሕይወታችሁን በማንም ላይ፣ ከማንም አንፃር አትመስርቱ። ከአላህ በታች በራሳችሁ ተማመኑ። ራሳችሁን ቻሉ። ስትወጡ ሁሌም ቢስሚላህ ተወከልቱ ዐለሏህ በሉ። መመካት በአላህ ብቻ በቃ።
Mostrar todo...
የዱንያ ባህር ሁሉ አንድ ጀሀነም ፍም እሳትን ማጥፋት አይችሉም። ነገር ግን ከአላህ የመጣች ትንሽዬ እንባ የጀሀነም እሳትን ልትጋርድልህ ትችላለች። منقول
Mostrar todo...
ــــــ ــــــ ــــــ ﷽ ــــــ ــــــ ــــــ     ❁ ❁❁ ❁ 💡ቁርአን❗️ 💡❁ ❁❁ ❁ 💎ታላቁ ዓሊም ኢማም ኢብኑ አል ቀይም (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦   📚 «ቁርአንን በአፅኖት(በማሰተንተን) በመቅራት ያለውን ጥቅም ሰዎች ቢያውቁ ኖሮ በእርሱ ብቻ ከሌሎች ነገሮች ይብቃቁ ነበር። አንድ አንቀፅ በማስተንተን መቅራት ያለ ግንዛቤና ማስተዋል ከ(ማኽተም) ሙሉውን ከመጨረስ ይሻላል። (ምክንያቱም)፦ ➫ይህ (ማስተንተንና ማሰተዋል) ነውና ቀልብን የሚጠቅመው! ኢማንን የሚያስገኘው እንዲሁም የቁርአንን ጥፍጥናን እንድንቋደስ የሚያደርገው!»                                      📃[ሚፍታህ ዳረ-ሠዓዳህ  1/553] 🤲አላህ ቁርአንን ለማንበብ፣ ለመገንዘብና ጥፍጥናውንም ለመቅመስ በሱም ለመተግበር ይወፍቀን!                    ــــــ ❁ ❁❁ ❁ ــــــ    ✍ አቡ ሀማድ #መልዕክት
Mostrar todo...