የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን
Ir al canal en Telegram
ይህ ሥለኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ትክክለኛ መረጃ የሚያገኙበት የባለሥልጣኑ የቴሌግራም አካውንት ነው።
Mostrar más1 411
Suscriptores
+224 horas
+257 días
+8530 días
Archivo de publicaciones
1 411
Food safety and Quality Management Practice practical training is happening now at Bishoftu Meareg Export Abattoir
Date: August 22, 2023
Bishoftu, Ethiopia
**
Ethiopian Agricultural Authority (EAA) with its development partner United Nations Industrial Development Organization (UNIDO) has organized and is providing hands-on practical training to 25 meat inspectors and experts coming from 11 Export abattoirs, 4 local abattoirs, EAA, and Halal Certification Department of Oromia Region Islamic Affair at Mearege Export abattoir Bishoftu, Ethiopia.
The training is supported by the UNIDO project “Capacity building to upgrade the livestock value chain in Ethiopia” financially supported by the Government of China under the Global Development and South-South Cooperation Fund.
The main objective of EAA is to establish and implement a strong regulatory system in the livestock sector to improve international and national competitiveness. EAA Director of Export Abattoir Inspection and Certification Directorate, Dr. Ayalew Shumet, officially opens the training. In the opening remark, He emphasizes the importance of building the capacity of experts working in the abattoir mandated for food safety and quality along the meat value chain and to achieve the objective of the authority. He notes that it is currently a main requirement for importing countries that meat inspectors acquire skills and knowledge and become certified in food safety and quality management practices based on international standards and practices.
Dr. Sentayhu Menda; UNIDO National Project Coordinator, stated in his keynote address that one of the project's goal is to boost Ethiopian meat competitiveness in the global market by strengthening local institutions and human capacities. The project is working closely with the government to capitalize on its livestock resources.
The training will run for 12 days, from August 21 to September 1, 2023, and will be conducted by qualified INDIGO trainers.
For more information፦
Website ፡- www.eaa.gov.et
Facebook፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority
Telegram፡- eaa_123
@EAA public relation and Communication Directorate
1 411
የደረጃ ዕድገት መሰላል ተጠቃሚ የሆኑ ሰራተኞች የደረጃ እድገት ኮሚቴ አባላት ምርጫ አካሄዱ
የደረጃ እድገት መሰላል ተጠቃሚ የሆኑ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእንስሳት ጤና ሀኪሞችና መለስተኛ ባለሙያዎች በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተገኝተው በደረጃ ዕድገት አፈፃፀም መመሪያ የድልድል ኮሚቴ አወቃቀር ላይ ተወያይተው የደረጃ እድገት ኮሚቴ አባላትን ምርጫ አካሄዱ፡፡በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በተለያዩ ምክንያቶች ለተወሰኑ ጊዚያት ተቋርጦ የቆየው የደረጃ ዕድገት አፈፃፀም መመሪያ በባለስልጣን መ/ቤታችንና በግብርና ሚ/ር ጥረት በአሁኑ ሰዓት በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተቀባይነት አግኝቶና ፀድቆ በመምጣቱ እንኳን ደስ አላችሁ፤ ካሉ በኋላ የዛሬው ስብሰባ ዋና ዓላማ በዚህ መመሪያ መሰረት መስፈርቱን የሚያሟሉ የደረጃ ዕድገት መሰላል ተጠቃሚ የሆኑ ሰራተኞች ማግኘት የሚገባቸውን የደረጃ እድገት ፈጥነው ማግኘት እንዲችሉ የደረጃ እድገት ኮሚቴ አባላትን ምርጫ ለማካሄድ መሆኑን ገልፀዋል፡፡በመቀጠልም የብቃትና የሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሪት ብርቱካን ቦጋለ የእንስሳት ጤና ሀኪሞችና መለስተኛ ባለሙያዎች የደረጃ ዕድገት አፈፃፀም መመሪያ የድልድል ኮሚቴ አወቃቀርን በተመለከተ ገለፃ አቅርበዋል፡፡ የእንስሳት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል በበኩላቸው የቀረበውን ገለፃ መሰረት በማድረግ የተቀመጠው መስፈርት የሚያሟሉ እና እነሱን ሊወክሉ የሚችሉ ሰራተኞችን ጠንካራ፤ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማካሄድ የኮሚቴ አባላትን እንዲመርጡ አሳስበዋል፡፡በመጨረሻም በስራ አፈፃፀማቸው የተመሰገኑ፤ በስነ ስርዓት አክባሪነታቸውና በታማኝነታቸው የታወቁ ሆኖ ሁለገብ አመለካከት አላቸው ተብሎ እምነት የሚጣልባቸው፤ ከተለያዩ ሱሶች ነፃ የሆኑ፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት በዲሲፕሊን ጉድለት ያልተቀጡ እና በመ/ቤቱ ውስጥ ሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ ያገለገሉ ሰራተኞች በምርጫ እንዲወዳደሩ በማድረግ ከእንሰሳት ሀኪም፤ከእንስሳት ሳይንስ ባለሙያና ከእንስሳት ጤና ረዳት የተውጣጡ የኮሚቴ አባላት እንዲመረጡ ተደርጎ የውይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡
1 411
በ2015 በጀት ዓመት የቁም እንስሳት፣ የእንስሳት ውጤቶች እና የእንስሳት ተረፈ ምርት ኢንፖርት ኤክስፖርት እንቅስቃሴ ምን ይመስላል?
******
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በኳራንታይን ኢንፖርት ኤክስፖርት ኢንስፔክሽንና ሰርተፊኬሽን ዳይሬክቶሬት አማካኝነት ወደ ውጪ የሚላኩ የቁም እንስሳቶችን የጤና ምርመራና ማረጋገጫ ይሰጣል፡፡ እነዚህ የቁም እንስሳት ጤናቸው ተጠብቆ ለመዳረሻ ሀገራት እንዲደርሱ አስፈላጊው የእንስሳት ጤና ምርመራ ያደርጋል፤ ከብቶቹ ክትባት ወስደው አለም አቀፍ የእንስሳት ጤና መስፈርትን አሟልተው ለተቀባይ ሀገር እንዲደርስ የማድረግና ከቁም እንስሳት በተጨማሪም የእንስሳት ውጤቶችና ተረፈ ምርቶች ወደ ውጪ ሲላኩ አስፈላጊውን መስፈርት ማሟላታቸውን ያረጋግጣል፡፡ ሌላው ከውጪ የሚገቡት በተለይ የእንስሳት ውጤቶችና ተረፈ ምርቱ የሀገሪቱን መስፈርት ማሟላቱ ተረጋግጦ ወደ ሀገር እንዲገባ የሚያደረግ ሲሆን ለዚህም ባለስልጣኑ የመግቢያ ፈቃድ የሚሰጥ ሲሆን ስለ ዳይሬክቶሬቱ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ በባለስልጣኑ የኳራንታይን ኢንፖርት ኤክስፖርት ኢንስፔክሽንና ሰርተፍኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ሰይፉ ሀይሉ የሰጡንን ማብራሪ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ በ2015 በጀት አመት የተላኩ የቁም እንስሳት 18,000 ( አስራ ስምንት ሺህ) እቅድ ተይዞ 18,115 ( አስራ ስምንት ሺህ አንድ መቶ አስራ አምስት) ተከናውኗል፡፡ የበግና ፍየል ደግሞ 78,000 ( ሰባ ስምንት ሺህ ) እቅድ ተይዞ 70,545 (ሰባ ሺህ አምስት መቶ አርባ አምስት) ተከናውኗል፡፡ ግመል 18,000( አስራ ስምንት ሺህ) እቅድ ተይዞ 4,721 ( አራት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ አንድ) ተከናውኗል፡፡ ሌላው ደግሞ የማር ምርት 200 ቶን እቅድ ተይዞ 179 ቶን ወደ ውጪ መላክ ተችሏል፡፡ የሰም ምርት ደግሞ 200 ቶን እቅድ ተይዞ 357 ቶን እንዲላክ ተደርጓል፡፡ የአንድ ቀን ጫጩት ስድስት መቶ ሺ ለመላክ እቅድ ተይዞ ወደ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን እንዲላክ ተደርጓል፡፡ የአንድ ቀን ጫጩቶች ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚላኩ ናቸው፡፡ ሌላው የለማ እንቁላል 500,000 ( አምስት መቶ ሺህ) ለመላክ እቅድ ተይዞ 439,000 ( አራት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ) አካባቢ ወደ ውጭ እንዲላክ ተደርጓል፡፡
የቁም እንስሳት ሲባል የዳልጋ ከብት፣ በግና ፍየል እንዲሁም ግመልን ያጠቃልላል፡፡ እነዚህ ወደ መከከለኛ ምስራቅ ሀገራት ማለትም ሳውዲ አረቢያ፣ ዱባይ፣ጆርዳን፣ ኦማን፣ የመን እና ኩዌት በብዛት እንዲላኩ ይደረጋል፡፡ የእንስሳት ተዋፅኦና ተረፈ ምርት ወደ ተፈለጉበት ሀገር እንዲላኩም ተደርጓል፡፡ ከውጪ ለሚገቡት ደግሞ 2015 በጀት አመት ለዘር መስረች የሚሆኑ የአንድ ቀን ጫጩቶች (Parent stock) እንዲገቡ ተደርገዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ከአውሮፓ ሀገራትና ከብራዚል የሚገቡ ናቸው፡፡ 500,000 ( አምስት መቶ ሺህ) የአንድ ቀን ጫጩቶችን ለማስገባት እቅድ ተይዞ 714,000 ( ሰባት መቶ አስራ አራት ሺህ) ጫጩቶች እንዲገቡ ተደርገዋል፡፡ የለማ እንቁላልም ከአውሮፓና ከሌሎች ሀገራት እንዲገባ ተደርጓል፡፡ በተወሰነ መልኩ ከአፍሪካ ሀገራትም የለማ እንቁላል እንዲገባ ይደረጋል፡፡ በበጀት አመቱ 100,000 ( መቶ ሺህ) የ ለማ እንቁላል ለማስገባት እቅድ ተይዞ 690,000 ( ስድስት መቶ ዘጠና ሺህ) የለማ እንቁላል ወደ ኢትዮጵያ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ የዳልጋ ከብት አበለዘር የሚገቡበት ሁኔታዎች ይኖራሉ፡፡ በበጀት አመቱ 10,000 (አስር ሺህ ) ዶዝ አበላዘር ለማስገባት እቅድ ተይዞ ነበር፡፡ 10,123.00 ( አስር ሺ 123 ) ዶዝ አበላዘር እንዲገባ ተደርጓል፡፡ ሌላው ለወተት ምርት የሚውሉ የተሻሻሉ ጊደሮች ከአውሮፓ፣ ከኬንያ እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት ይገባሉ፡፡ በበጀት አመቱ ጤንነታቸው የተጠበቁ 250 ( ሁለት መቶ ሃምሳ) የዳልጋ ከብት ለማስገባት ታቅዶ 32 ( ሰላሳ ሁለት) የተሻሻሉ ጊደሮችን ማስገባት ተችሏል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት አመት አለም አቀፍ ስታንዳርዱን ጠብቆ የተሰራው ሚሌ ኳራንታይን ጣቢያን ወደ ስራ ለማስገባት ችለናል፡፡ ኳራንታይኑ ለአስር አመት እንዲያስተዳድሩ ለግል ባለሀብት ኮንትራት የተሰጠ ሲሆን በኳራንታይኑ ውስጥ የሚሰጠው አገልግሎት የእንስሳት ጤና ክትትል ማለትም ክትባት፣ ላቦራቶሪ ምርምራ ስራዎች እንዲሰሩ ይደረጋል፡፡ ባሳለፍነው በጀት ዓመት ካጋጠሙን ችግሮች ውስጥ ዋነኛው የቁም እንስሳት ኤክስፖርት ላይ ሕገወጥ ዝውውር (ኮንትሮባንድ) መበራከቱ ነው፡፡ የኮንትሮባንድ ንግድ ደግሞ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ቀላል አይደለም፡፡ በመሆኑም ይህን ችግር ለመፍታት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራትን ይጠይቃል፡፡ በ2015 በጀት ዓመትም ይሄንን የቁም እንስሳት የኮንትሮባንድ ንግድ ለማስቆም ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመሆን ጠንካራ የክትትልና ቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት አንዳንድ አርምጃዎችን መውስድ ጀምራናል፡፡ ይህን ተግባርም ቀጣይ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፦
ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et
ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም፡- eaa_123
@የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤
1 411
በእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያዎች የሚደረገው የቁጥጥር ሥርዓት!
……የቀጠለ!
*****
ሁለተኛው ፋብሪካው ማምረት ከጀመረ በኋላ ፋብሪካው በተሰጠው የማምረት ብቃት ደረጃ ላይ ስለመሆኑና የሚጠቀመው ጥሬ ዕቃና የተመረተው መኖ የተቀመጠውን የጥራት እና ደኅንነት ባሟላ መልኩ ነው ወይ የሚለውን በአገር ደረጃ በዘጋጀው 32 የመኖ እና የመኖ ጥሬ እቃ ደረጃዎች መሰረት መሆኑን ቁጥጥር ይደርጋል፡፡ መኖው ጥራቱ ምን ይመስላል ማለትም ለእንስሳቱ የሚጠቅመውን ንጥረ ነገር በተሟላ መልኩ ይዟል ወይ? ከደህንት አንፃር ደግሞ መኖው በሽታ አምጪ ከሆኑ ነገሮች ( ስነህይወታዊ፣ ቁሳዊና ኬሚካለዊ ነገሮች) ነፃ ነው ወይ? የሚሉትን ነገሮችን እንደሚቆጣጠሩ ተናግረዋል፡፡ ይህን ስንቆጣጠር ደግሞ በአይን በማየት ጥሩ ነው መጥፎ ነው የምንለው ብቻ ሳይሆን ከተመረተ በኋላ የመኖ ናሙናዎችን በመውሰድ በላብራቶሪ ምርመራ በማድረግ ከወጣው ደረጃ ጋር እያወዳደርን ግብረ መልስና እርምጃ የሚወሰድበት የአሰራር ሥርዓት አለን፡፡ አወዳድረን ከተቀመጠው ስታንዳርድ በታች ከሆነ በተለይም በእንስሳት ጤናና በእንስሳት ምርት ውስጥ (ወተት፣ እንቁላልና ስጋ) አልፎ የእንስሳት ምርት ተጠቃሚውን የሰው ጤና የሚጎዳ ከሆነ በቀጥታ ምርቱ እንዲወገድ ይደረጋል፡፡
ምክንያቱም "የዛሬ መኖ ነገ የሰው ምግብ ስለሆነ" መኖው ከተበከለ በእንስሳ ምርት ውስጥ አልፎ የእንስሳት ምርት ተጠቃሚውን ጤና ሊጎዳ ስለሚችል፣ ፋብሪካዎች ጥራትና ደህንቱ የተጠበቀ ጥሬ ዕቃ በመጠቀም ጥራትና ደህንነቱ የተጠበቀ የእንስሳት መኖ ማምረት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሲሆን ጤናማ የሆነ እንስሳትና የእንስሳት ምርት ማግኘት ይቻላ፡፡ የጥራት ችግር ከሆነ ደግሞ ወደ ሚፈለገው የጥራት ደረጃ እንዲመጣ እንደገና ያንን መኖ የማቀነባበር ሥራ እንዲሰራ በማድረግ ወደሚፈለገው የጥራት ደረጃ እንዲመጣ የማድረግ ስራ የሚሰራ ይሆናል፡፡ ይህንንም የባለሥልጣኑ የመኖ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች በመኖ አምራች ተቋማት በአካል እየተገኙ የማረጋገጥና የመፈተሸ ሥራ ይሰራሉ፡፡
በሦስተኛ ደረጃ በባለሥልጣኑ የመኖ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች አማካኝነት የተሟላ የሰው ኃይል በፋብሪካው መኖሩን፣ የባለሙያዎች የሙያ እና የተቋሙ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መታደሱን፣ የጥሬ እቃ አደራደሩን፣ የወጣው ምርት አከመቻቸቱን እና ማንኛውም የመኖ ምርት ወደ ገብያ ሲቀርብ በአግባቡ የታሸገ መሆኑንና በማሸጊያው ከረጢት ላይ ገላጭ ፅሁፍ ሊኖረው እንደሚገባ ደረጃው ስለሚያስገድድ፣ የምርቱ ገላጭ ጽሁፍ በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት መሆኑንና መኖሩን የማረጋገጥ፣ የጥሬ እቃ አቅራቢዎቹ መረጃ ተመዝግቦ መያዙን፣ የጥሬ እቃ ቅበላ አሰራር መመሪያ እና የሙቀትና የእርጥበት መለኪያ መሳሪያ መኖሩን፣ ያለቀለት መኖ ምርት ተረካቢዎች መረጃ ተመዝግቦ መያዙን፣ የመኖ ጥሬ እቃ/ያለቀለት ምርት አቀማመጥ በመመሪያ መሰረት መሆኑን እና የመጋዘን ንጽሕናን በተመለከተ በቼክ ሊስት በየጊዜው ተቋሙ ላይ የኢንስፔክሽን ሥራ እንደሚሰሩና በግኝታቸው መሰረት እርምጃዎች እንደሚወሰዱ አቶ ዘላለም ያብራራሉ፡፡
በመጨረሻም የእንስሳት መኖ መቀነባበሪያ ፋብሪካዎች መስፋፋት ለዘርፉ እድገት ወሳኝ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ዘላለም አገሪቱ ባላት የእንስሳት ኃብት ልክ ተጠቃሚ እንድትሆንና የአገራችንን እንስሳት ጤና እንዲጠበቅ፣ የእንስሳት ምርትና ምርታመነትን በማሳደግ፣ አገሪቱ ከእንስሳት ሀብቱ ማግኘት የሚገባትን የውጭ ምዘሪ እንድታገኝና በቀጠናዊ፣ አህጉራና ዓለማቀፈ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንድትሆን፣ እንዲሁም እንደ አገር የተጀመረውን የሌማት ቱሩፋት ውጤታማ ለመድረግ፣ በተጨማሪም የዛሬው መኖ የነገው የሰው ልጆች ምግብ በመሆኑ የሕብረተሰብን ጤና ከመጠበቅ አኳያ የመኖ ጥራትና ደኅንነት ማስጠበቅ መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱም ሙሌን መሰል የመኖ ማቀነባበሪያ ፍብሪካዎች እንዲበዙ ለማድረግ አገልግሎት አሰጣጡን የዘመነና ቀልጣፋ የማድረግ፣ የመኖ ጥራትና ደህንነት የቁጥጥር ሥራን ውጤታማ ለማድረግ ራሱን በቴክኖሎጅ የማብቃት፣ ለቁጥጥር ስራ ምቹ የሆነ የአሰራር ስርዓት መዘርጋትና ከተለመደው አሰራር ወጥቶ በላብራቶሪ ፍተሻና ምዝገባ ላይ መሰረት ያደረገ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቅንጂታዊ አሰራር በመፍጠር የተጠናከረ የቁጥጥር ስራ ለመሥራት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አቶ ዘላለም ገልጸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፦
ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et
ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም፡- eaa_123
@የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤
1 411
የብሔራዊ ዝርያ አጽዳቂ ኮሚቴ ዓመታዊ ጉባዔውን በማካሄድ በዕጩ የዕጽዋት ዝርያዎች ላይ ውሳኔ አሳለፈ
የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ከተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት አንዱ ዕጩ የዕጽዋት ዝርያዎችን ብቃት በመረጃና በመስክ እንዲገመገሙ በማድረግ በብሔራዊ የዝርያ አጽዳቂ ኮሚቴ ውሳኔ እንዲያገኙ እና ዝቅተኛውን መስፈርት አሟልተው ተቀባይነት ያገኙ ዝርያዎችን በዝርያ መዝገብ እንዲካተቱ ማድረግ ነው፡፡ በዚህ መሰረት በ2014/15 የምርት ዘመን ከተለያዩ የፌደራልና የክልል የምርምር ተቋማት፣ ከዩኒቨርሲቲ፣ ከግል ካምፓኒዎች ከውጪ እና ከሀገር ውስጥ የቀረቡ ዕጩ የዕጽዋት ዝርያዎች ላይ ውሳኔ ለማሰጠት በዕጽዋት ዝርያና ዘር ሪጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈጻሚ አስተባባሪነት የተዘጋጀው የብሔራዊ ዝርያ አጽዳቂ ኮሚቴ ዓመታዊ ጉባዔ ከሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቢሾፍቱ ከተማ ቲ.ኬ ሆቴል ተካሂዷል፡፡የዕጽዋት ዝርያና ዘር ሪጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈጻሚ እና የብሔራዊ ዝርያ አጽዳቂ ኮሚቴ ፀሐፊ የሆኑት አቶ ፍስሃ ተሾመ ለተሰብሳቢዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ የዚህ ጉባኤ ዋና ዓላማ ከውጪ እና ከሀገር ውስጥ የቀረቡ ዕጩ የዕጽዋት ዝርያዎች ላይ ውሳኔ ለማሰጠት እንደሆነ ገልፀው እንዚህ ተቀባይነት ያገኙ ዝርያዎችን በዝርያ መዝገብ እንዲካተቱ መደረጉ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራቸው ገልፀዋል፡፡አያይዘውም በተቀመጠው ፕሮግራም መሰረት አቅራቢ መስሪያ ቤቶች ስላቀረቡት ዝርያ ለሚጠየቁት ተጨማሪ ማብራሪያ ተገቢ ምላሽ እንዲሰጡ እና በየሰብሉ ግምገማውን የመሩ የቴክኒክ ኮሚቴ ቡድን መሪዎችም በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ መሰረት ሪፖርታቸውን እንዲያቀርቡ በማመልከት፣ መልካም የውይይት ጊዜ እንዲሆን በመመኘት ጉባኤው በይፋ መጀመሩን አብስረዋል፡፡ከዚህ በመቀጠል የብሔራዊ ዝርያ አጽዳቂ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፕ/ር ፍሬው መክብብ መድረኩን ተረክበው አባላቱን ካስተዋወቁ በኃላ በተዘጋጀው ፕሮግራም መሰረት የተለያዩ ዕጩ የዕጽዋት ዝርያዎች የግምገማ ሪፖርት በቅደም ተከተል በየቴክኒክ ቡድን መሪዎቹ እንዲቀርቡ ተደርጓል፡፡የብሔራዊ ዝርያ አጽዳቂ ኮሚቴ አባላትም ከየቡድኑ የቀረበውን የዕጩ ዕጽዋት ዝርያዎች ሪፖርት እንዲሁም ከአቅራቢ መስሪያ ቤቶች ያቀረቡትን ተጨማሪ ማብራሪያ በዝርዝር ካዳመጡ በኋላ በእያንዳንዱ እጩ ዝርያ ላይ በጥልቀት ተወያይተዋል፡፡ በመጨረሻም ለውሳኔ ከቀረቡት 119 ዕጩ ዝርያዎች ውስጥ 63 ዝርያዎች ተቀባይነት አግኝተው እንዲመዘገቡ፣ 5 ዝርያዎች በተሰጠው አስተያየት መሰረት እንዲደገሙ፣ 51 ዝርያዎች ተቀባይነት ስላላገኙ ውድቅ እንዲሆኑ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ጉባኤው ተጠናቋል፡፡
1 411
በአንድ ጀንበር ከ566 ሚሊዮን በላይ ችግኝ!
****
ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ሪከርድ የሰበርንበት ታላቅ ቀን!
እንኳን ደስ አለን!
1 411
የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን፣ የግብርና ሚኒስቴር እና ሌሎች ግብርና ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች በአንድ ጀምበር የ500 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ የተያዘውን ግብ ለማሳካት ዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በአይ ሲቲ ፓርክ የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።
1 411
ተጀመረ
ነገን ዛሬ እንትከል!!!
**
ዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኞች የሚተከሉበት እለት ነው!
#በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞች በኅብረት!
1 411
በእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያዎች የሚደረገው የቁጥጥር ሥርዓት!
ክፍል 1
*****
ከኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን በመኖ ንግድ ሥራ ለመሰማራት አስፈላጊውን የቅድመ ፈቃድ መስፈረት አሟልተው ፍቃድ ወስደው በእንስሳት መኖ ማምረት ወይም ማቀነባበር ላይ ከተሰማሩት ድርጅቶች መካከል በአማራ ክልል በባሕር ዳር ከተማ አሰተዳር የሚገኘው ሙሌ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ አንዱ ነው፡፡ ፋብሪካው ወደ ምርት ከገባ 1 ዓመት እንደሆነውና በአሁኑ ወቅትም የማምረት አቅሙ በቀን ከ4800 ኩንታል በላይ መሆኑን የሚናገሩት የፋብሪካው ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ኮሎኔል ነገሰ ጫኔ፣ ፋብሪካው የዶሮ፣ የአመንጃኪ እንስሳት፣ የበግና ፍየል ጨምሮ ከ20 በላይ የመኖ ዓይነቶችን እያመረተ ለገበያ እንደሚያቀርብ ገልጸዋል፡፡ እነዚህን መኖዎች ለማምረት በግብዓትነት የሚጠቀመው በአብዛኛው ከአካባቢው አርሶአደር እና አግሮ ኢንዱስትሪ ፋብሪካዎችና ከድርጅቱ እህት ኩባንያዎች የሚገኙትን የስንዴ ፍሩሽካ፣ የሩዝ፣ የበቆሎ፣ የቦለቄ፣ ከዘይት ፋብሪካ የሚወጡ የኑግ፣ የሱፍ የመሳሰሉትን ተረፈ ምርት ነው የሚሉት ኃላፊው ምርታቸውንም በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙ ተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራትና ደኅንቱ በተጠበቀ ሁኔታ ተደራሽ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ የፋብሪካውን የማምረት አቅም በማሳደግ ከ50% በላይ የሚሆነውን የፋብሪካውን ምርት ለውጭ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ ግኝታችንን ከ300 ሺ ዶላር በላይ ለማድረስ አቅደን እየሰራን ነው የሚሉት ኮሎኔል ነገሰ እንደአገር በገበሬውና በእንስሳት አርቢው ዘንድ የተቀነባበረ መኖ የመጠቀም ልምዱ ያን ያህል ያደገ ባይሆንም፣ አሁን ከተጀመረው የሌማት ቱሩፋት አንጻር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የሚመጣ በመሆኑ የመኖ ምርት ጥራቱ፣ ደህንነቱ የተረጋገጠ መኖ ለተጠቃሚው ሕብረተሰብ ለማድረስ ከኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ጋር በትብብር እየሰሩ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ የእንስሳት መኖ ጥራትና ደኅንነትን ማስጠበቅ ከእንስሳት ዘርፉ የሚገኘውን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እጅግ ወሳኝ በመሆኑ የባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት ክፍልም በመኖ ማቀነባበሪያዎች የሚደረገው የጥራትና ደህንነት ቁጥጥር ምን ይመስላል ስንል በባለሥልጣኑ የእንስሳት መኖ ሬጉላቶሪ መሪ ሥራ አሥፈጻሚ የሆኑትን አቶ ዘላለም አበበን ማብራሪያ እንዲሰጡን ጠይቀናል፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 እና በደንብ ቁጥር 509/2015 የተቋቋመ ሲሆን ከተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት መካከል አንዱ የእንስሳት መኖን ጥራትና ደኅንነትን ማስጠበቅ ነው፡፡ ባለሥልጣኑ የመኖን ጥራትና ደህንነት ለማስጠበቅ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ያሉት አቶ ዘላለም ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል በእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ከቅድመ- ፈቃድ እስከ ድህረ ምርት ያለውን ሂደት በመቆጣጠር የመኖን ጥራትና ደህንነት ማስጠበቅ ይገኝበታል ብለዋል፡፡ ሙሌ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ በዘርፉ እጅግ መሰረታዊ ለውጥ እያመጡ ካሉ የመኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ግንባር ቀደሙ ነው የሚሉት አቶ ዘላለም ባለሥልጣኑ በመሰል የመኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ላይ ሦስት አይነት ቁጥጥር እንደሚያደርግ ይናገራሉ፡፡ የመጀመሪያው ፋብሪካው መኖ ወደ ማምረት ሥራ ሲገባ በተቀመጠው የአሰራር መመሪያ መሰረት የተዘጋጁ መስፈርቶችን ማሟላታቸውን በሰነድና በመስክ በሚደረግ ግምገማ በማረጋገጥ መኖ ለማምረት ብቁ ነው ብሎ ሲታመን የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ይሰጣል፡፡ ይህም ሲባል ተቋሙ መኖ በማምረትና በማቀነባበር ሥራ ላይ ለመሰማራት በማመልከቻ ለተቋሙ ጥያቄ ሲያቀርብ ፋብሪካው መኖን ሊበክሉ ከሚችሉ ነገሮች/አካባቢ ከ300 እስከ 500 ሜትር የራቀ መሆኑን፣ ሁለት ባለሙያዎች ማለትም የምርት ክፍል ኃላፊና የጥራት ቁጥጥር ባለሙያ መቅጠሩን፣ ሥለሚያመርተው መኖና ለምን አይነት እንስሳት እንደሚያመርት፣ ምን ዓይነት ጥሬ እቃዎች እንደሚጠቀም የሚገልጽና ሥለ አመራረቱ የሚያሳይ ቢዝነስ ፕላን ማቅረቡን፣ ፋብሪካው ጥሬ ዕቃ እና ያለቀለት ምርት ለማከማቸት ደረጃውን የተጠበቀና በውስጡም ምርቱን ለመደርደር በቂ የመደርደሪያ ፓሌቶች፣ የሙቀትና የእርጥበት መለኪያ የተገጠመለት ምቹ መጋዘን መኖሩን፣ ፍብሪካው በሚቋቋምበት አካባቢ ከፋብሪካው በሚወጣው ፈሳሽና ደረቅ ቆሻሻ በአካባቢውና በሕብረተሰቡ ላይ ብክለት/ጉዳት የማያደርስ መሆኑን፣ ከአካባቢው የሚወጣው ነገር የሚመረተውን መኖ ጥራትና ደህንት የማይጎዳ መሆኑን በዶክመንትና በአካላዊ ምልከታ በባለሥልጣኑ በተዘጋጀ ቼክ ሊስት በባለሙያች ተረጋግጦ ሲቀርብ፣ ፋብሪካው በመኖ ማነባበር እንዲሰማራ የብቃት ማረጋገጫ የሚሰጠው ይሆናል ይላሉ አቶ ዘላለም፡፡
ይቀጥላል….!
ለበለጠ መረጃ፦
ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et
ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም፡- eaa_123
@የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤
1 411
#ኢድ_ሙባረክ!
***
የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ለእስልምና እምነት ተከታይ የባለሥልጣን መ/ቤታችን አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም ለመላ ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ1 ሺ 444ኛው የኢድ አል-አድሃ(አረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ ይላል።
በዓሉ የሰላም፣ የጤናና የመተሳሰብ እንዲሆን ከልብ ይመኛል!
#ኢድ_ሙባረክ!
@የኢትዮጵያ_ግብርና_ባለሥልጣን
