cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ኢትዮጵዝዮን

Ethiozionethiopzion

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
208
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ከእንደዚህ ዓይነት ሰዎች ተጠንቀቁ ...! 👉ሃሳብ ሳኖራቸው የእናንተን አሳብ የሚያጣጥሉ 👉አንድም ነገር ሳያሳኩ የስኬትን መንገድ ለሚመክሩ 👉ስኬት የሚባልን ሳያውቁ የውሸት የስኬት ታሪክ እየፈጠሩ ከሚመክሩ 👉ሁልጊዜም ለተፈጠረው ስህተት ስበብ የሚያቀርቡ 👉የሚያወሩትና የሚያደርጉት የተለያዩ 👉የሚታያቸው የጎደለው እንጂ የሞላው ያልሆኑትን 👉የራሳቸውን አሳብ ብቻ ትክክል አድርገው የሚያቀርቡ... የሌላውን የሚገፉ 👉ሰዎችን ከላይ ባለው ገፅታቸው ብቻ የሚለኩ... 👉ብርን ከምንም በላይ የሚያስቀድሙ...! ራስን መለወጥ @ethiopzion @ethiopzion
Mostrar todo...
⚠️⚠️⚠️ አሽቸኳይ ⚠️⚠️⚠️ 🙏ለብዙዎች እንዲደርስ ያጋሩ🙏 ህጻን ሶሊያና እስከአሁን አልተገኘችም! እንደታገተች ናት! እናትና አባት በጭንቅ ውስጥ ሆነው  ያመሹት ነፋስ ስልክ ፖሊስ መምሪያ ነው። ይህችን ምንም የማታውቅ የ2 ዓመይ ህጻን ልጅ የሆነችውን ህጻን ሶሊያናን  ይዛ የተሰወረችው የቤት ሰራተኛ መልኳ ቀይ፣ መካከለኛ ቁመት ያላት እና ቀጠን ያለች ስትሆን አብዛኛውን ጊዜ ታይትና ሻሽ የምትለብስ ናት። ትንሿ ሶሊያናም ቢጫ ኮፍያ ያለው ሹራብ ከክፍት ጫማ ጋር አድርጋ ነበር። እባካችሁን በፈጣሪ ስም አፋልጉን ጸልዩልንም🙏 0951090999 - ዳንኤል 0947365252- የውብዳር
Mostrar todo...
ለራስህ ቃል ግባ! ነገሮች በፈለከው መንገድ ላይሄዱ ይችላሉ፣ ሰዎች ጀርባቸውን ሊያዞሩብህ ይችላሉ፣ በዚህ አለም ለመኖር የሚያጓጉህን ነገሮች ሁሉ ልታጣ ትችላለህ፤ ግን ሁላችንም በዚህ ስሜት ውስጥ አልፈን እናውቃለን ወደፊትም እናልፍ ይሆናል። ታላቅነት ግን በዚህ ከባድ ጊዜ መቼም ተሰፋ ቆርጠህ ጥረትህን እንደማታቆም ለራስህ ቃል መግባት ነው! ተስፋ የሞላበት ምሽት ተመኘሁላችሁ🙏 @ethiopzion @ethiopzion
Mostrar todo...
"በምትሞትበት ጊዜ በመጀመሪያ ስምህ ይቀየራል ስምህም ሬሳ ትባላለች" እከሌ/እከሊት ሳይሆን ሬሳዉ አልወጣም ወይ ትባላለህ። የቅርብ ሰዉ እንኳን ቢሆን ከጎንህ ሊሆን ይፈራል" ወደ መቃብር ስፍራ ወስደዉ አጣድፈዉ ከቀበሩህ በሗላ ብቻህን ጥለዉህ ለመሔድ ይቻኮላሉ። ላይጠቅምህ አብሬህ ካልሔድኩ እያለ የሚያለቅሱልህ እንኳን ቢኖር ቀብሮህ ተሎ ይሸሻል።ቀብረዉህ እደተመለሱ ንብረት ካለህ ለመከፋፈል ይጣደፋሉ ። ከሳምንት በሗላ ጭራሹኑ ከምድር ያልኖርክ እስኪመስል ድረስ በአብዛኞቹ ትረሳለህ ። የቅርብ ወዳጆችህ እንኳን ቢሆኑ ሀዘኑ በልባቸዉ ጥቂት ወራት ያክል ቢቆይ ነዉ ።በቃ ምድር ላይ የነበረህ ቆይታ በዚህ መልኩ ይጠናቀቃል ።ፍራሽህ አፈር ትራስህ ደሞ ድንጋይ ይሆናል😌 ይሔዉ ነዉ ። ያኔ ማንም ምንም አይጠቅምህም መልካም ስራህ ብቻ🙌 በዚች አለም ላይ እድለኛ ሠዉ ማለት በህይወት እያለ ወደ ፈጣሪዉ የተመለሠ ሰዉ ነዉ 🙌"👏 @ethiopzion @ethiopzion
Mostrar todo...
ደስታ ማግኘት ቀላል ነው! 1, እውነትህን ኑር :- እውነትህን ተጋፈጥ አታስመስል ከራስህ አትደበቅ ምንም ቢሆን ልብህ  እውነቱን ያውቃል ከላይ ከላይ ላስመስል ልሸውደው ብትልም አይቀበልህም ስለዚህ ደስታህን ይነፍግሀል መደሰት ከፈለክህ የእውነትህን ኑር እውነቱ ከባድ ቢሆንም ተጋፍጠህ ስታሸንፈው የምታገኘውን ደስታ እና እርካታ ማንም አይሰጥህም! 2 , በፍቅር ኑር :- ከሰዎች ጋር ከልብ በሆነ እውነተኛ ፍቅር ኑር ምንም ሳትጠብቅ ፍቅር  ስጥ ለሰዎች ሰላም መስጠት የምትችል ሁን ብርቱ ሁን ከልብህ ተቀበላቸው ለመጠንከራቸው ለመሳቃቸው ለማሸነፋቸው ለሰላማቸው ምክንያት ሁን ፍቅር በመስጠትህ ብቻ ህይወቱን የምታተርፍለት አንድ ሰው መኖሩን እወቅ ፤ ሞቅ ያለ ፈገግታህን በማየት ከህይወቱ ጨለማ የሚወጣ የሆነ ሰው አለ ስለዚህ በሄድክበት ሁሉ ፍቅርን የምትሰጥ እና ፈገግታህ ተስፋን የሚፈነጥቅ መሆኑን እወቅ ያኔ  ደስታ ሳትጠራው ራሱ ፈልጎህ ይከተልሀል ካንተ ርቆ መሄድ አይችልም!      "እነዚህን ካደረግህ ደስታ ራሱ ካንተ ጋር መሆን ያስደስተዋል " @ethiopzion @ethiopzion
Mostrar todo...
ደስተኛ መሆን! ደስተኛ የመሆን ትልቁ ሚስጥር ገና የሚመጣውን ማሰብ ብቻ አይደለም፤ ወደ ህይወታችን የመጣውንም ማሰብ ነው። ወደ ህይወታችን ከመጣው ምርጥ ስጦታ አንዱ የዛሬው ቀን ነው። የዛሬዋን ቀን ከዚህ በፊት ቀድሞ ያየው አለ? የለም! አዲስ ስጦታ ነው። ለሀብታሙም ለደሀውም፣ ለትልቁም ለትንሹም፣ ለሴቱም ለወንዱም ከፈጣሪ የተሰጠ ልዩ ስጦታ! እየተነፈስክ ተደሰትና ፈጣሪህን አመስግን ወዳጄ። @ethiopzion @ethiopzion
Mostrar todo...
ደስታችን በእጃችን ነው ! በህይወትህ በጣም ደስተኛ መሆን ከፈለግህ ደስተኛ የምትሆንበትን መንገድ ከሌሎች አትጠይቅ ወይም ሌሎች ሰዎች ይሄንን ስታደርግ ነው ደስተኛ የምትሆነው በሚሉህ ልክ ደስታህን አትለካው ! ደስታ መጠጣት፣ መጨፈር የመሳሰሉትን ማድረግ ማለት አይደለም ! መፅሀፍት ማንበብ ፣ ለብቻ ግዜ ማሳለፍ የራሳችን ነገር መፍጠር የምንወደውን ስራ መስራት ደስተኛ ሊያደርገን ይችላል ደስታችን ያለው በእጃችን ነው ! ራሳችን ደስታችንን መፍጠር እንደምንችል እንወቅ ! @ethiopzion @ethiopzion
Mostrar todo...
ውስጥህ ሲደሰት.... ደስታህን በኑሮህ ከሚገጥሙህ ሁኔታዎች ጋር አታገናኘው፤ ደስታ ማለት የችግር አለመኖር አይደለም፤ በችግር ውስጥ እያለፍክ መሳቅ ነው። ነገሮች ምርጥ ሲሆኑማ ሁሉም ይደሰታል እኮ፤ አንተ ግን በአምላክህ እና አጠገብህ ባሉ መልካም ነገሮች ሁሌም ደስተኛ ሁን። ውስጥህ ሲደሰት ውጪህ ላይ ይገለጣል፤ ከዛ አንተ ደስተኛ ስለሆንክ አለም አብራህ ትስቃለች፤ ከባድ የመሰለህ ነገር ተራ ሲሆን ታየዋለህ፤ ሰዎች የደስታህን ምንጭ ለማወቅ ሲሉ አክብረው ያደምጡሀል፤ ወዳጄ መቼም የማይተው አምላክ እንዳለህ ማሰቡ ራሱ የደስታ ጥግ ነው። @ethiopzion @ethiopzion
Mostrar todo...
የሚያቆመን ሀሳባችን ነው! የምንጎዳው የምንሰበረው የምንፈራው የምናጣው መጥፎ የሚባሉት ስሜቶች በአጠቃላይ የሚፈጠሩት በሀሳባችን ነው ፤ ገና በተግባር ያላየናቸው በእውኑ አለም ያላወቅናቸው ነገሮች በሙሉ ቀድመው በሀሳችን ይፈጠሩ እና ከመንገዳችን ያስቆሙናል መሰናክል ይሆኑብናል መሄድ ከምንፈልግበት መጓዝ ካሰብነው ቦታ ያርቁናል ስለዚህ እናስተውል እየተረበሽኩ ያለውት በምንድን ነው እውነት በተፈጠሩ ነገሮች ነው? ለምንድነው የቆምኩት ? ገብቼ አይቼው ነው ወይንስ በሀሳብ የሳልኩት መጥፎ ስዕል እየረበሸኝ ነው? ብለን እንነሳ ከመቆማችን በፊት ለምንድነው የቆምኩት ብለን እንመርምር ! @ethiopzion @ethiopzion
Mostrar todo...
ህግ ይኑረን ! ራሱን መቆጣጠር የማይችል ሰው መቼም ቢሆን ነፃ ሊሆን አይችልም ! በህግ የማይመራ ሰው ገደብ የለውም ህግ ማውጣት ወይም ራስን መቆጣጠር ነፃነት የሚነፍግ አሰልቺ የሆነ ነገር ነዉ ተብሎ ይታሰባል ነገር ግን በተቃራኒው ነው ህግ ሲኖረን የምናደርጋቸውን ነገሮች ቅደም ተከተል ስናውቅ ምን ያህል ግዜ እንዳለን እና ነገሮቻችንን መቼ አከናውነን መጨረስ እንደምንችል ጠንቅቀን እናውቃለን ስለዚህ ነፃ ሆንን ማለት አይደለም? ዛሬ አየሩ ከበድ ያለ ነው ፤ ያለውበት ቦታ ምቹ አይደለም እና የመሳሰሉት ሰበቦች ያሰብነውን ከማድረግ ወደ ኋላ እያስቀሩን ከሆነ እኛ ራሳችንን መቆጣጠር አቅቶን ሌሎች ውጫዊ ነገሮች እየመሩን እና እየተቆጣጠሩን ነዉ እና ነፃነታችንን አሳልፈን ለማንም አንስጠው ! @ethiopzion @ethiopzion
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.