የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን
Ir al canal en Telegram
ይህ ሥለኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ትክክለኛ መረጃ የሚያገኙበት የባለሥልጣኑ የቴሌግራም አካውንት ነው።
Mostrar más1 411
Suscriptores
+224 horas
+257 días
+8530 días
Archivo de publicaciones
1 411
በኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የእፅዋት ዝርያና ዘር መሪ ስራ አስፈፃሚ አስተባባሪነት የብሔራዊ ዝርያ አፅዳቂ ኮሚቴ የመጀመሪያ ዙር ስብሰባውን በቢሾፍቱ ከተማ ያቱ ሆቴል ማካሄድ ጀመረ
ኮሚቴው ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚያካሂደው ስብሰባ ከተለያዩ የምርምር ተቋማትና የግል ድርጅቶች የቀረቡ 144 ዕጩ ዝርያዎች ላይ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል
1 411
ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የሚቀርበውን የስጋ ምርት ጥራትና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው።
(አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)
ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ገበያ የሚቀርበውን የስጋ ምርት ጥራትና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ገለፀ።
የስጋ ምርት ጥራትና ደህንነትን ለማረጋገጥ እየተዘጋጀ ያለውን ረቂቅ አዋጅና የማስፈፀሚያ ደንቦች በግብዓት ለማዳበር ያለመ የዘርፉ ምሁራንና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት መድረክ ተካሄዷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የግብርና ሚኒሰቴር የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ እንደገለጹት፤ ስጋ ለሀገር ውስጥ ፍጆታ በስፋት ጥቅም ላይ ከመዋሉም ባለፈ ወደ ዓለም ገበያ ተልኮ ለሀገሪቷ የውጭ ምንዛሪ እያስገኘ ነው ብለዋል።
''ኢትዮጵያ የስጋ ምርቶችን በዋናነት ወደ መካከለኛው ምስራቅ እየላከች ትገኛለች'' ያሉት ዶክተር ፍቅሩ የተቀባይ ሀገራትን የጥራት ደረጃ ያሟላ የስጋ ምርት ለመላክም ሆነ የምርቱን የውጭ ገበያ ተደራሽነት ለማስፋት የህግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀት ማስፈለጉን ተናግረዋል።
በተለይ ተቀባይ ሀገራት በምርቱ ላይ ያላቸውን መተማመን ለማሳደግ ጤንነቱ፣ ደህንነቱና ጥራቱ የተረጋገጠ የስጋ ምርት ተደራሽ ማድረግ ሲቻል መሆኑን ጠቅሰዋል።
የዓለም የእንስሳት ጤና ድርጅት ያስቀመጠውን የጥራት ደረጃ ያሟላ የስጋ ምርት ለመላክ የህግ ማዕቀፎችና አሰራሮች ትልቅ ጠቀሜታ አላቸው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሃሚድ ጀማል በበኩላቸው የህግ ማዕቀፉ የስጋ ምርት የወጪ ንግድ ላይ ወሳኝ ሚና ያለው መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም ብቁና የሰለጠነ የሰው ሃይል በዘርፉ እንዲኖር፣ የቁጥጥር ስርዓቱ የሚመራበት ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ሀገሪቷ እንዲኖራት ለማስቻል የህግ ማዕቀፍ ማሻሻል ማስፈለጉን ገልጸዋል።
በባለስልጣኑ የእንስሳት ምርት ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አያሌው ሹመት የነበረው የስጋ ምርት ደህንነትና ጥራት ምርመራ አዋጅና ደንብ ለረጅም ዓመታት ስራ ላይ መቆየቱን ገልጸዋል።
ነባር ህጎች ከዓለም አቀፍ የእንስሳት ጤና ድርጅት መስፈርት አኳያ ማሰራት የማይችሉና በዓለም ገበያ በስፋት ዘልቀው ለመግባት ማነቆ መሆናቸውን አንስተዋል።
አዋጆቹ በ1962 ዓ.ም እንዲሁም ደንቡ በ1963 ዓ.ም የወጣ መሆኑን የጠቀሱት ዶክተር አያሌው በ1976 ዓ.ም ውስን ማሻሻያ ተደርጎበት እስከ አሁን በስራ ላይ ይገኛል ብለዋል።
የህግ ማዕቀፎቹ ኢትዮጵያ አሁን ከደረሰችበት ልማትና እድገት ጋር የማይጣጣሙ ከመሆናቸውም ባለፈ የተቀባይ ሀገራት አስቻይ ጥያቄዎችን መመለስ የማይችሉ በመሆኑ ማሻሻል ማስፈለጉን ተናግረዋል።
የዘገባ ምንጫችን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ነው
1 411
ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የሚቀርበውን የስጋ ምርት ጥራትና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው።
(አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)
ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ገበያ የሚቀርበውን የስጋ ምርት ጥራትና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ገለፀ።
የስጋ ምርት ጥራትና ደህንነትን ለማረጋገጥ እየተዘጋጀ ያለውን ረቂቅ አዋጅና የማስፈፀሚያ ደንቦች በግብዓት ለማዳበር ያለመ የዘርፉ ምሁራንና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት መድረክ ተካሄዷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የግብርና ሚኒሰቴር የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ እንደገለጹት፤ ስጋ ለሀገር ውስጥ ፍጆታ በስፋት ጥቅም ላይ ከመዋሉም ባለፈ ወደ ዓለም ገበያ ተልኮ ለሀገሪቷ የውጭ ምንዛሪ እያስገኘ ነው ብለዋል።
''ኢትዮጵያ የስጋ ምርቶችን በዋናነት ወደ መካከለኛው ምስራቅ እየላከች ትገኛለች'' ያሉት ዶክተር ፍቅሩ የተቀባይ ሀገራትን የጥራት ደረጃ ያሟላ የስጋ ምርት ለመላክም ሆነ የምርቱን የውጭ ገበያ ተደራሽነት ለማስፋት የህግ ማዕቀፎችን ማዘጋጀት ማስፈለጉን ተናግረዋል።
በተለይ ተቀባይ ሀገራት በምርቱ ላይ ያላቸውን መተማመን ለማሳደግ ጤንነቱ፣ ደህንነቱና ጥራቱ የተረጋገጠ የስጋ ምርት ተደራሽ ማድረግ ሲቻል መሆኑን ጠቅሰዋል።
የዓለም የእንስሳት ጤና ድርጅት ያስቀመጠውን የጥራት ደረጃ ያሟላ የስጋ ምርት ለመላክ የህግ ማዕቀፎችና አሰራሮች ትልቅ ጠቀሜታ አላቸው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሃሚድ ጀማል በበኩላቸው የህግ ማዕቀፉ የስጋ ምርት የወጪ ንግድ ላይ ወሳኝ ሚና ያለው መሆኑን ተናግረዋል።
የዘገባ ምንጫችን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ነው
1 411
በወተት ጥራት እና- ደህንነት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ከእንሰሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ፕሮጀክት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣንና ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ለአርባ የኮሜርሽያል ወተት አምራች ድርጅቶች በአዳማ ከተማ ሂል ሳይድ ሆቴል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
የስልጠና መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ሲሆኑ እሳቸውም የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ ደህንነቱና ጥራቱ የተጠበቀ ወተት ለተጠቃሚው ህብረተሰብ እንዲቀርብ ማድረግ ነው ብለዋል፡፡ አያይዘውም እዚህ የተገኛችሁ ባለሙያዎች ስለ ወተት ጤና አጠባበቅ ግንዛቤው ያላችሁ ቢሆንም ወተት ተጠቃሚውን ህብረተሰብ ከወተት ወለድ በሽታ ለመከላከል ያላችሁ ሚና የጎላ በመሆኑ ይህን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከወሰዳችሁ በኋላ የወተቱን ጥራትና ደህንነቱን በማሰጠበቅ በኩል የበኩላችሁን ድርሻ እንደምትወጡ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል፡፡
በመቀጠልም የወተት ደህንነትና ጥራት አጠባበቅ፤የወተት ደህንነትና ጥራት ተግዳሮቶች፤ Milk product Issue፣ እና Milk quality and Safety በሚሉ ርዕሶች ላይ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንሰቲትዩት እና ከኢትዮጵያ ምግብ እና መድሀኒት ባለስልጣን በመጡ ባለሙያዎች አማካኝነት ገለፃዎች ቀርበዋል፡፡
የቀረቡ ገለፃዎችን መሰረት በማድረግ ከተሳታፊዎች ከአርቢውና ከአሰባሳቢው፤ ከድጋፍ ሰጪ እና ከተቆጣጣሪ አካላት ምን ይጠበቃል፣ በሚሉ ነጥቦች ላይ ከቤቱ የተለያዩ ገንቢ ሃሳቦች የተሰጡ ሲሆን የወተት ላሞች መኖ በጥራትና በሚፈለገው መጠን አለመገኘትና በጣም ውድ መሆን፣የወተት ማለቢያ፣ ማጠራቀሚያና ማጓጓዣ ዕቃዎች ውድ መሆን፣ የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ ማነስ፣ በተለይም ከብድር አቅርቦትና ከመስሪያ ቦታ ጋር ተያይዞ፣ የወተት አምራቾች ማህበራት ውስን መሆንና አለመጠናከር፣ ተከታታይነት ባለው ሁኔታ ሥልጠና አለመሰጠት፣ የተቆጣጣሪ አካላት የቁጥጥር ማነስ እነደ ችግር ተነስተዋል፡፡
በመጨረሻም የውይይት መድረኩን የመሩት የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእንስሳት ምርት ሬጉላቶሬ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አያሌው ሹመት የወተት ደህንነትንና ጥራትን ለማስጠበቅ ከወተት ላም አርቢው ጀምሮ አስከ ማቀነባበሪያ ፋብሪካው ድረስ ብዙ ችግሮች እንዳሉ አንስተው ድንገተኛ የቁጥጥር ስራ ማካሄድ፤የወተት ላሞችን አያያዝና እንክብካቤ ማድረግ፤የተለያዩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ማስገባትና ማላመድ፤ጠንካራ ማህበራትን ማጎልበትና ማጠናከር፣ ችግር ፈቺ ምርምር በማካሄድ በመረጃ ላይ ተመስርቶ ያለውን ችግር መቅረፍ፣ ተቆጣጣሪ አካላት በወተት አካባቢ ያወጡትን መስፈርቶችና ግዴታዎች ለአርቢዎችና ለአሰባሳቢዎች ማሳወቅ፣ የመስፈርት ሟሟላት ስራዎችን በመደገፍ አብሮ ለማሟላት መስራት፣ ከእያንዳንዳችን የሚጠበቅ ተግባር ስለሆነ ሁላችንም የሚመለከተንን ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ በሰፊው አብራርተው የተነሱ ችግሮችን ለመቅረፍም ሁላችንም በጋራ ተቀናጅተን መስራት እነደሚያስፈልግ አንስተውና የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መድረኩ ተጠናቋል፡፡
