cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Online Medical Care and Medical Information🩺🔬 የጤና እና ጤና ነክ መረጃዎች

የጤና መረጃዎች ጤና ነክ መረጃዎች

Mostrar mĂĄs
Publicaciones publicitarias
275
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 dĂ­as
Sin datos30 dĂ­as

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Repost from N/a
የፕሮስቴት ካንሰር ✍🏻 ከቢቢሲ የዜና ተቋም (BBC NEWS) ጋር ካደረግነዉ ቆይታ የተወሰደ ነዉ። 📌 ፕሮስቴት ከሽንት ፊኛ በታች በወንዶች ላይ ብቻ የሚገኝ እጢ ነዉ!! 📌 ስራዉም የዘር ፈሳሽ ማመንጨት፣ በግንኙነት ጊዜ የዘር ፈሳሽ ወደ ዉጪ እንዲወጣ መርዳት ነዉ!! 📌 እድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ፣ ጥቁር ወንዶች እንዲሁም በቤተሰባቸው ውስጥ የፕሮስቴት ካንሰር የተያዘ ሰው ያላቸው ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ። 📌 የፕሮስቴት ካንሰር ምልክቶች ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት፣ ደም የቀላቀለ ሽንት፣ ሽንት ሲወጣ መቅጠን፣ የሽንት መቆራረጥ፤ ማስማጥ፣ ከሸኑ በኋላ የመጨረስ ስሜት አለመኖር፣ ወደ ጀርባ ከተሰራጨ በኋላ ደግሞ የታችኛው ጀርባ ክፍል ህመም ናቸዉ። 📌 ምርመራው ተደርጎ የፕሮስቴት ካንሰር መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ የተለያዩ ዓይነት የሕክምና አማራጮች አሉ። ከእነዚህም ውስጥ በቀዶ ሕክምና ካንሰሩን ማውጣት፣ የጨረር ሕክምና ወይንም ደግሞ የወንድ ልጅ ቴስቴስትሮን ካንሰሩን በዋነኛነት ስለሚመግብ በሰውነት ውስጥ ያለውን የቴስቴስትሮን መጠንን ለመቀነስ ሕክምና ይሰጣል። 📌 የፕሮስቴት ካንሰር አብዛኛውን ጊዜ ቀስ ብሎ የሚያድግ በመሆኑ አንድ ሰው እድሜው ከ50 አስከ 55 ዓመት ሲሆን ቅድመ ምርመራ እንዲያደርግ ይመከራል። ምርመራዉን በዓመት ወይንም በሁለት ዓመት አንዴ ማድረግ ጠቃሚ ነው። ሙሉ ህትመቱን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ BBC NEWS | አማርኛ - https://www.bbc.com/amharic/articles/cndxlne6nk9o BBC NEWS | AFAAN OROMOO - https://www.bbc.com/afaanoromoo/articles/cyxnlx2d9pyo BBC NEWS | ትግርኛ - https://www.bbc.com/tigrinya/articles/cx9yllppwqgo
Mostrar todo...
#ሔሞግሎቢን_ኤ_ዋን_ሲ_HbA1C ====================== በሰውነታችን ውስጥ ያለ ስኳር ከቀይ የደም ህዋሳት ፕሮቲን ጋር ሲጣበቅ/ሲያያዝ የሚፈጠር ነው። ከስኳር ጋር የተጣበቁ የደም ህዋሳት ሰውነታችን ላይ አገልግሎት አይሰጡም ይልቁንስ በድም ስሮች/ቧንቧዎች ላይ ይጠራቀማሉ። በትንንሽ የደም ስሮችን በመዝጋትም በስኳር ምክኒያት ለሚመጡት የኩላሊት፣የዐይን እና ነርቭ ችግሮችን ያስከትላሉ። የቀይ ደም ህዋሶቻችን እስከ አራት ወር ያህል እድሜ ስላላቸው በየ 3 ወሩ #ሔሞግሎቢን_ኤ_ዋን_ሲ_HbA1C በማሰራት የስኳር መጠንን መቆጣጠር ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው በስኳር ህክምና ጠበብቶች እና ተመራማሪዎች በጥናት አስደግፈው ይመክራሉ። #ሔሞግሎቢን_ኤ_ዋን_ሲ_HbA1C ስኳር መኖር አለመኖሩን፣በሶስት ወር ውስጥ የነበረዎትን የስኳር መጠን፣ እና አማካኝ የስኳር መጠንዎን በማወቅ የስኳር በሽታ ከሚያስከትላቸው ጉዳቶች መከላከል ይቻላል። The term "HbA1c" refers to glycated hemoglobin. It is created when your body's glucose (sugar) adheres to your red blood cells. More sugar sticks to your blood cells and accumulates in your blood because your body can't use it properly. Red blood cell activity lasts for about two to three months with age limit of four months, which is why the reading is taken every three to four months. HbA1c is medical blood test usually used to average the blood sugar level in body. HBA1C is known as hemoglobin A1C diagnostic test which average the blood sugar level in blood for past 3-4 months which help in diagnosing the diabetes level of patient. This is one of the most important test in diagnose and treatment process of sugar/diabetic patients። Grand Medical Clinic -ግራንድ ሜዲካል ክሊኒክ Grandmedical Gmc
Mostrar todo...
በአዲስ መልክ የሚሰጡ የላቦራቶሪ አገልግሎቶች New laboratory Tests available ====================== ●የስኳር/Diabetes:HbA1c ●የእንቅርት ሆርሞኖች/Thyroid Function:TSH,T3,T4 ●የመካንነት ሆርሞኖች/Fertility:β-HCG,LH,FSH, Progesterone, Prolactin, Testosterone ●የልብ ምርመራ/Cardiac Markers:CTnI,cTnT,CK-MB ■የደም መርጋት/Coagulation:D-Dimer ■የኢንፍላሜሽን/Inflammation Markers:CRP (hsCRP+CRP),IL-6 ●የተለያዪ ካንሰሮች/ Tumor Markers:AFP,PSA,CEA ●ሌሎችም/Others:cortisol,Vitamin D, Ferritin ========== Grand Medical Clinic -ግራንድ ሜዲካል ክሊኒክ
Mostrar todo...
"ዛሬ ሀኪም ቤት ሄጄ ታይፎይድ እና ታይፈስ አለብህ አሉኝ" ሲባል መስማት የተለመደ ሆኗል። እነዚህ ሁለት በሽታዎች የሚአዛምዳቸው ነገር ይኖር ይሆን 🤔? ለመሆኑ ታይፈስ ምንድነው? ======================= ✍ታይፈስ ሪኬቲሺአ (Rickettsia ) ተብለው በሚጠሩ እና እራሳቸውን ቅማል፣ ቁንጫ እና ተዛማጅ ነፍሳት ውስጥ በሚደብቁ ባክቴሪአዎች የሚመጣ የትኩሳት በሽታ ነው። ✍ተባዩ ባክቴሪአውን ከተበከለ ሰው ደም በሚመጥበት ጊዜ ወደ ራሱ ሰውነት ያስገባዋል ፤ ይህ ተባይ የጤነኛን ሰው ደም በመውጋት ይበክላል ወይም ተጠቂው ሰው በማከክ እና ተባዩን በሰውነት ላይ በማሸት ወደ ሰውነት የሚገባበትን መንገድ ይፈጥራል። ✍ምልክቶቹ፦ 🔹ትኩሳት 🔹ራስ ምታት ፣ የመዛል ስሜት ፥ ቁርጥማት 🔹በሆድ እና ጀርባ አካባቢ ሽፍታ 🔹ደረቅ ሳል፣ 🔹ባስ ሲል መፍዘዝ እና እራስን መሳት ሊያስከትል ይችላል። ❗️ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ሲገጥሙ ቶሎ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል። ✍ታይፈስም እንደ ታይፎይድ በወረርሽኝ መልክ ሊከሰት የሚችል እስከሞት የሚያደርስ በሽታ ነው። ✍የመከላከያ መንገዶች፦ 🔺ከልብስም ሆነ ከቤት ውስጥ እንደ ቅማል እና ቁንጫ የመሳሰሉ ተባዮችን ማስወገድ 🔺ልብስን በተገቢው ጊዜ መቀየር እና በደንብ ማጠብ 🔺ፀረ ተህዋስያንን በመጠቀም ከባቢን ከተህዋስ ነፃ ማረግ ❗️በተወሰኑ ምልክቶች መመሳሰል እና ለሁለቱም ንፅህና ወሳኝ የመከላከያ መንገድ ከመሆኑ በስተቀረ ታይፎይድ እና ታይፈስ የተለያዮ በሽታዎች ናቸው።ነገር ግን ሁለቱም በሽታዎች በአንድ ላይ ሊከሰቱ ይችላሉ። ዶ/ር ተሾመ አያሌው ©HakimEthio @grandmedicalclinic
Mostrar todo...
#የጥንቃቄ #መልክት ================ የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በቅርቡ በጋምቢያ ለህጻናት ሞት ክስተት በሆኑት አራቱ የመድኃኒት ምርቶች ሁኔታ እና በአለም ጤና ድርጅት በተሰጠው መረጃ መሰረት ሁኔታውን በቅርበት በመከታተል ላይ ይገኛል፡፡ አራቱ ምርቶች Promethazine Oral Solution, Kofexmalin Baby Cough Syrup, Makoff Baby Cough Syrup እና Magrip N Cold Syrup ናቸው፡፡የእነዚህ ምርቶች አምራች የሆነው በህንድ ሀገር የሚገኘው Maiden Pharmaceuticals ነው። አምራች ድርጅቱ ምርቶችን ወደ ኢትዮጵያ #ለማስገባት #እውቅና #ያልተሰጠው ፤#ምርቶቹም #ያልተመዘገቡ ከመሆናቸውም በላይ በየትኛውም #ህጋዊ በሆነ መልኩ #ወደ #ኢትዮጵያ #ያልገቡ መሆናቸውን ያሳውቃል፡፡ነገር ግን በተለያየ መልክ ህጋዊ ባልሆነ መልኩ ቢገባ እንኳን በሚል አስፈላጊውን የሰርቬይላንስ እና ክትትል ስራዎች እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከእነዚህ ከላይ ከተዘረዘሩት የመድኃኒት አይነቶች በተጨማሪ በአምራች ድርጅቱ የተመረቱ ሌሎች መድኃኒቶችም ላይ ክትትል እያደረገ ይገኛል፡፡ ባለስልጣኑ በየጊዜው ወቅታዊ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ የሚያቀርብ መሆኑን እየገለጽን #መረጃዎችን #ለመጠቆም ወይም #ለመስጠት #በነጻ #ስልክ #መስመር #8482 መጠቀም ህብረተሰባችን #ጥቆማ #መስጠት #እንደሚችል በአክብሮት ያሳውቃል፡፡ ======= የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን
Mostrar todo...
🌟ስለ ሾተላይ (Rh-isoimmunization) ማወቅ ያለብን ነጥቦች🌟 በዶ/ር ዳዊት መስፍን ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት 💥 ሾተላይ የሚባለው በሽታ ከሁለተኛ ጀምሮ የሚወለዱ ህፃናትን የሚያጠቃ በሽታ ሲሆን ይህም በእናትና በፅንሱ መሀከል የደም አይነት አለመጣጣም(Rh incompatability) ምክንያት የሚከሰት ነው።  💥 ሾተላይ የሚከሰተዉ  የሴቲቱ የደም አይነት Rh negative ፣ የባል የደም አይነት Rh positive እና የፅንሱ ደግሞ Rh positive ከሆነ ሲሆን በተጨማሪም በተለያዩ ምክንያቶች Rh positive ደም ወደ ሴቲቱ ደም ከገባ ወይም ከወሰደች ነው። 🌟 ነጥብ 💥 ሚስት Rh negative መሆን ይኖርባታል እና ፅንሱ Rh positive መሆን ይኖርበታል 💥 ባል Rh negative ከሆነ ሾተላይ አይከሰትም 🌟 ሾተላይ ለምን ይከሰታል?   👉 የሰው ልጅ ከወላጆቹ ዘረመል ተነስቶ ከ4 የደም አይነቶች ውስጥ አንዱን ሊይዝ ይችላል። እነኝህም 1. “A” 2. “B” 3. “AB” 4. “O”  ተብለው ይጠራሉ። 👉 በሰውነት ውስጥ የሚገኙ ቀይ የደም ህዋሶች(RBCs) የላይኛው ሽፋናቸው ላይ Rh የተባለ ፕሮቲን (protein) ካላቸው ሴቲቱ Rh positive ናት ማለት ሲሆን እነኚህ ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ Rh negative ናት ማለት ነው። ለምሳሌ:- ሴቲቱ የደም አይነቷ B ቢሆንና  ቀይ የደም ሴሎቿ ላይ Rh ፕሮቲን ካለ B Positive ናት ማለት ነው፤ እነኚህ Rh ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ B Negative ናት ይባላል። 👉 አንዲት ሴት ሾተላይ የሚባለው ችግር ሊከሰትባት የሚችለው እሷ Rh negative ሆና በተለያዩ አጋጣሚዎች Rh positive የሆነ ደም  ወደሰውነቷ ሲገባ ሰውነቷ እነኚህን Rh positive የደም አይነቶች የሚያጠፉ(የሚገሉ) ንጥረ ነገሮች (Antibodies) ሲያመነጭ (ሲያመርት) ነው። እነኚህም እስከ እድሜልክ በሰውነቷ ይቆያሉ። 👉 እነኚህ የተመረቱት ተከላካይ ንጥረ ነገሮች(Antibodies) የመጀመሪያው ልጅ ላይ ምንም ተፅዓኖ ሳይኖራቸው ልጁ በሰላም ሊወለድ ይችላል ነገር ግን የሁለተኛው ፅንስ የደም አይነቱ Rh positive ከሆነ ወደ ፅንሱ በማለፍ የፅንሱን Rh positive  የቀይ የደም ህዋሶች ያጠቃሉ ማለት ነው፤ ይህም ፅንሱን ለተለያየ አደጋዎች ሊያጋልጠው ይችላል። 👉 ይህም ችግር ፅንሱ ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን ሊያመጣ ይችላል ፤ እነኚህም ☘️ በፅንሱ የተለያዩ የአካል ክፍሎች ውሀ መቋጠር - Fetal hydrops ☘️ በተደጋጋሚ የፅንስ መውረድ - Miscarriage ☘️ የፅንሱ የደም ማነስ - Fetal anemia ☘️ ፅንሱ በማህፀን ውስጥ እንዳለ ጊዜው ሳይደርስ ህይወቱ ማለፍ ☘️ ህፃኑ ከተወለደ በውሃላ ቆዳው ቢጫ መሆን እና የጨረር ህክምና ማስፈለግ(phototherapy) ☘️ በከፍተኛ ደም ማነስ ምክንያት ደም ለመውሰድ መጋለጥ 🌟 ሾተላይ እንዴት ይታከማል? 👉 Rh negative የሆነችው እናት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ነገሮች ከገጠሟት ☘️ ባለቤቷ Rh positive ከሆነ ☘️ ውርጃ ካጋጠማት ☘️ ከማህፀን ውጭ እርግዝና ካጋጠማት ☘️ ከእንግዴ ልጅ ላይ የሚነሳ እጢ(Gestation trophoblastic disease) ካጋጠማት ☘️ በእርግዝና ወቅት አደጋ ከደረሰባት፤ ☘️ በክትትል ወቅት ከእንግዴ ልጅ ወይም ከሽርት ዉሃ በመሳሪያ ናሙና ከተወሰደ 👉👉 Anti D የተባለ ኢሚውኖግሎቡሊን (immunoglobulin) መድሀኒት በመውሰድ ሾተላይን መከላከል ይቻላል። 💥☘️ በእርግዝና ጊዜ Anti D የተባለውን መድሃኒትን በ 7 ወር(28 ሳምንት) ላይ እና ህፃኑ በተወለደ ቢቻል እስከ 72 ሰዓት ውስጥ በመስጠት የሾተላይ በሽታን መከላከል ይቻላል። 👉 Rh negative የሆነች እናት(ባል Rh positive) የእርግዝና ክትትሏ ከሌሎች እናቶች ለየት ያለ እና የሚሰጣትም ቀጠሮ በዛ ያለ ይሆናል። 👉 ይህም በልጇ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉትን የሰውነት ውሀ መቋጠር(መጠራቀም) እና የፅንሱ ደም ማነስ ካለ ቀድሞ በማወቅ ህክምናውን በቶሎ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ እዛው ማህፀን ውስጥ እንዳለ ደም በመለገስ እና ወቶ ለመኖር ብቁ በሆነበት ጊዜ ቀድሞ እንዲወለድ በማድረግ ተጨማሪ የሆኑ የህክምና እርዳታዎች እንዲደረግለት ማድረግ ይቻላል። ዶ/ር ዳዊት መስፍን ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ©HakimEthio
Mostrar todo...
Mostrar todo...
Online Medical Care and Medical Information🩺🔬 የጤና እና ጤና ነክ መረጃዎች

የጤና መረጃዎች ጤና ነክ መረጃዎች

ልጄ አሁን 4 ዓመቱ ነው በጣም ቀዥቃዣ እና አስቸጋሪ ልጅ ሆኖብኛል ምክንያቱ ምን ይሆን❓️😴😔 👦 ወንድ ልጆች ለምንድነው ቀዥቃዣ የሚሆኑት ግን ❓️ ✔️ ህፃናት በተለይ ደሞ ወንድ ልጆች አካባቢያቸው ለመቃኘት ለመቆጣጠር ወይም የወላጅን ትክረት አውቀው ለመሳብ ሲሉ በጣም ቀዥቃዣ እና አስቸጋሪ ሊሆኑ ይቺላሉ:: ✔️ ከበድ ሲል ደሞ በሕክምናው አጠራር ትኩረት የማጣት እና የመረጋጋት ችግር (Attention Deficit hyperactivity -ADHD) ሊኖራቸው ይቺላል:: 📌 ኤዲኤችዲ(ADHD) ልጆች ላይ ሊከሰት የሚችል ስነ አይምሮ እክል ነው። 📌 ይህ እክል ያለባቸው ህፃናት የሚይዙት የሚጨብጡት የሚጠፋባቸው፣ አንድ ነገር ጀምረው አፍታም ሳይቆዩ ሌላ የሚያምራቸው፣ ለመናገርና ለመጠበቅ ትዕግስት የማይኖራቸውና እጅግ ችኩል እና ቅብጥብጥ ናቸው፡፡ 📌 አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸውን ከሌሎች በተለየ ትዕግስት የለሽ፣ ቀዥቃዣና አስቸጋሪ ሆነውባቸው መፍትሔ ሲፈልጉ ይታያሉ፡፡ 📌 እነዚህ ህፃናት የሚይዙት የሚጨብጡት የሚጠፋባቸው ብቻ ሳይሆኑ ለመቆጣጠር በጣም አዳጋች ናቸው፡፡ አልፎ አልፎ ለ አደጋ ሊጋለጡ ይቺላሉ:: 🏄🏂 🤸 📌 ይህ አይነት የስነባህሪና የስነአእምሮ ችግር ያለባቸው ህፃናት ትኩረት ያጡ፣ ትዕግስት የለሽ ቀዥቃዣነት (ADHD) ህመም ተጠቂዎች ናቸው:: 📌 ይህ ADHD የሚባለው የስነ አይምሮ ቺግር 3 አይነት አለው እነሱም 1. ትኩረት የሌላቸው ( inattentive type) 2.  እረፍት የሌላቸው (hyperactive- impulsive) 3. የሁለቱም አይነት ምልክት ያለው (ከላይ የተጠቀሱን ሁለቱንም ምልክቶች ያለበት ❤️ እስኪ በዝርዝር እንያቸው❗️ 1.   ትኩረት የሌላቸው (Inattentive type) 🔷 ብዙውን ጊዜ ለጥቃቅን ነገሮች ትኩረት አለመስጠት 🔷  ከእኮዮቻቸው ጋር ሲነፃፀሩ በግዴለሽነት ስህተት መስራት 🔷 ከፍተኛ ትኩረትን የሚይጠይቁ ተግባራቶች ላይ ለመሳተፍ ወይም ለመሞከር አለመፈለግ ወይም አለመውደድ 🔷 ብዙውን ጊዜ ለሾል ወይም ለጨዋታ የሚያስፈልጉ አስፈላጊ ነገሮችን መርሳት ለምሳሌ የትምህረት መሳሪያዎችን ትምህርት ቤት በተደጋጋሚ ረሰተው መምጣት 🔷 በቀጥታ አንድ ሰው ሲያናግራቸው የሚሰማ ወይም የሚያዳምጥ አለመምሰል - አእምሮን ሌላ ቦታ መውሰድ 🔷 ብዙውን ጊዜ ትዕዛዞችን ለመተግበር ይቸገራሉ እንዲሁም የቤት ስራዎችን በትክክል ለመጨረስ ይቸገራሉ (often has difficulty in following instruction) 🔷 ቀላሉ መረበሽ(often easily distrusted by external stimuli) 2. እረፍት አልባ (በጣም ቀዥቃዣነት) Hyper Active type 🔺 በእጅ ወይም በእግር ጣቶች መሬት ወይም ሌላ ነገርን መምታት ፣መቆንጠጥ 🔺 መቀመጥ በሚገባቸው ቦታ ወይም ሁኔታ ውስጥ እያሉ ለመሮጥ ወይም ለመንቀሳቀስ መሞከር 🔺 ብዙውን ጊዜ በቦታው ላይ መቀመጥ ሲገባ ለመሮጥ ወይም ለመዝለል መሞከር፤መንቀⶵቀⶵ ወይም በአንድ ቦታ ተረጋግቶ ለመቆየት መቸገር 🔺 ብዙ ጊዜ ተረጋግተው ጨዋታ መጫወት አለመቻል 🔺 ከመጠን በላይ ያወራሉ 🔺 በሌሎች መሃል ብዙን ጊዜ ጣልቃ ይገባሉ ለምሳሌ ትልልቅ ሰዎች በሚያወሩ ሰአት ጣልቃ መግባትእና አላስፍላጊ ንግግር ማድረግ 🔺 አንድ ጥያቄ ሲጠይቅ ጥያቄው ከማለቁ በፊት ለመመለሾ መጣደፍ 🔺 ተራቸውን ጠብቀው መናገር ወይም ድርጊቶች መፈፀም ይቸገራሉ 3. የሁለቱም አይነት ምልክት ያለው( Combined type) ከላይ የተጠቀሱት የሁለቱም ምልክት አይነት ይታዩባቸዋል :: 🔷 ምክንያቱ ምን ይሆን ⁉️ 📌 ምክንያቱ በትክክል አይታወቅም 📌 በእርግዝና ጊዜ አልኮልና ሲጋራ መጠቀም እንደ አጋላጭነት ይጠቀሳሉ፡፡ 📌 ዓለም አቀፍ ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ ለትምህርት ከደረሱ ህፃናት መካከል ከ5-10 % የሚሆኑት ህፃናት ይህ ችግር ሊታይባቸው ይችላል፡፡ 👨‍⚕️ ሕክምና አለው ግን ⁉️ አዎ ሕክምናው የሚከተሉት ናቸው ✔️ ልቦና ህክምና(psychotherapy) ✔️ በአማራጭ ትምህርት(Special Education) ✔️ ሀኪም(child pshycitrist) በሚያዛቸው በመድሀኒቶች ከላይ ባሉት አማራጭዎች በመታገዝ የሚስተካከሉና መሻሻል ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡ 👉 ወላጆች እንዲህ አይነት ባህሪ ያላቸውን ህፃናት በአግባቡ በማሳከምና በቤት ውስጥ ድጋፍና አንክብካቤ በማድረግ ችግራቸውንና የትምህርት አቀባበላቸውን ቀስ በቀስ ማስተካከል ይችላሉ‼️ ❤️ መልእክቱ ጠቃሚ ነው ብለው ካመኑ ለሁሉም ወላጅ እንዲደርስ ለወዳጆ ያጋሩት ። Š ዶ/ር ሄኖክ ዘውዱ እና  ኢየሩሳሌም ተስፋዬ @grandmedicalclinic
Mostrar todo...