cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የማህበር መዝሙሮች

እናመስግነው በአንድነት መሰዋትም ነውና በመዝሙር እናወድሰው ይገባዋልምና ከመላክት ጋር ባንድነት ከፃድቃን ጋር ሆነን ቅዱስ ቅዱስ እንበል እናመስግን ስሙን https://t.me/menfesewizmare 🔷 🔶🔸🔶 🔷 🔷 🔷 (የመዝሙር ጥናት)

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
936
Suscriptores
Sin datos24 horas
+27 días
+1030 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

​ እሰይ-እልል-በሉ እሰይ እልል በሉ ተገኘ መስቀሉ /2/ የጥል ግድግዳ አበባ የፈረሰበት አበባ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር አበባ የታረቀበት አበባ የእግዚአብሔር ልጅ አበባ የነገሰበት አበባ የሞት አበጋዝ አበባ የወደቀበት አበባ አዝ ===== አይሁድ በቅናት አበባ መስቀሉን ቀብረው አበባ ቢከድኑት እንኳን አበባ በቆሻሻቸው አበባ ጌታን መቃወም ስለማይችሉ አበባ ይኸው ተገኘ አበባ ወጣ መስቀሉ አበባ አዝ ===== ደጉ ኪራኮስ አበባ ሽማግሌው አበባ እሌኒን መራ አበባ በደመራው አበባ ጌታ በሱ ላይ አበባ በመሰቀሉ አበባ ጢሱ ሰገደ አበባ ወደ መስቀሉ አበባ አዝ ===== የእምነት ምልክት አበባ መስቀል ነውና አበባ ተራራው ሜዳ አበባ ሆነ እንደገና አበባ እንደ ተነሳው አበባ ጌታ እንደቃሉ አበባ ከጉድጓድ ወጣ አበባ እፀ መስቀሉ አበባ አዝ ===== እኛም በመስቀል አበባ እንመካለን አበባ በእግዚአብሔር ጥበብ አበባ መቼ እናፍራለን አበባ ሞኝነት እንኳን አበባ ቢሆን ለዓለም አበባ ኃይል እፀ ወይን ነው አበባ ለዘላለም አበባ አዝ ===== ግድግዳው ፈርሷል አበባ የልዩነቱ አበባ ምድርና ሰማይ አበባ ሆኑ እንደ ጥንቱ አበባ ነብስና ስጋ አበባ በሱ ታርቀዋል አበባ ሕዝብና አሕዛብ አበባ ወንድም ሆነዋል አበባ @mahbere_kidstarsema @mahbere_kidstarsema @mahbere_kidstarsema
Mostrar todo...
✞ እሰይ እልል በሉ እሰይ እልል በሉ ተገኘ መስቀሉ  (2) የጥል ግድግዳ - አበባ -የፈረሰበት -አበባ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር -አበባ -የታረቀበት -አበባ የእግዚአብሔር ልጅ  - አበባ -የነገሰበት -አበባ የሞት አበጋዝ - አበባ -የወደቀበት- አበባ አዝ...... አይሁድ በቅናት -አበባ -መስቀሉን ቀብረው - አበባ ቢከድኑት እንኳን - አበባ -በቆሻሻቸው - አበባ ጌታን መቃወም - ስለማይችሉ - አበባ ይኸው ተገኘ - አበባ -ወጣ መስቀሉ አበባ አዝ...... ደጉ ኪራኮስ - አበባ -ሽማግሌው -አበባ እሌኒን መራ - አበባ - በደመራው  - አበባ ጌታ በሱ ላይ - አበባ - በመሰቀሉ - አበባ ጢሱ ሰገደ - አበባ - ወደ መስቀሉ - አበባ አዝ...... የእምነት ምልክት - አበባ  - መስቀል ነውና - አበባ ተራራው ሜዳ - አበባ  - ሆነ እንደገና  - አበባ እንደ ተነሳው - አበባ  -ጌታ እንደቃሉ  - አበባ ከጉድጓድ ወጣ - አበባ - እፀ መስቀሉ - አበባ አዝ...... እኛም በመስቀል - አበባ -እንመካለን - አበባ በእግዚአብሔር ጥበብ - አበባ -መች እናፍራለን - አበባ ሞኝነት እንኳን - አበባ -ቢሆን ለዓለም - አበባ ኃይል እፀ ወይን ነው - አበባ - ለዘላለም - አበባ አዝ..... ግድግዳው ፈርሷል -- አበባ -  የልዩነቱ - አበባ ምድርና ሰማይ - አበባ - ሆኑ እንደ ጥንቱ - አበባ ነብስና ስጋ - አበባ - በሱ ታርቀዋል - አበባ ሕዝብና አሕዛብ -አበባ - ወንድም ሆነዋል - አበባ                      መዝሙር             ዘማሪ ዲያቆን አበበ ታዬ  🌼Share and join ያድርጉ፤ ያስደርጉ። @m_ezmur21 @m_ezmur21
Mostrar todo...
✟መስቀል አበባ✟ መስቀል አበባ ነህ ውብ አበባ አደይ አበባ ነሽ ውብ አበባ መስቀል አበባ ጥራጊውን ሞልተው አደይ አበባ አይሁድ በክፋት መስቀል አበባ ጢሱ ሰገደ አደይ አበባ መስቀል ካለበት አዝ_ መስቀል አበባ ተቀብሮ ሲኖር አደይ አበባ ስነ ስቅለቱ መስቀል አበባ እሌኒ አገኘች አደይ አበባ ደገኛይቱ አዝ____ መስቀል አበባ ወንዙ ጅረቱ አደይ አበባ ሸለቆ ዱሩ መስቀል አበባ አሸብርቀው ደምቀው አደይ አበባ ላንተ መሰከሩ አዝ_ መስቀል አበባ ተቀብሮ ሲኖር አደይ አበባ ስነ ስቅለቱ መስቀል አበባ እሌኒ አገኘች አደይ አበባ ደገኛይቱ 🌼Share and join ያድርጉ፤ ያስደርጉ። @m_ezmur21 @m_ezmur21
Mostrar todo...
🌼ከዘመነ፣ሉቃስ፣ወደ፣ዘመነዮሀንስ🌼2016🌼፡በሠላም፣🌼በፍቅር 🌼፣ከነቤተሠብቦ፣አደረሰዎ፣ዘመኑ፣የይቅርታ ፣የመተሣሰብ፣ዘመን፣ያድርግልን  🌼ኢትዮጵያ ሀገራችን ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን የምትወጣበት ዘመን ያድርግላት
Mostrar todo...
👍 8
      ስለቴን ሰማ   ስለቴን ሰማ ፈጥኖ ከራም የአምላክ ባለሞል ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ገብርኤል----- መጣከሰማይ ቅዱስ ገብርኤል----- እኔን ሊራዳ ቅዱስ ገብርኤል----- ከነበልባሉ ቅዱስ ገብርኤል----- ክንዱን ከነዳ ቅዱስ ገብርኤል----- እሳት ሳይነካው ቅዱስ ገብርኤል----- ፅናፊላችን ቅዱስ ገብርኤል----- መላኩ ቆመ ቅዱስ ገብርኤል----- ከመሀላችን    ቅዱስ ገብርኤል----- ተመችቶናል ቅዱስ ገብርኤል----- ማበል እሳቱ ቅዱስ ገብርኤል----- ቅኔን ተቀኘን ቅዱስ ገብርኤል----- ቆመን በፊቱ ቅዱስ ገብርኤል----- ከቁጥር በዛን ቅዱስ ገብርኤል----- ሰፋን በጌታ ቅዱስ ገብርኤል----- በሞት ውስጥ ሆነን ቅዱስ ገብርኤል----- ዘመርን ለጌታ    ቅዱስ ገብርኤል----- ንጉስ ቢያቆምም ቅዱስ ገብርኤል----- ከዱራ መሀል ቅዱስ ገብርኤል----- ሰማይ ተከፍቶ ቅዱስ ገብርኤል----- እሳት ቢነድም ቅዱስ ገብርኤል----- ከቶም አናስብ ቅዱስ ገብርኤል----- በሰው ልጅ ስራ ቅዱስ ገብርኤል----- ያማልክት አምላክ ቅዱስ ገብርኤል----- ነው ከኛጋራ    ቅዱስ ገብርኤል----- ህፅኑ ቂርቆስ ቅዱስ ገብርኤል----- ከናቱ ጋራ ቅዱስ ገብርኤል----- ቢደርስባቸው ቅዱስ ገብርኤል----- ፅኑ መከራ ቅዱስ ገብርኤል----- በእግዚአብሔር ማዳን ቅዱስ ገብርኤል----- ስለታመኑ ቅዱስ ገብርኤል----- ገብርኤል ተልኮ ቅዱስ ገብርኤል----- ከሳቱ ዳኑ    ተሰማ ስለቴ (2) በገብርኤል ባባቴ ተሰማ ስለቴ (2) ስዕሉፊት ቆሜ ተሰማ ስለቴ ብነግረው ችግሬን ተሰማ ስለቴ መላኩ ገብርኤል ተሰማ ስለቴ ባረከው ዘመኔን ተሰማ ስለቴ ተሰማ ስለቴ (2) በገብርኤል ባባቴ ክፉ እንኮን ቢገጥመኝ ተሰማ ስለቴ አልፈራም ከንግዲ ተሰማ ስለቴ የጭንቄ ማረፊያ ተሰማ ስለቴ መርኩዜ ነው ስምህ ተሰማ ስለቴ ተሰማ ስለቴ(2) በገብርኤል ባባቴ ስለቴን ሰማ ፈጥኖ ከራም የአምላክ ባለሞል ቅዱስ ገብርኤል    https://t.me/menfesewizmare
Mostrar todo...
የማህበር መዝሙሮች

እናመስግነው በአንድነት መሰዋትም ነውና በመዝሙር እናወድሰው ይገባዋልምና ከመላክት ጋር ባንድነት ከፃድቃን ጋር ሆነን ቅዱስ ቅዱስ እንበል እናመስግን ስሙን

https://t.me/menfesewizmare

🔷 🔶🔸🔶 🔷 🔷 🔷 (የመዝሙር ጥናት)

👍 1
#ጷጒሜን ፪ "የካህናት ቀን!#አባቶቻችንን እኛ ካላከበርን ማን ያከብርልናል ኑሩልን አባቶቻችን🌹 📌ምሥጢረ ክህነት ካህን ማለት ፦ ተክህነ አገለገለ ። ካለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ፤ ካህን ማለት የእግዚአብሔር አገልጋይ ፤ የምዕመናን አባት ፤  ጠባቂ ፤ መጋቢ ማለት ነው ።ምሥጢረ ክህነት በብሉይ ኪዳንየክህነት አንዱ መገለጫው መስዋዕት ማቅረብ ሲሆን ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዚህ አገልግሎት የተመረጠውና ካህን ተብሎ የተጠራው መልከ ጼዴቅ ነው ። ዘፍ ፥ 14 ፥ 18 ። በኋላም እግዚአብሔር በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት በቤተ መቅደስ እግዚአብሔርን የሚያገለግል ፣ የሕዝቡን ኃጢአት እየተቀበለ ከእግዚአብሔር የሚያስታርቅ ካህን እንዲመርጥ ሙሴን ስላዘዘው ከመልከ ጼዴቅ በኋላ አሮን ተሾመ ። ዘፀ  ፥  ። ዕብ 7 ፥ 1 ። ከአሮን እስከ ዮሐንስ መጥምቅ ደረስ ረጅሙን የብሉይ ኪዳን ዘመን ከአሮን ዘር ብቻ የሚወለዱት ቅብዓ ክህነት እየተቀቡ በካህንነት እያገለገሉ አልፈዋል ። ነገር ግን በዘር ሐረግ ላይ የተመሠረተው ክህነት ለሐዲስ ኪዳኑ ክህነት ምሳሌ ስለነበረ ፍፁምና ዘላቂ አልነበረምና መስዋዕቱም ሆነ የአመራረጡ ሂደት በሌላ ተተካ ።ዘላቂ ያልሆነበትና በሌላ  የተተካበት ምክንያት– ህነቱ በዘር ብቻ የተገደበ ስለነበረ ፤ በሐዲስ ኪዳን ህጉንና ሥርዓቱን አሟልቶ ለተገኘ ለማንኛውም ሕዝብ የተፈቀደ ሆነ ። ክርስቶስ የመጣው ለዓለም ሁሉ ነውና ። – መስዋዕታቸው ፍጹም ድኅነት የማያሰጥ በመሆኑ ፤ በሐዲስ ኪዳን በክርስቶስ ሥጋና ደም ተተካ ። ዮሐ 6 – አገልግሎቱ ለጊዜው ከሥጋ መቅሰፍት ከማዳን ያላለፈ ነበረ ፤ በሐዲስ ኪዳን ግን በምድርም በሰማይም ማሰር በሚችሉ ፣ በነፍስም በስጋም ላይ ሥልጣን ባላቸው ካህናት ተተካ ። ማቴ 18 ፥ 18 ።ምሥጢረ ክህነት በሐዲስ ኪዳንበብሉይ ኪዳን የመጨረሻው ካህን መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ሲሆን ፤ ከእሱ በኋላ የብሉይ ኪዳን ክህነት አልፏል ። ጌታ ችን ወደ ዮርዳኖስ ሄዶ በዮሐንስ እጅ በመጠመቅ ፡ ካህኑ በሚገኝበት ቦታ ቤተ ክርስቲያን ድረስ ሄደን በካህኑ እጅ መጠመቅ እንዳለብን አስተምሮናል ። ማቴ 3 ፥ ጌታችን ሲያስተምር ስለ ካህናት በብዙ ቦታ ተናግሯል ። ሂድና ራስህን ለካህን አሳይ ። ማቴ 8 ፥ 4 ። አንተ ብፁዕ ነህ ፡ የመንግስተ ሰማያትንም መክፈቻ እሰጥሃለሁ…ማቴ 16 ፥ 17 ። እውነት እላችኋለሁ በምድር ያሰራችሁት በሰማይ የታሰረ ፣ በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሆናል ። ማቴ 18 ፥ 18 ። ይህን የተናገረው በመዋዕለ ስብከቱ ሲሆን  ከሙታን ከተነሳ በኋላም ለሐዋርያት አረጋግጦላቸዋል ። ሂዱና በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸው ። ማቴ 28 ፥19 ።..እፍ አለባቸውና መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ ። ዮሐ 20 ፥ 22 ። በመጨረሻም ቅዱስ ዼጥሮስን “….ስምዖን ሆይ በጎቼን ጠብቅ ፤ (ለጊዜው አስራ ሁለቱን ሐዋርያት ፡ ለፍጻሜው ወላጆችን) ፣ ጠቦቶቼን ጠብቅ ፤ (ለጊዜው ሰብዓ አርድዕትን ፡ ለፍጻሜው ወጣቶችን) ፣ ግልገሎቼን ጠብቅ (ለጊዜው ሰላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስትን ፡ ለፍጻሜው ህጻናትን)” በማለት ሐዋርያትን ዸዸሳት ፣ ቅዱስ ዼጥሮስን የመጀመሪያ ሊቀ ዻዻሳት አድርጎ ሾመው ። ዮሐ 21 ፥ 15 ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን በሊቀ ዸዸስና በዸዸሳት በሚመራ መንፈሳዊ ጉባኤ (ቅዱስ ሲኖዶስ) አማካኝነት እየተመራች አገልግሎቷን ታካሂዳለች ። ቤተ ክርስቲያን የክህነት ደረጃዎች ፤ የሚከተሉት ናቸው1 ሊቀ ዻሳሳት :- ሊቃነ ዸሳሳት “ፓትርያርክ” እየተባለም ይጠራል ። በአንዲት ቤተ ክርስቲያን (በአንድ ሲኖዶስ) ላይ የበላይ ሆኖ የሚሾም የሁሉም አባት ነው ። የሐ ሥ  20 ፥ 28 ። በሕዝብና በካህናት  ከተመረጠ በኋላ በዻሳሳት ይሾማል ። ፍት ነገ 5 ። ረስጣ 2 ። ፓትርያርክ ያወገዘውን ዻዻስ አይፈታውም ። መንፈሳዊ ሥልጣኑ ከሁሉም በላይ ነውና ። ሲኖ 51 ። ፓትርያርክ በመላዋ ቤተ ክርስቲያን በጸሎት ጊዜ ስሙ ይጠራል ።2 ኤዺስ ቆዾስ :- ዻዻስ በአንድ ሀገረ ስብከት አባት ሆኖ የሚሾም ነው ። ሲያገለግል በነበረበት አካባቢ ባሉ ምዕመናን ጥቆማና ድምጽ በርዕሰ ሊቃነ ዻሳሳቱና በሲኖዶስ ፈቃድ ይሾማል ። ፍት ነገ 5 ። አብጥ 2 ። በአንድ ዻዻስ ብቻ አይሾምም ። ፍት ነገ 5 ። ረስ 58 ።ዲድ 34 ። ዻዻስ በሀገረ ስብከቱ በጸሎት ጊዜ ስሙ ይጠራል ። ፍት 5 ። ክፍ 4 ። አዲስ ጽላት ፣ አዲስ ቤተ ክርስቲያን ፣ ይባርካል ። ለቄስ  ለዲያቆን ሥልጣነ ክህነት ይሰጣል ። 1 ጢሞ 5 ፥ 2 ። ፍት ነገ አን 5 ክፍ 4 ።3 ቀሳውስት :- ቅስና የሚቀበሉ ፤ በዲቁና ክህነት በማገልገል ላይ ያሉ ሲሆኑ ፤ በሁለት መንገድ ይሾማሉ ።3.1 በምንኩስና የተወሰነ ያላገባ ጌታን እንዴት እንደሚያገለግል የጌታን ነገር ያስባል ። 1 ቆሮ 7 ፥ 32 ። በማለት ቅዱስ ዻውሎስ እንደተናገረ ፤ በምንኩስና ለመኖር የፈለገ አስቀድሞ ወደ ገዳም ሄዶ የምንኩስናን ሕይወት መማርና አባቶችን እያገለገለ በተግባር ማየት አለበት ። በገዳም የሚሰጠውን አገልግሎት ከፈጸመ በኋላ አበምኔቱ ሲፈቅድለት ሥርዓተ ገዳሙ በሚያዝዘው መሠረት መዓርገ ምንኩስና ይቀበላል (ይመነኩሳል)ከምንከስና በኋላ ለክህነት የሚያበቃውን ትምህርት ተምሮ በየደረጃው ያሉትን የሥልጣነ መዓርጋት። በድንግልና ከመነኮሰና በትም ሕርቱም ሆነ በግብረ ገብነቱ በቂ ሆኖ ከተገኘ እስከ መጨረሻው የቤተ ክርስቲያን መዓርግ  “ጵጵስና” ሊደርስ ይችላል ።3.2 በህግ የተወሰኑ  ዲያቆናት በአንድ ህግ ከተወሰኑ ፤ በኋላ ለቅስና የሚያበቃ ትምህርትና ሥነ ምግባር ካላቸውና በሚያገለግ ሉበት አጥቢያ ሕዝብ ድምጽ ከተደገፉ ፤ ሊቀ ዻዻሱ ብቃታቸውን መዝኖ የቅስና መዓርግ ይሰጣቸዋል ። ፍ ገ 6 ።ሰላሳ ዓመት ያልሆነው ቅስና አይሾምም ። ፍት ነገ 6 ። የቀሳውስት የአገልግሎት ድርሻ አስተምሮ ማጥመቅ ፤ ንስሐ መቀበልና መናዘዝ ፣ (ማሰርና መፍታት) ፤ ቀድሶ ማቁረብ ፤ ማስተማር…. ናቸው ። ካህን የመጀመሪያ ሚስቱ ከሞተችበት ፤ መነኩሴም ምንኩስናውን ከተወው በኋላ የቅስና (የክህነት) ሥራ መሥራት አይፈ ቀድለትም ። ከማኅበረ ምዕመናን ግን አይለይም ።4 ዲያቆናት :- ዲያቆናት ካህናትን የሚራዱና የሚላላኩ ሲሆኑ ፤ በአገልግሎታቸው መሠረት የሚከተሉት ደረጃዎች አሏቸው –  ዲያቆን                          –  መዘምራን –  ንፍቀ ዲያቆን                    –  አጻዌ ኆኅት –  አናጉንስጢስ                    –  ሴቶች ዲያቆናውያት ናቸው ።ዲያቆን:- አስቀድሞ ሃይማኖቱን የተረዳ ፣ በምዕመናን ዘንድ በግብረ ገብነቱ የታወቀና የተመሰከረለት ፣ ለዲቁና አገልግሎት የሚያበቃውን ትምህርት ጠንቅቆ የተማረ ፤ ሆኖ ሲገኝ በአንብሮተ ዕድ (እጅ በመጫን) ይሾማል ። የተለየ ብቃትና ችሎታ ከሌለው በቀር ዕድሜው ከሃያ አምስት ዓመት በታች የሆነ ዲቁና አይሾምም ። ዲያቆን ከመጀመሪያ (ከህግ) ሚስቱ ከተፋታና ሌላ ካገባ ፣ ሃይማኖቱን ለውጦ በመናፍቃን ከተጠመቀ ፣ ከክህነቱ ይሻራል ። ፍት ነ 7 ክ ፍል 5 ።ዲያቆናት መቅደስ ይገባሉ ፤ ነገር ግን መንበር ፣ ታቦት ፣ (ከተለወጠ በኋላ) ሥጋውንና ደሙን በእጃቸው አይነኩም ። ዲያቆናት ለተልእኮ የሚፋጠኑ ፣ በትህትና የሚላላኩ ፣ በኑሯቸው ለሌላው አርአያ መሆን ይገባቸዋል ።ንፍቀ ዲያቆን :- የዲያቆን ረዳት ሲሆን ፤ መንፈሳዊ ሕይወቱ ፣ ግብረ ገብነቱና የሃይማኖቱ ጽናት በሚያገለግልበት አጥቢያ ካህናትና ምዕመናን የተመሠከረለት ። ፍት ነገ 8 ። ንፍቀ ዲያቆን በቃል ብቻ
Mostrar todo...
👍 1 1
ይሾማል አንብሮተ ዕድ “እጅ በማጫን” አይደረግለትም ። ፍ ነ 8 ክፍ 2 ። የዲያቆን ረዳት እንደመሆኑ መጠን በሥራው ሁሉ ያግዘዋል እንጅ ንዋየ ቅድሳት አይነካም ። ፍት ነገ ፰ ።ጾክ 45 ፣ 46 ። ጥፋት ሠርቶ ከተገኘ ከክህነቱ ይሻራል ። ፍት ነገ 8 ክፍል 4 ።አናጉንስጢስ :- አገልግሎቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መጻሕፍት ማንበብ ሲሆን ፤ ትምህርቱና በግብረ ገብነቱ ከታየ በኋላ ተመ ርጦ ይሾማል ። ፍት ነገ 8 ክፍል 1 ። አናጉንስጢስ አንብሮተ ዕድ አይደረግለትም በቃል ብቻ ይሾማል ። ፍት ነገ 8 ክፍ 2 ። በአገልግሎት ጊዜ ዲያቆናት በቅዳሴ ሠዓት የሚለብሱትን ልብሰ ተክህኖ አይለብስም ። ፍት ነገ 8 ክፍ 3 ። አናጉንስጢስ ፡ ጥፋት ከተገኘበት ከሥራ ታግዶ ከዓመት በኋላ ይመለሳል ። ከጥፋቱ ካልታረመ ከአገልግሎቱ ይሻራል ። ፍት 8 ክፍል 4 ። ሚስቱ ከሞተችበት ሌላ አግብቶ ማገልገል ይችላል ። ፍት 4 ክ 5 ።መዘምራን :- በቡራኬ ይሾማሉ ። ፍ ነገ 8 ክፍ 2 ። ከመዝሙረ ዳዊት ፣ በሀገራችን የቅዱስ ያሬድን ዝማሬም ይዘምራሉ ። በሚዘምሩበት ጊዜ ልብሰ ተክህኖ አይለብሱም ። ፍት ነ 8 ክፍ 3 ። መዘምራን ሚስታቸው ከሞተችባቸው ሌላ ማግባት ይችላሉ ። ፍት ነ 8 ክ 5 ። በሀገራችን መዘምራን ማለት የማኅሌት ትምህርት የተማሩትን ሲሆን ፤ እነዚህም ሥልጣነ ክህነት (ዲቁና ቅስና ፣ ከዚያም በላይ) ካላቸው በሁለቱም (በማኅሌትም በክህነታቸውም) ማገልገል ይችላሉ ። የሰንበት ት“ምህርት መንፈሳውያን ወጣቶችም መዘምራን ይባላሉ ።አጻዌ ኆኅት :- በቃል ብቻ ይሾማል ። አገልግሎቱ በር መክፈትና መዝጋት ሲሆን ፤ ልብሰ ተክህኖ አይለብስም ። ፍት ነገ 8 ክፍ 3 ። ሚስቱ ከሞተችበት ሌላ አግብቶ ማገልገል ይችላል ። ፍት ነገ 8 ክፍ 3 ።ሴቶች ዲያቆናውያት :- በትዳር ተወስነው የኖሩ ፣ ልጆቻቸውን በሥርዓት ያሳደጉ ፣ በቅዱስ ቁርባን የተወሰኑ ፣ ለአገልግሎት የሚፋጠኑ ፣ 8 ዓመት የሆናቸው ፤ ዲያቆዊት ሆነው በቃል ይሾማሉ ። 1 ጢሞ 5 ፥ 9 ። ፍት ፡ ነ 8 ፡1 ። ዲድ 17 ።አገልግሎታቸው– ከካህናቱ ወደ ሴቶች ይላላካሉ ፤ ሴቶች ክርስትና ሲነሱ ፤ ካህኑ እጃቸውን ይዞ ከአንገተችው በታች ቅብዓ ሜሮን ይቀባሉ ። – አይባርኩም ፤ ቄስና ዲያቆን የሚሠራውን የክህነት ሥራ አይሠሩም ፤ በሴቶች በር ቆመው ይቆጣጠራሉ ። – እንደ ዲያቆኑ ተንሥኡ ጸልዩ አይሉም ፤ ቅስና አይሾሙም ጉባዔ በጸሎት አይከፍቱም ። ፍ ነ 8 ክፍ 1 ።እነዚህም ፤ ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ ከሌላው ምዕመን ተለይተው እነሱ ወደ ቤተክርስቲያን ስለቀረቡ ፤ ምዕመናን በሥጋ ድካም ቢሳሳቱ ፤ ከሚያገለግሉት ጓደኞቻቸው መካከልም የተሳሳተ ወንድማቸው ቢኖር ሊመክሩት ፤ ሊያጽናኑት ይገባል እንጅ ፤ የራሳቸውን ጽድቅ የወንድማቸውን ስህተት እያወሩ ፤ ለሚድኑት መሰናክል ሉቃ 18 ፥ 9 ።
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን አደረሳችሁ የአባቶችን አብነ ተክለሃይማኖት ረድኤት በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን ።ከመጣብን መቅሠፍት ከአምላካችን ከመድሀኒታችን ከእየሱስ ክርስቶስ ምህረትን እንዲያሰጡን እንማፀናለን። @m_ezmur21 @m_ezmur21
Mostrar todo...
🙏 1