cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

GOSPEL FOR ALL PEOPLE GROUPS

ሰላም ቅዱሳን የቻናላችን ቤተሰቦች፣ በቻናሉ የሚንለቅላችሁ ፕሮግራሞች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ስሆን፣ ሌሎችም ተጠቃሚ እንድሆኑ እንድትጋብዙ እናሳስባለን።። ✔ መንፈሳዊ መጽሐፍቶች/መጽሔቶችን ✔ ወንጌልን ስለማሰራጨት የሚመለከቱ ት/ቶችን ✔ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ያደረጉ ት/ቶችን ✔ የቆዩ እና አዳድስ አምልኮ መዝሙሮችን ✔ አንዳንድ ጠቃሚ አባባሎችን

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
388
Suscriptores
+424 horas
+267 días
+6930 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#ርዕስ:-ማንነትን_ማወቅ
ጌታ ኢየሱስ/በአዲሱ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ #ምን_ናችሁ ይላል ፣ በሚል ሐሳብ ተነስቶ በትላንትናው ዕለት ከሰዓት እያስተማረ ካቆመበት ነበር የቀጠለው። ጌታ ኢየሱስ ሆነ ሐዋርያት በመጽሐፍ አማኞችን ናችሁ እያሉ ያስተማሯአቸው ትምህርቶች በሙሉ የአዲስ ኪዳን አማኞችን ማንነት ይገልፃሉ። ስለዚህ አማኞችን ስለ ክርስቲያዊ ማንነት በደንብ ልያሳስባቸው ይገባል። በመጽሐፍ:-👇 1...እናንተ የምድር ጨው ናችሁ። ማቴ 5:13 ጨው አልጫ ቢሆን ባይጣፍጠው እንደ ድንጋይ ወደ ውጪ ይጣላል። አማኞች በዚህ ዓለም እንደ ጨው ሊሆኑና ዓለምን ሊያጣፍጡ ጣዕም እንዲኖረው ሊያደርጉ ነው ጌታ የመረጣቸው። 2...እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። ማቴ 5:14 አንድ አማኝ ብዙ በጌታ ያልሆኑ ሰዎች ባሉበት ማህበረሰብ ውስጥ ቢኖር በከባድ ጨለማ ውስጥ እንዳለ #አምፖል(💡) ነው። አማኝ የዓለምን ክፉ ሥራ ሊያጋልጥ እና እንድ ብርሃን ለሚያይ ሁሉ ለመታየት በኢየሱስ ክርስቶስ ተመርጧል። ክርስቲያዊ ማንነታቸውን በትክክል ለመኖር የሚጥሩ ሰዎችን ሰይጣን በተለያየ መንገድ ለመጣል በዚህ ዘመን ይፈልጋል፣ ነገር አማኞች በክርስቶስ ኢየሱስ በሆነ ጽናት ሊበረቱ ይገባል። 3....ምስክሮቼ ናችሁ አለ። ሉቃስ 24:48 ቤተ ክርስቲያን፣ አገልጋዮች፣ በቤተ ክርስቲያን በልዩ ልዩ አገልግሎት ክፍልና ስጦታ ከሚያገለግሉ ሰዎች ጀምሮ ወንጌልን በጨለማ ላሉ ሰዎች መመስከር ወይም ስለ ኢየሱስ ምስክሮቹ መሆን ይገባናል። በተለይ ቤተ ክርስቲያን ወይም በመሪ አገልግሎት ክፍል ያሉ ስዎች በዚህ ጉዳይ በዚህ ዘመን በጣም ዝምታን መርጠዋል፣ Outrich( ወንጌልን በአደባባይ መስበክ) ፣ አንድ ለአንድ ሆነው የወንጌል ዘመቻ ማድረግ፣ በጀማ የወንጌል ስርጭት ማድረግ አሁን ጊዜ በቤተ ክርስቲያን እየተደረገ አይደለም። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን የምስክርነቱን ሥራ ጠንክራ መሥራት አለባት። አንድ ክርስቲያን ምንም ዓይነት ሥራ ይኑረው፣ ነገር ግን በሚሠራው ሥራ ቦታ የኢየሱስ መስካሪ ሊሆን ይገባል፣ የሥራ ባልደረባው በጌታ ካልሆነ ይህንን የፍቅር ወንጌልን ሊያሰማው ይገባል። 4...ወዳጆቼ ናችሁ አለ። የዮሐንስ 15:14 አማኝ ሁልጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት ሊያደርጉ፣ በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ ልመላለሱ ይገባቸዋል። አንዲት ሴት ለአንድ ወንድ ከታጨች እጮኛዋ ከሆነው ወንድ ውጪ ሌላን በፍጹም ሊታስተናግደው አትችልም፣ ልክ እንደዛው አማኞች የማይበጠስ ህብረትን ከእግዚአብሔር ጋር ስለጀመሩ ከሌላ ከማንም ጋር ወዳጅነትን ልፈጥሩ አይችሉም። 5....ሕንፃ ናችሁ አለ። 1ኛ ቆሮ 3:16 የሕንጻው ባህሪይ መያያዝ ነው። አንዱ ከአንዱ ጋር ተያይዞ ጥሩ ውበት ያለው ይሆናል። አማኞችም ከተለያዩ ሁኔታዎቻቸው ተጠርተው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስሰበሰቡ እንደ ሕንፃ ይሆናሉ። 6....እናንተ መልእክት ናችሁ። 2 ቆሮ 3:2 ሰዎች ከሁኔታዎቻችሁ ይሰማሉ፣ያነባሉ፣እናንተን ይከተሏቸዋል። ስለዚህ እናንተ ኢየሱስን ለሰዎች ማስተላለፍ፣ ማስነበብና ማስማት የምትችሉ መልእክት ናችሁ። እስከዚህ ያሉ መልእክቶችን ካስተላለፈ በኋላ ስለ አንድ አገልጋይ ምስክሪነትን እንዲህ በማለት በምሳሌ አነሳ:- 👉 ጠያቂ:- አገልጋዩን እስኪ ስለመለወጥህ ንገረኝ ፣ እንዴት ተለወጥክ 👉 አገልጋዩ:- ስመልስ እንድህ እኔን የለወጠኝ የተለወጠ ሰው ነው አለ። የተለወጥን ሰዎች ለዓለማዊያን ሰዎች የሚንነበብ መልእክት ነን። ጸጋ ይብዛላችሁ። ✏ Pastor Tamrat Haile
Mostrar todo...
👍 3
please,#ለሚትወዱት ሰው ወይም #በgroup #share ሳታደርጉ እንዳትተው እላለሁ። የተለያዩ መንፈሳዊ ፕሮግራሞች፣ ትምህርቶችን፣ መጽሐፍቶችን እና መዝሙሮችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ።👇 ሊንክ :- https://t.me/GFAPG
Mostrar todo...
የኢትዮጵያ_ቃለ_ሕይወት_ቤተክርስቲያን_የእምነት_አቋም.pdf14.59 MB
please,#ለሚትወዱት ሰው ወይም #በgroup #share ሳታደርጉ እንዳትተው እላለሁ። የተለያዩ መንፈሳዊ ፕሮግራሞች፣ ትምህርቶችን፣ መጽሐፍቶችን እና መዝሙሮችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ።👇 ሊንክ :- https://t.me/GFAPG
Mostrar todo...
የኢትዮጵያ_ቃለ_ሕይወት_ቤተክርስቲያን_የእምነት_አቋም.pdf14.59 MB
🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
#የመረጃ_ጥቆማ በwavesite በጣም የሚገርም የኋላ  የብዙ ዓመታት አስተማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ያለበት ፣ በኤስ አይ ኤም ከታተመውና ከአዲስ ኪዳን ጥናት ማብራሪያ ተወስዶ በsoftware የተዘጋጀ ለማንበብም ደግሞ በጣም ምቹ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ በቀላሉ በእጅ ስልክ በSoftware ጭነው መጠቀም ለሚፈል ምርጥ የመረጃ ጥቆማ ነው። ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ከplaystore በማውረድ ጭነው መጠቀም ይችላሉ። #Link:-  https://play.google.com/store/apps/details?id=org.armstrong.ika.ethiopiansite እኔ ጓደኞቼን እጅግ በጣም ስለሚወዳቸው መልካም ነገርን ለማድረስ ስመኝ እንደዚህ አደርጋለሁ። እናንተስ ምን ያህል ትወዱኛላችሁ? እስኪ ከወደዳችሁት መልእክቱ ለብዙዎች እንድደርስ #Like , #Comment , #share  አድርጉልኝ ። ጸጋ ይብዛላችሁ። ሁልጊዜም እንደዚህ ከአዳዲስ ነገሮች ጋር እንገናኛለን።
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
👌 2
በጌታ የተወደዳችሁ ቅዱሳን የጌታ ጸጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ። ሁልጊዜ አዳዲስ ወይም ጠቃሚ ነገሮችን ለእናንተ ማድረስ የሁልጊዜ ትጋታችን ነው። ስለዚህ መልእክት ለብዙዎች እንድደርስ #share በማድረግ እንድትተባበሩ በጌታ ፍቅር እናሳስባለን።            👉 በጸጋ ብቻ የዳንኩኝ ነኝ! 👉 #Join_us_and_share https://t.me/Gfapg
Mostrar todo...
የአዲስ ኪዳን ማብራሪያ.pdf55.30 MB
መሰረታዊ የክርስትና ትምህርት .pdf2.45 MB
በውኑ በማርያም ማመን ይገባሀልን_.pdf2.29 MB
ኢየሱስ ክርስቶስ ማነው_.pdf9.30 KB
የብሉይ ኪዳን ማብራሪያ .pdf23.25 MB
የጳውሎስ ህይወት አና ትምህርቱ.pdf3.80 MB
ጋብቻና የትዳር ሚስጥር .pdf1.39 MB
ለሙስሊሞች_ጥያቄዎች_የክርስቲያኖች_መልሶች_.pdf1.43 MB
የካታኮምቡ ሰማዕት .pdf31.13 MB
Repost from N/a
ስለ ጋብቻ እና የወጣቶች ጥያቄ_01.pdf1.51 MB
ስለ ጋብቻ እና የወጣቶች ጥያቄ_02.pdf1.27 MB
ስለ ጋብቻ እና የወጣቶች ጥያቄ_03.pdf1.33 MB
ይህች_አለም_ምን_ትሆናለች_ክፍል_አንድ.pdf1.41 MB
2
    #የሰውን_ነፍስ_መረዳት
=================== የእግዚአብሔር ቃል ስለ ነፍሳችን የሚናገረውን እንመልከት። 1. ነፍስ ፈቃድ፣ እውቀት እና ስሜት የያዘ ነው። 👉 እውቀት፦ “ነፍስ እውቀት የሌለባት ትሆን ያንድ መልካም አይደለም” (ምሳ 19፡2) 👉 ፈቃድ፦ “ነፍሴም ከአጥንቴ ይልቅ መታነቅንና ምትን መረጠች።” (ኢዮ 7፡5) 👉 ስሜት፦ ነፍሴ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይላታል፡ የማዳኑም ሐሴት ታደርጓት፡፡ (መዝ 35:9) 2. በቆይታ የሚድን ማንነት ነው፡ ጌታን ከተቀበልን እና ዳግም ከተወለድን ጊዜ ጀምሮ በመታደስ እየዳነ የሚሄድ የሰው ማንነት ነው። 3. ነፍሳችን የመንፈሳዊውን እና የቁሳዊውን ዓለም ጉዳይ ትርጉም ይሰጣል፡ ነፍስ በመንፈስ እና በሥጋ መካከል የሚገኝ መካከለኛ የሆነ የውስጠኛውን ማንነታችንን ከውጫዊ ማንነታችንን ጋር፤ የውጪውን ማንነታችንን ደግሞ ከውስጣዊ ማንነታችንን ጋር የሚያገናኝ ነው። 👉 እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያነባሉ። ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና መንፈስ  ግን ሕይወትና ሰላም ነው። (ሮሜ 8፡5-6) 👉 በሥጋችን በኩል በአምስቱ ስሜት ሕዋሳት የተገኙ እና በመንፈሳችን በኩል ከመንፈሳዊ ዓለም ያገኘናቸውን ነገሮች ትርጉም የሚያገኙት በነፍሳችን ነው። ሰው መንፈስ በሆነ ማንነቱ መንፈሳዊውን ዓለም ይገናኛል፣ በሥጋው ደግሞ ቁሳዊውን ዓለም ሲገናኝ፣ በመንፈሳዊውም ሆነ በሥጋዊው ዓለም ውስጥ የተገናኛቸውን ነገሮች ደግሞ ትርጓሜ የሚሰጠው በነፍሱ አማካኝነት ነው። ነፍስ ሰውን ሕያው የምታደርግ የሰው አካል ናት።
የነፍስ መዳን
=========== ብዙ ሰዎች ጌታን ከተቀበልኩ በኃላ እንዴት የአሮጌው ሰው ነፍስ እውቀት፣ ስሜትና ፈቃድ በእኔ ሊገለጥ ቻለ? ከየትስ መጣ? ለምንስ እነዚህን ለማስወገድ የሰው ድርሻ ብቻ ሆነ? በማለት ይጠይቃሉ። 👉 እስኪ ለእነዚህ ጥያቄዎች ተገቢ የሆነውን መልስ እንመልስ። የነፍስ ከፍሎች የተገነባው በኃጢአት በተበከለ ሕሊና፣ በአምስቱ የስሜት ህዋሶች፣ በቤተሰቦቻችን፣ በጓደኞቻችን፣ በባህላችን ወዘተ የተገነባ ነው። የሰው የማንነት ትክክለኛ ትርጉም ያለው በአምላኩ ቃል ውስጥ ነው። ነፍስ በሰላም መኖር የምትችለውም የእግዚአብሔርን ቃል ስትመገብ ብቻ ነው። በሰው ነፍስ ውስጥ ከወደቀው ዓለም የተዘራ ከፋት ስር የሰደደም የጨለማ ሀሳብ አለ። ይሄንን ስር የሰደደና የተንሰራፋን ከፋት መንቀልና ነፍሳችንን ማዳን የሚችለው የእግዚአብሔር ቃል ነው። ● ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፡ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ።"(ፊል 2:12) • “ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።”(ያዕ 1፡21) • “የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።”   (ሮሜ 12፡2) 👉 ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ” (ኛ ጴጥ 2፡2-3) 👉 ሰው በአስተሳሰቡ ምክንያት ከእግዚአብሔር ዓለም ውጭ ሆኖ በሰይጣን አገዛዝና ሥልጣን ስር ሲመላለስ ነበር(ኤፌ 2:1-2)። የነበረበት መንግሥት ደግሞ የራሱ የሆነ ስርአት፣ ባህርያቶችና የተለያዩ የውድቀት ልምዶች ነበሩበት። እኛም በዚህ ስርአትና የሕይወት ልምምድ እንድንጓዝ ስንገፋፋና ክፋትን ስናደርግም ኖረናል። ይህ ስርዓት በምልልሳችን ላይ ይህ ነው የማይባል አሻራ አሳርፏል። 👉 ጌታን ስንቀበል መንፈሳችን በቅጽበት ዳግም ሲወለድ፤ ነፍሳችን (አእምሯችን) ግን በእውቀት በኩል ወደ ውስጥ ያስገባቸውን የጨለማውን ዓለም እውቀት ለማስወጣት የብርሃን እውቀት እና ጊዜ ያስፈልጋታል። የነፍስ መዳን በአንድ ጀምበር የሚቋጭ ሳይሆን በሂደት (Through Process) የሚሆን ነው። ነፍስ ውስጥ የገባውን የጨለማ እውቀት አፍርሰን የብርሃንን እውቀት መገንባት የምንችለው ሁልጊዜ የእግዚአብሔር ቃል መማርና ማወቅ እንዲሁም መሞላት ስንጀምር ነው። 👉 ጠቅለል ስደረግ:- ነፍሳችን ዕውቀት፣ ስሜት እና ፈቃድ የያዘ የማንነታችን ክፍል ነው። በእግዚኣብሔር ቃል የሚድን ማንነታችን ነው። ስለ ራሳችን እውቀት (Self Awareness) እንዲኖረን የሚያደርግ ነው። • የእግዚአብሔር ቃል ስለ ነፍሳችን የሚናገረው፦ ✓ ፈቃድ፣ እውቀት እና ስሜት የያዘ ነው። ✓ ነፍሳችን የመንፈሳዊውን እና የቁሳዊውን ዓለም ጉዳይ ትርጉም ይሰጣል • ነፍስ ስብዕና፣ አመክኗዊ አስተሳሰብ፣ ስሜት፣ አእምሮ፣ ፈቃድ አቀናጅቶ የያዘ የሰው ክፍል ነው። • እውቀት፣ ፈቃድና ስሜት እርስ በእርሳቸው በመያያዘ የሚሰሩ ነገሮች ናቸው። • የነፍስ መዳን ግን ልክ ስናምን በቅፅበት የሚቋጭ ሳይሆን እለት ተለት በእግዚአብሔር ቃል እየታደሰ የሚድንና ወደ ፍጹምነት የሚመጣ ነው። • የነፍሳችንን መዳን በሶስት መንገዶች እንፈጽማለን ✓ የእግዚአብሔርን ቃል ማወቅና መሞላ ✓ የእግዚአብሔርን ቃል ማሰላሰል፤ ✓ የእግዚአብሔርን ቃል ማድረግ ነው፤ #ይቀጥላል.......🗣🔊📣 #ሼር_አድርጉ ❤❤❤
Mostrar todo...
👍 1🙏 1
መሐሉን እስከሚናገኝ አንብቡ ተባረኩ #ሼር_አድርጉ 💕🙏🙋
Mostrar todo...
ተሐድሶ 2.pdf6.23 MB
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.