cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የኔ መዝሙር

በዚህ ቻናል የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መሠረት ያላቸው መዝሙሮች ከግጥሞቻቸው ጋር ይቀርባሉ።

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
264
Suscriptores
Sin datos24 horas
+27 días
-130 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

✝ መርቆርዮስ ✝ መርቆርዮስ /4/ የችግሬ ደራሽ ና በፈረስ እንባዬን ልታብስ ፈጥነህ ድረስ ባስልዮስ ጎርጎርዮስ ሰምሯል ልመናችው በጸሎት ዘለለ ታምር አሳያቸው እናንተን የረዳ መጥቶ በፈረስ ዛሬም ለኛ ይድረስ ይምጣ መርቆርዮስ አዝ ዳኬዎስ ተገሏል ሀይማኖት ይስፋፋ ብሎ መሠከረ መርቆርዮስ ሀያል ገጸ ከለባቱ ባህሪ ቀየሩ እሱን ለማገልገል ከግሩ ስር አደሩ አዝ ትካዜ ሀዘኔ ይርቃል ጭንቀቴ መርቆርዮስ ሲመጣ ሲገባ ከቤቴ በጸሊም ፈረሱ እየገሰገሰ መርቆርዮስ ወዳጄ ስጠራው ደረሰ አዝ ስቃዩን ሊያረዝም ዳኬዎስ ወደደ ከጨለማ እስር ቤት ታስሮ ተወሰደ በጋለ አሾህ ብረት መርቆርዮስ ተወጋ ስሙ ተሰየመ ከሰማእታት ጋር አዝ አልፈራም መከራ አልፈራም ችግር መፍቀሬአብ ካለ ያ ፒሉፓዴር ቄሳርያ ስሚ መርቆርዮስ ታሰረ ወህኒ ቤቱ በራ እግዚአብሔር ከበረ t.me/mezmuryene
Mostrar todo...
መዝ መርቆርዮስ የችግሬ ደራሽ.mp36.14 MB
ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን ✝ ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን  ሶበ ተዘከርናሃ ለፅዮን ውስተ አፍላገ ባቢሎን ህየ ነበርነ ወበከይነ እንዚራቲነ ሰቀልነ ውስተ ጒዓቲሃ ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን በባቢሎን ወንዞች አጠገብ ተቀምጠን አለቀስን መሰንቆዋችንን ሰቀልን በዛፎቿ ላይ አዝ ፅኑ መከራን ተቀበልን ተጨነቅን በፈተና የደዌ ሞት በላያችን እንደዝናብ ወርዶዋልና አህዛብም ዘበቱብን እንዲ ብለው በየተራ ዘምሩለት ላምላካቹ ቢያድናቹ ከመከራ እግዚአብሔር ፅዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን አዝ የማረኩን በጦራቸውበኃይላቸው የተመኩ በጽዮን ደጅ ያለፍርሃት  የጽዮንን ክብሯን ነኩ ይህን ያየ ከላይ ሆኖ በደመና ተሸፍኖ ባቢሎንን አሻገረ የማረኩንን በትኖ እግዚአብሔር ፅዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን አዝ ስጋችንን ሊገንዘን የሞት ጥላ ቢያጠላም እናልፋለን ሁሉን ባንቺ የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ቅድስት ሆይ ከባረክሽን እንድናለን ከደወዌያችን ለስጋና ለነብሳችን መድኃኒት ነሽ እናታችን እግዚአብሔር ፅዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን የመጋቤ ምሥጢር ሰሎሞን ተስፋዬ ❤️🌿 እንኳን ለጽዮን ማርያም አደረሳችሁ አደረሰን 🌿❤️ t.me/mezmuryene
Mostrar todo...
አዲስ_መዝሙር_ጽዮንን_ባሰብናት_ጊዜ_መጋቤ_ምሥጢር_ሰሎሞን_ተስፋዬ360p_1_24122021.m4a7.02 MB
ታማኝ ምስክር ነህ ✝ ታማኝ ምስክር ነህ ለታመነው ጌታ በአስፈሪው እሳት ፊት ትጥቅህ ያልተፈታ ቂርቆስ አይተንሃል እምነትህ ሲረታ የልጅነት ልብህ በእምነት ጎልምሶ ፍጥረት አስደመመ ፍርሃትን አፍርሶ ጌታውን ተላብሶ አዝ አላሰጋህ እሳት አንተ ብላቴና ገና ከማህፀን ጌታ አይቶሃልና በፍቅሩ ልትጸና አዝ በጌታህ ስም ታምነህ ድንቅን አድርገሃል ለክርስቶስ ፍቅር ራስህን ሰሃተሀል ሰማዕት ሆነሃል አዝ በዓለም መጠላት መመነን ለጌታ አቁሞሃል ቂርቆስ ከምርጦቹ ተርታ ነፍስህ ክብርን መርጣ t.me/mezmuryene
Mostrar todo...
ታማኝ ምስክር ነህ.mp32.38 MB
 🕊  ጾመ ነቢያት   🕊     🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟 የጾመ ነብያት ምስጢር ምንድነው ? ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨      ጾመ ነቢያት [ የገና ጾም ] ከልደት አስቀድሞ የሚጾም ጾም ነው፡፡ ከህዳር ፲፭ [ 15 ] ጀምሮ ለ ፵፫ [43] ቀናት የሚጾም ሲሆን ፋሲካው [ ፍቺው ] በልደት በዓል ነው፡፡ ይህም ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ቅዱሳንና ምዕመናን ጾመውታል፡፡ ጾመ ነብያት ስያሜውን ያገኘው ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ስለተፈጸመበት ነው፡፡ በየዘመናቱ የተነሡ ነቢያት እግዚአብሔር ወደፊት ሊያደርግ ያሰበውን በእምነት ዓይን እያዩ ምስጢር ተገልጦላቸው የራቀው ቀርቦ ፣ የረቀቀው ገዝፎ ጎልቶ እየተመለከቱ ትንቢት ተናገሩ ፤ ያዩትም መልካም ነገር እንዲደርስላቸው ጾሙ ጸለዩ፡፡ ነቢያት ከእመቤታችን ስለ መወለዱ ፥ ወደ ግብፅ ስለ መሰደዱ ፥ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ ፥ ብርሃን በሆነው ትምህርተ ወንጌል ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ ፥ ለሰው ልጆች ድኅነት ጸዋትወ መከራ ስለመቀበሉና ስለ መሰቀሉ ፥ ስለ ትንሣኤው ፥ ስለ ዕርገቱና ስለ ዳግም ምጽአቱ ትንቢት ተናግረው አላቆሙም፡፡ ለአዳም የተሠጠው ተስፋ ተገልጦላቸው ለተናገሩት ትንቢት ፍፃሜ እንዲያደርሳቸው ፈጣሪያቸውን ተማፀኑትም እንጂ፡፡ በየዘመናቸው ፦ "አንሥእ ኃይልከ ፣ ፈኑ እዴከ" እያሉ ጮኹ፡፡ በጾምና በጸሎት ተወስነውም እግዚአብሔር ሰው የሚሆንበትን ጊዜ በቀናት ፣ በሳምንታት ፣ በወራትና በዓመታት ቆጠሩ፡፡ ለምሳሌ ነቢዩ ኤርምያስ ስለ ሥጋዌው ትንቢት በተናገረ በ፬፵፮ ዓመት ጌታችን ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኗል፡፡ ነቢያት ተስፋው በዘመናቸው ተፈጽሞ በዓይነ ሥጋ ለማየት ባይችሉም እግዚአብሔር ፦ "አያደርገውን አይናገር የተናገረውን አያስቀር" ብለው አምነው ከወዲሁ ተደሰቱ፡፡ ለዘመነ ሥጋዌ ቅርብ የነበሩ እነ ነቢዩ ኢሳይያስ ጾሙ እንዴት መፈጸም እንዳለበት ተናግረዋልም፡፡ [ኢሳ.፶፰፥፩]፡፡ በመሆኑም በጌታ ልደት ትንቢተ ነቢያት ስለተፈጸመበት ይህ ጾም "የነቢያት ጾም" ይባላል፡፡ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት ስለሆነም "ጾመ ስብከት" ይባላል፡፡ ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል፤ በዚህም ምክንያት የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት፡፡ እነርሱም፦ † ፩. [ ጾመ አዳም ] ፦ አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከገነት ከተባረረ በኋላ በፈጸመው በደል አዝኖ ፥ ተክዞ ፤ አለቀሰ [እንባ ቢያልቅበት እዥ እስከሚያፈስ ፤ እዥ ቢያልቅበት ደም በዓይኑ እስከሚፈስና ዓይኑ ይቡስ ወይም ደረቅ እስከሚሆን ድረስ አለቀሰ] ፥ ጾመ፣ ጸለየ፡፡ ከልብ የሆነ ጸጸቱን፣ ዕንባውን፣ በራሱ መፍረዱንም እግዚአብሔር አይቶ ተስፋ ድኅነት ሰጠው፡፡ "ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ፣ በደጅህ ድኼ ፣ በዕፀ መስቀል ተሰቅዬ፣ ሞቼ አድንሃለሁ፡፡" የሚል ነው፡፡ [ገላ. ፬፥፬፣ መጽ.ቀሌምንጦስ] ስለዚህ ጾሙ የተሰጠው ተስፋ ፥ የተቆጠረው ሱባኤ ስለተፈጸመበት "ጾመ አዳም" ይባላል፡፡ † ፪. [ ጾመ ነቢያት ] ፦ ነቢያትም የምሥጢረ ሥጋዌ ነገር ተገለጦ ስለታያቸው ፣ ክርስቶስ ለሰው ልጅ የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ በትንቢት ተመልክተው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል፡፡ ይህ ጾም ከአባታችን አዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የተነሱ አበውና እናቶች : ድኅነትንና ረድኤትን ሲሹ የጾሙት ጾም ነው:: በተለይ አባታችን አዳም : ቅዱስ ሙሴ : ቅዱስ ኤልያስ ፣ ቅዱስ ዳንኤልና ቅዱስ ዳዊት በጾማቸው የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው:: [ዘዳ.፱፥፲፱ ፣ ነገ.፲፱፥፰ ፣ ዳን.፱፥፫ መዝ.፷፰፥፲ ፻፰፥፳፬] ቅዱሳን ነቢያት በጭንቅ በመከራ ሆነው የጾሙት ጾም ወደ መንበረ ጸባኦት ደርሶ: ወልድን ከዙፋኑ ስቦታል:: ለሞትም አብቅቶታል:: † ፫. [ ጾመ ሐዋርያት ] ፦ ሐዋርያት "ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብራለን ፣ ልደትን ምን ሥራ ሠርተን እናከብረዋለን?" ብለው ከልደተ ክርስቶስ በፊት ያሉትን ፵፫ ዕለታት ጾመዋልና፡፡ † ፬. [ ጾመ ማርያም ] ፦ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ቅድስናዋን አይቶ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ አምላክን ያለ ሰስሎተ ድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ ጸንሳ እንደምትወልደው ቢነግራትም የትሕትና እናት ናትና "ምን ሠርቼ የሰማይና ምድርን ፈጣሪ እችለዋለሁ?" ብላ ጌታን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማለችና "ጾመ ማርያም" ይባላል፡፡ † ፭. [ ጾመ ፊልጶስ ] ፦ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ እያስተማረ ሳለ በሰማዕትነት ሲሞት ፤ አስክሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ ፤ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስክሬን እንዲገለጽላቸው ከኅዳር ፲፮ ጀምረው ጾመው በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስክሬን ተመልሶላቸዋል፤ ነገር ግን አስከሬኑ ቢመለስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል፡፡ † ፮. [ ጾመ ስብከት ] ፦ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት ፥ የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት ፥ የምስራች የተነገረበት ስለሆነ ጾመ ስብከትም ይባላል፡፡ † ፯. [ ጾመ ልደት ] ፦ የጾሙ መጨረሻ [ መፍቻ ] በዓለ ልደት ስለሆነ "ጾመ ልደት" ይባላል፡፡ በጾማችን በጸሎታችን - ስለ ቤተክርስቲያን ፥ ስለ ሀገር እና ስለ ሕዝብ በማሰብ በእንባ እራሳችንን ዝቅ በማድረግ እንጾም ዘንድ ይገባል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡ ወለወላዲቱ ድንግል ፡ ወለመስቀሉ ክቡር፡፡
Mostrar todo...
✝ የምህረት መላክ ✝ በሲና በረሃ ያወረደዉ መና የእስራኤል መሪ በአምደ ደመና የመላክት አለቃ ሚካኤል ነዉና የምህረት መላክ ቅ/ሚካኤል /2/ ፈጥኖ ይደርሳል ያማልደናል በስጋም በነብስ ይታደገናል/2/ አዝ ዳንኤልን ከአናብስት ባህራንን ከሞት ቅድስት አፎምያን ከሰይጣን ያዳንካት እኛንም አድነን መለአከ ምህረት አዝ ክብሩ ታላቅ ነዉ ድንቅ ነዉ ስሙ ማን እንደ እግዚያብሔር መላከ ምክሩ ቅዱስ ሚካኤል ድንቅ ነው ታምሩ አዝ ተራዳይነቱ መፅሐፍ መስክረዋል ስለ ህዝብ ልጆች ሚካኤል ይቆማል ምህረት የሚያሰጥ ኪዳን ተቀብሏል አዝ በመታሰቢያዉ ቀን ይነበብ ድርሳኑ ዝክሩን እናዘክር ይከበር በአሉ ሚካኤል ያድናል ምልጃዉ ቃልኪዳኑ t.me/mezmuryene
Mostrar todo...
የምህረት መላክ.m4a2.16 MB
✝ በሰማይ ሰልፍ ሆነ ✝ በሰማይ ሰልፍ ሆነ ውጊያው ተጀመረ በሚካኤል ነገድ ሳጥናኤል አፈረ ያቃጥላል ክንፉ የጠላትን ሰፈር አያልቅም ቢወራ የሚካኤል ነገር ዘንዶው ተወርውሮ ከምድር ወደቀ የቀድሞውም እባብ በክንዱ ደቀቀ ሚካኤል ሲነሳ ከሳሽ ይሸበራል በኃይለ መስቀሉ ተሰብሮ ተጥሏል አዝ ዲያቢሎስ አልቻለም ሚካኤል ፊት መቆም በተማመነበት በነገዱ አልዳነም የሰማዩን ስፍራ ለቀቀ ተመትቶ ሳጥናኤል ጨለመ ሚካኤል አብርቶ አዝ የሐሰት አባቷ ዛሬ ስፍራ አጥቷል መልአካዊ ኃይሉን በትዕቢት ተነጥቋል ሆኗል ምድረ በዳ እጅግ ተቅበዝብዞ አብረው የወደቁት ነገዶቹን ይዞ አዝ ስሙን እንጠራለን ኃይሉን እንዲሰጠን የማሸነፊያውን ክብሩን እንዲያለብሰን በመንገዳችን ላይ ሚካኤል ስላለ ሁሉንም አለፍነው በእርሱ እየቀለለ ዘማሪ አቤል መክብብ t.me/mezmuryene
Mostrar todo...
በሰማይ_ሰልፍ_ሆነ_ሚካኤል_አቤል_መክብብ_.mp35.86 MB
🌷ንግስተ ሰማያት🌷 ንግስተ ሰማያት ወምድር ማርያም ድንግል /2/ ተፈጸመ /5/ ማኀሌተ ጽጌ /2/ 🌹🌹🌹🌹
Mostrar todo...
ተፈጸመ_5_ማኅሌተ_ጽጌ_2__xAdoeHiXzJk_139.m4a9.23 KB
✝ መድኃኔዓለም ✝ መድኃኔዓለም አንተን ማን ይመስላል የከበደን በስምህ ይቀላል የማችለው የለም የሚሳንህ ነገር ቀላያት አይፀኑም አንተ ስትናገር አልቅሼ ነገርኩ በኃዘን ደክሜ አብዝቼ ጠራሁ ከመቅደስህ ቆሜ አዘነበልክልኝ ቃሌን መች አለፍከው አይዞህሽ ልጄ ብለህ እንባዬን አበስከው አዝ ከፊት እየቀደምክ መንገድ የምትመራ ብርሃን የሆንክልን በመስቀልህ ስራ እውነተኛ መድኅን የሕይወት እንጀራ የሁሉ አስገኚ ግሩም የእጅህ ስራ አዝ የአላለፍኩት የለም አንተን ተጠግቼ መጽናቴ በአንተ ነው ስምህን ጠርቼ የበረከቴ ምንጭ የጎጆዬ ሙላት ለደከመች ነፍሴ ማረፊያ ሆንክላት አዝ ዳግም ልጅህ ተባልኩ በደሌን ሻርክልኝ በከበረው ደምህ ባርያህን ገዛህኝ ሳወድስህ ልኑር ዘወትር በዝማሬ መድኃኔዓለም ሆንከኝ ሞገስ እና ክብሬ t.me/mezmuryene
Mostrar todo...
መድኃኔዓለም አንተን ማን ይመስላል.mp311.66 MB
✝ታላቅ በሆነው እምነትሽ ታመንኩኝ✝ ዘማሪት ሲስተር ልድያ ታደሰ t.me/mezmuryene
Mostrar todo...
ታላቅ_በሆነው_እምነትሽ_ታመንኩኝ_ዘማሪት_ሲስተር_ልድያ_ታደሰ_mXi4mmJmkl8_140.mp34.92 MB
✝ አየኸው ደመራ ✝ አየኸው ደመራ መስቀል ሲያበራ/2/ መስቀል አለ ወይ ቆሟል ወይ አለእንጂ ለምጽ ያነጻል እንጂ ያው ቆሟል ድውይ ይፈውሳል አምነዋለሁ የት አገኘዋለሁ አለልሽ እሰሪው በአንገትሽ ከልብሽ ተሳለሚው አምነሽ እኮራለሁ በእፀ መስቀል ይፈውሳል ሙታንን ያስነሳል ድል ያደርገል ድውይ ይፈውሳል t.me/mezmuryene
Mostrar todo...
625693767.mp34.57 KB
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.