cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ፍልስፍና እና ወግ

እዚ ቻናል ፍልስፍና ወግ እና አጫጭር ታሪኮች ይለቀቁበታል፡፡

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
181
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የተለየው(እብድ) ያ...ያ ከዚያ ማዶ እሚታየው ቡትት የመሰለ አዳፋ የለበሰው ይሄ ጎዳናው ላይ ሸራ የወጠረው ይታይሽ ከሆነ ሰው ሲሞት ሚስቀው አይተሽው ከሆነ ሰው ሲስቅ ሚያለቅሰው ጥያቄ ጠይቆ መልስ እማይጠብቀው እውነት እማይመስል እውነት የሚያወራው ሁሉም የተወውን ዝቅ ብሎ ሚያነሳው ሁሉ የፈራውን እሱ የሚደፍረው ተጠግቶ የፈሩትን እውነት ሲነግራቸው ያ...እኮ እብድ ነው እያሉ ይሮጣሉ የውሸት ስም ለጥፈው ያ እንኳን አታውቂውም ፈላስፋው ሌላው የሸሸውን እውነት ሚናገረው ነገሩ አንቺም እብድ ነው እምትይው አልገባሽ አለ እንጂ የምነግርሽ ስለሱ ነው እብድ የሚባል እውነተኛ ሰው https://t.me/joinchat/Ux0uuUTU-VKz9aXJ join us
Mostrar todo...
🇪🇹አሮዲዮን🎑🇪🇹®️

🇪🇹 @Arodyon 🇪🇹🎑 የናንተው ምርጥ ቻነል👇👇 #በዚህ_የመዝናኛ_ቻናላኝን_ውስጥ ✓መሳጭ ታሪኮችን ✓ልቦለዶችን ✓ሌሎች መፅሀፍቶችን(pdf) ✓አስደናቂ ና አስቂ እውነታዎች👌 ✓quotes,meme& wallpapers👌 ✓New Musics (kb) እንለቅላቿለን🎁። #ለሚወዱት_ሁሉ_share_ያድርጉ Cross👉 @Sol_the_great ለሀሳብ @temerach_comment_bot

በጣም አስተማሪ ታሪክ ይነበብ ♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️ አንድ በሥራው ታታሪ የሆነ ዓሳ አጥማጅ ነበር።ይህ አጥማጅ በየቀኑ ዓሳ ያጠምድና አስከሚያልቅ ድረስ ይጠቀማል። ልክ ሲያልቅ ወደ ባህር ዳርቻ በመሄድ ሌላ ያጠምዳል። ከእለታት አንድ ቀን የዓሳ አጥማጁ ሚስት ባሏ ያመጣላትን ዓሳ በመቆራረጥ ላይ ሳለች አሰገራሚ ነገር ታያለች። ይህች ሰው የተመለከተችው እጅግ የከበረ ሉል ነው ። በጣም እየተገረመች በዓሳ ሆድ ውስጥ ሉል ...? አያለች ባሌ... ባሌ... ባሌ... እያለች ባሏን መጥራት ጀመረች ከዚያም "ምን እንዳገኘሁ ተመልከት ሉል እኮ ነው!! ሉል ... ከዓሳው ሆድ ውስጥ " አለችው ። እሱም " እንዴት አሰደሳች ሚስት ነሽ እስኪ አቅርቢው ለዛሬ ለቤት ቀለባችን መግዣ ትሆነናለች ..... ከዓሳ ሌላ ምግብ እንበላለን!!" አላት..... ይህ ዓሳ አጥማጅ ሉሉን በመያዝ ወደ ሉል ገዢና ሻጭ በመሄድ ያሳየዋል። ገዢውም "እኔ ይህንን ሉል የመግዛት አቅሙ የለኝም፤ ዋጋው ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ይህንን ሱቄንና መኖሪያ ቤቴን ብሸጠው እንኳን ልገዛህ አልችልም። ይልቁንስ እከሌ የሚባል ሀብታም ነጋዴ አለ እርሱ ሊገዛህ ይችላልና ወደርሱ ሂድ። አለው ። ዓሳ አጥማጁ ሉሉን በመያዝ ወደ ተባለው ሀብታም ሰው በመሄድ ጉዳዩን ነገረው። ይህ ታላቅ ነጋዴም "እኔ አልችልም ይህ የያዝከው ሉል በገንዘብ የሚተመን አይደለምና እኔ መፍትሔ ብዬ የማስበው ወደ ከተማው አስተዳዳሪ ሄደህ ብታሳየው ነው እንደዚህ አይነት ውድ ሉል ከርሱ ውጭ የመግዛት አቅም አለው ብዬ የማስበው ሰው የለም " አለው። ጉዞውን ወደ ተባለው አስተዳዳሪ በማድረግ ቤቱ እንደደረሰ ወደ ህንፃው ለመግባት ፈቃድ እስኪያገኝ ድረስ መጠበቅ ጀመረ። (እንደገባም) ለአስተዳዳሪው የያዘውን ሉል ሲያሳየው አጅግ ተገረመ። "እንደዚህ አይነት ሉል ስፈልገው የነበረ ነው… እንዴት ተመኑን እንደምከፍልህ አላውቅም… ነገር ግን ለየት ወዳለው ካዝናዬ እንድትገባ እፈቅድልሃለሁ። እዛ ውስጥም ለስድስት ሰዓታት በመቆየት የቻልከውንና የፈለከውን ንብረት ተሸክመህ መውጣት ትችላለህ። ይህ እንግዲህ የሉልህ ክፍያ ነው።" በማለት ወደ ካዝናው እንዲገባ ጋበዘው። ዓሳ አጥማጁም "አለቃዬ ሆይ! ስድስት ሰዓት…!! እንደኔ ላለ ዓሳ አጥማጅ በጣም ብዙ ነው እንደው ሁለት ሰዓት ብታደርግልኝ " ሲል ጠየቀው። አስተዳዳሪውም "በጭራሽ አይሆንም ስድስት ሰዓት ሙሉ ከካዝናዬ የፈለከውንና የምትችለውን ያህል ይዘህ መውጣት አለብህ " አለው። ዓሳ አጥማጁ ወደ ካዝናው ሲገባ በጣም የሚያስደንቅ ሁኔታን ተመለከተ። በሦስት የተከፈለ ሰፊ ክፍል ☞ አንደኛው ክፍል በአልማዝ፣ በወርቅና በተለያዩ ጌጣጌጦች የተሞላ ክፍል ነው። ☞ሁለተኛው ክፍል ለመተኛት ምቹ የሆኑ ለየት ያሉ ፍራሾች ያሉበት ክፍል ነው። ☞ ሦስተኛው ክፍል አጠቃላይ በሚፈለጉና ውድ በሆኑ የምግብና የመጠጥ ዓይነቶች የተሞላ ነው። ዓሳ አጥማጁ ከራሱ ጋር መነጋገር ጀመረ። "ስድስት ሰዓት!! እንደኔ ላለው ድሃ ዓሳ አጥማጅ በጣም ብዙ ነው በዚህ ስድስት ሰዓት ምን ማድረግ አለብኝ? ጥሩ! በሦስተኛው ክፍል ባሉት ምግብና መጠጥ መጀመር አለብኝ ምክንያቱም ብዙ ወርቅ ለመሸከም የሚያስችለኝን ኃይል አገኝበታለሁ። " በማለት ወደ ሦስተኛው ክፍል በመሄድ መብላት ጀመረ። ይበላል… ይበላል… ይጠጣል… ከስድስቱ ሰዓታት በመብላት ሁለቱን ሰዓት ተጠቀመ። ልክ ሲጨርስ ወርቁንና ጌጣጌጡን ለመሸከም ወደ አንደኛው ክፍል በመሄድ ላይ ሳለ በሁለተኛው ክፍል ያለውን ያማረ ምቹ ፍራሽ ተመለከተና እራሱን ማናገር ጀመረ። "አሁን በጣም ጠግቤያለሁ ለምን ትንሽ በመተኛት በደንብ ለመሸከም የሚያስችለኝን እረፍት አልወስድም? ይህንን እድል ደግሜ አላገኘውምና ለምን አበላሸዋለሁ?" በማለት ወደ ፍራሹ በመሄድ በጀርባው ተዘረጋ በጣም ጭልጥ ያለ እንቅልፍም ወሰደው። ከተወሰነ ሰዓታት በኃላ "ተነስ ተነስ ቁም አንተ ጠባብ የሆንክ ዓሳ አጥማጅ ተነስ… ቁም...... ጊዜው አልቋል " አለው። ዓሳ አጥማጁም " እ እ እንዴ ምንድነው...?" አለ። ሰውዬውም " አዎ! ወደ ውጭ ውጣ " አለው። አጥማጁም "ኧረ ምንም በቂ ዕድል አላገኘሁም " አለ። ሰውዬውም "ስድስት ሰዓታት ሙሉ በዚህ ካዝና ውስጥ ሆነህ ጊዜህን ሳትጠቀም ቀርተህ አሁን ትባንናለህ? ከዚያም ሰዓት እንዲጨመርልህ ትጠይቃለህ? እነዚህን አልማዝና ወርቆች በፍጥነት ሰብስበህ በመውጣት የፈለከውን ምግብና መጠጥ እንዲሁም ያሰኘህን አይነት የመኝታ ፍራሽ መግዛት ትችል ነበር። ነገር ግን አንተ ዝንጉና ጠባብ በመሆንህ በዙሪያህ ያለውን እንጂ ሩቅ ያለውን ነገር አታስብም።" በማለት "ወደ ውጭ አስወጡት! " አለ። አጥማጁም "ኧረ ባካችሁ!! ኧረ!… እባካችሁ አንድ እድል ይሠጠኝ " ቢልም ሊሆንለት አልቻለም። ታሪካችን አለቀ በውስጡ ያለው ትምህርት ግን አላለቀም...... https://t.me/joinchat/Ux0uuUTU-VKz9aXJ ይቀላቀሉን።
Mostrar todo...
🎭ተመራጭ🎭✓

💘ተመራጭ✓✍️ የናንተው ምርጥ ቻነል👇👇 #እዚህ_የመዝናኛ_channel_ውስጥ ✓መሳጭ ታሪኮችን👍 ✓ልቦለዶችን📚ና ✓ሌሎች መፅሀፍቶችን(pdf)📕 #በተጨማሪም ✓አስደናቂ እውነታዎች🌌 ✓quotes👌meme& wallpapers💞 ✓New Musics🎶🎧 ✓informations ያገኛሉ። #ለሚወዱት_ሁሉ_share_ያድርጉ💕💕 Cross @sabiraw01 ለሀሳብ @temerach_comment_bot

ሰው ሁን ከሰውን ሰው ሁን እባክህ ሼር አድርግልኝ ባለኝ መሰረት ሼር በኪዳነምህረት የምትወዷት ከሆነ በፈጣሪ መወለድ ቋንቋ ነው እህቴን እርዱልኝ አረ በፈጣሪ አይታቹ አትለፍ እህታችን ይሄው የአጥንት እጢ ተብላ ይሄው ገና በወጣትነቷ የአልጋ ቁራኛ አርጎት አሰቀምጧታል ወዳጆቼ ግድ የላቹሁም ይሄ የሆነባት አመት እንኳን አልሞላትም እና እኛም መጨረሻችንን አናውቅምና ወዳጆቼ እርዱኝ በማለት ትማፀናቹኋለች በፈጣሪ መርዳት ባንችል እንኳን ሼር እያረግን እንለፍ እህታችንን ለመርዳት ከፈለጋቹ ብዙኋን ገዛህኝ 1000173773637 ንግድ ባንክ በፈጣሪ ሼር አርጉት ሰልክ 0912963798 0910716372 0942378593 ብዙሀን ብላቹ ደውሉላት እህታችን እግዚአብሔር በምህረቱ ይጎብኝሽ 🙏🏽🙏🏽🙏🏽 @Temerach_Entertainment
Mostrar todo...
🎭🎭🎭🎭🎭🎭🎭 እባካችሁ ከ18 አመት በታች የሆናቹ ጨዋታውን እንዳትቀላቀሉ። ለመቀላቀል ከስር ክቀረቡት Emojis እንዱን በመንካት መጀመር ትችላላችሁ። 🎭🎭🎭🎭🎭🎭🎭
Mostrar todo...
🎭
🥰
🤔
😎
🤩
🤐
😱
😉
😜
በጥቂት ጊዜ ውስጥ ተወዳጅነትን ያገኘ ምርጥ ቻናል🙈 👉ምክንያቱ ደግሞ በምናቀርባቸው ወቅታዊና ህይወት ለዋጭ መልዕክቶች ነው! እርሶም በወደዱት ምርጫ ይምጡና ይቀላቀሉን 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Mostrar todo...
👉አስቂኝ እና አዝናኝ ቀልዶች 😄
ተከታታይ ልቦለዶች
👉የ ፍቅር ታሪኮች ❤️
⚜አጫጭር ወጎች⚜
👀 ሁሉንምባንድ ላይ 👀
👉ይቀላቀሉን👈
👉Join👈
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 በአንድ ወቅት አንዲት ልጅ ፤ ህይወቷ የጎስቋላ እና በመከራ የተሞላ ሆኖባት እንዴት እንደምታደርግ ግራ ገብቷት አባቷ ጋር ሄዳ፤ "እኔ ሁል ጊዜ መቸገር እና መታገል ሰልችቶኛል ልክ አንዱ ችግር ሲፈታ፣ ሌላ ደግሞ ይተካል" እያለች አለቀሰች። አባቷም እያባበለ ኩሽና ወሰዳት። ከዚያም ሦስት ድስቶችን በውሃ ሞልቶ እያንዳንዳቸው በምድጃ ላይ አኖረ። ሦስቱ ድስቶች መንተክተክ ከጀመሩ በኋላ በአንድ ድስት ውስጥ ድንች ፣ በሁለተኛው ድስት ውስጥ እንቁላል እና በሦስተኛው ማንቆርቆሪያ ውስጥ የቡና ፍሬ አኖረ። ከዚያም ለሴት ልጁ አንዲት ቃል ሳይናገር ቁጭ ብለው እንዲበስሉ አደረገ። እሷም እየተንሰቀሰቀች እና ምን ሊያደርግ እንደሆነ እያሰበች በትዕግስት ጠበቀች። አባት ከሃያ ደቂቃዎች በኋላ እሳቶቹን አጠፋ። ድንቹን ከድስቱ አውጥቶ በአንድ ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ አስቀመጠው። እንቁላሎቹንም አውጥቶ ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ አስቀመጣቸው። ከዚያም ቡናውን ቀድቶ በአንድ ኩባያ ውስጥ አኖረው። ወደ እሷም ዞር ብሎ ጠየቀ። “ልጄ ፣ ምን ታያለሽ?” “ድንች ፣ እንቁላል እና ቡና” ብላ በችኮላ መለሰች። “ቀረብ ብለሽ እዩ አላት” እና ድንቹን እንድትነካ አደረጋት፤ ለስላሳ መሆናቸውን አስተዋለች። ከዚያም እንቁላል ወስዳ እንድትሰበር ጠየቃት። ቅርፊቱን ካወለቀች በኋላ ፣ የተቀቀለውን እንቁላል ተመለከተች። በመጨረሻም ቡናውን እንድትጠጣ ጠየቃት። የቡናው ጣዕም እና መዓዛ ፊቷ ላይ ፈገግታ አመጣ። “አባዬ ፣ ይህ ምን ማለት ነው?” ብላ ጠየቀችው። ከዚያም ድንቹ ፣ እንቁላሎቹ እና የቡና ፍሬዎች እያንዳንዳቸው አንድ ዓይነት ችግር ገጥሟቸው እንደነበር አብራራላት-የፈላ ውሃ። ሆኖም ፣ እያንዳንዳቸው በተለየ መንገድ ምላሽ ሰጡ። ድንቹ ጠንካራ ነበር በሚፈላ ውሃ ውስጥ ሲገባ ግን ለስላሳ እና ደካማ ሆነ። እንቁላሉ ተሰባሪ ነበር፤ በቅርፊቱ ውስጥ አስኳል ነበር በሚፈላ ውሃ ውስጥ ሲገባ ግን ውስጡ ከባድ እና ጠንካራ ሆነ። የተፈጨው የቡና ፍሬዎች ደግሞ ልዩ ነበሩ። ለፈላ ውሃ ከተጋለጡ በኋላ ውሃውን ቀይረው አዲስ ነገር ፈጠሩ። "አንቺ የትኛው ነሽ?" በማለት ሴት ልጁን ጠየቃት። እናንተስ “መከራ በራችሁን ሲያንኳኳ እንዴት ምላሽ ትሰጣላችሁ? እናንተ ድንች ፣ እንቁላል ወይም የቡና ናችሁ? በኮሜንት መልሱልን *** ንባብ ለህይወት
Mostrar todo...
👌 ውድ አባላቶቻችን ሊንካችንን እንደቀየርን ስንነግሮ በደስታ ነው። 💁ከዚህ ቀደም t.me/temerachnegeroch የነበረውን t.me/temerach_Entertainment በሚል ለውጠነዋል። ከአሁን ጀምሮ http://t.me/temerach_Entertainment በሚለው ያገኙናል።👆👍 ስለ አብሮነቶ ከልብ እናመሰግናለን።
Mostrar todo...
✽̶🌺✿ምኞቴ✿¶🌺̶̥✽̶┉┄             ▬▬▬❁ ክፍል አራት ❁▬▬▬      ✍....ረድኤት ተኝታለች፡፡ ያ ስታልመዉና ስታስበዉ ያደረችዉ ቢኒ የዉስጧን ሳነግረዉ የልቧን ሳታወራዉ ሄዷል፡፡ ... እማማ በለጡ ግራ ገብቷቸዉ "ልጄ አመማት እንዴ!?" እያሉ ይጨነቃሉ፡፡ ከተኛችበት አጠገብ ተቀምጠዉ ሲያዯት በረድኤት ፊት ላይ ላብ ይቀዳ ነበር፡፡ ለካስ እየቃዠች ነበር "ቢኒያም" "ቢኒ" "ቢኒያም" ትላለች፡፡ እማማ በለጡ ግራ ገብቶቸዋል፡፡ኧረ በስመአብ! ብለው አማተቡና ቀስ ብለዉ ልጃቸዉን ቀሰቀሷት "ረድኤት" "ረድኤት የኔ ልጅ ተነሽ ረፍዷል" "ረድኤት" ብለዉ ራሷን ደበስበስ ሲያደርጉ በቅዠቷ ስታልመዉ የነበረዉን ሰዉ "ቢኒያም" ብላ ብትት ስትል....፡፡  " አይዞሽ ልጄ" "ተነሺ..." "ዛሬ ምን ሆነሽ ነዉ የኔ ልጅ?" "አሁን ተነሺና ሸዋር ውሰጂ ....ረድኤት ከተኛችበት ነቅታ ከፊቷ ላይ ያለዉን ላብ ሟዠቀችዉ፡፡ በቅዠቷ ከቢኒያም ጋር ነበር ያደረችዉ ስትነቃ አጠገቧ እናቷን ስታገኝ ደንግጣለች፡፡ "የታለ ቢኒያም?" በሚል ፍለጋ አንገቷን እያዟዟረች መኝታ ቤቱን ትቃኛለች፡፡ ቢኒ ግን ... አጠገቧ የለም፡፡ ከአጠገቧ የተቀመጡት እናቷ እማማ በለጡ ናቸዉ፡፡ እናቷ በቅርቡ ባይመልሷት የትም ላደርስ በህልም ሩጫ ከቢኒ ጋር ነጉዳ ነበር፡፡ ረዲ ተነስታ ወደ ሻዋር ቤት አመራች..... . ...... ኤዲ የቤቷን ስራ ማንጎዳጎዱን ተያይዘዋለች፡፡ ቤቷን አፅድታና አነጣጥፋ ስጨርስ ምሳ ልሰራ ሽንኩርት እየላጠች የቤቷ በር ላይ ተሰይማለች፡፡ ...ረዲ ከቤት ስትወጣ ፊት ለፊት ኤዲን ተመለከተቻት "ደህና አደርሽ ኤዲዬ እንዴት አደርሽ?" አለቻት ይሄኔ በሆዷ "ባልሽን ልቀማሽ ነዉ ተዘጋጂ" እያለቻት ይመስላል፡፡ ኤዲም "ደህና አደርሽ ረዲ?"አለቻት ኤዲ ጉዷን አላወቀች አገር ሰላም ብላ ሰላምታ ትመልሳለች፡፡ ረዲም ወደ ኤዲ ጠጋ ብላ ከፈቲ ጎን እየተቀመጠች "የዛሬዉ ምሳ ምን ቢሆን ነዉ? በጠዋቱ መስራት ጀመርሽሳ?" አለቻት፡፡ኤዲም "ቢኒ ቀዝቀዝ ያለ ነገር ስለሚዎድ ቀድሜ ልስራ ብዬ ነዉ" አለቻት፡፡ ረዲም "ከዚያ እሱ ሊመጣ አከባቢ ተዉበሽ ልጠብቂዉ አይደል?!" ብላ ፈገግ አለች፡፡ "ኪኪኪ ባሌ አይደል? ብሽቀረቀርስ?" አለቻት፡፡ ኪኪኪኪ ሃሃሃሃ ሁለቱም ተሳሳቁ፡፡ .... ረዲ በሂወቷ በማንም ቀንታ የማታዉቀዉን በኤዲ መቅናቷ፤ ልቧ ለማንም...... ያልሸፈተዉን ለቢኒ እጅ ወደላይ ማለቷ ቤታቸዉና በፍቅራቸዉ የኔ በሆነ እያለች መመኘቷ ለራሷም ሳያስገርማት አልቀረም፡፡ በርግጥም ፍቅራቸዉ በጣም ያስቀናል፡፡ ...... ኤዲ ስለቢኒ ማዉራት ያስደስታታል፡፡ ረዲ ደግሞ ስለቢኒ መስማት...ኤዲ ስለ ቢኒ ታወራለች...ታወራለች.. ታወራለች፡፡ የሚገርመዉ ነገር ኤዲ ረዲን አላስተዋለቻትም እንጂ የቢኒን ስም ስጠራ ረዲ ወደ ኤዲ አፍ ተጠግታ ከንፈሯን ልስማት ደርሳለች፡፡ እንደገና "ኧረ ምን ሆኜ ነዉ?" ብላ ወደ ኀላ ፈቅቅ ፈቀቅ ትላለች፡፡ ስለሌላ ሳያወሩ የቢኒን ስም ብቻ እያነሱ ለረዥም ሰዓት ሲያወሩ ኤዲም ስራዋን ዘንግታ ረዲም ከልቧም ተመስጣ እየሰማች ነበር...፡፡ ኤዲ እንደገና "ኧረ ረዲ ስራዬን አስረሳሽኝኮ..." ብላ እቃ ልታመጣ ረዲን በተቀመጥችበት ትታት ወደ ዉስጥ ገባች፡፡ ...ረዲም ስለ ቢኒ የሰማችዉ ነገር እጅግ በጣም ስቧት ይበልጥ ወደደችዉ፡፡ ግን ... የሰዉ ነዉ፡፡ ቢሆንም ግን መንገር አለብኝ፡፡ "እሱን አጥቼማ መኖር አልችልም" "ልነግረዉ ይገባል..." እያለች እያሰበች   አስተማሪ የፍቅር ታሪክ📒               😘✍ታርኩ ቶሎ እንዲቀጥል ካነበባቹ በኋላ SHARE ሳታደርጉ አትለፉ::    ክፍል 5..... ይቀጥላል http://t.me/temerachnegeroch ክፍል 5ን እና ያመለጦትን ክፍል ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑት👍
Mostrar todo...

​​​​┄┉✽̶🌺✿ምኞቴ🌺̶̥✽̶┉┄             ▬▬▬❁ክፍል አንድ▬▬▬           ✍... ረድኤት ከረፋዱ አራት ሰዓት አከባቢ የቤታቸዉን በረንዳ በማፅዳት ላይ ሳለች የግቢያቸዉ በር ተንኳኳ፡፡ ማን ሊሆን ይችላል? ብላ እያሰበች ወደ በሩ ተጠጋች "አባዬና እማዬ ዛሬ የስራ ቀን ስላልሆነ ቤት ዉስጥ ናቸዉ፡፡" እና ማን ነዉ? እያለች የግቢዉን በር ጠጋ አለችና "ማን ነዉ?" አለች "እኔ ነኝ" የሚል ለስላሳ ድምፅ ከዉጭ የተሰጣት መልስ ነበር፡፡ ድምፁን ከዚህ በፊት ባታዉቀዉም ሰላም ያለ ሰዉ እንደሆነ በድምፁ ስለተረዳች በሩን ከፈተችለት፡፡ በጣም ቆንጅዬ ወጣት ነበር፡፡  "ደህና ነሽ" አላት፡፡ እሷም "ደህና ነኝ" ብላ ስትመልስለት "የሚከራይ ቤት አለ ብለዉኝ ነበር... አለ እንዴ?" ሲላት የረድኤት አባት ለረዢም ሰዓት በር ላይ እንደቆመች ስላዬ "ማን ነዉ?" እያሉ ወደ በሩ ተጠጉ፡፡ ወጣቱንም ባዩ ጊዜ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ወጣቱ ልጅ ለረድኤት የጠየቃትን ጥያቄ ለአባቷ ለጋሽ ሀብታሙ ደገመላቸዉ፡፡ ጋሽ ሀብታሙም አለ ወደውስጥ ግባ ልጄ፡፡ አሉት  እሺ ብሎ ገባ የሚከራየውን ቤት ገብቶ አየ ስንት እንደሚከራይ ጠየቃቸውና ተስማምተው ቢኒያም ወደ ቤት ተመለሰ ፡፡ ... ከዚህ ጊዜ በኃላ ነበር ረድኤት ቢንያምን ያወቀችዉ፡፡ ቢንያም እጅግ በጣም ዉብና ማራኪ ልጅ ነዉ፡፡ ሚስቱ ደግሞ ኤደን ትባላለች፡፡ እጅግ ሲበዛ ዝምተኛና ቆንጂዬ ናት፡፡ ቤት ስለምትዉልና ረድኤትም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ብትሆንም ሰመርን ከቤተሰቦቿ ጋር ስለምታሳልፍ ሁሌም አብረዉ ይዉሉ ነበር፡፡ ኤዲ ምንም ያክል ዝምተኛ ብትሆንም ለባሏ ግን ፍቅርን መስጠት የምትችል፤ በተለይ ሲጫወቱና ሰዉነቱ ላይ እየተንከባለለች ቅብጥብጥ ቅብጥ፤ ሽፍድ ስትልበት... ረድኤት "እኔ በሆንኩ" ብላ ትቀናባታለች፡፡ . . ..... ቢኒያም ከስራ ሊመጣ አከባቢ ኤዲ እጅግ በጣም ተዉባ ከወትሮዉ በተለዬ ይበልጥ አምራ የግቢዉን በር ለመክፈት ከቤቷ ወጥታ በሯ አጠገብ ትቀመጣለች፡፡ ልክ በሩ እንደተንኳኳ ሩጣ ትሄድና ቶሎ ትከፍታለች፡፡ ቢኒያምም እቅፉ ዉስጥ አስገብቶ ሲስማት ለተወሰነ ሰዓታት የተለያዩ ሳይሆን ለአመታት ተራርቀዉ ተነፋፍቀዉ የተገናኙ ይመስላሉ፡፡ ቢኒያም ፍቅር መስጠት ተክኖበታል፡፡ ሲያፈቅራትና ሲወዳት ምድር ላይ ሌላ ሴቶች እስከመፈጠራቸዉም ረስቶ ነዉ፡፡ ለሱ ሴት ማለት እሷ ብቻ ናት፡፡ እንደ እናት ያከብራታል፤ ያፈቅራታል በጣም ይሳሳላታል፡፡ ፍቅራቸዉ እንኳን አብሯቸዉ ለሚኖር ሰዉ ለአንድ ቀን በመንገድ ላይ ያያቸዉ ራሱ ይቀናባቸዋል፡፡ . ....ከግቢዉ ነዋሪም ጋር በጣም ተግባብቷል፡፡ ጋሽ ሀብታሙ ለብቻቸዉ ባገኛቸዉ ሰዓት "አባባ ገና ወጣት ነህ አረጁ የሚል ሰዉ ተሳስቷል፡፡ አሁን እኔ እና አንቱ ሩጫ ብንሽቀዳደም አዝነውልኝ ካልተዉልኝ በስተቀር ትበልጡኝ የለ እንዴ! አንቱኮ ሀይሌ ገ/ስላሴን ያስንቃሉ፡፡" እያለ ይቀልዳቸዋል፡፡ እሳቸዉም የወጣትነት ጊዜያቸዉ ታዉሷቸዉ በጨዋታዉ ከሳቁ በኃላ "አይ ልጄ..." ብለዉ ትረካቸዉን ይጀምራሉ፡፡ ለወሬያቸዉ አክብሮ ጆሮ ስለሰጣቸዉ ከስራ የሚመለስበትን ሰዓት እንደ ኤዲ እርሳቸዉም ይጠባበቃሉ፡፡ በተለይ ደሞ ረድኤት...!            አስተማሪ የፍቅር ታሪክ📒    ......ክፍል 2 ይቀጥላል.... ሙሉ ክፍሉን ለማንበብ ሊንኩን ተጭነው join ይበሉ። 👇👇👇👇👇 http://t.me/temerachnegeroch
Mostrar todo...