cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ካሲና🫳🏿

"ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ፣ትፍም ብትልባት ትጠፍለች ፣ ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ"

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
312
Suscriptores
Sin datos24 horas
+137 días
+8330 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

አይ ሰው መሆን ከንቱ !! (✍️እስራኤል ) ዘመኑ ሊፈጠም ጥቂት ምዕት ቀረው እገሌን ሸለመው እገሌን ቀበረው የሚል ሰበር ዜና፣ በጤና ይስጥልኝ የሚዘርፍ ጤና፣ ሺህ ሰው ተሰረዘ ከህይወት መዝገብ ላይ፣ የእግዜር እንባ መጣ ተመስሎ በማይ፣ ታጠበ ጎዳናው የማይጠራ እድፉን፣ ሰው ዘበት አያጥፈው መች ይተዋል ግፉን፣ ድንኳኑ ብስክስክ አያስጥልም ዶፉን። እንደ ሽማግሌ ሲመክረን ተፈጥሮ፣ ሰማይ ማይ ይሸናል አመት ተወጥሮ። አውሎው አኮርባጅ ነው የማይራራ በትር ረሀቡ ጅራፍ ነው የሚገርፍ ዘወትር። በሰቆቃም መሐል፥ በችግርም መሐል ሰው ጥፋትን አይተው፣ ሰንካላ ሀሳቡ መልካም የተባለን አያስመለክተው። አይ ሰው መሆን ከንቱ!! 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Mostrar todo...
👍 2
እንባ እንባ ይለኛል      ይተናነቀኛል እንባ የት አባቱ ደርቋል       ከረጢቱ ሳቅ ሳቅም ይለኛል   ስቆ ላይስቅ ጥርሴ     ስቃ እየነደደች መከረኛ ነብሴ             ፨ ፨ ፨ ❇️በአሉ ግርማ
Mostrar todo...
❤‍🔥 2😢 2

🔥 4
Repost from ውብ ወግ
ወዳጅ ወዳጁን አለዉ ወርቅ ያንን የመሰለ ዋጋዉን ይዞ አፈር በታች ምን ይሰራል !?የመሳፍንት የመኳንት ገንዘብ መሆኑን ዘንግቶት ነዉ  !? ወይንስ ነፍስ አልፈልግህም ብላዉ ነዉ 'ርቆ መደበቁ !? አካልስ ዘመዴ ነዉ ብሎ ቆፍሮ ፈለገዉ  እናም አጌጠበት ።ጎሽ እንዲህ ነዉንጅ ! ወትሮም  በዘመድ ማጌጥ የእናት የአባት ነዉ።  አካል በመደብ ተኛ ቢሉት ' እሽ ' ነዉ ።  ቁርበት ላይ ተንከባለል ቢሉት ' እሽ ' ነዉ ።  በኮሲ ዉደቅ ቢሉት ' እሽ ' ነዉ ። ይቺ ነፍስ የሚሏት ሞልቃቃ ናት'ንጅ ...      '' አንዴ ጎረበጠኝ   ፤ አንዴ ቆረቆረኝ  '' እያለች አርፋ የማትተኛ ። አዬ ነፍስ ... ያላገሯ መጥታ ተሰቃዬች ! ኮምጣጤዉንም ማሩንም አይጥመኝም ትላለች ።  ፍቅር ብቻ እየጠጣች ትኖር ይኾንን ።  ዋ! .... ብቻ በሰዉ ሀገር ሙታ እንዳታስወቅሰን ። ይኼ አካል .... ቅጠሉንም ፍሬዉንም   ጮማዉንም ወተቱንም '' አምጡ አምጡ  '' ይላል ።  ዘመዶቼ ያበቀሉትን ብሎ ዉርስ መጠየቁ ነዉ !? እንዴት ያለዉ አልጠግብ ባይ ስግብግብ  ነዉ ጃል ።  እርሷስ ማማሯ።  የሚርባት በቶሎ አይገኝም እንጅ ሲገኝስ በቃኝ ታዉቃለች ። ይቺ ነፍስ ሰዉን ሞኝ ማድረጓ ለምን ነዉ !?  ሀገሬ በሰማይ  ነዉ ትላለች ።  በሰማይ ጓደኞች አሉኝ ... ብርሃን ወንድሜ ነዉ ... ከዋክብት ዘመዶቼ ናቸዉ ትላለች ። ከሰማይ በላይ ቤት ያለ ይመስል ።  አካል ክንፍ የለዉ ... እንደ'ኔ በርሮ አይሄድ  ያየሁት አያይ ብላ ማሞኘቷ ነዉ !? ደግሞ አንተ የመሬት እኔ የሰማይ ነኝ ብሎ ኩራት ምንድን ነዉ !? ስትናገር ሰማናት እንጅ እኛ ክንፎቿን አላዬን ። ደግሞስ በክንፎቿ የምትኮራ ከሆነ ተነስታ ከአሞራ ጋር በኖረች ።ከሰዉ ልብ የምትሰርቀዉ እንቁ ቢኖራት ነዉንጅ ።  ይቺ ሌባ !   ደግሞ ወርቅና ገንዘብ አይጠቅምህም እያለች ለልብ ስታሞኘዉ ትዉላለች ።  እርሱ ሲጥለዉ አንስታ ልታጌጥበት ነዉ !? ሞኟን ትፈልግ እርሱ እንደሆነ ነቅቶባታል ።  ከገንዘቡ ጋር አፈር ይገባታልንጅ ቅንጣት አያቀምሳትም ። ወዳጅ ወዳጁን ነፍስ ምንድን ናት አለዉ። እርሱም የማትደርቅ የማትገኝ ቁስሌ ናት  አለ ።  ምነዉ ነገረኛ ሚስት መሆኗ  ፤ በወጣ በገባ ቁጥር የምትነዘንዘዉ ። ክፉ ሚስትንስ ይፈቷታል  ፤ ይቺን ቀጣፊ ግን እልብ ባህር መሀል ጠፍታ ምን ያድርጓት ። እርሷ ብልጥ ልጅ ናት ።  የአካልን ገንዘቡን እያስጣለች  ታስለቅሰዋለች ።  እንዳይነካት ደግሞ አባቴ በሰማይ አለ አስቆጥኻለሁ  ፡  አስገርፈኻለዉ እያለች ታስፈራራዋለች።  እንዲህ አድርጎ ጥጋብ ምንድን ነዉ  !? አባት የሌለዉ ማንን አይታለች  !?  ጌታዋ .... አካል ቀርፋፋ ነዉ... ጎተት ጎተት ይዎድዳል  እያለ ያማዋል ።  እርሷ አካል ገንቦዬ ነዉ እንዳሻሁ እፈላበታለሁ ትላለች ።  ዋ ! አባትና ልጅ ምነዉ ሃይ ባይ አጡ ። የገዛ ዘበናይ ልጁን ተሸክሞ ሲወዛዎዝ ነዉንጅ አካልማ ይቺን መንቃራ አዉጥቶ ቢጥል  የት በደረሰ ነበረ። ይቺ ወደል የት የበላችዉ እንጀራ እንዳከበዳት እንጃ ። ይኸዉ ሰዉን ሁሉ ታንገዳግደዉ ይዛለች። ወዳጅ ወዳጁን አካል ምንድን ነዉ አለዉ !? አለሁኝ መባያ አለዉ ።  አዬ ሚስኪኑ እርሷን ይዞ ምኑን አለሁት ይላል ! እስከመቼ የእሷ እንስራ ሁኖ ስታብበት ትኖራለች !? ይቺ አይናፋር ማስጠሎ ! ደግሞ በተወለወለ አካል ስር ተቀምጣ '' ዉበት ረጋፊ ነዉ ደምግባትም ከንቱ ነዉ '' ትላለች ።  እስቲ ትዉጣና ትታይ ጀግና ከሆነች ።  ተደብቆ መፎከር ማን ያቅተዋልና ነዉ ። ጀግናስ አካል ነዉ ማስጠሎቷን ደብቆ ያኖራታልና ። እርሷ ግን የዉስጥ እሳት ሆነችበት እለት እለት መልኳን እያጋባች አመነመነችዉ ። አባቷ በሰማይ ሁሉን መጋቢ ነኝ ይላል ።  ያለ'ኔ ገበሬ የለም ይላል ።  ልጁ ግን በሰዉ አካል ስር ትልከሰከሳለች ።  በልታም ጠገብኩ የለ ! ጠጥታም አታስመሰግን ።  ሁሌ የሚያቀርቡላትን እንዳማረጠች ነዉ ።  የጨዋ ልጅ በሆነችና የሰጧትን አመስግና በበላች ነበር ።  እርሷ ግን የምትተፋዉ በለጠ ።  ምነዉ ቀጭ ማጣት እቴ ! ወዳጅ ወዳጁን አለኹ አለኹ አዉቃለኹ አዉቃለሁ የሚል ሰዉ ምን ይመስላል አለዉ  !? ነፍሱ በሆዱ የሞተችበትን ሰዉ ይመስላል ብሎ መለሰለት ። ይቺ ግም ! የሞተች ለት እንዴት እንደምትሸትት ባዎቀች ።  ሁሌ እንዳማሩ መቅረት ያለ መስሏታል ።  የተወለወለ አካል ከስንት አንዴ ብታገኝ ነዉ ። ደግሞ አንዴ  ... ንቅሳት አምሮኛልና ተነቅሼ ካልሞትኩ አለች ።  አይ ዘመናይ መሆን እቴ ! አካል ደግሞ እኔ ላይ አትነቀሽም ፣ ሲያምርሽ ይቀራል እንጅ .... ፊቴንም ግንባሬንም ደረቴንም ጡንቻዬንም እምቢ አለ ።   አንተ ሞኝ አፈር ላይ ልኳኳል ማን አለ ።  እኔስ በሰዉ ደረት ስር በእሳት እነቀሳለሁ ይብላኝልህ ላንተ ስትረግፍ ለምትቀረዉ አለችዉ ።      ፍቅርም የህይዎት ንቅሳት ነዉ ። ©ቴዎድሮስ እንደ ጻፈው @wegochi
Mostrar todo...
👍 1🔥 1👏 1

❤‍🔥 2 2💘 1
"ሁላችንም አለማችን፤ ጠባሳችን ጋር ነው። --አዳም ረታ
Mostrar todo...
❤‍🔥 4🤝 1
1👌 1