cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

The Blue Pride ሰማያዊው ኩራት

ይህ የቴሌግራም ቻነል የእግር ኳስ ዜናዎችን፣ ታሪኮችን እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተለይ ለእንግሊዙ የለንደን የእግር ኳስ ክለብ ቼልሲ ትልቅ ትኩረት በመስጠት ያቀርባል! አላማችን ኢትዮጵያዊያን የቼልሲ ደጋፊዎች ጥራት ያለው እና ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ እንዲሁም ስለሚደግፉት ክለብ አኩሪ ታሪክ፣ ጠንካራ ማንነት፣ የድል አድራጊነት ባህል ጥሩ ግንዛቤ እንዲኖራቸው መስራት ነው።

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 185
Suscriptores
Sin datos24 horas
+17 días
-1730 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የብራይተኑ ካይሴዶ እየመጣ ነው? "ሞይሰስ ካይሲዶ በቼልሲ የመጀመሪያ ጨዋታዎቹ ላይ በእውነት በጣም ደካማ አፈፃፀም ነበር ያሳይ የነበረው። እናም ሲጫወት ባየሁት ቁጥር "ያ ለብራይተን ሲጫወት በድንቅ እንቅስቃሴው የማውቀው ተጫዋች የት ሄደ?" እያልኩ ማሰብ ጀምሬ ነበር። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ግን ሁኔታው እየተቀየረ እየተሻሻለ መጥቶ አሁን ላይ ቀደም ሲል በብራይተን የምናውቀውን አስደናቂውን ካይሴዶን የሚያስታውስ የእንቅስቃሴ ፍንጭ ማየት ጀምሬያለሁ" ጄሚ ሬድናፕ እናንተስ ምን ትላላችሁ?
Mostrar todo...
👍 2
ቻሎባህ - Jehovah Son ! በቼልሲ አካዳሚ አድገውም ይሁን ከሌላ ክለብ በወጣትነታቸው ያላቸው ያልተገለጠ እምቅ ችሎታቸው ከግምት ውስጥ ገብቶ በውድ ዋጋ ከተገዙ ተጨዋቾች መካከል እንደ ትሬቨር ቻሎባህ ብሩህ ግዜ ከፊቱ የሚጠብቀው ያለ አይመስለኝም። ከሶስት እና አራት አመት በኋላ ከአለማችን ምርጥ ተከላካዮች አንዱ እንደሚሆን የሚያሳዩ ብዙ አመላካች ነገሮች አሉት። ተክለ ሰውነቱ፣ እይታው፣ እርጋታው፣ ስነ ምግባሩ፣ ከኳስ ጋር ያለው ምቾት፣ … እና ከምንም በላይ በጠንካራ የእምነት መሠረት ላይ የታነፀ ማንነት ስላለው በህይወቱ የሚገጥሙትን አስቸጋሪ ወቅቶች በፅናት የሚሻገርበት እሴቶች አሉት። ይህን ያልተገለጠ እምቅ ችሎታውን ለማውጣት የሚፈልገው ሁለት ነገሮች ግዜ እና እምነት የሚጥልበት አሰልጣኝ ናቸው። ዛሬ የብቃቱ ግማሽ ላይ አልደረሰም፣ ነገ እንደሚደርስ ግን መገመት ቀላል ነው። አያድርገውና ቼልሲዎች ቻሎባህን የሚሸጡ ከሆነ ወደፊት ሁላችንም የምንቆጭበት ይመስለኛል።
Mostrar todo...
👍 5
ኦ ቲያጎ … 😢 የቼልሲ እግር ኳስ ክለብ በዓለም እግር ኳስ ምርጥ ተከላካዮች መካከል አንዱ የሆነውን ቲያጎ ሲልቫን በአንድ አመት ኮንትራት ያስፈረመው በወርሃ ነሀሴ 2020 ነበር። እንደታሰበው ሳይሆን ቲያጎ ከቼልሲ ጋር አራት አመታት ቆይቶ እና ከ150 በላይ ጨዋታዎችን አድርጎ፣ በእንግሊዝ የመጀመሪያ የውድድር ዘመኑ የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን አሸንፎ በውድድር አመቱ መጨረሻ በክብር ሊሰናበት እንደሆነ ይፋ ሆኗል። ባሰለፈቸው አራት አመታት ውስጥ ለክለቡ ያለውን ሁሉ ስለሚሰጥ ከቼልሲ ደጋፊዎች ጋር እድሜ ልክ የሚቆይ የስሜት ትስስርና ግንኙነት መፍጠር ችሏል። ከቼልሲ ጋር እንደሚለያይ በይፋ በገለፀበት ቃለ ምልልሱ እንዲህ ብሏል። "ደህና ሁኑ ብዬ እስከመጨረሻው መሰናበት አልፈልግም፣ ምክንያቱም አንድ ቀን በሆነ አይነት ሚና ልመለስ እንደምችል አስባለሁ። ወደ እዚህ ታላቅ ክለብ መመለስ እፈልጋለሁ" እኛም አንድ ቀን እንደምትመለስ እናምናለን፣ ስለ ሁሉም ነገር አመሰግናለን።
Mostrar todo...
13😢 2
"ቼልሲ ውስጥ የማፍርባቸው ተጫዋቾች አሉ" "ከቀድሞው የቼልሲ ቡድን ጋር በጣም ጠንካራ የስሜት ትስስር ነው ያለኝ፣ ክለቡን እወደዋለሁ። አሁን እየሆነ ባለው ነገር ስሜቴ ተጎድቷል። አብራሞቪች ቼልሲን በአለማቀፍ ደረጃ ስኬታማ ካደረገው በኋላ የእሱን መልቀቅ ተከትሎ በክለቡ ላይ እየደረሰ ያለው የውጤት ቀውስ የማይታመን ነው። በሮማን አብራሞቪች ከፍተኛ ጥረት የተገነባው የክለቡ ጠንካራ ማንነት በዚህ መንገድ ሲፈራርስ ዝም ብሎ መመልከቱ ተቀባይነት የለውም። አሁን ካለው የቼልሲ ስብስብ ቁልፍ ተጫዋቾች እነማን እንደሆኑ አላውቅም። በቡድኑ ውስጥ እንደዚህ ያሉ ቁልፍ የመሪነት ሚና ያላቸው ተጫዋቾች ያሉ አይመስለኝም። ጠንካራ እና ልምድ ያላቸው የእግር ኳስ ተጫዋቾች በአንድ ቡድን ውስጥ ከሌሉ መሰረታዊ ነገሮች ለማከናወን ራሱ በጣም አስቸጋሪ ነው። ዛሬ ቼልሲ ያለበትን ሁኔታ እንዲህ ነው ብሎ መናገር ራሱ አይቻልም። በቡድኑ ውስጥ ብዙ የሚያሳፍሩ እና የክለቡን ታሪክ የማይመጥኑ ተጫዋቾች አሉ። ባለቤቶቹ ብዙ ገንዘብ አውጥተዋል፣ ነገር ግን አሁንም በሜዳ ውስጥ እና ከሜዳ ውጪ በርካታ ችግሮች አሉ፣ በየቦታው ችግር አለባቸው። ይህ ለምን ሆነ? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። አሁን የሚሄዱበት አካሄድ ጥሩ አይደለም፣ ይህ ሁኔታ ሊቀጥል አይገባም። ይህ ሁኔታ ዝም ስለተባለ በራሱ ግዜ የሚስተካከል ነገር አይደለም። ችግሩ እየባሰ ከሄደ በመጨረሻም ቼልሲን ለማየት ማንም ፍላጎት አይኖረውም። በዚህ አካሄዳቸው ከቀጠሉ ቡድኑ እንደ ቀድሞው በሌሎች ቡድኖች ዘንድ መፈራቱ እና መከበሩ ይቀራል፣ በቅርቡ ይረሳል፣ ተራ ቡድን ይሆናል። እና ይህ ደግሞ በፍፁም ተቀባይነት የለውም፣ ይህ ነገር በፍጥነት መቆም አለበት" ጉስ ሂዲንክ
Mostrar todo...
8👍 6🔥 3
Capitain, Leader and Legend!! የቼልሲ የምንግዜም ምርጥ አምበል፣ መሪ እና ታሪካዊ ተጨዋች በመባል የሚታወቀው ጆን ቴሪ የፕሪሚየር ሊግ ድንቅ ተጨዋቾች ዝርዝር ውስጥ ተካቷል። እንኳን ደስ አለህ በሉት! 💙🙌
Mostrar todo...
🔥 10👍 1
የመረቡን ጀርባ ማግኘት ብቻ ነበር የጎደለን! "ደጋፊዎቻችን ለማስደሰት የቻልነውን ለማድረግ ወስነን ነበር፣ በቂ እድሎችንም አግኝተን ነበር። ይህንን ሽንፈት መቀበል ከባድ ነው። በጨዋታው ላይ ጥሩ ተንቀሳቅሰናል፣ የመረቡን ጀርባ ማግኘት ብቻ ነበር የጎደለን። አሁን ማድረግ ያለብን ከእንደዚህ አይነት መራር ልምዶች ለወደፊቱ መማር ነው" ትሬቮህ ቻሎባህ ……………………… በተያያዘ ዜና ቼልሲዎች ቻሎባህን የመሸጥ ፍላጎት አላቸው። ቼልሲ ቻሎባህን አሁን ቢሸጠው ይጠቀማል? ወይስ ቢቆይ ነው ክለቡ የሚጠቀመው? እኔ ቢቆይ እመርጣለሁ!
Mostrar todo...
🔥 2
L e g e n d ! በሰማያዊው ማልያ እንዳያቸው ከምመኛቸውና ስላየኋቸው ከምደሰትባቸው እና የማልያውን ክብር በሚገባ ይመጥናሉ ብዬ ከማምንባቸው ተጨዋቾች መካከል አንዱ ቲያጎ ነው። ቼልሲ በአዲሶቹ የክለቡ ባለቤቶች እጅ ከገባ ግዜ ጀምሮ ደስተኛ አይደለም፣ በውስጡ አምቆ የያዘው ብዙ የተከፋባቸው ነገሮች እንዳሉ ግልፅ ነው፣ ግን ለክለቡ ደህንነት ሲል እንዲሁም ፕሮፌሽናል ስለሆነ ዝምታን መርጧል። በውድድር አመቱ መጨረሻ ከቼልሲ ጋር እንደሚለያይ ፍንጭ የሰጠ አስተያየት ሰቷል። "ውሳኔውን ወስኛለሁ፣ በቅርቡ ይፋ ይሆናል" ብሏል። ስንብቱ በደስታ እና በዋንጫ የታጀበ ቢሆን እመኝ ነበር። ያም ሆነ ይህ ቲያጎ የቼልሲ ሌጀንድ ነው!
Mostrar todo...
👍 6🥰 5
ጨዋታውአልቆ ቲያጎ ያለቅሳል፣ ኖኒ ግን ይስቃል፣ ምንድነው የሆነው? ቼልሲ ተሸንፏል ወይንስ አሸንፏል? …………………………………………………………………………… በእርግጥ ቼልሲ ካለፉት ሁለት አመታት ጀምሮ የገጠመው ችግር የተወሳሰበ እና ዘርፈ ብዙ ነው። የክለቡ ባለቤቶች ስለ እግር ኳስ ኢንደስትሪው ያላቸው አነስተኛ ወይም የተሳሳተ ግንዛቤ፣ የዳይሬክተሮቹ ደካማ ስፖርታዊ ውሳኔ የምልመላና የቅጥር ስትራቴጂ፣ አሰልጣኙ የክለቡን ደረጃ (ስታንዳርድ) የሚመጥን አለመሆኑ፣ በርካታ ልምድ የሌላቸው ተጨዋቾች መኖራቸው ዋና ዋና ችግሮች ናቸው። እነዚህ ችግሮች በአጭር ግዜ የሚቀረፉ ባለመሆናቸው ክለቡ ላልተወሰኑ አመታት በውጤት ማጣት ውስጥ ሊቆይ እንደሚችል መገመት ይቻላል። ነገር ግን ምናልባት የክለቡ ባለቤቶች የክለቡን ጉዳት ለመቀነስ እና በአጭር ግዜ ውስጥ ክለቡን ከውድቀት ለመታደግ የሚፈልጉ ከሆነ በመጪው ክረምት እንደ ኖኒ ማዱኬ አይነት ተሸንፈው ከተቀናቃኝ ጋር ተቃቅፈው የሚገለፍጡ እና የቼልሲን አርማ ለብሶ መሸነፍ ምንም አይነት ህመም የማይፈጥርባቸውን ተጨዋቾችን አሰናብቶ በምትካቸው ሽንፈትን የሚጠሉ፣ የመሪነት ችሎታ ያላቸው እና ለክለባቸው አርማ አና ክብር እስከመጨረሻው የሚታገሉ፣ የደጋፊውን ስሜት የሚያከብሩ ተጨዋቾች ማስፈረም አለባቸው። የቲያጎን እንባ ማየት ግን ልብ ይሰብራል 😢 💔 የእሱን የማሸነፍ ስሜት ባልተረዱ ልጆች ህልሙ መክሸፉ ያሳዝናል፣ የቲያጎ ስሜት የደጋፊው ስሜት ነፀብራቅ ነው!
Mostrar todo...
11👍 3
ኒኮላስ ጃክሰን ወይስ ፖቼቲኖ? ዛሬ የቼልሲ ተጨዋቾች ለማሸነፍ እንደፈለጉና ያላቸውን ሁሉ ለመስጠት ቆርጠው እንደመጡ ከእንቅስቃሴያቸውና ከሰውነት ቋንቋቸው መረዳት ቀላል ነው። በእርግጥ የተገኙትን የጎል እድሎች ቢጠቀሙ ኖሮ ማሸነፍ የሚችሉት ጨዋታ ነበር። በጨዋታው ያለቀላቸውን እድሎች ያባከነው ጃክሰን ጎል አካባቢ ሲደርስና ከበረኞች ጋር ሲገናኝ እጅግ የበዛ የአቅም ውሱንነት አለበት፣ እግሩ ይዝላል፣ ግራ ይጋባል፣ ይደነግጣል፣ ምን ማድረግ እንዳለበት አያውቅም፣ ይደክመዋል፣ ምናልባት የሚያገባ ከሆነ ስለሚያሳየው የደስታ አገላለፅ እያሰበ ይሆናል… እናም ፈፅሞ ከመጨረሻ አጥቂ የማይጠበቅ የቂላቂል ውሳኔ ይወስናል፣ ወይም ተከላካዮች ደርሰው ኳሱን ይወስዱበታል፣ ከዛ ይበሳጫል፣ ከተጨዋቾች ይጣላል፣ ቢጫ ያያል… ህይወት ይቀጥላል። ይሄው ነው በየሳምንቱ እና በየ90 ደቂቃው የሚደጋገመው የጃክሰን በጭንቀት የተሞላ ትርዒት። እሱ የሚችለውን ነው እያደረገ ነው ያለው፣ መቼም "በቃ አልሆነልኝም" ብሎ ራሱን እንዲቀየር አይጠበቅበትም። ይህን ማድረግ ያለበት አሰልጣኙ ነው፣ ጃክሰን ተቀይሮ የሚወጣው ምን ሲያደርግ ነው?… መቼ? … ወይስ መቼም አይቀየርም? አንዳንዴስ ተቀይሮ መግባት የለበትም? … እንደዚህ አይነት ዝቅ ያለ አፈፃፀም እያሳየ እና ጫና ውስጥ ሆኖ አየተጫወተ በየሳምንቱ ሙሉ 90 ማሰለፉ ለእድገቱ ጠቃሚ ነው? አሰልጣኞች ከነባራዊ ሁኔታዎች ተነስተው በቀጣይ ሊመጣ የሚችለውን ነገር በመገመት በሚሰሩት ስራ ነው ልዩነት የሚፈጥሩት። ፖቼቲኖ የጃክሰንን ሁኔታ (አመላካች መረጃዎች) ከግምት በማስገባት ሊከሰት የሚችለውን ነገር ቀድሞ በመገመት ልጁንም ክለቡንም ለመታደግ የተለያየ ዘዴ አለመጠቀሙ ይገርማል። ሁሌም አንድ አይነት ነገር እያደረጉ የተለየ ውጤት መጠበቅ ሞኝነት ነው።
Mostrar todo...
ኮል ፓልመር የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ መባል አለበት! "ኮል ፓልመር በማንችስተር ሲቲ ቢሆን እና አሁን በቼልሲ የሚያደርገውን ነገር ቢያደርግ ኖሮ ሁሉም ሰው የፕሪምየር ሊግ ምርጡ ተጫዋች ነው ይለው ነበር። ቼልሲዎች በአጠቃላይ መጥፎ የውድድር ዘመን ስላሳለፉ ምናልባት ኮከብ ተብሎ ላይመረጥ ይችላል። ነገር ግን እኔ መመረጥ እንዳለበት አምናለሁ:: ከዚህ ቀደም በሊጉ ምንም ልምድ የሌለው ተጨዋች በፕሪሚየር ሊጉ ላይ በዚህ መጠን ጎል ማስቆጠር ከቀለለው እና ማንፀባረቅ ከቻለ ክብሩን መውሰድ እንዳለበት ምንም ጥርጥር የለውም። በዛ ላይ ገና 20 አመቱ ነው፣ የጨዋታ ቦታውም የፊት አጥቂ ሳይሆን ነው የሊጉ ኮከብ ግብ አግቢነትን እየመራ ያለው። እሱ ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ያቀብላል፣ የፍፁም ቅጣት ምቶችን የሚያስቆጥረው ተዝናንቶ ነው፣ ጨዋታው የቱንም ያህል ከባድ ቢሆን እሱ ግን ፍፁም የተረጋጋ እና ምን ማድረግ እንዳለበት ቀድሞ የሚያውቅ አይነት ሰው ይመስላል" ሳም አላርዳይስ የቼልሲው ኮል ፓልመር ለምን የዘንድሮ ፕሪሚየር ሊጉ ምርጥ ተጫዋችነት ክብርን ማሸነፍ እንዳለበት ሲናገሩ
Mostrar todo...
17