cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

❤️ቅን ልቦች❤️

Mostrar más
Etiopía6 318Amárico6 088La categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
839
Suscriptores
Sin datos24 horas
-77 días
-3130 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#ሺ_ሆህያት ሺ ሆህያት ቢሰደር ሺ ቃላት ቢመጣ፣ አንድም ላይገልጥልኝ የልቤን እውነታ፣ የመውደዴን ነገር  የፍቅሬን ልኬታ፣ በእኔነቴ ሙሉ ላንተ የኝን ቦታ፣ ይሄው እጽፋለው ሺህ ቃላት ሰድሬ፣ ተለያይቶ አያውቅም ብዕር ከደብተሬ፣ ፅፋለሁ ጽፋለሁ ፣ ደግሜ አጠፋለው ከሀ እጀምራው፣ እኔማ.... ፍቅርን እንደዋዛ በትንሿ ክታብ በስንኝ ቋጭቼ፣ ልጽፍልህ ነበር እስኪዝሉ እጆቼ፣ ግን ከንቱ ልፋት ነው ..... አንተን የሚመጥን ላላገኝ አንድ ቃል፣ መከረኛው ብዕር ሌት ተቀን ያለቅሳል፣ እናልህ አለሜ ከእንግዲህ ይበቃኛል፣ በደካማ ጽሑፍ ማፍቀሬን አልገልጥም፣ እገጥማለው ብዬ ብዕር አልጨብጥም፣ ግን ውዴ...... ድንገት ቃል አግኝቴ ብዕር እንኳን ባጣ፣ እጽፍልህአለው በደሜ ጠብታ !!!            🦋🙏ከወደዱት ሼር🙏🦋       ‌‌‌‌‌‌‌  ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! ➢           ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄┄:      ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌             ቅን ልቦች👇👇👇                  ❤️ @Qin_Liboch ❤️                  ❤️ @Qin_Liboch ❤️                ,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣🌹,,,,,              ••●◉Join us share◉●••    
Mostrar todo...
00:08
Video unavailableShow in Telegram
በፍቅር አለም ውስጥ እንዲህ ይላሉ!     ለአፍቃሪ ጥሩ አቀባበል ማድረግ ቢያቅትህ አሸኛኘቱን ግን አሳምር። ─━━━━♥️⊱✿⊰♥️━━━━━─        ,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,             •═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•                 ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄   ‌‌‌ ⚡️ቻናላችንን #ሼር በማድረግ ሌላ ምርጥ ምርጥ ታሪኮችን ይመልከቱ ያንብቡ     ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄   ‌‌‌            ቅን ልቦች👇👇👇          ❤️ @Qin_Liboch ❤️          ❤️ @Qin_Liboch ❤️        ,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣🌹,,,,,      ••●◉Join us share◉●••   ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
Mostrar todo...
00:08
Video unavailableShow in Telegram
‍ ‍ 🌺 ምኞቴ🌺 እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በቅን ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ የቀረበ💛        ▬▬▬❁ክፍል ሀያ▬▬▬          #የመጨረሻ_ክፍል ከተጓዘበት አለም የመለሰችዉ ኤዲ ናት፡፡ ..."ምን ሆንክ የኔ ፍቅር?" አለችዉ፡፡ 'የኔ ፍቅር' የምትለዋን ብቻ ነዉ የሰማት ..."ወዬ ኤዲዬ" አላት እንደመደንገጥ እያለ... "እ..." ፡፡ እሷም ጥያቄዋን እንዳልሰማት ስላወቀች ..."ምን ሆነክብኝ ነዉ እንደዚህ የምታስበዉ?" አለችና ጥያቄዋን ደገመችለት፡፡ እንዳለፈዉ ጊዜ ሊደብቃት አልፈለገም፡፡ ሁሉንም ነገር ከኤዲ ጋር ተነጋግሮ መወሰን እንዳለበት አምኗል፡፡ ..."ምን... የረድኤት ጉዳይ ትንሽ አሳስቦኝ ነዉ" አላት ፈራ ተባ እያለ ..."የረዲ ጉዳይ ምን? የሷ ጉዳይ ምን ያስጨንቀሃል?" ብላ እየጠየቀችዉ ወደሱ ቀረብ አለችና ከጎኑ ቁጭ አለች፡፡ ..."ኤዲዬ ... አሁን እንዴት ብዬ ነዉ መጋባት እንደማንችል የምነግራት?" አላት፡፡ ..."የኔ ፍቅር ረዲንማ ማግባት አለብህ" አለችዉ፡፡ ..."ለልጅ ብዬ አልነበር የማገባት ያዉ አሁን ደግሞ ዉዷ ሚስቴ በሆዷ ያብራኬን ክፋይ ይዛልኛለች!" ."አየህ ውዴ...(በትኩረት እየተመለከተችዉ ነበር) መጀመሪያም ተሳስተን እንደነበር አሁን ነዉ የገባኝ" አለችዉ፡፡ ..."እንዴት ዉዴ? ምንድን ነዉ የተሳሳትነዉ?" አላት እሱም ወደሷ ዞወር እያለ፡፡ ኤዲ ደግሞ ይበልጥ ወደሱ እየተጠጋች እጆቿን ትከሻዉ ላይ ጣል እያረገች... ..."መጀመሪያም እሄን ያህል ዓመት ታግሰን በችኮላ መወሰን አልነበረብንም ትንሽ መታገስ ነበረብን" አለችው፡፡ ...መጥፎ እንዳልሆንክ አዉቃለሁ፤ ስለ ጥሩነትህ የማወራልህ፤ ስለ መልካምነትህ የምመሰክርልህ ሚስትህ ነኝ ስለዚህ ረዲን አግባት!!!! እሺ ፍቅሬ....!!!" አለችዉ፡፡ በቃ የኔ ፍቅር ሁሉንም ነገር ነገ እናወራለን ብሏት ዛሬ የደስታችን ቀን ናት በቃ አሁን እንተኛ አላትና ተኙ፡፡ ..." ረድኤት እንቅልፍ እንቢ ብሏት ስትገላበጥ ተነስታ ቁጭ ስትል ምንም እንቅልፍ በዓይኗ ሳይዞር ሊነጋ ነው፡፡ሊነጋጋ አከባቢ አንድ ነገር አሰበች፡፡ለምን?የሰው ትዳር ውስጥ ገብቼ ፍቅራቸውን ለምን?አቀዘቅዘዋለው ግን ለምን?ለኔ ያለውን ፈጣሪ ልክ እንደ ቢኒ ዓይነት አፍቃሪ እንዲሰጠኝ መለመን ስችል፡፡  እያለች ብዙ አሰበች መንጋቱ አይቀርምና ነጋ ልክ እንደነጋ ብዙም ሳትቆይ ረድኤት ለቢኒያም ደወለች፡፡ ስልኩን አንስቶ ረድኤትን ማዋራት ጀመረ ..."ሄሎ ረዲ...." ..."ቢኒ ሰላም ነው"አለችው፡፡ ..."ደህና ነኝ..."ማታ እኔና ፈቲ ስላንቺ" ብሎ ሳይጨርስ" ረዲ... "ሄውልህ ቢኒ ምንም እንኳን ባንተ ፍቅር ብከንፍም ግን ያ እንደዛ ምትሳሱለትን የሞቀ ፍቅር በመሃላችሁ ገብቼ ማቀዝቀዝ በጭራሽ አልፈልግም እኔ ባንተና በኤዲ ፍቅር በጣም ነው የምቀናው ባይሆን ለኔም እንዳንተ አይነት ባል ፈጣሪ እንዲሰጠኝ ለምኑልኝ"አለችው፡፡ ..."ረዲ ምንም ሆነሻል ቤቲስ እነ እማማ ና አባባስ ምን ይሉኛል፡፡አላት ..."አይ ቢኒ አታስብ ለእማዬም ለአባዬም እኔ አስረዳቸዋለው እዚህ ጊቢ ውስጥ ከአንዱ ጋር ፍቅር ይዞኛል ብዬ እነግራቸዋለው፡፡ ደሞ እነሱም የሚፈልጉት እሄንኑ ነው በጣም ነው ደስ ሚላቸው አታስብ አለችውና ኤዲን ሰላም በልልኝ ብላ ስልኩ ዘጋችው። ቀናት በቀናት ወራት በወራት እየተተኩ የኤዲ መውለጃ ጊዜም ደረሰ ኤዲም ቆንጂዬ በጣም የሚያምር ልጅ ወለደች<< በፀሎት>> አለው ስሙን ቢኒ። ቢኒና ኤዲ በጣም ደስተኞች ናቸው። ከ 4 አመት ቡኃላ... ...ረድኤት ተመርቃ ምን የመሰለ ለአይን እንኳን የሚያሳሳ ባል አግብታ በፍቅር ኑሮዋን ጀምራለች።   ፈጣሪ ሁሌም ከምትወዱት አይለያቹ።                                         ተፈፀመ ምኞትቴ የተሰኘው የፍቅር ታሪክ ዛሬ በዚህ መልኩ ተጠናቀቀ ለሰጣችሁኝ አስተያየት ከልብ አመሰግናለሁ🙏።           ♥️ተ♥️ፈ♥️ፀ♥️መ ታሪኩን እንደወደዳችሁት እና እንደ ተማራችሁበት እምነታችን ነው። በቅርቡ አዲስ ታሪክ እንጀምራለን አሳብ አስተያየት ማድረስ ትችላላችሁ እናመሰግናለን። ✎ ክፍል ሀያ ከ 100 Like በኋላ ሌላ ታሪክ❤️‍🩹 ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር♥️ ማድረግ አይርሱ።           ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄┄:      ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌             ቅን ልቦች👇👇👇                  ❤️ @Qin_Liboch ❤️                  ❤️ @Qin_Liboch ❤️                ,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣🌹,,,,,              ••●◉Join us share◉●••    
Mostrar todo...
‍ 🌺 ምኞቴ🌺 እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በቅን ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ የቀረበ💛        ▬▬▬❁ክፍል አስራ ዘጠኝ▬▬▬ አለቻት እሺ እደውልልሻለው ኤዲዬ ደህና ሁኝ ብላ ረዲ ስልኩን ዘጋችው። ...ቢኒያም ከስራ መጥቶ ወደ ቤቱ ሲገባ ኤዲ ቤት የለችም፡፡ "ኤዲ...ኤዲዬ!" እያለ ተጣራ ምናልባት ወደ ጓዳ ዉስጥ እንደሆነች ብሎ ኤዲ ግን የለችም ነበር፡፡ ወደ ዉጭ ወጣና እማማ በለጡን ተጣራና... ..."ኤዲ የት ሄዳ ነዉ?" አላቸዉ፡፡  እማማ በለጡም ..."እ...ሐኪም ቤት ሄዳ ነዉ፡፡" አሉት፡፡ ቢኒ ድንግጥ አለ፡፡ ..."መቼ? ምን ሆና? ምን አገኛት? እና አትከተሏትም ነበር ወይም አደዉሉልኝ?" እያለ ጥያቄ በጥያቄ ላይ እየደራረበ እማማ በለጡን የጠየቃቸዉን ጥያቄ የመመለሻ አፍታ አሳጣቸዉ፡፡ ይሄን ከማለቱ ወዲያዉ የግቢዉ በር ተከፈተና ኤዲ መጣች፡፡ በጣም አምሮባት፤ ከደስታ ብዛት ፊቷ ላይ ፀሐይ የወጣች እስኪመስል ድረስ አብርታለች፡፡ በረዶ የሚመስሉት ነጫጭ ጥርሶቿ ይፍለቀለቃሉ፡፡ ቢኒያም እንዳያት በጣም ደስ አለዉ፡፡ አሟት ነበር የመሰለዉ እሷ ግን እንደጨረቃ ፈክታ፤ ከፀሐይ አብርታ ብቅ አለች፡፡ ገና የነጋ መሰለዉ፡፡ ለሱ ንጋቱ ኤዲ ነች፡፡ ያለ ኤዲ ሁሌም ጨለማ ነዉ የሚሆንበት፡፡ ወደነሱ ቀረበችና..."ቢኒ ና ወደ ቤት እንግባ" ብላዉ እጁን ይዛ ሳበችዉ፡፡ ሰላምታ እንኳን አልሰጠቻቸዉም ነበር፡፡ ደስታ አስክሯታል፡፡ ቢኒም ምንም አልተናገረም ዝም እንዳለ ተከተላት፡፡ እማማ በለጡ ..."ኤዲዬ ደህና መጣሽ?" ፊቷን ሳታዞር ወደ ቤቷ እያመራች "አዎ እማማ" አለቻቸዉ፡፡ ዉስጧ የሆነ ነገር አለ፡፡ ለቢኒያም እስከምትነግረዉ ቸኩላለች፡፡ ቤት ከገቡ ቡኋላ እየተፍለቀለቀች በደንብ ሳቀች፡፡ ..."ኤዲዬ ምን ተገኝቶ ነዉ? ሆስፒታል አይደለም እንዴ የሄድሽዉ" አላት ቢኒ ..."አዎ ሆስፒታል ነበር የሄድኩት" አለችዉ ..."ምንሽን አሞሽ ነዉ?" ..."ሆዴን" ..."ወይኔ በፈጣሪ እንዴት አደረገሽ የኔ ፍቅር"  ብሎ እጆቹን ሆዷ ላይ አድርጎ አይን አይኗን ያያታል፡፡ ኤዲ አሁንም ጥርስ በጥርስ እንደሆነች ናት፡፡ የምትስቀዉ እሱን ላለማስጨነቅ እንደሆነ አድርጎ ነዉ ያሰበዉ - ቢኒ፡፡ ..."የኔ ፍቅር" አለችዉ ድምፅዋን ለስለስ አድርጋ ..."ወዬ የኔ ቆንጆ" ..."የሆነ ነገር ልንገርህ?" ..."አዎ ንገሪኝ ፍቅሬ...ምንድን ነዉ እሱ?" እያለ ይመለከታታል፡፡ ..."የ ሶስት ወር እርጉዝ ነኝ!" አለችዉ፡፡ ቢኒ የሰማዉን ማመን አቃተዉ፡፡ አራት አመት እምቢ ብሏት እንዴት አሁን?? ..."እዉነትሽን ነዉ ኤዲዬ? ለማረጋገጥ ያክል ጠየቃት፡፡ ኤዲ ለአዎንታ እራሷን ነቀነቀች፡፡ ቢኒ ምድር ጠበበችዉ፡፡ ኤዲን እቅፍፍፍ አደረጋት፡፡ ሰዉነቷ ላይ ጥምጥም ብሎባት ይስማት ጀመር፤ ግንባሯን...፤ አይኗን...፤ ጉንጯን...፤ አፍንጫዋን...፤ ከንፈሯን...የቀረዉ የለም፡፡ በየመሃሉ እየጮኸ 'ፈጣሪ ሆይ ተመስገን' ይላል።ኤዲም ትፈለቀለቃለች፡፡ ደስታ ቢገድል ኑሮ ከቢኒ ቀድማ ትሞት ነበር፡፡ ከምንም በላይ ያስደሰታት መፀነሷ ሳይሆን ቢኒያም እንደዚህ ሲደሰት ማየቷ ነዉ፡፡ በርግጥ የደስታዉ ምንጭ ማርገዟ ቢሆንም...፡፡ቢኒ አሁንም እየጮኸ ጌታዉን ማመስገኑን አላቋረጠም፡፡ 'ጌታ ሆይ አመሰግንሀለው' እያለ ላንቃዉ እስኪበጠስ ድረስ ይጮሃል፡፡ እንደገና ቀጥ ብሎ ፈቲን በመሳም ያጣድፋታል፡፡ ደስታቸዉ እንደቀጠለ ነዉ፡፡... . ...ኤዲና ቢኒ ከዚያ ሁሉ ፈንጠዝያ ቡኃላ አብረዉ ቁጭ ብለዉ ራት እየበሉ ረዲ ደወለች፡፡ ቢኒም ስልኩን በኤዲ ሊያስነሳዉ አለና ..."ሆ ሆ ነገሩ እናንተ ወሬ ከጀመራችሁ ስለማታበቁ እኔ ካዋራኃት በኃላ እሰጥሻለሁ" ብሏት ስልኩን አንስቶት ረድኤትን ማወራት ጀመረ፡፡ እያወሩ እያለ ኤዲ አላስወራም አለችዉ፡፡ በትክክል እንዳያወራ ታጎርሰዋለች፡፡ በመሃል ትስመዋለች ቅብጥ ቅብጥብጥ አለችበትና ረበሸችዉ፡፡ ቢኒም "ዉይ እንቺ እስኪ አዉሪያት" ብሎ ስልኩን ሰጣት፡፡ ... ኤዲና ረዲ ማዉራት ጀመሩ፡፡ ..."ረዲዬ ራት እየበላን ነዉ፡፡ እንብላ አለቻት ኤዲዬ የተባረከ ይሁን ብሉ እሄ ቢኒ ሽሮ እንኳን መስራት አይችልም ስትላት ሁለቱም ተሳሳቁ በተለይ የኤዲ ሳቅ ከስከዛሬዉ ለየት ያለ ነበር፡፡ ፍንድቅድቅ አለች፡፡ ..."ደግሞ ለሽሮ ሌላም አስተምረዋለሁ" አለቻት ረዲ ለፈቲ ..."ሌላ ሌላዉንማ እኔ አስተምሬዋለሁ" ብትላት በሳቁ ላይ ቢኒም ተሳትፎ ነበር ከት ብለዉ ሳቁ፡፡ ሃሃሃሃ ሂሂሂ ኪኪኪኪ ... ..."ሆ" አለች ረዲ ..."ራትሽን የምትበይዉ ምላስ ነዉ እንዴ ወሬ ለቆብሻልሳ" ..."እረ እሱን ተይዉና ...ይልቅ የምወልዳት ልጅ ሴት ከሆነች ያንቺ ሞክሼ ነዉ የማረጋት ረድኤት ...እላታለሁ፤ ወንድ ከሆነ ግን ቢኒ ነው ስም የሚያወጣለት፡፡" ስትላት ረድኤት ደነገጠች፡፡ ..."ኤዲዬ አረገዝሽ እንዴ?" ..."ዉይ ረዲዬ በደስታ ብዛትኮ የነገርኩሽ መስሎኝ ነዉ፡፡ አርግዣለሁ፡፡ ዛሬ ሆስፒታል ሂጄ የሶስት ወር እርጉዝ ነሽ አሉኝ" አለቻት፡፡ ረድኤት... ✎ ክፍል ሀያ ከ 150 Like በኋላ  ይቀጥላል❤️‍🩹 ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር♥️ ማድረግ አይርሱ።      ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄   ‌‌‌              ቅን ልቦች👇👇👇                  ❤️ @Qin_Liboch ❤️                  ❤️ @Qin_Liboch ❤️                ,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣🌹,,,,,              ••●◉Join us share◉●••
Mostrar todo...
‍ 🌺 ምኞቴ🌺 እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በቅን ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ የቀረበ💛        ▬▬▬❁ክፍል አስራ ስምንት▬▬▬ ለነሱ ብዙም ቦታ ሳትሰጣቸዉ ቢኒያምን ወደራሷ ሳብ አደረገችዉና... ..."ከነገ ወዲያ ሀሙስ ቀለበት አትሰሩ፡፡" አለችዉ፡፡ ለማሜ ድንገታዊ ጥያቄ ነበር፡፡ ወዲያዉ መልስ መስጠት ያለበት ጉዳይ ነዉ፡፡ ይሄን ጥያቄ ስትጠይቀዉ የህመሟ ምክንያት የጧቱ የአባባ ሀብታሙ ወሬ እንደሆነ ገምቷል፡፡ አባባ ሀብታሙን እናትና ልጅ ባንድ ሌሊት አሳምነዋቸዉ እርሳቸዉም ልጃቸዉ እንዳትጎዳ፤ እንደገና ዩንቨርሲቲም ገብታ እንዳትበላሽ፤ በበፊት ባህሪዋ እንድትቀጥል ሲሉ ለቢኒ ለመዳር ቆርጠዋል፡፡ ....ቢኒ ... እማማ በለጡንና ረድኤትን ዞር ብሎ እያፈራረቀ ከተመለከተ ቡኃላ እንደገና ወደ ፈቲ ዞር ብሎ ሲመለከት፡፡...ሁሉም ተፋጠዋል፡፡ ኤዲ ቢኒን የጠየቀችዉ ጥያቄ ባሏን ብቻ ሳይሆን ረድኤትን ልቧን ቀጥ፤ የእማማ በለጡን አይን ፍጥጥ አድርጓቸዋል፡፡ ኤዲ በድንገት ባሏን ማጣት አልፈለገችም፡፡ ለዚያም ነዉ ይሄን ጥያቄ እነሱ ፊት ያፈረጠችዉ።ቢኒ ምን እንደሚመልስ ግራገባው፡፡ 'እሺ ቀለበት አናስርም' ብሎ አያስደስታት ረድኤትና እናቷ አጠገቡ ናቸዉ፡፡ ሊያዋርዳቸዉና ክብራቸዉን ዝቅ እንደማድረግ ሆኖ ተሰማዉ፡፡ 'አይ አይሆንም ማግባት አለብኝ' እንዳይል ደግሞ ኤዲን ማሳዘንና መጉዳት አልፈለገም፡፡ ዝም ብሎ በማሳዘን አይነት ስሜት እየተቅለሰለሰ ኤዲን ያያታል፡፡ ኤዲም ታየዋለች፡፡ እነሱም (ረድኤትና እማማ በለጡ) ያዩታል፡፡ ሁሉም ይተያያሉ፡፡ ቢኒ ምን ይመልስ፡፡ ዉድ ሚስቱ ኤዲ እንደተጨነቀ ስለተረዳች አይኑን በተመስጦ እያየች... ..."የኔ ፍቅር እኔ'ኮ አታግባት አላልኩህም (ዘወር ብላ እናትና ልጅንም አየቻቸዉ እንደገና ቢኒን እየተመለከተች) ቢኒ ... ታገባታለህ፡፡ ረድኤት ትወድሃለች፡፡ አንተም እንደዚያዉ በተለይ ደግሞ ልጅ መዉለድ አለብህ፡፡ እኔ ልሰጥህ ያልቻልኩትን ነገር እሷ ትሰጣሃለች፡፡ስለዚህ ትጋባላችሁ፡፡ ግን ትንሽ አቆዩት እባክ" ብላ ረድኤትንም በተማፅኖ ተመለከተቻት፡፡ ..."እሺ ኤዲዬ እናቆየዋለን" አለና ቢኒ ወደ ረድኤት  ዘወር ብሎ ..."መቼ ነዉ ግቢ የምትገቢዉ ረዲ?" ብሎ ጠየቃት፡፡ የረድኤት መልስ አጭር ነበር "እሁድ" ብላዉ በረዥሙ ተነፈሰች፡፡ እህህህ አተነፋፈሷ ለሁሉም ይሰማ ነበር፡፡ ቢኒያምም ወደ እማማ በለጡ ዘወር አለና.... ..."እማማ ረዲ ወደ ትምህርቷ ትሂድና ለእረፍት ስትመጣ ቀለበት እናስራለን፡፡ እስከዚያ ኤዲም ትረጋጋ" አላቸዉ፡፡ከረጅም ፀጥታ በኃላ ቢኒያም ወደ ረድኤት ዘወር አለና ..."አይሻልም ረዲ?" ብሎ ጠየቃት፡፡ ረድኤትም በአዎንታ ራሷን ወደ ታችና ወደ ላይ ነቀነቀች፡፡ እማማ በለጡ ቀጠል አደረጉና "መቼ ይሆን እረፍትሽ?" ብለዉ ረድኤትን አተኩረዉ እያይዋት ጠየቋት ..."የካቲት ዉስጥ ነዉ የሚሆነዉ" አለቻቸዉ፡፡ ..."የዛሬ አምስት ወር መሆኑ ነዉ?" አሉ እማማ፡፡ ኤዲ ይሄን ስሰማ የአምስት ወር ጊዜ መሰጠቷ አስደስቷት ከሌሎቹ ቀደም ብላ ..."አዎ እማማ" አለቻቸዉ፡፡ በዚሁ ተስማሙና የካቲት ላይ የዛሬ አምስት ወር ቢኒ ለረድኤት ቀለበት እንደሚያስርላት ተወሰነ፡፡ ....ከሶስት ወር ቡሃላ... ፡       ✍...ቢኒና ኤዲ አብረዉ በደስታ እየኖሩ ነዉ፡፡ ቢኒ ከረድኤትም ጋር አላቆሙም ይደዋወላሉ፡፡ ረድኤት ስትደዉል ቢኒን ብቻ ሳይሆን ኤዲንም ታዋራታለች፡፡ ሲያወሩና ሲጫወቱ በአንድ ወንድ ላይ የሚሻሙ ተቀናቃኞች ሳይሆኑ ምርጥ ጓደኛሞች ይመስላሉ፡፡ ይጫወታሉ፤ ይቀላለዳሉ፡፡ ረድኤት ከቢኒ ይልቅ ኤዲ ጋር ለረጅም ሰዓት ታወራለች፡፡ እንደዉም አንዴ እየቀለደች ቁም ነገር አስመስላ..."ኤዲዬ የወደፊት ባሌን ተንከባከቢልኝ እሺ!" አለቻት፡፡ ሁለቱም ያለማቋረጥ ለረጅም ሰዓታት ተሳሳቁ፡፡ ሂሂሂሂ...ክክክ....እሺ እንከባከብልሻለው በይ እንግዲህ በርትተሽ ተማሪ።አለቻት እሺ እደውልልሻለው ኤዲዬ ደህና ሁኝ ብላ ረዲ ስልኩን ዘጋችው ✎ ክፍል አስራ ዘጠኝ ከ 100 Like በኋላ  ይቀጥላል❤️‍🩹 ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ #ሼር♥️ ማድረግ አይርሱ።           ┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿🌺»‌✽‌┉┉┄┄:      ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌             ቅን ልቦች👇👇👇                  ❤️ @Qin_Liboch ❤️                  ❤️ @Qin_Liboch ❤️                ,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣🌹,,,,,              ••●◉Join us share◉●••    
Mostrar todo...
‼️ሼር ይደረግ🎉🎉🎉🎉

ሼር ይደረግ ቢያንስ 1000 sjbscribers እንሙላው
Mostrar todo...