cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ተዋህዶ ተነሺ ቲዩብ

ይህ ቻናል የዘማሪ ዲ ብርቅነህ ጎረምስ የቴሌግራም ቻናል ነው ፡፡ በዚህ ቻናል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ያሬዳዊ ዝማሬዎች ስብከቶች ስነፅሁፍ ወረብ እንዲሁም ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ታሪኮች መንፈሳዊ አገልግሎት ይሰጥበታል፡፡ JOIN Share አድርጉ

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
313
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
እመቤቴ ኪዳነ ምሕረት ሆይ! የሰማያዊ መንግሥት መገኛ መድኅን ነሽና ለአንቺ ሰላምታ ይገባል። ድንግል ሆይ! አንቺን የሚወድ ፍጹም ዋጋውን ለማግኘት ትንሣኤ ዘጉባኤ እስኪሆን ድረስ በተስፋ ይኖራልና ሰላምታ ይገባሻል፡፡ እመቤቴ ኪዳነ ምሕረት ሆይ! እንደ ቃል ኪዳንሽ ምስጋናሽ የሚነገርበትን ቤተ ክርስቲያን በስምሽ ያሳነጸውን መታሰቢያሽን ያደረገውን በስምሽ የጸለየውን ከበረከትሽ ታሳትፊውና ይቅር ባይ ከሚሆን ልጅሽ ይቅርታን ታሰጪው ዘንድ ሰላም እያልሁ ከፊትሽ ወድቄ በቃል ኪዳንሽ እማጸንሻለሁ፡፡ እመቤታችን ማርያም ሆይ! ወንዶችና ሴቶች ባሮችሽን በክፉ ሰዎች እጅ ከመውደቅ በቃል ኪዳንሽ ጠብቂን። በልዩ ጠላት በዲያብሎስ ወይም በሰይጣን ኃይል ተይዞ ከመቀጥቀጥ በእግረ አጋንንት ከመረገጥና ከመጠቅጠቅ አድኚን ለዘለዓለሙ፡፡ መልክዐ ኪደነምሕረት ።
Mostrar todo...
📍ጸሎታችን ለምን አይመለስም🤔? #2 ስለዚህ ጥያቄው ሳይመለስ በቆየ ቁጥር እንዲመልስልኝ እያለ እግዚአብሔርን ለመዘብዘብ ቤተክርስቲያን ሲመላለስ በዚያው የቤተክርስቲያን ሰው ሆኖ እንዲቀር ማለት ነው። ➟ ከቤቱ እንዳንወጣበት ጥያቄችንን ያዘገየዋል እግዚአብሔር የትኛውን ነገር መቼ ቢያደርገው አሳምሮ ያውቅበታል። ከእርሱጋር እንድንጣበቅ ከእርሱ እንዳንለይ ጥያቄውን ያዘገየዋል። ❸ኛ ደግሞ ➟ በጸለይነው ጸሎት "የማናውቀው መከራ" ተመልሶልናል።. ➟ ይሄኛው ደግሞ በጣም አስደናቂ ነው እግዚአብሔር ሁልጊዜ ለእኛ እያሳወቀ የሚሰራ ይመስላችኋል? ስንት ሰወች ሊገድሉን ተዘጋጅተው ለእኛ ሳይነግሩን ልቦናቸውን ምክራቸውን ሽሮ እንዳስቀረን የሚያውቅ እርሱ ብቻ ነው። ➟ ስንት ሰወች ሊያጠፉን ሊከሱን ተዘጋጅተው እንደገና ደግሞ አይይ ልተወው መሰል ብለው እንዲቀሩ ልቦናቸውን አራርቶ ለእኛ ሳያሳውቀን ያስቀረው ምክር ብዙ አለ። ➟ እግዚአብሔር ያንን ጥያቄ እኛ በጠበቅነው ስንፈልግ እግዚአብሔር ያልጠበቅናቸውን ብዙ መአቶች በጸሎት አስቀርቶልናል። ➟የማንኛውንም ሰው ጸሎት ጥያቄ ሳይመልስ ቀርቶ አያውቅም። ይሄንን አውቀን ከጸለይን ጸሎታችን መልስ ያገኛል "ስትጸልዩ እንደግብዞች አትሁኑ" (ማቴ 6፥5) {➛ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ ➛በርእሰ አድባራት ወገዳማት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም የ፬ቱ ጉባኤያት መምህር።}
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
🔷🔶🔷🔶🔷🔶🔷🔶🔷🔶 ጸሎታችን ለምን አይመለስም🤔? 🔶🔷🔶🔷🔶🔷🔶🔷🔶🔷 የሚል ጥያቄ ያስነሳል ሰይጣን ማለት ነው። ስለዚህ ጸሎቱን ለምንድን ነው የማይመልስልን ሲባል ሶስት አጭር ነገሮችን ብቻ ልንገራችሁ። ❶ኛው ምክንያት ➟ "ጸሎቱ የማይጠቅመን ከሆነ" ነው ለምሳሌ አንድ ነገር ልንገራችሁ፦ ➟ ህጻን ልጅ እናቱ እንጀራ እየጋገረች እያለ ክፉና በጎ ያልለየ ልጅ እናቱን እሳት እንድትሰጠው ይለምናታል መስጠት አለባት የለባትም? የለባትም። በልጁ አእምሮ ግን መጠየቁ ትክክል ነው አይደለም? ትክክል ነው። ምክንያቱም በምናውቀው አለም ሳትሰጠው ስትቀር ያለቅሳል። የሚጠቅመውን የምታውቅ ግን እናቱ ናት። ➟ ቅዱስ ያሬድ እንደተናገረ ❤"እግዚአብሔር አባታችንም እናታችንም ነው" "አንተ አቡነ ወአንተ እምነ" እንዳለ 🖌 እግዚአብሔር አባት ነው። 🖌 እግዚአብሔር እናት ነው። የሚያስብልን እሱ ነው። እሱ ስለሚያስብልን የለመንነውን ሁሉ አይሰጠንም ለምን?እንደማይጠቅመን ያውቃልና ። ➟ ስለዚህ ጥያቄያችንን ያልመለሰልን ስላልወደደን፣ ሃጢአተኛ ስለሆንን፣ ጸሎታችን ትክክልስላልሆነ ሳይሆን የማይጠቅመንን ስለለመንን ይሆናል። ከቃሉ ጋር ናችሁ? እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን። ❷ኛ "ተላጽቆተ ስኢን" ማለት "በጸሎት አንድ መሆን ወይም በጸሎት መዋሀድ" ➟ ለምሳሌ፦ ውሻ ስጋ ሲያይ ስጋውን ከወረወርንለት ስጋው እስከሚያልቅ ድረስ አይመጣም። ዝም ካልነው ግን ይመጣል። ተመልሶ ካልሰጠነው ግን የመላለሳል። ➟ ሰው እንደ ውሻ እንዳይሆን ሰው አንድ ጥያቄ ይጠይቃል እግዚአብሔር ይመልስለታል ከዚያ በኋላ ካልቸገረው ቤተክርስቲያን ተመልሶ አይመጣም። አንድ ጥያቄ ይጠይቃል ይመልስለታል ተመልሶ አይመጣም። ስለዚህ ጥያቄው ሳይመለስ በቆየ ቁጥር.... #2 👇👇👇👇👇👇
Mostrar todo...
+ ተማሪዎች ከፈተና በፊት ምን ብለው ይጸልዩ? https://t.me/yetewahedofera ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ ከሚታወቁባቸው በርካታ በጎ ነገሮች አንዱ ለተማሪዎች የነበራቸው ልዩ ፍቅርና ቅርበት ነበረ፡፡ አባ ሚናስ ተብለው ይጠሩ ከነበረበት የምንኩስናቸው ዘመን ጀምሮ አቡኑ በተማሪዎች የተከበቡ ነበሩ፡፡ ከልዩ ልዩ ክፍለ ሀገራት ካይሮ ዩኒቨርሲቲ ሊማሩ ለሚመጡ ተማሪዎች የማደሪያ አገልግሎት በቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰጡ ነበር፡፡ ይህ አገልግሎታቸውም በግብፅ ለዘመናዊው ቤተ ክርስቲያንን የሚያካትት የማደሪያ አገልግሎት(church- affiliated dormitory) መወለድ ምክንያት ሆኗል፡፡ የዚህ የማደሪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የነበሩ ተማሪዎችም ቀሳውስትና ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡(ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤልና ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊተጠቃሽ ናቸው፡፡) በወቅቱ መነኩሴ የነበሩት አባ ሚናስ (አቡነ ቄርሎስ) ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያኑ ካህን በተማሪዎቹ መኖሪያ ውስጥ የሥራ ድርሻ ሰጥተው ነበር፡፡ የእርሳቸውን የሥራ ድርሻ ምን እንደነበረ ግን ማንም ሰው አላወቀም ነበር፡፡ በሌሊት በድብቅ የሚሠሩት ሥራ ካህናቱና በቤተ ክርስቲያኑ የሚኖሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን መጸዳጃ ቤት ማጽዳት ነበር፡፡ https://t.me/yetewahedofera ይህ ለተማሪዎች ያላቸው በጎ አመለካከት በፓትርያርክነት ዘመናቸው አልተለያቸውም፡፡ ተማሪዎች ፈተና ሲደርስባቸው ወደ እርሳቸው እየመጡ ጸልዩልን ይሉአቸው ነበር፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ የሚያጠኑበትን መጽሐፍ ይዘው መጥተው ያስባርኩ ነበር፡፡ ቅዱስ አባ ቄርሎስ አንዳንዴ መጽሐፉን ገለጥ ያደርጉና ‹ይህንን አጥኑ› ብለው ይሠጡ ነበር፡፡ የፈተናውም አብዛኛው ጥያቄ ከዚያ ገጽ ይወጣ ነበር፡፡ እንዲሁም ለተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ የሚገጥማቸውን የመንፈስ ጭንቀትና የአእምሮ ውጥረት በመረዳት የሚከተለውን ከፈተና በፊት የሚጸለይ ጸሎት አዘጋጅተውላቸዋል፡፡ https://t.me/yetewahedofera + ጸሎት + ‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ! አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡ ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡ ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡  ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!" ታሪክ በማይረሳው የተወሳሰበ የትምህርት ዘመን አልፋችሁ ለምትፈተኑ ለዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን! የልባችሁን ዓይን ያብራላችሁ! ያጠናችሁትን ይባርክላችሁ የተማራችሁትን ያስታውሳችሁ! ባለቀ ሰዓት የሚደረግ ጥናት ከጭንቀት ውጪ ምንም አያተርፍምና ራሳችሁን በጸሎት አረጋግታችሁ ተፈተኑ:: 👇👇👇 ቻናሉን ይቀላቀላሉ 💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚 💛 @yetewahedofera 🟡 💛 @yetewahedofera 🟡 💛 @yetewahedofera 🟡 ❤❤❤❤❤❤❤❤❤ ለ12ኛ ክፍል 🧑‍🎓 ተማሪዎች ሼር አድርጉላቸው!! መልካም የዝግጅት ጊዜ መልካም ውጤት ለጥያቄ 👇👇👇👇👇👇 @Teyaka_Lemtykebot ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ 2015 ዓ.ም
Mostrar todo...
የተዋሕዶ ፍሬዎች

🎯 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን:: 👉 መዝሙር 👉ብሒለ አበው 👉ስብከት 🎯የሚለቀቅበት ቻናል ነው ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ ::

https://t.me/yetewahedofera

ለአስተያየት 👉 @Teyaka_Lemtykebot

Photo unavailableShow in Telegram
🕊   🕯🕯🕯    💖    🕯🕯🕯   🕊 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡ 🕊 "የተጨነቀውን የተጨቆነውን ነፃ የምታወጣው ሚካኤል ሆይ ፦ ሰላም ላንተ ይሁን ፡ ሠራተኛው ሠርቶ እንዲበላ ውሎ እንዲገባ የምትጠብቀው ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን፡፡ ችግረኛውን ለመርዳት ከልዑል ዘንድ የምትላክ ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። አዳኝነትህን በማመን የለመነህን በክንፈ ረድኤትህ የምትሠውረው ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን፡፡ በኀዘን በትካዜ ላይ ወድቆ የሚፍገመገመውን የሚንፈራገጠውን ፈጥነህ ደርሰህ ደግፈህ የምታጽናናው ሚካኤል ሆይ ፤ አንገትህን ዘንበል ቀለስ አድርገህ በፈጣሪ ፊት ሰግደህ እኛ ባሮቹን በቸርነቱ ይጎበኘን ዘንድ የማናዊት እጁን ዘርግቶ ይባርከን ዘንድ ለምን አማልድ ለዘላለሙ አሜን፡፡" [ መልክአ ሚካኤል ] 🕊  🕯🕯🕯    💖    🕯🕯🕯   🕊
Mostrar todo...
ቅደም በመንገዴ ቅዱስ ሚካኤል ቅደም በመንገዴ ምልጃ ፀሎትህን አምናለሁ በልቤ የተሰጠህ ኪዳን ከሰራዊት ጌታ ለሰው ልጆች ሁሉ ያሰጣል ይቅርታ ዘንዶውን ተዋግተህ በድል ያሸነፍከው ኃያሉ ሚካኤል ክብርህ ገናና ነው የአፎምያ እረዳት ደግሞም የባህራን እረዳታቸው ነህ ለብዙ ቅዱሳን (፪) ነብዩ ዳንኤል እንዳይቀር በመንገድ በክንፎችህ ወጣ ከአናብስቱ ጉድጓድ የእግዚአብሔር ኃይል በእንተ ይገለጣል ከሞት የተረፈ ሚካኤል ይልሃል(፪) የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነህ በተሰጠህ ስልጣን ሰላም ታሰጣለህ ከመቅደስህ ገብቶ ስምህን ለጠራ እንባው ታብሶለት ድኗል ከመከራ(፪) እኔም በደለኛው ሚካኤል እላለሁ ምልጃህን አምኜ አማልደኝ እላለሁ አንደበቴን ባርከው በዜማ በቅኔ አምላኬን ላገልግል በእድሜ በዘመኔ(፪) ዘ/ዲ ብርቅነህ 2013 ዓ.ም ህዳር 12 እልልልልልልልልልልልልል እረ በእጃችሁ እስኪ አብረን እዘምር ሁላችሁም ሼር በማድረግ ላልደረሳቸው ያዳርሱ ለቻናሉ አዲስ የሆናችሁ ይቀላቀሉን 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 t.me/TewahdoTeneshiTube
Mostrar todo...
ቅዱስ_ሚካኤል_በዘማሪ_ዲ_ብርቅነህ_ጎረምስ.mp35.30 MB
Photo unavailableShow in Telegram
መልዓከ ሰላምነ ቅዱስ ሚካኤል ሰዓል ወጸሊ በእንቲአነ አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለእግዚእነ
Mostrar todo...
9.40 KB
Photo unavailableShow in Telegram
✝️እንኳን ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓል አደረሰን:: ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ (ት-ዳ÷10
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.