cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ቅድሚያ ለተውሂድ ተውሂድ የነብያት ሁሉ ጥሪ ናት

ቅድሚያ ለተውሂድ ተውሂድ የነብያት ሁሉ ጥሪ ናት https://t.me/joinchat/WIwxbQPSg9sX6FvP

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
198
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 días
-430 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

አረ እንዲች ነችና ለካ አልተዋወቅንም ማንነቴን አላወክም አትበል አትፎክር ማንነትህን አላህ ካልሰተረልህ ብዙ አሳፋሪ ነገሮች በጀርባህ አሉ። ማንኛውንም ነገር ስትሰራ በአላህ እገዛ እንጅ በችሎታህ እንዳልሆነ አስብ ማንኛውንም ነገር ስትሰራ አላህ እንዲወድልህ ምናልባት ወንጀልህን ይቅር እንዲልህ ጀነትን እንዲናጎናፅፍህ እንጅ ማንነትህን ማሳያ አታድርገው ተጣጥረህ የሆነ ነገር በማሳየትህ ሰዎች በዛ የሚያስቡህ ማንነት አይደለም ያንተ ማንነት ያንተ ማንነት አንተ የረሳሀውንም ጨምሮ የሚያውቀው አላህ ብቻ የሚያውቀው ማንነት ነው። ሁሉም ሠው ወደ አላህ ከጃይ እንጅ በራሱ ምንም የማድረግ አቅም ያለው አይደለም። ۞ يَا أَيُّهَا النَّاسُ أَنتُمُ الْفُقَرَاءُ إِلَى اللَّهِ ۖ وَاللَّهُ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ ❝ እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ (ሁል ጊዜ) ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፡፡ አላህም እርሱ ተብቃቂው ምስጉኑ ነው፡፡ ❞ [ ሱረቱ አል-ፈጢር - 15 ]
Mostrar todo...
Photo unavailable
ሰለፍያ ትድመቅ !!    ❝ ዋና አስኳል የሆነች የኢስላም ነፀብራቅ    ከባጢል በመራቅ የተሞላች በሐቅ    ከላይ አውለብልባ የተውሒድን ሰንደቅ    በጣም ትለያለች ሰለፍያ ትድመቅ!! ❞ ____ t.me/Abdurhman_oumer/8540
Mostrar todo...
قال الإمام ابن كثير رحمه الله:- ‏أهل السنة يقولون في كل فعل أو قول لم يثبت عن الصحابة ‏ هو بدعة ، لأنه لو كان خيراً لسبقونا إليه. አላህ ይዘንላቸው ኢማም ኢብኑል ቀይም የሚከተለውን ብለዋል፦ ❝ የሱና ሰዋች ከሰሀቦች ያልተገኘ የሆነን (በዲን ውስጥ) ማንኛውንም ንግግርም ሆነ ተግባርን ይሄ መጤ ቢድዓ ነው ይላሉ መልካምና ጥሩ ቢሆን ኖሮ ሰሀቦች ለመተግበርም ሆነ ለመናገር ይቀድሙን ነበር። ❞ ‏📚(تفسير ابن كثير : ٢٧٨/٧)
Mostrar todo...
አላህን መብቃቃትን ጠይቀው ➛ በሚሊየን ኖሮት ምን ላይ እወድቅ ይሆን እያለ የሚሰጋ እና ➛ የነገ የምግብ ካለው ለቀጣዩ በአላህ ላይ ጥሩ ተስፋ የሚሰንቅ ይኖራሉ። ➛ ሀብታምነትን በገንዘብ አትለካው ሀብታምነት አላህ በሻላቸው ሰዎች ልብ ውስጥ የሚያደርገው መብቃቃት ነው። رَوَى البُخَارِيُّ فِي صَحِيْحِهِ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ (لَيْسَ الغِنَى عَنْ كَثْرَةِ العَرَضِ وَلَكِنَّ الغِنَى غِنَى النَّفْس)، አቡ ሁረይራህ ባወሩት ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፦ ❝ ሀብት ማለት ከዱንያ ቁሳቁሶች ብዛት አይደለም ነገር ግን ሀብት ብሎ ማለት የልብ መብቃቃት ነው❞ ቡኻሪ ዘግቦታል
Mostrar todo...
የዝንባሌ አካሄድ አስከፊነት ከሰለፎች (ከደጋግ ቀደምቶቻችን) 〰 وعن هشام بن حسان قال : " لا يقبل الله من صاحب بدعة صياما ولا صلاة ولا حجا ولا جهادا ولا عمرة ولا صدقة ولا عتقا " .  አላህ ይዘንላቸው ሂሻም ኢብኑ ሀሳን እንዲህ ብለዋል፦ ❝ አላህ ከቢድዓ ባለቤት ፆምንም ሶላትንም ሀጅንም ጅሀድንም ዑምራንም ሶደቃንም ባሪያ ነፃ ማድረግንም አይቀበልም። ❞ “ሱብሀነላህ” የቢድዓ ባለቤቶች አደጋቸው በኡማው ላይ በደጋግ ቀደምቶቻችን እይታ ምን ያህል የከፋ ቢሆን ነው!? زاد ابن وهب عنه : " وليأتين على الناس زمان يشتبه فيه الحق والباطل ، فإذا كان ذلك; لم ينفع فيه دعاء إلا كدعاء الغرق " .  አላህ ይዘንላቸው ኢብኑ ወህብ እንዲህ ሲሉ ጨምረዋል፦ ❝ በሰዎች ላይ ዘመን ይመጣል ሀቅና ባጢል የሚመሳሰልበት ይህ በሆነ ጊዜ ባህር ውስጥ መስመጥ ጊዜ የሚደረግ አይነት ዱዓእ ካልሆነ በስተቀር (ከዛ ያነሰ) ዱዓእ አይጠቅምም ❞ ከሁሉም በላይ ደጋግ ቀደምቶች እንደዝንባሌ አካሄድ የሚጠሉት ነገር የለም። قال أبي إدريس الخولاني : " لأن أرى في المسجد نارا لا أستطيع إطفاءها ، أحب إلي من أن أرى فيه بدعة لا أستطيع تغييرها " .  አላህ ይዘንላቸው አቢ ኢድሪስ አልኸውላኒ እንዲህ ብለዋል፦ ❝ መስጅድ ውስጥ እሳት እየተቀጣጠለ አይቼ (ለማጥፋት ስታገል) ማጥፋት ባልችል ይሻለኛል። የቢድዓ አካሄድ አይቼ መቀየር ከማልችል። ❞ ምን ይሄ ብቻ ደጋግ ቀደምቶች እንደዛሬው ለባጢል ወገባቸውን አስረው እየታተሩ ሠዎችን ሁሉ በማሳሳት ደስታ ሊያገኙ ቀርቶ አንድ ሠው በነሱ ሰበብ ተሳስቶ ሌላ ምንም ነገር አያስደስታቸውም ነበር። ከቶውንም ሠውን ሁሉ ቀናውን መንገድ ቢያሳዩኳ አንድ ሠው በነሱ ሰበብ ከተሳሳተ አይደሰቱም ነበር።  ، قال سفيان: " كان رجل فقيه يقول : ما أحب أني هديت الناس كلهم وأضللت رجلا واحدا " አላህ ይዘንላቸው ሱፍያን እንዲህ ይላሉ አንድ ፈቂህ የሆነ ሠው እንዲህ ይል ነበር፦  ❝ ሠዎች ሁሉ (በኔ ሰበብ) ቀናውን መንገድ ቢመሩልኝ አልወድም አንድን ሠው አሳስቼ ❞ t.me/Abdurhman_oumer
Mostrar todo...
«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ « ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡ » [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ] በአላህ ፈቃድ የተለያዩ ዲናዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል!! http://t.me/Abdurhman_oumer

Photo unavailable
የእዝነትና የጥበብ ጥግ! 〰 አላህ ይዘንላቸው ኢማሙ ማሊክ ኢብኑ አነስ እንዲህ ብለዋል፦ ❝ አንድ ተከራካሪ ሊከራከርህ ወዳንተ በመጣ ጊዜ ሱንናን ግልፅ አድርግለት አትከራከረው። ምክንያቱም ሱንናን ከገለፅክለት በእርሱ ላይ ከአንተ ዘንድ መረጃ አድርሰህለታል። (ከዚህ አልፎ ግን) ከተከራከረህ አንተን ሳይሆን አላህን ነውና የሚከራከረው ሱናን አብራራ እንጅ በሷ (በሱንና) ክርክር ውስጥ አታስገባው። ምክንያቱም ሱና ለእርሱ ግልፅ የሆነችለት ሠው ያለምንም ክርክር መቀበል ነው ግደታው። ❞ https://t.me/Abdurhman_oumer/8527
Mostrar todo...
በዚህች ምድር ከአላህ እዝነት ተስፋ የሌለው ሰይጣን ብቻ ነው። ወንጀል ሰራሁ ብለህ መልካም ስራ አትተው በወንጀልህም ላይ አትዘውትር!! وَمَن تَابَ وَعَمِلَ صَالِحًا فَإِنَّهُ يَتُوبُ إِلَى اللَّهِ مَتَابًا ❝ ተጸጽቶ የተመለሰም ሰው መልካምንም የሠራ እርሱ የተወደደን መመለስ ወደ አላህ ይመለሳል፡፡ ❞ [ ሱረቱ አል-ፉርቃን፣ - 71 ] وَالَّذِينَ إِذَا فَعَلُوا فَاحِشَةً أَوْ ظَلَمُوا أَنفُسَهُمْ ذَكَرُوا اللَّهَ فَاسْتَغْفَرُوا لِذُنُوبِهِمْ وَمَن يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا اللَّهُ وَلَمْ يُصِرُّوا عَلَىٰ مَا فَعَلُوا وَهُمْ يَعْلَمُونَ ❝ (ገነት) ለእነዚያም መጥፎ ሥራን በሠሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለኀጢአቶቻቸው ምሕረትን የሚለምኑ ለኾኑት ከአላህም ሌላ ኀጢአቶችን የሚምር አንድም የለ፡፡ (በስሕተት) በሠሩትም ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑ የማይዘወትሩ ለኾኑት (ተደግሳለች)፡፡ ❞   t.me/Abdurhman_oumer
Mostrar todo...
«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ « ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡ » [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ] በአላህ ፈቃድ የተለያዩ ዲናዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል!! http://t.me/Abdurhman_oumer

የቢድዓ ባለቤቶችን ስራ እየሰራ የፈለገውን ጥፋትና ዝንባሌ ካሰራጨ በኋላ ቁርአንና ሀዲስን ነው የምከተለው ብሎ ግግም ካለ . . . በዚህ ዙሪያ የሚናገሩ የደጋግ ቀደምቶችን ንግግሮቻቸውን ለታፔላነት ከተገለገለባቸው ታዝቦ ዝም ከማለት ውጭ ምን ይባላል!? በዚህ ከቀጠለ አህባሹም ከነኩፍሩ ቁርአንና ሀዲስን በሰለፎች አረዳድ በሚል ታፔላ አጉልቶ መነገዱ አይቀርም። ጉዳይ ግምት ውስጥ የሚገባው በተጨባጭ እንጅ በሙግት አይደለም!
Mostrar todo...
የሂጅራ አቆጣጠር!! 〰 ያነ የስደት ወቅት ከመካ መድና ነብዩ ሙሐመድ የኛ ሀቢቡና ፊት የነበረውን ሊያድሱ እንደገና ብዙ ጉድ ገብቶበት ተበርዟልና እንደቀድሞ እንዲሆን ታላቁ እስልምና መልእክት ሲመጣቸው ከአላህ ረበና ተነሱ ሊያደርሱ ያን ትልቅ አማና በአለም እንዲስፋፋ የተውሒድ ጎዳና!! የሰው ልጅ በምድር የመምጣቱ አላማ አንድ አምላክን ሊያመልክ መሆኑን እንዲሰማ ዘለአለም እንዲድን ወጥቶ ከጨለማ በእምነት አሸብርቃ ምድር እንዲትለማ በጣም ታገሉለት ለተውሒዱ ካስማ እስከ ጥግ ሠሩ አርገው እንዲደማ የታደለ እሺ አለ ያሾፈም አሾፈ ብዙ አይነት ስቆቃ አማኝ ላይ አረፈ ብዙ ተገደለ ብዙ ተገረፈ!! በተለይ የእነኝህ አይወራ ይቅር የያሲር ቤተሰቦች ሱመያና አማር ሌሎችም ልእልቶች ፋጡማና ዘኒር ቢላሉል ሀበሽይ ጀግና የጥቁር ዘር ጅሀድ አልታዘዙ አልገጠሙ በጦር ጥቂትም ነበሩ ትንሾች በቁጥር ያሳለፉት ስቃይ ደም ያስለቅስ ነበር!! ያን ሁሉ መከራ ችለው እያለፉ ይቅርታ እያረጉ ቢበረታም ግፉ ውስን አመታትን ችለው እንደገፉ በስደት ታዘዙ ወደ የስሪብ ሀገር መድና እንዲጎርፉ!! ወጥተው ሲሰደዱ አማኝ በአጠቃላይ አሁንም በረታ ግፉ ሚስኪኖች ላይ አብረው እንዳይሆኑ ከሂጅራው ተካፋይ ሰለማ ኢብኑ ሂሻም ወሊድና ዓያሽ ብዙ ተሰቃዩ በኩፋሩል ቁረይሽ ስደቱ ቀጥሏል መድና ተመሙ በፊት የወጡ አሉ ቀድመው የተመሙ የአለሙ መብራት ነብዩ ሊያዘግሙ ሊወጡ መሆኑ ቁረሾች ሲሰሙ በመኝታቸው ላይ ጥቃት ሊፈፅሙ ሴራ ጠነሰሱ በሂስድ ምቀኝነት በጣሙን ታመሙ ጅብሪልን ላከና አላህ ሲነግራቸው ሴራ ጠንስሰዋል አትተኛ አላቸው ሲመጡ ጊዜና አንድ ጊዜ ከበው ለአንድየ እና ለመጨረሻ ጊዜ ሽተው ሊያጠፏቸው ተአምር ሠሩና የዛን ጊዜ እሳቸው ዓልይን ተክተው እሱን አስተኝተው በላያቸው ላይ አፈር እየረጩ ወጡ በጎናቸው ከአቡበክር ጋራ “ጋሩ ሰውር” አመሩ—አቤት—ሲያምርባቸው ቁረይሾቹ መጥተው ዙሪያ ቢከቧቸው ታላቅ ሀያሉ አምላክ አላህ ጠባቂያቸው በማይታይ ዘማች ጥበቃ አርጎላቸው ከዋሻው ቆይተው ምንም ሳይነካቸው ጉዞ ወደ የስሪብ ቀጠለ እርምጃቸው ቁረይሾች በገኑ ቁጭት ጠናባቸው ሊከፍሉ ወሰኑ ለደረሰባቸው እነሱን ላመጣ መቶ ግመል አለው ብለው አሳወጁ በየ ጉባኤአቸው "ሱራቃ” ሞከረ ጋለበ ለብቻው ሲቀርብ ጊዜና ደርሶ ከኋላቸው ዱዓ አደረጉበት መሬትም ዋጠችው ይቅርታ ጠይቆ ተመለሰ በዛው!! ብዙም ዝርዝር ያለው አስገራሚም ታምር የሆነ ሆነና አልፎ ያ-ሁሉ አሳር ሀ"ብለው ጀመሩ መድና በመስፈር ከዛ ተይዞ ነው የሂጅራ አቆጣጠር!! ✍ አብዱረህማን ዑመር http://t.me/Abdurhman_oumer
Mostrar todo...
«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ « ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡ » [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ] በአላህ ፈቃድ የተለያዩ ዲናዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል!! http://t.me/Abdurhman_oumer

ረድ (ምላሽ መስጠት) ምንድን ነው ጥቅሙ???? 〰〰 ولتكن منكم أمة يدعون إلى الخير ويأمرون بالمعروف وينهون عن المنكر وأولئك هم المفلحون « ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ በመልካም ሥራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ፡፡ እነዚያም እነሱ የሚድኑ ናቸው፡፡» [ ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 104 ] በሌላ አንቀጽ ላይ  لعن الذين كفروا من بني إسرائيل على لسان داوود وعيسى ابن مريم ذلك بما عصوا وكانوا يعتدون كانوا لا يتناهون عن منكر فعلوه لبئس ما كانوا يفعلون  « ከእስራኤል ልጆች እነዚያ የካዱት በዳውድና በመርየም ልጅ በዒሳ ምላስ ተረገሙ፡፡ ይህ  ትእዛዝን በመጣሳቸውና ወሰንን የሚያልፉ በመኾናቸው እንድሁም  (አንዱ አንዱን) ከሠሩት መጥፎ ነገር አይከላከሉምና ነበር፡፡ ይሠሩት የነበሩት ነገር በእርግጥ ከፋ! » (ሱረቱ አል-ማኢዳህ: 78 - 79) عن أَبي سعيدٍ الخُدْريِّ رضي اللَّه عنه قال : سمِعْتُ رسُولَ اللَّه صَلّى اللهُ عَلَيْهِ وسَلَّم يقُولُ : « مَنْ رَأَى مِنْكُم مُنْكراً فَلْيغيِّرْهُ بِيَدهِ ، فَإِنْ لَمْ يَسْتَطعْ  فبِلِسَانِهِ ، فَإِنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَبقَلبهِ وَذَلَكَ أَضْعَفُ الإِيمانِ » رواه مسلم .  የአላህ መልእክተኛ  ﷺ  የሚከተለውን ብለዋል፦ {{መጥፎ ሲሰራ ያየ በእጁ ያስቁመው ያልቻለ በምላሱ (ይናገር) ያልቻለ በልቡ ይጥላ (ከቦታው ተነስቶ ይሂድ) በልብ መጥላት የእምነት ደካማው ነው}}  (ሙስሊም ዘግቦታል) እንዲሁ ከጥቅሞቹ ውስጥ . . .   ➖ለተናጋሪው ከጅሀድ የበለጠ ነው! የመናገር ሱስም ሆነ፤ ሰዎችን ዝቅ የማድረግ የመበቀል የቂመኝነት፤ የእልኸኝነት፤ የህሜት ሱስ ሳይኖርበት በጥሩ ንያ የአላህን ዲን ለመጠበቅ ብሎ ከሙኻሊፎች የሚያስጠነቅቅና ሱናን የሚጠብቅ ሙጃሂድ ነው። ከዛም እንደሚበልጥ ደጋግ ቀደምቶች እንደት እንደሚያስቀምጡት የሚከተሉትን ንግግሮቻቸውን በአንድነት እንመልከት! قال يحيى بن يحيى شيخ الإمام البخاري ومسلم الذب عن السنة أفضل من الجهاد نقض المنطق  ص:12) የቡኻሪና የሙስሊም ሸይኽ የሆኑት የህያ ኢብኑ የህያ እንዲህ ይላሉ፦ "ከሱና መከላከል፣ ከጅሃድ  ይበልጣል።" قال ابن تيمية – رحمه الله تعالى "فالراد على أهل البدع مجاهد   الفتاوى  ( 4/13 )     ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላሁ እንዲህ ይላል፦ "በቢድዓ ባለ-ቤቶች ላይ ረድ የሚያደርግ (ምላሽ የሚሰጥ)፣ ሙጃሂድ ነው። (አልፈታዋ ( 4/13 ) ) قال ابن القيم والجهاد بالحجة واللسان مقدم على الجهاد بالسيف والسنان مقدمة منظومته الكافية الشافية ص/ 19 ኢማም ኢብኑል ቀይም እንዲህ ይላሉ፦ በማስረጃና በአንደበት የሚደረግ ጅሃድ፣ በሰይፍና በጦር ከሚደረግ ጅሃድ ይቀድማል። (አልካፊየቱ አሻፊያህ: 19) ይሄውላችሁ እንግዲህ ጅሃድ ማለት አንድ ሰው ደይን (የሰዎች እዳ) ብቻ ከሌለበትና በአላህ ላይ ትክክለኛ ጥሩ እምነት (ተውሒድ) ኖሮት በጅሀድ ከሞተ ሌሎችን ማንኛውንም ወንጀሎች የሚያሰርዝ ጀነት የሚያኖር ነገር ነው። ከመሆኑም ጋር በኢኽላስ የሚደረግ ረድ ከጅሀድ ይበልጣል። ➖ለሰሚው ህዝብ፤ በሽተኛውን ከደህናው የሚለይበት ነው! ህዝብ ያም ሲናገር እውነት ይመስለዋል፤ ያም ሲናገር እውነት ይመስለዋል። ጥፋት የሚያሰራጨው ስም ተጠቅሶ በበቂ መረጃ እገሌ ተሳስቷል እንደሁኔታውም ተጠንቀቁት ሲባል፤ ያኔ በሽተኛውን ከደህነኛው መለየት ይችላል። قيل لأحمد بن حنبل: الرجل يصوم ويصلي ويعتكف، أحبّ إليك أو يتكلم في أهل البدع؟ فقال: إذا قام وصلى واعتكف فإنما هو لنفسه، وإذا تكلم في أهل البدع فإنما هو للمسلمين؛ هذا أفضل»  زكره ابن تيمية -رحمه الله في مجموع الفتاوى، ص 231/28. {{ ከፊሎች ለኢማም አህመድ ቢን ሀንበል እገሌ እንዲህ ነው እገሌ ደግሞ እንዲህ ነው እገሌም እንዲህ ነው ብየ (ሥለ ሰው ለመናገር) ይከብደኛል አሏቸው እርሳቸውም፡- አንተ ዝም ካልክ እኔም ዝም ካልኩ መቼ ነው አላዋቂው ጤነኛውን ከሕመምተኛው ለይቶ የሚያውቀው? ብለው መለሱ}} (መጅሙዑል ፈታዋ) ➖ጥፋተኛውንም ራሱ መጥቀም ነው! ጥፋተኛው አጉል እልህ፤ ሹብሀ፤ ጥቅማ-ጥቅም፤ ወገንተኝነትና ሌሎችም እዚሁ ዱንያ ላይ የሚያበቁ ነገሮች ሸንግለውት ለመመለስ ቢከብደውም፤ ማንኛዋንም ትክክል ያልሆነች ነገር ባሰራጨ ቁጥር ምላሽ ሲሰጠው፤ በርካታ ጥቅሞች ሲኖሩት፤ ከነሱም ውስጥ፦ 1.የሱን ንግግር ሰምተው ተደናድነው ጥፋት ላይ የሚወድቁትን የነዛን ሁሉ ወንጀል እንዳይሸከም ወንጀሉን ማቃለል ነው። 2.ምላሽ ሲሰጥበት ምናልባት ከእለታት አንድ ቀን አላህ ልቡን ለሀቅ ከፍቶለት ቢቶብት፤ ዲንን በማጥፋቱ ከአላህ ፊት እንዳይጠየቅ ምክንያት እንሆንለታለን! ይሄም ወንድምን መርዳት ከሚለው ነው የሚገባው። የአላህ ባሮች ሆይ ታዲያ እንደዚህ ርዕስ የተባረከ ነገር ምናለ በአላህ!? ሆኖም ግን ሁሉም ሊጠነቀቅ የሚገባው አንገትን ከማስሞሽለቅ ከጅሃጅ ጋር የሚወዳደር ያውም የሚበልጥ የሆነ ጉዳይ እንዲህ በዋዛ የሚገኝ አይደለምና የ ኢ ኽ ላ ስ ን ነገርን ትልቅ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል። ረድ አድራጊው የሱና ወንድሙ ላይም ሆነ የሌላ አካሄድ ባለቤት ላይ ምላሽ ሲሰጥ ረድ የተደረገባቸው በግልፅ ከተመለሱም እሰየው በግልፅ መመለስ ተስኗቸው ረድ አድራጊው ላይ ቂም ይዘው ቀድሞም ምንም አይነት ጥፋት እንደሌለ ለማስመሰል ቢጥሩም ራሳቸውን ይጎዳሉ እንጅ ዋናው ጉዳዩ መስተካከሉ ነውና በኢኽላስ እስካደረገው ድረስ ከአላህ ዘንድ አጅር መጠበቅ ነው ያለበት። ሌላው ረድ የሚደረገው ዛሬ እንደሚታየው ሌሎች እኛ ላይ ስለሚናገሩ ጥፋታችንን ስላጋለጡ ዘመቻ መክፈት አይደለም። ይህ ከሆነ ዛሬ ላይ ኢኽዋኖችና ሙመይዓዎች እንዲሁም ሀጃዊራዎችም ሁሉም የጥመት ቡድን የገቡበት ችግር ውስጥ መግባት ይሆናል። ከነሱ ዘንድ በአጥፊዎች ላይ ረድ ምላሽ መስጠት የለም። ነገር ግን እነሱን የነካቸው ላይ ዘመቻ ይከፍታሉ። ይሄ ሁሉ ኢኽላስን የሚፃረር አደገኛ ነገር ነው። ረድ ለቡድንተኝነት ከዋለና ኢኽላስ ከሌለው ህሜት ነው የሙስሊሞችን ነውር መከታተል ከሚለው ነው የሚካተተው። http://t.me/Abdurhman_oumer
Mostrar todo...
«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ « ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡ » [ ሱረቱ ጣሀ - 47 ] በአላህ ፈቃድ የተለያዩ ዲናዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል!! http://t.me/Abdurhman_oumer

Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.