የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን
Ir al canal en Telegram
ይህ ሥለኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ትክክለኛ መረጃ የሚያገኙበት የባለሥልጣኑ የቴሌግራም አካውንት ነው።
Mostrar más1 411
Suscriptores
+224 horas
+257 días
+8530 días
Archivo de publicaciones
1 411
የእጽዋት ዝርያ ለቀቃ፣ ጥበቃና የዘር ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ጥራቱና ደኀንነቱ የተረጋገጠ የእጽዋትና የዘር ምርት ተደራሽነትን ለማሳደግ ተግቶ እየሰራ መሆኑን ገለፀ፤
****
በኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የእጽዋት ዝርያ ለቀቃ፣ ጥበቃና የዘር ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ጥራቱና ደኅንነቱ የተረጋገጠ የእጽዋት ዝርያ ለቀቃና የዘር ጥራት ተደራሽነትን ማስፋት ሲሆን ይህንም ለማረጋገጥ ዝርያ ለቀቃና ምዝገባ በአገር ውስጥ ከምርምርና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ ከመሥራት በተጨማሪ በውጪ አገር ኩባንያዎች የሚፈልቁ እጩ የእጽዋት ዝርያዎች ጥቅም ላይ ከመዋላቸው በፊት ተገቢውን ዝቅተኛ መስፈርት የምርት ጭማሬ፣ በሽታ የመከላከል አቅም፣ ለአገራችን አዲስ መሆን፣ ያላቸውን ልዩ ጥቅም የመሳሰሉ መስፈርቶች ማሟላታቸውን መሰረት አድርጎ በቴክኒካል ኮሚቴ ግምገማ በማድረግ ዝርያው እንዲለቀቅ/እንዲወድቅ ውሳኔ መሰጠትና በኮሚቴው የጸደቁ ዝርያዎችን አስፈላጊውን መረጃ በማሰባሰብ በዝርያ መዝገብ እንዲመዘገብ የማድረግና ለተጠቃሚዎች የሚደርስበትን ሆኔታ የማመቻቸት ሥራ ይሰራል፡፡
ጥራቱና ደኅንነቱ የተረጋገጠ የእጽዋት ዘር እንዲኖርና ተደራሽነታቸው እንዲያድግ በተለይም ለአርሶ አደሩና ከፊል አርሶ አደሩ እንዲሁም ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ጥራቱ የተረጋገጠ ዘር ለማምረት በሚያስፈልጉ መስፈርቶች ላይ ግንዛቤ እንዲያገኙ በማድረግ በኩል በርካታ ተግባራት ማከናወኑን የገለጹት በባለሥልጣኑ የእጽዋት ዝርያ ለቀቃ፣ ጥበቃና የዘር ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍስኃ ተሾመ ለዘር አምራቾች የራሳቸውን የውስጥ ተቆጣጣሪ አካል በማቋቋም በመስክም ሆነ በላብራቶሪ ተገቢው የዘር ጥራት ቁጥጥር ሥርዓት ዝርጋታ እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም የግብርና ምርትና ግብዓት ጥራት፣ ቁጥጥርና ግብይትን ለማሳደግ ዓለም አቀፍ የግብዓት ቁጥጥር ተሞክሮዎችን በመቀመር ከውጪ ለሚገባውም ሆነ በሀገር ውስጥ ለሚመረት ምርት የጥራት ቁጥጥር እንዲከናወን የባለሙያዎችን ክህሎትና የላቦራቶሪዎቻችንን አቅም የማሳደግ ሥራ እየተከናወነ ነው ያሉት አቶ ፍስኃ በዚህም መሰረት በመንግስት በዘር አምራች ድርጅቶች እና በግል ባለሀብቶች የሚመረተውን ዘር ከማሳ መረጣ ጀምሮ በመስክ ላይ ተገቢውን የጥራት ቁጥጥር በማድረግ እንዲሁም በላብራቶሪ የዘር ፍተሻ በማካሄድ ዘር በትክክለኛ ጊዜ፣ በትክክለኛ ጥራት፣ በትክክለኛ ቦታ እና በትክክለኛ ዋጋ ለአርሶ አደሩ ተደራሽ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
አቶ ፍስኃ አክለውም ከውጪ በሚገቡ ባእድና ወራሪ የእጽዋትና የአትክልት ዝርያዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በዘር አዋጅ 782/2005 አንቀጽ 4/1 መሰረት ማንኛውም ዘር ጥቅም ላይ ከመዋሉ በፊት በዝርያ ለቀቃ ሂደት ውስጥ አልፎ መለቀቅና መመዝገብ እንዳለበት ገልፀው ከውጪ ለሚመጣ ማንኛውም ዘር ከማንኛውም ባዕድ/ተባይ/ በሽታ/አረም ነጻ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት አስመጪው አካል ማቅረብ ግዴታ እንዳለበትና ዘሩ ወደ ሀገር ውስጥ ከገባ በኃላም ለተጠቃሚዎች ከመቅረቡ በፊት መስፈርቱን ማሟላቱ በላብራቶሪ ምርመራ ውጤቱ ተረጋግጦ ጥቅም ላይ እንደሚውል ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን እንደአዲስ ከተቋቋመ በኃላ ለተገልጋዩ የሚፈልገውን አገልግሎት ለመስጠት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ፍስኃ በየሥነ-ምኅዳሩ የተመረጡ ለዝርያ ብቃት ፍተሻ የሚያገልግል ቦታ አለማግኘት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይት ያለው ሁለገብ የጥራት ቁጥጥር ሪፈራል ላቦራቶሪ ግንባታ መጓተት፣ በስራ ላይ ያሉ ላቦራቶሪዎች በሚፈለገው መልኩ የተደራጁ አለመሆን፣ የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት፣ የሕግ ማዕቀፍ ቶሎ ያለመጽደቅ፣ ሕገ-ወጥ የዘር እና ሌሎች ግብዓቶች ንግድ መስፋፋት፣ የተሸከርካሪና ሌሎች ግብዓቶች እጥረት እንዲሁም በየክልሉ ተዘዋውሮ ሥራዎችን ለማከናወን የጸጥታ ችግር በሥራቸው ላይ እንቅፋት እንደሆኑባቸው ገልፀው እነዚህንም ችግሮች ለመቅረፍ ባለሥልጣን መ/ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፦
ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et
ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም፡- eaa_123
@የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤
1 411
የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየ2 ወር የሚያዘጋጀው የውስጥ ዜና መጽሔት የየካቲት ወር እትም በፒዲኤፍ
ለበለጠ መረጃ፦
ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et
ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም፡- eaa_123
@የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤
1 411
“አስፈላጊ የሆኑ የእንስሳት መድኃኒቶች መዝርዝር መዘጋጀት የጸረ-ተሕዋሲያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ ችግርን ለመቅረፍ ያለው ሚና ከፍተኛ ነው!”
ዶ/ር ሰለሞን ከበደ በባለሥልጣኑ የእንስሳት መድኃኒት ጥራትና ደረጃ ምዝገባና ፍቃድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
**
የጸረ-ተሕዋሲያን መድኃኒት የረቂቅ ነብሳት(ጀርሞችን) በመግደል ወይም እድገታቸውን በመግታት እንስሳትን፣ ሰዎችን እና እጽዋትን ከበሽታ እንዲድኑ የሚያደርግ መድኃኒት ሲሆን እ.ኤ.አ ከ 1940 ዓ.ም ጀምሮ የብዙ ሰዎችን እና እንሰሳትን ሕይወት ከበሽታ ሲታደግ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን መድኃኒቶቹን በአግባቡ ለእንሰሳትም ሆነ ለሰው ጥቅም ላይ እንዲውል ባለማድረጋችን የጸረ-ተሕዋስያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ(Antibiotic resistance) እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል፡፡ በፊት በሽታን ሲያድን የነበረ መድኃኒት አሁን ረቂቅ ነብሳትን ወይም ጀርሞችን መግደል ወይም እድገታቸውን መግታት አቅቶት በሽታን ማደን ሳይችል ሲቀር የጸረ-ተሕዋስያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ(Antibiotic resistance) ይባላል፡፡ የዓለም ባንክ ሪፖርት ቁልፍ ግኝቶች እ.ኤ.አ በ2017-2050 የዓለም ኢኮኖሚ ትንበያ ላይ የተመሰረቱ ሲሆኑ በጸረ-ተሕዋስያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ ምክንያት እ.ኤ.አ. በ2050 ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገሮች ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርታቸው(GDP) ኪሳራ ከ5 በመቶ በላይ እንደሚሆን፣ ተጨማሪ 28.3 ሚሊዮን ሰዎች ለከፍተኛ ድህነት እንደሚዳርግ፣ የኤክስፖርት መጠን በ3.8% እንደሚቀንስ፣ የጤና እንክብካቤ ወጪዎች ከ300 ቢሊዮን ዶላር እስከ 1 ትሪሊዮን ዶላር በዓመት እንደሚያስወጣ እና የእንስሳት ምርት በ11% እንዲያሽቆለቁል እንደሚያደርግ አመላክቷል፡፡
በአገራችን በጸረ-ተሕዋሲያን መድኃኒቶችን በጀርሞች መለመድ ችግር ምክንያት ምን ያህል ኪሳራ፣ ምን ያህል ሰዎች ለከፍተኛ ድህነት እንደሚዳረጉ፣ የኤክስፖርት መጠን በምን ያህል እንደሚቀንስ እና የእንስሳት ምርት በዓመት ምን ያህል እንደሚቀንስ ስፋትና ጥልቀት ያለው ጥናት ባለመካሄዱ በመረጃ አስደግፎ መናገር የሚያዳግት ነው የሚሉት በኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የእንስሳት መድኃኒት ጥራትና ደረጃ ምዝገባና ፍቃድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ሰለሞን ከበደ ቢሆንም ካለን የእንስሳት ጤና ሥርዓት፣ የኑሮ ደረጃ እንዲሁም ለጸረ-ተሕዋሲያን መድኃኒቶች አያያዝ እና አጠቃቀም ካለን እውቀትና ግንዛቤ አንጻር ችግሩ የበለጠ ሊከፋ እንደሚችል በተበታተነ መልኩም ቢሆን በተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ምርምር ኢንስቲትዩቶች የሚወጡ የምርምር ውጤቶች እና በቅርብ ጊዜ በባለሥልጣኑ የእንስሳት ውጤቶች፣ መድኃኒትና መኖ ጥራት ምርመራ ማዕከል በተካሄዱት የዳሰሳ ጥናቶችም አመላካች መሆኑን ይናገራሉ። በመሆኑም የችግሩ አሳሳቢነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ሲሆን ይህንን ችግር ለመቅረፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ የዓለም የጤና ድርጅት(WHO)፣ የዓለም የእንስሳት ጤና ድርጅት(WOAH)፣ የዓለም ምግብና የእርሻ ድርጅት(FAO) እና የተባበሩት መንግሰታት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም(UNEP) የጸረ-ተሕዋስያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ ለመከላከል የአምስት ዓመት ስትራተጂ እቅድ በመነደፍ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ የደረሱ ሲሆን አገራችን ኢትዮጵያም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ስትራተጂ መሰረት በማድረግ የጤና ሚኒስቴር(MOH)፣ የግብርና ሚኒስቴር(MOA) እና የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ(EPA) በአንድ ላይ በመሆን የጸረ-ሕህዋስያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ ለመከላከል የአምስት አመት ስትራተጂክ እቅድ ማዘጋጀቷን ዶ/ር ሰለሞን ገልጸዋል፡፡
ከስትራተጂክ እቅዱ በመነሳት በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ያሉት ዶ/ር ሰለሞን በዋናነት ከእንስሳት ሐኪሞች ማኅበር እና ከብሩክ ኢትዮጵያ ጋር በመሆን ለስድስት የእንስሳት ዝርያዎች አስፈላጊ የሆኑ የእንስሳት መድኃኒቶች ዝርዝር (Essential veterinary drug list) ከተመረጡ ዩንቨርሲቲዎች ማለትም ለውሻና ድመት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ለጋማ ከብቶች በባህር ዳር እና ወሎ ዩነቨርሲቲ፣ ለዶሮ በሐሮማያ ዩንቨርሲቲ፣ ለበግና ፍየል በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ለዳልጋ ከብቶች በጅማ ዩነቨርሲቲ እና ለግመሎች በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ከተወጣጡ የእንስሳት ዝርያ መሰረት ተድረጎ በተዋቀረ ግብረ ኃይል መዘርዝሩ መዘጋጀቱን ያብራራሉ፡፡ የተዘጋጀው የስድስት እንስሳት ዝርያዎች አስፈላጊ የሆኑ የእንስሳት መድኃኒቶች መዘርዝር በተመረጡ ከ 3-5 በሙያው እና በዘርፉ የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች እንዲገመገም የተላከ ሲሆን በዚህ ወር መጨረሻ በመድረክ እንዲገመገም ተደርጎ በሚመለከተው አካል ፀድቆ ወደ ሥራ የሚገባ ይሆናል፡፡
የመዘርዝሮቹ መዘጋጀት በእንስሳት ጤና አገልግሎቱ የሚያስፈልጉ ገበያ ላይ መገኘት ያለባቸውን የእንስሳት መድኃኒቶች ጥቆማ የሚሰጥ ሲሆን መዘርዝሩን እና የእንስሳት ሕክምና አሰጣጥ መመሪያ(Standard Veterinary Treatment Guideline) መሰረት በማድረግ በፊልድ ላይ የሚሰሩ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች የሚፈልጓቸውን መድኃኒቶች በገበያ ላይ እንዲገኙ ጥያቄ ያቀርባሉ ተብሎ ይታመናል የሚሉት ዶ/ር ሰለሞን ይሄንንም ጥያቄ መሰረት በማድረግ አቢሲኒያ የእንስሳት መድኃኒት አስመጪዎች እና ጅምላ አከፋፋዮች ማኅበር፣ የእንስሳት መድኃኒት አስመጪዎች እና አምራቾች የተጠየቁት መድኃኒቶች ሕጋዊ ሂደቱን ተከትለው ተመዝግበው ወደ ገበያ እንዲቀርቡ የበኩላቸውን ሚና ይጫወታሉ ተብሎ እንደሚገመት ገልጸዋል፡፡
የእንስሳት መድሃኒት አቅረቦትንና ዋጋን ለማሻሻል እና በተጨማሪም በግል የእንስሳት መድሃኒት አስመጪ ባለሀብቶች የማያስመጧቸውን አስፈላጊ የእንስሳት መድሃኒቶች አቅርቦት ላማሻሻል ልክ እንደ በጤና ሚኒሰቴር የኢትዮጲያ የመድሃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ በግብረና ሚኒስቴር የመንግስት የልማት ድርጅት የሆነው የግብረና ግብዓት አቅርቦት ኮርፖሬሽን የእንስሳት መድሃኒት አስመጪ ይህን ክፍተት ቢሞላ የጸረ-ተሕዋስያንን በጀርሞች መለመድ በመከላከል በኩል የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንም ዶ/ር ሰለሞን አብራርተዋል፡፡
በአጠቃላይ የጸረ-ተሕዋሲያን መድኃኒት በጀርሞች መለመድን ችግር ለመቀልበስ የሚያስችል ስልት መንደፍ እና መተግበር፤ በእንስሳት ኃብት ልማት ዘርፍ ውስጥ የሚሳተፉ ባለድርሻ አካላትን ግንዛቤ ማሳደግ እንዲሁም ከሌሎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሥራት እጅግ አስፈላጊ ነው የሚሉት ዶ/ር ሰለሞን የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን መሰል የመድኃኒት አማራጮችን ለማስፋት እና ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚጠበቅበትን ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፦
ስልክ፡- 011 553 45 20
ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et
ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም፡- eaa_123
ነፃ ጥሪ፡- 8083
ፖ.ሳ.ቁ፡- 31303
1 411
የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የሚሌ የእንስሳት ኳራንታይን ጣቢያን ሥራ ለማስጀመር የሚያስችልየምክክር መድረክ ተካሄደ፤
*
የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የእንስሳት ኳራንቲን ጣቢያዎችና ቼክ ፖስቶችን በመገንባትና በግንባታ ላይ ያሉትን ደረጃቸውን እንዲጠብቁና ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ የውስጥ አደረጃጀታቸውን በመፈተሸ ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ ሞያዊ ድጋፍና ቁጥጥር በማድረግ በሌሎች አገራት ተቀባይነት እንዲኖራቸው እንዲሁም በተቀባይ ሀገሮች በማስገምገም እውቅና እንዲያገኙ የማድረግ ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ ይሄን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለውን የሚሌ እንስሳት ኳራንታይን ጣቢያን ሥራ ለመጀመር የሚያስችል የምክክር መድረክ ከቁም እንስሳት ላኪዎች፣ ከቁም እንስሳት ላኪዎች ማሕበርና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በአዳማ አካሂዷል፡፡
የምክክር መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ አገራችን ኢትዮጵያ በቁም እንስሳት ኃብቷ ከአፍሪካ የቀዳሚነቱ ከዓለም ደግሞ ከመጀመሪያዎቹ 10 አገራት ተርታ የምትመደብ ቢሆንም ከዘርፉ ባላት ኃብት ልክ መጠቀም አልቻለችም ብለዋል፡፡ ከእኛ በብዙ እጥፍ ያነሰ የቁም እንስሳት ኃብት ቁጥር ያላቸው ጎረቤት አገራት እንኳ ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው በመስራታቸውና አስፈላጊ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት እንዲሁም የግብይት ሥርዓታቸውን በማዘመን በስፋት ኤክስፖርት አድረገው የተሻለ ገቢ በማግኜት ላይ ይገኛሉ ያሉት አምባሳደር ድሪባ ከእንስሳት እርባታ እስከ ቁጥጥር ሥርዓታችን ድረስ መዋቅራዊ የሆኑ ማነቆዎች በመኖራቸውና በተለይም የግብይት ሥርዓቱ ሕግን ያልተከተለና ያልዘመነ መሆኑ አገራችን ከዘርፉ በሚገባት ልክ ተጠቃሚ እንዳትሆን ማድረጉን አብራርተዋል፡፡
አምባሳደር ድሪባ አክለውም በእንስሳት ዘርፍ የተጠናከረ የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋትና መተግበር ብሎም የንግድ ሥርዓቱን ማዘመንና በዓለምአቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነትን ማጎልበት ከዘርፉ የሚገኜውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ አይነተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣንም ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ዘርፉን ካሉበት ችግሮች ለማላቀቅና የአገራችንን ኹለንተናዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ የሚያስችሉ የሕግ፣ የአሰራርና የመዋቅር ማሻሻያዎችን እያደረገ ነው ብለዋል፡፡
የምክክር መድረኩ ዓላማም የቁም እንስሳት ላኪዎችን፣ የቁም እንስሳት ላኪዎች ማሕበርና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን እና ኳራንቲን ጣቢውን ለማስተዳደር ውል የወሰደውን ድርጅት በማስተዋወቅ የሚሌ እንስሳት ኳራንቲን ጣቢያውን ሥራ ለማስጀመር ነው ያሉት አምባሳደር ድሪባ መንግስት የሚሌ ኳራንታይን ጣቢያ ሥራ መጀመር እንስሳቶቻችን ከበሽታ ነጻ መሆናቸው እዚሁ አገራችን ላይ ተረጋግጦ እንዲላክ በማድረግ እንስሰታን በስፋት ወደ ውጭ ለመላክና አገልግሎቱን ለማሻሻል አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል፡፡ ደራጀውን የጠበቀ ኳራንቲን ራሱ ገንብቶ ራሱ አገልግሎት መሰጠት ውጤታማ ለመሆን አሰቸጋሪ ሰለሆነ የሌሎች አገራትን ተሞክሮና ልምድ በመውሰድ በመመሪያ መሰረት የሚሌ የእንስሳት ኳራንቲን ጣቢያን ሙሐመድ ሐሚድ አሊሳ ወደ ተባለ ግል ድርጅት ኢንዲዞር በማድረግ ሥራ ለማስጀመር በሥራ ላይ መሆኑን አምባሳደር ድሪባ ተናግረዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ በሚሌ እንስሳት ኳራንታይን ጣቢያው የግል ድርጅቱ፣ የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን፣ የቁም እንስሳት ላኪዎች፣ የቁም እንስሳት ላኪዎች ማሕበርና የሌሎች ባለድርሻ አካላት ተግባርና ኃላፊነት ምን ሊሆን ይገባል በሚለው ላይ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ሕገ-ወጥ የቁም እንስሳት ንግድ ለመከላከል፣ ለዘርፉ እድገት ወሳኝ የሆኑ ዘመናዊ መሰረተ ልማቶችን ለማሟላት እና አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ከማድረግ አኳያና ሌሎች በመንግስትና ኳራንቲን ጣቢያውን ለማስተዳደር ውል በወሰደው የግል ድርጅት በኩል በትኩረት ሊታዩ ይገባል ያሏቸውን ኃሳቦች ተሳታፊዎቹ አንስተዋል፡፡
የሚሌ የእንስሳት ኳራንቲን ጣቢያን ለማስተዳደር ውል የወሰደው ሙሐመድ ሐሚድ አሊሳ ድርጅትም አገልግሎቱን ለማዘመንና የቁም እንስሳት ንግዱን ለማሳደግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁሉ ተቀናጅቶ እንደሚሰራ ገልጧል፡፡
ባለሥልጣን መ/ቤቱ በውይይቱ ከባለድርሻ አካላት የተነሱትን ኃሳቦች ወስዶ ለዘርፉ እድገት በሚጠቅም መንገድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁሉ ተባብሮ ያሰራል ያሉት የባለሥልጣን መ/ቤቱ የእንስሳት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሐሚድ ጀማል የቁም እንስሳትን በስፋት ኤክሰፖርት ለማድረግና የዘርፉን ተወዳዳሪነት ብሎም ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ የሚሌ እንስሳት ኳራንታይን ጣቢያ ሥራ መጀመር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ሐሚድ አክለውም የሚሌ እንስሳት ኳራንታይን ጣቢያ ሥራ መጀመር የቁም እንስሳት ኤክስፖርተሮች ከአሁን ቀደም እንስሳቶችን ወደ ውጭ ለመላክ ይደርስባቸው የነበረውን መንገላታትና አላስፈላጊ ወጭ በመቀነስ በኩል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ በቀጣይም ደረጃቸውን የጠበቁ የኳራንቲን ጣቢያዎች እንዲገነቡ በማድረግና ሌሎች አስፈላጊ መሰረተ ልማቶችን በማሟላትና በማዘመን ከአሁን ቀደም ከነበሩን የቁም እንስሳት ኤክስፖርት መዳረሻ ገበያዎቻችን ማለትም ከመካከለኛ ምስራቅ እና ከሰሜን አፍርካ አገራት በተጨማሪ ለአውሮፓ እና ለሌሎች አገራት በመላክ የአገራችንን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ባለሥልጣን መ/ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም የሚሌ እንስሳት ኳራንቲን ጣቢያው የሚሰጠውን አገልግሎት ለመጠቀምና በሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍና የቁም እንስሳትንን ንግድ ለማሳደግ በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ በመድረስ የምክክር መድረኩ ተጠናቋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፦
ስልክ፡- 011 553 45 20
ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et
ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም፡- eaa_123
ነፃ ጥሪ፡- 8083
ፖ.ሳ.ቁ፡- 31303
@የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤
1 411
በሆርቲካልቸር ሴክተር ባላፉት ሰባት ወራት ከ400 ሚሊየን ዶላር ባላይ ገቢ መገኜቱ ተገለጸ፤
******
የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራች ላኪዎች ማኅበር ያዘጋጀው 8ኛው የሆርቲካልቸር ኤክስፖ በሚሊኒየም አደራሽ ዛሬ የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ተከፈቷል፡፡
በኤክስፖ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የሆርቲካልቸር ዘርፉ ለበርካቶች የስራ እድል የፈጠረና የውጭ ምንዛሬን እያስገኘ ያለ እንደሆነ የተናገሩት የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ በተያዘው የ2015 በጀት ዓመት ባላፉት ሰባት ወራት ውስጥ ከ400 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል።
ዶ/ር ግርማ አክለውም አገራዊ ኢኮኖሚውን ከሚደግፍ አንጻር ጥሩ ውጤት ከታየባቸው ዘርፎች መካከል ሆርቲካልቸር አንዱ እንደሆነ ተናግረዋል።
ኤክስፖው ዓለምአቀፍ የገብያ ትስስርን ለመፍጠርና የተወዳዳሪነትን አቅም ለማሳድግ ትልቅ ሚና እንዳለው ተጠቅሷል።
@ኢፕ.ድ
ለበለጠ መረጃ፦
ስልክ፡- 011 553 45 20
ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et
ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም፡- eaa_123
ነፃ ጥሪ፡- 8083
ፖ.ሳ.ቁ፡- 31303
@የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤
1 411
«እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ!»
***
የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ለሴት ሰራተኞቹና ለመላ ኢትዮጵያውያን ሴቶች «እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ!» በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ለ112ኛ እንዲሁም በአገራችን ለ47ኛ ጊዜ ለሚከበረው ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን(ማርች 8) እንኳን አደረሳችሁ ይላል!
ለበለጠ መረጃ፦
ስልክ፡- 011 553 45 20
ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et
ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም፡- eaa_123
ነፃ ጥሪ፡- 8083
ፖ.ሳ.ቁ፡- 31303
@የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤
1 411
የግብርና ሚኒስቴር እና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በግብርና ምርቶች ግብይት ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ውይይት አደረጉ፤
*
የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ.ር) እና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረ መስቀል ጫላ እና ሌሎች አመራሮች በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትላንት የካቲት 27 ቀን ተወያይተዋል።
በዕለቱ የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣንን ጨምሮ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹ እና ተጠሪ ተቋማቶቻቸው የተውጣጡት ባለድርሻ አካላት በግብርና ምርቶች ግብይት ችግሮችና በመፍትኄ አቅጣጫዎች ላይ ተወያይተዋል።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታዋ ሶፊያ ካሳ (ዶ.ር) በግብርና ምርት ግብይት አኹናዊ ቁመና ላይ የመነሻ ጽሁፍ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።
በመነሻ ጽሁፉ የሕገ ወጥ ደላላ ቁጥጥር ሥርዓት የላላ በመሆኑ በጥራጥሬ ብሎም በእንስሳት፥ በአትክልትና ፍራፍሬ ግብይት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳረፉ መሆኑ ተገልጿል።
በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ውጪ እየወጡ ያሉ የግብርና ምርቶች ፣የቁም እንስሳት፥ ማር፥ የግመል ወተትና የእንስሳት መኖ ላይ የቁጥጥር ሥርዓት ሊበጅለት ይገባል ተብሏል።
ለሕብረት ሥራ አባላት የሚቀርበው መሰረታዊ የድጎማ ሸቀጥ፣ ዘይትና ዱቄት በመጠንና በወቅቱ ለማቅረብ በጋራ ለመሥራት ሁለቱ መስሪያ ቤቶችና ተጠሪ ተቋማት ተወያይተዋል።
ለበለጠ መረጃ፦
ስልክ፡- 011 553 45 20
ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et
ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም፡- eaa_123
ነፃ ጥሪ፡- 8083
ፖ.ሳ.ቁ፡- 31303
@የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤
1 411
አቶ ብዙነህ፦ የማስተላልፈው መልዕክት ቢኖር የእጽዋት ኳራንታይን ጣቢያዎች በሰው ኃይል፣ በግብዓት እና በላቦራቶሪ የተጠናከሩ አለመሆን አገራችንን ለጎጅ ተባዮች በማጋለጥ በሕብረተሰብ ጤና ላይ ጉዳት ከማስከተሉም ባሻገር ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶቻችን የተቀባይ አገራትን መስፈርቶች ያሟሉ እንዳይሆኑ በማድረግ በአገሪቱ የውጭ ንግድ ላይ ክፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡ በመሆኑም ባለሥልጣን መ/ቤቱ የእጽዋት ኳራንታይን ጣቢያዎች በቁጥር እንዲጨምሩና በአቅምም እንዲጠናከሩ በማድረግ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ጥራትና ደህንነት በመጠበቅ በዓለምአቀፍ ገብያ ተወዳዳሪ እንድንሆንና ወደ አገር ውስጥ የሚገቡትም አገራችን ያስቀመጠችውን የማስገቢያ መስፈርት ያሟሉ መሆናቸውንና ምንም አይነት ስጋት የሌለባቸው መሆኑን በመስክ ቁጥጥርና በላብራቶሪ በተደገፈ ምርመራ በማረጋገጥ እንዲገቡ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል እላለሁ፡፡
ሕዝብ ግንኙነት፦ ለነበረን ቆይታ አናመሰግናለን!
አቶ ብዙነህ፦ እኔም አመሰግናለሁ!
ለበለጠ መረጃ፦
ስልክ፡- 011 553 45 20
ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et
ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም፡- eaa_123
ነፃ ጥሪ፡- 8083
ፖ.ሳ.ቁ፡- 31303
@የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤
1 411
ትኩረት የሚሻው የእጽዋት ኳራንታይን!
*****
የእጽዋት ኳራንታይን አሰራር ዓለምአቀፍ የሕግ ማዕቀፍን ተከትሎ የሚከናወን ቢሆንም አገራችን ኢትዮጵያ የእጽዋት ዘር ኳራንታይንን አስመልክቶ ዓለምአቀፉን አሰራር ለማሟላት ሳትችል ቆይታለች፡፡ በዚህም በርካታ ባዕድ ጎጅ ተባዮች ወደ አገር ውስጥ ገብተው በመስፋፋት ሰፊ ጉዳት በማድረስ ላይ ናቸው፡፡ በተጨማሪም የእጽዋት ዘር ኳራንታይንን ሥራ ይሰራ የነበረው በግብርና ሚ/ር ሥር በተበታተነ መልኩ ሥለነበረ ክፍሉም በልማት ሴክተሩ ውስጥ በመሆኑ በነጻነት የቁጥጥር ሥራውን ማከናወን ስለተሳነው እና ወደ ውጭ ለሚላኩ ምርቶች ደረጃውን የጠበቀ የኳራንታይን አገልግሎት መሰጠት ባለመቻሉ የኤክስፖርት አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሮ ቆይቷል፡፡ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳትም መንግስት የእጽዋት ኳራንታይን ሥራ በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ እንዲሰራ ለማድረግ እና ከአሁን ቀደም ይቆጣጠረው ከነበረው ከግል ሴክተር በተጨማሪ የልማት ሴክተሮችንም ለመቆጣጠር የሚረዳ ተቋም “የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን” ን የፌዴራል መንግስት የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣን እና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 45 ንኡስ አንቀጽ 1 መሠረት አቋቁሟል፡፡ የባለስልጣኑን አደረጃጀት፣ ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው ደንብ ቁጥር 509/2014 መሠረትም ባለስልጣኑ የእጽዋት ኳራንታይን አግልጋሎት የሚሰጥ የቅድመና ድኅረ መግባት የኳራንታይን እና የዘር ድኅረ ጥራት ጣቢያዎችን በማቋቋምና በማደራጀት የእጽዋት ግብዓቶች ከተመዘገቡ በኋላ በክምችት በማጓጓዝ፣ በሥርጭት፣ በግብይት፣ በአጠቃቀም እና በአወጋገድ ወቅት አግባብነት ባለው የሕግ ማዕቀፍ መሰረት የመቆጣጠር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በባለሥልጣኑ ይሄን ሥራ በውጤታማነት ለመፈጸም ያስችለው ዘንድ 11 የእጽዋት የኳራንታይን ጣቢያዎችን በመክፈት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በዛሬው እትማችንም የእጽዋት ኳራንታይን ጣቢያዎች አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ምን ይመስላል? የሚለውን የአደማ የእጽዋት ኳራንታይን ጣቢያን እንደናሙና በመውሰድ ከአደማ የእጽዋት ኳራንታይን ጣቢያ አስተባበሪ አቶ ብዙነህ ኃይሌ ጋር አጭር ቆይታ በማድረግ የምናስቃኛችሁ ይሆናል፤ መልካም ቆይታ፡፡
ሕዝብ ግንኙነት፦ የእጽዋት ኳራንታይን ማለት ምን ማለት ነው?
አቶ ብዙነህ፦ የእጽዋት ኳራንታይን ስንል እጽዋትና የእጽዋት ውጤቶች ለተጨማሪ ኢንስፔክሽን ወይም ለማከም ኦፊሴላዊ በሆነ መንገድ ለተወሰነ ጊዜ ማግለል ወይም ዘርንና እጽዋትን ከሚጎዱ ሕይወት ያላቸው ተባዮች ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር እንዳይገባ ለመከላከል የሚደረግ የቁጥጥር ተግባር ነው ነው፡፡ ቁጥጥሩ ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ፣ ወደ ውጭ አገር በሚላኩ እና በአገር ውስጥ በሚዘዋወሩ እጽዋት፣ የእጽዋት ውጤቶችና ሌሎች ቁጥጥር በሚደረግባቸው ቁሳቁሶች ላይ ይካሄዳል፡፡
ሕዝብ ግንኙነት፦ የአደማ የእጽዋት ኳራንታይን ጣቢያን የሚያከናውናቸው ተግባራት ምንድን ናቸው?
አቶ ብዙነህ፦ የአደማ የእጽዋት ኳራንታይን ጣቢያ ከባለሥልጣን መ/ቤቱ በተሰጠው ሥልጣንና ተግባር መሠረት በሚወጡና በሚገቡ እጽዋቶችና የግብርና ምርቶች ላይ ሁለት አይነት ማለትም የሠነድና አካላዊ ፍተሸ ያካሂዳል፡፡ ለምሳሌ አንድ እህል ወደ ቻይና ለመላክ የተዘጋጀ ቢሆን በሰነድ የተቀመጠው ነገር በትክክል መተግበሩንና ቻይና ከማትፈልገው ተባይ ነጻ መሆኑን ቼክ በማድረግ ይሄን ሲያልፍ 72 ስዓት መጋዘኑን አሽገን በኬሚካል አክመን እንዲላክ እናደርጋለን፡፡ በዋናነት ግን የአዳማ የእጽዋት ኳራንታይን ጣቢያ የወጭና ገቢ ምርቶች ላይ፣ የብቃት ማረጋገጫ እና የሕክምና አገልግሎት ላይ ይሰራል፡፡ ወደ ውጭ ከሚላኩ ምርቶች ጋር ተያይዞ በአዳማ የእጽዋት ኳራንታይን ጣቢያ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ስንመለከት የቅባት እህሎች፣ ጥራጥሬ፣ ቅመማ ቅመም፣ …. የአገዳ እህሎች፣ አትክልትና ፍራፍሬ የመሳሰሉት ናቸው፡፡ በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት በአዳማ የእጽዋት ኳራንታይን ጣቢያ በኩል 35981 ሜትሪክ ቶን ጥራጥሬ፣ 609 ሜትሪ ቶን አትክልት፣ 4637 ሜትሪክ ቶን ፍራፍሬ፣ 3485 ሜትሪክ ቶን የቅባት እህሎች፣ 2266 ሜትሪክ ቶን ቅመማ ቅመም ወደ ውጭ አገር የተላኩ ዋና ዋና ምርቶች ሲሆኑ ቻይና፣ ሕንድ፣ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬት፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ፓኪስታን፣ ሩሲያ፣ ጣሊያን የመሳሰሉት አገራት ደግሞ ዋና መዳረሻዎቻችን ናቸው፡፡
ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ገቢ ምርቶችን ስንመለከት በአዳማ የእጽዋት ኳራንታይን ጣቢያ በዋናነት ወደ አገር ውስጥ የሚገቡት የአፈር ማዳበሪያ እና የእርሻ ኬሚካሎችን ሲሆኑ እነዚህን በብዛት የምናመጣባቸው አገሮችም ቻይና፣ ሆላንድ፣ ሕንድ፣ ኖርዌይና ጀርመን ናቸው፡፡ እነዚህ ሲገቡ የሚያመጡት ሰነድ ላይ አስፈላጊ ነገሮች መሟላታቸውን ካረጋገጥን በኋላ ጉሙሩክ ጣቢያ በመገኜት በሰነዱ መሰረት መሆናቸውን አካላዊ ምልከታ በማድረግ ሕጉን ጠብቆ የገባ መሆኑን ስናረጋግጥ ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ መልቀቂያ እንሰጣለን፡፡ ሌላኛው የኳራንታይን ጣቢያው የሚሠራው ሥራ አስመጭና ላኪዎች ንግድ ፍቃድ አውጥተው በዘርፉ ላይ ከመሰማራታቸው በፊት በባለሥልጣን መ/ቤቱ የተቀመጡ መሥፈርቶች መሟላታቸውን በማረጋገጥ ለባለሥልጣን መ/ቤቱ የብቃት ማረጋገጫ እንዲሰጣቸው እንጽፋለን፡፡ ባለሥልጣን መ/ቤቱም ለንግድ ሚ/ር ንግድ ፍቃድ እንዲሰጣቸውና ንግድ ፍቃድ አውጥተው በዘርፉ እንዲሰማሩ ደብዳቤ ይጽፋል ማለት ነው፡፡ በኳራንታይን ጣቢያው 4ኛው ሥራችን የሕክምና አገልግሎት ሲሆን በዚህ ዘርፍ ወደ ውጭ አገር የሚላኩ እህሎች በአግባቡ ታክመው 72 ስዓት ታሽገው ከተባይ ነጻ ሆነው እንዲሄድ የምናደርግበት የአሰራር ሥርዓት ነው፡፡ በአጠቃላይ የአዳማ የእጽዋት ኳራንታይን ጣቢያ እነዚህን ከላይ የገለጽኳቸውንና ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
ሕዝብ ግንኙነት፦ የአደማ የእጽዋት ኳራንታይን ጣቢያን ሥራዎችን ሲያከናውን እንቅፋት የሆኑበት ነገሮች ምንድን ናቸው?
አቶ ብዙነህ፦ ብዙ ጊዜ የሚያጋጥሙን ችግሮች ውስጣዊና ውጫዊ ናቸው፡፡ ውጫዊ ስንል መጋዘኖቻችን በሕጉ በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ያለመሆንና የመጋዘን ጥበት መኖር ነው፡፡ የመጋዘን ጥበት ሲኖር ደግሞ ለተባይ የመጋለጥ እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ውስጣዊ ችግሮቻችን ደግሞ የእጽዋት ጤንነት የሚረጋገጥበት ላቦራቶሪ አለመኖር፣ ወደ አገር ውስጥ የገባን እጽዋት(ዘር) በኢንስፔክሽን ብቻ ተመስርቶ ከመሰራጨቱ በፊት ለዚሁ ተብሎ በሚደራጅ ቦታ በማሳደግ ክትትል የሚደረግበት የድኅረ መግባት ኳራንታይን መሰረተ ልማት አለመኖር፤ የቢሮ ጥበት፣ ለፍተሸ የምንቀሳቀስበት የተሸከርካሪ እጥረት፣ የሰው ኃይልና የግብዓት እጥረቶች በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ሕዝብ ግንኙነት፦ ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልዕክት ካለ?
1 411
የአድዋ ድል ለኢትዮጲያ ሕዝቦች አንድነት መጠናከርና ዘላቂነት መሠረት ነው ተባለ፤
****
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በአገር አቀፍ ደረጃ 127ኛ ጊዜ እየተከበረ ያለውን የአድዋ ድል መታሰቢያ በአል ‹‹ለአገራዊ አንድነት፣ ጀግንነትና ጽናት›› በሚል መሪ ቃል የባለስልጣኑ የሥራ ኋላፊዎችና ሠራተኞች በተገኙበት ዛሬ የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ አከብሯል፡፡
በዝግጅቱ ላይ የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓልን በተመለከተ የተዘጋጀውን የመወያያ ሰነድ በሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አዲስ እጅጉ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ውይይቱን የመሩት የባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ የዓድዋ ድል እኛ ኢትዮጲያዊያን በአንድነትና ላቅ ባለ አገራዊ ስሜት ተጋግዘን ጠላቶቻችንን ያንበረከክንበት፣ የነጮችን የበላይነት ሰብረን ነጻነታችንንና የጥቁር ሕዝቦች አሸናፊነትን ያወጅንበት እንድሁም ለሌሎች በቀኝ ግዥ ቀንበር ሥር ለነበሩ የአፍሪካ አገራት ከቅኝ ግዛት መውጣት እንደሚችሉ ተምሳሌት የሆንበት ነው ብለዋል፡፡
የአድዋ ታሪክን ስናስብ የመሪዎች ሚና እንዳለ ሆኖ ይህ ድልና ታሪክ የሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ድልና ታሪክ መሆኑን የገለጹት አምባሳደር ድሪባ መላ ኢትዮጵያውያን በብሔር፣ በቋንቋ፣ በፖለቲካ ሳንለያይ በአንድነት ስንቆም ማንኛውንም ፈተና በድል የመወጣት አቅም እንዳለን አደዋ በቂ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አምባሳደር ድሪባ አክለውም የዓድዋን ድልን በሚመጥን መልኩ በሚገባ በመዘከርና በዜጎች አስተሳሰብ ውስጥ እንዲሰርጽ በማድረግ ለሌላ ድል እንዲሰለፉ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን ወጣቱ ትውልድም በአባቶቻችን የተከፈለለትን የሕይወት መስዋዕትነት በውል በመገንዘብ ለአገራችን ሁለንተናዊ ሰላምና እድገት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
የአድዋ ድል የአንድነታችን፣ የጀግንነትና የጥንካሪያችን መገለጫ ነው ያሉት የውይይቱ ተሳታፊዎች አባቶቻችን አገራችን ኢትዮጵያ በጠላት እጅ እንዳትወረርና በቅኝ ገዥዎች ስር እንዳትሆን ለአንድያ ሕይወታቸው ሳይሳሱ በጀግንነት ተዋግተውና ውድ ሕይወታቸውን ሰውተዉ ዛሬ ላይ በነጻነት እንድንቆም አድርገዉናል ብለዋል፡፡ ከየአድዋ ታሪክ የምንማረው አሁን ላይ አገራችንን ለማፍረስና አንድነታችንን ለመሸርሸር በተለያየ መልኩ የሚነዙ አሉባልታዎችንንና እየገጠሙን ያሉ ችግሮችን በቁርጠኝነትና በጽናት በመታገልና ለሕዝባችንና ለአገራችን አንድነት ዘብ መቆም እንዳለብን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በየአመቱ የመታሰቢያ በአሉ ሲከበር ቀኑን አስቦ ከመዋል ባለፈ የአድዋን የድል ታሪክ ስንቅ በማድረግ እኔ ለአገሬም ምን ሰራሁ? በማለት እራስን መጠየቅና በውስጥ ያሉብንን ችግሮች በውይይት እየፈታን በተሰማራንበት የስራ መስክ ውጤታማ ሥራ በመሥራት ሊሆን ይገባል ያሉት አምባሳደር ድሪባ እንደባለሥልጣን መ/ቤት የተጣለብንን አገራዊ ኃላፊነት የአባቶቻችንን መንፈስ በመላበስ በአንድነትና በጊዜ የለኝም ስሜት መሥራት እንደሚገባ አሳስበው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፦
ስልክ፡- 011 553 45 20
ዌብሳይት፡- www.eaa.gov.et
ፌስቡክ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን/Ethiopian Agricultural Authority
ቴሌግራም፡- የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን
ነፃ ጥሪ፡- 8083
ፖ.ሳ.ቁ፡- 31303
@የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፤
