cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

✞ ፀሐየ ጽድቅ ✞

👉ፀሐየ ጽድቅ የሕይወት መብራት የጽድቅ ብርሃን በዚህ channel ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የጠበቁ ትምህርቶች እና መዝሙሮች እንዲሁም ቅዱሳንን እንዘክራለን ስለቅዱሳን እንማማራለን ዕለታዊ ዜና ቤተ-ክርስቲያ ስንክሳር ግጻዌ ጥያቄና መልስ እንዲሁም በየእለቱ አጥንትን የሚያጠነክሩ መንፈስን የሚያለመልሙ ጽሁፎችን ወደ እናንተ እናደርሳለን፡፡ ቻናሉን ይቀላቀሉ @Tsehaye_Tsidk ሼር ያርጉ!!

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
2 066
Suscriptores
Sin datos24 horas
-117 días
-2630 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#ሐምሌ_7 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 እንኳን ለአጋዝእተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!! 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 በስመ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ ቅዱስ          አሐዱ አምላክ። አሜን።           ✞ ቅድስት ሥላሴ ✞ ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡ አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡ ያች ሥላሴ የገቡባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡ እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡ እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡ አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡ ሥሉስ ቅዱስን የአብርሃሙ ሥላሴን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን! ✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣ "እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ:- 'በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ። እያበዛሁም አበዛሃለሁ' ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ። እንዲሁም እርሱ ከታገሠ በሁዋላ ተስፋውን አገኘ።" (ዕብ.6:13) ------------------------------------------- "የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።" (ቆሮ. 13:14) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> #ስንክሳር_ዘወርሃ_ሐምሌ #ይቀላቀሉን!! @Tsehaye_Tsidk @Tsehaye_Tsidk
Mostrar todo...
2🥰 1
ቅዱሳን አባቶቻችን "ሁል ጊዜ ከወደቃችሁ በኋላ ወዲያውኑ መነሳትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ አስፈላጊ ነው" ይሉናል፡፡ ሁላችንም ያለማቋረጥ ኃጢአትን እንሠራለን፤ ተንሸራተንም እንወድቃለን፡፡ ምንም እንኳን በቀን መቶ ጊዜ ብንወድቅም ወደ ኋላ ዞር ብለን ሳናይ ተነስተን ወደ እግዚአብሔር መመለስ አለብን የሆነው ሆኗል፤ ያ ጊዜም አልፎአል፡፡ ከእግዚአብሔር እርዳታ እንጠይቅ፤ ተስፋችንን ከውስጣችን ሊያጠፋ ለሚፈልገው ዲያብሎስ፤ "እግዚአብሔር ከእኔ በላይ እኔን ይወደኛል ይቅርም ይለኛል" እንበለው፡፡ (አረጋዊ ታዴዎስ)
Mostrar todo...
5🔥 1
#ሐምሌ_፭      ዝ    ክ    ረ   -   ቅ    ዱ    ሳ     ን    በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ              አሐዱ አምላክ አሜን! 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 እንኩዋን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን #ዼጥሮስ #ወዻውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!! 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 ፍጡር ቢከብር ከእመ ብርሃን ቀጥሎ የእነዚህን ቅዱሳን ያህል የሚከብር አይኖርም። ለቤተ ክርስቲያን ያልሆኑላት ምንም ነገር የለምና እርሷም "ብርሃኖቼ: ዐይኖቼ: ዕንቁዎቼ" ብላ ትጠራቸዋለች።   ✞ ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት ✞ የዮና ልጅ ስምዖን ዼጥሮስ (ኬፋ) የተባለው በጌታችን ንጹሕ አንደበት ነው። ይሔውም ዓለት (መሰረት) እንደ ማለት ነው። ¤ በቤተ ሳይዳ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሳ በማጥመድ አድጐ ¤ ሚስት አግብቶ ዕድሜው 56 ሲደርስ ነበር ጌታችን የተቀበለው። በዕድሜውም ሆነ በቅንዐቱ: በአስተዋይነቱም መሠረተ ቤተ ክርስቲያን ተብሏል። ለሐዋርያትም አለቃቸው ሆኗል። (ማቴ. 16:17, ዮሐ. 21:15) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተያዘባት ሌሊት ለሰራው ስሕተት ንስሃ ገብቶ ምሳሌም ሆኗል። ቅዱስ ዼጥሮስ እንደ እረኝነቱ ሐዋርያትን ጠብቆ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሲያበቃ ከበዓለ ሃምሳ በሁዋላም ለሁሉም ሃገረ ስብከት አካፍሏል። ምንም የርሱ ክፍል ሮሜ ብትሆንም አርድእትን ስለ ማጽናት በሁሉም አሕጉራት ዙሯል። በስተእርጅናው ብዙ መከራዎችን ተቀብሏል። አሕዛብ ግብራቸው እንደ እንስሳ ነውና በአባታችን ላይ ቀልደዋል። እርሱ ግን ሁሉንም ታግሷል። የቅዱሱን ታሪክ ለመናገር ከመብዛቱ የተነሳ ይከብዳልና ልቡና ያለው ሰው ሊቃውንትን ሊጠይቅ እንደሚገባ እመክራለሁ። ቅዱስ ዼጥሮስ መልካሙን ገድል ተጋድሎ በ66 ዓ/ም የኔሮን ቄሳር ወታደሮች ሲሰቅሉት ለመናቸው። "እባካችሁን? እኔ እንደ ጌታየ ሆኜ መሰቀል አይገባኝም" አላቸው። እነሱም ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለውታል። በበጐ እረኝነቱም የማታልፈውን ርስት ከነመክፈቻዋ ተቀብሏል። በሰማዕትነት ሲያርፍም ዕድሜው ወደ 88 አካባብ ደርሶ ነበር። #የቅዱስ_ዼጥሮስ መጠሪያዎች:- 1. ሊቀ ሐዋርያት 2. ሊቀ ኖሎት (የእረኞች / ሐዋርያት አለቃ) 3. መሠረተ ቤተ ክርስቲያን 4. ኰኩሐ ሃይማኖት (የሃይማኖት ዐለት) 5. አርሳይሮስ (የዓለም ሁሉ ፓትርያርክ)    ✞ ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ ✞ የቤተ ክርስቲያን መብራቷ ቅዱስ ዻውሎስን እንደ ምን ባለ ዐማርኛ እንገልጠዋለን? ¤ ስለ እርሱ መናገርና መጻፍ የሚችልስ እንደ ምን ያለ ሰው ነው? ¤ የዓለምን ነገር ሲጽፍ በኖረ እጄስ እንደ ምን እጽፈዋለሁ? ¤ ይልቁኑስ የርሱን 14ቱን መልዕክታትና ግብረ ሐዋርያትን መመልከቱ ሳይሻል አይቀርም። #ቅዱስ_ዻውሎስ ከነገደ ብንያም #ሳውል የሚባል የጠርሴስ ሰው ሲሆን ምሑረ ኦሪት: ቀናተኛና ፈሪሳዊ ነበር። ጌታ በደማስቆ ጐዳና ጠርቶ በ3 ቀናት ልዩነት ምርጥ ዕቃ አደረገው። ይህ የሆነው በ42 ዓ/ም: ጌታ ባረገ በ8ኛው ዓመት ነበር። ከዚያማ ብርሃን ሆኖ አበራ። ጨው ሆኖ አጣፈጠ። ከኢየሩሳሌም እስከ ሮም: ከእንግሊዝ እስከ እልዋሪቆን (የዓለም መጨረሻ) ወንጌልን ሰበከ። ስለ ወንጌል ተደበደበ: ታሠረ: በእሳት ተቃጠለ። በድንጋይ ተወገረ: በጦር ተወጋ። ባፍም በመጣፍም ብሎ አገለገለ። በየቦታውም ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ሠራ። ለ25 ዓመታት ቀንና ሌሊት ያለ መታከት ወንጌልን ሰበከ። እርሱን የመሰሉ: እርሱንም ያከሉ ብዙ አርድእትን አፍርቶ: በ67 ዓ/ም በኔሮን ቄሳር ትእዛዝ አንገቱ ተቆርጧል። ከ14ቱ መልዕክታቱ ባሻገር ቅዱስ ሉቃስ ወንጌልን ሲጽፍ አግዞታል። ልክ ቅዱስ ዼጥሮስ ማርቆስን እንዳገዘው ማለት ነው። #የቅዱስ_ዻውሎስ_መጠሪያዎች:- 1. ሳውል (ከእግዚአብሔር የተሰጠ) 2. #ልሳነ_ዕፍረት (አንደበቱ እንደ ሽቱ የሚጣፍጥ) 3. #ልሳነ_ክርስቶስ (የክርስቶስ አንደበቱ) 4. #ብርሃነ_ዓለም 5. #ማኅቶተ_ቤተ_ክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መቅረዝ) 6. #የአሕዛብ_መምሕር 7. #መራሒ (ወደ መንግስተ ሰማያት የሚመራ) 8. #አእኩዋቲ (በምስጋና የተሞላ) 9. #ንዋይ_ኅሩይ (ምርጥ ዕቃ) 10. #መዶሻ (ለአጋንንትና መናፍቃን) 11. #መርስ (ወደብ) 12. #ዛኅን (ጸጥታ) 13. #ነቅዐ_ሕይወት (የሕይወት ትምሕርትን ከአንደበቱ ያፈለቀ) 14. #ዐዘቅተ_ጥበብ (የጥበብ ምንጭ /ባሕር) 15.#ፈዋሴ_ዱያን (ድውያንን የፈወሰ) . . . ጌታችን እግዚአብሔር የአባቶቻችንን ብርሃን ያብራልን። ከበረከታቸውም ያድለን። ✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟ "ጌታ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። "የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይሕንን አልገለጠልህምና ብጹዕ ነህ። እኔም እልሃለሁ። አንተ #ዼጥሮስ ነህ። በዚህችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ። የገሃነም ደጆችም አይችሏትም። የመንግስተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ። በምድር የምታሥረው ሁሉ በሰማያት የታሠረ ይሆናል። በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።" (ማቴ. 16:17) ------------------------------------------- "በመሥዋዕት እንደሚደረግ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና። የምሔድበትም ጊዜ ደርሷል። መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ። ሩጫውን ጨርሻለሁ:: ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ። ወደ ፊት #የጽድቅ_አክሊል ተዘጋጅቶልኛል። ይሕንም ጻድቅ: ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል።"  (2ጢሞ. 4:6) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"። /የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል።  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ #ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያካፍሉ!! @Tsehaye_Tsidk @Tsehaye_Tsidk
Mostrar todo...
🥰 2
#ሐምሌ_፭      ዝ    ክ    ረ   -   ቅ    ዱ    ሳ     ን    በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ              አሐዱ አምላክ አሜን! 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 እንኩዋን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን #ዼጥሮስ #ወዻውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!! 🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺 ፍጡር ቢከብር ከእመ ብርሃን ቀጥሎ የእነዚህን ቅዱሳን ያህል የሚከብር አይኖርም። ለቤተ ክርስቲያን ያልሆኑላት ምንም ነገር የለምና እርሷም "ብርሃኖቼ: ዐይኖቼ: ዕንቁዎቼ" ብላ ትጠራቸዋለች።   ✞ ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት ✞ የዮና ልጅ ስምዖን ዼጥሮስ (ኬፋ) የተባለው በጌታችን ንጹሕ አንደበት ነው። ይሔውም ዓለት (መሰረት) እንደ ማለት ነው። ¤ በቤተ ሳይዳ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሳ በማጥመድ አድጐ ¤ ሚስት አግብቶ ዕድሜው 56 ሲደርስ ነበር ጌታችን የተቀበለው። በዕድሜውም ሆነ በቅንዐቱ: በአስተዋይነቱም መሠረተ ቤተ ክርስቲያን ተብሏል። ለሐዋርያትም አለቃቸው ሆኗል። (ማቴ. 16:17, ዮሐ. 21:15) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተያዘባት ሌሊት ለሰራው ስሕተት ንስሃ ገብቶ ምሳሌም ሆኗል። ቅዱስ ዼጥሮስ እንደ እረኝነቱ ሐዋርያትን ጠብቆ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሲያበቃ ከበዓለ ሃምሳ በሁዋላም ለሁሉም ሃገረ ስብከት አካፍሏል። ምንም የርሱ ክፍል ሮሜ ብትሆንም አርድእትን ስለ ማጽናት በሁሉም አሕጉራት ዙሯል። በስተእርጅናው ብዙ መከራዎችን ተቀብሏል። አሕዛብ ግብራቸው እንደ እንስሳ ነውና በአባታችን ላይ ቀልደዋል። እርሱ ግን ሁሉንም ታግሷል። የቅዱሱን ታሪክ ለመናገር ከመብዛቱ የተነሳ ይከብዳልና ልቡና ያለው ሰው ሊቃውንትን ሊጠይቅ እንደሚገባ እመክራለሁ። ቅዱስ ዼጥሮስ መልካሙን ገድል ተጋድሎ በ66 ዓ/ም የኔሮን ቄሳር ወታደሮች ሲሰቅሉት ለመናቸው። "እባካችሁን? እኔ እንደ ጌታየ ሆኜ መሰቀል አይገባኝም" አላቸው። እነሱም ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለውታል። በበጐ እረኝነቱም የማታልፈውን ርስት ከነመክፈቻዋ ተቀብሏል። በሰማዕትነት ሲያርፍም ዕድሜው ወደ 88 አካባብ ደርሶ ነበር። #የቅዱስ_ዼጥሮስ መጠሪያዎች:- 1. ሊቀ ሐዋርያት 2. ሊቀ ኖሎት (የእረኞች / ሐዋርያት አለቃ) 3. መሠረተ ቤተ ክርስቲያን 4. ኰኩሐ ሃይማኖት (የሃይማኖት ዐለት) 5. አርሳይሮስ (የዓለም ሁሉ ፓትርያርክ)    ✞ ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ ✞ የቤተ ክርስቲያን መብራቷ ቅዱስ ዻውሎስን እንደ ምን ባለ ዐማርኛ እንገልጠዋለን? ¤ ስለ እርሱ መናገርና መጻፍ የሚችልስ እንደ ምን ያለ ሰው ነው? ¤ የዓለምን ነገር ሲጽፍ በኖረ እጄስ እንደ ምን እጽፈዋለሁ? ¤ ይልቁኑስ የርሱን 14ቱን መልዕክታትና ግብረ ሐዋርያትን መመልከቱ ሳይሻል አይቀርም። #ቅዱስ_ዻውሎስ ከነገደ ብንያም #ሳውል የሚባል የጠርሴስ ሰው ሲሆን ምሑረ ኦሪት: ቀናተኛና ፈሪሳዊ ነበር። ጌታ በደማስቆ ጐዳና ጠርቶ በ3 ቀናት ልዩነት ምርጥ ዕቃ አደረገው። ይህ የሆነው በ42 ዓ/ም: ጌታ ባረገ በ8ኛው ዓመት ነበር። ከዚያማ ብርሃን ሆኖ አበራ። ጨው ሆኖ አጣፈጠ። ከኢየሩሳሌም እስከ ሮም: ከእንግሊዝ እስከ እልዋሪቆን (የዓለም መጨረሻ) ወንጌልን ሰበከ። ስለ ወንጌል ተደበደበ: ታሠረ: በእሳት ተቃጠለ። በድንጋይ ተወገረ: በጦር ተወጋ። ባፍም በመጣፍም ብሎ አገለገለ። በየቦታውም ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ሠራ። ለ25 ዓመታት ቀንና ሌሊት ያለ መታከት ወንጌልን ሰበከ። እርሱን የመሰሉ: እርሱንም ያከሉ ብዙ አርድእትን አፍርቶ: በ67 ዓ/ም በኔሮን ቄሳር ትእዛዝ አንገቱ ተቆርጧል። ከ14ቱ መልዕክታቱ ባሻገር ቅዱስ ሉቃስ ወንጌልን ሲጽፍ አግዞታል። ልክ ቅዱስ ዼጥሮስ ማርቆስን እንዳገዘው ማለት ነው። #የቅዱስ_ዻውሎስ_መጠሪያዎች:- 1. ሳውል (ከእግዚአብሔር የተሰጠ) 2. #ልሳነ_ዕፍረት (አንደበቱ እንደ ሽቱ የሚጣፍጥ) 3. #ልሳነ_ክርስቶስ (የክርስቶስ አንደበቱ) 4. #ብርሃነ_ዓለም 5. #ማኅቶተ_ቤተ_ክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መቅረዝ) 6. #የአሕዛብ_መምሕር 7. #መራሒ (ወደ መንግስተ ሰማያት የሚመራ) 8. #አእኩዋቲ (በምስጋና የተሞላ) 9. #ንዋይ_ኅሩይ (ምርጥ ዕቃ) 10. #መዶሻ (ለአጋንንትና መናፍቃን) 11. #መርስ (ወደብ) 12. #ዛኅን (ጸጥታ) 13. #ነቅዐ_ሕይወት (የሕይወት ትምሕርትን ከአንደበቱ ያፈለቀ) 14. #ዐዘቅተ_ጥበብ (የጥበብ ምንጭ /ባሕር) 15.#ፈዋሴ_ዱያን (ድውያንን የፈወሰ) . . . ጌታችን እግዚአብሔር የአባቶቻችንን ብርሃን ያብራልን። ከበረከታቸውም ያድለን። ✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟ "ጌታ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። "የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይሕንን አልገለጠልህምና ብጹዕ ነህ። እኔም እልሃለሁ። አንተ #ዼጥሮስ ነህ። በዚህችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ። የገሃነም ደጆችም አይችሏትም። የመንግስተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ። በምድር የምታሥረው ሁሉ በሰማያት የታሠረ ይሆናል። በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።" (ማቴ. 16:17) ------------------------------------------------------------------ "በመሥዋዕት እንደሚደረግ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና። የምሔድበትም ጊዜ ደርሷል። መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ። ሩጫውን ጨርሻለሁ:: ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ። ወደ ፊት #የጽድቅ_አክሊል ተዘጋጅቶልኛል። ይሕንም ጻድቅ: ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል።"  (2ጢሞ. 4:6) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"። /የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል።  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ #ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያካፍሉ!! @Tsehaye_Tsidk @Tsehaye_Tsidk
Mostrar todo...
አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር። ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ። ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም። ስለዚህ ተማር! ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን እየወቀስክ ትሠራለህ። ይህች የንስሓ በር ትኾንልሃለች፡፡ አንድ ቀን ወደ ንስሓም ትመራሃለች። #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
Mostrar todo...
3🥰 2👍 1
“ዘወትር በዐይንህ ፊት ፈሪሃ እግዚአብሔር ይኑር፤ ሕይወትና ሞት የሚሰጠውን አዘክረው፡፡ ዓለምንና በዓለም ያለውን ሁሉ ጥላው፤ ከሥጋ የሚመጣውን ደስታና ሰላም አትሻ፤ ለዚህኛው ኑሮ ሙትና ለእግዚአብሔር ሕያው ሁን፤ ለእግዚአብሔር ቃል የገባኸውን አትርሳ፤ ያም በፍርድ ቀን ካንተ ይፈለግብሃል፡፡ ረኀብን በጸጋ ተቀበለው፤ ተጠማ፥ ተራቆት፥ ንቁና በሐዘን የምትኖር ሁን፡፡ በልቡናህ አልቅስና ጩኽ፤ ለእግዚአብሔር የምትመች መሆን አለመሆንህን ፈትን፤ ሥጋህን ቀጥተህ ነፍስህን ታድናት ዘንድ፡፡” (አባ እንጦንስ)
Mostrar todo...
🔥 3
🔴 ግመልና መርፌ 🔴 ዛሬ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ያሳለፈው #ቅዱስ_ታዴዎስ በዓለ እረፍቱ ነው። ሲናገሩት የሚያስደንቅ ሲያስቡት ከህሊና በላይ የሆነ አስደማሚ ተአምር ሐዋርያው ታዴዎስ ፈፅሟል። ሐዋርያው ታዴዎስ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ነው። ወንጌልን ሲያስተምር ከዕለታት አንድ ቀን ባለፀጋ መንግስተ ሰማያት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል የሚለውን የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 18 ከቁጥር 25 ላይ ያለውን ሲያስተምር  ባለፀጋዎች ተሰብስበው ሐዋርያውን ሊፈትኑት ግመል በመርፌ ቀዳዳ አሳልፈህ አሳይን ካልሆነ የምታስተምረው ወንጌል እውነት አይደለም አሉት፤ ቅዱስ ታዴዎስም መርፌ የሚሰራ አንጥረኛ ወዳጅ ነበረው። ግመል የማሳልፍበት መርፌ ሰርተህ ላክልኝ አለው አንጥረኛውም ተጨንቆ የመርፌውን ቀዳዳ አስፍቶ ላከለት ቅዱስ ታዴዎስም ይህን አይቶ የመርፌ ቀዳዳ ቢሰፋ ግመል ያሳልፋልን በእግዚአብሔር ኀይል ካልሆነ ብሎ መልሶ ወደ አንጥረኛው መልእክተኛ ልኮ ትክክለኛውን መርፌ ላክልኝ አለው ቀዳዳው ያልሰፋ የተለመደውን መርፌ ላከለት። ባለፀጋዎች ተሰብስበው ግመል አቅርበው ይጠባበቁ ነበር ከዚያ በኋላ ሐዋርያው ስመ እግዚአብሔር ጠርቶ፤ እኔ እከብርበት እበላበት እሾምበት ብየ አይደለም ቃልህ እውነት መሆኑ ይታወቅ ዘንድ ነው ብሎ ሲፀልይ ግመሏ እስከ ሳቢዋ በመርፌው ቀዳዳ ውስጥ ሶስት ጊዜ ተመላለሰች። ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋልና የማይቻለው ተችሎ ድንቅ ተአምር ተፈፀመ ቅዱስ ታዴዎስም አምላኩን አመሰገነ። ባለፀጋዎች ተደመሙ ብዙዎችም በቅዱስ ወንጌል አመኑ። ከዚህ ላይ ባለፀጋ ከሰጠ ከመፀወተ  አይፀድቅም ማለት አይደለም፤ ንፉግ ከሆነ ጨካኝ ከሆነ ነው እንጂ። ከባለፀጋዎች መካከል እነ አብርሃም እነ ኢዮብ ሌሎችም የፅድቅ አባቶች ናቸው። ሰው እንደስራው ይፀድቃል ይኮነናልም። ድሃውም ሁሉ ይፀድቃል ማለት አይደለም መልካም ስራ ካልሰራ ሊኮነን ይችላል። ፅድቅ የስራ ውጤት ነው። ቅዱስ ታዴዎስ ወር በገባ በሁለት ቀን ይከበራል። የሐዋርያው ታዴዎስ አማላጅነት አይለየን     #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር!!! #ይቀላቀሉን!! @Tsehaye_Tsidk @Tsehaye_Tsidk
Mostrar todo...
😱 2
Photo unavailableShow in Telegram
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.