cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የዓለም እውነታ

ይህ ቻናል እራሳችንን እንድንመለከትና የተሰጠንን ትልቅ ሀብት እኛነታችንን ፈልገን እንድናኝ የተከፈተ ቻናል ነው፡፡ " አመለካከት ረቂቅ የአዕምሮ ተግባር ነው አካላችን ዓይን እንዳለው ሁሉ አዕምሯችንም ዓይን አለው የሀሳቡን ዓለም የሚያይበት ። "

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
194
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#ካነበብኩት_ አንብቡት እንደ እኔ ትወዱታላችሁ “የዓለማችን ምርጥ "የፍቅር ታሪኮች” ከተሰኘው መጽሐፍ ውስጥ ነው# “ፍቅር ዕብደት” የተሰኘው ታሪክ እነሆ# ድሮ ድሮ ነው አሉ….ያኔ በጥንት ዘመን፡፡ ገና አለም ሳይፈጠር ሰው የሚሉት ፍጥረት ሳይኖር!# እግዚአብሄር የሰው ልጅ ባህሪያት የሚባሉትን ሁሉ ባንድ የተወሰነ ቦታ ከልሎ አስቀምጧቸው ነበር# ለረጅም ጊዜ በአንድ ቦታ ተከርችመው መቀመጥ የሰለቻቸው ባህሪያት ድብርቱን ለመግፈፍ ጨዋታ አመጡ፡፡ ድብብቆሽ ሊጫወቱ ተነሱ፡፡# ከባህሪያቶቹ መካከል ድንገት እብደት ተብዬው ተነሳና እኔ እቆጥራለሁ እናንተ ተደበቁ አለ፡፡ ወዲያው ነው ሁሉም የተስማማው# አዎና…ማን ሞኝ አለ እብደትን ተደበቅ ብሎ እሱን የሚፈልግ፡፡ ከዚያ በኃላ እንግዲህ እብደት ፊቱን አዙሮ መቁጠር ጀመረ# አንድ…ሁለት…ሦስት፣ ይሄኔ ባህሪያቱ ለመደበቅ ይጣደፉ ጀመር፡፡ ሁሉም በአገኘው ስርቻ ተሸጎጠ ….ለምሳሌ ያህል ውሸት ድንጋይ ስር እደበቃለሁ ብሎ ለፍፎ ሲያበቃ ሀይቁ ውስጥ ገብቶ ተደበቀ፡፡ እብደት መቁጠሩን ቀጥሏል….ሰባ ዘጠኝ፣ ሰማኒያ ፣ሰማኒያ አንድ….ይሄኔ ከፍቅር በስተቀር ሁሉም ባህሪያቶች በየስርቻው ተደብቀዋል፡፡ ጅሉ ፍቅር ብቻ ሳይደበቅ ተንከርፍፎ ቀረ፡፡# ለነገሩ ይሄ አይደንቀንም፡፡ የፍቅር ባህሪው ይኸውም አይደል፡፡# ፍቅርን መደበቅ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ አይጠፋንም! ለማንኛውም እብደት መቁጠሩን ቀጥሏል፡፡ ዘጠና አምስት፣ ዘጠና ስድስት፣ ዘጠና ሰባት….እያለ ነው# እብደት ልክ መቶ ላይ ሲደርስ ፍቅር ዘሎ የፅጌረዳ ቁጥቋጦው ውስጥ ገብቶ ተደበቀ፡፡ እብደት መቁጠሩን ጨርሶ መጣሁላቸሁ እያለ መፈለግ ጀመረ፡፡ መጀመሪያ የተያዘው ስንፍና ነው፡፡ ዳተኛው ስንፍና ለመደበቅ ካለበት ቦታ ብዙም ሳይርቅ ተያዘ፡፡ እብደት ባለ በሌለ ሀይሉ በርብሮ ከሀይቁ ጥልቀት ውስጥ ውሸትን ፈልፍሎ አወጣ፡#፡ እብደት አንድ በአንድ ሁሉንም ባህሪያቶች መንጥሮ ሲያወጣ አንድ ባህሪ ግን እንደተደበቀ ቀረ፡፡ ፍቅር፡፡ እብደት ፍቅርን ፈልጎ ሊያገኘው ባለመቻሉ ተስፋ ወደ መቁረጥ አዘንብሎ ነበር# በስተመጨረሻ ግን በፍቅር ላይ ቅናት ያደረበት ባህሪ ወደ እብደት ጠጋ ብሎ ፍቅር የተደበቀው በፅጌረዳ ቁጥቋጦው ውሰጥ ነው ሲል አንሾካሾከለት፡፡# ይሄኔ እብደት ዘሎ የፅጌረዳው ቁጥቋጦ ውስጥ ሲገባ ፍቅር ከቁጥቋጦው ውስጥ ታላቅ ጩኸት አሰማ፡፡# የፅጌረዳው እሾህ የፍቅርን አይኖች ወግተው አጥፍተውታል፡፡ እንግዲህ ከዚህ በኃላ ፍቅር እውር ሆነ፡፡ የፍቅርን የስቃይ ጩኸት ሰምቶ የመጣው ፈጣሪ ባየው ነገር አዘነ እናም እብደትን ፈጣሪ እንዲህ አለው…. ‘ፍቅር እውር የሆነው ባንተ ሰበብ ነው# በመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ ፍቅር የገባበት ቦታ እየተከታተልክ የምትመራው አንተ ትሆናለህ፡፡ መቼም ቢሆን አብራችሁ ትሆናላችሁ፡፡ እናም አንተ መንገድ ታሳየዋለህ፡፡# ...እንግዲህ @Yefiqr ከዚህን ጊዜ ጀምሮ እውሩ ፍቅር በእብደት እየተመራ ያላሰሰው የምድር ክፍል ያልጎበኘው ጎጆ የለም፡፡ ከዚያን ዘመን አንስቶ የዕውሩ ፍቅር ክንፍ እብደት ሆነ፡#፡ እናም ከዚያን ጊዜ አንስቶ የንጉሱን ቤተ መንግስት ከደሳሳው ጎጆ ፣የሩህሩሁን ልብ ከጨካኙ፣ ቸሩን ከንፋጉ፣ ምሁሩን ከመሃይም፣ ደፋሩን ከፈሪ እንደቀየጠ አለ# አለምም በዚህ ቅይጥ ሳቢያ ይበልጥ ህብረቀለማዊ እንደ ሆነች አለች፡፡ @Yefiqr @Yefiqr ከወደዳችሁት share# share #እናመሰግናለን
Mostrar todo...
👆ጭንቀት_ ክፍል 2 (#ራስ አገዝ) በባለፈው ሳምንት የጭንቀት ምንጩንና ምንነቱን ለማየት ሞክረናል። በዚህ ሳምንት መፍትሄው ላይ አተኩረን እንመለከታለን። የጭንቀት መፍትሔ በህክምና እይታ 1. Questioning cognitions ብዙህ ጊዜ ሰዎች በጭንቀት ሲዋጡ በህክምናው ቅድሚያ ትኩረት የሚሰጠው ነገር የጭንቀቱን ምንጭ በመለየት በጣም ቀላል በሆነ መንገድ ለመረዳት መሞከር ነው። ለምሳሌ ብሌን ለምን እንደተጨነቀች ትጠይቃለች። በስራዋ ስትመሰገን የቆየች ጎበዝ ናት። አዎ ጎበዝ ነኝ ትላለች። ምን ተፈጠረ ታድያ? ሰሞኑን አለቃዋ በስራዋ ተችቷታል። ይሄ ያስጨንቃል። በመጨናነቋ ብዛት ከስራዋ ስለመባረር ማሰብም ጀምራለች። ከላይ በጠቀስነው መንገድ ግን ጥያቄውን ወደ ትንንሽ ጥያቄዎች በታትና እያንዳንዱን ጥቃቅን ነገር እየጠየቀች ይሄ በርግጥ ከስራ ያስባርር ይሆን? ካለች ግን እስካሁን ያላት performance በስራዋ የነበራት ተቀባይነት ከግምት ውስጥ ገብቶ የተፈጠረው እንኳን ሊያስጨንቅ ኢምንት መሆኑን ትረዳለች። ስለዚህ ስለምን እንደተጨነቅን በደንብ ለማወቅ እንሞክር። የጭንቀቱን ምንጭ እንወቅ! የትኛው አጋጣሚ ይሄንን ሊፈጥር እንደቻለ ልብ እንበል። ቀጥለን ነገሮቹን በተናጠል ስንመለከታቸው ከስሜታዊ ውሳኔ ወጥተን ምን እንደተፈጠረ እንድንረዳ ይረዳናል። በተጨማሪም በእኛ በኩል ያለውን ክፍተት እንድናይ እና ሚዛናዊ ውሳኔ እንድንወስን ይረዳናል። ይህ መንገድ ጭንቀትን ለመቀነስ አና ችግሮችንም ለመፍታት ይጠቅመናል መንፈሳዊ እይታ ሰዎች ሁሉን ነገር በራሳችን የምንፈታ በቤታችን ወይም በህይወታችን እኛ ብቻ ሁሉን ማድረግ የምንችል መስሎ ይሰማንና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን በጎ ነገር እንረሳለን። አንዳንድ ጉዳዮችን በቀጥታ ለእግዚአብሔር በጸሎት አሳውቆ ከማረፍ ይልቅ በራሳችን ጭንቀት የምንለውጠው ስለሚመስለን እንዳክራለን። ጌታችን በማቴዎስ ወንጌል 7:7 ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ወይስ ከእናንተ፥ ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? ያለውን ቅዱስ ቃል በማሰብ ሁሉን ለእግዚአብሔር መተው እና አለመጨነቅ ልንለምድ ይገባናል። ይበልጥ ደግሞ በተጨነቅን ቁጥር ለለመነ የሚሰጥ አባት አለንና ጭንቀታችንን ትተን የምንፈልገው እንዲሰጠን እንለምን። ኦርቶዶክሳዊው አባት አባ ፓይሲዮስ እንዲህ ይሉናል completely have trust in God, leave everything in his hands, believe that his love will act for your own benefit. Then God will take care of everything, because there is nothing he cannot do. Everything is easy for him. The difficult thing is is for man to decide to humble himself and leave everything to God's province and Love.[ በእግዚአብሔር ፍጹም ታመኑ ። ሁሉ ነገራችሁን አሳልፋችሁ ለእርሱ ስጡት ። ለማይጠቅማችሁ ነገር የአባትነት ፍቅሩ አሳልፎ አይሰጣችሁም ። ሁሉንም ነገር እርሱ ይፈታዋል ፤ ለእርሱ ቀላል ነው ምክንያቱም እርሱ የማይሳነው አምላክ ነውና ።ለሰው የሚከብደው ግን እራሱን በትህትና አዋርዶ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሄር ለመስጠት መወሰኑ ላይ ነው ።
Mostrar todo...
#ጨጓራ #ህመም # ለምን #በተደጋጋሚ # ይከሰታል ዠ? ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የቴሌግራም ቻላናችን ቤተሰቦቻችን ለዛሬ የጨጓራ ህመም ለምን በተደጋጋሚ እንደሚከሰት እንመለከታለን እነሆ፦ የጨጓራ ህመም፦ የጨጓራ መቆጣት፣ መብገን ወይም ጨጓራ ላይ ያለው ፈሳሽ ወደ ላይ መመለስን ያጠቃልላል ይህም የሚሆነው የጨጓራ አሲድ በሚበዛበት ወቅተ ነው፡፡ መንስኤው የጨጓራ ባክቴሪያ የሀሞት ወደ ላይ መመለስ የጨጓራ አሲድ መብዛት መድሀኒቶችን አብዝቶ መውሰድ የአመጋገብ ስርዓት ጭንቀት የአልኮል መጠጥ ምልክቶችን ማቅለሽለሽ በተደጋጋሚ የጨጓራ መቆጣት የሆድ መነፋት የሆድ ህመም ማስመለስ የምግብ አለመፈጨት ትንታ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ደም የቀላቀለ ትውከት የሰገራ መጥቆር ለምን በተደጋጋሚ እንታመማለን? የአመጋገብ ለውጥ ካላደረግን ውሀ ከምግብ በፊት የማንጠጣ ከሆነ ምግብ በስርዓት የማንመገብ ከሆነ ጭንቀት ካለ አልኮል ተጠቃሚ መሆን ምርመራው ወደ ሆደ በሚገባ ካሜራ(Endoscopy) መመልከት የደም ምርመራ የሰገራ ምርመራ መፍትሄው መፍትሄው በአጠቃላይ እንደ መንስኤው እና ምልክቱ ይለያያል ስለዚህ ለጨጓራ አሲድ መብዛት፦ አሲድ እንዲረጋጋ የሚያደርግ መድሀኒት መጠቀም እና የመጋገብ ለውጥ ማድረግ ይሆናል ለጨጓራ ባክቴሪያ፦ በባለሙያ የሚታዘዝ ሶስት አይነት መድሀኒቶችን መጠቀም እና የመጋገብ ለውጥ ማድረግ አልኮል ማቆም ውሀ ከምግብ 30 ደቀቃ መጠጣት እንዲሁም ከምግብ 30 በኋላ መጠጣት ጭንቀትን ማስወገድ
Mostrar todo...
#Tech_Facts 😁 የቴክኖሎጂ እውነታዎች 🔰 ዛሬ ከ3.8 ቢሊዮን በላይ ሰዎች Internet ይጠቀማሉ ይህም ከዓለም ህዝብ 40 በመቶው ነው። 🔰 በየ57 ደቂቃው ከ570 በላይ አዳዲስ Websites ይፈጠራሉ። 🔰 በየቀኑ ከ3.5 ቢሊዮን በላይ Google Search ይደረጋል። 🔰 በ2020 ቪዲዮ ከሁሉም ከInternet ትራፊክ 80% ያህሉን ይይዛል። 🔰 40,000 የTwitter ትዊቶች በደቂቃ ይላካሉ በቀን 500 ሚሊዮን ትዊቶች ማለት ነው። 🔰 በAmerica ከሚደረጉ ከ7 ፍቺዎች መካከል ለአንዱ ፌስቡክ ተጠያቂ ነው። 🔰 በ2020 ከ8.2 ቢሊዮን በላይ መረጃዎች ተሰርቀዋል ወይም Hack ተደርገዋል። 🔰 የመጀመሪያው ኮምፒዩተር ወደ 2.5 ሜትር የሚጠጋ ቁመት ያለው ሲሆን ክብደቱ ወደ 30,000 ኪ.ግ. ይመዝናል። 🔰 NASA ውስጥ የInternet ፍጥነት በሰከንድ 90GB ነው። 🔰 በዓለም ትልቁ ሃርድ ድራይቭ 60TB SSD ነው። 🔰 Bluetooth ኖርዌይን እና ዴንማርክን አንድ ባደረገው ሃራልድ ብሉቱዝ በተባለ ንጉስ ተሰየመ ነው። 🔰 የጉግል መሥራቾች እ.ኤ.አ. በ1999 ጉግል ን በ1 ሚሊዮን ዶላር ለመሸጥ ፈቃደኞች ቢሆኑም Excite ግን አልተቀበላቸውም። ጉግል አሁን 527 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ አለው። 🔰 እስኪ የ Gmail አካውንት ያላችሁ 2 ደቂቃ የማይፈጅ Task ልስጣችሁ እዚህ ላይ ገብታችሁ የKal Kal Tube Technology የYoutube ቻናል Subscribe አድርጉ 👉 https://youtu.be/O3SGMugWieU
Mostrar todo...
Ethiopia:ምርጥ የ Volume button style መቀየሪያ App |Habi faf||Lij bini||Key Tube|Abel brhanu|Shambel App|

ሰላም ውድ Kal Tube Technology ተከታታዮች ዛሬ በአይነቱ ለየት ያለ ምርጥ App ይዤ መጥቻለሁ የ App ስም ( Volume Style )ይባላል volume style ከፈለጉት በዚህ Link ማግኘት ይችላሉ

https://t.me/joinchat/...

ችግር የቀመሰ..!!! ሰላም ሰላም ውድ ቤተሰቦቼ እዴት ናቹ............ ዛሬ እንግዲ ስለ ችግር ጢቂት ነገር እን ልበላቹ ችግር በብዙ መልኩ ሊደርስ ይችላል በይዘቱም እደሰው ማንነትና ጥንካሬ ይለያያል ተብሎ ይታሰባል። በታርክ መነፅር ወደ ዋሊት ዞረን ስናይ ብዙ አይነት ችግሮች ማስተዋለ እችላለን ግን የሚደንቀው እዴት (solution) እደገኙም በዛው እንማርበታለን ሌላ ሰው በሌላ ሰው ችግርም መፍትሔም ሊያመጣ ይችላል ከቀላል እስከ ባድ ምክንያቱም እቅስቃሴ ካለ ሐይል ማውጣት ትጀምራለክ እየሰራክ ስለሆነ ስራክ ምንም ይሁን ባለ ስልጣንም ሁን ትንሽዬ ስራም ትኑርህ (በነገራችን ላይ ተራ ሰራተኛ አይባልም መክንያቱም ያ ስራ ለርሱ ድቅና እጅግ ምርጥ ስለሆነ የሰው ነገር ስናከብር የኛም ይከበርልናል) በቃ የፈለከውን ሁን የፈለከውን ስራ ችግር ግን ያንተ ጥላክ ናት እደ ወርቅ ነጥረህ ከወጣህ በጣም ታምራለህ ተፈላጊነትህም ይጨምራል የን ግዜ ያ ሌላ ሰው አጥብቆ ስላተ ያወራል ይፈልግሐል። በአለማችንም ታዋቂ ሰዋች ለስኬት የበቁት በችግር ተፈትነው ነዉ። ድቅ ድቅ ነገር የተባለላቸው የተፃፈላቸው የችግራቸው ተራራ መፍትሔ ሰተው የስኬት ተራራ ስለወጡ ነው አድ ሰው አላማ ካለው ላነገበው (ለታጠቀው)አላማ ምንም ሊያረግ ይችላል። ህወት እደ ሳይክል ናት ይለኝ ነበር አድ ወዳጄ ሳይክል ስንነዳው ገና ስንለምደው እየወደቅን እየተነሳን ነው አወዳደቁም እደየ ብቃታችን መጠን ይለያያል ለም ደንውም አንውደቅ እጂ አልፎ አልፎ መጠነኛ ነገር ይገጥመናል። እናም ጋደኛዬ ትክክል ነው ? እላለሁ ችግርን መፍራት የለብንም ስራ ቅጥር ለምዛና ሔደህ ካለልተሳካልን ማማርም የለብን ንግድም ጀምረን ካልተሳካልን ........ መፍትሔ... ከታርክም ። ከታላላቆቻችን የህወት መዝገብ ስንገልጥ ዋነኛ የምንማረው ❶ትግስት የትግስት ፍሬ ጣፋጭ ናት የቀመሰው ያቃል☺ ❷ጥበብ ለጠቢብ ሰው ጥበብ ምኑ ናት ❸አለማ አላማ ካለህ አተ የማይነቃነቅ ገዙፍ ተራራ ነህ ወይም ጠካራ ብረት ነህ '' ችግር ብለሐትን ያስተምራል '' መጨረሻላይ ላዝማር ባጃው የድልን ግጥም ትሰጣለህ ተቀበል.. ችግርማ ድቅነው ባጃው። ችግርማ ድቅነው አስተውሎ ላየው እደወረቅ የሚያነጥር የስኬት በር ነው ቀረሁኝ ◎◎◎◎◎ መጥፋቱንስ ጥፊ መቅረቱንስ ቅሪ ከጎኔ ስትለይ እሆናለሁ ፈሪ እህ..እህ..ህ አህት አለሜ ትመጪ መስሎኝ ቀረሁኝ ቆሜ 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 ይህ ቻናል እራሳችንን እንድንመለከትና የተሰጠንን ት @Tulubolotube
Mostrar todo...
ከጳውሎስ ኞኞ ታላቅ ሰው◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦??? በህይወት ታላቅ ሰው ለመሆን ከፈለክ ሞራልህን ጠብቅ ሞራልህን ሊያሳጣ የሚችሉትን አሉታዊ ንግግሮችን አታዳምጥ ◌◎◌◎◌◎◌◎◌◎◌◎◌◎◌◎◌◎◌◎◌◎◌◎◌◎◌◎◌◎◌◎◌ አተ የምትወድቀው ገንዘብ ወይም እውቀት አልፎ ተርፎ ዝና ስልጣን ስታጣ አይደለም ሞራል ሲወድ ብቻ ነው ሞራሉ የወደቀ ሰው ❶ ለሰው ሞራል አይጨነቅሞም ❷ ተጠራጣር ነው ❸ በራስ መተማመን የለውም መፍትሔው ❶ሞራሉን ከሚጎዱ ነገሮች መራቅ ❷በተቻለ መጠን አነቃቂ ንግግሮች ማበብ ና መልካም አስተሳሰብ ካላቸው ሰዋች ጋር ጋደኛ መፍጠር ❸በመንፈሳዊ ህወትና በማህበራዊ ተሳትፎ ማረግ ◎◌◎◌◎◌◎◌◎◌◎◌◎◌◌◎◌◎◌◌ ውድ ቤተሰቦቼ ስላነበባቹ ከልብ አመሰግናለሁ ደግ ደጉን እናስብ መልካምነት ተመልሶ ይከፍለናለንና መልካም አዳር🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌 📲📲📲📲📲📲📲ይህ ቻናል እራሳችንን እንድንመለከትና የተሰጠንን ትልቅ ሀብት እኛነታችንን ፈልገን እንድናኝ የተከፈተ ቻናል ነው፡፡ " አመለካከት ረቂቅ የአዕምሮ ተግባር ነው አካላችን ዓይን እንዳለው ሁሉ አዕምሯችንም ዓይን አለው የሀሳቡን ዓለም የሚያይበት ። "
Mostrar todo...
ሰላም ውድ ቤተሰቦቼ እካን አደረሳቹ የመስቀሉ ፍለጋ ከንጉሥ ኢንዳስ እስከ ንግሥት ዕሌኒ፤ ድርሳነ መስቀል አንዲት፣ ቅድስት፣ ኵላዊትና ሐዋርያዊት የሆነች በክርስቶስ ደም የተዋጀችውና በምድርና በሰማይ ያለችው የሥውርንና የገሃዳውያን፣ የረቂቃንና የግዙፋን፣ የሙታንና የሕያዋን፣ የብሉይና የሐዲስ ምዕምና አንድነት የሆነችው ቤተክርስቲያን በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያ በዓደባባይ ከምታከብረውና ለዓም ድኅነትን ከምትሰብክበት በዓላት አንዱ የመስቀል በዓል ነው፡፡ የዓለም መድኃኒትና ቤዛ የሆነው ክርስቶስ አዳኝነቱን ለዓለም ሊሰብክ ከዓለም ሁሉ ተለይቶ በሚገኝ በቀራንዮ ጎልጎታ በሚባል ቦታ በመስቀል ከፍ ብሎ ተሰቅሎ ድኅነትን ሰበከልን፡፡ ሰው ልቡ ከታወረ ከፍ አድርገህ ብታሳየውም እሱ ዝቅ ብሎ ይፈልጋልና ይህን የድኅነት መስቀል አይሁድ ባለመረዳት ብሎም ክርስቶስ ከተሰቀለ፣ ከሞተና ካረገ በኋላ መስቀሉ ለሰው ልጆች ሁሉ የሚሰጠው የድኅነት ሥራ በመቀጠሉና ዕውራን ሲበሩ ሀንካሳን ሲረቱ፣ ዲዳዎች ሲናግሩ፣ ደንቆሮዎች ሲሰሙ ለዚህ የድኅነት ምሥጢር ያልታደሉ አይሁዳውያን ዓይናቸው ታውሮ፣ እጅና እግራቸው ተሰነካክሎ፣ አንደበታቸው ታሥሮ፣ ጀሮአቸው ደንቁሮ በአጠቃላይ ልቡናቸው ጨልሞ የመድኃኒታቸውን መሣሪያ ለማሣሣት ሲባል ከወንበዴዎች መስቀል ጋር ቀበሩት፡፡ በዚህ ያላበቃው ክፋታቸው ለሦስት መቶ ዓመታት ሕዘቡ ሁሉ ቆሻሻ እንዲደፋበት እያደረጉ በተራራ ሸፈኑት፡፡ ይሁን እንጅ በዘመናት ብዛት ተቀብሮ የኖረውን መስቀል ለመፈለግ ብዙ ትውልድና ነገሥታት ደክመው የደከሙት ትውልድ ክፋይ የሆነችው ንግሥት ዕሌኔ እንድትገልጠው አደረገ፡፡ የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ አባ መቃርዮስ ያዘጋጁትና በአባ ገ/መድኅን ደስታ በግዕዝና አማርኛ የተዘጋጀው የደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ያሳተመው ድርሳነ መስቀል የተሰኘው መጽሐፍ ስለመስቀሉ ፍለጋ የደከሙትን ነገሥታትና ትውልድ እንድ ድርና ማግ አሰናስሎ ልብን አንጠልጥሎ አንደ ውሃ ጅረት እያከታተለ ይተርክልናል፡፡ በዚህ ረገድም የመስቀሉን ፈላጊ የመጀመሪያው ንጉሥ ንጉሥ ኢንዳስ ይለዋል፡፡ 1. ንጉሥ ኢንዳስ፡- የሮም ሀገር ንጉሥ የሆነው ኢንዳስ በዕውነትና በትክክል የሚፈርድ ስለቀናች ሃይማኖት ጌታ የሚወደውና ከጌታ የታዘዘች ደመና ከዕለታት አንድ ቀን ካህኑ መልከጼዴቅን አምጥታ ቅብዓ መንግሥት ቀብቶት መንግሥት ከዘሮቹ እደማይወጣ ነግሮት ሲሄድ በሌላ ጊዜ የተላከ መልአክም ከአንተ የልጅ ልጅ የክርሰቶስ መስቀል የገኛል የሚል የደስታ ቃል አሰምቶት ሄደ፡፡ ይህ ንጉሥ በእውነት አገልግሎ መስከረም 17 በመልአኩ ቅ/ሚካኤል አማካኝነት ዜና እረፍቱ ተነግሮትና ከእሱ ቀጥሎም ልጁ አልዓዳድን አንግሦ በዚህች ዕለት በክቡር በምትጥም ዕንቅልፍ አምሳል አረፈ ይላል፡፡ 2. ንጉሥ አልዓዳድ፡- እንደአባቱ በሃይማኖትና በመልካም ሥራ እግዚአብሔርን የሚያገለግል አላውያን ነገሥታትን በጌታችን፣ በእመቤታችን፣ በቅዱስ ሚካኤልና ገብርኤል ስም ብሎም በመስቀል በማማተብ ጦርነት እየገጠመ ድል እየነሣ ከኖረ በኋላ ሠራዊቱን አስከትሎ የጌታችንን የመቃብር ቦታ ለመጎብኘት 5 ወር ከ5 ቀን ተጉዞ በመጎብኘት መስከረም 17 ታላቅ ዝክርን እየዘከረ እርሱ ከሰንበትና ከጌታ በዓላት ውጭ እንጀራ ሳይበላ በአልጋ ሳይተኛ በድንኳን አመድ ነስንሶ እየተኛ ከኖረ በኋላ እረፍቱ በመልአክ ተነግሮት ታህሣሥ 12 እንደምትጥም እንቅልፍ ጻዕር ሳያገኘው ዐረፈ፡፡ 3. ንጉሥ አግድር፡- የሮሜ መሣፍንትና መኳንንትም ልጁ አግድርን አነገሡት እንዲል ቀጥሎም የነገሠው ይኸው አግድር የንጉሥ አልዓዳድ ልጅ ነው፡፡ እደአባቶቹ በሃይማኖት የጸና ሲሆን እስከአንገቱ ጉድጓድ አስቆፍሮ ከፊት ከኋላ ከቀኝ ከግራ እሾህ ተክሎ በዚያ እየተመላለሰ እየጸለየ ፈጣሪውን ደስ እያሰኘ በፍርድ ጊዜም ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በቀኝ በግራ ሆነው ትክክለኛውን ፍርድ እዲሰጥ እያደረጉና እየታዘዙት ኖረ፡፡ ከነገሠ ከ37 ዓመት በኋላ ጠላቶች ቢነሡበትም ወደ ብረት ሠራኞች ሄዶ መስቀል በማሠራት ለሠራዊቱ ሁሉ በመስጠት ከጠላቶቹ ወገን 2.8 ሚሊዮን ሲሞቱ በእርሱ በኩል ምንም ሳይሞት ድል አደረገ፡፡ መቶ ዓመት ሲሞላውም መልአኩ መጥቶ ልጁ ቆስዮስጦስን እንዲያነግሥ ነግሮት እርሱም ያለሕማም ጣፋጭ በሆነች እንቅልፍ አረፈ፡፡ 4. ንጉሥ ቆስዮስጦስ፡- እርሱም እደአባቶቹ ሆነ ወደ ግራም ወደ ቀኝም አላለም፡፡ ከብዙ ጊዜ በኋላ ከአረባውያን 11 ነገሥታት ጋር ጦርነት ገጥሞ ማርኮ አጥምቆ አላውያንን ድል እያደረገ አባቱ ባስቆፈረው ጉድጓድ አየጸለየ ከቆየ በኋላ መልአክ መጥቶ ሚስት አግባ አንድ ወንድና አንዲት ሴት ልጆች ትወልዳለህ፡፡ ወንድየው በሰማዕትነት ሲሞት ሴቷ ግን ብዙዎችን አረማውያንን ወደ ሃይማኖት ትመልሳለች ከእርሷ የሚወለደውም ይነግሣል አለው፡፡ ይህ ንጉሥ አንድ ወንድና ንግሥት ዕሌኒን ወልዶ እንደአባቶቹ ባለ ዕረፍት አረፈ፡፡ በሮም ሀገር መክስሚያኖስ ነግሦ ቤተክረስቲያንን አቃጠለ ሁለቱን የንጉሥ ቆስዮስጦስን ልጆችም አሳደደ፡፡ ዲዮቅልጥያኖስም ነግሦ በክርስቲያኖች ጽኑ መከራ አደረሰ፡፡ 5. ንግሥት ዕሌኒ፡- ንግሥት ዕሌኔ በተሰደደችበት ሮም ሀገር ወንድሟ በሰማዕትነት ሲያርፍ እርሷ አይሁዳዊውን ነጋዴ ተርቢኖስን አስተምራ አገባች፡፡ ተርቢኖስም ለንግድ ብዙ ወራት ትቷት ከተመለሰ በኋላ ሲመለሱ ከነጋድያን ጋር ሚስቶቻችን ሌላ ሳይለምዱ ቢኖሩ በሚል በሚስቱ የተማመነው ተርቢኖስ ቢወራረድም የክፉ አባት ዲያብሎስ እውነቱን በሐሰት ቀይሮ አንዱ ነጋዴ ከባሏ ጋር የምትተዋወቅበትን የዕንቁ ቀለበት ወስዶ ቢያሳየው እንዲህማ ከካድሽኝ ብሎ በሳጥን አድርጎ ባሕር ላይ ጣላት፡፡ የበራንጥያ ንጉሥ ቁንሥጣ ዓሣ ሲያስጠምድ ሳጥኑን አግኝቶ ወስዶ ቢከፍተው ንግሥት ዕሌኒን የመሰለች የምታምር ሴት አገኘ፡፡ እሷንም አግብቶ ቆስጠንጢኖስን ወለዱ፡፡ ንግሥት ዕሌኒ ልጇን አንግሣ ከ3፡00-6፡00 በፍርድ ወንበር እዲቀመጥ፣ ከ6፡00-9፡00 በጸሎት እዲተጋና ከ9፡00-11፡00 ለድሆች ታላቅ ምሳ እያዘጋጀ እዲምግብ አስተምራ መስቀሉን ፍለጋ ወደኢየሩሳሌም ሄደች፡፡ ታሪክ ነጋሪ ብታጣ የመስቀሉ መገኘት ፈቃዱ የነበረው አምላክ ኪራኮስንና አሚኖስን የተራኪ ነጋሪ አስነስቶ አንችም አትድከሚ ሰውም አታድክሚ አንጨት አስመጭ ደማራ ደምሪ ዕጣን አድርጊበትና አቃጥይው ጢሱም ያመለክትሻል ባሏት መሰረት መስከረም 17 ቀን ደመራውን ብታስደምረው “ወአርገ ጢሰ ዕጣኑ እስከ ሳብዕ ሰማይ ወሰገደ ቅድመ መንበረ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ወእምህየ ተመይጠ ውስተ ምድር ከዊኖ ከመቀስተ ደመና ወተተክለ ውስተ መካነ ጎልጎታ ኀበ ቀበርዎ ወደፈንዎ አይሁድ ለዕፀ መስቀል ዘክረስቶስ እግዚእ፤ ጢሱም እስከሰማይ ወጥቶ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ መንበር ፊት ሰገደ ከዚያም እደቀስተ ደመና ሆኖ በመመለስ የጌታ የክርስቶስን ዕፀ መስቀል አይሁድ ቀብረው በደፈኑበት በጎልጎታ ቦታ ላይ ተተከለ - ገጽ 176” እንዲል፡፡ ከዚህ ዕለት ጀምሮ ቁፋሮ በማስቆፈር መጋቢት 10 ቀን መስቀሉ ወጥቷል፡፡https://telegram.me/Antenetehen
Mostrar todo...
የዓለም እውነታ

ይህ ቻናል እራሳችንን እንድንመለከትና የተሰጠንን ትልቅ ሀብት እኛነታችንን ፈልገን እንድናኝ የተከፈተ ቻናል ነው፡፡ " አመለካከት ረቂቅ የአዕምሮ ተግባር ነው አካላችን ዓይን እንዳለው ሁሉ አዕምሯችንም ዓይን አለው የሀሳቡን ዓለም የሚያይበት ። "

..... የቀጠለ 👆👆👆 ✥ የንግሥት እሌኒ ድካምና ፍሬ #ክፍል 2 ንግሥት እሌኒ ልጇን ቆስጠንጢኖስን ከልጅነቱ ጀምሮ ስለ ክርስትና ሃይማኖትና ስለ ክርስቲያኖች መከራ ታስተምረው ስለነበር በክርስቲያኖች ላይ የነበረው አመለካከት በሮም ከነገሡት ቄሣሮች ሁሉ የተሻለ ነበር፡፡ ቆስጠንጢኖስ የሮም ንጉሠ ነገሥት ከሆነ በኋላ በ300 ዓመታት ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ ለክርስቲያኖች የነጻነት ዐዋጅ ዐወጀ፡፡ ክርስትናም ብሔራዊ ሃይማኖት ሆነች፡፡ ንግሥት እሌኒም የተፈጠረውን አመች ሁኔታ በመጠቀም የጌታችንን መስቀል ከተቀበረበት ለማውጣት በ327 ዓ/ም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች፡፡ ንግሥት እሌኒ ልጇ ቆስጠንጢኖስ ክርስቲያን ከሆነላት ወደ ኢየሩሳሌም ሔዳ መስቀሉን ለመፈለግ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ያሉ ቅዱሳት መካናትንና አብያተ ክርስቲያናትን ለማሳነፅ ለእግዚአብሔር ተሳለች፡፡ ከዚህ በኋላ ቆስጠንጢኖስ አምኖ በ337 ዓ/ም ተጠመቀ፡፡ ቅድስት እሌኒም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች እንደደረሰችም ስለ ክብረ መስቀል መረመረች ጠየቀች፡፡ ቦታውን የሚያስረዳት ግን አላገኘችም፡፡ አይሁድ የተቀበረበትን ቦታ ለማሳየት ባይፈልጉም በኋላ ባደረገችው ጥረት አረጋዊው ኪራኮስ የጎልጎታን ኮረብታ አመላከታት ዳሩ ግን ኪራኮስ ዘመኑ ከመርዘሙ ጋር ተያይዞ በአካባቢው ከነበሩት ከሦስቱ ተራሮች ውስጥ መስቀሉ የሚገኝበት የትኛው እንደሆነ ለይቶ ማወቅ አልቻለም፡፡ ንግሥት እሌኒ ከሦስቱ ተራሮች የቱ እንደሆነ ለመለየት በእግዚአብሔር መልአክ እርዳታ ደመራ አስደምራ ብዙ እጣንም በመጨመርና በማቃጠል ጸሎት ተያዘ፡፡ የእጣኑ ጢስ ወደ ሰማይ በመውጣት በቀጥታ ተመልሶ መስቀሉ ባለበት ተራራ ላይ በማረፍና በመስገድ መስቀሉ ያለበትን ትክክለኛ ስፍራ አመለከታት፡፡ ቅዱስ ያሬድም ጢሱ ሰገደ ብሎታል፡፡ ከዚያም መስከረም 16 ቀን ቁፋሮው እንዲጀመር አዘዘች፡፡ ሰባት ወር ያህል ከተቆፈረ በኋላ መጋቢት 10 ቀን ሦስት መስቀሎች በአንድነት ተገኙ፡፡የክብር ባለቤት ጌታችን የተሰቀለበት የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ተቸገሩ፡: መስቀሎቹን ወስደው በሞተ ሰው በተራ ቢያስቀምጡ ጌታችን የተሰቀለበትና በዕለተ ዐርብ ተሰቅሎ የዋለበትና በደሙ መፍሰስ የተቀደሰው መሰቀል የሞተውን ሰው በማስነሣት በሠራው ተአምር ሌሎቹ ሁለቱ ታምራት ባለማድረጋቸው የጌታን መስቀል ለይቶ ማወቅ ተችሏል። እሌኒና ክርስቲያኖች ሁሉ ለመስቀሉ ሰገዱለት፡፡ በየሀገሩ ያሉ ክርስትያኖች ሁሉ የመስቀሉን መገኘት በሰሙ ጊዜ መብራት አብርተው ደስታቸውን በመግለጥ ለዓለም እንዲታወቅ አደረጉ፡፡ ንግሥት እሌኒ ለመስቀሉ ቤተ መቅደስ ከሠራችለት ጊዜ ጀምሮ በመስከረም 17 ቀን አሁን በኢትዮጵያ እንደሚከበረው በክርስቲያኖች ዘንድ መስቀል ይከበር ነበር። #ሼር __ https://t.me/Antenetehen
Mostrar todo...
የዓለም እውነታ

ይህ ቻናል እራሳችንን እንድንመለከትና የተሰጠንን ትልቅ ሀብት እኛነታችንን ፈልገን እንድናኝ የተከፈተ ቻናል ነው፡፡ " አመለካከት ረቂቅ የአዕምሮ ተግባር ነው አካላችን ዓይን እንዳለው ሁሉ አዕምሯችንም ዓይን አለው የሀሳቡን ዓለም የሚያይበት ። "

✥ ክብረ መስቀል በኢትዮጵያ ‹መስቀል› ስንል ሦስት መሠረታዊ ቁም ነገሮችን መጥቀስ ይቻላል፤ የመጀመሪያው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ከሞተ ነፍስ ለማዳን ሲል የተቀበለው መከራና የከፈለው መሥዋዕትነት መስቀል ይባላል፡፡ ሁለተኛው በክርስትና ውስጥ የሚያጋጥም ልዩ ልዩ ዓይነት መከራም መስቀል ነው፡፡ ጌታችን ‹‹እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ›› /ማቴ.፲፮፥፳፬/ በማለት መናገሩም በክርስትና ሕይወት ውስጥ የሚደርሰውን ይህንኑ መከራ መታገሥ ተገቢ መኾኑን ሲያመለክተን ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ጌታችን የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል ሲኾን በሦስቱም ቁም ነገሮች ነገረ መስቀል (የመስቀሉ ነገር) ከክርስትና ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው፡፡ ስለ ክርስትና ሕይወት ሲነሣ ነገረ መስቀልም አብሮ ይታወሳል ስለ ክርስትና ሲነገር ክርስቶስ የተቀበለው መከራ፣ የተሰቃየበትና ነፍሱን በፈቃዱ አሳልፎ የሰጠበት ዕፀ መስቀል፣ በክርስትና ሕይወት ውስጥ የሚከሠት ፈተና አብረው የሚነሡ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ስለ መስቀል ሲነገር ክርስቶስ ሰውን ለማዳን ሲል በሥጋው የተቀበለው ስቃይ፤ ሰማዕታት በሃይማኖታቸው ምክንያት የሚደርስባቸው ስደት፣ መከራና ሞት፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በየዘመኑ በአረማውያንም በውስጥ ጠላቶችም የሚያጋጥማት የዘረፋና የቃጠሎ፣ እንደዚሁም የሰላም እጦትና የመልካም አስተዳደር እጥረት፤ በተጨማሪም በክርስትና ሕይወት ውስጥ የሚከሠቱ የኑሮ ውጣ ውረዶች መስቀልና ክርስትና የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ለመኾናቸው ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ከዚሁ ኹሉ ጋርም መስቀል ሲባል ክርስቶስ መከራ የተቀበለበት፣ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው የለየበት፣ ድንቅ ተአምራትን ያደረገበት፣ ከኹሉም በላይ ለአዳምና ለልጆቹ ነጻነትን ያወጀበት ዕፀ መስቀልም አንዱ የክርስትናችን አካል ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በጉልላቷና በሌሎችም ንዋያተ ቅድሳቷ መስቀልን እንደ ምልክት ትጠቀመዋለች፡፡መሠረቷ፣ የልጆቿ መድኀኒት ክርስቶስ በመስቀል ላይ የከፈለው ዋጋ ነውና ሰንደቅ ዓላማዋ መስቀል ነው፡፡ አባቶች ካህናት ጸሎት ሲያደርጉ ‹‹ከመስቀሉ ዓላማ፣ ከወንጌሉ ከተማ አያውጣን›› እያሉ የሚመርቁትም ስለዚህ ነው በእጃቸው ይዘውት የሚንቀሳቀሱት፣ እኛንም የሚባርኩትም በመስቀል ነው ። መስቀል የጠላት ሰይጣን ተንኮል የከሸፈበት፣ የክርስቶስ ቤዛነት የተረጋገጠበት የድኅነት ኃይል ነውና፡፡ በየገዳማቱና በየአብነት ት/ቤቱ፤ እንደዚሁም በክርስቲያኖች መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በሚከናወኑ ተግባራት መስቀል ሰፊ ድርሻ አለው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ፣ በጠበል ቦታ፣ በጸሎት ጊዜያት፣ ወዘተ ቡራኬ የሚፈጸመው በመስቀል በማማተብ ነው፡፡ የመስቀሉን ምልክት ባዩ ጊዜ አጋንንት ይንቀጠቀጣሉ፤ ካደሩበት ሰው ላይም በፍጥነት ይወጣሉ፡፡ ምእመናን በመስቀሉ ስንዳሰስ ከልዩ ልዩ ደዌ እንፈወሳለን፡፡ ወደ አገራችን ክርስቲያናዊ ባህል ስንመለስ በኢትዮጵያ የመድኀኒታችን የክርስቶስ መስቀል በብዙ ተግባራት ላይ በምልክትነት ጥቅም ላይ ሲውል ይታያል፡፡ ለምሳሌ በቡልኮ፣ ዐጋቢ፣ ነጠላ፣ ቀሚስ ወዘተ የመሳሰሉ የሸማ ልብሶች፤ እንደዚሁም በጆሮ፣ በአንገት፣ በእጅና ሌሎችም ጌጣጌጦች ላይ የመስቀል ምልክት አለ፡፡ ክርስቲያን ልጃገረዶች (በተለይ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል) በግንባራቸው፣ በጉንጫቸው፣ በአንገታቸው፣ በደረታቸውና በእጃቸው ላይ በመስቀል ቅርፅ እየተነቀሱ ያጌጡበታል። ክርስቲያኖች ከዚህ ዓለም በሞት ስንለይም በመቃብር ሣጥናችን ወይም በሐውልቶቻችን ላይ የመስቀል ምልክት ይቀመጣል፡፡ በቤት ውስጥም ስንተኛና ከእንቅልፋችን ስንነቃ ፊታችንንና መላ ሰውነታችንን በትእምርተ መስቀል እናማትባለን፤ አባቶችና እናቶችም ውሃ ሲቀዱ፣ ሊጥ ሲያቦኩ፣ እንጀራ ሲጋግሩ፣ ምግብ ሲቈርሱ፣ ወዘተ በመስቀል አማትበው ነው፡፡ በአጠቃላይ መስቀል ብዙ ነገር ነው፤ መስቀል በክርስትና ሕይወት ውስጥ በሚደረጉ ተግባራት ኹሉ ያለው ድርሻ ጕልህ ነው፡፡ ከዓለም ክርስቲያኖች በበለጠ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል የተለየ እምነትና አክብሮት አላቸው፡፡ ይቀጥላል ..... #ሼር __ #share #share ⤵️ https://t.me/Antenetehen                      
Mostrar todo...
የዓለም እውነታ

ይህ ቻናል እራሳችንን እንድንመለከትና የተሰጠንን ትልቅ ሀብት እኛነታችንን ፈልገን እንድናኝ የተከፈተ ቻናል ነው፡፡ " አመለካከት ረቂቅ የአዕምሮ ተግባር ነው አካላችን ዓይን እንዳለው ሁሉ አዕምሯችንም ዓይን አለው የሀሳቡን ዓለም የሚያይበት ። "

#እውነትን_በውሸት ፧ ፧ ገነት ያለጊዜው ሐሴት ያለቦታው ጽድቅም ያለወቅቱ ክብርም ያለ'ምነቱ አንድነት ደርሰውት በጭንቅ የኖረ ሰው ከኖረው አስታውሶ ለማንም እንዲደርስ የላከው ጦማር ነው ከጭንቁ ለውሶ፡፡ (ጦማር አንድ) መኖሩን ሳናውቀው ድንገት ከተፍ የሚል እውነት የተቀባ አንዳንድ ውሸት አለ በቦታና ጊዜ በሁኔታ ታዝሎ ማንም የማይሽረው ቅዱስ ቃል ያከለ፡፡ ለምሳሌ....(1) ባጡና በነጡ ሆዳቸው ተጣብቆ ከምግብ በራቁ ችጋራሞች መሐል ምግብ የሚደፋ በምቾት ያበጠ ታላቅ ባለፀጋ ቆሞ ይናገራል፡፡ ቃሉም ይወደሳል፡፡ 'ውነቱም ይነግሳል፡፡ ማን በሆዱ ፈርዶ ልገሳውን ገፍቶ ልፍለፋውን ሁሉ ውሸት ነው ይለዋል!? በመሞቶ ቆርጦ የትኛው ችጋራም ይገዳደረዋል!? ለምሳሌ...(2) ከማንነቱ አውድ ከራሱ ተሟግቶ አማናዊ ራሱን ከማወቅ የሸሸ በሚሰሙት መሐል በመሸታ ገድል ቃል እያቀረሸ ሰካራም ያወራል ሀገር ምድሩ ሁሉ እንደተበላሸ፡፡ ሰሚም ያዳንቃል የስካር ቃላቱን ከራዕይ አስተካክሎ አብሮ እየፎረሸ፡፡ ታማሚ ነውና በ'ውነቱ አምኖ ተጠምቆ ይቀበላል ሁሉ እንደቆሸሸ፡፡ ራ'ብና ብሶት ባነቃቸው መሐል አቅላቸው በጠፋ በሕማም ታግቶ ውነትህ ሲጋነን ታምነህ ስትከበር ባቃታቸው ሚዛን ታይቶና ተሰምቶ አዋቂ ስትባል ስምህ ሲመጻደቅ አንደበትህ ተብቶ ሰይፍ ቃልህ ሰልቶ ያን ጊዜ ተገንዘብ እንደዚህ ይሆናል ያን ጊዜ ልንገርህ ይኼ እውነት ይደርሳል፡፡ እውነት ቅብ ውሸትህ ታምኖ ተወድሶ ተቀድሶ ይፀናል ደብር አስገንብቶ፡፡ ያን ጊዜ ልንገርህ በጊዜና ቦታ በሁኔታ አስታከህ የዘራኸው ቅጥፈት ትውልድ ይሻገራል በጥፋቱ ሰብቶ፡፡ ያን ጊዜ ልንገርህ ባለጠጋም ብቶ'ን ሰካራምም ብቶ'ን ሰው መሆንህ ቀ'ሎ ማን መሆንህ ሻግቶ መንፈስህ ኮስሶ ክብር ያቃልልሀል በዘላለም ኑረት ስጋ ነፍስህ በክቶ፡፡ ገነት ያለጊዜው ሐሴት ያለቦታው ጽድቅም ያለወቅቱ ክብርም ያለ'ምነቱ አንድነት ደርሰውት በጭንቅ የኖረ ሰው ከኖረው አስታውሶ ለማንም እንዲደርስ የላከው ጦማር ነው ከጭንቁ ለውሶ፡፡ (ጦማር ሁለት) አወየው ወዳጄ አወይ የማላውቅህ ቢደርስህ ባይደርስህ ጦማር የላኩልህ አጉል ስዘባርቅ ላይሆን ስተረተር ዋናውን ዘንግቼ ስለኔ ሳልነግርህ፡፡ እኔማ ይኸውልህ... 'ተመስገን' እንዳልል ያለጊዜው ሞልቶኝ ጨንቆኛል ሐሴቴ 'የለህም' እንዳልል ያለወቅቱ ጠፍቶኝ አብሮ አደጌ ምለው መከራ ከቤቴ 'ባለህ የለህ' መሐል አለሁ ተቸንክሬ በ'ምነቴና ፅድቄ ያለፍላጎቴ ሆኜ በገነቴ፡፡ አየኸኝ ወዳጄ... ባለኝ ጭንቀት ወርሶኝ ባጣሁት ተክዤ ጭንቅ ያመሳቀለው ተሳክሯል ሕይወቴ፡፡ ስማኝ የማላውቅህ... የሰማይን ያህል ቢመተር የማያልቅ ርቆ የተሰቀለ ውቅያኖስን ያህል መንጣለሉ ገዝፎ ጠልቆ የተሳለ የኮከብን ያህል ከቁጥር የተረፈ ሰላምታ ብሰጥህ የተሽቀረቀረ የተቀማጠለ ሰላም አይሆንህም ግዴለም ይቅርብህ በጭንቅ ቤቴ ነው ልቤ ታቅፎ ያለ፡፡ ሰላሜን ሳላውቀው ሰላም ልልክልህ ስለማይቻለኝ ጭንቄ ከኔው ይርጋ በኔው እንዳየለ፡፡ ይልቅ ስለእውነት የገባኝን ያህል ይኼንን ልንገርህ ይህ ነው ከኔ ያለ፡፡ (ጦማር ሶስት) በጦማር ሐተታ ስለ'ውነት ለማውራት ቢከብድም ማጣቀስ በውሸት ምሳሌ በባለፀጋ ቃል በሰካራም ብሶት እውነትን ለማግኘት ቢያደክምም ባያሌ ሐሴት ያለጊዜው መከራ በወቅቱ በማታውቀው ምክንያት ተሰ'ተውህና ተሰውረውብህ በጊዜህ ጎ'ሎብህ የቆምክበት ከድቶህ በጭንቅ ተወጥረህ የሌለህን ናፍቀህ ስለ'ውነት ለማውራት እውነትን ለማግኘት ካንተ መጠበቁ ይከብዳል ብትልም የማወራህ ውሸት የምሳሌ ቅጥፈት ለቀልብያህ ገጥሞ እውነት ባይመስልህም የምለው አላጣም ይወጣኝ አይጠፋም አድምጠኝ ግዴ'ለም፡፡ ባለጠጋ ሁሉ የግፍ እናት አባት ወላጅ ነው አልልም የጉራ አሳዳጊ ሞቱ ከሕይወቱ እጅግ የቀረበው ጠኔ የጣለውም አይደለም ተበዳይ አይሆንም ፀዳቂ በብሶት የጠጣ ከራሱ የሸሸ የጥንበዛ ፈረስ ሆኖ የምታየው ጥላቻን አርቃቂ በተንኮል ተጥሎ በሾኬ ተጠልፎ ተስፋ ቆርጦ አይደለም የሆነው አጥማቂ፡፡ እነዚህ ሁሎቹ እኔንም ጨምሮ ከራስ ተጣፍተን ነው የምንሰብክ ሌላ ከቅጥፈት ተጋብተን ከውሸት አጣቅሰን እንደርሳለን ባይ ነን ከ'ውነታችን ኬላ፡፡ ለራስ ሽባ ሆነን ለሌላው የምንቆም ስንኩሎች ሆነን ነው የጠፋብን መላ፡፡ ፧ ፧ ፧ #ዮሐንስ__ሀብተማሪያም https://telegram.me/Antenetehen
Mostrar todo...
የዓለም እውነታ

ይህ ቻናል እራሳችንን እንድንመለከትና የተሰጠንን ትልቅ ሀብት እኛነታችንን ፈልገን እንድናኝ የተከፈተ ቻናል ነው፡፡ " አመለካከት ረቂቅ የአዕምሮ ተግባር ነው አካላችን ዓይን እንዳለው ሁሉ አዕምሯችንም ዓይን አለው የሀሳቡን ዓለም የሚያይበት ። "