cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Winners

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
168
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

🔆🔆 በአንድ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ዲፓርትመንት መምህሯ ተማሪዎቿን አንድ Assignment መስጠት ፈለገች። ተማሪዎቿን ድንች ይዘዉ እንዲመጡ አዘዘች፡፡ ድንቾቹ ላይም የሚጠሏቸዉን ሰዎች ስም እንዲፅፉ አዘዘቻቸዉ። የሚያመጡት የድንች ብዛትም በሚጠሏቸዉ ሰዎች ብዛት ልክ እንዲሆን አለች፡፡ በሁለተኛዉ ቀን አንዳንዶቹ 3 ሌሎች 5 ቀሪዎቹ ደግሞ 8 ድንቾቹን የሚጠሏቸዉን ሰዎች ስም ፅፈዉ አመጡ። መምህሯ ደግሞ <<ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት እኒህን ድንቾች በሻንጣችሁ ይዛችሁ ትዞራላችሁ...ሽንት ቤት ስትሄዱ እንኳ መተዉ አትችሉም! >> ብላ አዘዘች፡፡ ቀኑ እየጨመረ ሲሄድ ድንቹ በመበላሸቱ ሽታዉ ይረብሻቸዉ ስለጀመረ ተማሪዎቹ ቅሬታ ማቅረብ ጀመሩ። በተለይም 8 የያዙት ከሽታው በተጨማሪ ክብደቱ እንደበዛባቸው መናገር ጀመሩ፡፡ ከሳምንት በኋላ የ"አሳይመንቱ" ገደብ ስላበቃ ተማሪዎች ድንቹን አዉጥተዉ እንዲጥሉ ተፈቀደላቸዉ:: ከዛም መምህሯ<<እህ እንዴት ነበር?>> ብላ ጠየቀቻቸ። ሁሉም ማጉረምረም ጀመሩ ..."ኧረረረ ከክብደቱ ሽታዉ...ኧረ በጣም ነዉ የሚያስጠላዉ"...አሉ መምህሯም <<አያችሁ በልባችሁ የምትሸከሙት ጥላቻም እንዲሁ ነዉ...ጥላቻ ልብን ይመርዛል በምትሄዱበት ሁሉም እየተከተለ ይረብሻችኋል...ለአንድ ሳምንት የተበላሸ ድንችን ሽታ መቋቋም አልቻላችሁም። አስቡት ደግሞ በጥላቻ የተመረዘን ልብ እድሜ ልካችሁን ይዛችሁ ስትኖሩ!!>> አለቻቸዉ። ጥላቻን ከዉስጣችሁ አዉጡትና ከእዳ የፀዳችሁ ሁኑ!! እዉነተኛ ፍቅር እንከን አልባን ሰዉ ማፍቀር ሳይሆን ንፁህ ያልሆነን ሰዉ በንፁህነት መዉደድ ነዉና!!! Winnersess join share . ... .join Join 3 more 👉 http://t.me/Winnersess ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
Mostrar todo...

ለሌሎች መልካም በመሆንህ ከአንተ መልካም ስራ ላይ ምንም አይቀነስም…… ለሌላቸው ሰዎች ከአለህ እላይ ቆንጥረህ በመለገስህ ከአንተ ሀብትላይ ምንም አይቀንስም እጥፍ ድርብ አድርጎ ይዞልህ ይመጣል እንጂ ምንም ጊዜ ለሎች መልካም ደግ ነገሮች በሰራህ ቁጥር መልካም እና ውብ ነገሮች ወደ አንተ ይመጣሉ አንተን ለማስደሰት Winnersess Share😘share😘share😘 ◉● •• Join 3 More🙏🙏 👉 http://t.me/Winnersess
Mostrar todo...
እቺን ምርጥ ግጥም ተጋበዙልኝ ታንቄ እንዳልሞት ታንቄ እንዳልሞት አጥሬ በስብሷል፡ ኮረንቲ እንዳልጨብጥ መብራት ደሞ ሄዷል፡ " ከጎርፉ እንዳልገባ ዝናቡም #አቁሟል ፡ እንግዲህ ልጠብቅ ልጠብቅ #ይመጣል፤ ጠብቄ ጠብቄ ዝናቡም መጣልኝ፡ ጠብቄ ጠብቄ መብራቱም መጣልኝ፡ ግን ምን ያደርጋል ሰአቱም አለፈብኝ፡ እንዲያ ያስጨነቀኝ ንዴቴም ጠፋልኝ፤ ለካስ ሁሉም ያልፋል የጊዜ ጉዳይ ነው፡ ዛሬ ቢጨልምም ነገ ሌላ #ቀን ነው :: 👉 http://t.me/Winnersess
Mostrar todo...

💧'ከልጅነት ወደ አዋቂነት የተሸጋገርከው ለህይወትህ ሙሉ ሀላፊነት የወሰድክ ዕለት ነው' ይሄን የሚለን ጂም ሮን ነው። ልጅ እያለን ለወላጆቻችን ብለን የምንማር የምበላ ይመስለን ነበር፤ ከፍ ስንልም ከዛ አስተሳሰብ ሙሉ ለሙሉ ስለማንላቀቅ ለነሱ ብለን የማንፈልገውን ትምህርት እንማራለን ወይ የማንደሰትበን ስራ እንሰራለን፤ ከዛ ደስተኛ ያልሆንከው ለምንድነው ተብለን ስንጠየቅ ብዙ ሰበብ እንደረድራለን። አንድ ነገር እወቅ 👉 የምትኖረው መጀመሪያ ለራስህ እንደሆነ ካመንክ ለሚገጥምህ ነገር ሁሉ ሀላፊነቱን ውሰድ! ቆንጆ ጁምዓ ተመኘንላችሁ🙏 http://t.me/Winnersess
Mostrar todo...

🔆🔆ሰለም እንዴትነቹ እውነተኛ መውደድ የሚገለፀው መጀመሪያ ራስን በመውደድ ነው፤ ሰዎች አንተን ከማክበራቸው በፊት አንተ ራስህን አክብረው። እነሱ ሁኔታህን አይተው ነው ፥የሚለዋወጡት። የአንድን ዕቃ ዋጋ የሚያወጣው ሻጩ ነው ካላዋጣው እኮ መቼም አይሸጥም፤ የራስህን ዋጋ የምታወጣው አንተ ነህ! ራስህን ከምንም ነገር በላይ አክብረው ወዳጄ! Winnersess share & join ተመልሰናል ቤተሰቦች💪 👉http://t.me/Winnersess
Mostrar todo...

Mostrar todo...
ANY CALL - Apps on Google Play

Free Global internet WiFi phone caller, VoIP Call & Free texting

Check out this app! It's millions of students helping each other get through their schoolwork. https://brainly.app.link/qpzV02MawO
Mostrar todo...
Brainly - Homework Help & Problem Solver

Need homework help? Post your question on Brainly and receive a clear, superfast answer from another student!Brainly is the world’s largest social learning community! 350 million students trust and study with Brainly every month. Yup, that’s 350 million..

#CHAPTER_ONE #PART_THREE 🕘በፕሮግራም መመራት ጊዜን ሲያትረፈርፍ 🔹በአንድ ወቅት መምህርት የነበሩና ከዚያም የኢስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ለመሆን የበቁት ወይዘሪት ጓልዳ ሜር እንዲህ ብለው ነበር «ህይወትህን መቆጣጠር ከሻህ፤ ጊዜን መቆጣጠር ይኖርብሃል»። ታላቋ ሴት ሚስስ ጎልዳሚር እርሳቸው ጊዜን እንዴት እንደሚቆጣጠሩት እንዲህ ያስረዳሉ «የሰአትህ አለቃ መሆን ስትፈልግ መጀመሪያ አላማና እቅድ ሊኖርህ ይገባል፤ እነኚህንም በተግባር አዋልክ ማለት ጊዜን ተቆጣጠርከው ማለት ይሆናል»። 🔹«ጊዜ ወርቅ ናት» የምትለዋ አባባል እውነትነት አላት፤ እንዲያውም ጊዜ ከወርቅም በላይ ነች፤ ምክኒያቱም ወርቅን በገንዘብ መግዛት ይቻላል―ጊዜን ግን መግዛት አይቻልምና። በገንዘብ ሊተመን የማይችል ሀብት ደግሞ የውዶች ሁሉ ውድ ነው። ከዚህም ሌላ የእያንዳንዳችን የህይወት ምዕራፍ የተከፋፈለው በጊዜ በመሆኑ ጊዜ የህይወታችን ሁነኛው ክፍል እንደሆነ እንገነዘባለን፡ እድሜያችን፣ ስራችንና ማንኛውም አይነት ተግባራችን በጊዜ ላይ የተመሰረተ ነው። እናም ለጊዜ ሁሉም ሰው ክብር ሊኖረው ይገባል፤ ጊዜን ማክበር ማለት ደግሞ ጊዜን በአግባቡ መጠቀም ማለት ነው። 🔹ጊዜ ለሁሉም ሰው ትልቅ ዋጋ ይኑራት እንጂ ለተማሪዎች ግን እስትንፋሳቸው ናት። የተማሪ ጊዜ እጅግ ውድና ሽርፍራፊ ሴኮንድም ብትሆን በአልባሌ ልታልፍ የማይገባት ናት። በተለይም ጥሩ ተማሪዎች ጊዜያቸውን በስነ ስርዓት በመከፋፈል ሳይጨናነቁና የተጣበበ የጊዜ ሁኔታ ሳይገጥማቸው እያንዳንዷን ሰዓት ተግባር ላይ ያውሏታል። ጊዜን በእቅድ እና በፕሮግራም መምራት ብዙ ጥቅም ያስገኛል። ለምሳሌ፦ ከትምህርር ሰዓት ውጭ በሌላ ስራ መሰማራት የሚጠበቅበት ተማሪ እጅግ የተጣበበ ጊዜ ስለሚኖረው በእቅድና ፕሮግራም በማመቻቸት ያለውን ጊዜ ለትምህርቱም ለስራውም እንደሚመቸው አድርጎ ሊያከፋፍል ይችላል። በጣም የተጨናነቀና እርፍት አልባ የእለት እለት እንቅስቃሴ የሚኖርበት ሰው ጊዜውን ፕሮግራም በመንደፍ የሚንቀሳቀስ ከሆነ ለመዝናናትና ለሌሎች ተጨማሪ ጉዳዮችም ጊዜ ሊተርፈው ይችላል። 🔹ተማሪዎች ጊዜያቸውን በእቅድና በፕሮግራም በመከፋፈል የሚጠቀሙ ከሆነ እነኚህን ጥቅሞች ያገኛሉ። ―ለጥናት በከፍተኛ ሁኔታ ሊነሳሱ ይችላሉ፣ ―የማይወዱዋቸውን የትምህርት አይነቶች እንዲወዱዋቸው ይሆናሉ፣ ―ሁሉንም ትምህርቶች በእኩልና በሚገባ እንዲያጠኑዋቸው ይሆናሉ፣ ―ጥናትን አሰልቺ ወይም እንደስራ መቁጠር ሳይሆን ፊልምና ቲያትር ወይም ኳስ ጨዋታን እንደመመልከት ይዝናኑበታል፣ ―የትምህርት ክለሳ ፕሮግራማቸው ትክክለኛና ያልተዛባ ከመሆኑም በላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያጠኑትን እንዲረዱት ይረዳቸዋል፣ ―አእምሮን ነፃና ለጥናት የተዘጋጀ ያደርጋል፣ ―የጥናት ሰዓት የእረፍት ጊዜን በሚገባ እንዲጠቀሙበት ይረዳቸዋል፣ ―የጥናት ሰአትን ከሌሎች የመህበራዊ ግንኙነቶች ጋር የተመጣጠነ ስለሚያደርገው በጥናት ውጤታማ እንዲሆኑ ይረዳል፣ ―የጥናት ጊዜን እና የመዝናኛ ጊዜ ለይተው እንዲረዱና በአግባብ ሁሉንም እንዲጠቀሙ ይመራቸዋል፣ ―ማንኛውንም የእለት እለት እንቅስቃሴያቸውን በመምራት ሁሉም ነገር በታቀደለት ጊዜ እንዲከናወን ስለሚረዳ ከመጨናነቅ ያድናቸዋል:: Winners ለጓደኞቻቸው share http://t.me/Winnersess
Mostrar todo...

#CHAPTER_ONE #PART_TWO የተሳካ የተነሳሽነትን መንፈስ ለተሳካ ጥናት ለማዋል "በምድር ላይ እጅግ ውድ የሆነውን ንብረት ተቀብሮ የምናገኘው የት ነው? የአልማዝ ወይም የወርቅ ማዕድናት የሚገኙበት ስፍራ? አይደለም!! ከፍተኛ የነዳጅ ድፍድፍ ያለበት ምድር? በፍፁም!! እጅግ ውድ የሆነውን ንብረት የምናገኘው በመቃብር ስፍራዎች ነው። ማድረግ የሚችሉትን ሳያደርጉና ያላቸውን እምቅ ሀይል(potential) ሳያወጡ ያሸለቡ ሰዎች ናቸው ውዱን ንብረት እንደያዙ እንደተቀበሩ የምቆጠሩት የ " ሬቭረንድ ማይልስ ሙንሮ" ንግግር። ብንጠቀምበት በራሳችንም ሆነ በሌሎች ህይወት ላይ ታላቅ ለውጥ ልናመጣበት የምንችለውን እምቅ ሀይላችንን አስመልክቶ የተነገረ ግሩም አባባል ነው ከላይ ሰፍሮ የምናገኘው። ሆኖም በተለይ የትምህርት ህይወትን በተመለከተ ስኬት እንድናገኝ እንቅፋት የምሆንብን ያለንን ያህል በቅጡ አለመገናዘብና ራስን አሳንሶ ማሰብ በግምባር ቀደምነት ይመጣል። በመቀጠል ደግሞ ጥናትና ጠቅላላ ልማዶች የስኬታችን እንከን እንደሆኑ ለማየት ሞክረናል። ልማድ"habit" አልያም "በህሪይ" ብለን የምንጠራው ሀሳብ የሚወክለውን ነገር ከምናስበው ሰፋ ያለ እንደሆነ አይተናል። በህይወታችን ያለን አላማ፣ ያለን ቁርጠኝነት፣ ማህበራዊ ህይወታችን፣ ኢኮኖሚያዊ እና ግላዊ ስብዕናችን… በሙሉ በዚህ ሀሳብ ስር እንደሚጠቃለሉ አይተናል። ለስኬታማ ጥናት እንከን ሊሆኑብን የሚችሉትን እንቅፋቶች በዚህ መልኩ ልንዘረዝራቸው እንችላለን(ዝርዝሩን ከታች ይመልከቱ) ችግሮቻችንን በቅጡ ስናውቃቸው ብቻ ነው ወደ መፍትሄዎቹ መጓዝ የምንችለው። "ስለሆነም የትኞቹ ነጥቦች እኛን ይመለከታሉ?" ብለን ራሳችንን እንጠይቅ። 0⃣1⃣ የጥናት እና የትምህርት በህሪያት በራሳቸውና እነሱ ከኛ ጋር ያላቸው ዝምድና ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 🔹ፍላጎት ማጣት እና የድብርት ስሜት➖የምንወስደው የትምህርት አይነት ጠቀሜታ አይታየንም ወይም ደግሞ ከአላማችንና ግባችን ጋር ያለው ተዛምዶ ይላላብንና የቸልተኝነት ስሜት ይሰማናል። ለምሳሌ፦ በህክምና ትምህርት ህይወቱን ለመምራት የምያስብ ሰው ሂሳብ ነክ ትምህርቶች የሚፈጥሩት ስሜት 🔹የትምህርት ዓይነቱ ያለው የክብደት ደረጃ➖አስፈላጊውን መሰረት ካለማሟላት የመነጨ ወይም ደግሞ በተፈጥሮ ለትምህርት አይነቱ ብቃት የለኝም ብሎ ማሰብ ለምሳሌ፦ የእንግሊዝኛ ቋንቋ በቂ መሰረት አለመኖር በእንግሊዝኛ የሚሰጡ ትምህርቶች ላይ ያለው ተፅዕኖ ♣️ ሂሳብ ነክ ትምህርቶችን በተመለከተ የሚታይ የአቅም ማነስ 🤾🤾‍♀ የመውደቅ ስጋት፦ አእምሮ ውስጥ መሽጎ ጥናት በተጀመረ ቁጥር የውድቀትን ነገር ውል እያደረገ ሰላም የሚነሳ ስጋት 👌የአስፈላጊ መፅሐፍትናመሰል ማቴሪያሎች አለመሟላት ለምሳሌ፦ትምህርት በተጀመረበት ወቅት የምያጋጥም "ለማጥናት ብፈልግም የማጠናው ኖትም ሆነ ማመሳከሪያ የለኝም" የሚል ሀሳብ 📑የሚጠና ነገር መንዛዛት➖ጠቅላላ መሸፈን ያለበት ነገር በጣም ረጅም ከመሆኑ የተነሳ የሚመጣ የድካምና ተስፋ መቁረጥ ስሜት 0⃣2⃣ ከሌሎች የህይወት እርምጃዎች ጋር የሚፈጠር ግጭት 🔹ጥናትን ሳይሆን ሌላ ነገር የመስራት ፍላጎት ለምሳሌ፦በጥናት ፕሮግራም ሰዐት የሚተላለፍ የእግር ኳስ ጨዋታን የማየት ጉጉት 🔹ቀጠሮ፣ ግብዣ… የመሳሰሉ የማህበራዊ ህይወት ጣጣዎች 🔹ቤተሰብንና ጓደኞችን በተመለከተ የሚመጣ ጊዜ ተሻሚ የማህበራዊ ህይወት ግዴታ(commitment) 🔹በበርካታ ተጓዳኝ (extracircullar) ስራዎች የመጠመድ ነገር ለምሳሌ፦የትርፍ ጊዜ ስራ፣ ሆቢ፣… 0⃣3⃣ የጥናት ስፍራ ላይ የሚፈጠሩ ማስተጓጎያዎች 🔷ሙዚቃ፣ ቴሌቪቭንናመሰል ጮክ ያለ ድምፅ 🔷በጣም ቀዝቃዛ አልያም በጣም ሞቃትና የታፈነ ክፍል 🔹ለእንቅልፍ የሚጋብዙ ሁኔታዎች ለምሳሌ፦ ፍራሽ ላይ ሆኖ የማጥናት ዛይቤ 0⃣4⃣ ስለ ግላዊ የህይወት ጣጣዎች የሚፈጠር ጭንቀትና ጫና እነዚህና መሰል የውስጥ የተነሳሽነትን ስሜት የሚጋሩ ጉዳዮች በውል ለይቶ ማስቀረት ወይም ማለዘብ ወሳኙ እርምጃ ይሆናል ማለት ነው። #part_three ይቀጥለል Winners ለጓደኞቻቸው share 👉 http://t.me/Winnersess
Mostrar todo...
☝️ትጋት በጣም ከፍተኛ ከሆኑት የስኬት ሞተሮች አንዱ ነው። የሆነ ነገር ስትሰራ ያለህን ሀይል ሁሉ ተጠቅመህ ስራ። ነፍስህን ሁሉ በውስጡ አድርግ ፣ ለራስህ ማንነት አትመው። ንቁ ሁን ፣ ጉልበታም ሁን ፣ ጉጉና ታማኝ ሁን እና የምትፈልገውን ነገር ታሳካለህ። የትኛውም ትልቅ ነገር ያለትጋት አልተገኘም። ገራሚ ከሰዓት ተመኘን🙏 Winners ለጓደኞቻቸው share 👉 http://t.me/Winnersess
Mostrar todo...

Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.