cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

AAU - Muslim Students Union

This is the official channel of AAU-MSU. Email: [email protected] Telegram: @aaumsu Twitter: twitter.com/aaumsu12 Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
3 362
Suscriptores
+1224 horas
+607 días
+26530 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ وَيُعَلِّمُكُمُ ٱللَّهُ ۗ وَٱللَّهُ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌۭ "... አላህንም ፍሩ፡፡ አላህም ያሳውቃችኋል፡፡ አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡" (አል በቀራህ 282) “Observe Taqwaa of Allaah, and Allaah shall grant you knowledge. And Allaah is completely knowledgeable about all things.” (Al-Baqarah 282)
Mostrar todo...
👍 5
ልዩ የክረምት ስልጠና በኢሙዳት(የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዳዕዋና ትምህርት ማህበር) ኢሙዳት በየአመቱ ክረምት ወቅት አጠቃላይ የንፅፅር እውቀት ብልፅግና ላይ የሚያተኩሩ ስልጠናዎችን ያለ ምንም ክፍያ በታዋቂ ኡስታዞች እና አሰልጣኞች በመስጠት ተማሪዎችን እንደሚያስመርቅ ይታወቃል። በመሆኑም በዘንድሮ ክረምት ልዩ የሆነ ስልጠና በዋነኝነት ክረምታቸውን በአዲስ አባባ ለሚያሳልፉ  2ኛ ደረጃ ት/ት ተማሪዎችና ለዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ  በተጨማሪም በማንኛውም ዘርፍ ላይ ያሉ በሃይማኖት ንጽጽር  ዘርፍ ለኢስላም መስራት የሚፈልጉ ወጣቶችን ለይቶ ስልጠናዎችን ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል።  ስልጠናው የሚያጠነጥነው የንፅፅር እውቀት፣ ኢማንን ማጎልበት፣ የኦዲዮ ቪዥዋልና የሚዲያ ማኔጅመንት፣ የሊደርሽፕ ፣ አርት እና ኢስላማዊ ስልጣኔ፣ የማህበረሰባዊ አይዲዮሎጂዎች እና መሰል የወጣቶችን ንቃተ ሕሊናን የሚያጎለብቱ ጉዳዮች ላይ ሲሆን ስልጠናውም በሳምንት ለ6 ቀናት የግማሽ ቀን ከሀምሌ 01 እስከ ጷጉሜ 05, 2016 ድረስ የሚቆይ ይሆናል። በመሆኑም ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ ትምህርቱን በቋሚነት መከታተል የምትችሉ ወጣቶች (ወንድ እና ሴት) ይህንን ቅፅ በመሙላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። 🏢ኢሙዳት(የኢትዮጵያ ሙስሊም ዳእዋና ትምህርት ማህበር) 🕹ፒያሳ ⏰ 02:30-06:00LT ለበለጠ መረጃ ☎️ 0913242072 0945728270 0944078334 ይደውሉ። 🛑ያለን ቦታ ውስን ነው። የመመዝገቢያ Link👇 https://forms.gle/GSPGTQWnyuTfNnBQ7
Mostrar todo...
የ2016 ክረምት ስልጠና መመልመያ

This form will help us identify the best candidates that will be selected to participate in the 2016 winter break training program organized by ኢሙዳት. This program is the 6th of its kind organised every year from 2009 (Eth Calendar) until now. It will span for two-months' over the winter period and includes topics on Comparative Religion, Leadership, Islamic Art, Social and Political Thoughts, Atheism, Shubhat, etc. Trainers will include noticeable experts such as Ustaz Abu Hayder. Training schedule will be six days a week, half-days only (8:30AM in the morning until Zuhr prayer) *** Only fill out this form if you are serious about attending the whole program, participating in all the assignments that will be given throughout the program and gaining precious knowledge in the end. *** Only fill out the form truthfully and in a detailed manner. *** Limited number of applicants will be selected

👍 5 1
"በየዘመናቱ ከእውቀት ባለቤቶች እነዚያን የሳቱትን ወደ ትክክለኛው መንገድ የሚጣሩ፤ በነርሱ ላይ የሚደርስን በደል የሚታገሱ፤ በአላህ መጽሐፍ (የልብ) ሙታንን ህያው የሚያደርጉ፤ (የልብ) እውሮችን በአላህ ብርሃን የሚመሩ ቅሪቶችን ያደረገ አምላክ አሏህ የተመሰገነ ይሁን። ስንት ሰይጣን (ልባቸውን) የገደላቸው ህያው አደረጉ፤ ስንትንስ መንገድ የጠፋውን መሩ፤ በሰዎች ላይ ያላቸው ተጽዕኖ ምንኛ ያማረ ነው፤ በነርሱ ላይ የሰዎች ስራ ላይ ምንኛ የከፋስ ነው። የአሏህ መጽሐፍ ከድንበር አላፊዎች ማጣመም፣ የአስተባባዮችን ማጭበርበር፤ የአላዋቂዎችን ትርጓሜ ይከላከላሉ።" (አል-ኢማም አህመድ ኢብን ሐንበል) ዑለሞች እንዳሉ እንጠቀምባቸው፤ ሓለቃዎቻቸውን እንሳተፍ፤ ዑለሞች የነቢያት ወራሾች ናቸው፤ ከነብያት ውርስ ድርሻን የፈለገ ከስራቸው ቁጭ ብሎ ሊማር ይገባዋል። "አላህ እውቀትን ከሰዎች ልብ በመቀማት አይወስደውም። ይልቁንም በሊቃውንት ሞት እውቀትን ይወስዳል።" (ቡኻሪና ሙስሊም) @aaumsu
Mostrar todo...
9👍 1
"የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፡፡ በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡ አጋሪዎችንም በአንድ ላይ ኾነው እንደሚዋጉዋችሁ በአንድ ላይ ኾናችሁ ተጋደሉዋቸው፡፡ አላህም ከሚፈሩት ጋር መኾኑን ዕወቁ፡፡" (አት-ተውባህ 36) 💎 "በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡" ከተባለላቸው አራት የተከበሩ ወራት አንዱ የሆነውን ዙል-ሒጃን ዛሬ አንድ ብለን ጀመርን። 📌 በእነዚህ ወራት ውስጥ የአላህን ትእዛዛት ችላ በማለት ራሳችንን አንበድል። 📌 በእነዚህ ወራት ራሳችንን ከዒባዳ ሩቅ ከማድረግ ነፍሳችንን አንበድል። "በነዚህ ወራት ኢባዳ ላይ የጠነከረ ሰው በቀሪዎቹ ወራቶች ይበልጥ ጠንካራ ይሆናል። በተመሳሳይም በነዚህ ወራት ውስጥ ከወንጀል እና ከሌሎች መጥፎ ስራዎች ለመራቅ አስፈላጊውን ጥረት ያደረገ ሰው በቀሪዎቹ የአመቱ ወራት ከነዚህ እኩይ ተግባራት መጠበቁ ቀላል ይሆንለታል። በእነዚህ ወራት ውስጥ የአቅምን ያክል አለመስራት አስከፊ ኪሳራ ነው።" (አህካም አል-ቁርዓን) @aaumsu
Mostrar todo...
👍 6
የታቢዒዮች ኢማም የነበሩት አል-ሐሰን አል-በስሪ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፦ "ከጌታችን (ምህረት ከመጠየቅ) እፍረት ሊሰማን አይገባንምን? ምህረትን እንጠይቃለን ከዚያም ወደ ወንጀል እንመለሳለን ከዚያም ምህረትን እንጠይቃለን ከዚያም እንመለሳለን?!" እንዲህ በማለት መለሱ፦ "ሸይጣን በዚህ (ሀሳብ) ሊያሸንፋችሁ ይወዳል። ምሕረትን ከመጠየቅ አትታክቱ" 📌 በ10ሩ የዙል-ሒጃህ ቀናት ልናደርገው የሚገባው የመጀመሪያው ነገር ተወበትና ወደአሏህ መመለስ ነው። 📌 እስካሁን ለሰራናቸው ወንጀሎች ማበሻ ይሆንን ዘንድም በኸይር ስራ ላይ መበርታት አለብን። وَأَقِمِ ٱلصَّلاَةَ طَرَفَيِ ٱلنَّهَارِ وَزُلَفاً مِّنَ ٱلَّيْلِ إِنَّ ٱلْحَسَنَاتِ يُذْهِبْنَ ٱلسَّـيِّئَاتِ ذٰلِكَ ذِكْرَىٰ لِلذَّاكِرِينَ "ሶላትንም በቀን ጫፎች ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም፡፡ መልካም ሥራዎች ኀጢአቶችን ያስወገድዳሉና፡፡ ይህ ለተገሳጮች ግሳጼ ነው፡፡" (ሁድ 114) 📌 እነዚህን ውድ የዱንያ ቀናት በትክክል ተጠቅመውባቸው ከሚያልፉት ያድርገን! አሚንንን @aaumsu
Mostrar todo...
4
በሃገረ ሳዑዲ ዐረቢያ የወርሃ ዙል-ሒጃህ ጨረቃ ዛሬ ሐሙስ ስለታየች ነገ ጁሙዓህ ግንቦት 30, 2016 E.C. የዙል-ሒጃህ ወር የመጀመሪያው ቀን ይሆንና ወርቃማዎቹ የዙል-ሒጃህ 10 ቀናት ከነገ ይጀምራሉ። ስለሆነም ቅዳሜ ጁን 15, 2024 (ሰኔ 08, 2016 E.C.) የዕለተ ዐረፋህ ቀን ሲሆን እሁድ ጁን 16 (ሰኔ 09) ዒደ-ል-አዽሓህ ይሆናል። አላህ በሰላም ያድርሰን‼ እነዚህን ወርቃማ ቀናቶች በዒባዳህ ለማሳለፍ ከወዲሁ ዝግጅት አድርጉ። ቀናቶቹን ከምታሳልፉባቸው ዒባዳዎች መካከል፤ ጾም፣ ዚክር፣ ቁርኣን መቅራት፣ ሶደቃ፣ ለቻለ ሰው ሐጅና መሰል በጎ ተግባራትን ማከናወን ይገኙበታል። አላህ ያበርታን። ሌሎችንም አስታውሱ! @aaumsu
Mostrar todo...
👍 11
የልደታ ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አመታዊ የማጠናቀቂያ ፕሮግራሙን አካሂዷል ! አርብ ግንቦት 23 ከአስር በኋላ የቂርአት ፕሮግራም መዝጊያ፣ የተመራቂ ተማሪዎች መሸኛ እና የ2016 ሁለተኛ ሴሚስተር አዲስ ተማሪዎች የመቀበያ ፕሮግራም ባማረ እና በአስደሳች መልኩ አከናውኗል። በፕሮግራሙም ከምርቃት በኋላ ስላለው ጉዞ እና ትምህርት ጠቅላላ ምክር በአርክቴክት እና ፕላነር ቢኒያም አሊ የቀረበ ሲሆን ተማሪዎችም ከዲናቸው ጋር በተያያዘ ኡስታዛችን ሀሺም በሰና አማና ብለው ጥዑም መልዕክትን አስተላልፈዋል። እንዲሁም የጀመአው ሎጎ ውድድር አሸናፊ ይፋ ተደርጓል። በመጨረሻም የጀመአው አሚር የህያ አባረሻድ መዕክቱን ሲያስተላልፍ የሴክተር አሚሮች የአመቱን ሪፖርት አቅርበዋል። እንዲሁም የሽልማት ፕሮግራም ተካሂዷል። በዚህም መሰረት፡ •በቂራት ፕሮግራም (በኪታቡ ተውሂድ እና በመንሃጁ አስሳሊኪን ደስ)፡ 1.ወንድም ሙስአብ (3000 ብር) 2.እህት ነኢማ ጫኔ (2000 ብር) 3.እህት ነኢማ ቲጃኒ (1500 ብር) •በአጠቃላይ በቂርአት ዘርፍ በዚህ አመት ድንቅ እንቅስቃሴ ወንድም አብዱልሃፊዝ ጁማቶ እና እህት ሰላማ ዩሱፍ ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል። •ለተመራቂ ተማሪዎች በአጠቃላይ ከጀመአው ማስታወሻ የተበረከተላቸው ሲሆን ከነሱ ዉስጥ በሴክተር አሚርነት ሲሳተፉ ለነበሩ ወንድሞች እና እህቶች ተጨማሪ ሽልማት እና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል። የሴቶች ጀመአ አሚር ለነበረችው እህት ነኢማ ቲጃኒ ከጀመአው እና ከአአዩ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ስጦታ ተበርክቶላታል። •ጀመአዉን ለመወከል በነበረው የሎጎ ውድድር ላይ ለተሳተፉት የምስክር ወረቅት የተሰጠ ሲሆን አሸናፊ ለሆነው ወንድም ሙባረክ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል። በመጨረሻም ድንቅ ከሆነ ከእራት ግብዣ በኋላ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

👍 17 4