es
Feedback
Joseph Math Tutor

Joseph Math Tutor

Ir al canal en Telegram

Hello, welcome to Joseph Math Tutor channel! https://youtu.be/oavDFT_BLNM?si=-8fh6SmrX2jSsmC- Subscribe our youtube channel On tiktok : josephmathtutor Owner: Yosef Adefris @yosef_2580

Mostrar más
2 193
Suscriptores
+324 horas
+187 días
+30530 días
Archivo de publicaciones
🌻🌻ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም ወይረውዩ አድባረ በድው🌼🌼 "በቸርነትኽ ዓመትን ታቀዳጃለኽ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል የምድረ በዳ ተራራዎች ይረካሉ" መዝ ፷፬÷፲፩-፲፪(64÷11-12) እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም አሸጋገራችሁ። አዲሱን ዘመን የሰላም፣የፍቅር፣የአንድነት፣የመተሳሰብ ዓመት ያድርግልን። ሀገራችንንም ሰላም ያድርግልን ከምንሰማው ነገር ሁሉ ይሰውረን። @yoquestion21

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ። ተማሪዎች እና ወላጆች የፈተናውን ውጤት ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ። ውጤት የሚታየው ፦ ► በፖርታል 👉 https://result.eaes.et ► በ
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ። ተማሪዎች እና ወላጆች የፈተናውን ውጤት ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ። ውጤት የሚታየው ፦ ► በፖርታል 👉 https://result.eaes.et ► በአጭር የፅሑፍ መልዕክት 👉 6284 ► በቴሌግራም ቦት 👉 https://t.me/EAESbot ላይ ነው። ከፍተኛ የኔትዎርክ መጨናነቅ ስለሚኖር በትዕግስት ይሞክሩት። በ2016 ዓ / ም ለፈተናው ከተቀመጡት ከ684 ሺህ በላይ ተማሪዎች 36,409 ተማሪዎች (5.4 በመቶ) ናቸው በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባቸውን 50% እና ከዛ በላይ ውጤት ያመጡት። ምንም እንኳን በተማሪ ቁጥር ደረጃ ከአምናው የቀነሰ ቢሆንም በቀጣይ የትምህርት ዘመንም የሬሜዲያል ፕሮግራም ይኖራል።

በ2016 ዓ.ም በፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መውሰድ ላልቻሉ ተማሪዎች በተለይ (በአማራ ክልል) 2ኛ ዙር ፈተና ከመስከረም 13-15/2017 ዓ.ም ይሰጣል። - የትምህርት ሚኒ
በ2016 ዓ.ም በፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መውሰድ ላልቻሉ ተማሪዎች በተለይ (በአማራ ክልል) 2ኛ ዙር ፈተና ከመስከረም 13-15/2017 ዓ.ም ይሰጣል። - የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

ሬሜዲያል ዘንድሮም ይኖራል። " አምና ሰጥተናል። ዘንድሮ ከዓምናው የቀነሰ ቁጥር እንወስዳለን። የሬሜዲያል ፕሮግራም በሂደት እየቀነሰ ይሄዳል " ሲሉ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተግረዋል።
ሬሜዲያል ዘንድሮም ይኖራል። " አምና ሰጥተናል። ዘንድሮ ከዓምናው የቀነሰ ቁጥር እንወስዳለን። የሬሜዲያል ፕሮግራም በሂደት እየቀነሰ ይሄዳል " ሲሉ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተግረዋል።

🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳 ሬሚዲያል አለ።
🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳 ሬሚዲያል አለ።

ትልቁ ውጤት ከናቹራል ሳይንስ Chemistry ትንሹ ውጤት Mathematics🤯
ትልቁ ውጤት ከናቹራል ሳይንስ Chemistry ትንሹ ውጤት Mathematics🤯

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በኦንላይን እና በወረቀት የተሰጠ ሲሆን፤ ፈተናውን በኦንላይን ከወሰዱት መካከል 26.6 በመቶ የሚሆኑት የማለፊያ ውጤት አምጥተዋል።
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በኦንላይን እና በወረቀት የተሰጠ ሲሆን፤ ፈተናውን በኦንላይን ከወሰዱት መካከል 26.6 በመቶ የሚሆኑት የማለፊያ ውጤት አምጥተዋል።

ዋነኛው ጥያቄ Remedial አለ ወይስ የለም??!

ከ 684ሺህ 405 ተማሪዎች 36 ሺህ 409 ተማሪዎች አልፈዋል ፤ ይህን እያዩ የወደፊቷ ኢትዮጵያ እንደሚገጥማት ማሰብ እጅግ በጣም ከባድ ነው። 💔
ከ 684ሺህ 405 ተማሪዎች 36 ሺህ 409 ተማሪዎች አልፈዋል ፤ ይህን እያዩ የወደፊቷ ኢትዮጵያ እንደሚገጥማት ማሰብ እጅግ በጣም ከባድ ነው። 💔

ውጤቱ ሌሊት 6:00 ላይ ይለቀቃል።🤯
ውጤቱ ሌሊት 6:00 ላይ ይለቀቃል።🤯

ከ1200 ተማሪዎች በላይ ከ500 በላይ አምጥተዋል።👏
ከ1200 ተማሪዎች በላይ ከ500 በላይ አምጥተዋል።👏

በአጠቃላይ 1663 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳለፉም። ሀረሪ ውስጥ ሁሉም አሳልፈዋል። አዲስ አበባ 4 ትምህርት ቤቶች ምንም አላሳለፉም።
በአጠቃላይ 1663 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳለፉም። ሀረሪ ውስጥ ሁሉም አሳልፈዋል። አዲስ አበባ 4 ትምህርት ቤቶች ምንም አላሳለፉም።

አዲስ አበባ 10,690 ተማሪዎች በማሳለፍ ከፍተኛውን ስፍራ ይዟል። አዲስ አበባ ካስፈተናቸው ተማሪዎች 21.4 በመቶ አሳልፏል።
አዲስ አበባ 10,690 ተማሪዎች በማሳለፍ ከፍተኛውን ስፍራ ይዟል። አዲስ አበባ ካስፈተናቸው ተማሪዎች 21.4 በመቶ አሳልፏል።

አጠቃላይ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች 5.4 በመቶ ናቸው።
አጠቃላይ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች 5.4 በመቶ ናቸው።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ከፍተኛ ውጤት ይፋ ሆኗል የትግራይ ክልል 675 ከ 700 ወንድ ከፍተኛ ውጤት በናቹራል ሳይንስ ተማሪ 575 ሴት ከፍተኛ ውጤት በሶሻል ተማሪ 538 ሴት
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ከፍተኛ ውጤት ይፋ ሆኗል የትግራይ ክልል 675 ከ 700  ወንድ ከፍተኛ ውጤት በናቹራል ሳይንስ ተማሪ 575 ሴት ከፍተኛ ውጤት በሶሻል ተማሪ 538 ሴት

በትግራይ ክልል ትልቁ ውጤት 675/700👏
በትግራይ ክልል ትልቁ ውጤት 675/700👏

የወንዶች አማካይ ውጤት - 30.66 የሴቶች አማካይ ውጤት - 28
የወንዶች አማካይ ውጤት - 30.66 የሴቶች አማካይ ውጤት - 28

#ውጤት : የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ይገለጻል። የትምህርት ሚኒስቴር በውጤቱ ዙሪያ ከደቂቃዎች በኃላ መግለጫ ይሰጣል። መግለጫውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጥታ የሚያሰራጭ ይሆናል። ይጠብቁ !
#ውጤት : የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ይገለጻል። የትምህርት ሚኒስቴር በውጤቱ ዙሪያ ከደቂቃዎች በኃላ መግለጫ ይሰጣል። መግለጫውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጥታ የሚያሰራጭ ይሆናል። ይጠብቁ ! #TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba @tikvahethiopia

የ2016 የ12ተኛ ክፍል ውጤት ሲለቀቀ ውጤት ማያ ሊንኮች ይፋ ሁነዋል ! 1.በዌብሳይት - http://result.neaea.gov.et 2. በ6284 - SMS 3. በቴሌግራም - @eaesbot 📌Sh
የ2016 የ12ተኛ ክፍል ውጤት ሲለቀቀ ውጤት ማያ ሊንኮች ይፋ ሁነዋል ! 1.በዌብሳይት - http://result.neaea.gov.et 2. በ6284 - SMS 3. በቴሌግራም - @eaesbot 📌Share📌 @yoquestion21

ዘንድሮስ ምን አይነት ውጤት ይመዘገባል ? የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ነገ ይገለጻል። ትምህርት ሚኒስቴር በፈተናው ውጤት ዙሪያ ነገ ከሰዓት ማብራሪያ ይሰጣል። የብሔራዊ ፈተናው
ዘንድሮስ ምን አይነት ውጤት ይመዘገባል ? የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ነገ ይገለጻል። ትምህርት ሚኒስቴር በፈተናው ውጤት ዙሪያ ነገ ከሰዓት ማብራሪያ ይሰጣል። የብሔራዊ ፈተናው ውስጤት ነገ ሰኞ ጳጉሜን 4/2016 ዓ/ም ይገለጻል ተብሎ ይጠበቃል። ባለፉት ዓመታት በተለይም ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲ) አስገብቶ ፈተና መስጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እጅግ ዝቅ ያለ ውጤት / በብዛት ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት የማያስመዘግቡበት መሆኑ ይታወቃል። ለአብነት በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑ 845,099 ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ አምጥተው ማለፍ የቻሉት 27,267 / 3.2 በመቶ ብቻ ናቸው። ከዛ በፊት በ2014ቱ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 896,520 ተማሪዎች ተፈትነው 50 በመቶና በላይ አምጥተው ያለፉት 30,034 / 3.3 በመቶ ብቻ ናቸው። ትምህርት ሚኒስቴር በቀጥታ የሚያልፉ ተማሪዎች ዝቅተኛ መሆኑን ተከትሎ የሬሜዲያል ፕሮግራም በመስጠት ያን ያለፉ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ የማድረግ ስራ ሲሰራ ነበር። ይህ ስራ " ለአንድ ጊዜ ብቻ " ተብሎ የነበረ ሲሆን በ2015 ቀጥታ ያለፉ ተፈታኞች ውስን በመሆናቸው የትምህርት ሚኒስትሩ ቃላቸውን ስላጠፉ በይፋ ይቅርታ ጠይቀው የሬሜዲያል ፕሮግራሙ እንዲቀጥል አድርገው ነበር። ° ዘንድሮውስ ምን አይነት ውጤት ይመዘገባል ? ° ምን ያህል ተማሪ የማለፊያ ነጥብ ያስመዘግባል ? ሁሉንም አብረን የምናየው ይሆናል።