cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ATC NEWS

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA ለመልዕክት 👇🏻 @mujaabot For Advertisement👇🏿 @atcads

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
116 413
Suscriptores
+224 horas
+797 días
+41030 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#አሳዛኝ_ዜና ኢዩኤል ታዬወርቅ ሸዋታጠቅ ይባላል። ተወልዶ ያደገው አዲስአበባ ኬንያ ኢምባሲ ከፍ ብሎ ልደታ ቤተክርስቲያን አካባቢ ነው። በጣም የቅርብ ቤተሰቤና ዘመዴ የሆነው እዩኤል (አቢቲ) በጎንደር ዩኒቨርስቲ የኪነህንፃ ኢንጅነሪንግ 5ኛ ዓመት ተማሪ ነበር። የፋሲካ በዓልን አያቱ ጋር አክብሮና እዛው ሲጫወት አድሮ በማግስቱ ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ከመጣ ታናሽ ወንድሙ ጋር ወደቤተሰቦቹ ቤት ሲመለስ ኬንያ ኢምባሲ አካባቢ እየተሰራ ከሚገኝና 14 ፎቅ እርዝመት ካለው ፎቅ ላይ ተወርውሮ የወረደ ብረት ጭንቅላቱ ላይ መቶት በአበባነት እድሜው በአሳዛኝ ሁኔታ ተቀጥፏል። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Mostrar todo...
የግል ዋይፋያችን #WiFi እንዳይጠለፍ እና ለመረጃ ጥቃት እንዳያጋልጠን በምን መልኩ መከላከል እንችላለን? ብዙ ጊዜ ለቤት ዉስጥ አገልግሎትም ሆነ ለመስሪያ ቤት ያስገጠምነዉ ዋይፋይ እኛ ላሰብነዉ አገልግሎት እየሰጠ ከሆነ ስለ ደህንነቱ ብዙም ትኩረት ስንሰጥ አይስተዋልም፡፡ ይህም በአንድ በኩል ከቸልተኝነት ወይም የሚያስከትለውን ጉዳት በውል ካለመገንዘብ ሲሆን፤ በሌላም በኩል የግል ዋይፋያችንን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል እውቀትና ግንዛቤ በአግባቡ ካለመያዝም ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህ አኳያ ለዋይፋዮቻችን ተገቢውን የደህንነት ስርዓት ተግባራዊ የማናደርግ ከሆነ የሳይበር ወንጀለኞች አውታረ-መረቡን /networks/ በመጠቀም ሚስጥራዊ መረጃዎችን መመንተፍ እና ዋይፋዩን በሚገባው ፍጥነት እንዳንጠቀም ሊያስተጓጉሉብን ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ከአገልግሎት መስተጓጎል እና ከጠላፊዎች ለመጠበቅ የሚከተሉትን አማራጮች መጠቀም ይመከራል፡፡ 1. ጠንካራ የይለፍ ቃል /password/ ይጠቀሙ የዋይፋይ ራውተሮች ሲመረቱ ነባሪ መጠቀሚያ ስም /default username/ እና ሚስጥራዊ የይለፍ-ቃል ይኖራቸዋል። የራዉተሩ አምራች ከታወቀ እነዚህን የዲፎልት መጠቀሚያ ስሞችን እና ሚስጥራዊ የይለፍ-ቃላትን ለመገመት በጣም ቀላል ነው፡፡ በመሆኑም የግል ዋይፋዮቻችን ደህንነት ለማረጋገጥ “default username” በመቀየር ጠንካራ የይለፍ-ቃሎችን መጠቀም ይገባል፡፡ 2. የበይነ-መረብ አገልግሎት መስጫ መለያ ይቀይሩ /service set identifier - SSID/ እያንዳንዱ ራውተር ከነባሪ መጠቀሚያ ስም /default/ ጋር ስለሚመጣ የአውታረ መረባችንን አገልግሎት መስጫ መለያ ስም /SSID/ መለወጥ ያስፈልጋል። ይህንን በራውተራችን ገመድ አልባ መሰረታዊ ቅንብር ገጽ /wireless basic setting page/ በመሄድ መጠሪያውን በመለወጥ የዋይፋያችንን ተገማችነት በማስቀረት ለጥቃት እንዳንጋለጥ ማድረግ እንችላለን፡፡ 3. አውታረ-መረባችንን መመስጠር የዋይፋይ ራውተራችን ከመረጃ ጠለፋ እና የአገልግሎት መስተጓጎል ለመከላከል የአውታረ-መረብ ምስጠራን መተግበር አስፈላጊ ነዉ፡፡ 4. ሎጊንግ መፍቀድ (Enable Logging) ሎጊንግ አማራጭን ስንፈቅድ (Enable) ስናደርግ የዋይፋይ ኔትወርካችንን እንዳይጠለፍ ለማድረግ ከሚያግዙ መንገዶች አንዱ ነዉ፡፡ በዋይፋይ ራውተራችን ውስጥ ያለው የመለያ ባህሪ ሁሉንም የአይፒ አድራሻ ይመዘግባል፡፡ እንዲሁም ሁሉንም የግንኙነት ሙከራዎች ዝርዝር ይሰጣል። ምንም እንኳን ይህን ተግባራዊ ማድረግ ዋይፋያችንን ከጠላፊዎች የማይጠብቅ ቢሆንም ማንኛውንም አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ለመከታተል ይረዳናል፡፡ ይህንን ስርዓት "Enable" ማድረግ ይገባናል፡፡ 5. የዋይፋይ ሲግናል ማስተካከል የዋይፋይ ሲግናላችን ጠንካራ እና በአጭር የቆዳ ስፋት ብቻ ለመጠቀም የዋይፋዩን ሲግናል አቅም መቀነስ ይኖርብናል፡፡ ይህን ለማድረግ የራውተራችንን ሞድ 802.11n ወይም 802.11b ምትክ 802.11g መጠቀም ይመከራል፡፡ 6. የራውተራችንን ፈርምዌር ማዘመን ራውተራችን ፈርምዌር /Firmware/ ጊዜው ያለፈበት እና በወቅቱ ያልዘመነ ከሆነ ለአንዳንድ የደህንነት ስጋቶች የተጋለጠ መሆኑ አይቀርም፡፡ ምንም እንኳ የዘመናዊ ራውተሮች ፈርምዌር በራሳቸው የሚያዘምኑ ቢሆንም እርግጠኛ ለመሆን በየጊዜው መዘመናቸውን ልናረጋግጥ ይገባል፡፡ 7. የራውተራችን ፋየርዋል ማንቃት የራውተራችንን ፋየርዎል /firewall/ ማንቃት ይኖርብናል፡፡ ይህን በማድረጋችን ሊከሰት ከሚችል ተጨባጭ የሳይበር ጥቃቶች እራሳችንን መከላከል ያስችለናል፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Mostrar todo...
ATC NEWS

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA ለመልዕክት 👇🏻 @mujaabot For Advertisement👇🏿 @atcads

ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች Entrance Hubን ስጠቀሙ 👌የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ1972-2015ዓ/ም 👌የ10ኛ ክፍል ፈተና ከ1996-2010ዓ/ም 📒 አጫጭር Note ከ9-12ኛ 🔹በየቀኑ መጠናከሪያ ትምህርቶችን ማግኘት ይችላሉ። ለ2016 Online ፈተና  ልምምድ እንድታደርጉ ታስቦ የተዘጋጀ መተግበሪያውን ለማውረድ ይህን ይጫኑ👇https://bitly.yt/olan7 🔹ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎብኙ @EntranceHubEthiopia
Mostrar todo...
FULLY FUNDED - Fellowship Program in the USA 2025-26 Host Country: United States Host Institute: Harvard Radcliffe Institute Benefits: Fellows receive a stipend of $78,000 plus an additional $5,000 to cover project expenses. Fellows may also be eligible to receive relocation, housing, and childcare funds to aid them in making a smooth transition to Radcliffe. Health care support is made available as needed. Application Deadline: Humanities, Social Sciences, Creative Arts: September 12, 2024 Science, Engineering, Mathematics: October 3, 2023 For more information, Join @scholarshipsFESl
Mostrar todo...
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መስጠት ሊጀምር ነው። ዩኒቨርሲቲው በቅደመ ምረቃ እና በድኅረ ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች ተመርቀው ወደ ሥራ ዓለም ለሚገቡ ተመራቂዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ለመስጠት መዘጋጀቱን የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት ጀሉ ዑመር (ዶ/ር) ተናግረዋል። የሙያ ብቃት ማረጋገጫው ከመጪው መስከረም ጀምሮ መሰጠት የሚጀመር ሲሆን ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀና የገበያውን ፍላጎት መሰረት ባደረገ መልኩ እንደሚከናወን ም/ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል። የሙያ ብቃት ማረጋገጫው በሁሉም ዘርፎች ይሰጣል የተባለ ሲሆን ፕሮግራሙ የሚመራበት አሰራር ይዘረጋል ተብሏል፡፡ በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያሉ ተማሪዎችም ሆኑ በሥራ ገበያ ያሉ ሰራተኞች እና ምሁራን ለተማሩበት ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ወይም ፕሮፌሽናል ሰርትፊኬት መውሰድ እንደሚችሉ ተገልጿል። #ENA ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Mostrar todo...
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ!😍 ለ2016 Entrance ተፈታኞች  online ፈተና  ዝግጅት እንዲታደርጉ Entrance Hub Ethiopia አዲስ ነገር ይዞ መጥቷል👌 በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ሁሉንም ብሄራዊ ፈተና ጥያቆዎችን ከነመልሱ እና ማብራሪያ ጋር የያዘ መተግበሪያ ይፋ አድርጓል። በውስጥ 👉የ12ኛ ክፍል ፈተና  ከ1972-2015 ዓ/ም 👉የድሮ 19 ክፍል ፈተና ከ1996-2010ዓ/ም 👉 Short Note 👉 Review Tutorial ጭምሮ ይዞላችሁ መጥቷል። መተግበሩያውን 👉 https://bitly.yt/olan7  ያውርዱ ይጠቀሙ! ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎብኙ 👨‍🚒@EntranceHubEthiopia
Mostrar todo...
#ExitExam #Re_Exam #UnityUniversity ድጋሚ የመውጫ ፈተና ሰኔ ላይ ለምትወስዱ (June 2016 Re-Exit Exam) 1. 2015 ዓ.ም ለመፈተን ተመዝግባችሁ "Username"  ወስዳችሁ፣ ፈተናውን ያልወሰዳችሁ እና በቀጣዩ ሰኔ ላይ መውሰድ የምትፈልጉ ተማሪዎች፣ በአካል እስከ አርብ ድረስ ቢሮ ቁጥር 02 ማመልከት ይኖርባችኋል። 2. በ2016 የካቲት ላይ "username" ወስዳችሁ ያልተፈተናችሁ ቀጥታ መመዝገብ ስለምትችሉ ቢሮ መምጣት አይጠበቅባችሁም። 3. ፈተናውን በድጋሚ የምትወስዱ ተማሪዎች፣ ምዝገባና ክፍያ በራሳችሁ ሲሆን፣ ቀኑን እንዳሳወቁን እናሳውቃለን። 4. ክፍያ የሚከፈለው በቀጥታ በቴሌብር ለትምህርት ሚኒስቴር ነው። ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Mostrar todo...
ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና በከተማ አቀፍ ደረጃ ግንቦት 1 ቀን የሚሰጥ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ በመሆን የሚሰጠውን ከተማ አቀፍ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና አፈጻጸምን አስመልክቶ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ምዘናው መንግስት ለትምህርት ጥራትና መሻሻል ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በተሻለ ለመምራት የሚያስችል መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ቁልፍ ሚና ያላቸው አካላት በመሆናቸው ምዘና መደረጉ ተገቢና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ዋነኛው ሂደት ነው ብለዋል፡፡ ዶክተር ዘላለም አያይዘውም ፈተናውን በተሳካ መልኩ ለማካሄድ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ በበኩላቸው ምዘናው የመምህራንን የሙያ ብቃት ለማሳደግና እውቅና ለመስጠት ከማስቻሉም በላይ መምህራንና የትምህርት አመራሩን በበቂ ስነ-ልቦና ለማስተማርና ለመምራት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡ የምዘናውን አካሄድ ውጤታማ ለማድረግም የትምህርት አመራሩና የክፍለከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊዎች ለተፈታኞች የሚሰጡ ቅድመ ምዘና ገለጻዎች ላይ በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡ ምዘናው በፈቃደኝነት ለተመዘገቡ 18 ሺ 591 ለሚሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራሮች ሃሙስ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም በተመረጡ የመፈተኛ ጣቢያዎች እንደሚሰጥ እንዲሁም በምዘናው ወቅትም ተመዛኞች ስልክም ሆነ ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ ግብአቶች ይዘው ፈተና ክፍል መግባት እንደማይችሉ ፣ ተመዛኞች የታደሠ መታወቂያ ይዘው መገኘት እንደሚጠበቅባቸው ፣ ተመዛኞች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት 1:00 ሠዓት ቀደም ብለው (1:30) ላይ የምዘና መስጫ ቅጥር ግቢ ውስጥ መገኘት እንዳለባቸው እና አርፍዶ መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ ፣ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አድማሱ ደቻሳ ፣ የባለስልጣን መስራቤቱ ማኔጅመንት አባላት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳና አባላት ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እንዲሁም የሁለቱም ተቋማት የክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
Mostrar todo...
Repost from SKET TRAVEL AGENCY
Are you MECHANICAL, ELECTRICAL, ENVIRONMENTAL or CIVIL ENGINEER ? Do you want to pursue your masters degree in Italy🇮🇹 ? ✅low gpa possible ✅all engineering ✅computer science ✅no proficiency test ✈️no PRE PAYMENT required 🔵Required documents 🔵 ✔️Passport(national id ) ✔️original degree(Temporary) ✔️student copy ✔️recommendation letter ✔️medium of instruction (from the university) ✔️3*4 or DV format photo ☎️ contact us at : @consultfrit 🧡 🌐 https://t.me/consultfrit 🧡 ✈️ 0972859680💠 ✈️ 0934155601💠 https://t.me/studyinitalyconsultant
Mostrar todo...