የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን
Ir al canal en Telegram
ይህ ሥለኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ትክክለኛ መረጃ የሚያገኙበት የባለሥልጣኑ የቴሌግራም አካውንት ነው።
Mostrar más1 411
Suscriptores
+224 horas
+257 días
+8530 días
Archivo de publicaciones
1 411
መሠረታዊ የመድኃኒቶች መዘርዝር መዘጋጀቱ የእንስሳት ጤናን ለማሻሻል ይረዳል
አዲስ አበባ፡– መሠረታዊ የእንስሳት መድኃኒቶች መዘርዝር መዘጋጀቱ አጠቃላይ የእንስሳት ጤና ዘርፍን ለማሻሻል እንደሚረዳ የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ገለጹ፡፡
ባለስልጣኑ ብሩክ ኢትዮጵያ ከተባለ መንግሥታዊ ካልሆነ ድርጅትና ከኢትዮጵያ እንስሳት ሐኪሞች ማኅበር ጋር በመተባበር አስፈላጊ የሆኑ የእንስሳት መድኃኒት መዘርዝርን በትናንትናው ዕለት ይፋ አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በወቅቱ እንደገለጹት፤ መሠረታዊ የእንስሳት መድኃኒቶች መዘርዝር መዘጋጀቱ መንግሥት አጠቃላይ ለእንስሳት ጤና ዘርፍ መሻሻል ካስቀመጠው ፖሊሲ አኳያ ውጤታማ ሥራ ለመሥራት የጎላ ሚና ይኖረዋል፡፡
የመድኃኒት መዘርዝሩ ለስድስት የእንስሳት ዝርያዎች የሚውል አስፈላጊ የመድኃኒት መዘርዝር መሆኑን ጠቅሰው፤ በእንስሳት ላይ የሚያጋጥሙ በሽታዎችን በነባሩ መድኃኒት መከላከል ባይቻል ተጨማሪ ጥናት ሳያስፈልግ በተዘጋጀው መዘርዝር መሠረት መድኃኒት ከውጭ ማስገባት ወይም በሀገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በሀገር አቀፍ ደረጃ አስፈላጊ የሆኑ የእንስሳት መድኃኒት መዘርዝር ባለመኖሩ ዘርፉ በከፍተኛ ደረጃ መፈተኑን ገልጸው፤ በቀጣይ በተዘጋጀው የመድኃኒት መዘርዝር መሠረት የእንስሳት በሽታን በቀላሉ መከላከል እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡
ባለሥልጣኑ የእንስሳትና የግብርና ምርት ጥራትን ለማስጠበቅ በትኩረት እየሠራ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደር ድሪባ፤ የመድኃኒት መዘርዝሩ ለቀንድ ከብቶች፣ ለበግና ፍየል፣ ለአህያ፣ ለፈረስ፣ ለዶሮ፣ ለግመል፣ ለድመትና ውሻ የሚያገለግል ነው ብለዋል፡፡
የነበረው የእንስሳት መድኃኒት አቅርቦትና የጥራት ደረጃ አነስተኛ በመሆኑ የተዘጋጀው የመድኃኒት መዘርዝር አቅርቦቱን በማሻሻል የተለያየ የእንስሳት መድኃኒት አማራጮች እንዲኖሩ በማድረግ በኩል ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ አመልክተዋል፡፡
በመድኃኒት መዘርዝር ዝግጅቱ የእንግሊዝ መንግሥት፣ የተለያዩ አጋር አካላትና ከስድስት ዩኒቨርስቲዎች በተውጣጡ መምህራን ተጠንቶና ተገምግሞ ተግባራዊ እንዲሆን በግብርና ሚኒስቴር እንዲፀድቅ መደረጉን አምባሳደር ድሪባ አስረድተዋል፡፡
መንግሥት ከውጭ የሚገቡ የእንስሳት መድኃኒቶችን በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ አቅጣጫ ማስቀመጡን አውስተው፤ ለተግባራዊነቱ ባለሥልጣኑ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ ነው ብለዋል፡፡
የብሩክ ኢትዮጵያ ተጠሪ አቶ ዮሐንስ ቃሲም በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ መሠረታዊ የሆነ የእንስሳት መድኃኒቶችና ክትባቶች በበቂ ሁኔታ አለመኖር የእንስሳትን ደኅንነት ለማሻሻል የሚያስችል የእንስሳት ጤና አገልግሎት ግንባታ ላይ ተግዳሮት ሆኖ ቆይቷል ብለዋል።
ኅብረተሰቡ የእንስሳት መድኃኒትን በአግባቡ እንዲጠቀም የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡ የእንስሳት መድኃኒት አስመጭዎች ትርፍን ብቻ መሠረት አድርገውና ለኅብረተሰቡ ከሚሰጠው ጠቀሜታ አንፃር መዝነው ባለመሥራታቸው ዘርፉ በሚፈለገው ልክ ውጤታማ ሳይሆን ቀርቷል ብለዋል።
በቀጣይ የክልል ግብርና ቢሮዎች የእንስሳት መድኃኒት ግዥ ሥርዓታቸውን እንዲያሻሽሉና አስፈላጊ የሆኑ መድኃኒት ግዥ እንዲፈፅሙ የመድኃኒት መዘርዝሩ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።
አስፈላጊ የእንስሳት መድኃኒቶች በገበያ ላይ የሚገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸትና የተሻለ የእንስሳት በሽታን የመመርመር አቅም እንዲሻሻል ድርጅቱ የተለያዩ ሥራዎችን በአጋርነት እንደሚሠራም ጠቁመዋል፡፡
አማን ረሺድ
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 16/2016 ዓ.ም
1 411
የምግብና ስርዓተ-ምግብ ዋስትና መጓደል ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችሉ አሰራሮችን በቅንጅት መተግበር ያስፈልጋል
/አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2016 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር/
ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ብልፅግና አካላዊ እና አእምሮአዊ እድገቱ የተረጋገጠ እና ምርታማ የሆነ ትውልድ መፍጠር ወሳኝ ሚና አለው፡፡ የግብርና ሚኒስቴር የግብርና ምርትና ምርታማነት በመጨመርና በምግብ ራስን ለመቻል ከሚደረገው ጎን ለጎን የምግብና ስርዓተ ምግብ ዋስትና መጓደል ችግርን ለመቅረፍ የምግብ እና የስርዓተ-ምግብ መርሃ-ግብር ቀርጾ በመተግበር ላይ ይገኛል።
የምግብ ብክነትን ከመቀነስና ጥራትንና ደህንነትን ከማስጠበቅ አንጻር ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ አሁንም ሰፊ ስራ እየተሰራ ሲሆን የግብርና ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው የክልል ግብርና ቢሮዎችና አጋር አካላት ጋር በመተባበር የድህረ ምርት አያያዝን ማሻሻል፣ የምግብ ጥራትና ደህንነትን ማረጋገጥ እና ከምግብ ስርዓቱ ጋር የበለጠ የተቃኘ እንዲሆን የሚያስችሉ ሶስት ስትራቴጂዎች ተቀርፀው ተግባራዊ እንዲደረጉ ይፋ አድርጓል፡፡
ስትራቴጂዎችን ይፋ ያደረጉት የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) በግብርናው ዘርፍ በምግብ ንጥረ ነገር የበለፀገ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ የተሰባጠረና በቂ የምግብ አቅርቦት፣ ተደራሽነትና ተጠቃሚነትን ለማሻሻል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ተናግረው ይፋ የሆኑት ስትራቴጂዎች አገሪቱ ለምግብ፣ ስርዓተ-ምግብ ደህንነትና ለምግብ ሉዓላዊነት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
እነዚህ ስትራቴጂዎች የምግብ ደህንነትን ለማረጋገጥ፣ ጤናን ለማሳደግና ኢኮኖሚያዊ ደህንነትን ለማሻሻል ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ሚንስትሩ ገልጸው ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጃቸው ስትራቴጂዎች የምግብና የስርዓተ-ምግብ ደህንነትን ለማሳካት ለሚደረገው ጥረት እጅግ ጠቃሚዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ስትራቴጂዎቹ ከኢትዮጵያ አገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ የምግብ ስርዓት ሽግግር መንገድ፣ ከምግብና ስርዓተ-ምግብ ፖሊሲ እንዲሁም ከ10 አመቱ የልማት እቅድ ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
በሚኒስቴሩ የምግብና ስርዓተ ምግብ ጽ/ቤት ኃላፊ ዓለምፀሐይ ሥርጋዊ በበኩላቸው ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ የሚመረቱ ምርቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ብክነትን የቀነሱና በምግብ ንጥረ ነገር የበለፀጉ ሆነው ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ የሚያስችሉ ስትራቴጂዎች መሆናቸውንና ለተግባራዊነታቸው ባለድርሻ አካላትና ሚዲያው የራሱን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
ይፋ የተደረጉት ስትራቴጂዎች ብሔራዊ የምግብ ደህንነትና ጥራት ለተቀዳሚ የግብርና ምርቶች፣ ብሔራዊ የድህረ ምርት አያያዝ እንዲሁም ስርዓተ ምግብ ተኮር የምግብ ስርዓት ሲሆኑ ስትራቴጂዎች የኢትጵያ የምግብ ስርዓት ሽግግርን ለማሳለጥ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ በመንገንዘብ ለተግባራዊነታቸው በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንደሚወጡ በውይይቱ ተነስቷል።
ስትራቴጂው በክልሎች በየደረጃው ተግባራዊ እንዲሆን ክልሎች የትግበራ ፊርማቸውን በማስቀመጥ ከግብርና ሚኒስትሩ ሰነዱን ተቀብለዋል፡፡ የልማት አጋሮችም በትግበራ ሰነዱ ላይ የአጋርነት ፊርማቸውን አስቀምጠዋል፡፡
የካሜራ ባለሙያ :-ዮዲት እንዳለው
ዘጋቢ:- ተዋበ ጫኔ
1 411
የብሔራዊ ዝርያ አፅዳቂ ኮሚቴ የመጀመሪያ ዙር ስብሰባ ተጠናቀቀ
በኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን የእፅዋት ዝርያና ዘር መሪ ስራ አስፈፃሚ አስተባባሪነት ከመጋቢት 26/20016 ዓ.ም ጀምሮ ቢሾፍቱ ከተማ ለ3,ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው ስብሰባ ተጠናቀቀ
አቶ ፍስሐ ተሾመ በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የዝርያና ዘር ሪጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈጻሚና የብሔራዊ ዝርያ አጽዳቂ ቋሚ ኮሚቴ ፀሀፊ ለ2015/16 ምርት ዘመን በመስክ ለተገመገሙ 144 ዕጩ የዕጽዋት ዝርያዎች ውሳኔ በሚሰጥበት የመጀመሪያ ዙር ስብሰባ ለመጡ ተሰብሳቢዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ ፕሮግራሙን ለተሰብሳቢዎቹ አቅርበው የዕለቱ የክብር እንግዳ በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእፅዋት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬተክተር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ የመክፈቻ ንግግር እንዲያደርጉ ጋብዘዋል፡፡አቶ ወንዳለም፤ የተሸሻሉ ምርጥ ዘርን በመጠቀም እስከ 30 በመቶ ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚቻል ጥናቶች እንደሚናገሩ ገልጸው ከዚህ ጋር በተገናኘ ለአርሶ አደሩ በሚጠቅም ደረጃ ውሳኔ በሚተላለፍበት ጉዳይ ላይ መገኘታቸው ትልቅ ከብር ያለው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡አክለውም በአሁኑ ሰዓት የዘር ተፈላጊነት በመጨመሩ በመስክ የተገመገሙ ዕጩ ዝርያዎች ቶሎ ውሳኔ ተሰጥቷቸው ወደ ዘር ስርዓቱ እንዲገቡ በማስፈለጉ ዘንደሮ መድረኩ ወደፊት ተስቦ የተዘጋጀ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡ በመቀጠልም የዝርያ አጽዳቂ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም በየአካባቢው የጸጥታ ችግር ሳይበግራቸው በመስክ የገመገሙ የቴክኒካል ኮሚቴ አባላትን ለስራው መቃናት የበኩላቸውን አስተዋጽዎ ለበረከቱት ሁሉ በራሳቸውና በባለሥልጣኑ ስም አመስግነው ውጤታማ የውይይት ጊዜ እንዲሆን በመመኘት ስብሰባውን በይፋ መከፈቱን በማብሰር ቆይታቸው የተሳካ እንዲሆን በመመኘት ወደፊትም ለስራው መቃናት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸው መድረኩን ለብሔራዊ ዝርያ አጽዳቂ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሰጥተዋል፡፡ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢና የሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ፕ/ር ፍሬው መክብብ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ከተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት አንዱ ዕጩ የዕጽዋት ዝርያዎችን ብቃት በመረጃና በመስክ እንዲገመገሙ በማድረግ በብሔራዊ የዝርያ አጽዳቂ ኮሚቴ ውሳኔ እንዲያገኙ እና ዝቅተኛውን መስፈርት አሟልተው ተቀባይነት ያገኙ ዝርያዎችን በዝርያ መዝገብ እንዲካተቱ ማድረግ መሆኑን ገልጸው በዝርያና ዘር መሪ ስራ አሰፈጻሚ አሰተባባባሪት ይህን ትልቅ ሥራ በጥቂት ባለሙያዎች በመስክ እንዲገመገሙ በማስድረግ መረጀዎችን በማጠናከርና ለውሳኔ በሚያመች መልክ ለዚህ ማብቃታቸውን አመስግነዋል፡፡ አያይዘውም የመድረኩን አካሄድ በዝርዝር በመግለጽ ከተለያዩ የፌደራልና የክልል የምርምር ተቋማት፣ ከዩኒቨርሲቲ፣ ከግል ካምፓኒዎች ከውጪ እና ከሀገር ውስጥ የቀረቡ ዕጩ የዕጽዋት ዝርያዎች ላይ ውሳኔ ለማሰጠት በቀረበው ፕሮግራም መሰረት በየሰብሉ ግምገማውን የመሩ እያንዳንዱ የቴክኒክ ኮሚቴ ቡድን መሪዎች ሪፖርት እንዲያቀርቡ ጋብዘዋል፡፡አቅራቢ መስሪያ ቤቶችም ስላቀረቡት ዝርያ ለሚጠየቁት ተጨማሪ ማብራሪያ ተገቢ ምላሽ እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡ በመጨረሻም ለውሳኔ ከቀረቡት 144 ዕጩ ዝርያዎች ውስጥ 75 ዝርያዎች ተቀባይነት ያገኙና በዝርያ መዝገብ እንዲካተቱ፣ 4 ዝርያዎች በተሰጠው አስተያየት መሰረት እንዲደገሙ፣ 65 ዝርያዎች ተቀባይነት ባለማግኘታቸው ውድቅ እንዲሆኑ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ጉባኤው ተጠናቋል፡፡
1 411
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደርሳችሁ!
በዓሉ የጤናና የደስታ እንድሆንላችሁ እንመኛለን::
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ
ዌብሳይት http:www.eaa.gov.et
ፌስቡክ: የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን /Ethiop http://www.eaa.gov.et
ቴሌግራም: eaa_123
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን
