cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

CHUCHU(Beki b)

Inbox Manager Yemtfelgu @bekib2

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
168
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄😂😂 & Invite ur Friends👇👇 https://t.me/joinchat/TUu8EbLtHiL6Wxd5 😂•═• @tiktok_addis •═•😂
Mostrar todo...
ede23cc58bcd47e2b87bdc6ab5d70dcd.mp41.08 MB
#𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄😂😂 & Invite ur Friends👇👇 https://t.me/joinchat/TUu8EbLtHiL6Wxd5 😂•═• @tiktok_addis •═•😂
Mostrar todo...
3.92 MB
#𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄😂😂 & Invite ur Friends👇👇 https://t.me/joinchat/TUu8EbLtHiL6Wxd5 😂•═• @tiktok_addis •═•😂
Mostrar todo...
5ca0ffca11404358bd8647801962c668.mp46.53 MB
#𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄😂😂 & Invite ur Friends👇👇 https://t.me/joinchat/TUu8EbLtHiL6Wxd5 😂•═• @tiktok_addis •═•😂
Mostrar todo...
a3348e3739bc42938227ec99e81ae496.mp49.25 KB
#𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄😂😂 & Invite ur Friends👇👇 https://t.me/joinchat/TUu8EbLtHiL6Wxd5 😂•═• @tiktok_addis •═•😂
Mostrar todo...
aa88e9e2a0ae4602965604c9af871608.mp48.55 MB
እሷ=ናፍቀህኛል!?😞 እሱ=ኧረ ባክሽ?😒 እሷ=የምሬን ነው!💗 እሱ=እሽ።😐 እሷ= ይቅርታ..?🙏 እሱ=ለምኑ?😐 እሷ=እኔ ጋር ለመቅረብ በጣም ጥረት ስታደርግ ስለዘጋዉህ…😰 እሱ=ችግር የለዉም… ከጊዜ ጋር ለመድኩት…እናም ደከመኝ… መሞከሬን ትቸ መርሳት ጀመርኩ…🙌 እሷ= እኔ…እኔ…ስለ አንት አለማሰብ ሞክሬ ነበር…እና…አብረን ልንሆን…😟 እሱ= ችግር የለዉም!🙏 እሷ=ማለት?😟 እሱ=ለምጀዋለሁ..አንድቀን ወደኔ ትመጫለሽ እያልኩ ተስፋ አድርጌ ነበር ግን አልመጣሽም ነበር እና እኔ እዉነቱን መጋፈጥ ጀመርኩ…እና ወደፊት መራመድ እንዳለብኝ አመንኩ…🙏 እሷ= ቆይ…እና በጣም ረፍዶብኛል?😥😓 እሱ=ለምኑ ነው በጣም የረፈደብሽ?😐 እሷ=ካንተ ጋር ለመሆን..?💞❤️ እሱ=ታዉቂያለሽ?ይህን ካንች መስማት እፈልግ ነበር ግን ከአመት በፊት ነበር…በተስፋ አንችን ስመኝ… ግን ሊሆን እንደማይችል ተረዳሁ ከዛ ተስፋ ማድረጌን መመኘቴን አቆምኩ…💔🚫‼️ እሷ= በጣም ይቅርታ… አትጨነቅ… አሁን ግን ምኞትን ሁሉ አሳካልሃለው:)💏💝💘 እሱ=ያ ሊሆን እማይችል ነው… ሌላ ሰው በሂወቴ ገብቷል…💕 እሷ= ላንተ ጥሩ ነው…ማን ናት?መቼስ ነው እምገናኛት?😓❓ እሱ=መቼም ቢሆን ልታገኝሽ አትፈልግም!!‼️❌ እሷ=ለምን?ምን አድርጊያት አለሁ?🤔❓ እሱ=በቃ ልታይሽ አትፈልግም!❗️ እሷ=ቆይ እሽ ለምን?❓❓ ልጁም ቀስብሎ መለሰላት… እሱ= በቃ በጣም የጎዳችኝን ሴት ልታገኛት አትፈልግም… አሁን ይቅርታ ማያው ተራው የኔ ነው… ጊዜ በኔ ላይ ስለሆነ…ልቤን ሲጀመር ሰብረሽዋል እና ያን ድጋሚ ማሳለፍ ፣ ልቤን አደጋ ላይ መጣል አልችልም… ለማንኛዉም አመሰግናለሁ… ከአመታት ዝምታ በኋላ ስላናገርሽኝ…።🙏 😭እሷም አንገቷን ደፍታ በዝምታ ሄደች😔💔 ከሄደች በኋላ እሱም ከዋሌቱ የነበረዉን የሷን ፎቶ አዉጥቶ አነባ እናም ፎቶዉን ወደአፉ ጠጋ አርጎ "አሁንም አንች ነሽ" አለ።🖤 👉ልጁ ያልተቀበላትም የካንሰር በሽታ እንዳለበት እና በሁለት ወራት ዉስጥ እንደሚሞት ስለተነገረው ነበር።🙏😔🖤🖤💔🖤 በዚች አለም ትልቁ እና ዋጋ ያለው ነገር ጊዜ ነው!ለዝች አለም ሁላችንም እንግዶች ነን መቼ እና እንዴት እንደምንሞት አናዉቅም!ስለዚህ በቻለነው መጠን ጊዜችን በአግባቡ እንጠቀም ልቦናችንን እንክፈት…በእጅ ያለ ወርቅ እንደ መዳብ ይቆጠራል!! @
Mostrar todo...
እንኳን አደረሰህ/ሽ አዲሱ አመት🌻🌻 🏵️ያቆምከውን/ሽውን የምትቀጥልበት/ይበት 🌼የምትቀጣጠልበት/ይበት 🏵️የምትጨምርበት/ሪበት 🌼ክርስቶስን ይበልጥ የምታውቅበት/ቂበት 🏵️ከእርሱ ጋር ፍቅር በፍቅር ምትሆንበት/ኚበት 🌼ከጓደኛ በላይ የቅርብህ የምታደርግበት/ጊበት 🏵️ሰማይ ሰማይ ምትሸትበት/ቺበት 🌼በየስፍራው አምላክህን ምታስቀድምበት/ሚበት 🏵️ያሸነፈህን/ሽን ምታሸንፍበት/ፊበት 🌼አልጋፋ ያለህን/ሽን ምትገለብጥበት/ጪበት 🏵️ተስፋ ማትቆርጥበት/ጪበት 🌼ካሰብከው/ሽው በላይ ምትከናወንበት/ኚበት 🏵️እንደ አንበሳ ሞገሳም የምትሆንበት/ኚበት 🌼እንደ ንስር ከፍ የምትልበት/ይበት 🏵️አለምን የምታስደምምበት/ሚበት 🌼ራዕይህን ምታሳካበት/ኪበት 🏵️ፍጥረት አፉን ከፍቶ ሚሰማህበት/ሽበት 😍ይሁንልህ/ይሁንልሽ😍 ❤️ውድድድድድድድ…… አደርግሃለው/ሻለው❤️ 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 ይሄን የእንኳን አደረስዎ መልዕክት ቢያንስ ለሚወዱት 15 ሰው በማድረስ መልካም ምኞትዎን ይግለፁ።
Mostrar todo...
ነገር ጋር የተገናኘ አይመስለኝም…ማለቴ ከእነሱ ጥሩነት እና መጥፎነት ጋር… ከእነሱ ሀብታም መሆንና ድህነት ጋር….ከእነሱ የትምህርት ደረጃቸው ጋር አዎ ከእነዚህ ሁሉ ነገር ጋር የተገናኘ አይደለም..ዝም ብሎ ምከንያት አልባ ነው… ተፈጥሮዊው ብቻ…በደም ትስስር እና በነፍስ ቁርኝት የተገመደ ዝም ብለህ የምትቀበለው ሚስጥራዊ ጥምረት ነው..ለዛ ነው ሁለችንም ሳናስበው በዚህ ፍጥነት የተቀበልነው…በዚህ ፍጥነት ይቅር ያልነው..፡፡ ካንተ በስተቀር ሁላችንም ጋር ያለው ስሜት ተመሳሳይ ነው..እርግጥ የእኛን ካንተ ጋር ማወዳደራችን አይደለም …ግን ያው አባትነቱ ለሁላችንም እኩል ነው…አየህ አሁን እሱን ይቅር ብለነው ወደ ህይወታችን እንዲቀላቀል ካልፈቀድንለት ወደፊትም ባለው ሙሉ ህይወታችን ስለአባት ያለን ትዝታ ባዶና ጥቁር ብቻ ሊሆን ነው…ለልጆቻችንስ ምን እንነግራቸዋለን….?ስለአባታችን ሲጠይቁን ምንም የምንላቸው ነገር አይኖረንም..ይሄ ቀላል ይመስልሀል ?››› ቀኝ አጅን ከግራ ወደ ቀኝ በማወናጨፍ ፈጽሞ ይቅር ልለው እንደማልችል ደግሜ አስረዳውት እሱም የማሳመን ጥረቱን ቀጠለ‹‹አይ እኔ ምንም እንድትለኝ አልፈልግም…. ስለውሳኔህ እንድትነግረኝ አልፈልግም…እኔ እንዳልኩህ የውስጤን ነግሬህ ብቻ መሄድ ነው የምፈልገው….. አየህ አብዛኛውን ነገር ነግሬሀለው ግን አንድ ነገር ይቀረኛል..እናቴን በተመለከተ ..እናቴ እሱ ላይ እርግጠኛ ሁን ጥላቻ የላትም..ያን ያህል ቢበድላትም ግን አሁንም ይቅር ልትለው ትፈልጋለች..እንደውም በውስጧ ድሮ ገና ድሮ ይቅር ያለችው ይመስለኛል..አሁን እሷ ላይ የሚታው ንዴት ነው…ከፍተኛ ንዴት…አየህ ቅድም እንደነገርኩህ ከሁላችንም በላይ አንተን ጎድተቶሀል አቁስሎሀል..ግን ያ እውነት የሚሆነው ከእኛ ከልጆቹ ጋር ሲነፃጸር ብቻ ነው..ከእናታችን ጋር ሲነፃፀር ግን በአንተ ላይ ያደረሰው በደል ትንሽ ነው…አየህ ፍቅሯን ነው የነጠቃት… አራት ልጆቾን ነው ብቻዋን እንድታሳድግ በትኖባት የሄደው..ያለ ባል ነው ይሄን ሁሉ አመት እንድትኖር የፈረደባት…ሌላ ወንድ ላፍቅር ብትል እንኳን አትችልም.. ማን ነው አራት ልጆች ያሏትን ሴት ሚስቴ ብሎ የሚቀበለው.. ..አልፎ አልፎ ነበር የእሱ አለመኖር በውስጣችን የፈጠረው ሽንቁር የሚታወቀን፣ምክንያም እሷ ለደስታችን በየእለቱ ትፈለምልን ነበር …ለሳቃችን በየደቂቃው ትዋደቅልን ነበር…ሀዘኑን ሁሉ ለብቻዋ ውጣ ወደ እኛ እንዳይደርስ ግድግዳ ሆና ትከላከልልን ነበር….ችግር ወደቤታችን እንዳይገባ በፅናት ስትታገል ነው የኖረችው… እሷ ግን ይሄንን ሁሉ አመት በሀዘን እንደተለበለበች ነበር….ግማሽ እድሜዋን በፍቅር ክህደት የተጎዳ ልቧን እየመረቀዘባት ..ከምርቅዙ የሚመነጨውን መግል እየጠረገችና እያስታመመች የኖረች ሚስኪን ሴት ነች..ለልጆቾ ስትል መስዋዕት የሆነች ሴት …በተለይ ለአንተ ስትል መስዋዕት የሆነች ዕንቁ እናት ነች..እና አሁን እኔ አንተን ብሆን ለእሷ ስል መስዋዕት እሆን ነበር….›› ግራ ጋባኝ… አባባሉ እንዴት ነው?እንዴትስ ነው ለእናቴ ስል መስዋዕት ልሆን የምችለው..?እርግጥ ነው ለእናቴ ጥቂት ደስታ ማምጣት ከቻልኩ ህይወቴን እንኳን በመስጠት መስዋዕት ለመሆን አላቅማማም..ምክንያም ይህ ህይወቴ ይሄን ሁለ ዘመን በዚህ ምድር የኖረው በእናቴ ብርታትና ጥንካሬ ነው፣..ሀርሜ ኮ የህልውናዬ መሰረት ሁሉ ነገሬ ነች… …ወንድሜ ቀጥሏል‹‹አየህ ከልብህ እንኳዋን ባይሆን አባትህን ይቅር ብትለው ለእናታችን ትልቅ ነገር ይመስለኛል…አየህ አንተ ይቅር ማለትህን ካወቀች እሷም ይቅር ማለት አይከብዳትም… ያንን ደግሞ እንደምታደርግ በቃሏ አረጋግጣልናለች..አንተ ከእሱ ጋር መቀራረብ ብትጀምር እሷም ሁሉን ነገር ረስታ እንደአዲስ ትቀርበዋለች..እና ደግሞ በሂደት አንተ ከእሱ ጋር አንድ ላይ መኖር ብትፈቅድ እርግጠኛ ነኝ እሷም በደስታ ታደርገዋለች...አየህ እንዴት እንደሚሆን …ለእናቴ ደስታዋን መመለስ ምትችለው አንተ ነህ…ለእናቴ ከዘመናት በፊት የቆሰለ ልቧ እንዲጠገን መንገዱን ማመቻቸት የምትችለው አንተ ብቻ ነህ… እናቴን ዳግመኛ መዳር የምትችለው አንተ ብቻ ነህ..ግን ይሄንን የግድ ማድረግ የለብህም የምታደርገው ከፈለግክና ውስጥህ በትክክል ከተቀበለው ብቻ ነው...በል ይበቃኛል ..ይሄንን ብቻ ልልህ ነው የመጣውት አለና ከተቀመጠበት ተነስቶ በፍቅር ግንባሬን ስሞ እኔን በውጥረት ለተሞላ ሀሳብ ውስጥ ሰንቅሮኝ ጥሎኝ ሄደ እሱ ከሄደ ቡኃላ ለረጅም ስዓት በፍዘት አሰብኩበት ..በመጨረሻ ግን ወንድሜ የተናገረው ሁሉ በጣም ትክክል ሆኖ ነው ያገኘውት…ታናሽ ወንድሜ ቢሆንም ከእኔ በጣም የተሸለ ነገር ማሰብ በመቻሉ ኮርቼበታለው..እኔ ይሄን ጉዳይ በተመለከተ እራስ ወዳድ እየሆንኩ እንደሆነ እንዲሰማኝ አድርጎል ..አባቴን ይቅር ማለት እና አለማለት ከእኔ ፍላጎት አንጻር ብቻ ነው ያየውት ..የእኔ ከእሱ ጋር ሰላም አለመፍጠር ወንድሜንና እህቶቼን እንደሚረብሽ አስቤው አላውቀውም ነበር..ከሁሉም በላይ ከእናቴ አንጻር ማሰብ ነበረብኝ….ሰሞኑን አይኖቾ ውስጥ ለጣር የቀረበ ስቃይ አንብቤለው….. ስትፈዝና በተቀመጠችበት ስትደነዝዝ በተደጋጋሚ ጊዜ መታዘብ ችያለው…አዎ እርግጠኛ ነኝ ወንድሜ እንዳለው ሰውዬውን ቀድማ ይቅር ብላዋለች..እንደውም የናፈቃት ሁሉ ይመስለኛል… ልታወራው የጓጓች ..ብዙ ብዙ ጥያቄዎች ልትጠይቀው ፈለገች…..እና ልታቅፈውና ልትስመው የምታልም..ግን እኔ በብረት እና በእርማታ ተቀይጦ የተሰራ ጥብቅ ግድግዳ ሆኜባታለው..አዎ በመሀከላቸው የተደነቀርኩት ጋሬጣ እኔ ነኝ፡፡ እድሜ ለወንድሜ አሁን ሁሉ ነገር ፍንትው ብሎ ተገልፆልኛል……ስለዚህ ይሄን ሰውዬ ባልወድም ይቅር ልለው የግድ ነው..ለእናቴ ስል ..፡፡ደግሞ እንደዛ ማድረጌ ለራሴም ጤና ጥቅም ይኖወረዋል መቼስ ጥላቻና ቂም አፍራሽ ስሜቶች ናቸው ..በውስጤ ያለውን ፍቅር እና ተስፋ ያጨለሙታል እንጂ ሌላ እርባን አይኖራቸውም …ስለዚህ እጄን ጎኔ ወዳለው ኮመድኔ ላኩና እስኪሬብቶና ወረቀት ስቤ አነሳው… ‹‹ሰውዬውን ላገኘው ፈልጋለው››ብዬ ጻፍኩና ራስጌዬ ያለውን መጥሬያ ተጫንኩት… በሁለት ደቂቃ ውስጥ ትርሲቴ እየበረረች መጣች ‹‹ወይኔ ፍቅር ረሳውህ አይደል? ማዕድ-ቤት ስራ ይዤ እኮ ነው..ልጅቷን እያገዝኮት ነው..ትንሽ ነው ቀረኝ ከዛ መጣና ዘና እንላለን…›› የእሷን ንግግር ችላ ብዬ ወረቀቱን አቀበልኮት…ተቀበለቺኝና አነበበችው‹‹የቱን ሰውዬ..?አባትህን?›› ግንባሬን በመነቅነቅ እሱን መሆኑን አረጋገጥኩላት ተንደርድራ መጥታ ከንፈሬ ላይ ተጣበቀችብኝ..ይህ ተለመደ ተግባሯ ከሆነ ቆየ… እኔ ከንፈር ላይ ለመጣበቅ ምክንያት ነው የምትፈልገው…..እኔም ሁሌ መሳም ስፈልግ የሆነ ምክንያት ሰጣታለው ‹‹የእኔ ጀግን በጣም ነው ያስደስትከኝ…ውይ እህቶችህ ይሄን ሲሰሙ እንዴት እንደሚደሰቱ አትጠይቀኝ …ጥዋት ቁርስ ላይ ሁሉም ተጨንቀው ሲላቀሱ ነበር..ከአንተ ይሁኑ ከአባታቸው አጣብቂኝ ውስጥ ነው የከተትካቸው..ቆይ ይሄንን ዜና አሁኑኑ ላብስራቸው›› በለማለት ተንደርድራ በሩጫ ወጥታ ሄደች… እኔም የሆነ እፎይታ ተሰማኝ……. ፡፡ ይቀጥላል 🌹ከተመቸዎት Likun ይጫኑት.... ♥️Share ለወዳጅዎ @myguypicture 4 any comment @bekib27
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.