cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ግጥም እና ታሪክ

📖 የታሪክ ቤተ - መዛግብት 🏡 🌍ከዓለም ዙሪያ የተዉጣጡ እጅግ ማራክ የሆኑ አጫጭር እና ረጃጅም የፍቅር ታሪኮች ልብ አንጠልጣይ ልብ ወለዶች እና የታዋቅ ሰዎች የህይወት ታሪክ እንዲሁም አጠቃላይ አዝናኝ እና አስተማሪ የሆኑ ድንቅ ታሪኮች በሙሉ ዘወትር በተወዳጅ መልክ ወደ እናንተ ይቀርባሉ።🌺

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 623
Suscriptores
+1124 horas
+1597 días
+52030 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
🔥🔥  በጉጉት ሲጠበቅ የ ነበረው የ 👑ቴዲ አፍሮ 👑አልበም እጃችን ገብቶል 🔥🔥 በዚ ያለቀቅነው በ #COPYRIGHT ምክኒያት ነው አልበሙ #14TRACK የያዘ ሲሆን ወደ ሁለተኛ ቻናላችን ተቀላቅለው ያጣጥሙት😍😍 ቻናሉን #Join በማለት ይቀላቀሉ 👇
Mostrar todo...
ሙሉ አልበም
ለማየት
Mostrar todo...
Logo maker

Hi , I am and editor and artist I can add name in a photo,I can make logo regarding profile picture,YouTube banner Business card and I can do intro for your channel If you want anything ask me

https://t.me/logomaaker

Any comment or you want cross @Eyuul

🥰 1
የልብ_ነገር_ክፍል_ሁለት_ፀሐፊ_ዳንኤል.doc3.20 KB
👍 2
የልብ_ነገር❤❤❤              ክፍል_ሁለት ፀሐፊ ዳኒኤል✍✍✍ *** ጀግናውን ልቤን ከስንቱ ወዛም የሸፈንኩትን ዛሬ ጣለችው፣ ለነገ ብዬ ያስቀመጥኩትን። አለምን ሁላ በምህዋሬ እንዳላዞርኩት ተከታይ ሆንኩኝ፣ ወደድኳት ላልኩት። *** ከአራት አመታት በፊት ፌሪ በምትሰራበት የእርዳታ ተቋም አማካኝነት የትምህርት እድል አግኝታ ስትፍለቀለቅ ወደ‘ኔ መጣች። ቢሮዬ ውስጥ ቁጭ ብዬ ልጅ ስለመውለድ እያሰብኩ፤ በያዝኩት ብዕር የማላውቀውን ቅርፅ ማስታወሻዬ ላይ እየሳልኩ ነበር። የቢሮዬ በር ተበረገደ። ፀሀፊዬ ሳትደውልልኝ የቢሮዬ በር በዚህ መልኩ የሚበረገደው ማን ሲመጣ እንደሆነ አውቀዋለሁ። ባለስልጣኗ ስትመጣ ነው። የልቤ ባለስልጣን! ሚስትየዋ! «ፋሚዬ የኔ ... አሰላሙአለይኩም!» ተጠመጠመችብኝ። «ወአለይኩሙሰላም ፌሪዬ!» ታፋዬ ላይ ተቀመጠች። በሁለት እጆቿ ጆሮዎቼን ይዛ «ዛሬ በጣም ደስ ብሎኛል ... ገምት ለምን ይመስልሀል?» አለች። «አረገዝሽ?» ከማልፈልገው መልስ እየሸሸሁ እንጂ አርግዛ እንዳልሆነ አውቃለሁ። «እረፋ! ሌላ ሌላ!» ፈገግታዋ እና የአይኖቿ ጨረሮች አስገደዱኝ .... ማለት የማልፈልገውን እየቀፈፈኝ አልኩት። «የትምህርቱ ነው አይደል ... » «አዎ ... ተመረጥኩኝ!» ተፍነከነከች። ፊቴ ጨለመ። «ፋሚ ደግሞ ተስማምተን አይደል እንዴ!» ከላዬ ላይ ገፍቼያት ተነሳሁ። በመስታወቱ በኩል ወደ ውጪ መመልከት ጀመርኩ። ከኋላዬ መጥታ አቀፈችኝ። «ለሁለት አመት ብቻ እኮ ነው!» «ሁለት አመት ላንቺ ትንሽ ሊሆን ይችላል። ለኔ ግን ዘለዓለም ነው እሺ! ዘለዓለም!» ተናደድኩ። «ድጋሚ በዚህ ጉዳይ ልንከራከር ነው?» አኮረፈች። ስታኮርፍ ይጨንቀኛል። ጨረቃን በበትር ያረገፍኩ፤ ፀሀይን ከምድር የሸፈንኩ አይነት ኃጢያተኝነት ይሰማኛል። ወደወንበሬ እየተመለስኩ «ስለምፈራ እኮ ነው!» አልኳት። «ምኑን ነው የምትፈራው?» «መራራቅ መጥፎ ነው ፌሪዬ! ትቀየሪብኛለሽ ብዬ እፈራለሁ።» «እምልልሀለሁ አልቀየርም!» «ትናፍቂኛለሽ!» «ሁሌ እደውላለሁ! ቀኑን ሙሉ!» ይህን የትምህርት እድል ለረዥም ጊዜ ስትመኘው እንደቆየች አውቃለሁ። የሷን ደስታ መከልከል ልቤን ከብዶት እንጂ መሄዷ ህይወቴን እንደሚያቃውሰው አውቀዋለሁ። ቢሆንልኝ ልጅ ወልደን ተረጋግተን ብንኖር እመርጣለሁ። ግን ደግሞ ስትከፋ ማየት ይጨንቀኛል። የህይወቴን የተሳሳተውን ውሳኔ በፍቅር ስም ወሰንኩ። የፌሪ የአየር ቲኬት መጣ። ስህተትነቱን እያወቅኩ ሁሉነገሬን ሸኘኋት! ፌሪዬ ወደ ውጪ በሄደችበት የመጀመሪያው አመት በቻልነው መጠን በቪዲዮም ሆነ በቴክስት ያለማቋረጥ እናወራ ስለነበር የናፍቆት ህመሜን ቢጠናም እያስታገስኩ ነበር። ሁለተኛው አመት ግን ለእኔም ለእሷም ከባድ ነበር። ፌሪዬ ለእኔ ጊዜ አጣች። ስደውል ሀሌም ቤተመፅሀፍት ናት። ይህም ሳይበቃ ስራ ጀመረች። ቀኑን ሙሉ የምናወራው ቀረና በሳምንት አንዴ .... በወር ጥቂት ቀናት መሆን ጀመረ። በስሜቴ እሳት መንደድ ጀመርኩ። *** ሰው የሚፈተነው በሚወደው ነው ይላሉ። እኔ ደግሞ እላለሁ ...  ሰው የሚፈተነው ስለፍቅር ሲል ዝቅ በሚያደርጋቸው ጥንካሬዎቹ በኩል ነው። ፉአድ አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ሶስት አመት ሙሉ ይቆያል ቢባል ማን ያምናል? ማንም! ግን ሚስትየዋ ፌሪ ሆነች! ሁሉ ነገሬን ተቆጣጠረችው። ቆፍጣናውን ፉአድ በፍቅሯ ምርኮኛዋ አደረገችው። በተጋባንበት አመት የወሊድ መቆጣጠሪያ እየተጠቀመች እንደሆነ ነገረችኝ። ደነገጥኩ። «ለምን?» በግርምት ጠየቅኳት። «አሁን መውለድ አልፈልግም!» «እኮ ለምን? ምን ችግር አለው ብትወልጂ?» «ፋሚዬ ብዙ ብዙ ነው ልወልድልህ የምፈልገው ... ግን አሁን አይደለም። እንደሌሎቹ ሴቶች መሆን አልፈልግም!» «ፌሪዬ የምታወሪው ነገር ምንም ግልፅ እየሆነልኝ አይደለም!» «ሴቶቹን እያቸው እስኪ! ይወልዳሉ ከዚያ በቃ ከመኖር ነው የሚጠፉት! ለባላቸውም እንደድሮው ሳቢ አይሆኑም! ደግሞ ማስተርሴን ሳልሰራ አላገባም። ደግሞም ስንወልድም እንደነሱ መሆን አልፈልግም። የአሁኗን ፈሪሀ ነው መምሰል የምፈልገው!» «መውለድን ከመማር ጋር ምን አጋጨው?» «እንደሱ እያላችሁ ነው የምታጭበረብሩን ባክህ! መውለድ ቀላል አይደለም። ትልቅ ሀላፊነት ነው። ከመውለድ በኋላ ደግሞ ማሳደግ የሚባል ነገር አለ። ይለጠጣል ነገሩ! ቶሎ ማስተርሴን ልጨርስና እንወልዳለን!» ከሁለት አመት አይዘልም ያልኩት መውለድ ውጪ ካልሆነ አልማርም የሚል መስፈርት ታክሎበት የውጪ እድሉን እስክታገኝ ሶስት አመት ሙሉ ጠበቅን። ሶስተኛው ዓመት ላይ ግን የቤተሰብ ጭቅጭቅ ሰላም ስለነሳኝ እንድንወልድ ወደመወሰኑ ተቃርቤ ነበር። ምን ያደርጋል ይኼ የተረገመ የትምህርት እድል መጥቶ ሰላማዊ የፍቅር ህይወቴ ላይ መሰናክል ሆነብኝ! ይቀጥላል!.... . ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን! . t.me/gitim1 @gitim1 t.me/gitim1 @gitim1
Mostrar todo...
3
Photo unavailableShow in Telegram
የልብ  ነገር አዲስ አሳዛኝ የሆነ ልብ አንጠልጣይ ታሪክ እንደተለመደው በፀሐፊ ዳኒኤል የቀረበ ክፍል አንድ SHARE LIKE COMMENT JOIN
Mostrar todo...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የልብ  ነገር አዲስ አሳዛኝ የሆነ ልብ አንጠልጣይ ታሪክ እንደተለመደው በፀሐፊ ዳኒኤል የቀረበ ክፍል አንድ SHARE LIKE COMMENT JOIN
Mostrar todo...
╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗ ║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣ ╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝ 👉The Best Islamic  Channel On               Telegram ‼            ┏━━━━━━━━┓        🌹👀 ፍቅርን በፍቅር. 🌹             ┗━━━━━━━━┛             ┏━━━━━━━━┓      🌹ምርጥ ምርጥ ታሪኮች🌹             ┗━━━━━━━━┛             ┏━━━━━━━━┓           🌹    ለወጣቶች  🌹             ┗━━━━━━━━┛                       ┏━━━━━━━━━┓     🌹 አጫጭር ግጥሞች 🌹          ┗━━━━━━━━━┛                      ┏━━━━━━━━━━━┓   🌹 አጫጭር የቁርዓን አያወች 🌹         ┗━━━━━━━━━━━┛                ┏━━━━━━━━━┓            🌹 ጣፋጭ ንግግሮች 🌹                ┗━━━━━━━━━┛                      ┏━━━━━━━━━━┓      📖 የነብያቶች ሙሉ ታርክ 📖           ┗━━━━━━━━━━┛ 🌹. ምርጥ ኢስላሚክ ቻናል የሚፈልግ ብቻ! Wave @wase_vip1
Mostrar todo...
🆕Full Album 👤 Eminem 💽 The death of Slim Shady #19Tracks የEMINEM ሙሉ አልበም በሙዚቃው ቻናል ተለቋል
Mostrar todo...
Eminem - Somebody Save Me.mp38.91 MB
JOin FS Music
┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓           ". #አይናፋሯ_ሊና ".            ✎ፀሐፊ ፦ ዳንኤል✍ ┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛            ┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒ .  በ t.me/gitim1 የቀረበ .         . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ. ┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚ ┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯          #ክፍል_ሁለት {❷} ┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷ ...ኢብሮ ጉድህን እያየህ ነው ስትል ወደ አንድ ልጅ አፈጠጠች ክፍል ውስጥ ያሉ ተማሪዎች በሙሉ  ሳቁ ሊናም ደንግጣ ከክፍሉ ወጣች  ደረጃውን መውረድ ስትጀምር አንድ አስተማሪ አገኛት ወዴት ነው ሊና እ እ አስተማሪ ስለሌለ ላይብረሪ ልገባ አስቤ ነው ስንት ነሽ 11/8 ኦ እዛ እኔ ነኝ የምገባው ባሁኑ አመት ላስተምርሽ ስለሆነ ደስ ብሎኛል ነይ ተመለሺ አላት እሷም ምን አይነት እድል  ነው ኡፍፍ አለች በውስጧ አስተማሪው ከፊት እሷ ከኋላ ወደ ክፍል መሄድ ጀመሩ ተማሪዎቹ አሁንም መንጫጫታቸውን አላቆሙም አስተማሪው ሲገባ ሁሉም ቁጭ አሉና ዝም አሉ ሊናም ወደ ውስጥ ስትገባ ሳቁ የመጀመሪያ ወንበር ላይ ከአንድ ልጅ አጠገብ  ተቀመጠች  እስከ ሶስተኛው ተምረው የዕረፍት ሰአት ጥሪ ተሰማ አስተማሪው ክፍሉን ለቆ ወጣ እዛው ወንበሯ ላይ ጋደም አለች ከዛም አይናፋሯ ዘንድሮም አይናፋር እያሏት ይወጣሉ አንዱ ልጅ ተነስቶ አይናፋርነቷ ዘንድሮ የቀረ ይመስለኛል ቆይ የምን አይናፋር ነው ሲል ኢብራሂም አጠገቡ ያለውን ጓደኛውኝ ረሚዝ ጠየቀው ረሚዝም ይቺ ልጅ ስሟ ሊና ነው እናም ትምህርት ቤት ውስጥ ማያውቃት የለም በጣም በጣም ጓበዝ ተማሪ ናት ከምታስበው በላይ በዛ ላይ በጣም አይናፋርና ዝምተኛ ናት ልክ እንዳንተ  መናገር ብዙ ማውራት አትወድም ኧረ እሷ ጭራሽም ማውራት አትወድም አለው  እሱም በረጅሙ ኡፍፍፍ ብሎ ከተነፈሰ በኋላ እንደገባው   አንገቱን ከፍ እና ዝቅ በማረግ ገለፀለት ረሚዝም ና እንውጣ አይ አይ እዚህ ልሁን እሺ በቃ እኔም አብሬህ እሆናለሁ  ጥሩ በቃ ኢብራሂም ይባላል አዲስ ተማሪ ነው በጣም ዝምተኛ ነው እንደሊና እናም  ሴት ይፈራል አጠገቡ ስትቀመጥ ሚሆነው ነው የሚጠፋው በቃ በጣም ይፈራል ሁለት ታላቅ እህትና ታላቅ ወንድም አለው የመጀመሪያዋ ረዲና ልጅ ወልዳለች ቤተሰብ ከመሰረተች ቆየች ቀጣይ ደግሞ ሀያት ናት እሷ የኮሌጅ ተማሪ ናት ቀጣዩ ኦስማን ደግሞ ትምህርት አቁሞ የግል ስራ መስራት ጀምሯል ከቤቱ ሁሉ ዝምተኛ ኢብሮ ነው ሌሎቹ አይደሉም ሊና እምባዋ መጥቷል በጣም አስጠልቷታል አዲሱ ክፍሏ ተማሪዎች በዛ ላይ ፋኢዛ አለመኖሯ ሁሉ ነገር አስጠልቷታል መስኮቱን ከፍታ ቆመች ኢብሮና ረሚዝ እያወሩ እያለ  ኢብሮ የሊናን ፊት እየው ዛሬ ደሞ አይ ሊኑ ስታሳዝን እኮ  የምር አላቅም እኔ የቤተሰብ ችግር ያለባት ይመስለኛል አለ ልክ ኢብሮ ወደ ሊና ሲዞር እምባዋ ጠብ ጠብ እያለ ነው ኧረ ረሚዝ እያለቀሰች ነው ሄደህ  ጠይቃት አለው እሱም እስኪ እሺ እድሌን ልሞክር ብሎ ወደ ሊና ሄደ... ⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊ ╬╬═════════════╬╬    #ክፍል_ሶስት {❸} ይቀጥላል ╬╬═════════════╬╬ ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን! ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤    t.me/gitim1 @gitim1    t.me/gitim1 @gitim1 ╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
Mostrar todo...
👍 4
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.