cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የስኬት ቁልፎች

ውድ ቤተሰቦቼ እኩዋን ወደዚ chanal በደና መጡ! በዚህ ቻናል ላይ ለእናንተ ለውድ ቤተሰቦቻች ይጠቅማሉ ብለን ያሰብናቸውን ነገሮች post እናረጋለን ከዚህ በተጨማሪ እንዲጨመር ወይም እንዲቀነስ የምትፈልጉት ነገር ካለ @Dreamer2119 ማናገር ትችላላችው!

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
267
Suscriptores
Sin datos24 horas
-47 días
-230 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ዝቅ ማለትህን ለከፍታ ረጅም ፎቅ መሥራት የሚያስብ ሰው ወደታች ረጅም መሠረት መሥራት አለበት ። እኛም በህይወታችን ትልቅ ነገር መሥራት ሥናስብ ልክ ፎቅ ወደ ላይ ለማቆም ወደ ታች አንቆፍርም አንደማንለው ሁሉ  በህይታችንም ፈተና ሲያጋጥመን ወደ ላይ ነጥረን ለመውጣት ጠንካራ መሠረት እየሰራን አንደሆነ አስበን በደስታ እና በምስጋና ከስህተታችንም እየተማርን እንጠብቅ መልካም ቀን🙏
Mostrar todo...
ሰውየው ትልቅ ሰንጋ ይገዛና ጎረቤቶቹንና የአካባቢውን ማህበረሰብ ብሎም ወዳጆቹን ለመጋበዝ ይወስናል። ስጋው መጠባበስ መዘጋጀት ሲጀምር ታናሽ ወንድሙን ይጠራውና ፦        "እስኪ ሂድና ወዳጅ ጎረቤቶቻችንን ቶሎ ጥራና ከማዕዳችን ይቋደሱ " ይለዋል።          ታናሽ ወንድሙም ወደ ውጭ ይወጣና ጩኸት ይጀምራል፦        "ኡ ኡ ኡ ድረሱልን እሳት እሳት…ድረሱልን" ማለት ከጀመረ ብዙም ሳይቆይ ቁጥራቸው ትንሽ የማይባል ሰዎች ከየቤቶቻቸው ወጥተው ወደ ሰውየው ቤት አመሩ። ሆኖም ከሰውየው ቤት እንደገቡ ያጋጠማቸው የተለየ ነገር ነበር። የመጣው ሰው ሁሉ እስኪበቃው ድረስ በልቶና ጠጥቶ ወደ ቤቱ ተመለሰ።        ደጋሹ ወንድም ታናሽ ወንድሙን ጠራውና ፦" ዛሬ ከመጡት ሰዎች ብዙም የማውቃቸው ሰዎች የሉም ፤ ከዚህ በፊትም አይቻቸው አላውቅም፤ የት አሉ ወዳጆቻችንና ጓደኞቻችን !?" ሲል ጠየቀው።       ወንድሙም፦ "እነዚህ ሰዎች እኮ ቤታችን እሳት አለ ብዬ ስጠራቸው የመጡ ሰዎች እንጂ ድግስ አለ ብዬ ጠርቻቸው  አይደለም ፤ የዚህ አይነቱ ሰው እኮ ነው ክብርና እንክብካቤ የሚያስፈልገው" ሲል መልስ ሰጠው።      በቸገረህ ጊዜ ከጎንህ የማይቆምን ሰው ወዳጅ ወይም ጓደኛ አድርጎ መያዝ ጉዳት ነው። እውነተኛ ወዳጅ በቸገረህና በተጨነቅክ ጊዜ ከጎንህ የቆመ ሰው ነው።
Mostrar todo...
ጠቃሚ ሀሳቦች ====+====+====+====+====+====+ 👉 እንደገቢህ ሁኔታ በየሳምንቱ ወይም በየወሩ የተወሰነ ገንዘብ አስቀምጥ መጠኑ አያሳስብም ዋናው መቆጠብህ ነው። 👉 የቤተሰቦችህን ምክር ስማ በቀኑ በመጨረሻም ስለአንተ መልካም በመመኘት ብኜቹ እነሱ ሆነው ታገኛቸዋለህ 👉 ጓደኞችህን ተጠንቅቀህ ምረጥ አንተ የአከባቢህ ውጤት ነህ 👉  ጥቂቶች ብቻ የሚካኑበት ክህሎት ስለሆነ ብቻህን መሆንን እና እራስህን መቻልን ተለማመድ 👉 እራስህን አስተምር አንብብ አሁንም አንብብ፣ ጤናህን ጠብቅ፣ አካልህን ተመልከተው ሌሎች እንዲወዱህ አትጠብቅ በመጀመሪያ አንተ ራስህን ውደድ
Mostrar todo...
ስብሃት ገብረእግዚአብሄር አንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፥ "በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ፤ ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ፤ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ፤ በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ፤ ሰዎች ሊጠሉህ ፣ ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ይችላሉ።"በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል።አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል። "ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!" አንድ ነገር ልንገራችሁ፥ በህይወታችሁ ማንንም አትውቀሱ፤ ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጡልችሀል፤ መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኑችሁዋል። ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆናቹኋል፤ ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኑላችሁዋል።
Mostrar todo...
Hi, how are you? did you see what happened? look https://cutt.ly/pwT0ntu2
Mostrar todo...
#ዛሬን ማየት መቻል "ማየት የተሳነኝ ነኝ እባካችሁ እርዱኝ" የሚል ጽሑፍ ከፊት ለፊቱ አስቀምጦ በፈጣሪ ስም ይለምናል። አልፎ አልፎ ሳንቲም ቅጭል ይላል የምፅዋት መጣያ ባርኔጣው ውስጥ። ረፋዱ ላይ አንድ መንገደኛ ተመፅዋች የፃፈውን ጽሑፍ ካነበበ በኋላ ብዕር አውጥቶ ጽሑፉን ቀይሮት ሄደ። ብዙም ሳይቆይ ባርኔጣው በሳንቲሞች ሞልቶ መፍሰስ ጀመረ። ከሰዓት በኋላ ያ ሰው ውጤቱን ለማየት ተመልሶ ሲመጣ ተመፅዋች በኮቴው ለየውና "አንተ ነህ  አይደል ፅሑፌን የቀየርከው? ለመሆኑ ምን ብለህ ፅፈህ ነው የሳምንቱን ገቢ በሶስት ሰዓት ያንበሸበሽከኝ?" አለው በመደነቅ ስሜት። አስተዋዩም ልጅ:- "በአንተ ሃሳብ ላይ ትንሽ ለውጥ ነው ያደረኩት።  ምን ብዬ መሰለህ ፡- "ዛሬ ውብ ቀን ነው እኔ ግን አላየውም!" ብዬ ነው የፃፍኩት። "አየህ! ያንተ ጽሑፍ ያንተን አለማየት ብቻ እንጂ ማየት መቻል መታደል መሆኑን ለሰዎች አያስተምርም። ሰዎች ምስጋናቸውን ለፈጣሪ፣ ምጽዋት ላንተ  በመስጠት የገለፁልህ ለዚህ ነው።" ምን እንማር ከዚህ? ጥቂት የአስተሳሰብ ለውጥ የሚፈጥረውን ተአምር ወይስ ምስጋናን? ዛሬ ውብ ቀን ነው እኛ ግን እያየነዉ ነው?. https://t.me/followyourdreamstheyknowtheway
Mostrar todo...

ለውጥ! ለውጥ ማለት ከትንሽ ነገር ጀምሮ የሚያድግ ሂደት ነው ለመለወጥ ከትንሿ መነሳት ነው ዋናውና ጠካራው ነገር ግን በጀመርነው ላይ እንፀናለን ወይ ነው አባቢ ለመሆን ዛሬ ትንሽ በማንበብ መጀመር ልምድ እንዲሆን ሁልግዜም መደጋገም ለጤናችን ያካል እንቅስቃሴ ማድረግ ከትንሽ ነገር ብንጅምርም ያለማቋረጥ መቀጠል ለሂዎታችን አስፈላጊ የሆኑትን ልምዶች ከትንሽ ነገር ጅምረን በቋሚነት ማስቀጠል ግዜው ቢረዝምም የምንፈልገውን አይነት ሰው መሆናችን ግን አይቀርም። መልካም ቀን
Mostrar todo...