cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

❤የ ፍቅር እውነታዎች💕

💘የ ፍቅር ጥቅሶች 💑 💘ጣፋጭ የፍቅርአባባሎች💕 💘 Inspiration words 💘ግጥም❤ 💘 ቲክቶክ ቪድዮዎች 💘 አጫጭር ልብ ወለዶች ሁሉንም የምታገኙበት ቻናል ነው https://t.me/H_A_P_P_Y_N_E_S

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
1 096
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

​​​💞የድሀ ልጅ ፍቅር ♦ክፍል 26♦ 〰የመጨረሻ ክፍል🔚 👉በእዉነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ👈 ሜላትን ከስራ ስትወጣ ጠብቄ ተከትያት ሄድኩ ሆቴል ውስጥ ከሴቶቹጋ ተደባልቃ ስትጠጣ ወደ እሷ ተጠግቼ ሰላም ካልኳቸው በኃላ ...የሜላት በቁጣ እኔን ማየት የሴቶቹን ማፍጠጥ ሳይ የመጣሁበትን መናገር ጀመርኩ... ሁሉም ዝምታን መርጠዋል ያጨሳሉ ይጠጣሉ...ሜላት በእውነት ብትዝናኚ ምንም አይመስለኝም ግን ከማን ጋ እየተዝናናሽ እንደሆነ አላወቅሽም አልኳት ...ምን ማለት ነው አለችኝ? ስለ ሴቶቹ ምንነት በደንብ ነገርኳት ሴቶቹ ደነገጡም ተናደዱ ምን አገባህ አሉኝ...ግን እኔ ሚስቴን ከእነሱ መንጋጋ ውስጥ ማውጣት ስለነበረብኝ ሁሉንም ምን እንደሚሰሩ ነግሪያት እሷም ከእነሱ ጋር ከቀጠለች ትዳራችን እንደሚያበቃለት ነግሪያት ደህና እደሩ ብዬ ወደ እናቴ ቤት ሄድኩ.... ሜላት እንደዛ ካልኳት በኃላ ወደ ቤቷ ተመልሳ ነገሮችን እንዴት ማስተካከል እንዳለባት እንደምታስብ እርግጠኛ ነበርኩ...ምክንያቱም ሳታውቅ ዝም ብላ ነበር ጏደኛ ያደረገቻቸው..... በሳምንቱ ስራ ውዬ ድክም ብሎኝ ወደ ቤት እየተመለስኩ እያለ ስልክ ተደወለልኝ አነሳሁት ሜላት ታማለች እቤት ቶሎ ድረስ የሚል ድምፅ አሰምተውኝ ስልኩ ተዘጋ...በጣም ደነገጥኩ ወደ እናቴ ቤት መሄዴን ትቼ ወደ እኛ ቤት በፍጥነት መንዳት ጀመርኩ ብዙ ነገር እያሰብኩ ነበር...... እቤት ደርሼ በሩን ከፍቼ ስገባ ግን የጠበቀኝ ነገር ሌላ ነበር የሜላት ቤተሰቦች እናቴ ቅዱስ ወንድሜ በአንድ ላይ ተሰብስበው አገኝኃቸው ..ሜላቴስ አልኳቸው ..ሜላት ከመኝታ ክፍል ወጣች ..ጉልበቴ ላይ ወድቃ ይቅርታ ጠየቀችኝ ..በዛውም የ 3 ወር ነፍሰጡር እንደሆነች ነገረችኝ ይቅርታዋን ተቀበልኩ እናቴንም ይቅርታ ጠየቀች ... እናቴ ምንም እንኳን ይቅርታዋን ብትቀበል ተመልሳ ግን አብራን መኖር እንደማትችል ነገረችን እሽ አልን ምክንያቱም ድጋሚ ሌላ ፀብ እንዲፈጠር ስላልፈለግሁ ነበር በእናቴ ሀሳብ የተስማማሁት ...በጣም ደስ የሚል ምሽት አመሸን ፍቅራችን ወደ ድሮው ተመለሰ ...ቅዱስን የምትንከባከብ ሞግዚት ፈልገን አመጣን ..ስራ ከስራ እቤት መዝናናት ስንፈልግም አብረን ቤተሰብ መጠየቅ ብንፈልግም አብረን ..በቃ ሁሉም ድርጊታችን አንድ ላይ በመመካከር የተሞላ ሆነ..... ቅዱሴም እጅግ በጣም ደስተኛ ሆነ ሌላ ልጅ እህት ሊወለድ እንደሆነ ስላወቀ እሱም ደስተኛ ነው ፍቅራችን ወደ በፊቱ ተመልሶ ቤታችን የደስታ ቤት ሆኗል ...ፍቅር መጣላት መኮራረፍ ..በቃላት አለመግባባት..ሊኖረው ይችላል ግን ከሁሉም በላይ ትዕግስት ይጠይቃል ..ከሁሉም በላይ ግን ""ፍቅር ያሸንፋል" 〰ተፈፀመ🔚
Mostrar todo...
​​​​የድሀ ፍቅር❣️ ክፍል 25 👉በእዉነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ👈 ሜላት የቅዱስን መኝታ ክፍል መግባት ተከትላ .ከእናትህ ቤትና ከእዚህ ቤት አንዱን ምረጥ ብላ ስትጮህብኝ ቅዱሴ የመኝታ ቤት በር ላይ ቆሞ ይሰማ ነበረ ...ሳየው ደነገጥኩ ...ሜላትም አየችው .ቅዱሴ ወደ መኝታ ክፍል ገብቶ ቁጭ አለ ተከትዬው ገባሁ .ሊያናግረኝ አልፈለገም... ሜላትም መጣች .እሷንም መልስ ሊሰጣት አልፈለገም.... ቅዱስ አኩርፏል ስንጨቃጨቅ አይቶን አያውቅም ሜላትም ስሜቷን መቆጣጠር አቅቷት ስለነበር በደንብ ተቆጥታ ነበር የተናገረችኝ...መቼም የእናቴን ቤት መተው አልችልም እናቴ ናትና ...የሚስቴንም ቤት አልችልም ሚስቴ የልጄ እናት ናትና ከዛም በላይ አሁን ላለሁበት ትልቅ መሰዋአትነት ከፍላለችና ብቻ ግራ ገብቶኛል ምን እንደማደረግ አላውቅም.... እኔና ሜላት ከቀን ወደ ቀን ጭቅጭቃችን እየባሰ ቅዱስም እናቴጋ መዋል ማደረን ከመረጠ ሰነባበትን .. ቅዱስ ወደ ቤት እንሂድ ሲባል እናቴ እግር ላይ ተጠምጥሞ አልሄድም ይላል..ግራ ገብቶኛል ፍቅራችን እየተናደ እየተሸረሸረ ከመጣ ቀናቶች አለፉ...የተፈጠረውን እየተፈጠረ ያለውን ለእናቴ እነግራታለው.... ሜላት ሁሉን ነገር እርስት አድርጋው ጠጥታ አምሽታ ትመጣለች በጣም ሰለቸኝ በቃ ከአቅሜ በላይ ሆነችብኝ ምን ላድርጋት... ብመክራት ባስመክራትa ምንም ልትስተካከል አልቻለችም ...አንድ ቀን አምሽታ በጣም ሰክራ መጣች ያን ቀን ግን በጣም በሽቄ ስለነበር በቃ እኔ ከዚህ በኃላ እኔና አንቺ አብረን መሆን አንችልም እናቴ ጋ እሄዳለው አልኳትና እናቴ ክፍል አድሬ ጠዋት ሻንጣዬን አዘጋጅቼ ወደ እናቴ ቤት ሄድኩ..... የእኔና የሜላትን እንደዚህ መሆን ሰው ሲሰማው እጅግ ልገረምበት ይችላል እንዳንድ ሰዎች ገንዘብ ሲበረክት ፍቅር ይጨምራል ይላሉ ግን ውሽት ነው ገንዘብ ሲበረክት ፍቅር ይጠፋል....እኔና ሜላት በድህነቴ የነበረን ፍቅር እጅ በጣም ደስ ይል ነበር ገንዘብ ስናፈራ ብር ወደኛ ሲመጣ ግን ፍቅራችን ተሸረሸረ ...ልጃችንን እንኳን በፍቅር ማሳደግ አቅቶን ሁለታችንም በተለያየ መንገድ መጎዝ ጀመርን.... ብዙውን ጊዜ ቅዱስ እናቴ ጋ ነው የሚውለው ሜላትም ስትፈልግ ትወስደውና አሷ ጋ አድሮ ውሎ ይመጣል ... እኔና ሜላት አንድ ነገር ተነጋግረናል ከቤት ሰወጣ ...መጠጧን ትታ ወደራሷ ተመልሳ ...ትዳራችንን ለመቀጠልም ሆነ ለመፋታት እንደምንወስን ነገር ግን በዚህ ሁኔታ ምንም ነገር መወሰን እንደማልችል ነግሪያት ነበር ... ሜላት ሁሉንም ነገር አየችው ለሳምንታት ያክል እኔ እየተደበቅሁ እያየኃት እሷ እንዳታየኝ እየተጠነቀቅሁ ስከታተላት ከረምክ ..በጣም ተጎሳቁላለች የሚገርመው የያዘቻቸው ጏደኞች እልም ያሉ ጠጪዎች ናቸው አብዛኞቹ እንደ ሹገር ማሚ ነገር ይሰራሉ ..የተረፍት ደግሞ አግብተው የፈቱ ናቸው...ከእነሱ ጋር ሆና ነው እንደዚህ ቅይርይር ያለችብኝ ... አንድ ቀን ማታ ከሰራ ስትወጣ ተከትያት ሄድኩኝ ሆቴል ውስጥ ስትገባ አብሪያት ገባሁ ...በጣም በብዛት ተሰብስበው ወደ ሚጠጡ ሴቶች ተደባልቃ ቁጭ አለች ...ብርጮቆ አምጥተው ቀዱላት ..በአንድ ትንፋሽ ጭልጥ አድርጋ ጠጣችው አጠጣጧ ያስፈራል ...ሳትሰክር ማናገር ስለነበረብኝ ...ተጠጋኃቸው ስታየኝ ደነገጠች ሁሉንም ሰላም አመሻችሁ አልኳቸው ...እዚህ ምን ትሰራለህ ብላ አፈጠጠችብኝ...ምንም አልሰራም መቼም መጠጥ እንደማልጠጣ ታውቂያለሽ ግን አንዳንድ ነገሮችን አንቺ ያላወቅሻቸውን ላሳውቅሽ ብዬ ነው አልኳት....ሴቶቹ ግራ ተጋቡ እሷም አይኗን አፈጠጠችብኝ..... ይቀጥላል ...... 𝗝𝗢𝗜𝗡 🌸🍃 ‌‌‌‌‌••••❥ ♡🤍🌹 ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌@H_A_P_P_Y_N_E_S ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌@H_A_P_P_Y_N_E_S ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
Mostrar todo...
​​​​የድሀ ፍቅር❣️ ክፍል 24 👉በእዉነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ👈 ከስራ አምሽቼ እናቴ ጋ ሄጄ ማምሸት እያማረኝ ሜላቴ ቀድማኝ ከገባች ትናደድብኛለች ብዬ ቅር እያለኝ ወደ ቤት ሄድኩኝ ,...እቤት ስገባ ግን ማንም ሰው የለም ...ቤቱ ጠዋት ትቼው እንደወጣሁት ነው ምንም የተቀየረ ነገር የለውም,...እናቴ ክፍል ስገባ የተኛንበት አልተስተካከለም,..ልብሳችንን አነሳስቼ መኝታውን አነጠፍኩት.... ወደ እኔና ሜላት ክፍልም ስገባ አልተነጠፈም የቀየረችውን ልብስ እንኳን አላነሳችውም... እሱንም አስተካከልኩ ስልኬ ቻርጅ ስላልነበረው እሱን እያደረግሁ ቤቱን ማስተካከል ጀመርኩ.... ማታ እራት የተበላበት ሰአን አልታጠበም,...ብቻ በአጠቃላይ ቤቱ በጣም ያስጠላል ያስፈራል... እሪ ብዬ ብጮህ ደስ ይለኝ ነበር ግን አልችልም..... ስራውን ሰርቼ ጨረስኩ እራት መስራት ፈለግሁ ግን ቅድሚያ ሜላት ጋ ልደውል ብዬ ስልኬን ከፈትኩት ሜላት ደውላ ነበር ግን ባትሪ ዘግቶብኝ ስለሆነ አላየሁትም ...መልሼ ደወልኩ አታነሳም ትንሽ ልጠብቅ አልኩ ....ግን ማንም የመጣ ሰው አልነበረም ...በጣም ተበሳጨሁ ተናደድኩ ግን በቃ ትዕግስት ይኑርህ እያለች ነው እያቴ ያሳደገችኝ..... ጠብቄ ጠብቄ ሰው ሳይመጣ የሜላት ስልክ አልነሳ ሲለኝ እናቴ ጋ ደወልኩ ሰላም አልኳት እቤት ማንም እንደሌለ ነገርኳት እራት ቀርቧል ና አለችኝ ...ተነስቼ እናቴ ጋ ሄድኩ .... እናቴ ጋ እራት በልቼ ትንሽ ተጫውቼ ወደ ቤት ተመለስኩ ... እቤት ስመለስ ሜላት ተኝታ አገኝኃት ቅዱስም ተኝቷል ..... ወደ ሜላት ተጠግቼ ሜላት አልኳት ምን ላድርግህ ?አለችኝ በጣም ደነገጥሁ....ስልክ ስደውልልሽ አታነሽም ስጠብቃችሁ ስትቀሩብኝ እናቴ ጋ ሄድኩ አልኳት ...አሪፍ ነው ደክሞኛል ማረፍ እፈልጋለው አለች....ሜላት እየጠየቅሁሽ ነው ስደውልልሽ ስልክ አታነሽም ለምንድነው? አልኳት.... ሜላት በጣም በመቆጣት ከመኝታዋ ተነስታ ቁጭ አለችና በመጀመርያ ስደውል ለምን አላነሳህም አለችኝ.... ስልኬ ባትሪ ዘግቶ ነበር እንደከፈትኩ ስደውልልሽ አታነሺም ሲጨንቀኝ እናቴ ጋር ሄድኩ አልኳት.... አሪፍ ነው እኔም ስልኬን መኪና ውስጥ እርስቼው ስለነበር ነው አሁን ደክሞኛል ደህና እደር ብላኝ ትታኝ ተኛች..... ነገሩን ላለማክረር ብዬ እኔም ዝም አልኩ ልብሴን ቀይሬ ተኛሁ .....ጠዋት ስነሳ ሜላት ተኝታ ነበር እስከዛሬ እናቴ ነበረች በጠዋት ተነስታ ቁርስ ሰርታ ቅዱስን አልብሳ እኛን የምትቀሰቅሰን አሁን ግን ያ የለም..... እኔም ተነስቼ ቅዱስን ቀስቅሼ ሜላትን ቀሰቀስኳት .... ቅዱስን ልብሱን አልብሼው እኔም ለበስኩ ...ድንገት ቅዱስ አባቢ አባቢ እንደ ትላንትናው እነ እቴቴ ጋ ቁርስ እንበላለን አለኝ?..... በጣም ደነገጥኩ ሜላት አፈጠጠችብኝ ... አይ ቅዱሴ ዛሬ ማሚ የሰራችውን ቁርስ ነው የምንበላው እሽ አልኩትና ወደ መኝታ ክፍል ገባሁ...ሜላት ተከትላኝ መጣች ...ትላንት በጠዋት ልጄን ይዘህ የሄድከው የት ነው አለችኝ ... እናቴ ጋ.. አልኳት ...በጣም ተበሳጨች ግን እናቴን እንደምወዳት ስለምታውቅ ምንም ማለት አልፈለገችም ነበር..... ሜላት ቁርስ እስከምትሰራ እኔ መኝታችንን አነጠፍኩ የሚስተካከለእን አስተካከልኩ ...ቁርስ ደርሶ በልተን ቅዱስን ይዜ ወደ ትምህርት ቤት ሄድኩ በዛውስራዬ ገባሁ ....ስራ ውዬ ቅዱስን ወንድሜ ከትምህርት ቤት አውጥቶት ስለነበር ቅዱስን ላመጣ ሄድኩ ...በዛውም እራት ሳትበላ አትሄድም በለውኝ እራት በልቼ ወደ ቤት ሄድኩ .... እቤት ስንደርስ ሜላት እራት አዘጋጅታ ጠበቀችን ቅዱስ ጠግቧል እኔም ጠግቤያለው ግን በቃኝ ማለት ስላልፈለግሁ ቁጭ አልኩ..... ቅዱስ ወደ መኝታ ክፍል ሲገባ .. ሜላት በጣም ተቆጥታ ከዚህ በኃላ አንዱን ቤት ምረጥ እሺ ወይ እዚህ ወይ እናትህ ቤት ... ስትል ድንገት ቅዱስ መኝታ ቤት በር ላይ ሆኖ ሲሰማ አየሁት........ ይቀጥላል...... 𝗝𝗢𝗜𝗡 🌸🍃 ‌‌‌‌‌••••❥ ♡🤍🌹 ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌@H_A_P_P_Y_N_E_S ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌@H_A_P_P_Y_N_E_S ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
Mostrar todo...
​​​​የድሀ ፍቅር❣️ ክፍል 23 👉በእዉነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ👈 እኔና ቅዱስ ወደ ቤት ተመለስን እቤት ስደርስ ያጋጠመኝ ነገር ግን ያልጠበቅሁት ነገር ነበር ...እናቴ እራት ሰርታ ጠረቤዛው ላይ አስቀምጣ በትንሽዬ ወረቀት ይቅርታ ልጄ,,ብላ ፀፉልኝ አገኝሁት በጣም ደነገጥኩ,...እናቴ ክፍል ተንደርድሬ ስገባ የእናቴም የወንድሜም ልብስ የለም,.እናቴ ቤቱን ትታ ሄዳለች ...በጣም ተበሳጨሁ እንባ ተናነቀኝ ቅዱስ ዝም ብሎ ቆሞ ያየኛል ..... በዛው ቅፅበት ሜላት መጣች ቤቱ እርጭ ብሏል ግራ ገባት የደነገጠች ትመስላለች ደህና ዋላችሁ አለች...ካጎነበርኩበት እንባዬን ጠርጌ ቀና በማለት ሰልይምታ ሰጠኃት ...ውዱሴም ማሚ ብሎ ሄዶ ተጠመጠመባት አቅፋ ሳመችው ...እንዴት በጊዜ እንደመጣች ገርሞኛል ግን ልጠይቃት አልፈለግሁም ..እንዳቀተቀርኩ ዝም አልኳት... ሜላት ዝምታው ስለጨነቃት ምን እንደተፈጠረ ጠየቀችኝ እኔ ሳልሆን ቅዱስ እቴቴ ሌላ ቤት ሄደች..ስትናፍቀኝ መጥቼ አይሀለው ስናፍቅህ ና እሽ ብላኝ ሄደች አላት....እኔ ምንም አልተነፈስኩም..ሜላት ደነገጠች ..ትላንት ለተናገርኳቸው ነገር ይቅርታ ልጠይቃቸው ነበር በጊዜ የመጣሁ በጣም አዝናለው አለች,.ምንም ሳልላት ተነስቼ መኝታ ክፍላችን ገባሁ... ልብሴን ቀይሬ እናቴ መኝታ ላይ ጋደም አልኩ,... ቅዱስ አባቢ ተነሳ እርቦኛል እራታችንን እንብላ አለኝ ....እንቢ ማለት ስላልፈለግሁ ተነስቼ ወደ ምግብ ጠረቤዛው ሄድኩ የቤቱ ቅዝቃዜ በጣም ያስፈራል ለመጀመርያ ጊዜ ነው እንደዚህ ቅዝቅዝ አለ ቤት ውስጥ ስናመሽ ሜላትም ጨንቋታል እንዳታንይግረኝ ምን ትበለኝ ዝም እንዳትል ዝም ማለት አልቻለችም...እሽ ግን የት ነው የሄዱት እኛ እንውጣ እንጂ መቼ እነሱ ይውጥ አልኩ አለች..... ልጎእስ በእጄ የጠቀለልኩትን ትቼ ምንም ሳልል ከመቀመጫዬ ተነስቼ እጄን ታጠብኩና ደህና እደሩ ብዬ እናቴ ክፍል ገብቼ ተኛሁ..... ሜላት የምትይዘው የምትጨብጠው ጠፍቷታል ቅዱስም አባቢ ካንተ ጋር መተኛት እፈልጋለው ብሎኝ አጠገቤ መጥቶ ተኛ,.....ሜላት የበላንበትን አንስታ ክፍላችን ገብታ ተኛች,በአይኔ እንቅልፍ ሳይዞር ነጋ ....እናቴ ጋ ያልደወልኩት ምንም የምለው ነገር ስለሌለኝ ነበር ምክንያቱም እናቴ ቅር ብሏታል ስለዚህ ደውዬ ምንም አልላትም... ዝም ብዬ አደርኩ,ጠዋት ከመኝታዬ ተነስቼ ቅዱስን አስነስቼ ልብሳችንን ቀያይረን ልንወጣ ስንል ሜላት ነቃች ... ወዴት ልትሄዱ ነው ቁርስ ልስራ ስትል አይ ተይው ውጪ እንበላለን ስራ እንዳይረፍድብሽ ብያት .ቅዱስን ይዝኡ ወጥይሁ...ወንድሜ ጋ ደውዬ የቤታቸውን አድራሻ ተቀብዬ እናቴ ጋ ሄድኩ..እናቴ ጋ ደርሰን ገና እናቴን ሳያት ቅዱስ ከመኪናው ወርዶ እየሮጠ እቴቴ ቁርስ ደርሷል እርቦኛል አላት ,...ና ልጄ ቁርስ ደርሷል ብላ እኔን ሰላም ብላኝ ወደ ውስጥ ገባን ....እናቴን ሳያት እንባ ተናንቆኛል ግን በፍፁም ማልቀስ አልፈለግሁም ምክንያቱም እናቴ ሳለቅስ ማየት እንደማትወድ ስለማውቅ..... እናቴ የፊቷ ፈገግታ ምንም አልቀነሰ ...ገብተን የተዘጋጀውን ቁርስ በላን ወንድሜ ጎበዝ ነው ቤቱን አሟልቶታል,...ቁርስ በልተን ቅዱስን ይዜ ልወጣ ስል ሜላት ደወለች.ቅዱስ ከትምህርት ሲወጣ እኔ አወጣዋለው አለችኝ እሽ ብያት ቅዱስን ትምህርት ቤት አስገብቼ እኔም ወደ ስራዬ ገባሁ,..ስራዬን እንደምንም ስሰራ ዋልኩኝ .....ማታም ወደ ቤት ሄድኩ እቤት ስደርስ ግን ማንም ሰው አልነበረም...... ይቀጥላል.......... 𝗝𝗢𝗜𝗡 🌸🍃 ‌‌‌‌‌••••❥ ♡🤍🌹 ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌@H_A_P_P_Y_N_E_S ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌@H_A_P_P_Y_N_E_S ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
Mostrar todo...
​​​​የድሀ ፍቅር❣️ ክፍል 22 👉በእዉነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ👈 እኔና ሜላት አብረን አምሽተን እሷም የእኔን ቀልብ ስትገፍና ስታስደነግጠኝ አምሽታ ሂሳብ ከፈለች ...ምንም አላልኩም አንዳንዴ ብዙ ከመናገር ብዙ ማዳመጥ ይባል የለ,... ለዛ ነበር ዝም ያልኩት,እቤት ገብተን እራት ስለበላን ወደ መኝታ ክፍላችን ተኛን ቅዱሴ ተኝቶ ነበር የደረስነው ምክንያቱም አምሽተን ስለደረስን..... በዚህ ሁኔታ እስከመቼ መቀጠል እንዳለብን ባለውቅም ብቻ ስራ ስለበዛብኝ መጣደፍ ጀመርኩ.....በእኔና በሜላት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት እኔቴ በፈፁም እንድታውቅ አልፈለግሁም ስለዚህ እናቴ ፊት እኔና ሜላት ሰላማዊ እንሆናለን....ታናሽ ወንድሜ ግን አንድ ቀን ስንጨቃጨቅና እናቴን ተለይተን መኖር እንዳለብን ስትነግረኝ ስምቷታል ... እናቴን ማስጨነቅ ስላልፈለገ ብቻ ዝምታን መርጧል..... እኔም ከስራ እቤት ከቤቴ ስራ እንጂ ሌላ የትም ቦታ አልሄድም ልጄን ሳጫውት ማምሸት እመርጣለው ...ለነገሩ የስራ ባልደርቦቼ እንኳን እንዝናና ሲሉኝ ደስታኛ አልሆንም.... እናቴ ሜላት የት ነው የምታመሸው ብላ ስትጠይቀኝ...ሰበብ እየፈጠርኩ እዋሻታለው .አንዳንዴ ቤተስብ ጋ እህቷ ጋ ከጏደኞቿ ጋ ስራ ቦታ ....ብቻ ያልዋሸሁበት መንገድ የለም ... አንድ ቀን እንደተለመደው ቀድሜ ገብቼ ቀኑ ገብረኤል ስለነበር .እናቴ ብና አፍልታ ቤቱን አድምቃ ሜላትን መጠበቅ ጀመርን እንጠጣ ቡናውን ስላት ሜላት ሳትመጣ አይሆንም አለችኝ.....ጨነቀኝ መሽ ሲመሽ እናቴ ተስፋ ቆረጠች ቡናውን እኛው ጠጣንም...ቡናው ልክ ሲያከትም ሜላት መጣች ...እናቴ ሜላቴ ጠብቀንሽ ስትቆይብን ጠጣነው ይቅርታ አለቻት.... ሜላት ግን ትንሽ ጠጥታም ስለነበር ስደብቀው የከረምኩትን በመሀከላችን የተፈጠረውን አለመግባባት ምንም ሳታስቀር ለእናቴ ዘረገፈችላት ...ቀልቤ ተገፈፈ ወንድሜ ሁሉንም ያውቅ ስለነበረ ምንም አላለም እናቴን ወደ መኝታ ክፍል ይዟት ሄደ ...ሜላትን ምን እንደምላት ግራ ገባኝ ትቻት ክፍላችን ገብቼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ ...እንባም ተናንቆኛል ..እናቴ ለመጀመርያ ጊዜ አንገቷን ስትደፋ አየኃት ...በድህነቷ የምትኮራ ማዘን የማትወድ ባላት የምትደሰት ለሰዎች ብርታት የነበረችው እናቴ በሜላት ከልክ ያለፈ አነጋገር አንገቷን ስትደፋ ሳይ ልቤ ተሰበረ በጣም አዘንኩ ...ግን በቃላት ሜላትን ማስከፋት ስላልፈለግሁ ጥቅልል ብሎ መተኛትን ምርጫዬ አደረግሁ.... ጠዋት ከመኝታዬ ስነሳ ሜላት ተኚታለች ዝም ብዬ ልብሴን ለብሼ ወደ ሳሎህ ሄድኩ ማንም ሰው የለም እናቴ ክፍል ስገባ እናቴ ተኝታለች ደህና አደርሽ ብዬ ግንባሯን ስይምኳት ግን የተኛች ስላስመሰለች ዝም አለችኝ ወንድሜ የለም ... ወደ ቅዱስ መኝታ ክፍል ስሄድ ቅዱስ የለም ወንድሜ ትምህርት ቤት ሊያደርሰው ሄዷል....ከቤት ልወጣ ስጣደፍ በስልኬ ሜሴጅ ደረሰኝ ወንድሜ ነበር ላናግርህ እፈልጋለው ከቤት ከወጣህ የት እንገናኝ?ይል ነበር ደወልኩለት ...ቦታ ተቀጣጥረን ወደ ስራ ከመግባቴ በፊት እንዳገኝው ወደ ተቀጣጠርንበት ካፌ አመራሁ.... ቀድሞኝ ደርሶ ስለነበር የተቁመጠበትን በምልክት ነግሮኝ አገኝሁት ....ከቤት ለመጀመርያ ጊዜ ቁርስ ሳልበላ ወጣሁ ....ጠዋት ጠዋት የእናቴ ጉርሻ ሱስ ሆኖብኛል ግን ዛሬ ሳልጎርስም ቅርስም ሳልበላ ከቤት ወጣሁ... ቁርስ አዘዝንና እስከሚደርስልን ድረስ ...ወንድሜ ለምን እንደፈለገኝ መነጋገር ጀመርን ...ወንድሜ ሁሉንም ነገር ቀድሞ እንደሚያው ነገረኝ ቀልቤ ተገፈፈ ...እንዴት እንዳወቀና እስከዛሬም ዝም ያለው ቤት እየፈለገ ስለነበር ነገረኝ...አሁን ግን አታስብ ቤት አግንቻለው አለኝ..... ቁርሳችን ደርሶ ቀረበልን ግራ ገባኝ እናቴ ሳታጎርሰኝ ቀድሜ ጎርሼ አላውቅም .ወንድሜ ልማዴን ስለሚያውቅ .እንካ ጉርስ እናቴ ከእንግዲህ የለችም ልመደው ብሎ አጎረሰኝ .ጉርሻውን ጎርሼ መብላት ጀመርኩ.... ቆይ ግን እስከዛሬ ቢያንስ ለእኔ እንዴት አትነግረኝም አልኩት ላጨናንቅህ ስለማልፈልግ ነው አለኝ ....አሁን ምንም እንዳትጨናነቅ አንተና ሚስትህ ሜላት በሰላም ትኖራላችሁ እኛም ስትናፍቅርን መጥተን እንጠይቃችኃለን አለኝ..... ከስደት ተመልሼ ከቤተሰቤ ተደባለቅሁ ስል ድጋሚ ሌላ ጣጣ ይገርማል,....እኔና ወንድሜ ተነጋገርን ብር እስከዛሬ ለታክሲ ለትምህርት ቤት በቃ ለተለያዩ ነገሮች እያልክ የምትሰጠኝን አጠራቅሜ የ 3 ወር ቤት ኪራይ ከፍያለው አለኝ ደነገጥሁ ለምን አልኩት ችግር የለውም ከፈለግሁ ደግሜ እጠይቅሀለው አለኝ,... እሽ ብዬው እንኡም ወደ ስራ መግባት ስለነበረብኝ ወደ ስራ ሄድኩ..ስራ ከመድረሴ በፊት ለወንድሜ በባንክ አካወንቱ ብር አስገባሁለት,....ከዛም ወደ ስራ ሄድኩ..... ስራ ቦታ ስራ በዝቶብኝ እየተጣደፍኩ ሜላት ደወለች,ሰላም አልኳትና ልታናግረኝ የምትፈልገው ነገር አንዳለ ስትነግረኝ ከስርይ በኃላ ብያት ስልኩን ዘጋሁት ..ስደክም ውዬ ማታ ወደ ቤት ልሄድ ስል ወንድሜ ደወለልኝ ስራ ቦታ በር ላይ ከቅዱስ ጋ እየጠበቅንህ ነው ና አለኝ እሽ ብዬ ወጣሁ ስላም አልኳቸውና ወደ ቤት እንሂድ ስለው እሽ እናንተ ሂዱ እኔ እዚህ ሰው ቀጥሪያለው ብሎኝ ወንድሜ ሄደ,..እኔና ቅዱስ እየተጫወትን ወደ ቤት ሄድን ,.. እቤት ስደርስ ያጋጠመኝ ነገር ግን ያልጠበቅሁት ነገር ነበር........ ይቀጥላል......... 𝗝𝗢𝗜𝗡 🌸🍃 ‌‌‌‌‌••••❥ ♡🤍🌹 ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌@H_A_P_P_Y_N_E_S ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌@H_A_P_P_Y_N_E_S ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
Mostrar todo...
​​​​የድሀ ፍቅር❣️ ክፍል 21 👉በእዉነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ👈 እኔና ሜላት በቃላት አለመግባባት ከመነጋገር ዝም መባባልን ከጀመርን ቀናቶች ተቆጥረዋል እሷም ማምሸቱን ውጪ መብላት መጠጣቱን አዘውትራበታለች እየሄድንበት ያለው መንገድ በጣም መሰዋዕት ሊያስከፍለን እንደሚችል አሰብኩ ሜላቴንም ለማናገር ወሰንኩ .ለልጃችን እንዲሁን ለእናቴና ለወንድሜ ስል እነሱ ፊት ምንም ነገር ተናግሪያት አላውቅም በተለይ ለልጄ,... ጠዋት ስራ ከመሄዴ በፊት ቅዱሴን ትምህርት ቤት አድርሼው በዛው ወደ ስራ ገባሁ የሻይ ሰአት ጠብቄ ሜላት ጋ ደወልኩ ..ማታ አብረን እራት እንድንበላ እንደምፈልግ ነገርኳት ደስተኛ አልነበረችም ግን እሽ አለችኝ,ማታ ምን ብያት እንደምንነጋገር እያሰብኩ ዋልኩ በቃ ግልፅ በግልፅ መነጋገር እንዳለብን አሰብኩ ,እንደዛ ካልሆነ ትዳራችን አደጋ ላይ ነው,.... ከስራ እንደወጣሁ እቤት ሄጄ ልብሴን ቀይሬ ወደ ሜላት መስሪያ ቤት ሄድኩና እሷን ይዤ ወደ አንድ ሆቴል እራታችንን እንድንበላ ገባ ያቺ ፍልቅልቋ ሜላት ሳትሆን ሌላ የማላውቃት ሜላት አጠገቤ ያለቺ መሰለኝ ነገረ ስራዋ ሁሉ በሀይለ ቃል የተሞላ ነው የምናገረውን ነገር በቀጥተኛ ሳይሆን በተዘዋዋሪ እየተረጎመች ትቆጣኛለች,ለደቂቃዎች ዝም ተባባልን ይገርማል ያልጠበቅሁት ነገር አጋጠመኝ..... ዝምታውን ለመስበር ምን ማድረግ እንዳለብኝ ማሰላሰል ጀመርኩ እስኪ በድሮ ትዝታ ልጀምር ብዬ ,.ሜላቴ ታስታውሻለሽ ድሮ ከአመታት በፊት ካፌ ስንገባ እንዳልሸማቀቅ አንተ ክፈል ብለሽ ቅድሚያ የምትሰጪኝ ብር .ብዬ ፈገግ አልኩ.ሜላቴ ግን ፊቷን ቅይርይር አስርጋ የትላንትን ትዝታ ልታመጣና ልታስታውሰኝ ነው እራት እንብላ ያልከኝ አለች ....አፈጠጠችብኝ...እኔም ተርበተበትኩ ,..አ አ አ ስል ገና ልናገር አሁን አብረን እራት እንድንበላ ከፈለግህ ዝም በል አለችኝ ,እሽ ብዬ ዝም አልኩ.... በዝምታ የታጀበ እራት በላን ግን አሁንም አላስቻለኝም ,ሜላቴ ላናግርሽና ልንነጋገር ስለፈለግሁ ነው እዚህ እራት እንድንበላ የጠየቅሁሽ አልኳት ,መነጋገር እንችላለን አይደል አልኳት እንደጥያቄ አድርጌ አወ አለችኝ,.ምን መሰለሽ ሜላቴ ከትንሽ ቀናቶች ጀምሮ ጥሩ አይደለሽም ሙሉ ለሙሉ ተቀይረሽብኛል ሌላው ቢቀር የምትወጂውንና የምትሳሺለትን ቅዱስን በስርዓቱ ማጫወት ትተሻል ለምን ግን አልኳት አይናይኗን እያየሁ.... ሜላቴ በረጅሙ ተንፍሳ አየህ ብላ ጀመረች እኔ ለፍቅራችን የቻልኩትን ሁሉ አድርጌ እዚህ አድርሼዋለው አንተ ግን እየናድከው እያፈረስከው ነው .አለችኝ .ደነገጥኩ ምን አደረግሁ እናቴ ምን አጥፍቼ ነው አልኳት ...ቢያንስ ላንተ ስል የከፈልኩትን መሰዋዕትነት ልታስታውስ ይገባህ ነበር ,አለችኝ ተወሳሰበብኝ እንዴይ አልገባኝም ምን ለማለት ፈልገሽ ነው አልኳት ..... እየውልህ እኔ ከዚህ በኃላ መጨናነቅ አልፈልግም በሰላም ለብቻዬ የራሴ ቤትና የራሴ ህይወት እንዲኖረኝ እፈልጋለው...አየህ የእኔ እህት ሁለት ወልዳ በሰላም እየኖረች ነው እኔ ግን አለችኝ ,ደነገጥኩ ,,ምን አጎደልኩብሽ ,ላደረግሽልኝ ነገር ሁሉ ውለታሽን ለመክፈል እየሞከርኩ ነው የምችለውን ሁሉ አደርጋለው አልኳት ,እሽ የምትችለውን ሁሉ ማድረግ ከቻልክና የትላንት ፍቅራችን እንዲመለስ ከፈለግህ እናትህንና ወንድምህን ትተህ ለብቻችን መኖር እንድንችል አድርግ ...አሁን ወደ ቤት እንሂድ ብላ ሂሳብ ልትከፍል ቦርሳዋን አነሳች ቆይ እኔ እከፍላለው ስላት ...ችግር የለውም መክፈል ልማዴ ነው ብላ ቀልቤን ግፍፍ አደረገችው ........ ይቀጥላል...... 𝗝𝗢𝗜𝗡 🌸🍃 ‌‌‌‌‌••••❥ ♡🤍🌹 ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌@H_A_P_P_Y_N_E_S ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌@H_A_P_P_Y_N_E_S ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
Mostrar todo...
​​​​የድሀ ፍቅር❣️ ክፍል 20 👉በእዉነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ👈 በናፍቆት የሚንከራተቱ አይኖቼን ይዜ ወደ ናፈቁ ቤተሰቦቼ ለመሄድ ጉዞ ጀመርኩ ,ልጄን, እናቴን ,ወንድሜን,ፍቅሬ ,ለማየት በጣም ጏጎቻለው.የበረራው ሰአት ደርሶ .በረራ ጀመርን .ብዙ ነገሮችን እያሰብኩ መድረስ አይቀር በሰላም ደረስን ከፕሌን ወርጄ ዕቃዎቼን ይዜ ወደ ውጪ ወጣሁ የናፈቁኝን ቤተሰቦቼን ለማግኝት በአይኔ መፈለግ ጀመርኩ , ትንሽ መቆም ስለነበረብኝ ቆምኩ ድንገት አባቢ የሚል የህፃን ልጅ ድምፅ ስማሁ ዞር ዞር ብዬ መፈለግ ጀመርኩ ከሰሞች መሀከል ሜላቴ ቅዱስን ታቅፋ እጃቸውን ሲያውለበሉብ አየኃቸው.ሰውነቴን ኤሌክትሪክ የነዘረኝ ያክል ውርር ስትያደርገኝ ታወቀኝ ,ተንደርድሬ ሄጄ አቀፍካቸው ወንድሜ እናቴ ልጄ ፍቅሬ ሁሉንም ሳገኝ የደስታ እንባ አነባሁ ሁላችንም ተቃቅፈን ተላቀስን ለ 3 አመት ያጣሁትን የቤተስብ የልጅ ፍቅር መልሼ አገኝሁት ... የፍቅር የደስታ እንባ ተራጭተን ወደ ቤት አመራን ልጄ ቅዱስ እኔ ላይ ተጠምጥሞ የሚላቀቅ አይመስልም ,ስለእኔ ጥሩ ጥሩ ነገር እየነገሩ ነው ያሳደጉት በዛ ላይ ሁሌም ስደውል አወራዋለው በጣም እንደምወደው ሁሌም ስለምነግረው በቃ የናፈቀውን ናፍቆት እኔ ላይ ጥምጥም በማለት እየተወጣ ነው,እቤት ስንደርስ በጣም ደስ አለኝ ,ከጠበቅሁት በላይ አሪፍ ኑሮ እየኖሩ ነው .ሁሉ ነገር ተሟልቶላቸዋል .ይበልጥ ተደሰትኩ...... ከቤተሰቦቼ ጋር ሆኜ የደስታ ጊዜ ማሳለፍ ጀመርኩ ሁሉም ነገር መልካም እየሆነ መጣ ሜላቴም መነጫነጫንም ሆነ መቆጣቷን ትታለች ደስተኛ ነች .ልጃችንን በሳምንት አንድ ቀን እሁድ ዘና ለማለት ከፈለጉ ከከተማ ውጪ ካልሆነም አሪፍ መናፈሻ ሄደን ትንሽ እንዝናናለን ያ ነው መሰለኝ ሜላትን ደስተኛ አድርጏታል ...እኔም የራሴን ስራ ለመጀመር በዝግጅት ላይ ነኝ ,እናቴ ስራ ስለሌላት ቅዱስት መንከባከብ ሆኗል ስራዋ .ታናሽ ወንድሜ በጣም ጎበዝና ጠንካራ ተማሪ ሆኗል .በቃ ከእኔ በላይ ጎበዝ ተማሪ ሆኗል በጣም በሱ ደስተኛ ነኝ... ህይወት እንደ አዲስ እየተቀየረ ነው ሁላችንም እንደ አዲስ ህይወት የምንጀምር ነው የሚመስለው በተለይ እኔ ,ለእኔ ሁሉም ነገር አዲስ ነው የራሴን ስራ መስራት መጀመሬ አስደስቶኛል.ሜላቴም ስራዋን በደንብ እየስራች ነው ,ልጄ መዋለ ህፃናት ገብቷል .እናቴ ሄዳ ታመጣዋለች እሷው ስትንከባከበው ትውላለች.... ሁሉም ነገር እየተቀየር $ገንዘብ እየመጣ በስራ መወጥር ሲጀመር ፀባይም እየተቀየረ መጣ!! እኔ ፍፁም እናቴንና ወንድሜን ትቼ ለብቻዬ ቤት ተከራይቼ የመኖር አላማዬም ፍላጎትም ኖሮ አያውቅም ሜላት ግን ,ብር ስላለን የራሳችን ቤት የራሳችን ህይወት እንዲኖረን እፈልጋለው ማለትን ተያይዘዋለች . # ገንዘብ ሲበረክት ፍቅር ይላላል!! የሚባለው እውነት ነው.በእኔ ላይ እየደረስ እያየሁት ነው .በቃ ሜላትም ንግግሯ ሁሉ ገንዘብ ሆኗል, እኔ የማስበው ስለ ፍቅራችን እንጂ ስለ አለን ገንዘብ አውርቼ አላውቅም ምክንያቱም ያገናኝን ፍቅር እንጂ ገንዘብ አይደለም ለሜላት ደግሞ ገንዘብ ማግኝት ብርቋ አይደለም! የሀብታም ልጅ ነጮችን ,እኔ ነኝ እንጂ የድሀ ልጅ ገንዘብ ማግኝት ብርቅ የሆነብኝ ,ግን ገንዘብ ማግኝታችን በፍፁም ፍቅራችንን ያላላዋል ብዬ አስቤ አላውቅም እንዲያውም እንደሚጠነክር ነበር የማስበው ግን አልተሳካልኝም,.ሜላት ድሮ የሴት ጏደኞች አልነበሯትም አሁን ግን ብዙ ጏደኞች አፍርታለች,ከእነሱ ጋር ነው ውሎዋ ምሳም እራትም ውጪ ትበላለች ,ለሁለታችን ጊዜ መስጠት አቁማለች በቃ ግራ ግብት ብሎኛል ሁሌ መሸማቀቅ ስልችት ብሎኛል ቀድሜ ስራ ጨርሼ እቤት ስገባ እሷ ግን አምሽታ ትመጣለች ,ሁኔታዋ አስፈርቶኛል...... ይቀጥላል...... 𝗝𝗢𝗜𝗡 🌸🍃 ‌‌‌‌‌••••❥ ♡🤍🌹 ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌@H_A_P_P_Y_N_E_S ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌@H_A_P_P_Y_N_E_S ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
Mostrar todo...
​​​​የድሀ ፍቅር❣️ ክፍል 19 👉በእዉነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ👈 የልጃችንን ልደት አብሪያቸው ማክበር ባልችልም በስልክ ተደዋውለን እብሬያቸው ማክበር ጀመርኩ .በቃ የሜላት እህቶች እና እናቷ አብረው እናቴ ቤት ተሰብስበው እያከበሩ ነው,.እኔም አብሪያቸው የሆንኩ ያክል ተሰማኝ,በ(Skype ) ስለነበር የምናወራው,ሁለም ነገር ይታየኛል ሜላቴ ጠጋ አለችና ቆይ ውዴ ወደዚህ አትይ አለችኝ እሽ አልኳት. ከደቂቃዎች በኃላ ሜላት ውዴ አለችኝ ዞር ብዬ ሳይ ከፊት ለፊቴ ትልቅዬ ኬክ አየሁ ,አያምርም አለችኝ ያምራል ውዴ አልኳት በደንብ እየው አለችኝ ስልኩን አስጠግታ አሳየችኝ .. የሚገርም ነገር የልጃችን ስም"ቅዱስ ቢኒያም"ይላል እንዴ የኔ ፍቅር ቅዱስ አልሽው አልኳት አወ ,ባይሆን ሁለተኛ ስንወልድ ናታኒኤል ,እንለዋለን አለችኝ በጣም ደስ አለኝ ዋውው የኔ ፍቅር አመሰግናለው አልኳት.... አብረን አክብረን ኬኩ ከተቆረሰ በኃላ ቻው ብያቸው ስልኩ ተዘጋ እኔም ወደ ጏደኞቼ ጋር ሄድኩ ከእነሱ ጋር ዞር ዞር ስንል አመሸን,ደስ ስላለኝ እራት ጋብዣቸው ተለያየን.የልጄ ስም ቅዱስ ሆኗል .ተመስገን እግዚአብሄር ያሳድግልኝ ..ሜላቴንም ይጠብቅልኝ ... ቀኑ እየነጎደ ቅዱሴም እያደገ እኔም የትምህርት ጊዜየን ወደ ማጠናቀቅ እየተዳረስኩ ነው.ሜላቴ አትመጣም ወይ ጥያቄን ተያይዘዋለች ሁሌ ስልክ ባወራን ቁጥር መቼ ነው የምትመጣ ሳትለኝ ስልኩ ተዘግቶ አያውቅም.ወራቶች ናቸው የቀሩኝ ትንሽ ጊዜ ብቻ እሽ የኔ ፍቅር እላታለው...ባይዋጥላትም እሽ ትለኝና ስልኩ ይዘጋል.... በፊት በፊት እኔ እንኳን ካልደወልኩ ሜሴጅ ካልፃፍኩ ሜላት ፀፋ ታስታውሰኝ ነበር አሁን ግን ሁሉም ነገር ተቀይሯል ስደውል ብቻ ነው የምታወራኝ.ለምን አትደውይልኝም ስላት ይቅርታ ስራ ይዜ በቃ ብዙ ምክንያቶችን ትነግረኛለች እኔም እሽ ከማለት ውጪ ምንም አማራጭ አልነበረኝም የሜላቴ መቀየር አሳስቦኛል. ሁሉም ነገር ተቀይሯል በቃ የትላንት ድህነታችን ታሪክ ሆኖ ዛሬ አሪፍ ህይወት ላይ ነን ግን የሜላት ነገር አሳስቦኛል ወደ ሀገሬ ለመግባት ሁለት ወር ብቻ ነው የቀረኝ ይሄንን እንኳን ነግሪያት ብዙም ደስተኛ አላደረጋትም.አንዳንዴ ልክ ልትመጣ ሰአታት ሲቀሩህ ልመጣ ነው በለኝ እንጂ ወራት ሳምንታት አትበለኝ ብላ ትቆጣለች .አንዳንዴ ታለቅሳለች.ግራ ግብት ሲለኝ እናቴ ጋ እደውላለው እናቴ ግን ምንም እንዳልተፈጠረና .አንዳንዴ ግን መዝናናት እፈልጋለው ቢያንስ ልጄን ይዜ ከቤት መውጣት እፈልጋለው እያለች ስታማርር እስማታለው አለችኝ እናቴ.... ሜላቴ ይሄ ስሜት ስለተሰማት ይሆናል የምትቆጣና የምታለቅሰው ብዬ አሰብኩ,ግን መሄጃዬ ስለደረስ ,ዝም እላታለው ,ልጅህ አስቸግሮኛል ቻው ብላ ስልኩን ስትዘጋው ቢከፋኝም ዝምታን መርጫለው በእሷም አይፈረድም .3 አመት ዮኒቨርሲቲ,3 አመት ለትምህርት አወስትራሊያ.6 አመት ሙሉ ብቻዋን መሆኗ ጎድቷት ይሆናል ብዬ ስለማስብ ዝምታን መርጫለው... የናፈቅሁትን ሀገር የናፈቅሁትን ቤተሰብ የናፈቅሁትን ነገር ሁሉ ላገኝው ወራቶች አልፈው ቀናቶች ቀናቶች አልፈው ሰአታት ቀርተውታል,በቃ ጏደኛቼ ትንሽ እዚህ ስራና ሂድ ለመሄድ አትቸኩል ሲሉኝ እኔ ግን መሄድን መርጬ ወደ ናፈቅሁት ቤተሰብ መቀላቀልን ወስኜ ለመሄድ ዝግጅቴን አጠናቀቄ በመጠባበቅ ላይ ነኝ .ስልክ ደውዬ ለቤተስብ ልመጣ እንደሆነ ተናገርኩ ጏደኞቼን ተሰናብቼ መንገዴን አቀናሁ...... ✍🏼ይቀጥላል...... 𝗝𝗢𝗜𝗡 🌸🍃 ‌‌‌‌‌••••❥ ♡🤍🌹 ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌@H_A_P_P_Y_N_E_S ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌@H_A_P_P_Y_N_E_S ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
Mostrar todo...
​​​💕የድሀ ልጅ ፍቅር❤ ክፍል18 በእዉነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ ስለ ሜላቴ ስጨነቅ አምሽቼ የግዴን እንቅልፍ ወሰደኝ እኩለ ሌሊት ላይ የስልክ ጥሪ ቀሰቀሰኝ... በድንጋጤ ተነስቼ ተቀመጥኩ ስልኩን ሳየው የእናቴ ስልክ ነው.. ደነገጥኩ እጄ እየተንቀጠቀጠ አነሳሁት.... ስልኩን እንዳነሳሁት የሰማሁት ድምፅ በጣም ያስደስት ነበር ... የህፃን ልጅ ድምፅ! እያለቀሰ በቃ ደስ የሚል ድምፅ! ሰማሁ!...እንዴት ደስ ይላል በጌታ... ልጄ አለችኝ እናቴ በደስታ እያነባች!... እማ ምን ምንድነው የሰማሁት? እኔም ወግ ደርሶኝ አባት ልሆን ነው?ልጄ ነው? አልኳት። ጥያቄዬን አከታተልኩት... እንባዬ ግን በደስታ ብዛት ይፈስ ነበር... ልጄ የወንድ ልጅ አባት ሆነሀል! አለችኝ እናቴ... ኦ አምላኬ ተመስገን አልኩ... እማ ሜላቴስ እንዴት ናት ? አልኩ ስቃይዋን እያሰብኩት... ደህና ናት ልጄ አትጨነቅ በሰላም ተገላግላለች አለችኝ ደስ አለኝ ...ግን ድምፆን መስማት እፈለግሁ... እማ ሜላቴን ላናግራት አልኳት... ጠዋት ታወራታለህ አሁን ትንሽ ደክሟት ተኝታለች አለችኝ.. እሽ ብዬ ስልኩን ዘጋሁት.... የሰላም የደስታ ሌሊት ሳልተኛ በደስታ ቁጭ ብዬ ነጋ ..ጠዋት ተነስቼ ቁርሴን በልቼ ወደ ትምህርት ከመሄዴ በፊት ሜላቴን ማናገር ፈለግሁና እናቴጋ ደወልኩ... ስልኩን ሜላት ነበርች ያነሳችው.. ወዬ ውዴ ስትለኝ በጣም ተደሰትኩ.. የኔ እናት ደህና ነሽ አይደል? አልኳት ደህና ነኝ ውዴ አትጨነቅ እሽ አለችኝ... የኔ ውድ የኔ ፍቅር አመስግናለሁ! ስላት.. ለምን ውዴ? አለችኝ ...ለዚህ ለአባትነት ክብር አበቃሽኝ አይደል አልኳት ውዴ እኔም ደስ ብሎኛል .. ምስጋና አያስፈልገውም አፈቅርህ የለ አለችኝ እሽ አልኳትና ትምህርት እንዳይረፍድብኝ ስልኩን ዘግቼ ወደ ክፍሌ ገባሁ.... ትምህርቴን በደስታ ተምሬ ጨረስኩ.. ከክፍል መልስም ስራ ቦታ በደስታ ዋልኩኝ,ማታ ጏደኞቼ የሜላትን መውለድ ነግሬያቸው ስለነበር ፕሮግራም አዘጋጅተው ና ሲሉ እነሱጋ ሄድኩ....ደስ የሚል ምሽት በደስታ አመሸን... እኔም ሜላቴን ደውዬላት አወራን ... ነገ ከሆስፒታል እንደምትወጣ ነገረችኝ በቃ ፈፁም ደስተኛ ነኝ,.ልጄን የማቅፍበትን ቀን እየናፈቅሁ ነው ..... ሜላቴ ጋ ደውዬ እያወራን የልጃችን ስም ማን እንዲሆን እንደምፈልግ ጠየቀችኝ እኔ ከድሮው የልጄ ስም ቅድስ ቢሆን ደስ ይለኛል እሷ ደግሞ ናትናኤል እንዲሆን እንደምትፈልግ ደጋግማ ነግራኛለች,... የመጀመርያ ልጄን ናታኒኤል ነው የምለው ትለኝ ነበር ከበፊትም እኔም ልቃወማት አልፈለግሁም....እና ለምን ስም አውጣ እንዳለችኝ አልገባኝም ,.የኔ ውድ "ቅዱስ ቢኒያም"ቢባል ደስ አይልም አልኳት,... "ናትናኤል ቢኒያምስ" አለችኝ...የኔ ፍቅር ስም አያጣላንም ያልሽው ይሁን አልኳት እሽ አለችኝ..... ሜላቴ ከቤተስቦቿ ቤት ወጥታ ከእናቴ ጋር አሪፍ ቤት ተከራይተው መኖር ጀምረዋል ልጄ በሁለት እናቶቼ እጅ መሆኑን ሳስብ እጅግ እደሰታለው...ሁለቱም ለእኔ የፍቅር መምህሮቼ .በህይወት የመኖር ሚስጥሬ ናቸው...ስለዚህ ልጄ በእነሱ እጅ ስለሆነ ፍቅር ተምሮ እንደሚያድግ ሳስብ ደስታ ይሰማኛል..... ሰአታት ቀናትን ቀናት ወራትን እየተኩ የልጄ ስደስተኛ ወር ሊሆነው ነው..እኔ ግን እስካሁን አቅፌው ለመሳም አልታደልኩም..ግን ሲናፍቀኝ በእስካይፕ ስለማየው ትንሽ ይሻላል ,ሜላቴ የእኔ መራቅ የእሷ ብቻዋን መሆን ትንሽ የጎዳት ይመስላል... ሜላቴ ከስታለች በቃ ጥሩ ስሜት እንደሌላት ይገባኛል የልጃችን ስደስተኛ ወር ሊከበር ነው እያለች ደጋግማ ትነግረኛለች ...ግን ምን ላድርግ ,የኔ ፈቅር ትንሽ ነው የቀረኝ በቅርቡ እመጣለው እሽ በጣም እኮ ናፍቃችሁኛል እያልኩ አፀናናታለው ብዙ ባይዋጥላትም እሽ ማለት አልሰለቻትም,.. የሷ እንደዚህ መሆን እኔንም በጣም ጎድቶኛል,ለብዙ አመታት ብቻዋን እንድትሆን ፈርጄባታለው ልረዳት ይገባል ,...ግን ምን ማድረግ እችላለው .. በቃ በተስፋ መኖርን መርጫለው..... ከትምህርት መልስ ስራ ውዬ እቤት ገብቼ እራቴን ሰርቼ በላሁና ጋደም አልኩ እያሰብኩ እያለ .የልጃችን ስድስተኛ ወር ነገ መሆኑ ትዝ አለኝ ,ተንደርድሬ ሜላቴ ጋ ደወልኩ.. ሰላም ተባባልን...የኔ ውድ አልኳት ወዬ አለችኝ.ነገ የቤቢ ስደስተኛ ልደት ነው አይደል አልኳት አዎ ውዴ አስታወስክ አይደል አለችኝ አዎ አልኳት,.. በቃ ነገ እረፍት ስለሆንኩ እኔም በ(Skype) ደውዬ አብሬያችሁ አከብራለው እሽ አልኳት እሽ ደስ ይለኛል አለችኝ.....ስልኩ ተዘጋ... ሜላቴ የልጃችንን ስም ማን እንዳለችው ልትነግረኝ አልፈለገችም እኔ በቃ መቼም እሷ በምትፈልገው ስም ነው የምትጠራው ብዬ ስላሰብኩ ደጋግሜም መጠየቅ አልፈለግሁም.... የልደት ፕሮግራሙ ተጀምሮ እኔ በስልክ እብሪያቸው ማክበር ...ጀመርኩ...ድንገት ሜላት የኔ ፍቅር ቆይ ወደዚህ እንዳታይ አለችኝ እሽ ብያት ፊቴን አዞርኩ... መለስ ስል የሚገም ያልጠበቅሁትን ነገር አሳየችኝ....... ይ.....ቀጥላል✍🏻 𝗝𝗢𝗜𝗡 🌸🍃 ‌‌‌‌‌••••❥ ♡🤍🌹 ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌@H_A_P_P_Y_N_E_S ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌@H_A_P_P_Y_N_E_S ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
XXXTENTACION🖤 nigga crazy😋
Mostrar todo...
Xxxtentacion crazy video
Xxxtentacion sad video
Xxxtentacion full video
Xxxtentacion photo
Xxxrentacion story
Join
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.