cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ቀን ሳለ

“ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች።” — ዮሐንስ 9፥4 “ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።” — ኤፌሶን 4፥30 @asiben @asiben Our youtube channel https://youtu.be/OiNz2jZb8WY WhatsApp channel :https://whatsapp.com/channel/0029Va8rf7y7

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
202
Suscriptores
Sin datos24 horas
+17 días
-530 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

w selemon.wav249.35 MB
ርዕስ፦ አንተም ለዚህ ዘመን ተመርጠሃልና ዕድልህን ተጠቀም                  በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከዘፍጥረት እስከ ዮሐንስ ራዕይ ድረስ ስንመለከት በየዘመናቸው የተጠሩና የተመረጡ ሰወች በቁጥሪቸው መግለጽ ባልችልም በጣም ብዙ ሰወች እንደሆኑ ለማንም ግልጽ ነው። አንዳንዶቹ የተመረጡትን ዓላማ አውቀው ዓላማቸውን የፈጸሙ ናቸው፤ አንዳንዶቹ ግን በሩጫቸው ላይ ደክመው በመንገድ ወድቀው የቀሩ ናቸው። በመንገድ ላይ የቀሩት ተመርጠው ዕድላቸውን በአግባቡ ያልተጠቀሙ ናቸው። ብሆንም ግን እግዚአብሔር በየዘመኑ የተመረጠ ትውልድ ያስነሳል። "መርጬ ያነሳው ሰው ጠፍቷልና ከእንግዲህ አላነሳም" አይልም። ምክንያቱም በምህረቱ ባለጠጋ ስለሆነ ለሕዝቡ ይራራልና። ተመርጦ እድሉን አለመጠቀምና በመንገድ ላይ መቅረት የተመረጠ ሰው ድርሻ ስሆን እግዚአብሔር ግን በየዘመኑ የተመረጠ ትውልድ ያነሳል። ለዚህም በምሳሌነት የኤልያስን ዘመን ስንመለከት፥ ኤልያስ ብቻዬ ቀረሁ፣ የእኔ እድል ይጥፋ፣ ግደለኝ እያለ እየለቀሰ ባለበት ሰአት እግዚአብሔር ግን አትፍራ፣ ገና አንተ ያላወከው ትውልድ አለኝ፣ ብቻህ አይደለህም፣ ይልቅ ሂድና ኢዩን ቀባው ብሎ ስያጽናናው እናያለን። (ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕ. 11) ---------- 2፤ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ሕዝብ አልጣላቸውም። መጽሐፍ ስለ ኤልያስ በተጻፈው የሚለውን፥ በእግዚአብሔር ፊት እስራኤልን እንዴት እንደሚከስ፥ አታውቁምን? 3፤ ጌታ ሆይ፥ ነቢያትህን ገደሉ መሠዊያዎችህንም አፈረሱ እኔም ብቻዬን ቀረሁ ነፍሴንም ይሹአታል። 4፤ ነገር ግን አምላካዊ መልስ ምን አለው? ለበአል ያልሰገዱትን ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስቀርቼአለሁ። 5፤ እንደዚሁም በአሁን ዘመን ደግሞ በጸጋ የተመረጡ ቅሬታዎች አሉ። እንደዚሁም በአሁኑ ዘመናችንም በጸጋ የተመረጡ ቅሬታወች አሉ። ነገር ግን ከባዱ ነገር የተመረጡ ትውልድ መሆናቸውን መዘንጋትና አልባሌ ቦታዎች ጊዜያቸውን ማሳለፍ ነው እንጅ። ማለትም የተመረጡ መሆናቸውን አለማስተዋል እድላቸውን ያጠፋል እንጅ። አሁን በዚህ ዘመን በየቦታው የሚንሰማው ነገር ስሰለቸንና ሀሰተኞች ነብያት እንደበዙ ስንሰማ፦ ውይ በዚህ ዘመን ኤልያስ ብኖር!!! እንላለን። ነገር ግን ኤልያስ የተዘጋጀውና የተመረጠው ለዚያች ዘመን ነው እንጅ ለዚህ ዘመን አይደለም። ለዚህ ዘመን የተመረጥነው አንተ/ቺ እና እኔ ነኝ። ኤልያስ በዘመኑ ዕድሉን ተጠቅሞ ተዓምራትን ሠርቶ ለኤልሳ አሳለፈ፤ ኤልሳዕም ዕድሉን ተጠቅሞ አለፈ...... አእያለ እያለ ዛሬ ተራው ለእኛ ደረሰ። አንተና እኔ ግን ያኔ እነርሱ የሠሩትን እንተርካለን እንጅ ዛሬ ምን ሠራን? በ2ኛ ጴጥ 2፥7 ስንመለከት በሎጥ ዘመንም ትውልድ ረከሱ፤ ሎጥ ግን ብቻው ቀርቶ ነፍሱን ያስጨነቅ ነበር። ለዚህ ዘመንም በረከሱት ትውልድ መካከል አንድ የተመረጠ ትውልድ ነፍሳቸውን እያስጨነቁ ያሉ አሉ። ከእነዚህ ከተመረጡትና አላማቸውን ካወቁት ጋር እንድንሰለፍ ኢየሱስ ይርዳን። ነገር ግን አንድ የሚያሳዝነው ነገር በየዘመኑም እግዚአብሔርን የማያውቅ ትውልድ ይነሳል። ስለዚህ እኛ እራሳችንን ስንፈትሽ በየትኛው ትውልድ ውስጥ ተመድበናል ብለን መጠየቅ ያስፈልገናል። በመሳፍንት ዘመን እግዚአብሔርንና እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው የሠራውን ተዓምራት ያላወቀ ትውልድ ስነሳ እግዚአብሔር ግን ቸር አምላክ ስለሆነ ሌላ መሳፍንት በመካከላቸው ያስነሳቸዋል። የተነሱ መሳፍንቶችም አንዳንዶቹ ዕድላቸውን ተጠቅመው እንደ ሀሳቡ አገልግለው አሳልፈዋሉ፣ አንዳንዶቹ ግን አልተጠቀሙም። (መጽሐፈ መሳፍንት ምዕ. 2) ---------- 10፤ ትውልድ ሁሉ ደግሞ ወደ አባቶቻቸው ተከማቹ፤ ከእነዚያም በኋላ እግዚአብሔርን ለእስራኤልም ያደረገውን ሥራ ያላወቀ ሌላ ትውልድ ተነሣ። 11፤ የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነ ነገር አደረጉ፥ በኣሊምንም አመለኩ። 12፤ ከግብፅ ምድርም ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ተዉ፥ በዙሪያቸውም ካሉት ከአሕዛብ አማልክት ሌሎችን አማልክት ተከተሉ፥ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔርንም አስቈጡ። 13፤ እግዚአብሔርንም ትተው በኣልንና አስታሮትን አመለኩ። ዛሬም እኔና አንተ/ቺ የተመረጥን ትውልድ መሆናችንን ብናውቅ ኖሮ ለዚህ ትውልድ መፍትሔ ሊንሆን እንችላለን፣ እድላችንን እንጠቀም። እግዚአብሔር ለዚህ ትውልድ መፍትሔ አድርጎ እንድያስታጥቀን ጸልየን እንውጣ፣ ነገም በዚህ ርዕስ እንቀጥላለን።                       መልካም ቀን!!
Mostrar todo...
አሁን ብትመጣ ወደ አንተ ልትወስደኝ ከሆንኩኝ በሰማይ የምትቀበለኝ በቃልህ ብርሃን ልቤን ስትመረምረው እውነተኛ ንፁህ ሆኖ ካገኘኸው አንተን ደስ ካለህ ህይወቴን ስታየው ይሄ ነው መሻቴ ምን እፈልጋለሁ ሰው ብቻ ነው ወይስ አንተም የምትለኝ ጻድቅ ፍፁም ሽንገላ ነው ወይስ ህይወት በልቤ ውስጥ ይኑር እውነት ኢየሱስ አንተስ ለኔ መልስ አለህ ወይ ጠላቴ ሲከሰኝ ትነግረዋለህ ወይ ቅን ናት ቅን ነው ፍፁም ናት ፍፁም ነው ጻድቅ ናት ጻድቅ ነው ትላለህ ወይ በአንደበቴ ከምናገረው በአደባባይ ላይ ከማሳያው የልቤ ሀሳብ የተሰወረው የጓዳ ኑሮዬ አንተ ምታየው ደስ ያሰኝሃል ወይ ስትመዝነው ቃልህ ነው ሚዛኔ የምለካበት አንተ ነው የማየው እንደመስታወት የሚለይ ነገሬን በፀጋህ እየጣልኩት ፈፅሜ ልመስልህ የምተጋው በህይወት የእምነቴ ራስና ፈፃሚ ህይወቴ ኢየሱስ አንተ ነህ ፍለጋህን ዘውትር ልከተል ክብርህ ከራቀኝ ምን አለኝ አይተካውም ምንም ነገር መንፈስህ በውስጤ ይኑር ብቻህን ፀንተህ ንገስበት ይህ ልቤ ዙፋንህ ይሁን ልቤን እንካ ጌታ ሆይ ልቤን እንካ ልቤን እንካ ኢየሱስ ሆይ ልቤን እንካ ልቤን እንካ ጌታ ሆይ ልቤን ያዘው በዘመኔ ሁሉ ያዘው ከማውቀውም በላይ ጥልቅ ነው አንተ ነህ የምትመረምረው የህይወት መውጫ የሆነውን አባቴ ሰጠውህ ልቤን ካንተ ሌላ እንዳልል በዘመኔ ሁሉ @Apostolicsonglyrics @Apostolicsonglyrics @Apostolicsonglyrics
Mostrar todo...
ስለእኔ ምን ትላለህ.mp320.69 MB
ነፍሴ ቀና በይ ወደ ፈጣሪሽ እርሱን ተመልከቺ አለ ሊረዳሽ       አትድከሚብኝ ነፍሴ        ተይ አትድከሚብኝ ነፍሴ በርታ በይ ፍፃሜው ቀርቧል ቀና በይ ኢየሱስ ይመጣል በርታ በይ ሊያበቃ ነው ድካም ቀና በይ ሊሆን ነው መልካም 1 ግዜውም ከፍቷል ሚታየው ተስፋን አይሰጥም ድቅድቁ ጨለማ በርትቷል ከቶ አያስተኛም ይህንን እያየሽ አትዛይ ተስፋ አለሽ በላይ ብርታትሽ ይመጣል ጌታሽን የሱስን ስታይ       ይሻልሻል ቀና በይ አዎ       ያዋጣሻል በርታ በይ አሜን 2 አይዞሽ ሁሉም ያልፋል በርቺልኝ ኢየሱስን ያዢው የሚጠብቅሽም ደስታ ታላቅ በረከት ነው አይወዳደርም ፈፅሞ ይበልጣል ኋለኛው ሀዘንሽን እረስተሽ ከአምላክሽ ጋራ የምትኖሪው        የምትጠብቂው ይመጣል ያሳርፍሻል        ሁሉን የተውሽለት ኢየሱስ/አምላክሽ መች ይተውሻል እንዳይረሳሽ/እንዳይተውሽ እርሱ ሰው አይደለም ክቡር ደሙ በከንቱ አልፈሰሰም         በዋጋ ገዝቶሻል የራስሽ አይደለሽም         ታምነሽ ተከታዪው ኢየሱስ አይጥልሽም @Apostolicsonglyrics @Apostolicsonglyrics @Apostolicsonglyrics
Mostrar todo...
IMG_3137.mp37.02 MB
በቅድስናው ዙፋን የሚቀመጥ መንግስቱ የጸና ክብሩ ማይለወጥ በቅዱሳኑ ላይ ከፍ ያለ ልዑል እርሱን ከአማልክት ማን ይመስለዋል የሱስ ነው የኔ ጌታ በሞገስ የገነነ ልያመልከው ለዘላለም ይኸው ልቤ ጨከነ በክብሬ እነሳለሁ ስሙን ላደናንቅ በቅዱሱ ተራራ እርሱ ብቻ ትልቅ @Apostolicsonglyrics @Apostolicsonglyrics @Apostolicsonglyrics
Mostrar todo...
ኢየሱስ_ነው.mp311.31 MB
#ዘማሪት ዘነበች መህዲ #ዝማሬ ምስጋናዬ ማደርያህን ይሙላው እንጂ ጌታዬ አንድም እንዳይጎልብኝ ከጸጋ ስጦታ ያለሁበት ድረስ ፈልጎኝ የመጣ ከጥሜ ልያረካኝ የህይወት ውሃ ሰቶ በደሙ ውስጥ አየኝ ማንነቴን ትቶ    የመታሰቤን ቀን አሀሀ አስቤ አስቤ    የምስጋናን መዝሙር ኦሆ አፈለቀ ልቤ    ትባርከዋለች አሜን ነፍሴ ጌታዬን    አጽናንቶኛልና አብሶ እንባዬን እኔማ ከአንተ ብዙ መልካም ነገር ተቀብያለው በምላሹ ለአንተ መስጠት የምችለው ምንድነው? ምስጋናዬ ማደርያህን ይሙላው እንጅ ጌታዬ አምልኮዬ ማደርያህን ይሙላው እንጅ ኢየሱሴ እልልታዬ ማደርያህን ይሙላው እንጅ ጌታዬ ዝማሪዬ ማደርያህን ይሙላው እንጅ ኢየሱሴ ህይወት ከነ ትርፉ አልጎደለብኝም እንደ ቃልክዳኑ አምላኬ(በእውነት) አሰበኝ ልቤ በአባቴ ላይ ጸናልኝ በርትቶ አፌም በጠላት ላይ ዘመሬ ተከፍቶ  ከፍ ብሎ ይሰማ አሀ የደስታ መዝሙሬ   ምስጋናና እልልታ አሀ ሞልቷል በድንኳኔ   ቤቴን የበረከት አሀ የእረፍት አረክልኝ   አንተን መጠበቄ ለመልካም ሆነልኝ ሁሉ የእርሱ ለሆነው ጌታ ምን ሰጥቼው እደሰታለሁ? ምን ሰጥቼው እረካለሁ? ከአምልኮ ጋር ፊቱ እታያለሁ ከእልልታ ጋር ፊቱ እታያለሁ እጆቹን ለእጆቼ ልይዘኝ ዘረጋ ከእስትንፋሴ ይልቅ ወደ እኔ ተጠጋ እሱን ብቻ እንዳይ አገዘኝ ቀና አርጎ የምጎትተኝን አንድ በአንድ አስጥሎኝ
በደሙ ውስጥ አየኝ ማንነቴን ትቶ 🙌🥰
@Apostolicsonglyrics @Apostolicsonglyrics @Apostolicsonglyrics
Mostrar todo...
Zeni .m4a10.22 MB
Sebeta crusade live worship by Singers Abenezer and Amanuel
የእንደገና አምላክ ስራ የማያልቅ አብቅቷል ሚባል ነገር የማታውቅ ባለቀው ላይ ባበቃው ላይ ትሰራለህ ያለከልካይ ይነሳል የሞተው ነገር አይችልም በፊቱ ልቆም ሸለቆ በውኃ ይሞላል ይህም ለእርሱ ቀላል ነው ቀላል @Apostolicsonglyrics @Apostolicsonglyrics @Apostolicsonglyrics
Mostrar todo...
የእንደገና አምላክ.m4a1.81 MB
ዘማሪት አስቴር ሰይፉ ዝማሬ አመሰግነዋለሁ
ኢየሱስ ኢየሱስ ያለው የፈለገው ልቤ ደስ አለው ሆነልኝ በቃ በእርሱ መጽናት በቅዱስ ስሙ ተጓደድኩበት አሰላስላለሁ የሰራሁን ድንቅ የእርሱን ታምራት ይኸው መጥጭያለው ልዘምርለት ልቀኝለት በፊቴ የሚኸድ እልሻዳይ የተማመንኩበት እርሱ አለልኝ ብዬ ነገረን በእጁ የተውኩለት 2* ሀይሉን አሳየኝ ቀኙ ደገፈኝ ሳመሰግን ቅጥሩን እያዘለለኝ ስሙን ስጠራው ጋረደኝ 2 * በአንዳች ሳልጨነቅ ነገረን በጸሎት ከምስጋና ጋሪ ካሳወኩኝ ወዲያ አምኜ እንደማይ የአምላኬን ክብር ዳግም ሀዘንተኛ ሆኜ አልታይም ይልቅ በደስታ እንደተቀበለ አመስግናለሁ አይዘገይም ጌታ በአምልኮ ውስጥ ነው የኃይሉ ጎዳና ኢየሱስ ስከብር እጁ ስትመጣ ይሆናል አሜን አድስ ነገር እሱ እያለ በታንኳዬ ማእበል አይችል ልያጠፋኝ በቃሉ ስልጣን ያዘዋል በጸጥታ ልመራኝ የሞተው እንኳን ይነሳል ሰው ተስፉ የቆረጠበት የሚያስደንቅ ኤልሻዳይ ነው አምላኬ የተማመንኩት በዘመኔ ሁሉ አዉታር ባለው እቃ ቅኔ እየተቀኘው ነፍሴን አኑሯዋታል በህያዋን ጉባኤ አመሰግናለሁ ልመናዬ በዝቶ ምስጋና እያነሰ ስንቴ አልፍያለሁ እንደተቀበልኩት ምህረት መጠን ዛሬ ላክብረው ወዳለው ስለ ምህረቱ አመሰግነዋለሁ ስለ ቸርነቱ አመሰግነዋለሁ ስለ እጆች ስራው አመሰግነዋለሁ ስለ ታላቅ ኃይሉ አመሰግነዋለሁ @Apostolicsonglyrics @Apostolicsonglyrics @Apostolicsonglyrics
Mostrar todo...
amesegnewalew (Sis. Aster).mp310.32 MB
ይሁዳ 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³ ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ። ⁴ ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ ንጉሣችንንና ጌታችንንም ብቻውን ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።
Mostrar todo...
ራእይ 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁷ ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ ¹⁸ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።
Mostrar todo...