cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የተዋህዶ መዝሙሮች ✝✝✝

የኢትዮጵያ የሆነችዉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮቿ እና አስተማሪ አጫጭር የስብከት ቪዲዬ ከፈለጉ ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 241
Suscriptores
-324 horas
-117 días
-830 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን (3)🙏🙏🙏 ♻️#ሥላሴን_አመስግኑ♻️ ስላሴን አመስግኑ /2/ የምድር ፍጥረታት ዘምሩ እልል በሉ አዝ_________________ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል ከምንም በፊት ዓለማትን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ ምስጋና ይድረሰው ከጠዋት እስከማታ አዝ________________ ኪሩቤል ሱራፌል የሚያመሰግኑት መላእክት በሰማይ ስሉስ ቅዱስ ያሉት እኛም የአዳም ልጆች እንዘምራለን በሰማይ በምድር እንጠራሃለን አዝ________________ ብራብ በሥላሴ እጠግባለሁኝ ብጠማም በአምላኬ እረካለሁኝ ስላሴ አምባዬ ክብሬ ናቸውና ሁሌም ይመሩኛል በህይወት ጎዳና እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን
Mostrar todo...
እመቤታችን ባንቺ ምልጃ  (2) ድንግል ማርያም ባንቺ ምልጃ (2) መድኃኒዓለም ታምር ሰራ በማየ ቃና (2) ለጌታችን ታምር >>> በማየ ቃና ተመርጣ ታድላ >>> በማየ ቃና መጀመርያ ሆነች >>> በማየ ቃና ቃና ዘገሊላ >>> በማየ ቃና ቃናን ሊያደርጋት የታምሩ ቀዳሚ ስፍራ የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ አዝማች ----------------------- ታውቅዋት ስላለችው >>> በማየ ቃና ወይንኪ አልቦሙ >>> በማየ ቃና ውሃ ወይን ሲሆን >>> በማየ ቃና ሁሉ አዩ ሰሙ >>> በማየ ቃና ቃናን ሊያደርጋት የታምሩ ቀዳሚ ስፍራ የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ አዝማች ----------------------- አሳላፊዎቹ >>>በማየ ቃና ግራ ቢገባቸው >>> በማየ ቃና የድንግል ማርያም ልጅ >>> በማየ ቃና ከጭንቅ አወጣቸው >>> በማየ ቃና ቃናን ሊያደርጋት የታምሩ ቀዳሚ ስፍራ የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ አዝማች ---------------------- እኛም እናምናለን >>> በማየ ቃና ተስፋ ትንብልና >>> በማየ ቃና ስለ ቃልኪዳኗ >>> በማየ ቃና ሁሉ እንደሚቀና >>> በማየ ቃና ቃናን ሊያደርጋት የታምሩ ቀዳሚ ስፍራ የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ @nu_abren_enzemr @nu_abren_enzemr @nu_abren_enzemr @nu_abren_enzemr
Mostrar todo...
🌸 ክብሬ_ነው 🌸 ክብሬ ነው ክብርህን መናገሬ ፅድቄ ነው ፍቅርህ መመስከሬ ጌታዬ አምላኬ እልሃለሁ (2) ስጠራህ ሳመልክህ እኖራለሁ (2) 🌸 አዝ አይቼ የእጅህን ታምራት ሰምቼ የቃልህን ትምርት ሆኛለሁ ምስክር ላዳኝነትህ ስጋን ተዋህደህ ለኛ መገለጥህ (2) 🌸 አዝ ተከተልኩ ሁሉን ነገር ንቄ መድኃኒት መሆንክን አውቄ ከመልካሟ ቤትህ ተጠልያለሁ የእጅህን በረከት ካንተ እጠግባለሁ (2) 🌸 አዝ እርፍ ይዤ ላላርስ ወደኅውላ እያየው መረቤን ስትሞላ እመካብሃለሁ ባንተ መድህኔ አምላኬ ነህና የምትራራ ለኔ አባቴ ነህና የምታስብ ለኔ 🌸 አዝ ቸርነት ምረት ከበዛልኝ ለስምህ ውዳሴ ቅኔ አለኝ ክብሬና ሞገሴ አንተ ነህ ጌታ ተመስገን (2) ጠዋትና ማታ (2) በቀሲስ ዘማሪ ምንዳዬ  🌸🌸🌸🌸🌸
Mostrar todo...