cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

CNN News አማርኛ

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 620
Suscriptores
+124 horas
-37 días
+930 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
01:23
Video unavailableShow in Telegram
video_2024-06-06_09-43-56.mp45.47 MB
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዛሬ ያልቃል፤ ኢሰመኮ በአዋጁ የታሰሩ እንዲለቀቁ አሳሰበ ምክንያቱን በአማራ ክልል የተከሰተውን ግጭት ያደረገው እና ለ10 ወራት የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ የጊዜ ገደብ በማለቁ በእስር የቆዩ ሰዎች ሊለቀቁ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በአማራ ክልል በመንግሥት እና በታጣቂ ኃይሎች (በተለምዶ “ፋኖ”) መካከል ከሚካሄደው የትጥቅ ግጭት ጋር ተያይዞ የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ የጊዜ ገደብ በማለቁ በእስር የቆዩ ሰዎች የመልቀቅ ሂደት እንዲቀጥልም አሳስቧል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የነበረው እና ጥር 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ለተጨማሪ 4 ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተፈጻሚነት ዛሬ መጠናቀቁን ኮሚሽኑ አሳትውሷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ያለውን ተጽዕኖ በተመለከተ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ እንደቆየ የገለጸው ኮሚሽኑ ከአዋጁ ትግበራ ጋር የተስተዋሉ ክፍተቶችንና የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያመላክቱ፣ እንዲሁም ምክረ ሐሳቦችን ያካተቱ መግለጫችን ሲያወጣ የቆየ ሲሆን በዚህም የመንግስት እና ሌሎች የታጠቁ ኃይሎች በመብት ጥስቶች ላይ መሳተፋቸውን እንዳረጋገጠ አዲስ ማለዳም በተደጋጋሚ መዘገቧ አይዘነጋም። በመሆኑም በዚሁ አዋጅ አተገባበር ዐውድ ውስጥ በእስር ላይ የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ ማድረግን ጨምሮ ወደ መደበኛው የሕግ አተገባበር ሂደት መመለስ፣ እንዲሁም በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ እና ሌሎች ማኅበረሰባዊ አገልግሎቶች እንዲመለሱ ኢሰመኮ ጥሪ አቅርቧል። @cnn_amharic1 @cnn_amharic1
Mostrar todo...
የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይ መፍትሄ እንዲያገኝ ለሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ሆኖ ቀረበ ‘’አዲስ አበባ ክልል ትሁን ወይስ አትሁን’’ የሚሉ ጥያቄዎች በምክክር እንዲፈቱ አጀንዳ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ አዲስ አበባን ወከለው በምክክሩ የተሳተፉ ተወካዮች የአዲስ አበባ ባለቤትንት እና የወሰን ጉዳይ መፍትሄ እንዲገኝ ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ አጀንዳ አድርገው አቅርበዋል፡፡ በአጀንዳ ልየታ የተሳተፉት የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አዲስ መሃመድ፤ የታሪክ እና ትርክት ጉዳይ የህግ መንግስት፣ የሰንደቅ ዓላማ፣ የአዲስ አበባ ባለቤትንት እና የወሰን ጉዳይ የሃይማኖት፣ የቋንቋ እንዲሁም ከፍርድ ቤት ጀምሮ ተቋማት ነፃ እና ገለልተኛ ሆነው እንዲቋቋሙ በአጀንዳነት ቀርበዋል ብለዋል፡፡ የመሬት ባለቤትነት ጉዳይ፣ የምርጫ፣ የመንግስት አስተዳደር ስርዓትም ባለው ይቀጥል ወይስ ይሻሻል የሚለው ጉዳይ በሕዝብ ውይይት ውሳኔ እንዲገኝ የአዲስ አበባ አጀንዳ ሆነው መቅረባቸውን ሰምተናል። ብሄራዊ ጀግና ማነው? ብሄራዊ ጀግናን ጉራጌው፣ ኦሮሞው፣ አማራው ሌላው እንዴት ነው የሚያየው? ብሄራዊ ምልክት ምንድነው? አንበሳ፣ ፒኮክ፣ ዋልያ፣ ነው ወይስ ሌላ ነው የሚለው እንዲለይ የአዲስ አበባ አጀንዳ ሆኖ መቀረቡን አዲስ መሃመድ ተናግረዋናል። አዲስ አበባ ባለቤቱ ማን ይሁን? ወሰኑ እስከየት ይሁን? ቋንቋዋ ምን ይሁን? በፌደሬሽን ምክር ቤት ውክልናዋ ምን ይሁን? የሚሉ ጥያቄዎች በምክክር እንዲፈቱ አጀንዳ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ ትናንት በአዲስ አበባ በተጠናቀቀው የመጀመሪያ ምዕራፍ ምክክር የሀገሪቱ የምርጫ ሰርዓት በድምፅ ብልጫ ወይስ በሌላ አማራጭ ይወሰን እንዲሁም ከፍርቤት ጀምሮ በከተማዋ ያሉ ተቋማት ነፃና ገለልተኛ እንዲሆኑ በአጀንዳ መቅረባው ተነግሯል፡፡ #ሸገርኤፍኤም
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
10:10
Video unavailableShow in Telegram
China
Mostrar todo...
Catch_100_Extremely_Poisonous_Black_Gold_Snakes_With_Bare_Hands.mp4437.25 MB
በኢትዮጵያና በኮሪያ ሪፐብሊክ መካከል የ1 ቢሊየን ዶላር የፋይናንስ ማዕቀፍ ስምምነት ተፈረመ በኢትዮጵያና ኮሪያ ሪፐብሊክ መካከል በቀጣይ አራት ዓመታት ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የ1 ቢሊየን ዶላር የፋይናንስ ማዕቀፍ ስምምነት ተፈረመ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኮሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት በፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ይኦል አቀባበል ተደረጎላቸዋል። ሁለቱ ወገኖችና የልዑካን ቡድኖቻቸው የሁለትዮሽ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ፌዴራል የሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እና በደቡብ ኮሪያ ፀረ ሙስና እና ሲቪል መብቶች ኮሚሽን መካከል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል። በሁለትዮሽ ውይይቱ አማካኝነት በቀጣይ አራት ዓመታት ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የ1 ቢሊየን ዶላር የፋይናንስ ማዕቀፍ ስምምነትም በዛሬው ዕለት ተፈርሟል ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል። @cnn_amharic1 @cnn_amharic1
Mostrar todo...
#Update #EOTC " የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻ አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ ፤ የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው " - ቅዱስነታቸው ግንቦት ወር ላይ የሚካሄደው ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀመረ።   የጉባኤውን መጀመር አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መልዕክት አስተላልፈዋል። ቅዱስነታቸው ምን አሉ ? ቅዱስነታቸው ፥ " ቤተ ክርስቲያን ከፈተና ተለይታ አታውቅም  " ሲሉ ገልጸዋል። ፈተናው ከተወሰነ አቅጣጫ ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ከብዙ አቅጣጫ እንደሚከባትም አመልክተዋል። " የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻ አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ " ያሉ ሲሆን " የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው " ብለዋል። በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች ሲሉ ገልጸዋል። የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት እንደሆኑ አሳውቀዋል። ቅዱስ ፓትርያርኩ ፥ " ከጥንት ጀምሮ የነበረ ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ፣ የጸሊአ ሢመትና የጸሊአ ንዋይ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩ ፦ ° ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ ° መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል፣ ° ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጐደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን #ተሰሚነትና #ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው " ብለዋል። " እነዚህና እነዚህ የመሳሰሉ ክሥተቶች በውስጥ ሥር በሰደዱ ቁጥር ጉዳትን እያስከተሉ ነው " ያሉት ቅዱስነታቸው " ሰዎች ከኦርቶዶክሳዊ ቀኖና እና ሥርዓት ባፈነገጠ መልኩ ራስን በራስ የመሾም አባዜ እየተለማመዱ ነው፤ እሽቅድምድሙም በዚህ ዙሪያ አይሎአል " ሲሉ ገልጸዋል። " የፈተናው መንሥኤ ውጫዊ ሳንካ ባይጠፋበትም የውስጣችን ሰዎች ለሱ ምቹ ሆነው መገኘታቸው አልቀረም፤ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ፈተና የማይናቅ ጉዳት እየደረሰባት ነው፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ሰላምዋና አንድነቷ ጥያቄ ላይ ወድቆአል " ሲሉም አሳውቀዋል። ቅዱስነታቸው፤ " በመልካም አስተዳደርና በቂም በቀል እያሳበቡ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ብሎም ለማፍረስ መሮጥ በማናቸውም መመዘኛ ሚዛን አይደፋም፤ ውሃም አያነሣም " ያሉ ሲሆን " ችግር ሲኖር በመወያየት በጥበብና በሕግ ማረም እንጂ የጋራ ችግርን ለተወሰነ አካል በመለጠፍና እሱን ብቻ ተጠያቂ በማድረግ ንጹህ መሆን አይቻልም " ብለዋል። ባለፉት ዓመታት አስከፊ የሆነ በደል መፈጸሙን የገለጹት ቅዱስነታቸው " አሁንም አልቆመም፤ ይሁን እንጂ በደል ዛሬ ብቻ የተጀመረ አድርገን አናስብ፤ ይብዛም ይነስ በደል ፊትም ነበረ፤ ዛሬም አለ፤ ነገም የተለየ ነገር ይኖራል ተብሎ አይታሰብም " ሲሉ ገልጸዋል። " በደልን በካሣና በዕርቅ በይቅርታና በምሕረት መዝጋት፣ ተመሳሳይ በደል እንዳይፈጸም አስተማማኝ የሆነ ተቅዋማዊ ሥርዓትን ማበጀት መልካም ፈሊጥ ይሆናል፤ በደልንና ጥፋትን ምክንያት አድርገን እስከ ዘለቄታው መለያየትን መምረጥ ግን ራስን በራስ መጉዳት ይሆናል " ሲሉም አስገንዝበዋል። ጉባኤውም በዚህ ዙሪያ በስፋትና በጥልቀት በመወያየት ሁሉንም ሊያስማማ በሚችል መልኩ ወደ ሰላምና ዕርቅ ሊያደርስ የሚችል ስራ መስራት ይኖርበታል ብለዋል።
Mostrar todo...