cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ዳሩል ኢቅረእ darul ekra

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ {{«ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡}}       [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ] "ከወሰን መተላለፍና ከመንሸራተት ተጠብቆ ታማኝ የሆነውን የተቀና አቋም የተቸረ ታድሏል።!" በአላህ ፈቃድ ኢስላማዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል ቻናሌ ላይ ስህተት ሲገኝ ቶሎ አሳውቁኝ @abuk29 https://t.me/darulekra

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
242
Suscriptores
+424 horas
+117 días
+3730 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

‏ ጥሩ_ ትዳር _ትፈልጋለህ??! ከፈለክ ኢማም አህመድ ኢብን ሀንበል (አላህ ይዘንላቸው) ልጃቸው ሲያገባ የለገሱት ምክር እኔም አንተንም ስለሚመለክት ጆሮህን አውሰኝ! ! ☞ ልጄ ሆይ እነዚህን አስር ነገሮች ለባለቤትህ መፈጸም ካልቻልክ በትዳር ህይወትህ ደስተኛ መሆን ስለማትችል ምክሬን ጠበቅ አድርገህ ለመያዝ ሞክር፦ “①- ሴት ልጅ ምቾትን ስለምትፈልግ ያለህን ነገር ሳትሰስት አጋራት ②- ሴት ፍቅርህን እንድትገልጽላት ትሻለች። (ባገኘከው አጋጣሚ) ፍቅርህን ከመግለጽ ወደኋላ አትበል ③- ሴቶች ግትር ወንዶችን ይጠላሉ። ደካማ ወንዶችን ደግሞ ይንቃሉ አንተጥንካሬ በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር ለመሆን ሞክር። ④- ሴቶችን መልካም ንግግር፡ ውብ ገጽታ ንጹህ ልብሶችና ጥሩ መአዛ ስለሚማርካቸው ሁሌም እነዚህ ነገሮች እንዲኖሩህ ጥረት አድርግ ⑤- ለሴት ቤቷ የቤተ መንግስት ያህል ክብር የምትሰጠው ስፍራ ነው ቤቷ ስትሆን ዙፋኗ ላይ በክብር የተቀመጠች ንግስት ያህል ክብር ይሰማታል በምንም ተአምር ይህን ቤተ መንግስቷን የሚያፈርስባትን ነገር እንዳትፈጽም ከንግስና ዙፋኗ ላይ ልታወርዳትም አትሞክር ይህን ካደረክ ንግስናዋን እንደመቃወም ይቆጠራል። ለንጉስ ንግስናውን ከመቀናቀን የበለጠ ትልቅ ወንጀል የለምና ጥንቃቄ አድርግ። ⑥- ሴት የቱን ያህል ብትወድህም ቤተሰቧን ማጣት አትፈልግም አንተን ከቤተሰቦቿ በላይ እንድትወድህ ለማድረግ አትጣር ይህን ማድረግ ፍጻሜው የማያምር ጠላትነትን ሊያመጣብህ ይችላል። ⑦- ሴት ከጎንህ (ጠማማ አጥንት) መፈጠሯን አትዘንጋ ይህ አፈጣጠሯ የውበቷ ሚስጥር መሆኑን እወቅ። ትንሽ ስህተት ባየህ ቁጥር አቃናታለሁ እያልክ እንዳትሰብራት ተጠንቀቅ። ስብራቷ ፍቺ ነው ላቃናት ከሞከርኩ ትሰበራለች በማለትም የባሰ እንድትጠም መንገድ አትክፈትላት መካከለኛ ሰው ሁንላት። ⑧- ሴት አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋ ትችላለች (ስትናደድ) ያደረክላትን ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል ነገር ግን እንዲህ አደረገች በማለት ብቻ እንዳትጠላት ይህን ባህሪዋን ባትወድላት ሌሎች የሚስቡህ ብዙ ባህሪዎች እንዳሏት አትዘንጋ። ⑨- ሴት አካላዊ ድካምና ስነልቦናዊ ጫና ሊያርፍባት ይችላል በዚህን ወቅት አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) የግዴታ አምልኮዎችን (ሰላትና ጾም) ሳይቀር ውድቅ አድርጎላታል። በዚህን ጊዜ እዘንላት ትእዛዝ አታብዛባት። ⑩- ሴት አንተ ዘንድ ያለች (የፍቅር) ምርኮኛህ መሆኗን አትዘንጋ ምርኮኛህን በጥሩ ሁኔታ ያዛት እዘንላት በድክመቷ (የምትፈጽመውን ስህተት) እለፋት ምርጥ የሂዎት አጋርህ ትሆናለች። @darulekra @darulekra
Mostrar todo...
[{#እስተዋ"]} "እስተዋ"  ከላይ  ሆነ  ወይስ   ተቆጣጠራ??መልሱን  ከሰለፎች ደግሞም "እስተውላ "ማለትም  "ተቆጣጠረ"የሚባለው  ተቀናቃኝ  ላለው  አካል ነው ።ዐርሽ  ቀድሞ  በማን  ቁጥጥር  ስር  ሆኖ  ነው  አላህ  እንደገና  ተቆጣጠራው  የሚባለው ?የሆነ ሰው "#አርረሕማኑ_ዐለልዐርሺ_  ኢስተዋ  የሚለው  ምንድን ነው  መልእክቱ?"ሲል  ታዋቂውን የቋንቋ  ሊቅ  ኢብኑልአዕራቢይን  ሲጠይቅ "እንዳለው  እሱ  ከዐርሹ ላይ ነው "አሉት።ሰውየው  "እንደሱ  አይደለም  የዐብደላህ  አባት ሆይ!።  መልእክቱ  'ተቆጣጠረ 'ማለት ነው "አለ ።"ዝም    በል !እንዲህ  እንዳሆነ  ምን  አሳወቀህ?? ዐረቦቹ #ተቀናቃኝ  ሲኖረው  ነው አንድን ነገር "ተቆጣጠረ  "የሚሉት ።አንዱ  ሲያሸንፍ"ተቆጣጠረ "ይባላል ።አላህ  ተቀናቃኝ የለውም ።እሱ  እንደተናገረው  ከዐርሹ  ላይ  ነው ።"አሉት ።[{ታሪኹ  በግዳድ:5/284]}ስለዚህ  "ተቆጣጠረ"የሚባለው አንድ  ተቀናቃኝ የለበት  ሃይል  ቀድሞ  በቁጥጥር ስር  ያልሆነን  ግዛት  ኃላ  ላይ  በእጁ  ሲያስገባ ነው ። ይህ  ደግሞ  ለሃያሉ  ጌታ  የሚገባ  አይደለም ።ሁሉን የፈጠራ  ፣ምንም የማያቅተው  ሁሉን ቻይ አምላክ ነውና ። // በዚህ  አጋጣሚ "እስተዋ" የሚለውን ቃል  በ"እስተውላ"ማለትም "ተቆጣጠረ " የሚተረጉሙ ሰዎች  ይሄ  ፍቺያቸው  በዐረብኛ  ቋንቋ   ውስጥ  መሰረት  ያለው   ለማስመሰል   የሆነ ግጥም የጣቅሳሉ ። በመጀመሪያ  ደረጃ  በእስላም  ግጥም  ቀርቶ  ሐዲስ  እንኳን ሰነዱ  ተፈትሾ ደካማ  አለመሆኑ  ሲረጋገጥ ነው  ለማስረጃነት የሚውለው ።የነዚህ  ሰዎች  ግጥም ግን  መነሻውም  አይታውቅም ።ቀድሞ  ነገር  መነሻውን  የሚያሳይ  ሰንሰለትም(ሰነድም)የለውም ሰነድ ከሌለው ደግሞ  ለማስረጃነት  ቀርቶ ለፍተሻ  እንኳን  መቅረብ አይችልም ።ከመሬት አንስቶ "ይሄ  ሶሒሕ ነው  ዶዒፍ? እስኪ  ፈትሹልኝ "ይበላልንዴ? // ከዚያ ባለፈ  ግጥሙ ጠንካረ ሰነድ እንኳን  ቢኖረው  ግልፅ  መልእክት  የላቸውን  የቁርኣን  አንቀፆችንና  የነብዩ  ሶለላሁ  ዐለይሂ  ወሰለም   ሐዲሶች   እንደዋዛ   በግጥም  አንሽርም ። ግጥሙ  አኽጦል    የተባለ  ክርስቲያን   ስንኝ  እንደሆነ  በወሬ  ደረጃ  ይወራል ። ይህን   ብንቀበል  እንኳን  ኢብኑ  ከሢር   ረሒመሁላህ  ግጥሙን  መረጃ    የሚያደርጉት ፡ጀህሚያዎች   እንደሆኑ   ከጠቀሱ  ቦኃላ  "እንደ  ጀህሚያህ ደካማ  ማስረጃ  ያለው  አናገኝም "።የመረጃ ድህነታቸው  አንድ  አስቀያሚ  የክርስቲያን  ግጥም   እስከሚጠቀሙ  አድርሷቸዋል "ይላሉ ።[{አልቢዳያ ወንኒሃያህ]}:9/295 // አልቃዲ  አቡ የዕላ  (458ሂ.)ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ ፦"ጥራት  ይገባውና  #አረርሕማን_ከዐርሹ_በላይ_ሆነ፣#ከዚያም_ከዐርሹ_በላይ_ሆነ ።ሲል እሱ  ከዐርሹ  በላይ  አንደሆነ እራሱ  ገልጿል።ይህን  መገለጫ ከላይ  መሆኑን  መልእክቱን   ሳይጠመዝዙ  መቀበል  ግዴታ ነው ።ዐርሹ ላይ  መሆኑ  በዛቱ ነው ።ያ ማለት ግን  መቀመጥ  ወይም መነካካት ማለት አይደለም ።ልቅናና የበላይነት  ማለትም አይደለም ።ሙዕተዚላዎች  እንደሚሉት መቆጣጠርና  ማሸነፍ   ማለትም  አይደለም  ።አሻዒራዎች እንደሚሉት  የደረጃ ፣የክብርና የችሎታ(ከፍ  ማለትም  አይደለም ።ከራሚዎች እንደሚሉትም መነካካትና ዐርሹ ላይ  መቀመጥም   አይደለም ።- -  - - ያለን  ምርጫ  ይህን  የአላህ  መገለጫ  ያለገደብ  ልቅ አድርጎ   መቀበል  ነው ።"[{አል ሙዕተመድ  ፊ  ኡሱሊድዲን :[{54--55] ተውሒድ   የሁለት  ሀገር  የስኬት  ቁልፍ  መፅሐፍ lbnu  munewor  (ሀፊዛሁላህ) ገፅ [{98---100]} የተወሰደ ጥርት  ባለው   ሰማይ  ላይ         ሙሉ  ጨረቃ  እየበራ      እይታህን   እክል  ገጥሞት ፤       አይንህ  ስራውን  ባይሰራ "ጨረቃ  የለም "እየልክ፥፥በከንቱ አትገላገል   -----አለም  እያየው  ነውና   እውነቱን ካዩ  ተቀበል። https://t.me/darulekra
Mostrar todo...
ዳሩል ኢቅረእ darul ekra

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ {{«ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡}}       [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ] "ከወሰን መተላለፍና ከመንሸራተት ተጠብቆ ታማኝ የሆነውን የተቀና አቋም የተቸረ ታድሏል።!" በአላህ ፈቃድ ኢስላማዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል ቻናሌ ላይ ስህተት ሲገኝ ቶሎ አሳውቁኝ @abuk29

https://t.me/darulekra

ወሳኝና አስለቃሽ ሙሐደራ ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ➧ ርዕስ ➘     ↪️ ሽርክና አደጋው 🗓 በ25/3/2015 ቃጥባሬ ላይ የተደረገ ሙሓደራ። 🎙 آلأُسْتَاذ بَحْرُو تَكَا أَبُو عٌبَيْدَة «حَفِظَهُ اللَّهُ» 🎙 በኡስታዝ ባህሩ ተካ አቡ ዑበይዳህ አላህ ይጠብቀው! https://t.me/Abdurhman_oumer/8488
Mostrar todo...
ሽርክና አደጋው ቃጥባሬ.mp311.02 MB
Photo unavailableShow in Telegram
ጥሩ ንግግር ሰደቃ ነው ✅መልካም ንግግርን አብዙ https://t.me/darulekra
Mostrar todo...
« وَاتَّقُوا فِتْنَةً لَّا تُصِيبَنَّ الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنكُمْ خَاصَّةً ۖ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ » " ከናንተም ውስጥ እነዚያን የበደሉትን ብቻ ለይታ የማትነካን ፈተና ተጠንቀቁ ፡፡ አላህም ቅጣቱ ብርቱ መኾኑን እወቁ ፡፡ " የአላህ መልእክተኛ የዘረኝነት አስከፊነትና የከረፋ ጥንብ መሆኑን እንዲሁም አንዱ ሙስሊም በሌላው ላይ ያለው ሐቅ ምን እንደሆነና መግደሉ ኩፍር መስደቡ ፊስቅ መሆኑን የተናገራባቸው ሐዲሶች አንድ መፅሀፍ ይወጣቸዋል ። ነገር ግን የሰው ልጅ ልቦና በወንጀል ከታወረ ማየትም መስማትም አይችልምና ከልቦና መታወር ጠብቀኝ ብሎ አላህን መለመን ያስፈልጋል ። አላህ አላዋቂዎች በሚሰሩት ግፍ ምክንያት ከሚመጣ መቅሰፍትና ፈተና ይጠብቀን ። የሰውም የአጋንንትም ሸይጣኖችን የስራቸውን ሰጥቶ የወንድሞቻችንን ደም ይጠብቅልን ። https://t.me/bahruteka
Mostrar todo...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👉 የማንም ብሄር ሆኖ መፈጠር ወንጀል አይደለም ። ይድረስ በሳውዲና በየትኛውም የዐለማችን ክፍል ለምትኖሩ ኢትዮዽያዊያን ሙስሊሞች ። የትም ኑሩ የትም ተፈጠሩ የየትኛውም ብሄር ወይም ጎሳ አባል ሁኑ ይህ በማናችሁም ላይ ወንጀል ሊሆን አይገባም ። ምክንያቱም ማንም ከዚህ ብሄር ( ጎሳ ) መፈጠር እፈልጋለሁ ብሎ አላህ ዘንድ ማመልከቻ አስገብቶ የተፈጠረ የለም ። ለምን ኦሮሞ ሆንክ ለምን አማራ ሆንክ ብሎ ሰውን መግደል ፣ አካል ማጉደል ፣ ደም ማፍሰስ የተከበረውን የሰው ልጅ ከፈጠረው አምላክ ጋር መዋጋት ነው ። በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው ነብዩ ከመላካቸው በፊት የነበሩት የመሀይማን ህዝቦች ተግባር ነው ። እንደዚህ አይነቱ ተግባር በተለይ በሙስሊሞች ሲፈፀም በጣም ያሳዝናል ። በአላህና በመጨረሻ ቀን ያመነ ሙስሊም ፣ ነገ ራቁቱን አላህ ፊት የሚቆም መሆኑን ያመነ ሙስሊም ። እንዴት ወንድሙን ከዚህ ብሄር ነው የተፈጠርከው ስለዚህ ሞት ይገባሀል ብሎ ይገድላል ? ‼ አሳፋሪ ነው ። ኢስላም አላህ የሰውን ልጅ በብሄርና በጎሳ ከፋፍሎ የፈጠረው ሊተዋወቁበት እንጂ ሊፎካከሩበት ፣ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ሊባባሉበት እንዳልሆነ በሑጅራት ምእራፍ 13ኛው አንቀፅ እንዲህ በማለት ይነግረናል : – « يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَاكُمْ شُعُوبًا وَقَبَائِلَ لِتَعَارَفُوا ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ » " እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው ፡፡" በዚህ መለኮታዊ የአላህ ቃል አላህ የሰውን ልጅ ከወንድና ከሴት በጎሳና በነገድ ከፋፍሎ የፈጠረው ለመተዋወቅ እንደሆነና ከዚህ ውጪ ትርጉም የሌለው መሆኑን ነው ። በዚህ መለኮታዊ የአላህ ቃል የሚያምን ሙስሊም በምን መመዘኛ አንዱን ከዚህ ጎሳ መፈጠር አልነበረብህም ወይም ሆነህ በመፈጠርህ ወንጀለኛ ያደርግሀል ብሎ አባሮ አድኖ ይገድለዋል ? ‼ እስኪ መልሱን ይንገሩን ። ይህ ማለት ጦርነቱ ከአላህ ጋር ነው ማለት ነው ። እንዴት እገሌን አማራ ወይም ኦሮሞ አድርገህ ፈጠርክ ብሎ ጠርነት መክፈት ነው ። በጣም አሳፋሪ ተግባር መሆኑ ብቻ ሳይሆን በምድር ላይ ጥፋት እንዲሰፍን መቅሰፍት እንዲመጣ የሚያደርግ ነው ። የዚህ አይነቱን ተግባር የማያወግዝ ትውልድ መቆሚያ የሌለው በላእ ለመቀበል ራሱን ያዘጋጅ ። እንዲህ አይነቱን ድርጊት ማስቆም የማይችል መንግስት በመከራና ሰቆቃ የሚኖር ሀገርን ለመምራት ራሱን ያዘጋጅ ። አላህ የሰው ልጆች የሚሰሩት ሀጢያት በምድር ላይ ጥፋት እንዲንሰራፋ ምክንያት የሚሆን መሆኑን ሲነግረን በሩም ምእራፍ በ41 ኛው አንቀፅ እንዲህ ይለናል : – « ظَهَرَ الْفَسَادُ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ بِمَا كَسَبَتْ أَيْدِي النَّاسِ لِيُذِيقَهُم بَعْضَ الَّذِي عَمِلُوا لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ » " የሰዎች እጆች በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት የዚያን የሠሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው በየብስና በባሕር ተገለጠ ፤ (ተሰራጨ) ፡፡ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና ፡፡ " በዚህ አንቀፅ አላህ እንደሚነግረን የሰው ልጆች በሚሰሩት ግፍ ምክንያት በምድርና በባህር ላይ መከራ እንደሚንሰራፋ ( አላህ መቅሰፍት የሚያመጣ ) መሆኑን የመቅሰፍቱ መምጣት ሰዎቹ ከግፋቸውና ከበደላቸው ይመለሱ ዘንድ ተፈልጎ መሆኑን ነው ። ይህ ማለት ሰዎች በሰው ሲመከሩ አሻፈረኝ ካሉ የሚመክራቸው መከራ መምጣቱን ነው ። ነገር ግን መከራም መጥቶ ላይመከሩ ይችላሉ ። እንከን የሌለው የኢስላም አስተምሮ አንድ ሰው ሌላውን ያለ ወንጀሉ በግፍ ከገደለ የሰውን ዘር በሙሉ እንደገደለ መሆኑን በተቃራኒው አንዲትን ነፍስ ከሞት ለመትትረፍ ምክንያት የሆነም የሰውን ዘር ባጠቃላይ ከሞት ለመትረፍ ሰበብ እነደሆነ ነው የሚነግረን ። ይህ የመጠቀ መርህ በማኢዳ ምእራፍ በ32 ኛው አንቀፅ አላህ እንዲህ ብሎ ይነግረናል : – « مِنْ أَجْلِ ذَٰلِكَ كَتَبْنَا عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنَّهُ مَن قَتَلَ نَفْسًا بِغَيْرِ نَفْسٍ أَوْ فَسَادٍ فِي الْأَرْضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ النَّاسَ جَمِيعًا وَمَنْ أَحْيَاهَا فَكَأَنَّمَا أَحْيَا النَّاسَ جَمِيعًا ۚ وَلَقَدْ جَاءَتْهُمْ رُسُلُنَا بِالْبَيِّنَاتِ ثُمَّ إِنَّ كَثِيرًا مِّنْهُم بَعْدَ ذَٰلِكَ فِي الْأَرْضِ لَمُسْرِفُونَ » " በዚህ ምክንያት በእስራኤል ልጆች ላይ እነሆ ያለ ነፍስ (መግደል) ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት (ካልሆነ በስተቀር) ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው ፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው ማለትን ጻፍን ፡፡ መልክተኞቻችንም በግልጽ ተዓምራት በእርግጥ መጡዋቸው ፡፡ ከዚያም ከዚህ በኋላ ከእነሱ ብዙዎቹ በምድር ላይ ወሰንን አላፊዎች ናቸው ፡፡ " የእነዚህ ረቂቅ መርሆችና አስተምሮዎች ባለቤት የሆነ ሙስሊም ወንድሙን በግፍ እንዴት እንደ ከብት አስተኝቶ ያርዳል ?‼ ነው ወይስ ለሸይጣናዊ አመለካከት ዲኑን ሽጦ ከአላህ ጋር መገናኘት የሚባል ነገር የለም ብሎ በመጪው ዐለም ክዶ ነው ? ይከብዳል ።!!!!! እባካችሁ ሙስሊሞች ከእንቅልፋችሁ ንቁ አኼራን አስታውሱ ካልነበራችሁበት ያስገኛችሁን እሱ ፊት ራቁታችሁ የምትቆሙት አላህን ፍሩ ። ወደራሳችሁ ተመለሱ ሀገራችሁንና ህዝባችሁን ከመከራ አድኑ ። በሰው ልጆች ደምና መከራ ለሚከብሩ በሰው አምሳል ለተፈጠሩ ሰው በላ አውሬዮች ሸቀጥ አትሁኑ ። በጣም የሚያሳዝነውና የሚያሳፍረው በአሁኑ ጊዜ ቁርኣን በወረደበት ፣ ጅብሪል በተመላለሰበት ፣ ነብዩ አውስና ኸዝረጅን ከ50 አመት የእርስ በርስ የመሀይምነት እልቂት በኋላ በላ ኢላሃ ኢልለላህ ( በኢስላም) አንድ ባደረጉበት ሀገር ሳውዲ ላይ የዚህ አይነቱ አሳፋሪ ተግባር በሀገራችን ሙስሊሞች መካከል መፈፀሙ ነው ። ውድ በሳውዲ የምትኖሩ የሀገራች ሙስሊሞች ዛሬ ነገ ሳትሉ ካላችሁበት የዘረኝት ስካር ወጥታችሁ ወደ አላህ ተመልሳችሁ ተውበት አድርጉ ። ውድ የኦሮሞና አማራ መሻኢኽና ዑለሞች እንዲሁም ዱዓቶች አላህ የጣለባችሁን አደራ ከምን ጊዜውም በላይ የምትወጡበት ጊዜ አሁን ነውና በመልካም በማዘዝና ከመጥፎ በመከልከል ድርሻችሁን ተወጡ ካልሆነ የሚመጣውን ፊትና ለመቀበለደ ተዘጋጁ ። ‼ አላህ በምድር ላይ ጥፋት ተንሰራፍቶ ግፍ ሲበዛ ግፈኞቹን ብቻ ለይቶ የማይነካ ፈተና የሚመጣ መሆኑንና እንድንጠነቀቅ በአንፋል ምእራፍ በ25ኛው አንቀፅ እንዲህ ብሎ ይነግረናል : –
Mostrar todo...
🔴 የጋብቻ መጀመሪያ ለሊት…❓ ፈታዋ መልስ 🔊አሸይኽ ዐብዱልሀሚድ አለተሚይ https://t.me/darulekra
Mostrar todo...
196 የጋብቻ መጀመሪያ ለሊት.mp34.86 MB
ሽርክና ቢደዓ እኮ የሚንሳቀስበት እግር ወይም ጎማ የለውም። የሚያሰራጨው ሰው ነው።ጀሀነምም የሚገባው ሺርክ ሳይሆን ሙሪክ ነው፣ቢደዓም ሳይሆን ሙብተዲዕ ነው። https://t.me/darulekra
Mostrar todo...
ዳሩል ኢቅረእ darul ekra

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ {{«ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡}}       [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ] "ከወሰን መተላለፍና ከመንሸራተት ተጠብቆ ታማኝ የሆነውን የተቀና አቋም የተቸረ ታድሏል።!" በአላህ ፈቃድ ኢስላማዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል ቻናሌ ላይ ስህተት ሲገኝ ቶሎ አሳውቁኝ @abuk29

https://t.me/darulekra

🚫 ኸድር ከሚሴ ወደ ተምይዕ ዋሻ ከመግባቱ በፊት፣ ስለ መርከዙ ሰዎች ከተናገረው... 🚫 ከኢልያስ አሕመድ፣ከአሕመድ ኣደም፣...መማር አይቻልም ብሎ ነበር...የዛሬውን አያርገውና የከሚሴው ልጅ፤ታዲያ አሁን ምን ተገኘ?! ተውባ አደረጉ?! ኣ? አላህ ሁላችንንም ወደ ቀጥተኛው ጎዳና ይምራን! https://t.me/semirEnglish
Mostrar todo...
_ኸድር ከሚሴ ሳይከረበት በፊት!_.mp36.81 MB
ሙመያዎች የሚጣሩት ወደ ኢኽዋን ኢኽዋኖች የሚጣሩት ወደ ሱፍይ ሱፍዬች የሚጣሩት ወደ =ቀብር አምልኮ ሰለፍዬች የሚጣሩት=አላህን በብቸኝነት ስለማምለክ(ወደ የሁሉም ነብያት ጥሪ ወደሆነው ተውሂድ) https://t.me/darulekra
Mostrar todo...
ዳሩል ኢቅረእ darul ekra

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ {{«ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡}}       [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ] "ከወሰን መተላለፍና ከመንሸራተት ተጠብቆ ታማኝ የሆነውን የተቀና አቋም የተቸረ ታድሏል።!" በአላህ ፈቃድ ኢስላማዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል ቻናሌ ላይ ስህተት ሲገኝ ቶሎ አሳውቁኝ @abuk29

https://t.me/darulekra

Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.